cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Circle media - ሰርክል

Advertising posts
446Subscribers
+324 hours
-17 days
+5730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የጋዛን ፍርስራሽ ለማጽዳት 14 አመታትን ሊፈጅ እንደሚችል ተመድ ገለጸ እስራኤል ሀማስን ለማጥፋት በወሰደችው ወታደራዊ ዘመቻ 2.3 ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርባትን ጠረፋማዋን ጋዛ ወደ ፍርስራሽነት ቀይራታለች። https://bit.ly/3UBpVAJ
Show all...

Tsion Maryam hosaena celebration yesterday
Show all...
የተመድ የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ፣ በመጋቢት ወር በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በቀወት፣ ኢፍራታና ጊደም እና አንጾኪያ ወረዳዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች፣ 18 ሺህ ነዋሪዎች ከቀያቸው እንደተፈናቀሉና 290 መኖሪያ ቤቶች እንደተቃጠሉ አዲስ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል። በክልሉ ኦሮሞ ልዩ ዞን በግጭት የተጎዱ 36 ሺህ 450 በላይ ሰዎች አስቸኳይ ዕርዳታ እንደሚፈልጉም ቢሮው ገልጧል። በክልሉ በቀጠለው ግጭት ሳቢያ፣ 4 ሺህ 178 ትምህርት ቤቶች እንደተዘጉም ቢሮው የጠቀሰ ሲኾን፣ በምሥራቅና ምዕራብ ጎጃም እንዲኹም በደቡብ ጎንደር ዞኖች ብቻ 89 በመቶዎቹ ትምህርት ቤቶች በግጭቱ ሳቢያ ዝግ ናቸው ብሏል። ድርጅቱ በኢትዮጵያ አሁን ላይ 21.4 ሚሊዮን ዜጎች እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ጠቅሶ ከእነዚህ ውስጥ 15.8 ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ብሏል። ይሄን ለማድረግ አጠቃላይ 3.2ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ገልፆ እስካሁን 287ሚሊዮን ዶላር መሰብሰቡን ገልጿል።። ከዚህ በተጨማሪ በቀጣይ በሚኖረው ዝናብ 1ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው ሊፈናቀሉ እንደሚችሉም ድርጅቱ አዲስ ባወጣው ሪፓርት ገልጿል።
Show all...
በአዲስ አበባ ባለፉት 9 ወራት የተጋቡ አዳዲስ ጥንዶች ቁጥር የቀነሰ ሲሆን ፍቺ እና ልደት ደግሞ መጨመሩን የከተማዋ የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት ኤጀንሲ ተናግሯል፡፡
Show all...
በርካታ የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ‼️ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንዳስታወቀው ከሆነ ከሚሰጣቸው ሀላፊነት እና ስልጣን ውጪ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በርካታ የፀጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን እና ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ይፋ አድርገዋል። የከተማዋ አንዳንድ የፀጥታ አካላት በአማራ ክልል የተጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተገን በማደረግ ህገወጥ እስራት እና እንግልት እንደፈፀሙ ሪፖርተር ጋዜጣ በዘገባው መጥቀሱን አዩዘሀበሻ ተመልክቷል። የአዲስ አበባ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በአማራ ክልል የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአዲስ አበባ እንደማይተገበር ገልፀው ከተማው ውስጥም ጉዳዮች ሲኖሩ በየትኛውም ሰዓት ኦፕሬሽን እንደሚሰራ ጠቁመዋል። በቅርቡ በተደረገው ፍተሻ ከ140ሚሊዮን ብር በላይ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተጠቁሟል። በዚህም 1.5 ሚሊዮን ብር በቁማር የተሰበሰበ ብርን ጨምሮ ሌሎች ሀሰተኛ የብር ኖቶች ተይዘዋል ተብሏል። ከዚህ በተጨማሪም ከ16,000 በላይ ተተኳሿችን ጨምሮ የስውር ትጥቅ እስከ ትልልቅ መሳሪያዎች መያዛቸው ተገልጿል። ለስራ ፍለጋ እና ለሌሎች ጉዳዮች ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ የሰዎች ብዛት በአጅጉ መጨመሩን ቢሮዉ አስታውቋል። ፈጣንና ዕውነተኛ ዕለታዊ መረጃዎችን ለመከታተል፤ የሰርክል ሚዲያን ይቀላቀሉ! 👉ለወቅታዊ መረጃዎች ቻናላችንን join አድርጉ❗️ https://t.me/mneny1
Show all...
<< ተግባር ከሌለ መወያየት ብቻውን ባዶ ተስፋ ነው >> - ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ << መወያየት ብቻውን በቂ አይደለም፤ መተግበር እንዳለበት >> ተናግረዋል። ፕሬዝደንቷ ይሄን ያሉት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሴቶችን ተሳፎ በተመለከተ በዛሬው ዕለት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው። << በኢትዮጵያ መናናቅ እና የት ይደርሳል ማለት ችግር ሲፈጥር እየታየ መሆኑንም >> ፕሬዝደንቷ አመልክተዋል። << መወያየት ብቻውን በቂ አይደለም >> ያሉት ፕሬዝደንቷ << መተግበር መቻል እንደሚኖርበት በግልፅ ቋንቋ ተናግረዋል። አክለውም << እንደ ሀገርም የመወያየት ችግር ባይኖርም መሠረታዊ ችግሩ አፈፆፀም መሆኑንም >> አብራርተዋል። ውይይቶች ተሞክሮዎች ሁሉ መሬት ወርደው ካልተተገበሩ ባዶ ተስፋ መስጠት ነው ያሉን ሳህለወርቅ የምክክር ሂደቱ ችግሮችን በዘለቄታዊነት ለመፍታት የሚደረግ ጥረት እንጂ ለተወሰነ ጊዜ የተወሰኑ ሲሉ የጠሯቸውን ሁኔታዎች ለማስተገሻ እንዳልሆነ ግልፅ ማድረግ ይገባል ብለዋል። የማይሆን ተስፋ ሆኖ እንዳይታይም በጣም ሲሉ በገለፁት ደረጃ መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግም አመላክተዋል። << ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ መስራት ያስፈልጋል በማለትም ብዙ ጊዜ የሚስተዋለው እንወያይ እንጋገር ከማለት የዘለለ አይደለም >> ሲሉ ተችተዋል። ሳህለወርቅ እንደሚሉት << አሁን በተለይ መናናቁ እና የት ይደርሳል መባባሉም ለሀገሪቷ ችግር እየሆነ መጥቷል >> ሲሉ አንክሮ ሰጥተዋል። በመሆኑም እንደሀገር ያለብንን ችግር ለመቅረፍ የሚረዳው አማራጭ ሰው ያለውን ሁሉ ሓሳብ እንዲያዋጣ ማበረታታት እና መረዳት ብሎም መግባባት ነው ብለዋል። በንግግር ፋንታ ቂምንና ማግለልን ብሎም መሰል ነቀፌታዎችን ማስወገድ ያስፈልጋል ሲሉ መክረዋል። በሌላ በኩል ህዝብ ማዕከል ያደረገ ውሳኔ ሲሰጥ ሴቶችን አካታች ማድረግ ግዴታ መሆኑን አስቀድመው በህወሓት ሃይሎች እና በፌደራሉ መንግስቱ መካከል የነበረውን ጦርነት በቋጨው የፕሪቶርያ ዘላቂ ግጭት ማቆም ስምምነት ሴቶች አለመወከላቸውን ጠቁመዋል። በጦርነቱ ሂደት ውስጥ ሴቶች ደርሶባቸዋል ያሉትን ከፍተኛ ጉዳትም እስታውሰዋል። ይሁን እንጂ አሁን ላይም በተመሳሳይ መልኩ ሀገሪቷ ውስጥ ውጊያዎች፣ ጦርነቶች፣ መገዳደልና መፈናቀል መኖሩን አስቀድመው በጥቅሉ ከጦርነት ካለመግባባት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች መኖራቸወን ገልፀዋል። በመጨረሻም በርትቶ መስራት፣የተናገሩትን መኖር እንደሚገባ አስገንዘበው ስራችን የሚወሰነውም የህዝቡን ኑሮ በመለወጥ ላይ፣ ሰላምን ለማስፈን መሆኑን አስቀድመው ሰለም ደግሞ << በመደለል >> ብቻ የሚገኝ አይደለም ብለዋል። ምንም እንኳን ሳህለወርቅ ከመወያየት ባሻገር ተግባር ግድ እንደሚል አፅዕኖት ቢሰጡም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን < ምክክርሩን > ሲያጠናቅቅ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ምክረሃሳቡን ከማቅረብ በዘለለ የመተግባር ስልጣን እንደሌለው በታህሳስ 2014 ዓ.ም የጸደቀው የማቋቋሚያ አዋጅ ያስረዳል። asham tv
Show all...
😁 2
👍 5
የስዊድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር Tobias Billström በተገኙበት ዛሬ Alexandra Völker የአማራን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ በተመለከተ የስዊድን መንግስት ምን እየሰራ ነው ?በማለት ሞግታለች:: በስዊድን ፖርላማ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ጭፍጨፋ እንዲቆም ተጠየቀ: በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጸመ ያለው ግፍ እንዲቆም ወንጀለኞች እንዲጠየቁ እና ሰላም እንዲሰፍን ጥሪ አቅርባለች::
Show all...
ከተገደለችው እናቷ ማህጸን በህይወት የወጣችው ህጻን ህይወቷ አለፈ በእስራኤል የአየር ጥቃት ከተገደለችው እናቷ ማህፈን በህይወት የወጣችው የጋዛዋ ህጻን የተወሰነ ቀናት ከቆነች በኋላ ህይወቷ ማለፉን ዶክተሩ ተናግረዋል። https://bit.ly/44fVx22
Show all...
ከተገደለችው እናቷ ማህጸን በህይወት የወጣችው ህጻን ህይወቷ አለፈ

በእስራኤል የአየር ጥቃት ከተገደለችው እናቷ ማህፈን በህይወት የወጣችው የጋዛዋ ህጻን የተወሰነ ቀናት ከቆነች በኋላ ህይወቷ አለፈ