cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ነገረ ሰውነት /Biruk Takele/

በመጀመሪያው ቃል ነበረ ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ

Show more
Advertising posts
213
Subscribers
No data24 hours
+17 days
+130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በዓተ ጾመ ነቢያት... ኅዳር ፲፭ ====+++===== በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል ÷ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው ኤፌ ፪ ፥ ፳ ጾም የነፍሱን ቁስል ታድናለች የሥጋን ፍላጎት ታስወግዳለች ቅዱሳን መላእክት ለእረኞች የአምላክን ሰው መሆን እንዳበሰሯቸው ሁሉ÷ እኛም በጾማችን ፍጻሜ የጌታን ልደት ስናከብር ሀገራችንም ከእርሱ ጋ በጸጥታ ተወልዳ እንድናይና ቤተክርስቲያናችንም ከመከራ አርፋ እንድንዘምር ይርዳን ቸር የጾም ጊዜ ይሁንላችሁ ቡሩክ ዘብሔረ መቂዬ
Show all...
6👍 2
...ከታችኛው የቀጠለ...በዚህ አጋጣሚ በእነሱ ቤት የተራቀቁ በእውቀት የመጠቁ የሚመስላቸው ለአቅመ ምንፍቅና እንኳ ያልደረሱ ተረፈ ሉተራውያን ይህን የሐዋርያውን ቃል በመምዘዝ [ከሥጋና በደም ተካፈለ የምትለዋን] ጌታ ከማርያም ሥጋና ደም እንጂ ነፍስን አልነሳም ይላሉ። "አይ ሞኜ ጴንጤ" የሕፃኑን ነፍስ የሚፈልጉት ሞተዋልና ተነሳ እናቱንና ሕፃኑን ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ" ማቴ ፪ ÷ ፳ ሚለውን አታነብም። የሕፃኑን #ነፍስ ይላል እኮ ጎበዝ ምን ሆነህ ነው!? ሲጀመር ነፍስን ከእመቤታችን ካልነሳ ሰው አልዳነም ማለትህ እንደሆነ አታውቅም? ሞኜ ነህ ባክህ። ሞኜ። ማስተዋልን ይስጥልን። ቆይ እኔ ምል ይህን ለምን ረሳችሁት ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንኃለው የሚለውን የቀለሜንጦስን መጽሐፍ ትምህርት? ውይ ለካ እናንተ መጽሐፍ ከ፷፮ ውጭ እንደሌለ ነው ምታውቁት። መጽሐፍ ቅዱስ ግን የመጽሐፍ ብዛት ፷፮ ብቻ ነው አይልም። ኸረ በቃኝ። ዋጋ ለሌለው ነገር መደናቆር አግባብ አይደለም። እንዲህ ሲባል የኦርቶዶክሳዊው የመዳን ትህርት የገባቸው, የፕሮው አሰላለፍ የተረዳቸው, ሳያውቁት መንገደኛ ብሎም በቤተሰብ ተመርተው የፐረሰቱ ? አይረዳቸውም ማለት ግን አይደለም። ብዙ አሉና ቤተክርስቲያን ምታስተምረው ምንም ነቅ እንደሌለው የሚያምኑ። ነፍስና ልባቸው ከኛ ጋር የሆነ። ጠቅለልው እንዲመጡልን በእርሷም ሕይወት እንዲኖሩልን ፈጣሪ ይርዳልን። ብቻ ሁሉንም መንፈስ ቅዱስ ዐይነ ልቡናቸውን ይከፈትልን። ለኛም መጽናቱን ማፍራቱንና ክርስትናን በሕይወት ለመኖር እርሱ ይርዳን። በመጨረሻ በዚህ ነገር ተሰናበትን። የገባው ብቻ ይህን ያስተውላል ዲያቆን ሔኖክ ኃይሌ በአንድ ትምህርቱ ላይ መልአኩ መጥቶ አምላክን ትወልጃለሽ ብሎ ሲያበስራት እንቢ ብትለውስ? ምን እንሆን ነበር? ብሎ ይጠይቅና መልሱንም እመቤታችን በነገረ ድኅነት ያላትን ሱታፌ በግሩም ሁኤታ ያስቀምጣል....? #ይኩነኒ_የሚለው_የመታዘዝ_መልስ በዚህ ጥያቄና መልስ ግን ፀረ-ማርያም ወንድሜ አስገድዶ ያደርባት ነበር እንደማትል ተስፋ አደርጋለው... እግዚአብሔር የነጻነት አምላክ እንጂ በግድ የሚገዛ አምላክ ስላይደለ ~ አብርሂ አብርሂ ናዝሬት ሀገሩ ንጉሥኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መፆሩ ጣዖታተ ግብፅ ኩሎ ቀጥቂጦ በበትሩ ይጉየዩ ወይትኀፈሩ ሠራዊተ ሄሮድስ ፀሩ ዘበላዕሌሁ እኩየ መከሩ ትርጉም በእሱ ላይ ክፉ የመከሩ የሄሮድስ ሰራዊት ሁሉ አፍረው ይሸሹ ዘንድ የግብፅን ጣዖታት በሥልጣኑ አጥፍቶ ከአዘለችው ከእናቱ ከማርያም ጋር ንጉሥሽ ስለደረሰ ሀገሩ ናዝሬት አብሪ። [ሰቆቃወ ድንግል አብርሂ አብርሂ] ~ ወተመይጠት ማርያም ሀገረ ፳ኤል አቡሃ ነቢራ በግብፅ ፵ ወ፪ተ አውራኀ እንዘይሰግዳ ላቲ አዋልደ ጢሮስ በአምኅ እምእዜሰ ነገፍኩ ላሀ ለእምየ በእትወታ ረኪብየ ፍሥሓ ትርጉም ማርያም ፵፪ ወር [፫ ዓመት ከ፮ ወር] ቆይታ የጢሮስ ደናግል በምስጋና እየሰገዱላት ወደ አባቷ ሀገር ወደ እስራኤል ተመለሰች ከዛሬ ጀምሮ በእናቴ መመለስ ደስታን አግኝቼ ልቅሶን ተውኩ። [ማሕሌተ ጽጌ ወተመይጠት ማርያም] ለአብ ምስጋና ይገባል, ለወልድ ምስጋና ይገባል? ለመንፈስቅዱስም ምስጋና ይገባል አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያምም ምስጋና ይገባል መልዕክት:- መቂ በቆርኬ አዲ እግዚአብሔር አብ እና ቅድስት ቁስቋም ማርያም ቤተክርስቲያን ንግስ ተሳተፉ ከበዓሉ ረድኤት በረከት ያሳትፈን ከስደቷ እንደተመለሰች ቤተክርስቲያንንም ከስደት ይመልስልን አሜን ቸር ሁኑ ቡሩክ ዘብሔረ መቂዬ
Show all...
👏 3 1
#ገሊላ_እትዊ ® "ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች ልጇም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ። ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀንም(ሦስት ዓመት ከመንፈቅ) በዚያ እንዲመግቧት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሀ ሸሸች" ራዕ ፲፪ ÷ ፬- ፯ ሴቱቱ የተባለች ንግስተ ሰማይ ወምድር የሆነች, ንጽይት ቅድስት ድንግል ማርያም እንደሆነች ጥርጥር እንደሌለው ጠላትም ይቀበለዋል። በፍጹም ካልሸመጠጠ በቀር። ማቴዎስም የእመቤታችንን ስደት "ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ "ማቴ ፪ ÷ ፲፫ በማለት ይጨምርልናል። ከዚህም ባሻገር ማቴዎስ ለመሰደዷ ምክንያት የነበረው መሞቱንና ከስደት መመለሷን ደግሞ ለጠባቂዋ ዮሴፍ መልአኩ በኅልም ተገልጦ እንደነገረውና ወደ እስራኤል እንደተመለሱ ማቴ ፪ ÷ ፳ አስቀምጦልናል። ይህንንም ምክንያት በማድረግ ቅድስት ቤተክርስቲያን ለእመቤታችን በዓመት ኅዳር ፮ ቀን መታሰቢያ በዓል ታደርጋለች። "የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው" ምሳ ፲ ÷ ፯ እንዲል መፍቀሬ ጥበብ ሰሎሞን። ባዘለህ ጀርባዋ, በታቀፈህ ክንዷ, በጠባኸው ጡትዋ ብለህ ማረን ራራልን ይቅርበለንም ብለን ልጇን እንማጸናለን ወላዲተ አምላክ ልጇን አዝላ የአሸዋውን ግለት, የውሃውን ጥማት የሽፍታን ማስደንገጥ ችላ ከእስራኤል ወደ በረሀ ግብፅ እንደወረደች ዮሐንስ በራዕይ መጽሐፉ እንዳኖረው ነው። እመቤታችን በዚህ የስደት ዓመት የኢትዮጵያን ምድር ዙራ, ዋልድባ ገዳምን እንዲህ ለሰማይ ለምድር ሚከብዱ ደጋግ መነኮሳት ይኖሩባት ዘንድ ካምላኳ ዘንድ ለምና አግኝታ, ይህ ብቻ አይደለም ሙሉ የኢትዮዽያን ምድር አስራት አድርጎ ካምላኳ ተችራ, በሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳምም ፻ ቀናት ቆይታ በመጨረሻም ለእግዚአብሔር ምርጥ ዕቃ ለመሆን የመረጡ ውሉደ ኢትዮጵያውያንም ስጦታ ሰጥተዋት, ስጦታዋንም በግመል አስጭና ወደ ግብፅ ደብረ ቁስቋም የገባችበት ከድካሟ ያረፈችበት ቀን ናት። ተዓምረ ማርያም ተመልከት ለምን ግን( ክስቶስ)? ኢየሱስ አምላክ ሲሆን ተሰደደ? ለምንስ የስደቱን መዳረሻ ኢትዮጵያ እና ግብፅ አደረገ ያልን እንደሆነ, መምህራን ሲያስተምሩን ፩. የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ፪. ሰው መሆኑ ለማጠየቅ ፫. በግብፅ ጣኦት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ ፬. ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ "በፈጣን ደመና ወደ ግብጽ እንደሚወርድ( መጻፍ )?ስለሚናገር" ኢሳ ፲፱ ÷ ፩ ዕን ፫ ÷ ፯ ፭ . ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት ፮. የግብፅና የኢትዮጵያን ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ ፯. ምሳሌውን ለመፈጸም, የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም ያዕቆብ, ኤርሚያስ ግብፅ ተሰደዋልና። ብለው እንዳስተማሩን #ስርዋጽ ===£=== ቤተሰቦች እዚህ ምድር ላይ ግን እንደ ፕሮቴስታንት ውለታ ቢስ አለ? ለእመቤታችን ያላቸውን እሳቤ ስናጠናው የበሉበትን ወጭት የመስበር ያህል ስለሚያሳይ። እርሷም ሰው ናት, ምን ታካብዳላችሁ, ተሰቅሎ ያዳነን ክርስቶስ ነው ምናምን በሚሉ ደንቋራ ንግግሮችን የሰርክ ወሬአቸው አይደል? እንደው በማርያም ሌላው ቢቀር አምላክን ለመውለድ ራስን በንጽሕናና በቅድስና ጠብቆ ማኖር, የዓለም መድኃኒት እንዲያድርባት ራስን ማዘጋጅት በራሱ ትልቅ ውለታ አይደለምን? መታዘዙስ ብትሉ" ተመልከት አሁን ይሄን ሰላምታ...ተራ ምድራዊ ሰው አይደለም ያለ...."አንቺ ከዓለም ሴቶች ሁሉ ተለይተሽ ተመርጠሽ #ቡርክት ነሽ" ሉቃ ፳፰ ÷ ፴፫። መልአኩ እኮ ነው ያላት እናንተ! በጎስቋላ ሰውነት እንደ እንቁ ማብለጭለጭ! በኃጢአተኞች መንደር ጻድቅ ሆኖ መገለጥ! በተጠላ ዓለም ምስጉን ሆኖ እንደ መገኘት! ምን ልዕልና አለና ወዳጆቼ? ለኛስ አንቺ ሽልማታችን ነሽ። ስምሽን ጠርተን ጠርተን ማንጠግብሽ። #ማርያም በነገራችን ላይ መምህራን እንዳስተማሩን ሰው መንፈሰ እግዚአብሔር ካልረዳው በቀር እመቤታችንን ማመስገን አይችልም። ኤልሳቤጥ ድምጽዋን አሰምታ ቡርክት ነሽ ያስባላት መንፈስ ቅዱስ ነውና። ለመረዳት እስኪ ይህን የሉቃስን መጽሐፍ እንመልከት... "ማርያምም በዚያ ወራት ተነሥታ ወደ ተራራማው አገር ወደ ይሁዳ ከተማ ፈጥና ወጣች። ወደ ዘካርያስም ቤት ገብታ ኤልሳቤጥን ተሳለመቻት። ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማሕፀኗ ውስጥ ዘለለ። በኤልሳቤጥም #መንፈስ ቅዱስ ሞላባት። በታላቅ ድምጽም ጮኻ እንዲህ አለች። አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ" ሉቃ ፩ ፴፱ - ፵፫ ይሄው ጮኻ እንድታመሰግን ያደረጋት መንፈስ ቅዱስ ከሞላበት በኋላ አይደለምን!? እንክትነዋ? መንፈስ ቅዱስ ማርያም ማርያም ያስብላል ከመጽሐፍ አሳብ በተቃራኒው የቆሙ ጸረ ማርያሞች ግን ዮሐንስ በራዕይው ፲፪ ÷ ፲፯ እንዳለ "ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቆጥቶ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ በባሕርም አሸዋ ላይ ቆመ" እንዳለ እርሷን ያሳነሱ መስሎአቸው የስድብ አፋቸውን ይከፍታሉ። ልብ ይስጥልን። ወገኖቼ ግን እኮ አይፈረድባቸውም ምክንያቱም እነርሱ ጋ መንፈስ ቅዱስ የለማ! ሳር የሚያስግጥ, ፌንት የሚያስበላ, ዘይት የሚያስገዛና የሚያንከባል መንፈስ ነዋ ያለው። የጥንተ ጠላታችን የጋርዳኤል መንፈስ። አሞራና ዶሮን ያለመለየት ችግር። ምስኪናን ታሳዝኑናላችሁ ለምን ክርስቶስ ለናተም ስለሞተ ያም ብቻ አይደለም ስለሚወዳችሁም ጭምር። የእውነት እናቱን ጠልታችሁ እርሱን እንወዳለን ማለት ልክ አይደላም። በሽንገላ ካልሆነ በቀር። "በድፍረትና ብትዕቢት በመናቅም በጻድቅ ላይ ሚነገሩ የሽንገላ ከንፈሮች ድዳ ይሁኑ" መዝ ፴ ÷ ፲፰ እንዳይሆንባችሁ ነቄ ወጥንቃቄ ያስፈልጋል። አንድ ሐቅ በእውነት እውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጆች ይወዷችኋል ስህተታችሁን ግን አጥብቀን እንጠላለን። ነገር ግን ከመንጋው መነጠላችሁ ከሕይወት መራቃችሁ ያሳዝነናል። በዚህም በቅዳሴ ጸሎት በእንተ ቅድሳት ላይ ስለናንተም እንማልዳለን። አይ ቤተክርስቲያን! በእውነት ፍቅር እኮ ነሽ። ስለ ሁሉ የምትለምኝ, ለሚገልሽ ምትማልጅ! አንዳዴ ይህን ሳስብ በእውነት ያለ ሀሰት ውስጤ በሆነ ነገር ሲወረር ይሰማኛል። ፍጥረትን ሁሉ መውደድ! ምንድ ነው የዚህን ያህል ፍቅር ብዬ ስጠይቅ ለካ ልቧ ክርስቶስ ስለሆነ ነው። "እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን" እንዲል ጳውሎስ ፩ ቆሮ ፪ ÷ ፲፮። በሉ በሉ ወደ ነገራችን። የኔ ነገር በቃ መንገድ ካገኘ እኮ.... ሌላው ደግሞ የጴንጤ ትልቁ ችግሩ ማምታት ነው። ማደናገር። ለምሳሌ እንዲህ ይላሉ ክርስቶስ ያዳነን በደሙ ነው የሚል የሁልጊዜ ንግርታቸው...አዎ ዓለም የዳነው የአምላክ ሥጋ መቆረስ ደመሙም መፍሰስ ነው, ግን ደሙን የነሳው ከማን ነው ነው ጥያቁው! ከሰማይ ነው ይዞት የመጣው? እንደዛ እንዳይደለማ መጽሐፍ እንዲህ ይልም? የለ.... "የአብርሃምን ዘር ይዟል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም" ዕብ ፪ ÷ ፲፮ "የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶ የትውልድ መጽሐፍ" ማቴ ፩ ÷ ፩ "ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በሞገስም በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያድግ ነበር" ሉቃ ፪ ÷ ፶፪ "የበኩር ልጇን ወለደችው በመጠቅለያም ጠቀለለችው" ሉቃ ፪ ÷ ፯ "በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ" ዕብ ፪ ÷ ፲፬ እና ሌሎችም የመጽሐፍ ቃል ክርስቶስ መባሉ የነሳው ሥጋና ነፍስ ከሰው እንደሆነ ከሰውም ከተመረጠች ንጽይት ድንግል እንደሆነ ልብ ይለዋል።ሰውም አምላክም ነው ኢየሱስ ክርስቶስ። በተዋሕዶ ከበረ እንዲል ቄርሎስ በዚ
Show all...
👍 1 1
#ጢሞቴዎስ_ሆይ_በውሸት_እውቀት_ከተባለ_ለዓለም_ከሚመች_ከከንቱ_መለፍለፍና_መከራከር_እየራቅህ_÷_የተሰጠህን_አደራ_ጠብቅ_÷_ይህ_እውቀት_አለን_ብለው_አንዳንዶች_ስለ_እምነት_ስተዋልና ጢሞ ፮ ÷ ፳፩ ለሐዋርያ ጳውሎስ ባደረበት እያደሩ ከዋለበትም እየዋሉ ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት ምን መምሰል እንደሚገባው, የዓለሙ መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ማን እንደሆነ, ብሎም አንድ ጥሙቅ ኦርቶዶክሳዊ በውርዝውና ዕድሜው በቤተክርስቲያን እንዴት መኖር እንዳለበት ልምድ የሚቀስሙ የሕይወት ትምህርት የሚማሩ በአገልግሎትም የሚራዱት ደቀ መዛሙርት ነበሩት። ለምሳሌ:- ስልዋኖስ, ፊልሞና, ቄርቂስ, ቲቶ, ማርቆስ, ቲኪቆን, ሌሎችም። ከኒህም መሓል ለዛሬ ነገራችን ለወሰድነው የመጽሐፍ ኃይለ ቃል መጠሪያነት የተሰጠው ጢሞቴዎስ አንዱ ነው። ይህ ንኡድ አባት ከዲቁና እስከ ላይኛው የቤተክርስቲያናችን ማዕረገ ክህነትተ ጵጵስና ድረስ የተቀበለ, የልጅ አዋቂ የነበረ, በአገልግሎትና በሕይወት እርሱን የሚመስለው ቅዱስ አባት ነው። "አንተ ግን ትምህርቴንና አካሄዴን, አሳቤንም, እምነቴንም, ትዕግስቴንም, ፍቅሬንም, መጽናቴንም, ስደቴንም, መከራዬንም, ተከተልህ" ፪ ጢሞ ፫ ÷ ፲ እንዳለው ነው። ፈጽሞ አባታችንን የመሰለ አገልግሎቱን ፈጽሞ ከድካሙ ያረፈ ነው። ባለ መቶ ያፈራ። እንደዚህ ነው ክርስትና። አረስከ መጨረሻው መጓዝ። እስከ ጥግ ድረስ። እስከ ሞት። ልክ እንዲህ ብፁእ አባት። በረከቱ ሁላችንንም ትርዳን እንደዚሁ ሁሉ አስተምሮ, ጠብቆ አሳድጎ, ሁሉ ነገር አድርጎ መጽናት ያቃታቸው, ለፍቶባቸው የመንፈስ ፍሬ ማፍራት የተሳናቸው, እንደ አብዛኞቻችን የክርስትናና የአገልግሎትን ጽንሰ ሀሳቡ ያልተረዳቸው, ባጭት ቃል ያልቆረጠ ልብን ገንዘብ ያደረጉ ተከታዮችም ነበሩት። [አንድም ክርስትና ቆርጦና ወዶ ፈቅዶ ሁሉን በመተው ክርስቶስን መከተል ስለሆነ]። ይህ ከሆነባቸው መሀል #ዴማስ አንዱ ነው። ይህ ሰው ዓለም ማርካው አገልግሎቱን ሳይፈጥም ከዓለም መኮብለል ሲገባው ወደ ዓለም የኮበለለ አሳዛኝ ተማሪው ነበር። "ዴማስ የአሁኑን ዓለም ወዶ ትቶኛልና ወደ ተሰሎንቄ ሄዶአል" ፪ ጢሞ ፬ ÷ ፲ እንዲል። ይህ ተማሪ "እስከ ሞት የታመንህ ሁን እኔም የሕይወትን አክሊል እሰጥሀለው" ራዕ ፪ ÷ ፲ የሚለው የእግዚአብሔር ቃል ያልሰረጸው የከሰረ ተማሪው ነበር። ከሕይወት የተለየ። ብርሃን ጳውሎስ አጠገቡ ኖሮሎት በብርሃን መመላለስ የጠፋበት። ብዙ ደክሞ, ተጉዞ, መጨረስ አልሆን ያለው ሚያሳዝን ተማሪ። እግዚአብሔር በመንፈስ ጀምሮ በሥጋ ከመጨረስ ይጠብቀን ኹለተኛው ምሳሌ ምናደርገው #እስክንድሮስ ነው። ይህ ሰው ደግሞ ከላይኛው ይለያል። ተምሮ አምኖ ነገር ግን ወደ ቀደመ ግብሩ የተመለሰ, የውሻ ጠባይ የነበረው ሰው ነው።[ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል እንዲል መጽሐፍ]። እንደታወቀ ሐዋርያው [ጳውሎስ] ሲያስተምር በዘመኑ ብዙ ተቃዋሚዎች እንደነበሩበት ይታወቃል። ከጠንቋዩ በርያሱስ ጀምሮ እስከ አላውያን ነገሥታት ድረስ። ሐዋ ፲፫ ÷ ፮ - ፲፪ , ሐዋ ፲፯ ÷ ፲፱, ሐዋ ፭ ÷ ፳፰ ተመልከት። በዘመኑ ከአይሁድ መናፍቃን ከፈላስፎችም ቀኑን ሙሉ ክርክር ያደርግ ነበር። "ሁል ጊዜ ሚያሳስበኝ የአብያተ ክርስቲያናት ጉዳይ ነው" ፪ ቆሮ ፲፩ ÷፳፰ እንዳለ ራሱ ታድያ በዚህ ሁሉ ጳውሎስ ለሁሉም እንደአመጣጡ ይመክር ያስተምር ነበር። በዚህም አሳምኖ ያጠመቃቸውን እርሱ ለአገልግሎት ወደ ሌላ ሀገር ጉዞ ሲያደርግ ምእመናንን ሚያጸኑለት, ቃሉን ሚመመግቡለትና አንዳድ የክህነትንም ሥራ ሚፈጽሙለት ከላይ ያየናቸው ደቀመዛሙርትና ሌሎች ተራዳኢያን ናቸው። ከኒህ ተራዳእያን መሓል አንዱ የነበረ ነው እለስክንድሮስ። ነገር ግን ይህ ሰው ማልያውን ቀይሮ በተቃራኒው ጎራ ተሰልፎ, ምቹ ጊዜ ፈልጎ መምህሩን ጳውሎስ ከተቃዋሚዎች ጋር በማበር የተከራከረው ነበር። መከራከር ብቻ አይደለም እጅግ የከፋበት ሰው ነበር። እንደውም ስለ እርሱ ጳውሎስ የሚለው ሲጠፋው እግዚአብሔር እንደሥራው ይሰጠዋል ነበር ያለ። ፪ ጢሞ ፬ ÷ ፲፬ ከዚህም ሰው መራቅ እንደሚገባው ለእውነተኛ ልጁ ለዚህ አባት ይመክረዋል። አምኖ መካድ የሀሰት ተባባሪ ከመሆንና ወደ ተውነው ኃጢአት መመለስ እንዳይገባን ከዚህ ሰው እንረዳለን። የአስቸጋሪነቱ መጠን "እግዚአብሔር እንደሥራው ይመልስለታል" በሚለው ቃለ እግዚአብሔር ይታወቃል ለጸናው መንገዱን ለተከተለው ለዚህ ደቀ መዝሙር ግን በዚህና በሌሎችም ምሳሌ እየመሰለ ይመክረዋል። የጸናውን መመልከት እንዳለበትና በመንፈሳዊ ሕይወት መበርታት እንዳለበት በመልእክቱ ይቃኘዋል። ከውሸት እውቀት መለየት እንዳለበት። እውቀት ሁሉ ጤናኛ ስላይደለ። ወደ ሞትም የሚወስድ እውቀት ስላለ። ከማይረባ ንግግርም ራሱን ማራቅ እንዳለበትም ጭምር። አሁን የዚህ ዘመን የኛ ትውልድ ትልቁ ፈተናው ወሬ ነው። ቀኑን ሙሉ በሆነ ሥፍራ ተጎልቶ መለፍለፍ። አንዳዴም ስለ ማያቁት ነገር እያነሱ መቀባጠር። የባዶ ጀሪካን ጩኸት ችግር። የአጋንንት ወደ ሰው ልጅ ትልቁ መግቢያ ቀዳዳ ከንቱ መለፍለፍ እንደሆነ ያለመረዳት ዕዳ። "ከንግግርህ የተነሳ ትኮነናለህ" ማቴ ፲፪ ÷ ፴፯ እንዳለ ጌታ። መጽደቂያህም ሊሆን ይችላል። ንግግርህ ከንቱ ኬ ካልሆነ። አብዛኞቻችን ኦርቶዶክሳውያን በዚህ አደገኛ ችግር ተውጠናል። እግዚአብሔር በቸርነቱ ከዚህ አዘቅጥ ያውጣን በተጨማሪ ከክርክርም መራቅ እንደሚገባው ይጽፍለትም ነበር። የሥጋ ሥራ ነውና። የሥጋ ሥራ የተገለጠ ነው እርሱም ሟርት, ጥል , #ክርክር....እንዲል ራሱ በገላትያ መልእክቱ ፭ ÷ ፳ ከእንደዚህ ዓይነቱ ነገር መራቅ እንደሚገባው ይመክረዋል። እኛም በዚህ ቀሳፊ በሽታ ወድቀናል። ስለ ሟንሟገተው ነገር የለም። ስለ ኳስ እንሟገታለን። ስለ ፖለቲካ እንፋጫለን። ስለ ብዙ ብዙ ጉዳይ። በጣም ደግሞ ከሚያስገርመኝ ባለቀና በተቋጨ ወይም ለኛ ባልተገባ ስለ ሃይማኖት ነገር እንከራከራለን, እንበሻሸቃለን። በእውነት እግዚአብሔር ከዚህ አዙሪት ያውጣን። የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እውቀት ያስታብያል, ሃይማኖትንም ሊያስት ይችላልና ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ሲጀመርም አናውቅም። ሰይጣን እንዳወቀን አስመስሎ በሕሊናችን የሀሰት መስል ሲፈጥርብን እንጂ። በዚህ በዘመናችን ያሉ አንድ ሊቅ ምናሉ "በዚህ ዘመን ሊቅም መናፍቅም የለም" ነበር ያሉ። እውነት ነው መናፍቁም ጥንት ከተወገዙት በኩረ መናፍቃን ምን የተለየ ምንፍቅና ይዞ መጣና? ምንም። ሊቁም ከእነ ዮሐንስ አፈወርቅ, ከእነ ቄርሎስ, ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሚተካከል አይደለም ሚጠጋስ እውቀት መች ይዞ ተከሰተና? ምንም እንኳ የእነርሱ የመንፈስ ፍሬ የሆኑ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ቢኖሩንም። እውቀታቸው ከኑሮአቸው የተስማማላቸው። "ፈጽሞ የተማረ ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ ይሆናል" እንደለ ጌታ። የነርሱ ፍሬዎች እልፍ አሉን። ሊቃውንትን የሰጠን እግዚአብሔር ይመስገን እናም የልኡል ልጆች ከክርክር, ከመለፍለፍ, ከዋል ፈሰስ ማንነት, ከትውዝፍትና ከእኩያት ተላቀን ኦርቶዶክሳዊ ሕይወትን ገንዘብ ማድረግ አለብን። ይህም ነገርህን ሁሉ በልክ አድርግ እንዳለው ለዚሁ ሐዋርያ ነገራችን በልክና በአግባብ, በሥርዓተ ቤተክርስቲያን በመወሰን መሆን እናድርግ። በትንሳኤ ዘጉባ ለክብር ለመብቃት ላለማፈርም። ከዚህ በተጨማሪ በክርስቲያናዊ ኑሮ ለመጓዝ መልእክቱን ሙሉውን አንብቡ ቸር ሁኑ ቡሩክ ዘብሔረ መቂዬ
Show all...
👍 3
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ይህችዋ ቅመምዋ
Show all...
👍 1
#ነገረ_መጽሐፍ + ጊዜውን በውል ባላስታውሰውም ብራና የሚል የራድዮ መርሐ ግብር አልፎ አልፎ አደምጥ ነበር። [Fm adis 97.1] ሸጋ ነገር ያሻግሩ ነበር አጋፋሪዎቹ። መርሃቸው ራሱ አንባቢ ትውልድን መፍጠር ላይ ያነጣጠረ ነበር። ለአእምሮ የሚመች ዝግጅት። ኢትዮጵያዊ ለዛ የነበረው, ኦርቶዶክሳዊ ትውፊትን ከሩሩሩሩሩሩ....ቅም ቢሆን ሚያሳይ። አዝናንቶ ሚያታርፍም። ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል የምትል የአየር ሰዓት~ ምናልባት በዚህ አጋጣሚ ማንበብ ብቻውን ሙሉ ሰው ያደርጋል የሚል እሳቤ አብዛኞቻችን ይኖረናል ብዬ አላስብም። ምክንያቱም አንደኛ ሰው ሚያነበውን መምረጥና መለየት ይኖርበታል:... ማነበው መጽሐፍ ወደ ሕይወት ያቀርበኛል ወይስ ወደ ሞት ያደርሰኛል ወይ የሚለው ነገር መታወቅ አለበት። ለምን አንዳድ አንባቢ በወረቀት የተሰነደ ሁሉ በሆነ አጋጣሚ ሲያነብ ሁሉን ለመኖር ሲኳትን ይታያል። በተለይ በስነ_ልቦና ላይና በፍልስፍና ጉዳዮች ዙሪያ ሚያጠነጥኑ መጽሐፍትን ሲያገኝ። ስህተት ነው። #ማይሞከር። የተጣፈ ሁሉ ጤነኛ ነው ማለት ጤነኝነት አይደለም። ስለዚህ ጉዳይ ጳውሎስ ሐዋርያዊ በታላቁ መጽሐፍ በመጽሐፍ ቅዱስ ስለ መጽሐፍት ለደቀ መዝሙሩ ለጢሞቴዎስ እንዲህ ይለዋል "ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጽሐፍትን አውቀሀል" ፪ ጢሞ ፫ ÷ ፲፭ ። ስለዚህ ከዚህ ምንባብ ምንረዳው በተቃራኒው አምላክን የማያሳውቁ ብሎም ጥበብን ሳይሆን ድንቁርናን የሚያመጡ ርኩሳት መጽሐፍት እንዳሉ ነው ሲቀጥል ሰው ሙሉ የሚሆነው በእግዚአብሔር እንጂ በንባብ ብቻ አይደለም። "ፊደልማ ይገድላል መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል" እንዲል ዐለት ጴጥሮስ....ትዝ ይላችኋል.. 'ያ' ከመወለዱ ጀምሮ ዓይነ ስውር የነበረው ሰው ሙሉ የሆነው ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአንድነት በሚመለክ በኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ? ዮሐ ፱ ÷ ፳፩። በዚህና በሌሎችም አመክንዮዎች ከተመለከትነው ማንበብ እንደ አንድ ጥበብ ማግኛ እና እውቀት መገብያ እንጂ መታበያ ሊያደርገን እንደማይገባ መገነዛዘብ ያስፈልጋል ከዚያ በተረፈ ማንበብን ሁሉም ሰው ገንዘብ ማድረግ አለበት። ሁሉን ማንበብ ጥሩ ነው ሁሉን መኖር ግን ጎጂ ነው። ማይዋሽ ሐቅ ማንበብ እጅጉን ወሳኝ የመኖሪያ ኮምፓስ ነው ልንለው እንችላለን። እንደውም የማያነብ ሰው በእውነቱ ከሕይወት ዛፍ እንደተከለከለ ዓይነት ሰው ነው። ሳያውቀው ለዛ ቢስ ይሆናል። ደስታው ከውስጥ አይመነጭም, ሀዘንተኛ ነው። ደስታን የተቀማ ማለት ነው። መጮህ እንጂ መናገር አያውቅም። ባጭር ቃል አለማወቁን እንኳ አያውቀውም። በእውነት ወዳጆቼ አንብቡ, ተመራመሩ, ጠይቁ አዎንታዊ ማንነትን ትገነባላችሁና። በመጨረሻ ይህን አልኩ #ማንበብ_ጎዶሎነትን_ያሳውቃል ወደ ነገሬ ልግባ....እጅግ ተወዳጅ ደራሲ ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ እሸቴ በእመጓ ክታባቸው ሰሜንን አስቃኝተውንና መልአኩ ኡራኤልን ብሎም ቅዱሱን ጽዋ በዓይናችን ስለውብን, በዝጎራቸው የእጽዋትን ድንቅ ነገር ብሎም ዓለም የጠላቻቸው ሳይሆን ዓለምን ጠልተው ቤተክርስቲያን የከተቱ ምሁራንን አስቃኝተውን, በመርበብት የጸላኢን ቀሽምነት የካቶሊክን መሰሪነት አሳውቀውን, በሰበዛቸው ገጠመኞቻቸውን አውገውተን ሳናበቃ በሚተራሊዮን ሀገራችን ታማ ሳያት አመመኝና ፍጹም ድኅነቷን ሳስብ ተጽናናው። እኔም ከዚህች ቅመም መጽሐፍ ከውስጥ በገጽ ፻፷፬ ላይ የኖረች የደራሲውን ብዕር አንብቡልኝማ...... [ሰሜን ተራራ በረዶ ከሚፈላበት ስፍራ እራፊ ጨርቅ የለበሱ እረኞችን አይቶ እሱ ራሱ ደራርቦ ለብሶ ብርዱን አልቻለውም ነበርና ሁኔታቸው ገርሞት:- "ልጆች አይበርዳችሁም?" ሲላቸው "ጋሼ ሀገር ይበርዳል እንዴ?" እውነትነት አለው። ሀገር ቀዝቃዛ ሊሆን ይችላል ግን አይበርድም ፤ ሀገር በረኃ ሊሆን ይችላል ግን አያቃጥልም ፤ ሀገር ጋራ ሸንተረር ሊሆን ይችላል ግን አያታክትም። በተለይ እኛ ኢትዮዽያውያን ሀገራችንን ምንም ትባል ምንም ለኛ ምቹ ናት እንወዳታለን] "ይዤ አላነሳም እጄን ከቀሚሷ እናት እኮ ናት ተስፋ አልቆርጥም በሷ" እንዳለ አዝማሪ እንዲያና እንዲህ እያሉ ውድዬን ይገልጧታል ወረድ ብለው ደግሞ እኚሁ ብርቱ ባለ ብዕር በገጽ ፪፻፷ ላይ ውዲቷን ትንሳዬዋን በምን ዓይነት ዐለት ላይ እንደምትቆም ምኞትም ትንቢትም በሚመስል ሲጦምሩልን [እማማ ኢትዮጵያ እንደገና ስትወለድ....የምትታመም ወይም የማትታመም ሆና ዳግም አልተወለደችም እንዳትታመም እንጂ..... የምትፈርስ ወይም የማትፈርስ ሆና ዳግም አልተወለደችም እንዳትፈርስ እንጂ....የምትሞት ወይም የማትሞት ሆና ዳግም አልተወለደችም እንዳትሞት እንጂ] እያሉ እኚህ ዋርካ ባለ ቀለም ሰው እማማን ይስሏታል። በእውነት ገዝታችሁ አንቡት ታተርፉበታላችሁ ጋሼ እናመሰግናለን ቤተሰቦች መጽሐፍትን በPDF በቅርብ እናዘጋጃለን መዘግየታችን በምክንያት ነው ቸር ንባብ ቡሩክ ዘብሔረ መቂዬ
Show all...
👍 3
#ምክረ_ሐዋርያ_ዻውሎስ + ፩.የሚሰጥ በልግስና ይስጥ ፪.የሚገዛ በትጋት ይግዛ ፫.የሚምር በደስታ ይማር ፬.#ፍቅራችሁ_ያለ_ግብዝነት_ይሁን ፭.ክፈፉውን ነገር ተጸየፉ ፮.ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ ፯.በወንድማማች መዋደድ እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ ፰.እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ ፱.ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ ፲.በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ ፲፩.ለጌታ ተገዙ ፲፪.በተስፋ ደስ ይበላችሁ ፲፫.#በመከራ_ታገሱ ፲፬.በጸሎት ጽኑ ፲፭.ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ ፲፮.እንግዶችን ለመቀበል ትጉ ፲፯.የሚያሳድዷችሁን መርቁ, መርቁ እንጂ አትርገሙ ፲፰.ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ ፲፱.ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ ፳.እርስ በእርሳችሁ በአንድ ሀሳብ ተስማሙ ፳፩.የትእቢትን ነገር አታስቡ, ነገር ግን የትህትናን ነገር ለመሥራት ትጉ ፳፪.ልባሞች የሆናችሁ አይመሰላችሁ ፳፫.ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ ፳፬.በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ ፳፭.#ቢቻላችሁስ_በእናንተ_በኩል_ከሰው_ሁሉ_ጋር_በሰላም_ኑሩ ፳፮.ተወዳጆች ሆይ ራሳችሁ አትበቀሉ, ለቁጣው ፈንታ ስጡ እንጂ "በቀል የእኔ ነው እኔ ብድራቱን እመልሳለው ይላል ጌታ" ተብሎ ተጽፎአልና ፳፯.ጠላትህ ግን ቢራብ አብላው, ቢጠማ አጠጣው ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና ፳፰.ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ (ከመጽሐፈ ኀበ ሰብአ ሮሜ የተገኘ) እስኪ የጠቆረውን ትንሽ እንመልከተው.....ማለት ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን የሚለውን ቁጥር....መምህራን ሲያስተምሩ ግብዝነት ማለት ነገሩን ወይም ድርጊቱን ሰው እንዲመለከትለት የሚሻ, አድርጎ ዋጋውን እጅ በእጅ የሚፈልግ ማለት ነው ይሉናል። ታድያ ይህ ግብዝ ፈቃድ መንፈሳዊ ዋጋን ያጣ የንታ ከንቱ ኬ እንደሚሉት ይሆናል ማለት ነው። ፍቅር ምንም እንኳ ትርጓሜ ትንታኔ ባያሻውም..... መጽሐፍ ፍቅር የሕግ ሁሉ ፍጻሜ, አንድም ፍቅር እግዚአብሔር ነው ይለዋል። በሌላው ከፈጣሪ ባሕሪ ምንጋራው ወይም ከእርሱ በጸጋ የሚሰጠን የሰውነት ውኃ ልክ ነው። ይህ ከፈጣሪ የተቸረ ደግ ስጦታ, ለማንም ከማንም ምንም ሳይጠብቁ የሚሰጡት ትክክለኛ ትእዛዝም ስጦታም ነው ልንለው እንችላለን። "በፍቅር ተመላለሱ" እንዲል ጳውሎስ ኤፌ ፭ ÷ ፪ ። እኔ እንዲ እንዳደረኩ እናተም እንዲሁ አድርጉ ማለቱም እኮ ፍቅሩን ነው። ፍቅሩን ደግሞ በፈቃዱ አይደል የሰጠን። ከኛ ምንም ሳይሻ። ዓለም እንደሚለው ፍቅር ሰጥቶ መቀበል ነው የሚል ትርጉም #ኧረ_ወዲያ ነው። ስለዚህ ከላይ እንዳየነው ፍቅር መስጠት ብቻ ነው ማለት ነው። ከማንም ሳንጠብቅ ሳንፈልግም እደው ዝም ብለን ብቻ የምንሰጠው ቸርነት። ፍቅርህ ደግነትህ እንዲያ ካልሆነ, ሰው እንዲያልህ ነጋሪት እንዲመታልህ መለከት እንዲነፋልህ ወይም ቸርነትን አድርገህ በተነሳኸው ሰልፊ ላይክ ፈልገህ ከፖሰትክ ዋጋህን እዛው ተቀብለሀል ነው ነገሩ። ከፈጣሪህ አንዳች አታገኝም ዓይነት። በቃ አለቀ ይሄው ነው!!!። በፍቅረ ቢጽም በፍቅረ እግዚአብሔርም ኹለተኛው የጠቆረው በመከራ ታገሱ የሚለው ነው....መከራ በነገራችን ላይ የክርስትና ዋናው መገለጫና "በሃይማኖት ስትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ" እንዲል ማኅቶተ ቤተ ክርስቲያን ጳውሎስ አንድ ክርስቲያን በሃሳበ እግዚአብሔር ውስጥ መኖር አለመኖሩን, በፍቅረ ክርስቶስ መኖር አለመኖሩን ቼክ የሚያደርገው ከክርስቶስ መከራ ሱታፌ ሲያደርግ ነው። እንደውም መጽሐፍ በሌላ ስፍራ ስለ ክርስትና ጉዞ ጋሬጣ ሚጀምረው ክርስትናን ለመኖር ሲነሳ, ሲያስብና ፍላጎት ሲያድርበት ነው ይለናል። "በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ #ሊኖሩ_የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ" ፪ ጢሞ ፫ ÷ ፲፪ ። ምንም እንኳን በራሱ ንዝህላልነት ክርስቲያን መከራ ሚደርስበት ሁኔታዎች ቢኖሩም። ይህንም ሲያስረዳ አለት የተባለ ሊቀ ሐዋርያት ጴጥሮስ "ኃጢአት አድርጋችሁ ብትታገሱ ምን ክብር አለው?" ፩ ጴጥ ፪ ÷ ፳ ይለናለናል። ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ሃሳብ እንደ መጽሐፍ ነገር እየኖሩ መከራን መቀበል ሽልማት እንዳለው በዛው የመጽሐፍ ክፍል "ነገር ግን መልካም አድርጋችሁ መከራን ስትቀበሉ ብትታገሱ ይህ ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ ምስጋና ይገባዋል" ይለናል። ስለዚህም ነው በመከራ ታገሱ መባሉ ሦስተኛወና የመጨረሻው በቁጥር ፳፭ ላይ ያለው ከማንም ጋር በሰላም ስለመኖር ነው ሚያትተው። ሰለ ዚህ ጉዳይ መናገር አሁን አሁን እየዘገነነ መጥቷል ማለት ይቻላል። ምላሳችን ሰላም ሰላም ይላል ነገር ግን ሰላምን አርቆ ሰቃይዋ እኛው እራሳችን ሆነናል። ምን ያህል አስፈላጊነትዋ ቢገባን እኮ ጎበዝ......! በርግጠኝነት ያልገባንማ ነገር አለ! ሳስበው እንደውም ተውኩት ብቻ ሰላምን ከፈለግን ይህን የሐዋርያውን ቃለ ሕይወት ተግባራዊ ማድረግ ግድ በግድ ነው። አንዱን ነጥሎ ብቻ አይደለም ሁሉንም ትእዛዘ እግዚአብሔርን በመፈጸም እንጂ። ሲጀመርስ ግን መች ተረዳን አሁን ያለንበትን ሁኔታ! ማለቴ የህመሙን መጠን ብንረዳው ለመፍትሔ እንቸኩል አልነበር!? ነፍሳችን ጨንቋታል መታወኳ መጠኑ በማይነገርለት ሁኔታ በብርቱ ታውካለች! እጅግ በኃይል። ነገር ግን መድኃኒቱ ይሄው ነው። በክርስቶስ ሕይወት መኖር። በመድኃኒቱ ላይ እንዳመጸ በሽተኛ እንዳንሆን አንተ እርዳን ዱያንን የምትፈውስ ባለ መድኃኒት ዻውሎስ, እንድን ዘንድ ከሕማማችን ፈውሰን ለምንልን ከቸሩ አምላካችን አሜን። ቸር ሁኑ ቡሩክ ዘብሔረ መቂዬ
Show all...
👍 4👎 1