cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

𝗦𝗠𝗨_𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠𝗦

[ اُولٰٓـئِكَ عَلٰى هُدًى مِّنۡ رَّبِّهِمۡ وَاُولٰٓـئِكَ هُمُ الۡمُفۡلِحُوۡنَ‏ ] 𝐉𝐨𝐮𝐫𝐧𝐲 𝐭𝐨 𝐨𝐮𝐫 𝐭𝐫𝐮𝐞 𝐬𝐞𝐥𝐯𝐞𝐬, 𝐭𝐡𝐫𝐨𝐮𝐠𝐡 𝐫𝐞𝐦𝐞𝐦𝐛𝐫𝐚𝐧𝐜𝐞 𝐨𝐟 𝐀𝐥𝐥𝐚𝐡. St. Mary's university Muslim students official telegram channel.

Show more
Advertising posts
248
Subscribers
-124 hours
-37 days
-430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ጥንቃቄ ~ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ብዙ ወጣት ሴቶች በሚዝናኑባቸው ቦታዎች ትላልቅ ከተማዎች ላይ GHB የሚባል ኬሚካል ተበራክቷል። "ጋባዦች" አንድ መጠጥ ውስጥ  የGHB ጠብታ ሲጨምሩበት ተጠቂዎች (አብዛኛውን ጊዜ ሴቶች) በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ያሉበት፣ አብረዋቸው የነበሩበትን እና የተወሰዱበትን ቦታ አያስታውሱም። ገንዘብ ተከፍሏቸው የደነዘዙ ሴቶችን ለማስደፈር የሚያቀርቡ ውጣት ወንዶችም ሴቶችም ይሄንን እየሰሩ የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው። በተለይ "የቤት ልጅ" አይነት የሚባሉ (ተማሪዎች) እና ሌሎች ወጣት ሴቶች የዚህ ወንጀል ተጠቂ እየሆኑ ነው። GHB ከሰውነታቸው ወጥቶ ሲነቁ በማይታወቅ ቦታ ብዙ ጉዳት ደርሶባቸው ራሳቸውን ያገኛሉ። ምን እንደተፈጠረ አያውቁም። GHB የሰው ሕይወት ሊያጠፋ ይችላል። በከተሞች መዝናናት እና መገባበዝ ደግሞ የተለመደ ስለሆነ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። እንዲህ አይነት ወንጀሎች በቅርብ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ውጪ ከኖሩ ኢትዮጵያውያን ነው። ኮፒ "ሟር" ቢደረግ ለወገን ይጠቅማል። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Show all...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

💔 3
. . #መዓዘላህ ደሀ ወጣት ነበር፡፡ …በመንገዶች ላይ እየተዘዋወረ ይሸጣል። አንዲት ባዶ የሆነች ሴት ነበረች… ሀራምን ከመስራት አትቆጠብም… የሸይጣን ተላላኪ ነበረች … አንድ ቀን በቤቷ አጠገብ አለፈ… በበሩ በኩል ብቅ ብላ ስለሸቀጦቹ ጠየቀችውና ነገራት… እቃዎቹን እንድታይ እቤት እንዲገባ ጠየቀችው ቤት ሲገባ በሩን ቆለፈችበትና ወደ ሀራም ጋበዘችው… መዓዘላህ! ብሎ ጮኸ፡፡ … ጊዜያዊ ጣፋጭ ነገሩ ጠፍቶ ፀፀቱ በሚቀርብበት ጊዜ የሚኖረውን ሁኔታ አስታወሰ… ዚና የሰራባቸው አካላቶች… የተራመደባቸው እግሮቹ… የዳሰሰባቸው እጆቹ… የተናገረበት ምላሱ… በእሱ ላይ የሚመሰክሩበትን ቀን አስታወሰ… የእሳትን አቃጣይነትና የአላህን ቅጣት አስታወሰ… ዝሙተኞች በእሳት ውስጥ እንዲንጠለጠሉ ተደርገው ከብረት በሆነ አለንጋ ይገረፋሉ… ከዝሙተኞች አንደኛው ከቅጣቱ እንዲያድኑት ጮኾ ሲጠይቅ መላኢኮች… አላህን ሳትፈራና ይቆጣጠረኛል ሳትል(ሀራም በመስራት) ስትስቅ ስትደት-ስትፈነድቅ …ይሄ አሁን ያሰማኸው ድምፅ የት ነበር? ይሉታል… ወጣቱ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለው የተናገሩትን አስታውሰ፡፡ “የሙሐመድ ህዝቦች ሆይ! ወላሂ እኔ ማውቀውን ብታውቁ ኖሮ ትንሽን ስቃችሁ ብዙ ባለቀሳችሁ ነበር፡፡” በአንድ ወቅት ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) በህልማቸው ያዩትን አስታወሰ…ከታች ሰፊ ከላይ ጠባብ በሆነ ምድጃ በሚመስል ጠባብ ቦታ ውስጥ ወንዶችና ሴቶች ራቁታቸውን ሆነው ይጮሀሉ -ያጓራሉ… የእሳት ነበልባል ከስራቸው ይመጣባቸዋል… ነበልባሉም በመጣባቸው ጊዜ ከግለቱ ብርታት የተነሳ ይጮሃሉ… ረሱልም(ሰ.ዐ.ወ) ጂብሪል ሆይ! እነዚህ ምንድን ናቸው? ብለው ጠየቁት… ጂብሪልም፡- እነዚህ ሴት ዝሙተኞችና ወንድ ዝሙተኞች ናቸው… እስከ የውመል ቂያማ ይህ ቅጣቸው ነው፡፡” ብሎ መለሰላቸው፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ የአኼራ ቅጣት እጅግ የበረታና ዘልአለማዊ ነው… አላህ(ሱ.ወ) ምህረት እንዲያደርግልንና ሰላማ እንዲያደርገን እንጠይቀዋለን… ነፍሲያውም፡- “ስራና ትቶብታለህ!” አለችው፡፡ እሱም አዑዙቢላህ የጌታዬን ግርዶ እንዴት እዳፈራለሁ? የተከበረውና የላቀው አላህ ከበላያችን ሆኖ እየተመለከተን የማትፈቀደልኝን ሴት እንዴት እመለከታለሁ? …እንዴት ከፍጡራን እየተደበቅን ፈጣሪ ፊት እናምጻለን? …አለ፡፡ …ወደ በሩ እየተመለከተና እንዴት መውጣት እንደሚችል እያሰበ ዝም አለ… አመጸኛዋ ሴትም፡- ወላሂ የምፈልገውን ካልፈጸምክ ጮኼ ሰዎች እንዲሰበሰቡ አደርግና ይህ ወጣት ዘሎ ቤቴ ገባብኝ እላለሁ… የዚህ ጊዜ ሞት ወይም እስር እንጂ ሌላ አይጠብቅህም” አለችው፡፡ ጥብቁ ወጣት ይንቀተቀጥ ጀመር… በአላህ አስፈራራት… ምንም አልመሳት… ይህን ሁኔታ ያየ ጊዜ ከሷ የሚገለልበትን ዘዴ ማሰብ ጀመረ… ከዛም ሻወርና ሽንት ቤት እፈልጋለሁ አላት፡፡ እሷም ወደ ሽንት ቤቱ አመለከችው… መጸዳጃ ቤት ሲገባ ወደ መስኮቱ ተመለከተ… ነገር ግን በመስኮቱ ማምለጥ አይችልም… ከእሷ የሚላቀቅበትን መንገድ አሰላሰለ… ሠገራ ወደሚጠራቀምበት ሄደና ከሰገራው እያነሳ ልብሱን እጁንና ሰውነቱን መቀባት ያዘ… ከዚያም እሷ ጋር ወጣ… ያየችው ጊዜ ጮኸች… እቃውን ፊቱ ላይ ወርውራለት ከቤቷ አባረረችው… ቤቱ እስኪደርስ ድረስ ህፃናት ከኋላው ሆነው እብድ! …እያሉ ይጮሁበት ነበር፡፡ …ቤት ሲደርስ ነጃሳውን አስወገደና ገላውን ተጠበ… ከዚያም በኋላ ወጣቱ እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ሰውነቱ የሚስክ ሽታ ሽታ ይሸት ነበር፡፡ (ታሪኩን ኢብኑ ጀውዚ ጠቅሰውታል) አንተ ወጣት ሆይ እራስህን ፈትሽ? ጊዜ መልክና ገንዘብ የታደልክ ወጣት ሆይ የት ነው ያለኸው? ጣፋጭ አንደበት እንደ ወፍ ሚያምር ድምጽ ያለህ ወጣት ምን እየሰራህ ነው? እህቴ ምን እየሰራሽ ነው? ወንዶችን እያማለልሽ? ውበትሽን ቁጅናጅሽን እንዲያደንቁልሽ ብለሽ ለምን ትገላለጫለሽ? አላህን አትፈሪምን? በፍቅረኞች ስም ምን ችግር አለው እያልን ዝሙትን ምንዳፈር ሰዎች አላህን እንፍራ!
Show all...
❤ 3
#ከዋክብቶቻችን #ክፍል 2 #አብደላህ_ኢብኑ_ሰላም "ከጀነት ሰዎች አንዱ ማየት የሚሻ ሰው አብደላህ ኢብኑ ሰላምን ይመልከት"። ነብዩ(ሰዐወ) አል ሑሰይን ኢብኑ ሰላም በየስሪብ የሚኖር የአይሁድ ካህን ነበር። አይሁድ ባልሆኑ ሰዎች እንኳ ሳይቀር በከተማይቱ ህዝብ ዘንድ በጣም የተከበረ ሰው ነበር። ሰላማዊና የተረጋጋ ሕይወት የነበረው፣ በጊዜ አጠቃቀሙ በእቅድ የሚመራ፣ በመልካም ጸባዩና በበጎነቱ፣ በቀና ባህሪውና በሐቀኝነቱ ይታወቅ ነበር። አል ሑሰይን በመካ አንድ ነብይ መጣ ስለመባሉ ወሬ እንደሰማ ጉዳዩን ለማጣራት ወድያውኑ ብርቱ ፍላጎት አደረገበት። ይህንኑ አስመልክቶ ሲናገር፦ "የአላህ መልዕክተኛ(ሰዐወ) መምጣታቸውን ስሰማ ስሙን፣ የዘር ሃረጉን፣ ባህሪያቱን እንዲሁም ስለነበረበት ጊዜና ቦታ አጠያየኩ። ከዚያም ይህንን በመጽሃፎቻችን ውስጥ ከተጠቀሰው ጋር ማነጻጸር ጀመርኩ። ከነዚሁ ጥያቄዎችም በመነሳት ስለነብይነታቸው ተማመንኩ። የግዳጃቸውንም ሃቀኝነትም አረጋገጥኩ። ይሁንና ይህንን ከአይሁዶች ደበቅኩ፣ ምላሴን ያዝኩ… ከዚያም ነብዩ(ሰዐወ) መካን ለቀው ወደ የስሪብ ያመሩበት ቀን መጣ። የስሪብ ደርሰው ቁባ ላይ ሲቆሙ አንድ ሰው ሰዎችን በመጥራትና የነብዩን መምጣት በመለፍለፍ ወደከተማዋ እየሮጠ መጣ። በዚያን ጊዜ እኔ በአንድ የቴምር ዛፍ ላይ ስራ ይዤ ነበር።" ወሬውን እንደሰማሁ፦ "አላሁ አክበር!አላሁ አክበር!ብዬ ጮህኩ። አክስቴ ይህንን ውዳሴ በሰማች ጊዜ 'አላህ ይዝጋህ! ...' በአላህ ስም እምላለው ሙሴ እየመጣ መሆኑን ብትሰማ ኖሮ ግን ከዚህ የበለጠ ባልጓጓህ ነበር።' ስትል ተቃወመችኝ። አክስቴ በአላህ ስም እምላለሁ! እሱ በትክክል የሙሴ ወንድም ነው። የኢስላምን ሃይማኖት ይከተላል። እንደ ሙሴ ከተመሳሳይ መልዕክት ጋር ነው የተላከው፤ አልኳት።" "እሷም ለአፍታ ያህል ዝም ካለች በኋላ ለመሆኑ በቀደምዎቹ (ነብያት) ሲሰበክ የኖረውን ሐቅ ለማረጋገጥና የጌታውን መልዕክት ለመደምደም ይመጣል እያልክ ስትናገር የነበረው ነብይ እሱ ነው? አለች። አዎ ስል መለስኩላት።" ያለ አንዳች መዘግየትና መጠራጠር ነብዩን ለማግኘት ወዳሉበት ቦታ ሄድኩ። ወደ እርሳቸው በደንብ እስከምቀርብ በተሰበሰበው ህዝብ መሃል እያቆራረጥኩ ሄድኩ። በደንብ ቀርቤ አየኋቸው። እንዲህ ሲሉ ሰማሁ፦ "እናንት ህዝቦች ሆይ! ሰላምታን አስፋፉ፣ ምግብን አብሉ፣ ሌሊት ሰዎች በሚተኙበት ጊዜ ስገዱ፣ ጀነት ትገባላችሁ!" አጥብቄ መረመርኳቸውና ፊታቸው የአታላይ አለመሆኑን አረጋገጥኩ። "ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ፣ ሙሃመድ ደግሞ የአላህ መልዕክተኛ እንደሆነ እመሰክራለሁ" ወደ እርሳቸው ይበልጥ ጠጋ በማለት የምስክርነት ቃሌን ሰጠሁ። ነብዩ ወደኔ ዘወር ብለው፣ ስምህ ማነው? ሲሉ ጠየቁኝ 'አልሑሰይን ኢብኑ ሰላም' ስል መለስኩላቸው። አዲስ ስም በማውጣት "ከሱ ይልቅ ዐብደላህ ኢብኑ ሰላም ብለንሃል" አሉኝ። "እሺ! ዐብደላህ ኢብኑ ሰላም ይሁንልኝ። ከሃቅ ጋር እርሶን በላከው ጌታ እምላለሁ ከዚህ ቀን በኋላ ሌላ ስም እንዲኖረኝ አልሻም" በማለት መስማማቴን ገለጽኩ። ወደ ቤቴ ተመለስኩና ለሚስቴ፣ ለልጆቼና ለቀረውም ቤተሰብ ኢስላምን አስተማርኳቸው። ትልቅ ወይዘሮ የነበረችው አክስቴ ኻሊዳን ጨምሮ ሁሉም ኢስላምን ተቀበሉ። ይሁንና ፍቃድ እስከምሰጣቸው ድረስ ኢስላምን መቀበላችንን ከአይሁዶች እንዲደብቁ መከርኳቸው እነሱም ተስማሙ። ዐብደላህ ኢብኑ ሰላም ኢስላምን የቀረበው እውቀት የጠማው አዕምሮ ይዞ ነበር። በከፍተኛ ፍቅር ተጠምዶ አካሉንም ጊዜውንም በቁርዐን ላይ ያውል ነበር። ከነብዩ ጋር በጣም የቀረበ ግንኙነት የነበረው ከመሆኑም ባሻገር ብዙውን ጊዜ ከእርሳቸው አይለይም ነበር። መስጊድ ውስጥ መሰብሰብ ያዘወትሩ ለነበሩ ሶሃባዎች ይሰጥ በነበረው ጣፋጭ፣ ማራኪና ውጤታማ የማስተማር ዘዴው አድናቆት አትርፏል። አብደላህ ኢብኑ ሰላም በሶሃቦች መካከል የጀነት እንደሆነ ተደርጎ ይታሰብ ነበር። ይህ የሆነበት ምክንያት ከሃብት ሁሉ የላቀ የሆነውን፣ በአላህ ማማንና ለእሱ ተጠቃሎ መገዛትን አጥብቆ እንዲይዝ ነብዩ በለገሱት ምክር ላይ የነበርው ቁርጠኝነት ነው። አላህ ያጠንክረን . . #ቀጣይ በሌላ ሶሃባ ታሪክ እንገናኝ @smu_muslim
Show all...
❤ 2👍 1
#ምዕራፍ_አንድ #ክፍል_አንድ #ከዋክብቶቻችን '''''''''''"""""""""""""""""""""""""""""""" #አብዱረህማን_ኢብኑ_አውፍ =================== ኢስላምን በመጀመሪያ ከተቀበሉት ሰዎች መካከል አንዱ ነው። ጀነት መግባታቸው ከተረጋገጠላቸው አስር ሰዎች መካከል ነበር። ዑመር በጠና በታመሙበት ወቅት፤ ህዝበ ሙስሊሙን የሚመራውን ኸሊፋ፣ የሚመርጥ ምክር ቤት እንዲያቋቁሙ ዑመር ከመረጣቸው ስድስት ሰዎች መካከል ይገኝበታል። አብዱረህማን ሙስሊሞች በቁረይሽ እጅ ከቀመሱት ስቃይ አላመለጠም። እሱም እንደነሱ በአይበገሬነቱ ከፍተኛ ስቃይና መከራን ተቀብሏል። እንደነሱ ሁሉ እሱም እንደጸና ቆየ። የማያቋርጥ እና መሸከም የማይችሉት ስቃይ ሲደርስባቸው ወደ አቢሲኒያ ለመስደድ በተገደዱም ጊዜ አብዱረህማን አብሮ ሄዷል። በሐበሻ እያሉ ሁኔታው ተሻሽሏል፤ ጭቆናው ረግቧል የሚል ወሬ በተናፈሰ ጊዜ ደግሞ ወደ መካ ቢመለስም የተባለው ነገር ሁሉ ውሸት መሆኑን ሲያረጋግጥ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ አቢሲኒያ ተሰዷል። ከመካ ወደ መዲናም ስደት አደርጓል። ነብዩ(ሰዐወ) ከዚህ ዓለም ሲለዩ አብዱረህማን የእርሳቸውን ቤተሰብ ለመንከባከብ አደራ ተቀበለ። እነሱ  የትም ለመሄድ በፈለጉ ጊዜ አብሯቸው ይሄዳል። ሃጅ ለመፈፀም በሄዱ ጊዜ እንኳ የፈለጉት ነገር ሁሉ መሟላቱን ለማረጋገጥ ሲል አብሯቸው ተጉዟል። ይህ ከነብዩ ቤተሰብ ያገኘው የታማኝነትና በራስ የመተማመን ስሜት ምልክት ነው። አብዱረህማን ለሙስሊሞቹ፣ በተለይ ደግሞ ለነብዩ ሚስቶች ይሰጥ የነበረው እርዳታ በጣም ከፍተኛ ነበር። አንድ ጊዜ አነስተኛ መሬት በአርባ ሺ ዲናር ሽጦ ገንዘቡን በሙሉ ለነብዩ እናት(አሚና) ዘመዶች፣ ለነብዩ ሚስቶችና ለሌሎች ባለመብቶች አከፋፈለ። ዓኢሻ(ረዐ) ከዚህ ገንዘብ የተወሰነውን በተቀበለች ጊዜ፦ "ይህንን ገንዘብ የላከው ማነው?"ስትል ጠየቀች። አብዱረህማን መሆኑ ተነገራት። ይህንን ስታውቅ፦ "የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ)እኔ ከምትኩ በኋላ ማንም ለእናንተ አያዝንላችሁም! ሷቢሮች(ታጋሾችና አይበገሬዎች)ቢሆን እንጂ ብለዋል" በማለት ተናገረች። አላህ በአብዱረህማን ሃብት ላይ በረካ እንዲያወርድለት የተከበሩት ነብይ ያደረጉት ዱዓ ከአብዱረህማን ጋር አብሮ የኖረ ነው ሚመስለው። የንግድ እንቅስቃሴዎቹ በተለያዩ መንገዶች ትርፍን ያስገኙለት ነበር። ከመዲና የሚያስወጣውም ሆነ ወደ መዲና የሚያስገባው የንግድ ቅፍለት በየእለቱ እጅግ እየጨመረ ሄደ። ለመዲና ህዝብ ስንዴ፣ ዱቄት፣ ቅቤ፣ ጨርቃ ጨርቅ፣ የማብሰያ እቃዎችና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን ሁሉ ሲያመጣ፣ እነሱ ያላቸውን ማናቸውም ተረፈ ምንጮች ደግሞ ወደሌላ ሃገር በሽያጭ ይልክ ነበር። አንድ ክስተት እናጫውታችሁ፦ ፀጥ ባለችውና ሰላማዊ በሆነችው መዲና ከተማ ጠረፍ አንድ ቀን ከፍተኛ ድምጽ ተሰማ። ቀስ በቀስ እየጨመረ መጣ። በተጨማሪም የአቧራና የአሸዋ ደመና በመነሳት በነፋስ ይጥሞሎሞል ጀመር። የመዲና ሰዎች አንድ ታላቅ የንግድ ቅፍለት ወደ ከተማይቱ እየገባ መሆኑን ወዲያውኑ ተረዱ። ሰባት መቶ ግመሎች እቃ እንደተጫነባቸው ወደከተማይቱ ሲገቡና ጎዳናዎችን ሲያጨናንቁ ቆመው በአድናቆት ተመለከቱ ሁኔታውንና ምን አይነት ሸቀጦችና ምግቦች የግመል ቅፍለቱ እንዳመጣ ሰው ሁሉ መጥቶ እንዲያይ አንዱ ሌላውን ይጣራ ስለነበር ከፍተኛ ጩኸትና ረብሻ ተሰማ። አዒሻ "ይሄ በመዲና ውስጥ የተፈጠረው ነገር ምንድነው? በማለት ጠየቀች።" "ከሶሪያ ሸቀጣ ሸቀጦችን ጭኖ የመጣ የአብዱረህማን ኢብኑ አውፍ የንግድ ግመል ነው" አሏት። "ይህ ሁሉ ግርግር አንድ የንግድ ቅፍለት ፈጠረው ነው የምትሉኝ" በማለት በድጋሚ ጠየቀች። "አዎ የምእመናን እናት ሰባት መቶ ግመሎች ናቸው" አሏት። ዓኢሻ ራሷን ነቀነቀችና የአንድ የድሮ ትዕይንት ወይም ንግግር ለማስታወስ እንደምትሞክር ያህል ሆና በርቀት አተኩራ ተመለከተች። "ነብዩ(ሰዐወ)፤ አብዱረህማን ኢብኑ አውፍ እየዳኸ ጀነት ሲገባ አይቻለው ሲሉ ሰምቻለው" በማለት ተናገረች። አንዳንድ የአብዱረህማን ጓደኞች አዒሻ ያወራችውን ሃዲስ ለአብዱረህማን ነገሩት። እሱም ይህንን ሃዲስ ከአንድ ጊዜ በላይ ከነብዩ(ሰዐወ) እንደሰማ አስታወሰ ወደ ዓኢሻ ቤት ፈጥኖ በመሄድ" እናታችን ሆይ! ይህንን ቃል ከአላህመልእክተኛ(ሰዐወ) ሰምተሻልን?" ሲል ጠየቃት። "አዎ"ብላ መለሰችለት። "የረሳሁትን ሃዲስ አስታወሺኝ" ካለ በኋላ እንዲህ አለ፦ "እኔ ብችል በእርግጥ የምወደው እየሄድኩ ወደ ጀነት መግባት ነው። ይህን የንግድ ቅፍለት እንዳለ ከነሸቀጡ በአላህ መንገድ እንደምሰጥ ለአንቺ ለእናታችን እምላለሁ አላት። እንዳለውም አደረገ። ያንን የሚያህል ብዛት ያለው ሸቀጥ ለመዲናና ለአካባቢው ህዝብ አከፋፈለ። አብዱረህማን ምን አይነት ሰው እንደነበር ይህ የሚያሳይ አንድ አጋጣሚ ብቻ ነው። ብዙ ሃብት አለው። ነገር ግን ለክብረትና ለዝና ሲል ከሃብቱ ጋር የሙጥኝ አላለም። ሃብት እንዲገዛው አልፈቀደም። አብዱረህማን በሚስጥርም በግልጽም መስጠቱን አላቆመም። ከሰጣቸው መሃከል ጥቂት አሃዞችን እንመልከት፦ አርባ ሺ የብር ዲናሮች፣ አርባ ሺ የወርቅ ዲናሮች፣ ሁለት መቶ የወርቅ አውቂያህ፣ አምስት መቶ ፈረሶች በአላህ መንገድ ለመሄድ ተነስተው ለነበሩ ተፋላሚዎች፣ አንድ ሺ አምስት መቶ ግመሎች፣ ለሌላ የሙጃሂድ ቡድን አራት መቶ የወርቅ ዲናሮች ከበድር ለተመለሱና ለምእምናን እናት የሚሆን ብዛት ያለው ውርስ....ዝርዝሩ ይቀጥላል። ይህንን ድንቅ ለጋስነት አስመልክታ ዓኢሻ እንዲህ ብላላች፦ "አምላክ የጀነት ምንጭ ያጠጣው። "ይህ ሁሉ ሃብት አብዱረህማንን አላበላሸውም፤ አለወጠውምም። ከሰራተኞቹና ከረዳቶቹ ጋር በሚሆንበት ጊዜ ሰዎች እሱን ከታዳሚዎቹ መሃል ለይታው አያውቁትም ነበር። አላህ(ሱወ) እንደርሱ ያሉ ግለሰቦችን እንደማይረሳ ሲናገር፦ "እነዚያ ገንዘቦቻቸውን በአላህ መንገድ የሚለግሱ፤ ከዚያን የሰጡትን ነገር መመጣደቅንና ማስከፋትን የማያስከትሉ ለነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፤ በነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም። እነርሱም አያዝኑም"(2:262) . . #ከታሪኩ የተማራችሁትን እንዲሁም ያንና(ሶሃቦችን) ይሄን ትውልድ እያነጻጸራችሁ በመሃላችን ለተፈጠረው ርቀት መፍትሄ ምትሉቱንም ከታች ባለው ኮሜንት ሴክሽን ማድረስ ትችላላችሁ። @smu_muslim
Show all...
በቁርአን ዉስጥ የተወሱ ታሪኮች #ክፍል_25
Show all...
በቁርአን_ዉስጥ_የተወሱ_ታሪኮች_ክፍል25.pdf2.06 MB
በቁርአን ዉስጥ የተወሱ ታሪኮች #ክፍል_24 #day_24
Show all...
በቁርአን_ዉስጥ_የተወሱ_ታሪኮች_ክፍል24.pdf1.49 MB
በቁርአን ዉስጥ የተወሱ ታሪኮች #ክፍል_23 #day_23
Show all...
በቁርአን_ዉስጥ_የተወሱ_ታሪኮች_ክፍል23.pdf1.68 MB
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
🌙 42 ቀናት ብቻ 🌙
Show all...
🥰 3
በቁርአን ዉስጥ የተወሱ ታሪኮች #ክፍል_22 #day_22
Show all...
በቁርአን_ዉስጥ_የተወሱ_ታሪኮች_ክፍል22.pdf2.48 MB
🙏 2
በቁርአን ዉስጥ የተወሱ ታሪኮች #ክፍል_21 #day_21
Show all...
በቁርአን_ዉስጥ_የተወሱ_ታሪኮች_ክፍል21.pdf2.30 MB
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.