cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

"ነፍሳችን በስጋ ስንኖር ብዙ መከራ አለባት። እንዲሁም ከስጋችን ከተለየች በኋላ እንደሰራነው ስራ ጥሩ ወይም መጥፎ እጣፈንታዎች ይገጥሟታል። ታዲያ በህይወት ስንኖር ነፍሳችንን የምታሻግር አንድ መንገድ አለች ይህችም ቀጥተኛዋ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ናት። " https://t.me/MoaeTewahedoB አስተያየት ና ጥያቄ ያለው ብቻ‼️ @sosi5555 ይህ ፔጅ ታህሳስ 30/4/2014

Show more
Advertising posts
11 058
Subscribers
-1224 hours
-87 days
+2030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ባለመጥፋት_ከሚወዱ# 💦ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች በላካት መልእክት "ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ባለ መጥፋት ከሚወዱ ኹሉ ጋር ጸጋ ይኹን፤ አሜን" ይላል፤ ኤፌ 6፥24። በዚህች ንባብ ውስጥ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን መውደድ የሚገባን በምን ዓይነት መንገድ እንደ ኾነ ሲያስረዳ "ባለመጥፋት ከሚወዱ" በማለት ይገልጻል። በእርግጥም አንድ ክርስቲያን በእውነት ክርስቶስን ሊወድ የሚገባው በዚህ ፍቅር ነው። ለመኾኑ "ባለመጥፋት መውደድ" ምንድን ነው? 💦አንደኛው ትርጓሜ፦ እለ ያፈቅርዎ በኢጥፍአት፤ ትስብእቱን ከመለኮቱ፡ መለኮቱን ከትስብእቱ ሳይለያዩ ለሚወዱት ሰዎች (ጸጋሁ በኢጥፍአት) ጸጋው ባለመለያየት ይደረግላቸዋል ማለት ነው። (ትርጓሜ ኀበ ሰብአ ኤፌሶን)። ይህም ማለት ያፈቅርዎ በኢጥፍአት ተዋሕዶን መውደድ፥ የሥግው ቃል የኢየሱስን ክርስቶስን ሥጋዌውን መውደድ፥ ከተዋሕዶ በኋላ ልዩነት የሌለ መኾኑን መረዳትና ያን መውደድ ነው። በኢጥፍአትን = ባለመለያየት ይለዋልና። ስለዚህ አምላክ ሰው የኾነው እኛን በጸጋ አምላክ ለማድረግ ነው፤ በእርሱ ሥጋዌ ለእኛ የተሰጠንን ጸጋ ማድነቅና ያን እያሳቡ የጸጋውን ሰጪ በፍጹም ልብ መውደድ ነው። ስለ እኔ ብለህ የእኔን ሥጋና ነፍስ በተዋሕዶ ገንዘብ አደረግህ! ይህ እኔን ከፍ ለማድረግ ስትል ያሳየኸው ትሕትና እንዴት ድንቅ ነው! ትሕትናህን እያደነቅሁ ሥጋዌህንም እያሰብኹኝ ባለመጥፋት እወድሃለሁኝ። 💦ኹለተኛ በኢጥፍአት የሚለውን መጋቤ ሐዲስ ስቡሕ አዳምጤ "ባለመጥፋት ሲል በእምነት ውስጥ የሚኖሩ ማለቱ ነው። በእምነት ውስጥ የሌሉ ሰዎች የጥፋት ልጆች ናቸውና።" በማለት ያብራሩታል። (ስቡሕ አዳምጤ (መጋቤ ሐዲስ)፣ ከኤፌሶን እስከ ዕብራውያን ትርጓሜ፣ 2013 ዓ.ም፣ ገጽ 61)። ስለዚህ ባለመጥፋት ከሚወዱ ማለት በኦርቶዶክሳዊት እምነት ውስጥ ኾነው የሚወዱ ማለት ነው። አብርሃም ካረጀ እና የመውለጃ ጊዜው ካለፈ በኋላ በእምነት እግዚአብሔር ዘሩን እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደ ምድር አሸዋ እንደሚያበዛለት ተቀብሏል። ያለምንም መጠራጠር ስለሚወደው በፍጹም እምነት ቃሉን ተቀብሏል። አብርሃም በእምነት እግዚአብሔርን ከልጁ ይልቅ ወድዶት ልጁን እንኳን ሳይራራ ሊሠዋለት ወደ ሞርያ ተራራ በሄደ ጊዜ ለእግዚአብሔር ያለውን የእምነት ፍቅር ገልጿል። ከዚህ በተጨማሪ ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል ስለ ኾነ፥ በሰው አንጻር ለእግዚአብሔር ያለው ፍቅር ይገለጽ ዘንድ ያለመታከት እንግዳ ይቀበል ነበር። አብርሃም እንግዳ አድርጎ የሚቀበለው እየመረጠ አይደለም፤ ይልቅስ ኹሉንም የሰው ልጅ ያለምንም አድሎና ልዩነት ነበር። በእውነት እግዚአብሔርን የሚወድ ሰው ኹሉንም ያለ ልዩነት እኩል ይወዳል። የሕይወቱ መርሕም በእምነት መሠረት ላይ የቆመ ይኾናል እንጂ በዚህ ዓለም ፍልስፍናና ኃላፊ ጠፊ ነገር ላይ ፈጽሞ አይመሠረትም። እግዚአብሔርን በእምነት የሚወድ ሰው በማንኛውም የሕይወት ፈተና ውስጥ እግዚአብሔርን እያሰበ ይበረታል፤ ልቡናውም አይናወጽም። እግዚአብሔርን በእምነት ወድደን የምንከተል ከኾነ በችግርም ኾነ በመከራ ጊዜ ለእርሱ እንታመናለን።  💦ሦስተኛ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ "ባለመጥፋት" የምትለዋን ሲተረጒም "ባለመጥፋት" ሲል ምን ማለት ነው? ፍቺው "በንጽሕና" ማለት ነው፤ ወይም "ስለማይጠፉት ስለእነዚያ ነገሮች ሲባል" ማለት ነው፣ ለምሳሌ በሀብት፣ በክብር እንዳለው ሳይኾን ስለማይጠፉት ስለእነዚያ ጸጋዎች ለማለት ነው። ... በአለመጥፋት ሲል በበጎነት ማለቱ ነው። ምክንያቱም ኹሉም ኃጢአት ጠፊ ነው።" በማለት ያብራራል። (ኀይለ ኢየሱስ መርሻ (ተርጓሚ)፣ ትርጓሜ ኤፌሶን በቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፣ 2013 ዓ.ም፣ ገጽ 289)። ከዚህ እንደምንረዳው ባለመጥፋት ከሚወዱ ማለት በማይጠፉ በተባሉ ንጽሕና፣ በጎነት፣ ትሕትና፣ የውሃት ውስጥ ኾኖ መውደድ ነው። የማይጠፋ ሰማያዊ ጸጋን ከእግዚአብሔር ለመቀበል የእግዚአብሔር ግብረ ባሕርይ ተብለው በሚጠሩት ቋሚ በኾኑ በጎነቶች ውስጥ ኾኖ እግዚአብሔርን መውደድ ያስፈልጋል። አንዳንዶች ስለሚያልፉ ተራ ምድራዊ ነገሮች ብለው ብቻ እግዚአብሔርን የሚፈልጉና እንወድሃለን የሚሉ አሉ፥ ይህ በእጅጉ ስሕተት ነው። እግዚአብሔርን መውደድ ያለብን ባለመጥፋት ውስጥ ኾነን ነው። ኃጢአት ባላጠፋው ንጹሕ ኦርቶዶክሳዊ አስተሳሰብ ውስጥ ኾነን! 💦ስሜታዊ ኾነን ሳለ፥ እግዚአብሔርን እንወድሃለን ብንለው፥ ይህ መውደዳችን የተመሠረተው ስሜት ላይ ስለ ኾነ ጠፊ መውደድ ነው። ብዙዎች በዚህ ጠፊ መሠረት ላይ ኾነው ስለወደዱት ትንሽዬ መከራ ስንኳን መቋቋም አቅቷቸው ክርስትናን ከሕይወታቸው ገፍተው ወደ ሌላ ዓለም ገብተዋልና። ባለመጥፋት መውደድ "ከማይጠፋ ዘር እንድንወለድ" ያደረገበትን ምሥጢር መውደድ፥ የማትጠፋ ፍጽምት የኾነችውን የእርሱን ለዓለም የተደረገች ድኅነት መውደድ፥ ከዚህም የተነሣ ከእርሱ ጋር መኾንን ጽኑዕ ማድረግን ይመለከታል። በዚህ ዓለም ካለው የጥፋት መንገድ ልቡናን ጠብቆ፥ ሕሊናን በክርስቶስ መሠረትነት ላይ መትከል፥ በማይቋረጥ የመንፈሳዊነት ዕድገት ኹል ጊዜ ወደ ቅድስና መጓዝን ኹሉ ያመለክታል። ይህ ባለመጥፋት የመውደድ መንገድ ነውና። አንድ ኢግናጥየስ የተባለ ሊቅ ለክርስቶስ ያለውን ጽኑ ፍቅር ለመግለጥ ከእርሱ ጋር በእርግጥም መኾን በዓለም ላይ የገዢነትን ሥልጣን እንደሚሰጠን እንዲህ ያስረዳል፦ "አንድን ነገር መሻት ብቻ እጅጉን ጠቃሚ ነው፤ ይኸውም ከክርስቶስ ጋር መኾን። ከክርስቶስ ጋር የሚኾን ሰው ምንም እንኳን በምድራዊ ነገር ደሃ ቢኾንም ባለጸጋ ነው። ኹል ጊዜ ምድራዊውን ነገር ከሰማያዊው ነገር ይልቅ የሚፈልግ ሰው፥ ኹለቱንም ያጣቸዋል። ነገር ግን ሰማያዊውን ነገር የሚሻ ሰው የዓለም ኹሉ ገዢ ነው።" ይላል። (St. Ignatius Brianchaninov, Patericon)። እንግዲህ ክርስቶስን "ባለመጥፋት ስንወድ" ከምንም ነገር በፊት እርሱን እንሻለን፤ በእርሱ ፍቅርም ልቡናችን ተቃጥላ ትእዛዛቱን በመፈጸም እየተደሰተች ትኖራለች። 💦በዚህ ዘመን ያለን ሰዎች ኹሉንም ነገር በመጥፋት የምንወድ አይመስላችሁምን? እግዚአብሔር ለበጎ ያዘጋጃቸውን ነገሮች እንኳን እኛ ለጥፋት ስናደርግና በእጅጉ ስንሳሳት እንታያለን። እግዚአብሔርን በእውነት ወድደው ፍቅራቸውን በተግባር የገለጹትን ቅዱሳንን መመልከት ይገባናል። እኛን እጅግ የሚናስደስቱን ነገሮች እግዚአብሔርን ደስ የማያሰኙ መኾናቸውን ከተረዳን ስለ እርሱ ብለን ልንተዋቸው ይገባል። እግዚአብሔርን በምናፈቅረው ፍቅር ላይ ተገዳዳሪ አድርገን ልናቀርብ የሚገባን ምንም ነገር ሊኖር አይገባውምና። የእውነት ይህን ሐሳብ ተቀብለን ፍላጎታችንን ብንገራና በፈቃደ እግዚአብሔር መሠረት ላይ ብናደርገው ኹሉ ነገር እየተስተካከለ ይሄድልናል። እንግዲህ ወደ ልባችን እንመለስ፥ እግዚአብሔርንና የእርሱ የኾኑትን ኹሉ ባለመጥፋት ከሚወዱ ከቅዱሳን ኅብረት ለመደመር እንትጋ። እግዚአብሔር ባለመጥፋት ከሚወዱት ያድርገን አሜን። https://t.me/MoaeTewahedoB
Show all...
ሞዐ ተዋሕዶ ልጆች ፔጅ

"ነፍሳችን በስጋ ስንኖር ብዙ መከራ አለባት። እንዲሁም ከስጋችን ከተለየች በኋላ እንደሰራነው ስራ ጥሩ ወይም መጥፎ እጣፈንታዎች ይገጥሟታል። ታዲያ በህይወት ስንኖር ነፍሳችንን የምታሻግር አንድ መንገድ አለች ይህችም ቀጥተኛዋ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ናት። "

https://t.me/MoaeTewahedoB

አስተያየት ና ጥያቄ ያለው ብቻ‼️ @sosi5555 ይህ ፔጅ ታህሳስ 30/4/2014

🥰 4 1
🕰🔔 3:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰           @MoaeTewahedoB
Show all...
🥰 4👍 1 1
#ትዝብት         #አጭር_አስተማሪ_ታሪክ 🥀ልጅቷ ሥራ የላትም ፣ ከመኖሪያዋ አጠገብ ካለው የመድኃዓለም ቤተክርስቲያን ዘወትር እየተገኘች ልመናዋ ሥራ ስጠኝ ብቻ ከሆነ ሰንብታለች፡፡ በነጋ በጠባ ቁጥር “እባክህን አምላኬ ውዬ የምገባበት ሥራ ስጠኝ እያለች” እያለች ትጸልያለች፡፡ አንድ ቀን ቤተክርስቲያን ደርሳ ወደ ቤቷ ስትመለስ ከአንድ መሥሪያ ቤት አጠገብ ትደርስና የተለጠፈ የሥራ ማስታወቂያ አይታ ቆማ ማንበብ ትጀምራለች፡፡ የሥራው ዓይነት እና የትምህትቱ ደረጃ ሁሉ በዝርዝር ሰፍሯል፡፡ 🥀ሁሉም እሷ ልታሟላ የምትችለው መስፈርት ነበር፡፡ ደሞዙም አንድ ሺህ ብር ይላል፡፡የመሥሪያ ቤቱ ለመኖሪያ ቤቷ ቅርብ መሆን፣ የትምህርት ደረጃ መስርቱ ከእርሷ የትምህርት ደረጃ ጋር መመሳሰል፣ የመነሻ ደመወዙም ቢሆን ይህ ሁሉ ተደምሮ የመቀጠር ጉጉቷን ከፍ አደረገው፡፡ ይኹን እንጂ ከሌሎች ተመዝጋቢዎች ጋር መወዳደር ግድ ስለሆነ የማለፍና ያለማለፍ ጉዳይ እንዳለ ስትረዳ በጣም ተጨነቀች፡፡ ስለዚህ ተመዝግባ ስታበቃ ወደ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አቅንታ “እባክህን ይህን ፈተና አሳልፈኝና የሥራውን እድል ስጠኝ” ስትል ተማጸነች፡፡ ሁሉም አልፎ ውጤት የሚለጠፍበት ቀን ደረሰና በናፍቆትና በጉጉት ታጅባ ታነብ ለማንበብ ሄደች፡፡ውጤቱ ግን የእሷን ማለፍ የሚያረጋግጥ አልነበረም፡፡ የእሷ ስም የለም ያለፉት ሌሎች ናቸው፡፡ ምንም ሳትናገር ወደ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ሮጠች፡፡ እዚህም እንደደረሰች “መድኃኔዓለም ታዘብኩህ” ስትል የምሬት ድምጽ አሰማች፡፡ 🥀ይህ በሆነ በሳምንቱ ሌላ ማስታወቂያ በሌላ መ/ቤት ወጣ፡፡ ደመዎዙ አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ነበር፡፡ ይህን ስታይ እንደመጸጸት አለችና “የእኔመድኃኔዓለም ለካስ ይሄ እንደሚሻል አውቀህ ነው ያኛው እንዲያልፈኝ ያደረከው፣ እባክህን ይቅር በለኝ የአፌን አትቁጠርብኝ ይህን ግን እንዳትከለክለኝ አደራ” ስትል ተማጸነችና ተመዝግባ ውድድሯ ጀመረች፡፡ ሁሉም አልቆ ውጤት ሲለጠፍ አሁንም የእሷ ስም የለም፡፡ ያለፉት ሌሎች ናቸው፡፡ አሁን በጣም አዘነች፡፡ በሃይማኖቷ ላይ ያላት ተስፋ ሲሟሽሽ ተሰማት፡፡ በረዶ እንደወረደበት ሰው የክርስትና ወኔዋ ቀዘቀዘ፡፡ ጊዜ ሳታባክን ወደ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ሄደችና  “አሁንስ በጣም ታዘብኩህ” ስትል እሱ የሰጣትን ምላስ እሱው ላይ ዘረጋችው፡፡ 🥀በዚህ ሁለት ሳምንታት አለፉና አንዲት ጓደኛዋ አንድ መሥሪያ ቤት የሥራ ማስታወቂያ መለጠፉን ነግራት አልመዘገብም ብላ በማኩረፏ በብዙ ጉትጎታ ከቦታው ደረሰች ማስታወቂያውን ስታነበው ሁሉም መረጃ ከሷ ጋር የሚሄድ ሲሆን ደሞዙም ከመጀመሪያው በሁለት እጥፍ ጨምሮ ሦስት ሺህ ብር ይላል፡፡ ከሚቀር እስኪ ልሞክረው ብላ ተመዘገበች፡፡ ተገቢውን ሁሉ አድርጋ የመጨረሻ ውጤት የሚለጠፍበት ቀን ከስፍራው ተገኘች፡፡ አሁን ስሟ አንደኛ ተራ ቁጥር ላይ ተለጥፏል፡፡ በከፍተኛ ብቃት ማለፏን ስታይ ዕንባዋ በዐይኗ ግጥም አለ፣ ሁለቱን ዐይኖቿን 🥀 ስትጨፍናቸው ቋ ጥረው የያዙትን የደስታ ዕንባ በጉንጮቿ ላይ ከለበሱት፡፡ ቃል ማውጣት አልቻለችም እየበረረች ወደ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን መጣችና እየተንቀጠቀጠች ከታቦቱ ፊት ቆማ ለአፍታ ውስጧን አዳመጠች፡፡ ውስጧም አምላኳን በዚሁ ቦታ ተገኝታ ታዘብኩህ ስትል እንዳማረረችው አስታወሳት ያኔ “የኔ መድኃኔዓለም ታዘብከኝ አይደል?” አለች ለራሷ ብቻ በሚሰማ ድምጽ በቀስታ፡፡ 🥀እኛስ በክርስትና ውጣ ውረድ በማይገባን መዓረግና በሌለን አቅም መድኃኔዓለምን  ስንት ጊዜ ታዝበነው ይሆን? አሁን እኛ እሱን ለመታዘብ ብቃቱ አለን ? እሺ ይሁን እሱስ እኛን አንድ ጊዜ ከፍ አንድ ጊዜ ዝቅ እያልን በክርስትና ጉዞ ብልጭ ድርግም በማለት ስንጓዝ ስንት ጊዜ ታዝቦን ይሆን ለማንኛውም አይደለም እግዚአብሔርን ሰውንም እንኳን ቢሆን ለመታዘብ አንቸኩል ያ ሰው እኛንም ሊታዘበን ይችላልና፡፡             🥀የሰራዊትጌታ ታጋሾች ያድርገን።  @MoaeTewahedoB @MoaeTewahedoB @MoaeTewahedoB
Show all...
15👍 2🥰 1
🕰🔔 9:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰           @MoaeTewahedoB
Show all...
👍 5🥰 3 1
🕰🔔 6:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰           @MoaeTewahedoB
Show all...
👍 6 2🥰 2
Photo unavailableShow in Telegram
🥰
Show all...
🥰 15👍 7 7😢 1
#ቅድስት_ሥላሴ - (#ሐምሌ_7) ሐምሌ ሰባት በዚች ቀን ሥሉስ ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት ነው፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስትነት በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ተገኙ፣ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና፡፡ ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እንላቸዋለን፡፡ የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም፡፡ የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል፣ በቤቱም መጥተው ያድራሉ፡፡ ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም፡፡ አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል፡፡ አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኳናቸው አስተናገዱ፡፡ አብርሃም እግራቸውን አጠበ፡፡ በጀርባውም አዘላቸው፡፡ ምሳቸውንም አቀረበላቸው፡፡ እነርሱም እንደሚበሉ ሆኑለት፡፡ በዚያው ዕለትም የይስሃቅን መወለድ አበሠሩት፡፡ አብርሃም ከደግነቱና እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በተመሳቀለ ጎዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ የወጣ የመረደውን፣ የመጣ የሄደውን ሁሉ እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ የሚኖር ጻድቅ ነበር፡፡ ለዚህም ነው አብርሃም በወይራ ግራር (በመምሬ) ዛፍ ሥር ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር አንድነቱን ሦስትነቱን የገለጠለት፡፡ ዘፍ 18፡1-25፣ ሮሜ 4፡-3፡፡ ቀትር ሰዓት ላይ በድንኳኑ ደጅ ተቀምጦ እንግዳ ሲጠብቅ እግዚአብሔር ታየው ተነጋገረው፡፡ አንገቱን ቀና አድርጎ ዐይኑን አራምዶ በተመለከተ ጊዜ እነሆ ሦስት ሰዎች ከበላዩ ባለ ተራራ ላይ ቆመው አያቸው፣ ወደ እርሱም ሲወርዱ አይቶ ፈጥኖ ሄዶ ከሰግደላቸው በኋላ ‹‹አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ…›› እያለ በትሕትና በመጋበዝ ወደ ድንኳኑ አስገብቶ በሚገባ ጋበዛቸው፡፡ ‹‹በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ›› ብሎ አንድነታቸውን፣ ‹‹ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ›› ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡ ያች ሥላሴ የገቡባት የአብርሃም ድንኳን የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡፡ ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ሁሉ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም አብ ለአጽንዖ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋዋን ለመዋሐድ የማደራቸው ምሳሌ በመሆኑ አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ናት፡፡ ሉቃ 1፡35፡፡ እግዚአብሔርም አብርሃምን የዛሬ ዓመት ልጅ እንደሚወልድ ነግሮት በዓመቱ ይስሐቅን ወልዷል፡፡ ሁለቱ ሰዎች ከአብርሃም ድንኳን ወጥተው ወደ ሰዶም ወደ ገሞራ ሄዱ፣ አብርሃምም ይሸኛቸው ዘንድ አብሯቸው ሄደ፡፡ የሄዱትም ሁለቱ ሰዎች አብና መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ ነገር ግን አንዱ ወልድ በአብርሃም ቤት ቀርቷል ይኸውም ከቤተ አብርሃም ሰው እንደሚሆን ለማጠየቅ ነው፡፡ አብርሃምም ተመልሶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ፡፡ እግዚአብሔርም የሚሠራውን ሁሉ ከአብርሃም አይሠውርም ነበርና የሰዶምን የገሞራን ጥፋት ነገረው፡፡ አብርሃምም ይቅር እንዲላቸው አብዝቶ ለመነላቸው፡፡ ሥሉስ ቅዱስን የአብርሃሙ ሥላሴን በምግባር በሃይማኖት ሆነን እናገለግል ዘንድ የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን አሜን። @MoaeTewahedoB
Show all...
5🥰 2
🕰🔔 3:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰           @MoaeTewahedoB
Show all...
🥰 3 1
የክርስትና መሰረት  ዘውግ አይደለም !! በጎሳ (ዘውግ) አንድነት ላይ የተመሰረተ እና ይህን ተጠቅመው በሌሎች ላይ የበላይ ለመሆን የሚሰሩ ሰውች የሚመሩት ሃይማኖት ብዙ ተከታይ ሊኖረው ይችላል ። ክርስትና በምድር ሁሉ የተበተኑ ፣ ከሁሉም ዘውጎች የተሰበሰቡ ፣ ምድራዊ ክብርን እና የበላይነትን የማይፈልጉ ፣ ለመግደል ሳይሆን የክርስቶስ ምስክሮች ሆነው ለመሞት እንደ በግ በተኩላዎች መካከል የተላኩ ሰዎች የሰበኩት ሃይማኖት በመሆኑ የዘውግ አንድነት እና የኃይል የበላይነት ከክርስትና አመሰራረት እና እሳቤ ጋር አይሄድም ። ክርስትና በምድራዊ ኃይል እና ስልጣን በሌሎች ላይ የበላይ መሆን መፈለግ ስለሚከለክል የዘውግ እና የኃይል አንድነት የክርስትና  ማኅበር ለመቀላቀል ጥሩ ምክንያት አይደለም ። ("የልቦና ችሎት" በረከት አዝመራው ) @MoaeTewahedoB
Show all...
🥰 10👍 3 1
🕰🔔 9:00 ተንስኡ ለጸሎት በዚህ ሰዓት ይህንን የምታይ ሰው የምታደርገውን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔር እያሰብን ቢያንስ አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ እግዚኦ ተሰኃለነ❖ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አቤቱ ማረን ይቅርም በለን✥ አገር ውስጥ ያላቹሁ  በስደትም በስራም እንኳን ቢሆን አንድ አባታችን ሆይ እንበል🥰           @MoaeTewahedoB
Show all...
🥰 5👍 1 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.