cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የኤልዔዘር ማስታወሻ

ሀሳብ አስተያየት ካሎት @El_Ezer1216 ላይ ያገኙናል

Show more
Advertising posts
201
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
የመጨረሻዋ ሰኑይ ❤ )የመጀመሪያዋ.... [ የሕይወት ባስ ] ህዝብን የሚያመላልስ አንድ ባስ ውስጥ አራት አይነት ተሳፋሪ እናገኛለን፤ ከመነሻው እስከ መጨረሻው ቋሚ/ዘላቂ የሆኑ ተሳፋሪዎች ፣ ከመነሻው እስከ ግማሽ መንገድ የሚጓዙ ፣ ከግማሽ እስከ ዘለቄታው የሚጓዙ ፣  ከግማሽ እስከ ግማሽ የሚጓዙ ናቸው። የሰው ልጅ ሕይወትም እንዲሁ ነው። ...እያንዳንዳችን ሕይወት መንገድ ላይ ከመነሻው እስኸ መጨረሻው የሚጓዙ <የራሳችን ሰዎች> ፣ <ከግማሽ ገብተው የሚዘልቁ ወዳጆቻችን> ፣ <ከመነሻ ተነስተው ግማሽ ላይ የሚወርዱ እምነታችንን የሸረሸሩ ሰዎች> ፣ <ከግማሽ ተነስተው ግማሽ ላይ የሚወርዱ ጊዜያዊ ሰዎች> መንገዳችን ላይ ይረማመዳሉ። የእስካሁን መንገዳችን በዚህ አጥር የታጠረ ነበር፣ ከዚህ በኋላስ? ከፊት የሚጠብቀን መንገድስ በየትኛው እንዲታጠር እንሻለን? ምናልባትም መጪው ዓመት ትክክለኛን ተሳፋሪ ብቻ በሕይወታችን ባስ ላይ እንድንጭን የተሰጠን ጊዜ ነው! ሁሉንም መጫን ባሱን ጥቅም አልባ ማድረግ ነው፤ እኛም የምንጭነውን ተሳፋሪ ጥቅም አልባ እንዳንሆን መምረጥ መቻል ግድ ይለናል! መውረድ የሚፈልጉትን ከሚያልፈው ዘመን ጋር አብረን ማውረድና ዘላቂ ተሳፋሪዎችን መጫን ያለብን ዛሬ ከዛሬም አሁን ነው! ለመሳፈር ቢፈልጉ እንኳን ትኬት አልቋል ብለን መመለስን መልመድ አለብን....እኛም በሌሎች ላይ ቋሚ ተሳፋሪ ለመሆን ያብቃን...! 🌼 🌼የተሻለ ፣ የተሳካ ፣ የሰላም ፣ የምሕረት ፤ የፍቅር ፣ የአንድነት ፣ የተስፋ ዘመን ያድርግልን! 🌼🌼 ኤልዔዘር ✍
Show all...
👍 2
ሰኑይ ❤ የሕልም ዓለም የመጨረሻ ክፍል... እጆቼን ይዞ ሲዳክር ሀሴት ይሰማኛል አይኖቹ አይኔን ሲያዩ በፍቅር ይገርፈኛል ድርቆሽ የሚያደማቸው እጆቹን ጉንጮቼ ላይ ሲያሳርፋቸው ሕይወት ዘመኔን ሁሉ ተሰምቶኝ የማያውቅ ደስታ ውስጤ ይዘላል...አፍ ባልፈታ አንደበቱ ለማውራት ሲታገል ወደ ራሴ ልጅነት ይመልሰኛል፤ እኔም እንዲህ ነበር እናቴን የማስደስታት? በርግጥም አዎን! እናትነት ያልተነገረለት የስሜት የፍቅር የስስት የደስታ ዓለም አለው ከምወደው ሰው የምወደውን ልጄን ካገኘሁ ወራት ተቆጠሩ። የሁለትነት ፍቅራችን ወደ ሶስት ገመድ ታሰረ፤ ቤተሰብ! ቤተሰባዊነታችን የፍቅር ማማ ላይ ከፍ አድርጎናል። ዕለቱ እሁድ ደመናማው የሐምሌ ወር እየተጋመሰ ዝናቡም እየበረታ የነበረበት ጊዜ ፤ የነበረንን ፕሮግራም ጨርሰን ምሸት ሶስት ሰዐት ገደማ ወደ ቤታችን እየተመለስን ነው ከኋላ ያለው መቀመጫ ላይ ልጃችንን አቅፎ መምሸቱን እያወጋን ወደቤታችን እየተመለስን ነበር። ሰማዩ ጠቁሯል መንገዶቹ አልፎ አልፎ ከሚያልፈው መኪና በቀር ተስተናጋጅ አልነበራቸውም ከመንገድ መብራቶች ይልቅ የሆቴልና የካፌ መብራቶች ጨለማውን ደፍረዋል ዝናቡ በኃይል መዝነብ ጀመረ..."ዝናብ ይወደናል አይደል?" አልኩት ፈገግ እያልኩ "አዎን የዝናብ ፍቅር አይደል እንዴ እዚህ ያደረሰን?" አለኝ "አዎ እንደቀልድ ሁለተኛ አመታችን መጣ አልኩት እግረ መንገድ ለማስታወስ ያህል   መኪናዋ ውስጥ ያለችው መብራት ጨለማውን ማሸነፍ ባትችልም ፊቶ ለማሳያት በቂ ነበረች የደስታ ፊት አነበብኩበት። ዝናቡ እየበረታ ሲመጣ ሹፌሩ ፍጥነቱን እየጨመረ መጣ ፤ እኛም ድካም ላይ ስለነበርን እና መንገዱም ተሽከርካሪ ስላልነበረው ፍጥነት መጨመሩን አልተቃወመንም። ከፍታውን ጨርሰን ቁልቁለቱን በመውረድ ላይ እንደነበርን አስታውሳለሁ ምን አይነትና እንዴት ይሁን አላውቅም ብቻ...ሁላችንም ሆስፒታል ነበርን፤ ስነቃ ድብልቅል ብሎ በደም የታጠበ አልጋ ላይ ራሴን አገኘሁት ሁለት ሶስት ሀኪሞች ዙሪያዬ ቆመዋል አይኔን እንደገለጥኩ "አይዞሽ አይዞሽ" እያሉ ደገፉኝ ጠንክሬ ለመነሳት ሞከርኩ አንደኛዋ ነርስ አንገቴን ደገፍ አድርጋ እንድቀመጥ ረዳችኝ ባባስ ባለቤቴስ አልኩ ከመቅፅበት ሁሉም ተያዩና አንደኛው ሀኪም "ትንሽ ተረጋጊ እ እዛኛው ክፍል ውስጥ ናቸው" አለኝ እየተንተባተበ ልቤ ስትሰነጠቅ ታወቀኝ አንሱኝ ብዬ አበድኩ ማስተው አልቻሉም ደግፈው ወሰዱኝ...። የኔን ዓለሞች የኔን ደስታዎች ሰላሞች መኖሮች ሕይወቶች ልጄን ባሌን በነጭ ከፈን ተሸፍነው አገኘሁ ፤ ለመጮህ ለማልቀስ ደረት ለመድቃት የሚሆን አቅም አጣሁ ደግሜ ራሴን ሳትሁ። ቀናት አለፉ እሳት ታቅፌ ቆየሁ ማንም የማያጠፋው እሳት...ለምን አልኩት ራሴን  ከሰልስት በኋላ አብዛኛው ሰው ተበተነ፤ ጭር ያለ ሰዐት ጠብቄ ወደ መቃብራቸው አመራሁ አሁንም አቅም የለኝም በቃ አልኩ....! . . . .አሁን ደስተኛ ነኝ ነፍሴን ከነሱ ጋር አገኘኋት!። ኤልዔዘር ✍️ https://t.me/Elezerbooks
Show all...
የኤልዔዘር ማስታወሻ

ሀሳብ አስተያየት ካሎት @El_Ezer1216 ላይ ያገኙናል

3🔥 2
ሰኑይ ❤ የቀጠለ.... "ከምዕራፉ በፊት መግቢያ አለው መግቢያውን መጥረግና ማሳመር አለብን መግቢያው ከተብራራ ምዕራፎቹን ሁሉ ማወቅ አያዳግተንም" ጥዑም አገላለፅ አድርጎ መንገዱን መራኝ አዎን ትክክል ነህ አልኩት ለማበርታት ያህል "ሁሉም ነገር በሰከነ ሁናቴ እንዲሆን እፈልጋለሁ" አንገቴን ነቀነኩለት አሁንም እጆቼን እንደያዛቸው ነው በየወሬው መሀል ዳሰስ ዳሰስ ያደርጋቸዋል እኔም አይን አይኑን አያለሁ አደምጠዋለሁ "ለሁሉም ነገር መጀመሪያ ጸሎት ነው! " የጠለቀ መንፈሳዊነቱ ልቤን ከገዙት መሀል ይቆጠራል "ፈጣሪ ትላንት ሲያገናኘን ምክኒያት አለው ስለዚህ እኛ የተሰጠንን ጠብቀን ፍሬውን ለእርሱ ማሳየት አለብን" እንዴት? ባውቅም እንዲብራራልኝ ሻትኩ ፤ "ሁለታችንም የተገናኘነው ባልጠበቅነው ቀን ሰዐት ጊዜ ነው ፍቅራችን የጀመረው በማግስቱ ነው ታዲያ ይህ ትዕንግርት ያለ ፈጣሪ ፍቃድ እንዴት ይከወን ነበር?" እንዴትም አስረገጥኩለት ፤ "ስለዚህ ፍቅራችንን ጠብቀን እጆቻችን ሳይላቀቁ መኖር አለብን" አዎን አልኩ ፈገግ አለ በነፃነት ስላወራኝ ደስ ብሎኛል በርግጥም የነፃነት ሰው ነው ነፃነቱን እወድለታለሁ ትንሹ ጌታ አልኩት ለመጠሪያነት ከተሰጡት ስሞቹ አስቀድሜ በምወድለት ስም "ወዬ" አለኝ በሚያሳሱ አይኖቹ እያየኝ ከእኔ የማትወደው ባህሪ ምንድነው? ጠይቄው አላውቅም ነበር "አንድ ፀባይሽ አስቸግሮኛል" አለኝ ምን አልኩት ለመስማት እየተጋሁ "ውብ ፍቅርሽ" አለኝ ልቤ አረፈች ከእሱ አፍ ይህን መስማት ደስታን ይጭራል "አልመሸም አንነሳም "አለኝ ሰዐቱን እያየ ወሬያችንን እንጂ መምሸቱን አላጤንኩም እንነሳ አልኩት ከተቀመጥኩበት እየተነሳሁ ሂሳቡን ከፍሎ ካፌውን ለቀን ወጣን ። የተወሰኑ እርምጃዎችን እንደተራመድን የመጣውን ዝናብ ለማባረር ነፋሱ በሀይል መንፈስ ጀመረ አጥብቆ አቀፈኝ መራመዳችንን ቀጠልን ንፋሱ ምንም ያህል ቢነፍስ ዝናቡን ሊያስቆመው አልቻለም ዘነበ እንደ ጠዋትጠበል ተጠበልነው ሰዉ ሁሉ መጠለያ ፍለጋ መሯሯጥ ጀመረ ከፊታችን ያለው ታክሲ ውስጥ ዘሎ ገባ እኔና የተወሰኑ ሰዎች ተሯሩጠን ተከተልነው ፤በፍቅር እንዳቀፈኝ የፍቅር ውሀ ተጠምቀን ሰፈሬ አድርሶኝ ተመለሰ። [ ለንጋት የሞላሁት መጥሪያ ከመቅጽበት ቀሰቀሰኝ ጠረቀምኩና በእጆቼ አልጋውን ዳሰስኩ አብሮኝ አለ ጉንጮቹኝ ሳምኩት ወደ ደረቱ ወሸቀኝ ከህልም ወደ እውነት መጣሁ ግንባሬን ሳመኝ ትንሹ ጌታ አልኩት "እምም" በደንብ አልነቃም የዛሬ አመት ትዝ ይልሀል ስለ ምዕራፍ አንድ ስናወራ "ምዕራፍ አንድ?" መንቃቱን አረጋገጥኩ አዎ አዎ አንተ ነህ እንደውም ያወራኸኝ እና ሙሉ ለሙሉ ያደረግነውን ያወራነውን በህልሜ አየሁት "ምዕራፍ አንድ ተጠናቀቀ ማለት ነው" አለኝ ደግሞ በፍቅር ወደራሱ አጠለቀኝ ጠለቅሁ....። [ምዕራፍ ሁለት]....] ኤልዔዘር ✍️ https://t.me/Elezerbooks
Show all...
የኤልዔዘር ማስታወሻ

ሀሳብ አስተያየት ካሎት @El_Ezer1216 ላይ ያገኙናል

4👍 2👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
ናፍቆት መች ያስተኛል?!... እንደ ብርድ ቁስል      ደርሶ ይጠዘጥዛል ክረምቱን ይመስል       ረሀብ ያፀናል ህፃን ልጅ አድርጎ      ስሜት ያስገረሻል በመገርሻት መሀል..... ሥጋን እያስቀረ... ስሜትን ሕዋስን     አፈር ያስከድናል። ኤልዔዘር ✍
Show all...
4👍 3🥰 2
#ምዕራፍ ልቤን ታገልኩት አይ አይሆንም እያልኩ ግን እሱም መልሶ ታገለኝ ይሆናል እርሱ ነው አለኝ! ፈራሁ...ትግሉ ግን በረታ አሜን አልኩ ተቀበልኩት...ሰዐታት ቀናት ሳምንታት ወራት...አመት...በክረምት መግቢያ የተፈጥሮ ፀሀይ መጥለቅ ስትጀምር ለኔ ግን አዲስ ፀሀይ ወጣ!!!...የደስታ ፀሀይ! የሰላም ፀሀይ! የፍቅር ፀሀይ!.....በፍቅር ጥም የደረቀ ልቤ ክረምቱን አጅቦ ከመጣው ሰው ጋር ልቤን አራሰው አጠመቀኝ በፍቅሩ ተጠመቅሁ!! ይህ ሰው አንተ ነህ!!! ለዳግም ሕይወት ያዘጋጀኸኝ ሳላውቅህ የሳሳሁልህ ሳውቅህ የጠለኩብህ አንተ! .................................. መተዋወቃችን ይገርመኛል! አልኩት አይኖቹን በፍቅር ዝቅታ እያየሁ "እኔም ይገርመኛል!" አለኝ ቀበል አድርጎ ፣ በየዕለቱ የምናደርነው ንግግር ለፍቅራችን ጥንካሬ እያጎናፀፈው መሆኑ ይሰማኛል። ያንተን ንገረኝ እና የእኔን መገረም እነግርሀለው አልኩት ወሬያችንን ለማስቀጠል "ብቸኛ ነበርኩ ፣ ለማንም ስለምንም መንገር የማልችል ሰው! ከፍቶኝ እንኳን ብቻዬን ነው የማለቅሰው!..." ዝም አለ እጆቼን ከጠረጴዛው ሳብ አድርጎ በእጆቹ ከተታቸው። ወንድ ልጅ ብቸኛ ሆኜ ከፍቶኝ አልቅሼ እያለ መስማት እንደ ሀገራችን ባህል አልተለመደም ቆጣ ማለትና ጀግንነት የወንዶች ባህሪ ተደርገው ይሳላሉ ግን ለምን? ወንድ ልጅ ስሜት አይኖረውም? ሀዘን አይሰማውም? አይከፋውም? ውስጤ በንግግሩ ተነክቷል ምናልባት ሌላ ሰው ቢሰማው ያፌዛል እንጂ ልቡን የሚረዳው አልመሰለኝም ለምን? ያው አንዴ ተለክፈን መከፋትን ለሴቶች ሰጠን ራሴን ፈገግ አደረኩት ፊቴ ላይ አሳበቀ መሰለኝ "ምነው?" አለኝ ምንም እንዲሁ...እኔም ብቸኛ ነበርኩ...ለራሴ ያወጋሁትን እንዳላካፍለው ወደጀመርነው ወሬ ተመለስኩ እኔም ብቸኛ ነበርኩ ረሀቤን የሚያስታግስ አልነበረም እና ያገኘሁህ ቀን ከፍቶኝ ነበር ስትጨብጠኝ ግንመላ ሰውነቴ እንደ አዲስ የተሰራ መሰለኝ የማላውቀው ነገር ከላዬ ላይ ረገፈ በቃ ያኔ ነው ያፈቀርኩህ! አሁን የሕይወታችን ምዕራፍ አንድ ላይ ጀምሯል አልኩት! [ ይቀጥላል ...] ኤልዔዘር ✍ https://t.me/Elezerbooks
Show all...
የኤልዔዘር ማስታወሻ

ሀሳብ አስተያየት ካሎት @El_Ezer1216 ላይ ያገኙናል

🥰 6👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
https://t.me/Elezerbooks #የኤልዔዘርማስታወሻ
Show all...
5🥰 2
ዳበሰኝ በመልኩ      አተመው ከ'ኔነት ታሰሰ በጨርቁ      የነበረ ጽልመት ነጠቀኝ በብርሀን     ሸለመኝ በድንገት በድንገት... ትላንትን ሲያበቃ       ዛሬን እየሻረ ነገን ነው የቸረኝ      ይዞኝ ነ' ያሻገረ ከቀቢጸ ተስፋ   ወደ ምሉዕ እኔ እግዚአብሔር ይመስገን   ጀመረ ዘመኔ። ኤልዔዘር ✍ https://t.me/Elezerbooks #የኤልዔዘርማስታወሻ
Show all...
የኤልዔዘር ማስታወሻ

ሀሳብ አስተያየት ካሎት @El_Ezer1216 ላይ ያገኙናል

👍 8 3👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
https://t.me/Elezerbooks #የኤልዔዘርማስታወሻ
Show all...
3👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ልዩ የማይቀርበት መፅሀፍ ምርቃት "በኩር ዓለሜ" ሩት ውብሸት ✍ https://t.me/Elezerbooks #የኤልዔዘርማስታወሻ
Show all...
03:17
Video unavailableShow in Telegram
161.85 MB
👍 2 1