cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

ይህ ቻናል በላፍቶ ቢላል መስጂድ የሚሰጡ ደርሶችን እና የተለያዩ ሙስሊሙን የሚጠቅም ሙሀደራዎችና አጫጭር መልዕክቶች የሚለቀቅበት ሲሆን ሊንኩን በመጠቀም ለራሳችንም ሌሎችም እንዲጠቀሙ እናድርግ https://t.me/lafto_qirat

Show more
Advertising posts
1 371
Subscribers
+524 hours
+117 days
+4130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

«ከኃጢአት ጭንቀት ውጭ ያሉ ሁሉም ጭንቀቶች ይወገዳሉ።» ✍(በክር ኢብል ዓቢድ) 📚አልሀም ወልሑዝን ሊኢብኒ አቢ አዱንያ (28)
Show all...
👍 3 1
ህጻናትን ከቤት ወደ ሌላ ስፍራ ይዘናቸው ስንወጣ በሰውና በጂንኒ አይን (አይነ-ናስ ወል-ጂን) እንዳይለከፉ ቀጥሎ ያለውን ዚክር አናታቸውን በመያዝ እንበል፡-  1. አንድ ህጻን ብቻ ከሆነ፡- ‹‹ኡዒዙከ ቢከሊማቲላሂ-ታምማህ፣ ሚን ኩልሊ-ሸይጧኒን ወሃምማህ፣ ወሚን ኩልሊ-ዐይኒን ላምማህ››  2. ሁለት እና ከዛ በላይ ከሆኑ፡- ‹‹ኡዒዙኩማ ቢከሊማቲላሂ-ታምማህ፣ ሚን ኩልሊ-ሸይጧኒን ወሃምማህ፣ ወሚን ኩልሊ-ዐይኒን ላምማህ››  (ቡኻሪና አቡ ዳዉድ)፡፡  የዚህ ዚክር ትርጉም፡-  1. ‹‹አዒዙከ ቢከሊማቲላሂ-ታምማህ›› ማለት፡- ሙሉ በሆነው የአላህ ቃላት እጠብቅሀለው ማለት ነው፡፡ ወደ አንድ መንደር ወይም ቤት ሲገባ ‹‹አዑዙ ቢከሊማቲላሂ-ታምማቲ ሚን ሸርሪ ማ-ኸለቅ›› ያለ ሰው፡ ያንን ቤት እና መንደር ለቆ እስኪወጣ ምንም እንደማይደርስበት በሌላ ሐዲሥ ተነግሮአል፡፡  2. ‹‹ሚን ኩልሊ-ሸይጧኒን ወሃምማህ›› ማለት፡- ከሸይጧናትና ከመርዛማ ገዳይ ነገራት (ሙሉ በሆነው የአላህ ቃል እጠብቅሀለሁ) ማለት ነው፡፡  3. ‹‹ወሚን ኩልሊ-ዐይኒን ላምማህ›› ማለት፡- ከክፉ አይኖች በጠቅላላ (ሙሉ በሆነው የአላህ ቃል እጠብቃለው) ማለት ነው።
Show all...
👍 4
"አብዛኛውን ጊዜ የሚያስቸግረን፣ የሚቆረቁረን፣ አላራምድ የሚለንና ከዓላማችን የሚጎትተን ችግር ትልልቁ አይደለም፡፡ በየቀኑ የሚያጋጥሙን ጥቃቅን “አሸዋዎች” ናቸው፡፡ ትንንሽ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ባህሪይ፣ ትንንሽና አናሳ ወሬን የሚያወሩ ሰዎች ሁኔታ፣ ትንንሽና ስሜትን የሚነካኩ የየቀን ገጠመኞች . . . ጉዟችንን አዳጋችና አድካሚ ያደርጉታል፡፡ “በትንንሽ” ሰዎችና ሁኔታዎች ሳትበገሩ ትልቁ የሕይወት ስእልና ዓላማችሁ ላይ በማተኮር ወደፊት መገስገስን ያወቃችሁበት ጊዜ ዋናውን የሕይወት ድል የተጎናጸፋችሁበት ጊዜ ነው፡፡ በርቱ!" COPY
Show all...
3
አንድ ነገር አውቃለሁ... ጉድለቴ እጅግ የበዛ ከመሆኑም ጋር በጥፋቴ ላይ አይኔን ግንባር ያድርገው ብዬ ከኢስላም ውጪ በሆነ ተግባር ለመጋጋጥ አልሞክርም። በኢስላም ውስጥ የሚጠነሰሱ ተንኮሎችና የኢስላምን መርህ የመሸርሸር ተግባር በስመ ኢስላም የሚፈበረኩ የአውሮፓውያን ውጤት የሆኑ.... ከኢስላም ትውውቅ የሌላቸው ተግባራት ናቸው። እነዚህ ደግሞ መርሀቸው አይደለም ሸሪዐህ ይቅርና ዐቅል ራሱ የማይቀበለው በሽተኛ አካሄድ ነው። አላማቸው ሁሉ ለሚያገኙት ጥቅማጥቅም ብልሽትን ነው የሚሹት። በአሏህ ይሁንብኝ ለሴት ልጅ ኢስላም ያዘዘው መሸፋፈንና መሰተርን ነው። ይህ ነው የልቅና መንገድ.... ከዚህ ውጪ በሆነ መንገድ ልቅናን በፈለግን ጊዜ መዋረዳችን ቅሮት የለውም። ነስኣሉሏህ አስሰላመተ ወል ዐፊያህ 🤲 منقول
Show all...
2
لمثل هذا فأعدوا
Show all...
👏 2
🖇ከ11–18 አመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ልጆች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች የአቻ ግፊት (ተፅእኖ)         በዚህ ከ11–18 የእድሜ ክልል በልጅዎ ስብእና ላይ አስቀያሚ ጥላውን የሚያጠላ ችግር ቢኖር የአቻ ግፊት ነው።ለምሳሌ:–ተመሳሳይነት ያላቸውን ልብሶች መልበስ፣የፀጉር አበጣጠር እና ፋሽኖችን መከተል አይነት የአቻ ግፊት የሚንፀባረቅባቸው ለውጦችን መምጣት ሲያስተውሉ ልጅዎን ይዞት ሊጠፋ የሚችል  ሀይል እየተቆጣጠረው ሊሆን ይችላልና ሊጠነቀቁ ይገባል።በተለይ ልጅዎ በማህበረሰቡ ውስጥ ተቀባይነት ለሌላቸው ልማዶች እያጎበደደ ከሆነ በአቻ ግፊት ተጠምዷል ማለት ነውና የእርስዎ ጣልቃ ገብነት የግድ ይላል።         ለዚህ አይነተኛ መፍትሄው ልጅዎ ስለ ጎጂ ነገሮች ከሌሎች ጓደኞቹ በመስማት ሳያመልጥዎ በፊት ስለ ምንነታቸው እና ስለሚያስከትሉት ጉዳት ማነጋገር ነው።ብዙሃኑ ስላደረገው እኔም ላደርገው ይገባል የሚል ስሜት እንዳይሰማው ሊያደርጉ ይገባል።            📚ኢስላማዊ የልጆች አስተዳደግ
Show all...
👍 2 1
▪️ የአላህ መልእክተኛ ﷺ  እንዲህ ብለዋል፦ ⛔️“ሰዎች እንዲስቁ ብሎ ውሸት ለሚያወራ ወዮለት ወዮለት ወዮለት!” 📚አቡ ዳዉድ እና ቲርሚዚ ዘግበውታል
Show all...
👍 4
"#ኢላሂ! በድሎት ጊዜዬ ብረሳህም በችግር ጊዜዬ አትርሳኝ!ሰማይና ምድርን የሰፋ ትእግስት አለህና አትበቀለኝ!የትላንት ወራዳነቴ ነገም ይኖራልና አትያዝብኝ!"
Show all...
👍 5👌 2
✏️ ስልክን ያለ ገደብ መጠቀም     ይህ እድሜ ልጆች ስልክን የሚያውቁበት እና ጥቅሙን የሚገነዘቡበት እድሜ ነው።በዚህ እድሜ ላይ ያሉ ልጆች ረጅም ሠዐት በስልክ መነጋገር ይወዳሉ።ይህ ሁኔታ ስር ሰዶ ወደ ባሰ ችግር ከመሄዱ በፊት ገደብ ሊያበጁለት እና ሀሳብን አጭርና ግልጽ አድርጎ የመጠቀምን ባህል ሊያዳብሩላቸው ይገባል።      በመሆኑም በመጀመርያ ለልጅዎ የስልክ ምልልስ ማድረግ በቤተሠብ ፍቃድ የሚገኝ እንጂ መብት እንዳልሆነ ያስገንዝቡት ልጅዎ በቀን ውስጥ ሊቀበል የሚገባውን የደዋይ ብዛትም ሊወስኑ ይችላሉ።ከዚህም በተጨማሪ "በዚህ ሰዓት ስልክ መመለስ አይቻልም"አይነት ህጎችን ሊያወጡ ይችላሉ።
Show all...
👍 3
معنى قوله ﷺ: «ومَن يَسْتَغْنِ يُغْنِهِ اللَّهُ.» من يستغن يغنه الله، أي: من يستغن بما عند الله عما في أيدي الناس؛ يغنه الله عز وجل. وأما من يسأل الناس ويحتاج لما عندهم؛ فإنه سيبقي قلبه فقيراً - والعياذ بالله- ولا يستغني. والغنى غنى القلب، فإذا استغنى الإنسان بما عند الله عما في أيدي الناس؛ أغناه الله عن الناس، وجعله عزيز النفس بعيداً عن السؤال. [ شرح رياض الصالحين لابن عثيمين ج١ ص١٩٤ ]
Show all...