cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Perfect😍😍😍

Fkrn emayak egzhabyern ayakm slezih enwaded enfaker rnsasam en****just hule feta

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
188
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
#አትፍረድ_2 በጣም የሚዋደድ ጓደኛሞች ነበሩ፡፡ አብረው ተምረው አብረው ተመርቀው አብረው ስራ ይዘው የሚኖሩ፡፡ የማይለያዩ፡፡ እውነተኛ ጓደኛሞች፡፡ አንድ ቀን የአንደኛው እናት ታመመች፡፡ ሆስፒታሉም 4000 ብር ጠየቀውት፡፡ ልጁ በግዜው ገንዘብ አልነበረውምና ወደ ጓደኛው ደውሎ "ጓደኛዬ እናቴ ታማ ሃኪም ቤት ነኝ፡፡ 4000 ብር ጠየቁኝ፡፡ ለግዜው ደሞ እኔ የለኝም፡፡ ከቻልክ ፈልግልኝ" አለው፡፡ ጓደኛውም "እሺ ወንድሜ ትንሽ ጠብቀኝ፡፡" ብሎት ስልኩን ዘጋው፡፡ ጓደኛው ወደ ባንክ ሄደ፡፡ ወደ እሚያቃቸው ሰዎች ጋር ሄደ፡፡ በቂ ብር ግን ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ሲደውልለት "ትንሽ ጠብቀኝ ወንድሜ እየፈለኩ ነው" ብሎት ዘጋው፡፡ በተደጋጋሚ ይደውልለታል፡፡ ትንሺ ጠብቀኝ እያለ ይዘጋዋል፡፡ መጨረሻ ላይ ግን ስልኩ ሙሉ በሙሉ ተዘጋ፡፡ አይጠራም፡፡ አይሰራም፡፡ እናቱ የታመመችበት በጣም ተናደደ፡፡ ሆስፒታል በተቀመጡት ሰዎች ፊት ጓደኛውን ይረግም ጀመር" ጓደኛ ለዚ ግዜ ካልሆነ ለመቼ ሊሆን ነው፡፡ ባይችል እንኳ ስልኩን ከሚዘጋብኝና ቆይ እያለ ሌሎች ጋር እንዳልሞክር ከሚያዘናጋኝ ምናለ አልችልም ቢለኝ፡፡ ይሄ እርጉም፡፡ እናቴ ታማ እየማቀቀች እንዴት ይቀልድብኛል፡፡ ይሄ ክፉ ይህን ቀን የማላልፍ መስሎታል ይሄ አረመኔ ......." በቃ ያለ ማቋረጥ በተቀመጡት ታካሚዎች መሀል ይረግመው ጀመር፡፡ ትንሺ ቆይቶ ጓደኛው በሩጫ መጣ፡፡ ከዛ ከኪሱ ብሩን አውጥቶ ሰጠው፡፡ እናቱ የታመመችበትም " ቆይ ለምን ነበር ስልክህን የዘጋሀው፡፡" ጠየቀው፡፡ ጓደኛውም ብር ሳጣ ሸጥኩት፡፡ ለዛ ነው የማይሰራው፡፡ ብሎ መለሰለት፡፡ እናቱ የታመመችበትም ጓደኛውን ሲሰድብ በሰሙት ሰዎች ፊት ተዋረደ፡፡ እንዲያ የረገመው ጓደኛው ለካ እንዲህ ይወደው ነበር፡፡ ቸኩላችሁ ስትፈርዱ ለሚመጣው ለሚከተለው ፀፀት አቅም አይኖራችሁምና ...ቶሎ አትፍረዱ፡፡ ቸኩለው ፈርደው ብዙዎች ፀፀት ውስጥ ገብተዋል፡፡ ቸኩላችሁ አትፍረዱ፡፡ መልካም ጊዜ!
Show all...
Hey guys
Show all...
  • File unavailable
  • File unavailable
# ይህችን_ታሪክ_ተጋበዙልኝ ። የታጠቁ ዘራፊዎች ወደ ባንክ ገብተው “አንድም ሰው እንዳይንቀሳቀስ!ገንዘቡ የመንግሥት ነው፤ ህይወታችሁ ግን የእናንተ ነው” ሲሉ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ተናገሩ፡፡ሁሉም ሰው ወለሉ ላይ በደረቱ ተኛ፡፡ይኼ “Mind Changing Concept” ይባላል፤ ከተለመደው ወጣ ባለ መልኩ የሰዎችን አስተሳሰብ መቀየር ነውና፡፡ ጠረጴዛ ላይ ተደፍታ የነበረች አንዲት ሴት የማጉረምረም ድምጽ ስታሰማ፣ ከዘራፊዎች አንዱ ቆጣ ብሎ፣ “እመቤት እንደሰለጠነ ሰው አስቢ እንጂ፡፡ ይህ እኮ ዘረፋ እንጂ አስገድዶ መድፈር አይደለም ” አላት፡፡ ፀጥ አለች፡፡ ይኼ “Being Professional” ነው፤ በሰለጠንክበት ጉዳይ ላይ ብቻ ትኩረት ታደርጋለህና፡፡ዘራፊዎቹ ያለምንም ችግር ቤታቸው ገቡ፡፡ ከዘራፊዎቹ መካከል ልጅ እግሩ እና የMaster of Business Administration ተመራቂው የተዘረፈው ገንዘቡ እንዲቆጠር ሃሳብ አቀረበ፡፡ ነገር ግን በዕድሜ ታላቅ የሆነውና እስከስድስተኛ ክፍል ብቻ የተማረው ዘራፊ፣ በቁጣ “አንተ የማትረባ ደደብ! ይህን ሁሉ ገንዘብ ማን ይቆጥራል? ዛሬ ማታ በቴሌቪዥን ዜና ላይ ስንት እንደዘረፍን ይነግሩናል፡፡”ይኼ “Experience” ይባላል፡፡ ዛሬ ዛሬ በትምህርት ከሚገኝ ዕውቀት ይልቅ ‘ልምድ’ የበለጠ ዋጋ አለው፡፡ ዘረፋው ከተፈፀመ በኋላ፣ የባንኩ ማናጀር የባንኩን ሱፐርቫይዘር ጠርቶ በአስቸኳይ ፖሊስ እንዲጠራ ነገረው፡፡ ሱፐርቫይዘሩ ግን፣ “ቆይ ተረጋጋ! እየውልህ፣ መጀመሪያ ከካዘና 10 ሚሊየን አንስተን ለራሳችን እንውሰድ፡፡ ከዚያም ባለፉት ወራት የወሰድነውን 70 ሚሊየን እንጨምርበት፡፡ ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ ያለብን ይህን ገንዘብ ዛሬ ከተዘረፈው ጋር ደምረን ነው” አለው፡፡ ይኼ “Swim with the tide” ይባላል፡፡ የተፈጠረን አስቸጋሪ ሁኔታ ለራስ ጥቅም ማዋል እንደማለት፡፡ ሱፐርቫይዘሩም አለ፣ “በየወሩ ዘረፋ ቢካሄድብን እንዴት መልካም ነበር!” በሚቀጥለው ቀን፡፡ ከባንኩ የተዘረፈው ገንዘብ 100 ሚሊየን እንደሆነ በቴሌቪዥን ዜና ተነገረ፡፡ ዘራፊዎች ደነገጡ፤ የዘረፉትንም መቁጠር ጀመሩ፤ማመን አቃታቸው፤ ደግመው ቆጠሩ፤ ያው ነው፡፡ ትንሽ ቆይተው እንደገና መቁጠር ጀመሩ፤ ተመሳሳይ መጠን – 20 ሚሊየን ብቻ! በጣም ተናደዱ፣ “እኛ ህይወታችንን ለአደጋ አጋልጠን 20 ሚሊየን ብቻ ስናገኝ፣ የባንክ ማናጀሩ ቁጭ ብሎ 80 ሚሊየን እንዴት ያገኛል?” ከንፈራቸውን ነከሱ፣ ጠረጴዛውን በቡጢ ነረቱ፡፡ ሌባ ከመሆን መማር ይሻላል ማለት ይህ አይደል?i (Africa’s elites are lords of poverty! ያለው ማን ነበር?) የማናጀሩ ፊት በፈገግታ እንደ ማለዳ ፀሐይ አብረቅርቋል፤ የደስታ ግምጃ አድምቆታል፡፡ በሽርክና ገበያው የተፈጠረበት ጉድለት ተሞልቶለታልና፡፡ ይኼንን “Seizing the opportunity” ይሉታል፡፡ ዋነኞቹ ዘራፊዎች እነማን ናቸው? የሚል ጥያቄ ማስቀመጥ ፈልጌ የነበረ ቢሆንም ከወቅቱ ጋር ላይሄድ ይችላል ብዬ በማሰብ ትቼዋለሁ፡፡ # ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
Show all...
  • File unavailable
  • File unavailable