cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

WIMA TUBE

✔️በቻናላችን✔️ ✅ 📲 የAndroid መተግበሪያ ✅ 💻 የPC SoftWare ✅ 📌 አዲስ ለሆኑ የቴክኖሎጂ ምርቶች ልዩ ዘገባ ✅ 🏦 የonline money making website and app👉እኚህን ፕሮግራሞችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀላሉ👉https://t.me/WIMATUBE https://youtube.com/@WimaTube?si=KenitfQa1

Show more
Advertising posts
147
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
✳️ አንድ አስፋልት ላይ ብስክሌት ሰው ሳይነዳው ብቻውን እየሄደ፣ መሰናክሎችን እያለፈ ቢያዩ ምን ይላሉ❓ 🔺ዢሂ ጁን የተባለ አስደናቂ የሃርድዌር መሐንዲስ ከብስክሌቱ ላይ መውደቁን ተከትሎ ከላይ በምስሉ ላይ የሚታየውን  መሰናክሎችን የሚከላከል እና ራስን መቻልን ወይም Balance የሚያደርግ እንዲሁም ራሱን የሚነዳ ብስክሌት ሰራ ሲል የአልጀዚራ ዘገባ ያስረዳል። 🔺ወጣቱ ኢንጂነር ይህን የብስክሌት ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ 4 ወራትን ብቻ የፈጀበት ሲሆን የሚገርመው ደግሞ ፕሮጀክቱን የሰራው በትርፍ ሰአቱ መሆኑ ነው። 🔺ብስክሌቱ የፍጥነት መለኪያ እና ጋይሮስኮፕ ሴንሰሮችን በመጠቀም የብስክሌቱን የፊት ተሽከርካሪ እንዳይንገዳገድ  እና በፍጥነት የሚወድቅ ከሆነ አቅጣጫውን ለመቀየር፣ መሰናክሎችን ማገናዘብ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተካቶለታል። 🔺በሚያስደንቅ ሁኔታ የብስክሌቱ እንቅስቃሴ በጣም ለስላሳ ነው፤ እና ስለ ፕሮጀክቱ ብዙ ሰዎች ሞክረውት ተወዳጅነትን አትርፈዋል። ይህ አስደናቂ መሐንዲስ ባጋጠመው ችግር ላይ ተመርኩዞ ችግሩን የሚፈታለት መፍተሄ አግኝቷል። #Tech_News
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
✳️ዜጎች የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ በኦንላይን ተመዝግበው ባሉበት እንዲመጣላቸው የሚያስችል አገልግሎት ተጀመረ❗️ 🔺ብሔራዊ መታወቂያ ካርድን በኦንላይን ተመዝግቦ በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት በኩል ካርዱን ካሉበት ሆነው በማዘዝ ባሉበት የማድረስ ሥራ መጀመሩን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ማስታወቁን ኢፕድ ዘግቧል። 🔺የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ የሕትመት ሥራ በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ሲከናወን የቆየ ሲሆን የብሔራዊ መታወቂያ ካርዱን ማግኘት የሚፈልጉ ዜጎችም አገልግሎቱን ለማግኘት በአካል መገኘት ይኖርባቸው ነበር። አሁን ግን ዜጎች አገልግሎቱን በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ የኦንላይን ምዝገባ የተጀመረ ሲሆን የክፍያ ሥርዓቱም በቴሌ ብር እና በባንክ መክፈል እንደሚቻል ተጠቁሟል። 🔺የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ ማግኘት የሚፈልጉ ዜጎች fayda net ድረ ገጽ ላይ በኦንላይን መመዝገብ እንደሚችሉ ሲገለፅ ፥ በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት በኩል ካርዱን ባሉበት ቦታ እንዲመጣላቸው ማዘዝ ይችላሉ ተብሏል። Online መመዝገቢያ link https://id.gov.et/
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
✳️በ2023 በአፍሪካ ከፍተኛ ሽያጭ ያገኘው ስማርት ስልክ የትኛው ነው? 🔺በአፍሪካ በፈረንጆቹ 2023 የስማርት ስልክ ሽያጭ በከፍተኛ ሁኔታ ጭማሪ ማሳየቱን አዲስ የወጣ ሪፖርት አመላክቷል። 🔺TECNO, SAMSUNG, iPHONE, INFINIX እና ITEL በፈረንጆቹ 2023 ላይ የአፍሪካን ገበያ በስፋት ከተቀቆጣጠሩት ውስጥ ቀዳሚዎቹ ናቸው ተብሏል። 🔺በ2023 በብዛት የተሸጡ ስማርት ስልኮች በሪፖርቱ መሰረት ቴክኖ ስማርት ስልክ በፈረንጆቹ 2023 ዓመት የስማርት ስልክ ገበያ ከሳምሰንግ እና አፕል በመብለጥ አንደኛ ደረጃ ላይ መቀመጡም ተነግሯል። 🔺የቴክኖ ሞባይል የአፍሪካ ገበያን እንዲቆጣጠር ከረዱት ውስጥ አንደኛው ዋጋው ነው የተባለ ሲሆን፤ በተለይ ከ150 ዶላር ጀምሮ የሚሸጡት “Tecno Pop 7” እና “Camon 20 Pro” በተጠቃሚዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝተዋል ነው የተባለው። 🔺በሪፖርቱ በአንስተኛ ዋጋ ገበያ ላይ የሚገኙት ቴክኖ፣ አይ ቴል እና ኢንፊኒክስ ስማርት ስልኮች በ2023 የአፍሪካ ስማርት ስልክ ገበያ ውስጥ 48 በመቶውን የገበያ ድርሻ መቆጣጠራቸውን ሪፖርቱ አመላክቷል። 🔺ከዚህ ውስጥ ቴክኖ 26 በመቶ ሲይዝ፣ ኢኒፊኒክስ 12 በመቶ እንዲሁም አይ ቴል 10 በመቶ ድርሻ መያዛቸውን ሪፖርቱ አመላክቷል። ሌሎች የቻይና ስማርት ስልኮች የሆኑት ዛዮሚ እና ኦፖ የተባሉ ስማርት ስልኮችም በአፍሪካ ገበያ ውስጥ ከፍተኛ እድገት እያስመዘገቡ እደሆነ ተመላክቷል።
Show all...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የቻይና ሳይንቲስቶች አየር ላይ ወደ ስድስት ትንንሽ ድሮኖች የሚቀየሩ ወታደራዊ ድሮኖች መስራታቸው ተሰማ የቻይና ሳይንቲስቶች በአየር ላይ ወደ ስድስት የተለያዩ ትንሽ ድሮኖች መቀየር የሚችሉ ወታደራዊ ሰው አልባ ድሮኖች መስራታቸውን ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት ዘግቧል። እነዚህ የድሮን ጦር መሳሪያዎች ከተለምዷዊው ድሮኖች የበለጠ ፈጣን እና ቀልጣፋ ሲሆኑ ባልተጠበቀ ሁኔታ በጦር ሜዳ ላይ ወደ ተለያዩ ትንንሽ ድሮኖች በመቀያየር ጠላትን የማጥቃት ሀይል እንዳላቸው ሳይንቲስቶቹ ገልፀዋል። ድሮኖቹ አወቃቀራቸውና ንድፋቸው ጠመዝማዛ እና የተለያየ ጠርዝ ባለው ሜፕል በተሰኘው ተክል ላይ የተመሰረተ ሲሆን ድሮኖቹ  ሲነጣጠሉ  የበረራ ቅልጥፍናቸው ከአብዛኞቹ ትናንሽ ድሮኖች በ40 በመቶ ከፍ ያለ መሆኑ ተጠቁሟል። ምንጭ: @TikvahethMagazine
Show all...
👍 2
#ፎቶ: የመጀመሪያዎቹ በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሠሩ  የህዝብ ማመላለሻ  አውቶብሶች በአዲስ አበባ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ተገልጿል።         አውቶብሶቹን ወደ ስራ ያስገባው በቅርቡ 20 በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሠሩ ሚኒባሶችን  ወደ ስራ ያስገባው የበላይነህ ክንዴ እህት ድርጂት ቬሎሲቲ ኤክስፕረስ ነው። ዛሬ ስራ የጀመሩት አውቶብሶች መነሻቸው ቦሌ ሲሆን መዳረሻቸው በእስጢፋኖስ አራት ኪሎ  ስድስት ኪሎ ሽሮ ሜዳ ነው።
Show all...
👍 1
https://t.me/notcoin_bot?start=r_573984_12671944 #መልካም_ዜና ቀድመው የ #Notcoin ባለቤት ይሁኑ ፣ #Notcoin ሳያልቅቦ ቀድመው ከጆ ያስገቡ ፣ ቴሌግራም በቅርቡ ከ #Bitcoin ጋር የሚስተካከል #Notcoin የሚባል የገንዘብ አይነት አርቅቋል ፣ ይህን #Notcoin ልክ እንደ ፌደራል ባንክ (ገንዘብ አታሚ) የተወሰኑ የዲጂታል #Notcoin ኤክትሮኒክ ገንዘብ ዲጂታሊ አትሞ አዘጋጅቷል ፣ እነዚህን የተዘጋጁ ዲጂታል ገንዘቦች ለተጠቃሚዎቹ በጨዋታ (Game) መልክ በማከፋፈል ላይ ይገኛል ፣ እርሶም የድርሻዋን #ሳያልቅቦ ፈጥነው ይውሰዱ ፣ NB. ይህን ሲስተም (የተወሰኑ ኤሌክትሮኒክ ገንዘቦችን ማተም እና ለመጀመሪያዎቹ ሰዎች ማከፍፈል) ከዚህ ቀደም #Bitcoin ተጠቅሞታል ፣ በአሁኑ ሰአት የቢትኮይን ዋጋ ከታች የተጠቀሰው ላይ ደርሷል 1 BTC(bitcoin) = $42,600 USD ማን ያውቃል ከሆነ ሰአት በኋላ የ #Notcoin ዋጋ ከፍ ሊል ይችል ይሆናል ። ዋጋው ከፍ ቢልም ባይልም አሁን ላይ ነፃ ስለሆነ ከጃችን ብናስገባው ይጠቅም ይሆን እንጂ አይጎዳንም ፣ ከታች በተጠቀሰው ሊንክ በመንካት ቀድመው የራሶን ድርሻ ይውሰዱ ፣ ይሄንን ንኩትhttps://t.me/notcoin_bot?start=r_573984_12671944
Show all...
Notcoin

Probably nothing @notcoin

Photo unavailableShow in Telegram
ኣባይ ✔<<የዓባይ ግድብ የኤሌክትሪክ ማመንጫው ግንባታ በሰባት ወራት ይጠናቀቃል። ✔በዓባይ ወንዝ ላይ የሚገነባው ድልድይና የፕሮጀክቱ ሙሉ ሥራ በቀጣይ ዓመት ይጠናቀቃል። ✔ቀንና ሌሊት በሚሠሩ ባለሙያዎች አማካኝነት የግድቡ ግንባታ የሲቪል ሥራው 99 በመቶ ተጠናቋል። ✔ዋናው የግድቡ ክፍል 107 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የኮንክሪት ሙሌት ይይዛል።አሁን ላይ ሊጠናቀቅ አንድ በመቶ ብቻ ቀርቶታል ተብሏል።
Show all...
#Update የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ የዲጂታል ባንክ አግልግሎት ሙሉ በሙሉ መጀመሩን ገለጸ። ባንኩ ፤ በሲስተም ችግር ምክንያት ፦ - በቅርንጫፎች፥ - በኢንተርኔት ባንኪንግ፥ - በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሞ እንደነበር አስታውሷል። በቅርንጫፍ እና በኤቲኤም የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀደም ብለው መጀመራቸውን ገልጾ አሁን ደግሞ በዲጂታል የሚሰጡ የባንክ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ መጀመራቸውን አሳውቋል። @remoteict
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ንግድ ባንክን ምን አጋጠመው? ከትናንት ለሊት ጀምሮ ተመሳሳይ መልዕክቶች እየደረሱኝ ነበር፣ መልዕክቶቹም "በርካታ ሰዎች፣ በተለይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከንግድ ባንክ ከኤቲኤም እና ከኦንላይን ትራንስፈር በነፃ ገንዘብ ወስደዋል ወይም ትራንስፈር አርገዋል" የሚል ነው። አንድ ተማሪ እንደጠቆመኝ "እኛ ጋር ጓደኞቻችን ከ100 ሺህ እስከ 50 ሺህ  የሰሩ አሉ። 435ሺ ብር የሰራ ተማሪ አለ በዛች ቅፅበት ምክንያቱም ለሊት ላይ ንግድ ባንክ የፃፍክለትን ብር ያወጣ ነበር። ይህ የሆነው ለሊት ከ6 ሰአት እስከ 9 ሰአት አከባቢ ነበር።" ሌላ ተማሪ ሲያስረዳ "ለምሳሌ እኔ ጋር 500 ብር ቢኖረኝ  ዝም ብዬ ወደ አንተ 50,000 ብር ፅፌ በሞባይል ባንክ ብልክ ዝም ብሎ ይልክ ነበር" ብሏል። ወደ ኢ-ብር የላኩት ልጆች ግን አካውንታቸው ወዲያው እንደታገደባቸው ታውቋል። አንድ መምህር ደግሞ "እኔ በምሰራበት ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ተማሪዎች ለሊቱን ሙሉ በዛ ያለ ገንዘብ በኤቲኤምና በትራንስፈር ገንዘብ ሲያስተላልፉ እንደነበር ሰምቻለሁ። ይህም ነገር በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎችም እንደነበር ስለሰማሁ ጥቆማ ልስጥህ በሚል ነው የጻፍኩልክ" ብለዋል። ይህን ተከትሎ ባንኩ "በሲስተም ችግር ምክንያት" አገልግሎቶቹ ላይ ማለትም በቅርንጫፎች፥ በኢንተርኔት ባንኪንግ፥ በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሟል ብሏል። የባንኩን የስራ ሀላፊዎች በስልክ ለማግኘት ያደረግኩት ሙከራ አልተሳካም፣ ባንኩ ግን ምን እንደተከሰተ ዝርዝር መረጃ ለህዝብ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ቴሌግራም በአንድ ቀን ብቻ ከ70 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ተጠቃሚዎች ማግኘቱን አስታወቀ **** በትናንትናው ዕለት ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ሜሲንጀር አገልግሎት ማቋረጣቸውን ተከትሎ ቴሌግራም የተሰኘው የማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያ ከ70 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ደንበኞች ማግኘቱን አስታውቋል። አገልግሎቶቹ ለስድስት ሰዓታት በተቋረጡበት ወቅት የቴሌግራም ዕለታዊ ዕድገት መጠን ከዚህ ቀደም ከነበረው በበለጠ ሲጨምር፤ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ ከሌላ የትስስር ገፆች የተሰደዱ ከ70 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ተጠቃሚዎችን ተቀብለናል ሲሉ የቴሌግራም መስራች የሆኑት ፓቬል ዱሮቭ በቴሌግራም ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። የፌስቡክ ኩባንያ 3.5 ቢሊዮን በሚሆኑ ተጠቃሚዎቹ ላይ ተፅዕኖ ያሳደረው የአገልግሎቱ መቋረጥ የጥገና ሂደት ላይ ባጋጠመ ችግር መከሰቱን ሲገልፅ፤ ኩባንያው አክሎም በተቋረጠባቸው ሰዓታት ውስጥ የተጠቃሚዎች መረጃ ምንም ዓይነት አደጋ አልገጠመውም ብሏል። ፌስቡክን በበላይነት የሚመራው የሜታ ድርጅት ለአገልግሎቱ መቋረጥ  ላደረሰውም ችግር ይቅርታ በመጠየቅ ስለተፈጠረውም ነገር ይበልጥ ለመረዳት እንደሚሰራም አሳውቋል።
Show all...