cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

መንፈሳዊ መንደር🙏🙏

Welcome to our Telegram channel! 🌟 🙏 We're grateful for your support and excited to have you on board.

Show more
Advertising posts
200
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

01:11
Video unavailableShow in Telegram
12.69 MB
ሐሙስ     ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፦ ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል።     የምስጢር ቀን ይባላል፡- ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል።   የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡- መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል። የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡- ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል። https://t.me/menfesawimender
Show all...
1
በሌሊት ከአምላኩ ተምሮ ምሥጢሩ የተገለጸለት ኒቆዲሞስ ቀድሞ በአደባባይ ሔዶ መማርን ይፈራ እንዳልነበረ ምሥጢሩ ሲገለጽለት ግን አይሁድ ጌታችንን በሰቀሉት ዕለት ፍርኃት ርቆለት ከአርማትያሱ ዮሴፍ ጋር ቅዱስ ሥጋውን ገንዞ ለመቅበር በቃ፡፡ ‹‹ወአልቦ ፍርኃት ውስተ ተፋቅሮትነ፤ ፍጹም ፍቅር ፍርኃትን አውጥቶ ይጥላል›› ተብሎ እንደ ተጻፈ (ማቴ. ፳፯፥፶፰፤ ፩ኛዮሐ. ፬፥፲፰)፡፡ ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ያመነ፣ የተጠመቀ ይድናል፡፡ ያላመነ፣ ያልተጠመቀ ግን ይፈረድበታል›› (ማር. ፲፮፥፮) በማለት በሰጠን ቃል ኪዳን መሠረት በአምላክነቱ አምነን የመንግሥቱ ወራሾች እንኾን ዘንድ ለኒቆዲሞስ ምሥጢሩን እንደ ገለጸ ለእኛም ይግለጽልን፡፡ https://t.me/menfesawimender
Show all...
🥰 2
❖ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
          ❤ መጋቢት ፳፱ (29) ❤️ ✝️እንኳን ለክብር_ባለቤት_ለጌታችን_ለአምላካችን ለመድሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ ለበኵረ በዓላት ለሆነ ለጽንሰተ በዓልና ለጥንተ ትንሣኤ በአል ዓለም ለተፈጠረበ ቀንና ለሀዋሪያው ቅዱስ ጳውሉሎስ እልዋሪቆን በምትባል አገር ገብቶ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ረዳትነት (አማላጅነት) ላስተማረበትና ብዙ ሺህ ሰዎች በጌታችን ስም ላጠመቀበት በሰላም አደረሰን። ❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ገብርኤል መልአክ ውእቱ ዜነዋ ለማርያም ወይቤላ ትወልዲ ወልደ ትቤሎ ከመ ዝኑ እንጋ ይትምኁ አምኃ"። ትርጉም፦ ቅዱ ገብርኤል መልአክ መጥቶ ማርያምን ወንድ ልጅን ትወልጃለሽ አላት፤ እርሷም ይኽ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው አለች። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። ❤ "ሰላም ለፅንሰትከ በከርሠ ማርያም ፅሌ። መጽሐፈ ሐሤት ክርስቶስ ዘኢኮንከ መጽሐፈ ወይሌ። ሶበ ርእዩከ በታሕቱ እንዘ ኢተዓርቀ እምሉዔሌ። አእኰቱከ ቃለ አኰቴት በሃሌ። ሰላም በምድር ወበሰማይ ሃሌ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመጋቢት_27። ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "አንሰ ተሠየምኩ ንጉሠ በላዕሌሆሙ። በጽዮን በደብረ መቅደሱ። ከመ እንግር ትእዛዞ ለእግዚአብሔር"። መዝ 2፥6-7። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥26-39። ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "አንተ እግዚኦ አቅደምከ ሣርሮታ ለምድር። ወግብረ እደዊከ እማንቱ ሰማያት። እማንቱሰ ይትኃጎላ ወአንተሰ ትሄሉ"። መዝ 101፥25 ወይም 109፥3። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 1፥1-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 1፥13-22 እና የሐዋ ሥራ 17፥13-30። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 1፥1-15። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ወይም የቅዱስ ባስልዮስ ወንድም የቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘኑሲስ ነው።
🌺መልካም የጌታችን የጽንሰት በዓልና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።  
           https://t.me/menfesawimender             
Show all...
✞ ኪዳነ ምሕረት ✞ ኪዳነምህረት የእረፍቴ እናት ሰላም ሆነ ባንቺ አማላጅነት ንጽህት ድንኳን በእምነት ያጌጥኩብሽ ሰላም ሆነ በአማኑኤል ልጅሽ (፪) የብርሃን ዝናር ባይኖረኝም በንጉሥ ፊት ተሸልሜ ብቆም በልጅሽ ነው ውበቴ ማማሩ በምልጃሽ ነው ስሜ መቀየሩ በልቤ ላይ ተነበበ ልጅሽ አሁን ስሜ ተጠርቷል በልጅሽ ከታች በምድር እስከ ሰማይ ደረስ ድርሻዬ ነው ስምሽን ማወደስ(፪) አዝ= = = = = የከበረ ሆነሽ ንግግሬ ቅኔ አነሳሁ ለስምሽ ዘምሬ እንደ ዝግባ ከፍ ብዬ ብታይ ወጥቶልኝ ነው በሰማይሽ ፀሐይ ስለ ምልጃሽ ዘይቱ ፈሰሰ አንቺን ይዤ ሙሽራው ደረሰ ቀንዲሌ ነሽ ድንግል አዛኝቱ በልጅሽ ነው የነፍሴ ጽናቱ(፪) አዝ= = = = = ከኤልያብ ቢደምቅ ደም ግባቴ ማን ሊመርጠኝ ያለአንቺ እናቴ ተዋብኩብሽ ገጼ በአንቺ አበራ አንደበቴ ስምሽን ሲጠራ እንደ ሙሴ እንደ አሮን በትር ማምለጫዬ ከፈርዖን ቀንበር ከእንግዲህማ እኔ እንዴት አዝናለሁ አማላጄ አንቺን ይዤሻለሁ(፪) መዝሙር ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
Show all...
_ ኪዳነምህረት .mp33.22 MB
👍 1 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.