cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

pics📷

🎶musics🎶 📷pics📷 😃memes😃 😂funny vedio😂 🎬tik tok and dance🎬 ❤lovely qoutes❤ ✍️best pomes✍️ 🎉H.B.D wishes🎉 @funnyvideo93 ❤😍 join All much love 💞 @Christiangroups1 join❤ promotion...... owner @Nati_sha

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
259Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

HBD ❤ Natan
Show all...
😉
Show all...
Happy birth day🎉 kale🤞✌️
Show all...
እስኪ meme ይሰራ የሚል🙌🙌
Show all...
​​​​🌿🌿"ጤዛዉ ፍቅሬ"🌿🌿 🍂🍂ክፍል አስራ አንድ🍂🍂 ✍✍(biniyam) . .... "ወይዬ ሀቢቢ..." አለችዉ። በአይኖቿ አይኖቹን ስታይ የመጀመሪያዉን ሀቢብ ሆኖ አገኘችዉ። ፍቅርን እንጂ ጸብን የማያዉቀዉ ሀቢብ! - ፍፁም ተቀይሯል። ያን መጥፎ ባህሪ አስወግዶ ወደራሱ ማንነት ተመልሷል። ..ያን ጣፋጭ ጠረን ካገኘዉ ቆይቷል። ፍቅሯን ሁሌም ባትነፍገዉም በራሱ ሽሽት ግን ገላዋን ከማቀፍ ፤ ጸጉሯን እየደባበሰ ከንፈሯን ከመሳም ርቆ ኑሯል። ሁለቱም ተርበዋል። ከየት እንደሚጀምርና እንዴት ሊያስደስታት እንደሚችል ተደናግሮታል። ......"ታዉቂልሽ ማሬ?" አላት። ......"ምኑን ሀቢቢ?" ......"ልቤ ማፍቀር ከሚችለዉ በላይ እንደማፈቅርሽ!" ድምጹ ልስልስ ያለ ለጆሮ የማይጎረብጥ ፤ ሀሴትን የሚያፈናጥጥ በመሆኑ ዉስጧ በፌሽታ ተሞላ። አይታዉ የማታዉቀዉ አለም ዉስጥ የገባች መሰላት። ምንም ጠራራ ፀሐይ የወጣበት ከቀኑ ስምንት ሰአት ቢሆንም የቤቱ በርና መስኮቶች ተዘጋግተዉ ቤቱ ጨልሟል። እንደተከዘ ህፃን ልጅ ቡዝዝ ፍዝዝ ብላ የምትበራዉ መብራት ፎዚን በዉብት ላይ ዉበት አክሎላታል። .... እጆቿን አንገቱ ላይ ጣል አድርጋቸዉ እሱም ቀጭን ወገቧን በእጆቹ ይዞ ጣፋጭ ጠረኗን እየማገ አንገቷ ስር ዉትፍ ብሏል።.... . . .... ነርሶቹ ሀምዛን አይተዉት ከሄዱ በኃላ በመኪያና በሀምዛ መካከል የዝምታ አዋጅ የተጣለባቸዉ እስኪመስል ድረስ ተኮራርፈዉ ዝምታ በመካከላቸዉ ነግሷል። ቀደም ብሎ ዶክተሩ መኪያን አስጠርቷት የሀምዛ እግሮች ወደ ቀድሞ ሁኔታዉ መመለስ እንደማይችልና ቀሪ ህይወቱን ዊልቸር ላይ ሆኖ እንደሚያሳልፍ አርድቷታል። አላርፍ ያለች ነርስ ደግሞ በማያገባት ጥልቅ ብላ...."አይይ ይሄ እግር ቢቆረጥ እንጂ ከዚህ በኃላ እንኳ አያገለግልም።" ብላ በሁለቱም ፊት ላይ ጨለማ ጥላዉን እንዲያጣላ ፈረደችባቸዉ። ሁለቱም ተፈራርተዋል። መኪያ ቀና ብላ ሀምዛን ስታዬዉ ከአጠገቧ የሀምዛ ዛቱ እንጂ ሙሉ ሆኖ ከአጠገቧ እንደሌለ ፊቱ ላይ ተመለከተች። ..."ይሄዉልህ ዉዴ...." ብላ ጸጥታ የነገሰችበትን ክፍል ፈራ ተባ እያለች ምናልባት ከሰማኝ ብላ ንግግሯን ጀመረች። ነገር ግን ሀምዛ አልነቃም። የሚጓዝበት አለም የማይገፋ ፤ የሚሄድበት መንገድ የማያልቅ ፤ የሚቀዝፈዉ ዉቅያኖስ ክንድን የሚፈትን... ማዶን ተሻግሮ ሲመለከተዉ እንደ ሀረግ ዉስብስቡ የበዛ ሆኖ ታየዉ። ....."ጠንካራ አልነበርክ'ዴ ዉዴ? ለምን በቀላሉ ትሸነፋለህ?" እያለች የዉስጧን ህመም ፤ የባሏን ጉዳትና ስቃይ በዉስጧ አምቃ ይዛ እሱን ለማበረታታት ተቀምጣ ከነበረበት እግርጌዉ ወደ ራስጌዉ ተጠጋች። ....."ትዕግስት ማድረግኮ አለብህ ሁቢ ... ደግሞስ አላህ የወሰነዉና እሱ የፈለገዉን የሚያደርግ የሚያደርግ ጌታ መሆኑን ዘንግተህዉ ነዉ?" በእጇቿ የሀቢብን አገጭ ይዛ ወደ'ሷ አዞረችዉ። ፊቱ ኩስምን ፤ ሰዉነቱ ምንምን ብሏል። "ሀቢቢ አናግረኛ!!... አላህ እንደሚወድህ ለምን ትረሳለህ? እሱ የወደደዉን ባሪያዉን ወንጀሉን ሊያብስለት ሲፈልግ አይደል የሚፈትነዉ። ያ የሚሆነዉ ደግሞ ተወዳጁ የአላህ ባሪያ በሚደርስበት ፈተና ላይ ሶብር ሲያደርግ ነዉ። ሶብር...!!።" ታወራለች እንጂ ከልቡ አልሰማትም ፤ ከዉስጡ አላዳመጣትም። እንደምታወራ እንጂ ምን እንደምታወራ ፤ ስለምን እንደምታወራና ለምን እንደምታወራ በዉል አያዉቀዉም። "ሀምዛ... ሀምዛ" አለችዉ። በተዳከመ ድምጽ "ወይ መኪ" አላት። ...."እስኪ ለሀቢብ ደዉልልት" አለችዉ። ምናልባት ይሄን ትካዜ ሀቢብ መጥቶ ቢያጽናናዉና ስለሌላ ጉዳይ እያወራዉ የተወሰነ ቢረሳዉ ብላ በመመኘት ነዉ። ሀምዛ "እሺ" አላትና ወደ መስኮቱ አቅጣጫ አንቱን ቀለበስ አደረገ። .... "ደዉልለታ ሀምዛ" እሺ አባባሉ እሷን ላለመቃረን አንጂ ለመደወል እንዳልሆነ ገብቷታታል። ..."እንደዉም እኔ እደዉልለታለሁ" ብላ የእጅ ቦርሳዋን ፍለጋ ተነሳች። እሱ ግን የምትናገረዉንና የምታዘዉን ከማዳመጥ ዉጭ ምንም አይነት ምላሽ አልሰጣትም። ስልኳን ከቦርሳዋ አወጣችና የሀቢብን ቁጥር ተጫነች 091471። የደወሉላለቸዉ ደንበኛ........ "ኤጭ ይቺ ደግሞ...." ብላ ብላ ስልኩን ዘጋችዉና እንደገና ደወለች። . . .... ሀቢብና ፎዚ የጦፈ ፍቅር ዉስጥ ናቸዉ። አንዳቸዉ አንዳቸዉ ላይ ተለጣጥፈዉ አንድ አካል ፤ አንድ አምሳል እስኪመስሉ ድረስ ተቃቅፈዋል። በመካከላቸዉ ማስቲሽ ያጣበቃቸዉ እስኪመስል ድረስ ሙቀቱ አቆራኝቷቸዋል። የፎዚ ትንፋሽ ቁርጥ ቁርጥ እያለ ስሙን በየመሀሉ ትጠራዋለች። የሀቢብ ስም በሙሉዉ ቢጠራም የተቆላመጠ ይመስላል። ሀቢብ... ሀቢቢ... ሁቢ የሀቢብ ወላጆች ለፎዚያ መጥራት እንዲመቻት ተመካክረዉ ያወጡለት እስኪመስል ድረስ ገርቶላታል። ሀቢብ ከዚህ በፊት ፎዚን የማያዉቃት መስሎ እስኪሰማዉ ድረስ ጣፍጭ ሆናለታለች። ፀጉሯን እየደባበሰ ፤ መላ አካላቶቿን በጣቹ እያመሰ የቱን ስሞ የቱን እንደሚተወዉ ግር አለዉ። ከናፍሮቿ....፤ ጉንጮቿ....፤ የአንገቷ ጠረን ... እያንዳንዱ ገላዋን ማር የተቀባችዉ ይመስል የሀቢብ ከናፍሮች ፎዚን አልጠግባት ብለዋል። አንዱን እየሳመ ፤ አንዱን እየላሰ እንደተቃቀፉ ከፎዚ ኃላ ከነበረዉ ሶፋ ላይ ተያይዘዉ ወደቁ።.... . . . ..... መኪያ የሀቢብ ስልክ ባለመስራቱ እንደመበሳጨት ብላለች። "ቆይ አሁን ስለኩን ለምን ዘጋዉ?" ብላ የሀምዛን አይኖች አየቻቸዉ። ሀምዛም "በፎዚያ ሞክሪ..." አላትና ያቋረጠዉ ህልም እንዳለ አይኖቹን ግጥም አደረጋቸዉ። ትእግስት በማጣትና ተስፋ በመቆረጥ መካከል እንዳለ ሁኔታዉን አይቶ መገመት አያዳግትም። ነገር ግን መኪያም ተመሳሳይ ስሜት ዉስጥ በመሆኗ የሀቢብን መምጣትና ሀምዛን እንዲያበረታዉ ተመኘች እንጂ የሀምዛን ሁኔታ ለመረዳት አቀበት ሆኖባታል። ከብዷታል። .... "የፎዚን ስልክ ቁጥርኮ አላዉቀዉም" አለችዉ። .... "09 23 " ብሎ ነገራት። መኪያም ወደ ፎዚ ስልክ ደወለች። . . . ..... "ሙሀመድ ነቢና ኡሙሁ አሚና አቡሁ አብደላህ....." እያለ የሚጠራዉ የፎዚያ ስልክ አቃጨለ። ነገር ግን ሀቢብም ፣ ፎዚያም አልሰሙትም። የጋለ ስሜት ዉስጥ ናቸዉ። እንኳን የስልክ ጥሪና አጠገባቸዉ ብየዳጠቤት ቢከፈት የግላይንደር ድምጽ የሚያነቃቸዉ አይመስሉም። ለሀቢብ ከዚህ ድምጽ በላይ በለሰለሰ ድምጿ 'ሁቢ' የምትለዉ የፎዚያ ጥሪ ገኖ ይሰማዋል። ይሳሳማሉ ... እ.... እ.... . . . ...."አትመልስም" አለችዉ። ...."ተይዉ በቃ ምልክቱንጨስታየዉ መልሳ ትደዉላለች" ...." ቆይ ደግሜ ልደዉል..." አለችና በድጋሜ ደወለች። . . "ሙሀመድ ነቢና ኡሙሁ አሚና አቡሁ አብደላህ...." ╔═══❖•💕💕•❖═══╗ ይቀጥላል ከ 30 ❤️ like በኋላ ╚═══❖•💕💕•❖═══╝ ❥............🍃👑👑?..............❥ 🌹ቶሎ እንዲቀጥል Like @funnyvideo93
Show all...