cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሸገⓇⒺ➬🆓

የሸገⓇⒺ➬🆓 ya Telgrame Takatayoche holame ባባበዱ የፍቅር ታሪኮች ለናንተ ያበደ ፊልም ከ20 ደቂቃ ያልበለጡ ፊልም እንለቃለን ይመቻ ↪️ 🎶 ⏮ ⏯ ⏭ 🎥 ↩️ ይመልከቱ ይከታተሉን🙏

Show more
Advertising posts
194
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
​​​​​​​  ​​         ┈┈••◉❖◉●••┈          ዝም ብለሽ ስሚኝ🌺       ❣ :¨·....................:¨·.❣ ......... ✍ፃፍኩልሽ💌 ........ አንድ ቀን እንደኔው የፍቅር ትርጉሙ ሰው ወደሽ ካየሽው ስቃዩ ህመሙ ላንቺ ብዙ እንደሆንኩ ያኔ ይገባሻል ስነግርሽ ዝም ያልሽው ዛሬ ይቆጭሻል አሁን ምን ያደርጋል ቢያዝኑ ቢቆጩ ፍቅር አገርሽቶ በእንባ ቢራጩ ያ የኔ ምስኪኑ እንግልቱ ልቤ የፍቅርን ትርጉም ባየው ሰው ቀርቤ እኔም ቆጨኝ ዛሬ ያኔ ያለቀስኩት ሌላ ሌላ ስትይ አንቺን አንቺን ያልኩት ዛሬ ግን ልቤም ልብ ገዛ ሌላ ሰው ወደደ አንቺን ለሰው ትቶ እሱ ከሰው ሄደ በቃህ ሂድ ብለሽው ልቤ ሄዷል ቆርጦ ይዟል አንቺን ትቶ የራሱን ሰው መርጦ እኔስ የሰው ሆንኩኝ አንቺም ሰው ፈልጊ ይመለሳል ብለሽ ተስፋ እንዳታደርጊ ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»✽‌┉┉┄┄ ‌‌‌‌‌‌‌‌🌹🍃✨𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑✨🍃🌹 ‌‌‌ 🥀 @MENTA_LIBOCHE🥀 🥀 @MENTA_LIBOCHE🥀 🥀 @MENTA_LIBOCHE🥀       ▬▬ #መንታ_ልቦች▬▬
Show all...
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘 ክፍል 2️⃣6️⃣ 💝 #የመጨረሻ_ክፍል "እሱን እንዳታስቢው ወይም ራስሽ ፈልገሽ አግኝው... ደግሞ አታገኝውም" አማራጭ የለኝም ሻንጣዬን ይዤ ወደኋላ ተመለስኩ። "እሺ ውሰደኝ አሁን ውሰደኝ" "አይ አይሆንም ነገ ነው የምንሄደው" በእሽታ አንገቴን ነቀነኩለት። ወደቀኝ ገልመጥ ብዬ ሳይ የሰርግ ቬሎዬ ተሰቅሏል። ለራሴ ወደኋላ የለም አልኩ... ።።።።።። ።።።።። ።። ። ።።።።። "አንደርስም እንዴ ደግሞ እኮ አይኔን በጨርቅ አስረህዋል። የት ነው የምንሄደው ራቀብኝ? ያ ውሻ የት ነው ያለው?" "አይንሽን ከገለጥሽ ከኔ ጋ ትጣያለሽ ማርያምን የምሬን ነው። ታገሽ ትንሽ ነው የቀረን ደርሰናል" ጥቂት ደቂቃ ከተጓዘ በኋላ መኪናውን አቆመው "አሁን ጨርቁን ማንሳት ትችያለሽ" ቶሎ ብዬ ፈታሁት... ሰው የሌለበት ቦታ ነው። "ምንድነው ቢኒ እየቀለድክብኝ ነው" ፊቴን አዙሬ በንዴት አየሁት "ውረጂ.,. ያውልሽ እዛጋ ይታይሻል...( በወዳደቁ ነገሮች የተሰራች ቤት) እዛ ውስጥ አለልሽ ውረጂና የፈለግሽውን አድርጊው" ሳላቅማማ ወረድኩ። በእልህና ንዴት እየተራመድኩ ወደቤቱ ተጠጋሁ ልገባ ስል "እባቷ ነኝ ባሏ. ... ሀ ሀ ሀ... ንገሩኝ እስኪ እናቷን አግብቶ ልጁን ያስረገዘ አባት ታውቃላችሁ... አታውቁም? ሙትቻ ለምንድነው የምታፈጡብኝ... መልሱልኝ... ኧረ ተውኝ ኡ ኡ ኡ..." ጩኸቱ አስደንግጦኝ ወደኋላ ተመለስኩ። ትንሽ ተራምጄ ቆምኩና ልጄን አሰብኳት "እገለዋለሁ" ወደ ቤቷ ተመለስኩና ከፍቼ ጎንበስ ብዬ ገባሁ። የቤቱ ጠረን ይገፈትራል ሰው የመጣም አልመሰለው ዝምም ብሎ ልፍለፋውን ቀጥሏል። የማላውቃቸውን ብዙ የሴት ስሞች ይጠራል... ያለቅሳል፣ ይስቃል፣ ይራገማል፣ ድንገት ደግሞ አስደንጋጭ ጩኸቱን ይለቀዋል። ለደቂቃዎች ዝምምም ብዬ ሰማሁት... በብዙው የቤቱ ቀዳዳ በሚገባ ብርሀን አየሁት ከድምፁ ውጪ ምኑም እሱን አይመስልም። ልብሱ ተቀዳዷል፣ ፊቱ ጠቁሮ ከሰል መስሏል፣ ፀጉሩ ተንጨባሯል፣ እላዩ ላይ ተፀዳድቶ መሬቱ ጭምር በሽንትና ሰገራ ተበክሏል። ዮኒ እኔ ልሰጠው ካሰብኩት ሞት በላይ በቁሙ ሞቷል... ልቤን ሽው የሚል የሀዘኔታ ጦር ወጋኝ። ወዲያው ደግሞ ልጄን የከዳኋት መሰለኝ... እየሮጥኩ ከቤቱ ወጣሁ... ልፍለፋው ከኋላዬ ይሰማኛል... እያለቀስኩ መኪናውን ከፍቼ ስገባ "አደረግሺው ሩት ገደልሽው" አለኝ "ሞቷል እኮ ቢኒ የሞተን ሰው ድጋሚ እንዴት እገለዋለሁ" ድፍት ብዬ ተንሰቀሰቅሁ ።።።።። ።።።።። ።።።።። ።።።።። "ቢኒ እባክህ ምንም ሰላም ሊሰማኝ አልቻለም ዮኒን ሆስፒታል እንውሰደው" ደረቱ ላይ ተኝቼ ለቀናት ከራሴ ጋ ስከራከርበት የነበረውን ሀሳብ ነገርኩት "እኔ የማውቃትም የምወዳትም ሩት ይቺ ናት ለጠላቷ ሳይቀር የምትራራ። አታስቢ የኔ ቆንጆ ዛሬውኑ እናደርገዋለን" እዛው ቦታ ተመልን ሄድን። ወደዛች ቤት ገባን አጠገቡ ዳቦ ቁጭ ብሏል። ለነፍሱ ያደረ ሰው እንደሚመግበው ገባኝ። መለፍለፉን አላቆመም እንጂ ተዳክሟል... ይዘናቸው የሄድነው ባለሞያዎች በግድ አንስተው ስትሬቸር ላይ አደረጉት... ከኪሱ የተጣጠፈ ወረቀት ወደቀ፤ ቀልጠፍ ብዬ አነሳሁትና ዞር ብዬ ከፈትኩት በትልቁ ርዕስ "ፀፀት" ይላል። ከስሩ ደግሞ "ለማታዩኝ እኔ ግን ብየቀኑ ለማያችሁ ለበደልኳችሁ ሁሉ" ይላል... ትርጉም ያለው ነገር ሊሆን ቢችልም ማንበብ አልፈለኩም... ሌላ ሸክም መሸከም አልፈልግም... እጄ ላይ ያለውን ሶስት ገፅ ወረቀት ቀዳድጄ ዱቄት አደረኩትና ለነፋስ ሰጠሁት ብትትንን... አምቡላንስ ውስጥ አስገብተው ይዘውት ሄዱ። ሰላም ተሰማኝ ።።።።። ።።። ።።።።። ።።።። አዳራሹ በእንግዶች ጢም ብሎ ተሞልቷል። ቃል የሚያገባቡን ቄስ ቦታቸውን ይዘው ተቀምጠዋል። "በሀዘን በደስታዋ በህመም በጤናዋ..." ቢኒ ቃል ገባ እሱ ያለውን መልሰው እኔንም አስባሉኝ። የጋብቻ ቀለበት ጣቴ ላይ አደረገልኝ እኔም እንደዛው አደረኩለት..... ገና ወደሰውነት ቅርፅ ያልተቀየረው የአምስት ሳምንት ልጄ ደስ ብሏት/ብሎት ይሆን ሆዴን ዳበስኩት። የልጄ አባት ቢኒ ፈገግ ብሎ አየኝ "ተመስገን" አልኩ በልቤ የማያልፉ የመሰሉኝ ሁሉ አለፉ... ዛሬ ደስተኛ ነኝ... ነገን አምላክ ያውቃል። ተ ፈ ፀ መ ። በፅሁፉ ላይ ያላችሁን ማንኛውንም አስተያየት @Menta_liboche_bot ላይ አድርሱኝ። ፅሁፉን እያዘገየሁ ላበሳችጨኋችሁ ከጉልበቴ በርከክ ከወገቤ ሸብርክ ብዬ ይቅርታ እጠይቃለሁ 💔 መክንያቱ ምን መሰላችሁ ታሪኩን ከመፅሐፍ ላይ ነበር የምጽፍላችሁ 🙏🙏🙏 በሌላ ፅሁፍ እስከምንገናኝ ቻው ፅሁፉን ከወደዳችሁት ለምትወዱት #share አድርጉ ያልተነበቡ ታሪኮችን ለማንበብ ቻናላችንን ይቀላቀሉ @MENTA_LIBOCHE ነፍ ደስታ የበዛ ፍቅር ለእናንተ😘😘😘 ከወደዳችሁት ❤️ ✳️በሌላ ተከታታይ ታሪክ በቅርቡ በአሪፉ አቀራረብ እንመለሳለን 🙏
Show all...
00:15
Video unavailableShow in Telegram
5.18 MB
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘 ክፍል 2⃣4⃣ #ከጊዜያት_በኋላ "ንገሪኝ እስኪ ሩቴ ሀኪም እንዲያይሽ ባትፈልጊም ህመምሽን ለኔ ንገሪኝ ዝምምም ብዬ እሰማሻለሁ። ስለ ልጅሽ ስለ ዮኒ ስለተፈጠረው ሁሉንም ንገሪኝ" ሶስት ወራትን በዝምታ ስለዚህ ነገር ሳያነሳብኝ ሳላወራው በየጊዜው የአእምሮ ህመሜ እየተነሳ ከኔው እኩል ሲሰቃይ አሳልፈናል። ትዕግስቱ እንክብካቤው ፍቅሩ ድሮ ከማውቀው የበለጠ ተወዳጅ ሆኖ ነው ያገኘሁት። ግን ምን ዋጋ አለው ፍቅር አንዳንዴ ፍትሀዊ አይደለም ቢሆንማ ኖሮ የማፈቅረው ዮኒን ሳይሆን ቢኒን ነበር። ወደ መኝታ ቤት ሄድኩ... ተከተለኝ... በሩን ከፍቼ ገባሁና ቤቴ ሄደን ካመጣናቸው እቃዎች መሀል አነስተኛውን ሻንጣዬን አወረድኩት... ከፈትኩት... ውስጡ ያለው ሁሉም የልጄ ማስታወሻ ነው። ለአዲስ አመት የሳለችልኝን አበባ አገኘሁት... እሱን አቅፌ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ "የኔ ልጅ... የኔ እንቁ... ናፈቅሽኝ እኮ" ቢኒ አጠገቤ ብርክክ ብሎ ትከሻዬን ያዘኝ ከዛም ወደራሱ አስጠግቶ አቀፈኝ።  ህመሜ ሳይነሳ ለመጀመሪያ ጊዜ ራሴን አረጋጋሁና ከእቅፉ ወጥቼ ከመፅሀፍ መሀል አጣጥፌ ያስቀመጥኩትን ደብዳቤ አወጣሁት... ከባዱን መርዶ ያረዳኝን... መራራውን እውነታ የጋተኝን ደብዳቤ አወጣሁና ለቢኒ ሰጠሁት። ግራ በተጋባ ፊት ካየኝ በኋላ ከፈተው... ደጋግሜ ከማንበቤ የተነሳ እያንዳንዱን ቃል እንደ ውዳሴ ማርያም የሸመደድኩትን ደብዳቤ እሱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊያነበው ከፈተው... እንዲህ ነው የሚለው... "ማሚ ከበደል ሁሉ የቱ እንደሚከፋ ታውቂያለሽ... አባቴ የምትይው ሰው በስሜት ጦዞ ጭንሽን ሊከፍት ሲታገል ማየቱ...... ማም እውነቱ ይገልሻል አውቃለሁ ...ግን እንደዛ ጠንካራ ስነ ልቦና እንዲኖራት አድርገሽ ያሳደግሻት ልጅሽ ለምን ራሷን አጠፋች? የሚለው ጥያቄም ይገልሻል። ማም እውነቱን እወቂው..... መጀመሪያ የውሸት ቆይቶ ደግሞ የእውነት አባት የሆነኝ ዮኒ የውሸት አባቴ እያለ አንዴ ብቻ ሳይሆን በተደጋጋሚ ደፍሮኛል። ታስታውሻለሽ ያኔ ፔሬድ አሞኝ ነው ብዬሽ የተኛሁ ጊዜ... ለመጀመሪያ ጊዜ የደፈረኝ ቀን ነበር። አንቺ ውስጥ እያለሽ ሊጠይቀኝ ሲመጣ ፊቴን አዙሬበት ነበር አይደል? ከዛ አንቺ ወጣሽ ምን እንዳለኝ ታውቂያለሽ 'በሶስተኛው ቀን መድገም አለብን ካላዛ ተደፍነሽ ትቀሪያለሽ' አለኝ። እናም በሶስተኛው ቀን መኝታ ቤቴ ድረስ መጣ... መከላከል ደከመኝ እና በዝምታ አየሁት ሳይራራልኝ እላዬ ላይ ጨፍሮ ሄደ...  ያንኑ ድርጊቱን የአባትነት እውነታው እስከሚታወቅ ድረስ ደጋገመው። በተለይ ፊልድ መውጣትሽ ለሱ ምቹ ሁኔታ ለኔ ደግሞ ስቃይን ፈጠረ ካንቺ ፊት ላይ የየሁትን ደስታ እኔ ጋር ፈልጌ አጣሁት። ማም እንዴት ልደሰት... አባቴን አገኘሁ ብዬ እንዴት ደስ ይበለኝ...?  አባትነቱን እኮ ጭኔ መሀል ቆፍሮ ቀብሮታል። እናም አባቴ አይደለም ሊሆንም አይችልም ብዬ በዝምታ ተሸብቤ ቁጭ ብዬ እያለ ሌላ ክስተት ተፈጠረ። በየጊዜው እየመጣ ይቅርታ ብሎኝ 'አደራ ለናትሽ እንዳትነግሪያት' ከሚለኝ ከህሊናቢሱ አባቴ የስምንት ሳምንት ነብሰ ጡር እንደሆንኩ ሆስፒታል አረጋገጥኩ። ያኔ በራሴ ላይ ወሰንኩ... ታሪክ ራሱን አይደግምም... ማም አንቺ አባት እንደሌለኝ እያሰብሽ ወልደሽ እሳደግሺኝ... የኔ ልጅ አባት ግን አባቴ ነው... እናም በራሴ ላይ እና ባልወለድኩት የአባቴ ልጅ ላይ የሞት ፍርድ ወሰንኩ። ማሚዬ ለኔ ስትይ ጠንክረሽ ኑሪ እወድሻለሁ። እድለቢሷ ልጅሽ" ደብዳቤውን አንብቦ ከጨረሰ ቢቆይም እንባ ከአይኖቹ እየወረደ ፍዝዝ ብሎ ተቀምጧል። "ይህን ደብዳቤ ሳገኘው ቢኒ ጊዜው ረፍዷል... የልጄ ገዳይ አጠገቤ አልነበረም... ትቶኝ ሄዶ ነበር... ፈለኩት በየሆስፒታሉ በየሆቴሉ ግን አጣሁት... ባገኘው በአደባባይ ስጋውም ዘልዝዬ ለአሞራ እሰጠው ነበር"።  እያለቀሰ መጥቶ አቀፈኝ ረጅም ሰአት ተቃቅፈን ተላቀስን...። "እባክሽ አንድ ነገር እሺ በይኝ የስነልቦና ሀኪም ይይሽ እባክሽ ለኔ ስትይ" ለብዙ ጊዜ ደጋግሞ ቢጨቀጭቀኝም እምቢ ነበር መልሴ "እሺ ደስ ያለህ ሀኪም ጋ ውሰደኝ" ።።።።። ።።።።። ።።።። ።።።።። ።።። የስነ ልቦና ህክምናዬን ከጀመርኩ አንድ ሳምንት ቢያልፈኝም ለዶክተሬ ምንም የነገርኩት ነገር አልነበረም። የሆነ ቀን ግን ልክ ከዚህ በፊት ያለውን ታሪክ እንደሚያውቀው ሁሉ "ዮኒን ብቻ ጥፋተኛ አድርጌ እንዳልፈርድ የሚያደርገኝ እንደዚህ ያሳመመኝ ብዙ ፀፀት ውስጤ አለ። ብዙ ቢሆን ኖሮ.... ብዙ.... ብዙ.... •ከመጀመሪያው ታሪኬን ነግሬው ቢሆን ኖሮ •ስራ ስራ ማለቴን ትቼ ለልጄ ጊዜ ሰጥቻት ቢሆን ኖሮ •እንደዛ ሆና እያየኋት ትንሽ እንኳን ለምን አልተጠራጠርኩም... አሁን እኔ ዶክተር እባላለሁ... ከሁሉም በላይ ፀፀቱ በልቶ ጨረሰኝ... መገጣጠሚያ አጥንቴ እስከሚታይ ከሳሁ... ጠቆርኩ... ታመምኩ... አበድኩ ...ግን ትርጉም አልነበረውም... እኝህ ሁሉ የኔን እንቁ አይመልሱልኝም ባዶ... አንተስ የኔን እንቁ ትመልስልኛለህ? አየህ እዚህ መጥቼ መፋጠጣችንም ትርጉም የለውም ባዶ..." አልኩት። ዝምምም ብሎ ካየኝ በኋላ ከወንበሩ ተነስቶ መጥቶ ፊት ለፊቴ ሶፋ ላይ ተቀመጠ 🥀 @MENTA_LIBOCHE🥀 🥀 @MENTA_LIBOCHE🥀 🥀 @MENTA_LIBOCHE🥀       ▬▬ #መንታ_ልቦች▬▬ ይቀጥላል.... ቻናላችንንይቀላቀሉ ከወደዳችሁት ❤️
Show all...
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘 ክፍል 2⃣5⃣ ከስድስት ወራት ያላሰለሰ የህክምና ክትትል በኋላ ወደራሴ ተመለስኩ ወደ ስራየም ጭምር። ከቢኒ ጋር ደስ የሚል የፍቅር ግንኙነት ጀመርኩ... ህይወት ድጋሚ ቀጠለች። ያለፈው ባይረሳም ህመሙ ቀንሷል... የልቤ በልቤ ተቀብሮ መሳቅ ቻልኩ። ከቢኒ ጋ ልንጋባ ነው ማለትም ከሁለት ወር በኋላ እንጋባለን። ለፊርማው እንጂ የምንኖረው አንድ ቤት የምንተኛው አንድ አልጋ ላይ ከተጋባን ቆይተናል ለማለት ነው። ልንጋባ መሆኑን ያወቀው ሀብታሙ ካለበት ሀገረ አሜሪካ የሚያምር ቬሎና ሱፍ ልኮልናል። ለቢኒ ሚዜ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ። የሆነኛው ሌሊት ላይ ተኝቼ ልጄን በህልሜ አየኋት... ብቻዋን አይደለም ዮኒ ሲደፍራት "ድረሽልኝ" እያለች ስትጮህ... ጮኬ ከእንቅልፌ ነቃሁ... አጠገቤ የተኛው ቢኒ ጩኸቴ አስደንግጦት "ምንድነው ፍቅር አይዞሽ ቅዠት ነው" አለና እቅፉ ውስት ከተተኝ... እኔ ግን የበቀል ጥሜ ድጋሚ አንሰራራ... እፈልገዋለሁ እናም እገለዋለሁ... እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ። ለቀናት በሀሳብ ተብሰከሰኩ እናም ወሰንኩ ይህን ነገር ከስሩ መንግዬ መጣል ይኖርብኛል። ተቆርጦ ባቆጠቆጠ ቁጥር ህመሙ እየባሰ ነው የሚሄደው ስለዚህ እ ገ ለ ዋ ለ ሁ። ።።።።። ።።።።።። ።።።።።።።        #አሁን ትቼው ልሄድ ነው። በቃ ልሄድ ነው የመጨረሻ ውሳኔዬን ወስኛለሁ የምሄደው እንደ ሌላው ጊዜ ጥላቻንና ክህደትን ሽሽት አይደለም...  ፍቅርን እንጂ። እናም በሀሳብ እየዋዠኩ ደብዳቤ ልፅፍለት ወሰንኩ ቢያንስ ምክንያቴን ማሳወቅ አለብኝ አይደል... ደግሞ ጠፋች ብሎ ሀገር ምድሩን ነው የሚያምሰው... መፃፍ ጀመርኩ "አንዳንዴ ልቋቋመው ከምችለው በላይ ይሆንብኛል። ፍቅርህ፣ ስስትህ፣ እንክብካቤህ፣ አንተን ትተህ ለኔ ደስታ መድከምህ፣ ከቃላት ጋጋታ ይልቅ በተግባር የምታሳየኝ መውደድህ በአጠቃላይ ሁሉም ነገርህን መቋቋም ያቅተኛል። ሰው እንዴት ይህን ያክል ሰውን ሊወድ ይችላል እንዴትስ ሁሉ ነገሩ ፍቅር ብቻ ይሆናል ፍቅር... ፍቅር... አሁንም ፍቅር.... አንተጋ ያለው ፍቅር ብቻ ነው እኔጋ ደግሞ ላንተ ያለኝን ፍቅር ሊፈታተን የሚችል የበቀል ጥም አለ። ያንተ ፍቅር እና የኔ በቀል ጥም ተጣጥመው ሊሄዱ አይችሉም ስለሆነም ጥሜን ልቆርጠው ፍቅርህን መሸሽ መርጫለሁ። ያጣሁት ልጄን... ማያዬን... እንቁዬን... ሁሉ ነገሬን ነው። ገዳይዋን ሳልገድል እረፍት እይሰማኝም። አዝናለሁ ቢኒ... አፈቅርሀለሁ ግን ልሄድ ነው። ትቼህ ልሄድ ነው... ጠንካራ ነህ ትወጣዋለህ። ደህና ሁን ሩት " ደብዳቤውን ፅፌ ከጨረስኩ በኋላ አጥፌ ፊት ለፊት ጠረጴዛ ላይ አስቀመጥኩትና ሻወር ልወስድ ገባሁ። ቢኒ ቶሎ እንደማይመጣ ስለማውቅ ዘና ብያለሁ... ታጥቤ ፎጣዬን እንዳሸረጥኩ ስወጣ ቢኒን አልጋ ላይ ቁጭ ብሎ አገኘሁት በእጁ የፃፍኩትን ደብዳቤ ይዟል። "ምንድነው ፍቅር? ድጋሚ ወደኋላ... ለምን እኔንስ ታደክሚኛለሽ አላሳዝንሽም" አለኝ አጠገቤ መጥቶ አይን አይኔን እያየኝ "ልጄን በህልሜ አየኋት ቢኒ... አድኚኝ እያለች ስትጮህ አየኋት... ልጄ ከመሬት ስር ተቀብራ...(ሳግ አነቀኝ) አፈር ተጭኖባት እሱ ግን እየተነፈሰ ነው። እፈልገዋለሁ እናም በእጄ እገለዋለሁ" እልሄ ልኩን አለፈ...  ፎጣዬን ጥዬ ልብሴን ለባበስኩና ሻንጣዬን ይዤ ልወጣ ስል። "ዮኒን አግኝቼዋለሁ" አለኝ። ባለሁበት ቀጥ ብዬ ቆምኩ "ምን?" "ይሄን በቀል የተውሽ መስሎኝ ነበር ግን ከፈለግሽ አብሬሽ እሄዳለሁ ያለበትንም አሳይሻለሁ ስትገይውም ቆሜ አይሻለሁ።" "የት ነው ያለው ቦታውን ብቻ ንገረኝ ብቻዬን እሄዳለሁ" "እሱን እንዳታስቢው ወይም ራስሽ ፈልገሽ አግኝው... ደግሞ አታገኝውም" አማራጭ የለኝም ሻንጣዬን ይዤ ወደኋላ ተመለስኩ። "እሺ ውሰደኝ አሁን ውሰደኝ" "አይ አይሆንም ነገ ነው የምንሄደው"  በእሽታ አንገቴን ነቀነኩለት። ወደቀኝ ገልመጥ ብዬ ሳይ የሰርግ ቬሎዬ ተሰቅሏል። ለራሴ ወደኋላ የለም  አልኩ... ይቀጥላል.... ቻናላችንንይቀላቀሉ ┏━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┓ 🥀 @MENTA_LIBOCHE🥀 🥀 @MENTA_LIBOCHE🥀 🥀 @MENTA_LIBOCHE🥀 ┗━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━ ከወደዳችሁት ❤️
Show all...
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘 ክፍል 2⃣4⃣ #ከጊዜያት_በኋላ "ንገሪኝ እስኪ ሩቴ ሀኪም እንዲያይሽ ባትፈልጊም ህመምሽን ለኔ ንገሪኝ ዝምምም ብዬ እሰማሻለሁ። ስለ ልጅሽ ስለ ዮኒ ስለተፈጠረው ሁሉንም ንገሪኝ" ሶስት ወራትን በዝምታ ስለዚህ ነገር ሳያነሳብኝ ሳላወራው በየጊዜው የአእምሮ ህመሜ እየተነሳ ከኔው እኩል ሲሰቃይ አሳልፈናል። ትዕግስቱ እንክብካቤው ፍቅሩ ድሮ ከማውቀው የበለጠ ተወዳጅ ሆኖ ነው ያገኘሁት። ግን ምን ዋጋ አለው ፍቅር አንዳንዴ ፍትሀዊ አይደለም ቢሆንማ ኖሮ የማፈቅረው ዮኒን ሳይሆን ቢኒን ነበር። ወደ መኝታ ቤት ሄድኩ... ተከተለኝ... በሩን ከፍቼ ገባሁና ቤቴ ሄደን ካመጣናቸው እቃዎች መሀል አነስተኛውን ሻንጣዬን አወረድኩት... ከፈትኩት... ውስጡ ያለው ሁሉም የልጄ ማስታወሻ ነው። ለአዲስ አመት የሳለችልኝን አበባ አገኘሁት... እሱን አቅፌ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ "የኔ ልጅ... የኔ እንቁ... ናፈቅሽኝ እኮ" ቢኒ አጠገቤ ብርክክ ብሎ ትከሻዬን ያዘኝ ከዛም ወደራሱ አስጠግቶ አቀፈኝ።  ህመሜ ሳይነሳ ለመጀመሪያ ጊዜ ራሴን አረጋጋሁና ከእቅፉ ወጥቼ ከመፅሀፍ መሀል አጣጥፌ ያስቀመጥኩትን ደብዳቤ አወጣሁት... ከባዱን መርዶ ያረዳኝን... መራራውን እውነታ የጋተኝን ደብዳቤ አወጣሁና ለቢኒ ሰጠሁት። ግራ በተጋባ ፊት ካየኝ በኋላ ከፈተው... ደጋግሜ ከማንበቤ የተነሳ እያንዳንዱን ቃል እንደ ውዳሴ ማርያም የሸመደድኩትን ደብዳቤ እሱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊያነበው ከፈተው... እንዲህ ነው የሚለው... "ማሚ ከበደል ሁሉ የቱ እንደሚከፋ ታውቂያለሽ... አባቴ የምትይው ሰው በስሜት ጦዞ ጭንሽን ሊከፍት ሲታገል ማየቱ...... ማም እውነቱ ይገልሻል አውቃለሁ ...ግን እንደዛ ጠንካራ ስነ ልቦና እንዲኖራት አድርገሽ ያሳደግሻት ልጅሽ ለምን ራሷን አጠፋች? የሚለው ጥያቄም ይገልሻል። ማም እውነቱን እወቂው..... መጀመሪያ የውሸት ቆይቶ ደግሞ የእውነት አባት የሆነኝ ዮኒ የውሸት አባቴ እያለ አንዴ ብቻ ሳይሆን በተደጋጋሚ ደፍሮኛል። ታስታውሻለሽ ያኔ ፔሬድ አሞኝ ነው ብዬሽ የተኛሁ ጊዜ... ለመጀመሪያ ጊዜ የደፈረኝ ቀን ነበር። አንቺ ውስጥ እያለሽ ሊጠይቀኝ ሲመጣ ፊቴን አዙሬበት ነበር አይደል? ከዛ አንቺ ወጣሽ ምን እንዳለኝ ታውቂያለሽ 'በሶስተኛው ቀን መድገም አለብን ካላዛ ተደፍነሽ ትቀሪያለሽ' አለኝ። እናም በሶስተኛው ቀን መኝታ ቤቴ ድረስ መጣ... መከላከል ደከመኝ እና በዝምታ አየሁት ሳይራራልኝ እላዬ ላይ ጨፍሮ ሄደ...  ያንኑ ድርጊቱን የአባትነት እውነታው እስከሚታወቅ ድረስ ደጋገመው። በተለይ ፊልድ መውጣትሽ ለሱ ምቹ ሁኔታ ለኔ ደግሞ ስቃይን ፈጠረ ካንቺ ፊት ላይ የየሁትን ደስታ እኔ ጋር ፈልጌ አጣሁት። ማም እንዴት ልደሰት... አባቴን አገኘሁ ብዬ እንዴት ደስ ይበለኝ...?  አባትነቱን እኮ ጭኔ መሀል ቆፍሮ ቀብሮታል። እናም አባቴ አይደለም ሊሆንም አይችልም ብዬ በዝምታ ተሸብቤ ቁጭ ብዬ እያለ ሌላ ክስተት ተፈጠረ። በየጊዜው እየመጣ ይቅርታ ብሎኝ 'አደራ ለናትሽ እንዳትነግሪያት' ከሚለኝ ከህሊናቢሱ አባቴ የስምንት ሳምንት ነብሰ ጡር እንደሆንኩ ሆስፒታል አረጋገጥኩ። ያኔ በራሴ ላይ ወሰንኩ... ታሪክ ራሱን አይደግምም... ማም አንቺ አባት እንደሌለኝ እያሰብሽ ወልደሽ እሳደግሺኝ... የኔ ልጅ አባት ግን አባቴ ነው... እናም በራሴ ላይ እና ባልወለድኩት የአባቴ ልጅ ላይ የሞት ፍርድ ወሰንኩ። ማሚዬ ለኔ ስትይ ጠንክረሽ ኑሪ እወድሻለሁ። እድለቢሷ ልጅሽ" ደብዳቤውን አንብቦ ከጨረሰ ቢቆይም እንባ ከአይኖቹ እየወረደ ፍዝዝ ብሎ ተቀምጧል። "ይህን ደብዳቤ ሳገኘው ቢኒ ጊዜው ረፍዷል... የልጄ ገዳይ አጠገቤ አልነበረም... ትቶኝ ሄዶ ነበር... ፈለኩት በየሆስፒታሉ በየሆቴሉ ግን አጣሁት... ባገኘው በአደባባይ ስጋውም ዘልዝዬ ለአሞራ እሰጠው ነበር"።  እያለቀሰ መጥቶ አቀፈኝ ረጅም ሰአት ተቃቅፈን ተላቀስን...። "እባክሽ አንድ ነገር እሺ በይኝ የስነልቦና ሀኪም ይይሽ እባክሽ ለኔ ስትይ" ለብዙ ጊዜ ደጋግሞ ቢጨቀጭቀኝም እምቢ ነበር መልሴ "እሺ ደስ ያለህ ሀኪም ጋ ውሰደኝ" ።።።።። ።።።።። ።።።። ።።።።። ።።። የስነ ልቦና ህክምናዬን ከጀመርኩ አንድ ሳምንት ቢያልፈኝም ለዶክተሬ ምንም የነገርኩት ነገር አልነበረም። የሆነ ቀን ግን ልክ ከዚህ በፊት ያለውን ታሪክ እንደሚያውቀው ሁሉ "ዮኒን ብቻ ጥፋተኛ አድርጌ እንዳልፈርድ የሚያደርገኝ እንደዚህ ያሳመመኝ ብዙ ፀፀት ውስጤ አለ። ብዙ ቢሆን ኖሮ.... ብዙ.... ብዙ.... •ከመጀመሪያው ታሪኬን ነግሬው ቢሆን ኖሮ •ስራ ስራ ማለቴን ትቼ ለልጄ ጊዜ ሰጥቻት ቢሆን ኖሮ •እንደዛ ሆና እያየኋት ትንሽ እንኳን ለምን አልተጠራጠርኩም... አሁን እኔ ዶክተር እባላለሁ... ከሁሉም በላይ ፀፀቱ በልቶ ጨረሰኝ... መገጣጠሚያ አጥንቴ እስከሚታይ ከሳሁ... ጠቆርኩ... ታመምኩ... አበድኩ ...ግን ትርጉም አልነበረውም... እኝህ ሁሉ የኔን እንቁ አይመልሱልኝም ባዶ... አንተስ የኔን እንቁ ትመልስልኛለህ? አየህ እዚህ መጥቼ መፋጠጣችንም ትርጉም የለውም ባዶ..." አልኩት። ዝምምም ብሎ ካየኝ በኋላ ከወንበሩ ተነስቶ መጥቶ ፊት ለፊቴ ሶፋ ላይ ተቀመጠ 🥀 @MENTA_LIBOCHE🥀 🥀 @MENTA_LIBOCHE🥀 🥀 @MENTA_LIBOCHE🥀       ▬▬ #መንታ_ልቦች▬▬ ይቀጥላል.... ቻናላችንንይቀላቀሉ ከወደዳችሁት ❤️
Show all...
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘 ክፍል 2⃣3⃣ "የምን እእ ነው ምንድነው ንገሪኝ" ለአመታት ስቃዥ የነበረው ትዝ አለኝ... አይ አይሆንም "በህልሜ የሚያስፈራ ሰው ገደል ውስጥ ሊከተኝ ሲል አየሁ" ኡፍፍፍፍ.... እኔ ደግሞ ስንቱን አሰብኩት "አሁን እንዴት ነው ቁርጠቱ ተሻለሽ" ዮኒ በሩን ከፍቶ ገባ "ምን ሆነሽ ነው ምናሴ ብዙ አመመሽ እንዴ ጠዋት እኮ ረፍዶብኝ ሳላይሽ ሄድኩ" የቅድሙን የተፀፀተ ፊት ሳይሆን ፍም እሳት የሚተፋ አይኑን አየሁት... እንቁ ፊቷን አዙራ ተኛች "ምንድነው አንቺ ባለጌ ለአባትሽ መልስ ስጪው እንጂ" ፊቷን እንዳዞረች "ደና ነኝ ተሽሎኛል" አለችው። ተነሳሁና ትቻቸው ወጣሁ። ሳሎን ሶፋ ላይ ቁጭ ብዬ ቲቪው ላይ አፈጠጥኩ..... ሀሳቤ ግን ሩቅ ሄዶ ነበር። መች ነው ይሄን ክፍተት የፈጠርኩት... ለራሴ ደግሜ ልነግረው አልፈልግም የምለውን ያን የመደፈር ታሪኬን ከመደበቅ... አዎ ከዛ ነው የጀመርኩት... ከዛ  የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ አልኩት... ከዛ... ከዛ... ከቢኒ ጋር እንኳን ምንም ግንኙነት የለንም... እሱም እንዳስረዳው እድሉን አልሰጠኝም። ቢዘገይም ነገሮችን አጥርቼ መሄድ እንዳለብኝ ተሰማኝ እና ታሪኬን ከአንድ ጀምሬ እነግረዋለሁ ብዬ ወሰንኩ... ግን አሁን አይደለም። ።።።።።።  ።።።።።  ።።።።። ።።።።። ።።።። ሩትን ምን ይጨንቃታል ብትሉ ሰውን ተጣልቶ ማኩረፍ እላችኋለሁ። በህይወቴ እንደመኮራረፍ የምጠላው ነገር የለም አኩርፌ ማደርም አልችልም... በቃ ከሰው ጋ ተጋጨሁ አይደል ወይ እዛው ጋ ችግሩን እነግረዋለሁ ወይም ዝም ብዬ አልፈዋለሁ... ብቻ ያስከፋኝም ላስከፋውም ድጋሚ ሳገኘው ያንን ሰው አዋራዋለሁ። ከዮኒጋ በአንድ ጣራ ስር... አንድ አልጋ ላይ እየተኛን በየቀኑ እያየሁት ለማኩረፍ ሞከርኩ ግን አልተሳካልኝም በደሉን ባልረሳውም ሳላስበው አዋራሁት። "መነጋገር ያለብን አይመስልሽም" አለኝ። ወደ ስራ ለመሄድ እየተጣደፍኩ እያለ "አስቤበታለሁ ማውራት አለብን ግን አሁን አይደለም... ሆስፒታላችን የልምድ ልውውጥ ሌላ ከተማ ሊልከኝ ነው። ከአስራ አምስት ቀን በኋላ እመለሳለሁ ያኔ እናወራለን" መኪናዬን አስነስቼ ወጣሁ ።።።።   ።።።።    ።።።።     ።።።። ሳሎን ቁጭ ብለን ከታሪኬ ሀ ጀመርኩለት "የአስራ ሶስት አመት ልጅ እያለሁ ነው........." ሁሉንም አንድ በአንድ ዘርዝሬ ነገርኩት ከሱ ግን ያላሰብኩትን ነገር ሰማሁ "እና ያኔ የደፈርኩት አንቺን ነበር" "ምን? ምንድነው የምታወራው?" "ብርቄን ታውቂያታለሽ? ጎረቤታችሁ ናት መሰለኝ" "አዎ ብርቄን ከነ ነገሯ የማያውቅ አለ እንዴ... ግን አንተ እንዴት?" "የዩንቨርስቲ ተማሪ እያለሁ እናቴ የማልወዳት አክስቴ ጋ መልዕክት ይዘህ ሂድ ብላ ላከችኝ... እረፍት ስለነበርንም እየተነጫነጭኩ ብርቄ ጋ መጣሁ። በዛውም ከአክስቴ ጎረቤት ልጅ ዘመናይ ጋር ተዋወቅሁ። በሁለት ቀን ውስጥ ተዋደን ሴክስ አደረግን( አውቃታለሁ አገር ያወቃት ወንድ አሳዳጅ ናት አልገረመኝም ) የዛን እለት ግን እዛ የጭቃ ቤት ውስጥ እያለን ወደኛ የሚመጣ ሰው ድምፅ ሰማን እና እሷ ቶሎ ብላ ወጥታ ሄደች እኔ ግን እዛው ቀረሁ። በወሲብ ስሜት ጦዤ ስወጣ አንቺን ከሩቅ አየሁሽ እና ጠራሁሽ.... ያ ሁሉ ነገር ተፈጠረ" ከነገረኝ ታሪክ ውስጥ አንድ አስደሳች ነገር አገኘሁ... የእንቁን እውነተኛ አባት "አክስቴ እኔ እንደደፈርኩሽ ስታውቅ... ማንም ሳያየኝ በሌሊት ሀገሩን ለቅቄ እንድሄድ ድጋሚም እንዳልመለስ አስጠንቅቃ ወደ እናቴ ላከችኝ። በሶስት ቀን ቆይታዬ ብዙ ታሪክ ፈጥሬ ተመለስኩ" ' ሳትፈልግ ማን ሊነካት' እያለች ስታወራ የነበረችውን ብርቄን አሰብኳትና ተገረምኩ ወዲያው ደግሞ ደስ የሚለውን ሁኔታ አሰብኩት "ደስ ሲል" ሳላስበው ቃል ከአፌ ወጣ "ምኑ ነው ደስ የሚለው የኔ አንቺን መበደል ድሮ እንደጀመረ ማወቅሽ ነው" ግራ ግብት ብሎት ያየኛል "እንቁ እውነተኛ አባቷን ማግኘቷ" "ማለት...? ምን እያልሽን ነው? ምናሴ የኔ ልጅ... አይ አይሆንም... ማለት ተደፍረሽ ነው የወለድሻት...? አይ ውሸትሺን ነው።" መልስ ሳልሰጠው እየሮጥኩ እንቁ መኝታ ቤት ገባሁ ቁጭ ብላ እያነበበች ነው። ስገባ ቀና ብላ አየችኝ " ምን ተገኘ ማሚ ፊትሽ እኮ በፈገግታ ሊፈነዳ ነው" "የተገኘውማ አባትሽ ነው" "የእውነት...(እንባዋ ኮለል ብሎ ወረደ ሰፍ ብላ አፍ አፌን አየችኝ) የት ነው ያለው ማሚ... የኔ አባት የት ነው?( ሳግ አነቃት) ማሚ በተለይ በዚህ ሰዓት አባቴን በጣም እፈልገዋለሁ... እማ ንገሪኛ..." "ዮኒ እውነተኛ አባትሽ ነው" አንገቷን ወደኔ አስግጋ ሁለመናዋ ጆሮ ሆኖ በአይኗ ሳይቀር ስትማፀነኝ የነበረችው ልጄ ከኣካሏ እኩል ስብር ስትል አየኋት "እሱ አባቴ አይደለም... ትክክለኛ አባቴን የአብራኩ ክፋይ የሆንኩትን ሰው ነው የምፈልገው" አለችኝ እንዳቀረቀረች "አዎ የኔ እንቁ አንቺ የዮኒ የአብራኩ ክፋይ ነሽ ታሪኩን እነግርሻለሁ። የአስራ ሶስት አመት ልጅ እያለሁ..." ዝምምም ብላ ሰማችኝ... ምንም አይነት እንቅስቃሴም ሆነ ንግግር አላደረገችም... ዝምምምም.... አውርቼ ስጨርስ "ደስ አይልም የኔ እንቁ" አልኳት እንባዋ ገደቡን ጥሶ ወረደ 'ምንድነው እንቁ ለምንድነው የምታለቅሺው' "ደስ ብሎኝ ነው እማ... የደስታ እምባ ነው። ነይ እቀፊኝ" ተቃቀፍንና "በቃ ይሄን ቀን ፏ አድርገን እናከብረዋለን ነይ ተነሺ" እጇን ይዤ አስነሳኋትና ወደ ሳሎን ሄድን ዮኒ የለም... መኝታ ቤት አየሁት የለም... ቤት ውስጥ የለም... ለአንድ ቀን ብቻ ሳይሆን ለሳምንታት የለም... ።።።። ።።።። ።።።። ።።። የሆነኛው ቀን ሌሊት ላይ ስልክ ተደውሎልኝ ዮኒ ያለበትን ቦታ ነገሩኝ... ጭፈራ ቤት ነው። ስሄድ ከሁለት ሴቶች ጋ አብሮ እያበደ ነው... ምንም ሳልል ወደቤቴ ተመለስኩ... ለራሴ ግን አንድ ውሳኔ ወስኜ ነበር 'ተመልሶ እዚህ ቤት አይረግጥም'። ብቸኝነት ተሰማኝ... ቅዝቃዜው አንዘፈዘፈኝ.. እናም ብቸኛዋ እንቁዬ ጋ ልሸሸግ ወደሷ መኝታ ቤት ሄድኩ። በሩን ከፍቼ ስገባ ግን የኔ እንቁ መሬት ላይ ተዘርራ አየኋት ጮኩ። እልፍነሽ ስትሮጥ መጣች... ከመሬት አንስተን አልጋ ላይ ካደረግናት በኋላ የልብ ምቷን አየሁት... ቆሟል... አፏን አሸተትኩት ገዳይ መርዝ ጠጥታለች። ሰውነቷን ነካሁት ከበረዶ ቀዝቅዛለች... የኔ እንቁ የለችም... ትታኝ ሄዳለች... ይቀጥላል.... ┏━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┓ 🥀 @MENTA_LIBOCHE🥀 🥀 @MENTA_LIBOCHE🥀 🥀 @MENTA_LIBOCHE🥀 ┗━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━ ቻናላችንንይቀላቀሉ ከወደዳችሁት ❤️
Show all...
#መንታ_ልቦች 😘 ያበደው ፍቅሬ 😘                                ክፍል 2⃣2⃣ "ባልሽን አሳርፊው ልንማር እንጂ ልንሸረሙጥ አልመጣንም ቴሌግራም ላይ ሙሉ መረጃውን ታገኛለሽ" ይላል። እየተጠራጠርኩ ቴሌግራም ከፈትኩ ፊት ለፊት የመጣልኝን መልዕክት ስከፍተው ፎቶ እና አጭር ቪድዮ.....  ዮኒ ከሌላ ሴት ጋር.... እየሰሙ አለማመን ያለም የሚጠበቅም ነው። እያዩ አለማመን ግን ምን ይባላል። በአካል መጥተው ዮኒ ከእከሊት ጋር ማገጠብሽ ቢሉኝ አይደለም እሱን ልጠራጠር ከነገረኝ ሰው ጋር ልጣላ እችላለሁ። አሁን ግን እውነታ ነው ቁጭ ያለልኝ... ከምወደው ባሌ ጋር እርቃን ገላዋን አብራው የምታብድ ሴት እያየሁ ነው። የአንዷ አልበቃ ብሎ ከሌላ ሴት ጋር ደግሞ ከንፈሯ ላይ ተጣብቆ ያለ ፎቶ እያየሁ ነው... ግን አንድ ነገር ብቻ ነው የምለው። "የኔ ዮኒ አያደርገውም" አድርጎታል እኮ ...ግን ይህንን ማመን ያልፈለገ ውስጥ አለኝ... እናም እውነታውን እያየ ግግም ብሎ አላምን አለኝ። አንደኛው ውስጤ ደግሞ ፍቅርን ሳይቀር ወደጎን ብሎ በቀልን ፈለገ። ቢችል አሁን ያለበት ሄዶ ስጋውን ቢዘለዝለው ተመኘ። የማያምነው ውስጤ ገኖ ወጣና "ዮኒ አያደርገውም" በጩኸት ቤቱን አደበላለኩት። ሰራተኛዬ እልፍነሽ መኝታ ቤቴን ከፈት አደረገችና "ሰላም ነው ሩት" አለችኝ "ሰላም ነው እልፌ ወደ ስራሽ ተመለሽ" በሩን ዘግታ ተመለሰች። ረጅም ደቂቃ ዝምምም ብዬ ስልኬ ላይ አፈጠጥኩ ሀሳቡ አደከመኝ ያየሁት እውነት አራደኝ በዛ ላይ ሰሞኑን የተለየ ኬዝ ስለነበረ ያለ እንቅልፍ ሆስፒታል ነበርኩ። ስልኬን ዘግቼ ያስቀመጥኩት መሰለኝ... ከዛ ወደ አልጋዬ ተራመድኩ.... አንድ.... ሁለት..... ጭልም አለብኝ። "እናት ኧረ ንቂ የኔ ፍቅር" ይሄን ጥሪ ከሰማሁት ስንት አመት ሆነኝ.... ሁለት.... ሶስት... ብቻ በዛ መሀል... አሁንስ ለምንድነው እየሰማሁት ያለሁት... ሁሉም ነገር ከረፈደ... ካለፈበት በኋላ ለምን?... አይኔን ሳልገልጥ እንቅስቃሴውን እየተከታተልኩ ነው። "ንገሪኝ እስኪ እናት ማነው ጥፋተኛ እኔ ወይስ አንቺ? በእርግጥ የኔ ጥፋት ሚዛን ይደፋል... ምክንያቱም ካየሽው ውጭ እንኳን ብዙ ጥፋቶችን ሰርቻለሁ ግን ባንቺ ጥፋት ላይ ተመርኩዤ ነው። ታውቂያለሽ ከቢኒ ጋር ድሮም እጠረጥርሽ ነበር እና ጥርጣሬዬን የሚያረጋግጥልኝ ነገር ሳገኝ እውነት አይደለም ብዬ ማመን አቃተኝ። ልታስረጅኝ ስትሞክሪ ውሸቷን ነው ብዬ አልሰማም አልኩሽ እናም ከዛን ጊዜ ጀምሮ ያለማቋረጥ ማገጥኩብሽ... ግን እናት ያሁኑ በደሌ በዛ..... (ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ እና ትንሽ ዝም ካለ በኋላ ቀጠለ) ከስንት ጊዜ በኋላ በአንዲት ልጅ ምክንያት ራሴን አዳመጥኩት። አብረሽኝ ካልተኛሽ ውጤትሽን አበላሸዋለሁ ብዬ አስፈራራኋት.... ብዙ ለመነችኝ... ልመናው አልሰራ ሲላት ግን ያንቺን አድራሻ ፈልጋ ሆስፒታል መጣችና አየችሽ። ስለትዳራችን ሳይቀር ብዙ መረጃ ሰበሰበች ከረፈደ ቢሆንም  ንግግሯ ከእንቅልፌ አነቃችኝ... ትልቁን በደሌን የሰራሁ እለት ከእንቅልፌ ነቃሁ 'ሚስትህ ነፍሷን ሳትሰስት ትሰጥሀለች... አንተ ማመን ባልፈለከው ውሸት ውስጥ ተደብቀህ በሀጢያት ተጨማልቀሀል... ለሷ አትገባትም ምክንያቱም ንፁህ ናት... ግን እግዜር ይቅር የማይለው የለም አምላክህንም ሚስትህንም ይቅርታ ጠይቀህ ወደራስህ ተመለስ። ለውጤቴ ስል አብሬህ ላድር አልፈልግም በተለይ ያቺ ሚስኪ ላይ ይሄን ላደርግ አልችልም። ከፈለግህ ኤፍ አድርገው ህሊናዬን አላቆሽሽም'  ብላኝ ስላንቺ እንዴት እንዳወቀች ሁሉንም ነገር አብራራችልን እና ለአመታት ከተኛሁበት እንቅልፍ ዛሬ ቀስቅሳኝ ሄደች። ያሰብኩት ለሀያ ደቂቃ ብቻ ነው። ወደራሴ ተመለስኩ... እውነታውን ማየት ቻልኩ... በንግግሮቼም ሆነ በተግባር ብዙ እንደገፋሁሽ አወቅሁ... በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን እንዴት እንደምትጠነቀቂልኝ... ምን ያክል እንደምትወጂኝ ተረዳሁ። ወደዚህ ለመምጣት እየተጣደፍኩ ስወጣ ቢሮ በር ላይ ከዚህ በፊት በውጤት አስፈራርቻት አብሪያት የተኛሁትን ልጅ አገኘኋት እናም ቪዲዮና ምስል ላንቺ እንደላከችልሽ ነገረችኝ። ምንም ሳልል ወደዚሁ መጣሁ ወድቀሽ አገኘሁሽ። ሩቴ እየሰማሽኝ እንደሆነ አውቃለሁ። ይቅር በይኝ አልልሽም በተለይ በአንድ ጉዳይ ያንቺ ይቅርታ አይገባኝም... ብቻ አይንሽን ግለጪና የፈለግሺውን ቅጪኝ" አይኔን ገለጥኩ ከወገቤ ቀና አልኩና ትራስ ተደግፌ ቁጭ አልኩ። ለረጅም ደቂቃ በዝምታ አፈጠጥኩበት "ደስ ያለሽን አድርጊኝ የፈለግሺውን ቅጪኝ " አንደበቴ ሊናገር ቢፈልግ እንኳን ውስጤ ዝምምምም ብሏል የሚያስፈራ ዝምታ "ደግሞ አሁን እሰማሻለሁ ከቢኒ ጋር ያደረጋችሁትን ንገሪኝ እኔ እንደተናዘዝኩ ተናዘዢልኝ.... ይቅር ተባብለን  አብረን ባንቀጥልም ጥያቄዎቼን እንድትመልሽልኝ እፈልጋለሁ... የምናሴ አባት ማነው። ሩት አንቺም እኮ ድብቅ ነሽ ከኔ የደበቅሺው ብዙ ሚስጥር አለሽ" ዝምምምም "እንቁን አሟት ነበር ልያት" ከመኝታ ቤታችን ወጥቼ ወደሷ ስሄድ "እወቂ ለዚህ ሁሉ ነገር ያንቺም እጅ አለበት....ወይኔ አምላኬ ምንድነው ያደረኩት" ሰማሁት ግን ባልሰማ ወደ ልጄ ክፍል ሄድኩ በሩን ከፈት አድርጌ ሳያት ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ተኝታለች ወደ ውስጥ ገባሁና ቀስ አድርጌ ዘጋሁት። የአልጋዋ ጫፍ ላይ ቁጭ ብዬ የትኛችውን እንቁዬን አየኋት ግንባሯ ላይ ቸፈፍ ያለ ላብ አለ። ፎጣ አንስቼ ስጠርግላት እጄን ለቀም አድርጋ ወረወረችውና "እባክህ አትንካኝ እባክህ" ከእንቅልፏ ደንግጣ ነቃች "ምንድነው ልጄ ማንን ነው አትንካኝ የምትይው" "አይይ እእ....እ ይቀጥላል.... ┏━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┓ 🥀 @MENTA_LIBOCHE🥀 🥀 @MENTA_LIBOCHE🥀 🥀 @MENTA_LIBOCHE🥀 ┗━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━ ቻናላችንንይቀላቀሉ ከወደዳችሁት LIKE ❤️
Show all...
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘 ክፍል 2⃣1⃣ እናቴ ጥላኝ ሄደች እንደሚሰበር እንቁላል የምትጠነቀቅልኝ እናቴ እንደ አይኗ ብሌን የምትጠብቀኝ እናቴ ለኔ እንደኖረች ተምሬ ደርሸላት ትንሽ እንዳሳረፍኳት ገና ውለታዋን ሳልመልስ በደንብ እፎይይይ ብላ መኖር ሳትጀምር ሞት ነጠቀኝ። አመመኝ.... እጅግ በጣም አመመኝ። ከኔ የበለጠ እንቁን ማፅናናት ከባድ ነበር። እማዬ ሁሉ ነገሯ ነበረች። ለአንድ ቀን መዓድ የተጋራሀውን ሰው እንኳን በሞት ማጣት ከባድ ነው። እማ ከዛም በላይ አለሜ ነበረች፤ የራሴን ውብ አለም ፈጥራ ከፍራቻዬ የሸሸገችኝ፣ ጓደኛዬ፣ ስታመም ሀኪሜ፣ ስጨነቅ አማካሪዬ፣ ተቆጪ መካሪዬ፣ ዘጠኝ ወር በሆዷ ተሸክማ ሶስት አመት ጡቷን አጥብታ ያሳደገችኝ እናቴ ለሰው አንድ ለኔ ግን ብዙዬ ነበረች። ይገርማል አይደል ነው ከመባል ነበር ወደመባል የምንሸጋገርባት የሽርፍራፊ ሰከንዶች ሞት.... አስፈላጊ ያልናቸውን እቃዎች ሰብስበን ወደኔ ቤት ካመጣን በኋላ ቤቱን አፅድተን ለአከራይዋ ቁልፉን አስረከብን። አከራይዋን ቻው ብለናቸው ልንወጣ ስንል እንቁ "ማሚ እዚሁ ነው መኖር የምፈልገው እማዬን ትቼ የትም አልሄድም" እየተንሰቀሰቀች የተቆለፈው በር ስር ሄዳ ቁጭ አለች። አጠገቧ ሄጄ ቁጭ አልኩና አቀፍኳት.... ለረጅም ደቂቃ አብረን ተላቀስን። አከራይዋ ወ/ሮ ትርንጎ ከቤት ሲወጡ ተቃቅፈን ስንላቀስ አዩንና  ወደኛ መጡ " ምነው ልጆቼ ተነጋግረን አውርተን... ተው እንጂ እኔንም ሆድ አታስብሱኝ እናታችሁንም አትረብሿት ነብሷ በሰላም ትረፍ። በእናንተ እንደዚህ መሆን ደስተኛ የምትሆን ይመስላችኋል በሉ ልጆቼ ኑ ተነሱ" እጇችንን ይዘው ካነሱን በኋላ እንባችንን ጠራረጉልንና መክረውንና አፅናንተውን በር ድረስ ሸኙን። "በቃ ቻው እማማ ትርንጎ እየመጣን እንጠይቆታለን ብዬ ቃል አልገባልዎትም ግን ቤተ ክርስቲያንም ቢሆን መገናኘታችን አይቀርም። የምሰራበትንም ሆስፒታል ያውቁታል አይደል ለጤናዎትም ብቅ ማለት ይችላሉ። ቤትም ይምጡ አይጥፉ። በሉ ቻው... ከዚህ በላይ አይቸገሩ" ተሳስመን መኪና ውስጥ ገባንና ወደ ቤት ሄድን። ።።።። ።።።።። ።።።።። ።።።።።። ።።።። እንቁ ሙሉ ለሙሉ እኛ ቤት መኖር ከጀመረች በኋላ የዮኒ ፀባይ ተስተካክሏል። ቶሎ ወደ ቤት ይገባል ትምህርት ቤት ያደርሳታል እልፎ አልፎ አብረው ይዝናናሉ። እኔ ብዙውን ጊዜ በስራ ስለማሳልፍ ባልቀላቀላቸውም የልጄ የአባትነት ክፍተት ሲሞላ በማየቴ ደስተኛ ነበርኩ። ሁልጊዜ አባቴ ማነው የሚለው ጥያቄዋ ሊያሳብደኝ ነበር የሚደርሰው.... ለጊዜውም ቢሆን ጥያቄዋን ትታ ዮኒን እንደ አባት ስታየው ማየቴ እፎይታን ሰጥቶኛል። ትልቅ ልጅ እየሆነች ነው። አንዳንዴ እማዬ እየሳቀች "መልኳ እኮ አንቺን አስደግፈው የሳሏት ነው የምትመስለው። አንቺም ልጅ ሆነሽ እንደሷ እኮ ነው መልክሽ ካላመንሽ  ያንን አልበም አምጪና ፎቶሽን እና እሷን አስተያይ" ትለኝ ነበር። ልጅ ሆና ብቻ ሳይሆን እያደገች ስትመጣም የኔኑ መልክ ያዘች። ከዮኒጋ አልፎ አልፎ ጭቅጭቅ እንደ ቅመም ጣል ጣል ያለበት ራት በልተን እንገባለን። ቢሆንም ግን ከበፊቱ ጋር ሲነፃፀር ተመስገን ያስብላል። ትንሽም ቢሆን ቤቴ ትዳሬ ማለት ጀምሯል ያ ለኔ ትልቅ ነገር ነበር። ።።።።  ።።።።።   ።።።።።።   ።።።።።። ቢኒ ከሄደ ጀምሮ ሶስቴ ነው የደወለልኝ። አንደኛው ከእናቴ ሞት በኋላ እግዜር ያፅናሽ ለማለት ነበር። ከዛ በፊት ሁለቴ ደውሎ ቢያውቅም ያን ያክል ግን አላወራንም ነበር ሌላው ቢቀር ስለመጫረሻው ቀናችን ደፍሮ የጠየቀ እንኳን አልነበረም። ቻው ከማለቱ በፊት " ግን ደስተኛ ነሽ" ይለኛል። እርግጠኝነት በጎደለውና በቀዘቀዘ መንፈስ "አዎ" አለዋለሁ ሁለቴም ሳወራው ዮኒ ሰምቶኝ የጥላችን ምክንያት ሆኖ ነበር። ቢኒ የሚባል ስም ቤት ውስጥ በተለይ ከኔ አፍ መስማት አይፈልግም። ።።።። ።።።።  ።።።። ።።።።  ።።።። ከቀናት በአንዱ አዳር ስራ ገብቼ ደክሞኝ ቤት ስደርስ ከእንቁ መኝታ ቤት የለቅሶ ድምፅ የሰማሁ መሰለኝና ደንግጬ ሄጄ በሯን ስከፍት አልጋ ላይ ኩርምት ብላ ተኝታ ታለቅሳለች። "እንቁዬ ምንድነው የኔ ልጅ ምን ሆንሽ" ድንግጥ ብላ ተነሳችና እንባዋን እየጠራረገች "ምንም አልሆንኩም ማሚ" "ምንድነው ፊትሽ ገርጥቷል እኮ አይንሽም አብጧል አሞሻል እንዴ" እጄን ግንባሯ ላይ አድርጌ ትኩሳቷን ለካሁት ግላለች "አይ ትንሽ ሆዴን አሞኝ ነው። ማለቴ ፔሬድ ስለመጣብኝ ቁርጠቱን አልቻልኩትም" ፔሬድ ሲመጣ እንደሚያማት ባውቅም እንደዚ በህመም ስታለቅስ አይቻት አላውቅም ነበር። ማስታገሻ ኪኒን እንድትውጥ ካደረኳት በኋላ ተመልሳ ጥቅልል ብላ ተኛች። መኝታ ቤት ገብቼ ልብሴን ቀይሬ ልተኛ ስል ስልኬ ላይ መልዕክት ገባልኝ። "ባልሽን አሳርፊው ልንማር እንጂ ልንሸረሙጥ አልመጣንም ቴሌግራም ላይ ሙሉ መረጃውን ታገኛለሽ" ይላል። እየተጠራጠርኩ ቴሌግራም ከፈትኩ ፊት ለፊት የመጣልኝን መልዕክት ስከፍተው ፎቶ እና አጭር ቪድዮ.....  ዮኒ ከሌላ ሴት ጋር.... ይቀጥላል.... ┏━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┓ 🥀 @MENTA_LIBOCHE🥀 🥀 @MENTA_LIBOCHE🥀 🥀 @MENTA_LIBOCHE🥀 ┗━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━ ቻናላችንንይቀላቀሉ ከወደዳችሁት ❤️
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.