cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሙሐመድ የንፅፅር ማህደር

የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደኾነች ቃል ኑ፡፡(እርሷም) አሏህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአሏህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፣በላቸው። እምቢ ቢሉም፦እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው።3:64 መልካም የማንበብና የማነፃፀር ጊዜ ይሁንሎ!

Show more
Advertising posts
975
Subscribers
+124 hours
+77 days
+830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ክፍል 4 አርዮሳውያን (250-336 ዓ.ል) በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ፥ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡       የአስተምህሮቱ ዋና አራማጅ የእስክንድርያው ቄስ አርዮስ ሲሆኑ የተወለዱትም በሊቢያ ነው። አርዮስ ወደ ግብፅ በመሄድ በትክክለኛው የወንጌል ትምህርት ላይ ጥናትእንዳደረጉናበዋናነትም ከአንፆኪያው ሰማዕቱ ፃድቅ ሊሲያን ዘንድ እንደተማሩ ይነገራል። ፃድቁ ሉሲያን ከአርዮስ በፊት የነበሩ አርዮስ ይሏቸዋልም።       የካቶሊኩ የታሪክ ተመራማሪ ዋረን ካሮል ስለ አርዮስ በፃፈው ‹‹ቀጭንና ረጅም ሲሆኑ የሚማርክ ገፅታና የጠራ አነጋገር አላቸው። ሰዎች በስብዕናቸው ልቀትና በእውቀታቸው ምጥቀት ይማረኩላቸዋል።››       በማለት ይገልፃቸዋል።(1)       አርዮስ ኢየሱስ እንደማንኛውም ሰው ፍፁም ፍጡር ሲሆን ለፈጠረውም ለአብ ተገዥ ነው በማለት አስተምረዋል። ኢየሱስ የአብ ልጅ መባሉ አምላክነቱን እንደማይገልፅ ‹‹አብ ከኔ ይበልጣል›› በማለት የመሰከረውን በማስረጃነት ይጠቅሳሉ። ‹‹አብ ወልድን እንደ ልጁ ከያዘው ወልድ ለልጅነቱ መነሻ አለው ማለት ነው፤ ይህም ወልድ ያልነበረበት ጊዜ መኖሩን ያሳያል። ስለዚህም ወልድ ከምንምነት የተገኘ ፍጡር ነው።››       በማለት የሥላሴ አስተምህሮት ስህተት መሆኑን ለአትናቴዎስና ለተከታዮቹ በማስረጃነት አቅርበዋል።(2)       ይህም በአብያተክርስቲያናት መካከል ያለው ሰፊ የአስተምህሮት ልዩነት ለኒቂያ ጉባዔ መጠራት ምክንያት ሆኗል። የባዛንታየኑ ንጉስ ቆስጠንጢኖስ በጊዜው ክርስትናን የማይቀበል አረማዊ ቢሆንም በግዛቱ ውስጥ የተፈጠረውን የእምነት ክፍፍል ለፖለቲካ ትርፉ ሲል መቋጫ ሊያበጅለት ጉባዔው እንዲካሄድ አድርጓል። በጉባዔው ላይም ከፍተኛ ውግዘት የደረሰባቸው የእስክንድርያው ቄስ አርዮስ ‹‹ወደ ትክክለኛው የኢየሱስ ትምህርት እንመለስ። ኢየሱስ አንድም ቀን አምላክ ነኝ ሲል ያላስተማረም። በሥላሴ አራማጆች አምላክ መደረጉ ፍፁም ስህተት ነው። ኢየሱስ እንደማንኛውም ሰው የአምላክ ፍጡር ነው።››       በማለት ማስተማራቸውትችና ስድብ አሸልሟቸዋል። በስተመጨረሻ የአርዮስን አስተምህሮት የሚገልፁ መጽሐፍት እንዲቃጠሉና ይዟቸው የተገኘ ሰውም በሞት እንዲቀጣ ንጉሱ ውሳኔውን አሳልፏል።(3)       አርዮስም ከውግዘቱ በኋላ ጥገኝነት ወዳገኙበት የፍልስጤም ምድር ሄደው ማስተማራቸውን ቀጥለውበት እንደነበር ይነገራልም። በዚያም እያሉ በ327 ዓ.ል የእስክንድርያው ጳጳስ ‹‹እስክንድር›› በመሞቱ በምትኩ አትናቴዎስ ይሾማል። ንጉስ ቆስጠንጢኖስም በአርዮስና በአትናቴዎስ መካከል ያለው ልዩነት ለማርገብና በመካከላቸው የትብብር መንፈስ እንዲፈጠር አርዮስን ወደ ቤተመንግስቱ እንዲመጡ ይጋበዛሉ። አዛውንቱ አርዮስም ግብዣውን ተቀብለው በቁስጥንጥንያው ቤተመንግሥት በተገኙበት ሌሊት ድንገት በተፈጠረ ህመም በአፋቸው ብዙ ደም ከፈሰሳቸው በኋላ በ86 ዓመታቸው ህይወታቸው ልታልፍ ችላለች።       የአርዮስ አሟሟት በሥላሴ አራማጆች የአምላክ ቁጣ ነው ሲያሰኝ በአንድ አምላክ የሚያምኑት ተከታዮቻቸው ግን ያለጥርጥር በምግብ ተመርዘው ነው ይላሉ።(4)       አርዮስ በድንገት በመሞታቸው ክፉኛ ያዘነው ንጉስ ቆስጠንጢኖስም የአሟሟታቸውን ጉዳይ የሚያጠና ቡድን አቋቁሞ እንደነበረ ይጠቀሳል። በምርመራው የአትናቴዎስ እጅ እንዳለበት በመረጋገጡ ለውግዘት ተዳርጓልም። ከዓመት በኋላምንጉስ ቆስጠንጢኖስ የአርዮስን ትምህርት ተቀብሎ በኒቆዶሚያው ጳጳስ ኢዮሲበስ እጅ እንደተጠመቀና እምነቱን እንደያዘ መሞቱ በታሪክ ተዘግቧል።(5)       ከአርዮስ ሞት በኋላ የእምነቱ ተከታይ የነበሩት በአብዛህኛው የሰሜን አፍሪካና የሜድትራኒያን አካባቢ ሕዝቦች ኢስልምና ሲመጣ ተልዕኮውን በቀላሉ ሊቀበሉት ችለዋል። በዚህም የካቶሊክ ሊቃውንት ነቢዩ ሙሐመድን (ዐሰወ) ዳግማዊ አርዮስ ይሏቸዋል።       በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በአገረ እንግሊዝ የሚገኙ ‹‹የቅድስት ካቶሊክ እና የአርዮሳውያን ሐዋርያት ቤተክርስቲያን›› የአርዮስን አስተምህሮት እንደሚከተሉ ገልፀዋል። ነገር ግን አርዮስ የሚቀበሏቸውን የማርያምን በተዓምር መፀነሷንና የኢየሱስን በአካሉ ወደ ሰማይ ማረግ አይቀበሉም። ይልቁንም ኢየሱስ ከዮሴፍና ከማርያም የተገኘ የስጋ ልጅ መሆኑንና ወደ ሰማይ ያረገውም በመንፈስ ብቻ እንደሆነ ያስተምራሉ።       የይሆዋ ምስክር ተከታዮችም ‹‹የዘመኑ አርዮሳውያን›› የሚል ስያሜ የተሰጣቸው ሲሆን ‹‹ወልድ አብን ፍፁም ያውቀዋል።››       የሚለው አስተምህሮታቸው ከአርዮስ የተለየ ያደርጋቸዋል። አርዮስ አብ ለሰዎች በፈቃዱ ካሳወቃቸው ውጭ እውቀቱም ይሁን ስራው በወልድም ቢሆን በሌላ አካል አይመረመርም ይላሉ። መንፈስ ቅዱሳን በተመለከተ ደግሞ የይሆዋ ምስክሮች ‹‹እግዚአብሔር ፈቃዱን የሚፈፅምበት ኃይል ነው›› ሲሉ አርዮስ ግን መንፈስ ቅዱስ ‹‹ሰው ወይም የተመረጠ መልዓክ›› ሊሆን በማለት አስተምረዋል።       በብዛት በአሜሪካን የሚገኙትና ጥንታዊ የአካባቢውን የእምነት ፍልስፍናዎች እንደያዘ የሚታመነውን የጆሴፍ ስሚዝ (1830) ‹‹ሞርሞን›› የተሰኘውን መጽሐፍ እንከተላለን የሚሉት ‹‹Church of Jesus Christ of Latter day Saints›› ተከታዮችም የአርዮስን አስተምህሮት እንደሚከተሉ ይነገራል። ይሁን እንጅ አብዛሃኛው የእምነታቸው መመሪያዎች ከአርዮስ እንደሚለይ ጥናት ያደረጉ ሰዎች ፅፈዋል።(6) __ (1) Warren H. Carroll (1987). “The Building of Christendom” (History of Christendom, Vol 2), pp.10 (2) John McClintock (1867). “Cyclopedia of Biblical, Theological and Ecclesiastical Literature”(Vol.7), p. 45. (3) Wisconsin Lutheran College (2010).“Fourth Century Christianity: Edict by Emperor Constantine against the Arians   (4) Edward Gibbon (2012). “The History of the Decline and fall of the Roman Empire” (Vol 8)   (5) Vasilief, Al (1928).“History of the Byzantine Empire: The Empire from Constantine the Great to Justinian” (6) Daniel S. Tuttle (1981). Mormons A Religious Encyclopedia: 1578 ------------------------------Ω-------------------------------------- https://t.me/muhammed6964 ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
ክፍል 3 ሥላሴ በቀደምት ክርስትና በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ፥ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡       ክርስትና ዛሬ ላይ ያለውን አቋም ከመያዙ በፊት በኢየሱስ ማንነት ላይ የተለያየ አመለካከት ያላቸው በርካታ የክርስትና ቡድኖች ተፈጥረው እንደነበረ በታሪክ የተመዘገበ እውነታ ነው። ሁሉም ቡድኖች (አንጃዎች) ታዲያ የየራሳቸው የሆነ የኃይማኖት መመሪያ ሲኖራቸው የሚጠቀሙበትም ወንጌል አንዱ ከሌላው የተለየ ነበር። እኛም ከርዕሳችን ጋር የሚዛመዱትንና የሥላሴን አስተምህሮት አመጣጥ ታሪክ ለመረዳት ንድፈ ሃሳብ ይሰጡናል ያልናቸውን ጥቂቱን እንጥቀስ።የአይሁድ ክርስትና       የአይሁድ ክርስቲያኖች ከሁሉም ቀደምት የሚባሉት ሲሆኑ ኢየሱስ ከፈጣሪ የተላከ ነቢይና ምንም ዓይነት መለኮታዊ ስልጣን እንደሌለው በፅኑ ያምኑ ነበር። እነዚህ ሰዎች የራሳቸው የሆነ ወንጌል ሲኖራቸው ለሌሎቹ ወንጌሎች ምንም ዓይነት እውቅና አይሰጡም ነበር።       ኢየሱስ አጥባቂ አይሁድ እንደሆነ የሚያምኑት እነዚህ ሰዎች በወንጌል ከተሻሻሉት የብሉይ ህግጋት በስተቀር በአንድ ብቸኛ አምላክ ማመን የኢየሱስ ዋነኛ አስተምህሮት እንደሆነ ይመሰክራሉ። የኋላ ኋላ እነዚህ ህዝቦች በአምላክ ሶስትነት ላይ መሰረቷን በጣለችው የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን አስገዳጅ ጫና የተነሳ ተበታትነው ሊጠፉ ችለዋል።(1) ማርኪዮናይት ክርስትና (150-200 ዓ.ል)       ማርኪዮን በተባለ ቱርካዊ ሰው የተመሰረተ እምነት ሲሆን የጳውሎስን አስተምህሮት ይቀበላል። ከጳውሎስ ትምህርት የተለየ የሚያደርገው ደግሞ በሙሴ እግዚአብሔርና በኢየሱስ አምላክነት መካከል የባህርይ ልዩነት አለ ብሎ ማመኑ ነው።       ‹‹የሙሴ እግዚአብሔር ጨካኝ ነው፤ በኦሪት ላይ የተፃፉት መመሪያዎች ለሰዎች በጣም አስቸጋሪ የሆኑ ህግጋት ናቸው፤ ኢየሱስ ግን በጣም አዛኝ ነው፤ ሰዎችን ከህግ ፈተና አውጥቷቸዋል፤ በእሱ በማመን ብቻ በሞቱ እንዲድኑ ምክንያት ሆኖላቸዋል።››       ሲሉ ያስተምራሉ።       ኢየሱስ በምድር ላይ ይሰራው የነበረው ስራ ሁሉ ስጋ ለብሶ ስለመጣ ለማስመሰል ብሎ እንጅ ምንም ዓይነት ሰዋዊ ባህርይ ኖሮት አይደለም የሚል እምነትም ነበራቸው።(2) ጊኖስቲክ (2ኛው ክ.ዘ)       የዚህ እምነት አራማጅ የነበረው ቫሌኑቲስ ከ100-160 ዓ.ል የኖረ ፈላስፋ ሲሆን የሙሴ እግዚአብሔር እና ኢየሱስ በመለኮተ ባህርይ ይለያያሉ የሚለውን የማርክዮናይት አስተምህሮት ይቀበላል።       ጊኖስቲኮች ኢየሱስ ስጋ የለበሰው ሰውነቱ ሲሆን ክርስቶስ ደግሞ በውስጡ ያለው መለኮታዊ መንፈሱ ነው ብለው ያምናሉ። አስተምህሮታቸውም በሶርያ፣ ቱርክ፣ ሮም እና በሜድትራኒያን አካባቢ ተዳርሶ የነበረ ሲሆን ሥላሴ ስለሚባለው ጉዳይ ግን እንደ ማርክዮናይቶች ምንም ዓይነት እምነት እንዳልነበራቸው ታውቋል።(3) ቀዳማይ-ኦርቶዶክስ (ከ2ኛው-3ኛው ክ.ዘ)       የሐዋርያት አባት በመባል የሚታወቁትና የሥላሴን ትምህርት በክርስትናው ዓለም እንደሰበኩ የሚነገረው ሶስተኛው የአንፆኪያ ፓትርያርክ አግናጥዮስ (ስማቸው ከላይ የተጠቀሰ) የእምነቱ አራማጅ ከሆኑት በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ። ኢየሱስ ከማርያምና ከዮሴፍ የተወለደ የስጋ ልጅ እንደሆነ ያምኑ ነበር። ኢየሱስ ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ ነው ብለው ቢቀበሉም ሁለት የተለያዩ ባህሪያት እንጅ ውህድ የሆነ አንድ ባህርይ አለው የሚለውን አለመቀበላቸው ከሌላው ኦርቶዶክስ ለየት ያደርጋቸዋል። የአዲስ ኪዳን ታሪክ አጥኚ የሆኑት ኢህርማን ቀዳማይ-ኦርቶዶክሶች የአይሁድ አስተምህሮትንና ክርስትናን አጣምረው የሚቀበሉ ቀደምት የክርስትና ቡድኖች ናቸው ይላሉ። የበርናባስ ወንጌልን መቀበላቸውም ሌላው ለየት የሚያደርጋቸው ነው።(4) ሴባሉሳውያን       በእነዚህ ሰዎች አስተምህሮት አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ በባህርይ አንድ ሲሆኑ ልዩነታቸው በስም ብቻ ነው። በዚህም የተነሳ ኢየሱስ በተሰቀለበት ወቅት አብም በአካል አብሮት እንደተሰቀለና ስቃዩንም እንደተሸከመ ይታመናል።       የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከምታምንበት የሥላሴ አስተምህሮት ጋር የከረረ ግጭት ውስጥ የገባው ይኸው የሴባሉሶች አመለካከት በ220 ሮም ላይ ውግዘት ደርሶበታል።(5) -------------------------------- (1) Bart D. Ehrman (2015).“The New Testament: A Historical Introduction to the Early Christian Writings”, pp.3 (2) Bart D. Ehrman (2015).“The New Testament: A Historical Introduction to the Early Christian Writings”, pp.4- (3) Bart D. Ehrman (2015).“The New Testament: A Historical Introduction to the Early Christian Writings”, pp.5-6 (4) Bart D. Ehrman (2015).“The New Testament: A Historical Introduction to the Early Christian Writings”, pp.5-6 (5) Vladimir Lossky (1997). “The Mystical of Theology of the Eastern Church”, pp.51-55 ------------------------------Ω-------------------------------------- https://t.me/muhammed6964 ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
ክፍል 2 ታሪካዊው ሥላሴ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ፥ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡      ሥላሴ በታሪካዊ ሂደት ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገና እየተለወጠ የመጣ አስተምህሮት እንጅ በአንድ ጊዜ አሁን የያዘውን ቅርፅና ይዘት እንዳልያዘ የታሪክ መዛግብት ያስረዱናል። ከክርስትና መምጣት በፊት ያሉትን የነቢያት አስተምህሮቶችና በታሪክ የተመዘገቡትን የቀደምት ፃድቃን ሰዎች እምነት በምናጠናበት ወቅትም የአምላክን ሶስትነት አንዳቸውም ሰብከው እንደማያውቁ እንረዳለን። ይህም ሥላሴ የኢየሱስን መምጣት ተከትሎ የተነሳ እሳቤ እንጅ ቀድሞም የነበረ የነቢያት መንገድ እንዳልሆነ ማሳያ ነው። ለዚህም ይመስላል የቤተክርስቲያን አስተማሪዎች ስለሥላሴ ሲናገሩ ከመጽሐፍ ቅዱስ አንቀፆች ይልቅ የቀደምት አባቶች ድንጋጌ ላይ ትኩረት የሚያደርጉት።    ‹‹ሥላሴ›› የሚለው ቃል ወይም ‹‹አንድ አምላክ በሶስት አካላት›› የሚለው ትንተና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በቀጥታ የተገለፀ እንዳልሆነ ሁሉም የክርስትና ምሁራን ይስማሙበታል። ‹‹ሥላሴ›› በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ቦታ ያልተጠቀሰ ባዕድ ቃል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ስያሜው የተሰጠው ከመጽሐፉ የተለያዩ ጥቅሶች በመነሳት እንደሆነም ይነገራል። እርግጥ በመጠኑ በጣም ትልቅ እና የመጽሐፍት ስብስብበ ሆነው መጽሐፍ ውስጥ ቃሉ አንድም ጊዜ እንኳን አለመጠቀሱ አለባብሰን የምናልፈው ነገር አይደለም። በአስገራሚ ሁኔታ ግን ይህ ቃል ‹‹በቁርኣን›› ውስጥ ብቻ ተፅፎ እናገኘዋለን። የማዒዳህ ምዕራፍ አንቀፅ 73 ላይ እንዲህ ይላል፡-    ‹‹እነዚያ አላህ የሶስት ሶስተኛ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ።››       ለመሆኑ የቃሉ መነሻ ከየት መጣ? የአስተምህሮቱ አጀማመር ምን ይመስል ነበር? የሚለውን ስናጠና መጀመሪያ ስሙ የሚጠቀሰው ቴዎፍሎስ የአንፆኪያው (170 ዓ.ል) ነው። ይህ ሰው በአሁኗ ቱርክ በምትገኘው ጥንታዊቷ የአንፆኪያ ከተማ ጳጳስ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ ሥላሴ ፍንጭ ሰጪ ሃሳቦችን የፃፈ ነው ተብሎም ይታመናል። ኢየሱስ ወደ አባቱ ካረገበት ጊዜ ጀምሮና ይህ ሰው እስከነበረበት ድረስ ባሉት 140 ዓመታት ውስጥ ስለ ሥላሴ የሚገልፅ ምንም ፅሁፍ አልተገኘም።   የአንፆኪያው ጳጳስ ከሥላሴ አስተምህሮት ጋር ይቀራረባል የሚባልለት ፅሁፉ እንዲህ የሚል ነው፡-    ‹‹ፀሐይ ከመፈጠሯ በፊት ያሉት ሶስት ቀናት የሥላሴ ምሳሌዎች ናቸው። የአምላክን፤ የቃሉን እና የጥበቡን። አራተኛው ቀን የሰው ምሳሌ ነው፤ ብርሃን ይፈልጋል። ስለዚህ አምላክ አለ፣ ቃሉም አለ፣ ጥበቡም አለ፣ እንዲሁም ሰው አለ።››  (1)     ከዚህ ፅሁፍ የምንረዳው እግዚአብሔር ፀሐይን ከመፍጠሩ በፊት ያሉት ሶስት ቀናት ‹‹የፈጣሪ፣ የቃሉ እና የጥበቡ›› ምሳሌዎች መሆናቸውን ከመናገሩ በስተቀር የአብ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ አምላክነትን በትክክል እንደማይገልፅ ወይም አስተምህሮቱን እንዳልደረሰበት ነው።   ቴርቱሊያን (160-225 ዓ.ል) የተባለው የኃይማኖት አበው ሁለተኛው ተጠቃሽ ሰው ሲሆን ከቴዎፍሎስ ቀጥሎ ለመጀመሪያ ጊዜ በላቲነኛ ‹‹trinitas›› ወይም ‹‹ሥላሴ›› የሚለውን ቃል የፃፈ ነው። ‹‹ሥላሴ››፣ ‹‹አካል›› እና ‹‹ባህርይ›› የሚሉትን ቃላት ለያይቶ ከመፃፉም በተጨማሪ አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ‹‹በባህርይ አንድ በአካል ሶስት ናቸው።››   ሲል አትቷል። ይሁን እንጅ የእሱም አስተምህሮት በሥላሴ ላይ ባለው የባህርይ ልዩነት ከዛሬው አስተምህሮት ጋር የተዛመደ አልነበረም።(2)   ሌላው ስመጥር ሰው አግናጥዮስ የአንፆኪያው (35-107 ዓ.ል) ነው። ይህ ሰው የሥላሴን ትምህርት በክርስትናው ዓለም ሰብኳል የሚባልለት ሲሆን በዚህም አስተምህሮቱ ከፍተኛ እውቅናና ዝናን አግኝቷል። አግናጥዮስ በቀደምት አባቶች ዘንድ የሚታወቀውና በተለይ በሶስቱ ሥላሴዎች መካከል ስላለው አንድነትና ልዩነት የፃፈው እንዲህ የሚል ነው፡-   ‹‹አብ አብ ነው እንጅ ወልድን መንፈስ ቅዱስን አይደለም፤ ወልድም ወልድ ነው እንጅ አብን መንፈስ ቅዱስን አይደለም፤ መንፈስ ቅዱስም መንፈስ ቅዱስ ነው እንጅ አብን ወልድን አይደለም።››    (3)       ከዚህ ሁሉ ሂደት በኋላ የሥላሴን አስተምህሮት አንድ ወጥ ድንጋጌ ይዞ እንዲንቀሳቀስ ያደረገው ደግሞ አትናቴዎስ የእስክንድርያው (296-373 ዓ.ል) ነው። አትናቴዎስ በሥላሴ አስተምህሮት ላይ ትልቁን ለውጥና መሻሻል ያመጣው ሃያኛው የእስክንድርያ ጳጳስ ስለመሆኑ ሁሉም የታሪክ ምሁራን ይስማሙበታል። የዓለም አብያተክርስቲያናት ወደውም ይሁን በጫና ሥላሴን የክርስትናቸው መሰረት እንዲያደርጉት ትልቅ የፖለቲካ ጨዋታ የተጫወተ ሰው እንደሆነ ይነገራል። በአሁኑ ሰዓት ያለው የሥላሴ አስተምህሮት ሙሉ በሙሉ የአትናቴዎስ ነው ቢባልም የሚታበል አይደለም።       አትናቴዎስ በሥላሴ አስተምህሮት ላይ ሁለት ዓበይት ለውጦችን አምጥቷል። አንደኛው ቀድሞ በእነ ቴዎፍሎስ፣ ቴርቱሊያን እና አግናጥዮስ እያደገ የመጣውን የሥላሴ ትምህርትለውጥና መሻሻል በማድረግ አንድ ወጥ ድንጋጌ እንዲኖረው አድርጓል። ሁለተኛው ደግሞ የመንፈስ ቅዱስን ፍፁማዊ አምላክነት ማፅደቁ ነው። ቀደምት አባቶች በመንፈስ ቅዱስ ምንነት ጉዳይ ላይ ሲወዛገቡና የተለያየ ትርጉም ሲሰጡት ቆይተዋል። ይህንን ክፍፍል ለማስወገድ አትናቴዎስ በእድሜው መገባደጃ አካባቢ ‹‹መንፈስ ቅዱስ አካል ያለው አምላክ ነው።››       ሲል ብይን ሰጥቷል። በዚህም መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ እኩል ፍፁማዊ አምላክ ተብሎ እንዲታመን ለየአብያተክርስቲያናቱ ውሳኔውን አስተላልፏል።(4)       ከአትናቴዎስ የሥላሴ አስተምህሮት ድንጋጌዎች ለአብነት የመረጥኳቸው አንቀፆች እንዲህ የሚሉ ናቸው፡-       ‹‹ወንድሞቻችን እኛስ እንዲህ እናምናለን። ያልተወለደ እግዚአብሔር አብ በተለየ አካሉ አንድ ነው። የተወለደ እግዚአብሔር ወልድ ዋሕድ ኢየሱስ ክርስቶስም በተለየ አካሉ አንድ ነው። በወደደው የሚያድር የአብ የወልድ እስትንፋስ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም በተለየ አካሉ አንድ ነው። አብ አልተወለደም ዓለም ሁሉ ሳይፈጠር ወልድን የወለደ ነው እንጂ። ወልድም ዓለም ሁሉ ሳይፈጠር ከእግዚአብሔር አብ ተወለደ። መንፈስ ቅዱስም ዓለም ሁሉ ሳይፈጠር ከእግዚአብሔር አብ ሠረጸ።››    (5)       ‹‹አብ በአካሉ በገፁ በመልኩ ያለ ነውና፤ ወልድም እንዲሁ በአካሉ በገፁ በመልኩ ያለ ነውና፤ መንፈስ ቅዱስም እንዲሁ በአካሉ በገፁ በመልኩ ያለ ነውና። እንደ ሰውም አይወሰኑም፤ አምላክነት ያለው አካላት ናቸው። በአካል ሶስት በባህርይ አንድ ብሎ ይህን ኃይማኖት የማያምን እንዲህ እኛ እንደወሰንነው አድርጎ ሃይማኖቱን የማይፅፍ ቢኖር ሃዋርያት ያስተማሯት ቅድስት ቤተክርስቲያን ታወግዛለች።›› __ (1) Early Christian Writingde: Theophilus of Antioch”, II.XV (2) Justo L. Gonzalez (2010). “The Story of Christianity, Vol. 1: The Early Church to the Dawn of the Reformation”, pp.91-93 (3) ሃይማኖተ አበው ዘአግንጥዮስ፡ ገፅ 37 - ክ፡1 ቁ፡8 (4) Trinity Britannica Encyclopedia of World Religions, Chicago: Encyclopedia Britannica. 2006 (5) 1ሃይማኖተ አበው ዘአትናቴዎስ ገፅ-55 (6) ሃይማኖተ አበው ዘአትናቴዎስ ገፅ-81 https://t.me/muhammed6964 ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
ሙሐመድ የንፅፅር ማህደር

የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደኾነች ቃል ኑ፡፡(እርሷም) አሏህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአሏህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፣በላቸው። እምቢ ቢሉም፦እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው።3:64 መልካም የማንበብና የማነፃፀር ጊዜ ይሁንሎ!

ክፍል 2 ታሪካዊው ሥላሴ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ፥ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡      ሥላሴ በታሪካዊ ሂደት ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገና እየተለወጠ የመጣ አስተምህሮት እንጅ በአንድ ጊዜ አሁን የያዘውን ቅርፅና ይዘት እንዳልያዘ የታሪክ መዛግብት ያስረዱናል። ከክርስትና መምጣት በፊት ያሉትን የነቢያት አስተምህሮቶችና በታሪክ የተመዘገቡትን የቀደምት ፃድቃን ሰዎች እምነት በምናጠናበት ወቅትም የአምላክን ሶስትነት አንዳቸውም ሰብከው እንደማያውቁ እንረዳለን። ይህም ሥላሴ የኢየሱስን መምጣት ተከትሎ የተነሳ እሳቤ እንጅ ቀድሞም የነበረ የነቢያት መንገድ እንዳልሆነ ማሳያ ነው። ለዚህም ይመስላል የቤተክርስቲያን አስተማሪዎች ስለሥላሴ ሲናገሩ ከመጽሐፍ ቅዱስ አንቀፆች ይልቅ የቀደምት አባቶች ድንጋጌ ላይ ትኩረት የሚያደርጉት።    ‹‹ሥላሴ›› የሚለው ቃል ወይም ‹‹አንድ አምላክ በሶስት አካላት›› የሚለው ትንተና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በቀጥታ የተገለፀ እንዳልሆነ ሁሉም የክርስትና ምሁራን ይስማሙበታል። ‹‹ሥላሴ›› በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ቦታ ያልተጠቀሰ ባዕድ ቃል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ስያሜው የተሰጠው ከመጽሐፉ የተለያዩ ጥቅሶች በመነሳት እንደሆነም ይነገራል። እርግጥ በመጠኑ በጣም ትልቅ እና የመጽሐፍት ስብስብበ ሆነው መጽሐፍ ውስጥ ቃሉ አንድም ጊዜ እንኳን አለመጠቀሱ አለባብሰን የምናልፈው ነገር አይደለም። በአስገራሚ ሁኔታ ግን ይህ ቃል ‹‹በቁርኣን›› ውስጥ ብቻ ተፅፎ እናገኘዋለን። የማዒዳህ ምዕራፍ አንቀፅ 73 ላይ እንዲህ ይላል፡-    ‹‹እነዚያ አላህ የሶስት ሶስተኛ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ።››       ለመሆኑ የቃሉ መነሻ ከየት መጣ? የአስተምህሮቱ አጀማመር ምን ይመስል ነበር? የሚለውን ስናጠና መጀመሪያ ስሙ የሚጠቀሰው ቴዎፍሎስ የአንፆኪያው (170 ዓ.ል) ነው። ይህ ሰው በአሁኗ ቱርክ በምትገኘው ጥንታዊቷ የአንፆኪያ ከተማ ጳጳስ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ ሥላሴ ፍንጭ ሰጪ ሃሳቦችን የፃፈ ነው ተብሎም ይታመናል። ኢየሱስ ወደ አባቱ ካረገበት ጊዜ ጀምሮና ይህ ሰው እስከነበረበት ድረስ ባሉት 140 ዓመታት ውስጥ ስለ ሥላሴ የሚገልፅ ምንም ፅሁፍ አልተገኘም።   የአንፆኪያው ጳጳስ ከሥላሴ አስተምህሮት ጋር ይቀራረባል የሚባልለት ፅሁፉ እንዲህ የሚል ነው፡-    ‹‹ፀሐይ ከመፈጠሯ በፊት ያሉት ሶስት ቀናት የሥላሴ ምሳሌዎች ናቸው። የአምላክን፤ የቃሉን እና የጥበቡን። አራተኛው ቀን የሰው ምሳሌ ነው፤ ብርሃን ይፈልጋል። ስለዚህ አምላክ አለ፣ ቃሉም አለ፣ ጥበቡም አለ፣ እንዲሁም ሰው አለ።››  (1)     ከዚህ ፅሁፍ የምንረዳው እግዚአብሔር ፀሐይን ከመፍጠሩ በፊት ያሉት ሶስት ቀናት ‹‹የፈጣሪ፣ የቃሉ እና የጥበቡ›› ምሳሌዎች መሆናቸውን ከመናገሩ በስተቀር የአብ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ አምላክነትን በትክክል እንደማይገልፅ ወይም አስተምህሮቱን እንዳልደረሰበት ነው።   ቴርቱሊያን (160-225 ዓ.ል) የተባለው የኃይማኖት አበው ሁለተኛው ተጠቃሽ ሰው ሲሆን ከቴዎፍሎስ ቀጥሎ ለመጀመሪያ ጊዜ በላቲነኛ ‹‹trinitas›› ወይም ‹‹ሥላሴ›› የሚለውን ቃል የፃፈ ነው። ‹‹ሥላሴ››፣ ‹‹አካል›› እና ‹‹ባህርይ›› የሚሉትን ቃላት ለያይቶ ከመፃፉም በተጨማሪ አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ‹‹በባህርይ አንድ በአካል ሶስት ናቸው።››   ሲል አትቷል። ይሁን እንጅ የእሱም አስተምህሮት በሥላሴ ላይ ባለው የባህርይ ልዩነት ከዛሬው አስተምህሮት ጋር የተዛመደ አልነበረም።(2)   ሌላው ስመጥር ሰው አግናጥዮስ የአንፆኪያው (35-107 ዓ.ል) ነው። ይህ ሰው የሥላሴን ትምህርት በክርስትናው ዓለም ሰብኳል የሚባልለት ሲሆን በዚህም አስተምህሮቱ ከፍተኛ እውቅናና ዝናን አግኝቷል። አግናጥዮስ በቀደምት አባቶች ዘንድ የሚታወቀውና በተለይ በሶስቱ ሥላሴዎች መካከል ስላለው አንድነትና ልዩነት የፃፈው እንዲህ የሚል ነው፡-   ‹‹አብ አብ ነው እንጅ ወልድን መንፈስ ቅዱስን አይደለም፤ ወልድም ወልድ ነው እንጅ አብን መንፈስ ቅዱስን አይደለም፤ መንፈስ ቅዱስም መንፈስ ቅዱስ ነው እንጅ አብን ወልድን አይደለም።››    (3)       ከዚህ ሁሉ ሂደት በኋላ የሥላሴን አስተምህሮት አንድ ወጥ ድንጋጌ ይዞ እንዲንቀሳቀስ ያደረገው ደግሞ አትናቴዎስ የእስክንድርያው (296-373 ዓ.ል) ነው። አትናቴዎስ በሥላሴ አስተምህሮት ላይ ትልቁን ለውጥና መሻሻል ያመጣው ሃያኛው የእስክንድርያ ጳጳስ ስለመሆኑ ሁሉም የታሪክ ምሁራን ይስማሙበታል። የዓለም አብያተክርስቲያናት ወደውም ይሁን በጫና ሥላሴን የክርስትናቸው መሰረት እንዲያደርጉት ትልቅ የፖለቲካ ጨዋታ የተጫወተ ሰው እንደሆነ ይነገራል። በአሁኑ ሰዓት ያለው የሥላሴ አስተምህሮት ሙሉ በሙሉ የአትናቴዎስ ነው ቢባልም የሚታበል አይደለም።       አትናቴዎስ በሥላሴ አስተምህሮት ላይ ሁለት ዓበይት ለውጦችን አምጥቷል። አንደኛው ቀድሞ በእነ ቴዎፍሎስ፣ ቴርቱሊያን እና አግናጥዮስ እያደገ የመጣውን የሥላሴ ትምህርትለውጥና መሻሻል በማድረግ አንድ ወጥ ድንጋጌ እንዲኖረው አድርጓል። ሁለተኛው ደግሞ የመንፈስ ቅዱስን ፍፁማዊ አምላክነት ማፅደቁ ነው። ቀደምት አባቶች በመንፈስ ቅዱስ ምንነት ጉዳይ ላይ ሲወዛገቡና የተለያየ ትርጉም ሲሰጡት ቆይተዋል። ይህንን ክፍፍል ለማስወገድ አትናቴዎስ በእድሜው መገባደጃ አካባቢ ‹‹መንፈስ ቅዱስ አካል ያለው አምላክ ነው።››       ሲል ብይን ሰጥቷል። በዚህም መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ እኩል ፍፁማዊ አምላክ ተብሎ እንዲታመን ለየአብያተክርስቲያናቱ ውሳኔውን አስተላልፏል።(4)       ከአትናቴዎስ የሥላሴ አስተምህሮት ድንጋጌዎች ለአብነት የመረጥኳቸው አንቀፆች እንዲህ የሚሉ ናቸው፡-       ‹‹ወንድሞቻችን እኛስ እንዲህ እናምናለን። ያልተወለደ እግዚአብሔር አብ በተለየ አካሉ አንድ ነው። የተወለደ እግዚአብሔር ወልድ ዋሕድ ኢየሱስ ክርስቶስም በተለየ አካሉ አንድ ነው። በወደደው የሚያድር የአብ የወልድ እስትንፋስ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም በተለየ አካሉ አንድ ነው። አብ አልተወለደም ዓለም ሁሉ ሳይፈጠር ወልድን የወለደ ነው እንጂ። ወልድም ዓለም ሁሉ ሳይፈጠር ከእግዚአብሔር አብ ተወለደ። መንፈስ ቅዱስም ዓለም ሁሉ ሳይፈጠር ከእግዚአብሔር አብ ሠረጸ።››    (5)       ‹‹አብ በአካሉ በገፁ በመልኩ ያለ ነውና፤ ወልድም እንዲሁ በአካሉ በገፁ በመልኩ ያለ ነውና፤ መንፈስ ቅዱስም እንዲሁ በአካሉ በገፁ በመልኩ ያለ ነውና። እንደ ሰውም አይወሰኑም፤ አምላክነት ያለው አካላት ናቸው። በአካል ሶስት በባህርይ አንድ ብሎ ይህን ኃይማኖት የማያምን እንዲህ እኛ እንደወሰንነው አድርጎ ሃይማኖቱን የማይፅፍ ቢኖር ሃዋርያት ያስተማሯት ቅድስት ቤተክርስቲያን ታወግዛለች።›› __ (1) Early Christian Writingde: Theophilus of Antioch”, II.XV (2) Justo L. Gonzalez (2010). “The Story of Christianity, Vol. 1: The Early Church to the Dawn of the Reformation”, pp.91-93 (3) ሃይማኖተ አበው ዘአግንጥዮስ፡ ገፅ 37 - ክ፡1 ቁ፡8 (4) Trinity Britannica Encyclopedia of World Religions, Chicago: Encyclopedia Britannica. 2006 (5) 1ሃይማኖተ አበው ዘአትናቴዎስ ገፅ-55 (6) ሃይማኖተ አበው ዘአትናቴዎስ ገፅ-81
Show all...
-----------------------------Ω-------------------------------------- https://t.me/muhammed6964 ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
ክፍል 1 ሥላሴ መለኮት ነውን? በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ፥ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡       በዚህ ርዕስ የክርስትና እምነት መሰረት ስለሆነው የሥላሴ አስተምህሮት ታሪካዊ አመጣጡንና ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ አስተምህሮቱ መረጃ ተደርገው የሚቀርቡትን አንቀፆች ትርጉምና ፍች በመተንተን የመረጃዎቹን ትክክለኛነት እንፈትሻለን።       ሥላሴ የክርስትና ምሰሶ እንደመሆኑ መጠንት ክክለኛ አስተምህሮት ከሆነ እምነቱን ህያው የሚያደርገው፥ የተሳሳተ አስተምህሮት ከሆነ ደግሞ እምነቱን ሙሉ በሙሉ የሚያፈርሰው በመሆኑ አንባቢ ይህንን ርዕስ በጥንቃቄ ይከታተለው ዘንድ እጠይቃለሁ። የቃሉት ትርጉም       ቃሉ የመጣው ‹‹ትሪንትስ›› ከሚል የግሪክኛ ቃል ሲሆን ‹‹የሶስት አካላት ጥምረት›› የሚል ትርጉም አለው። ‹‹ሥላሴ›› የሚለው የግዕዝ ቃልም ‹‹ሶስትነት›› የሚል ተመሳሳይ ፍች ሲኖረው አብያተክርስቲያናት የአምላክን በአካል ‹‹ሶስት›› በመለኮት ‹‹አንድ›› መሆን ለመግለፅ የሚጠቀሙበት ቃል ነው።       ‹‹ሥላሴ›› የክርስትና እምነት መሰረት እንደሆነው ሁሉ ሌሎቹም ኃይማኖቶች እንዲሁ የየራሳቸው የሆነ የእምነት መሰረት አላቸው። ለአብነትም የአይሁድ የእምነት መሰረት ‹‹ሼማ›› በመባል የሚጠራ ሲሆን ቃሉ ‹‹አንድ አምላክ በአንድ አካል›› የሚል ፍች አለው። የኢስላም መሰረት ደግሞ ‹‹ተውሂድ›› በሚል ቃል ሲጠራ ትርጓሜውም ‹‹አምላክ በአካል፣ በቁጥር፣ በብዛት አንድ መለኮት ነው።››       የሚል ነው።       በዓለም ላይ በአንድ አምላክ ብቻ የሚያምኑ ‹‹Monotheism›› በሚለው የእንግሊዘኛ ቃል ሲጠሩ እነሱም በዋናነት ኢስላምና አይሁድ ናቸው። ክርስትና በአምላክ ‹‹ሶስትነት›› የሚያምን በመሆኑ ‹‹Modalism›› ወይም ‹‹አንድ አምላክ በሶስት አካላት›› በሚል ቃል ይጠራል።       በሶስት ፍፁማዊ አካላት አምላክነት ላይ የተመሰረተውን የሥላሴ አምላክነት የእምነቱ ምሁራን በሶስት የባህርይ ስም ይከፍሉታል። • 1ኛ፡- አብ - አባት ሲሆን አባትነቱ የባህርይ ነው። • 2ኛ፡- ወልድ - ተወላዲ ሲሆን ወልድነቱ የባህርይ ነው። • 3ኛ፡- መንፈስቅዱስ - ሰራፂ ሲሆን ሰራፂነቱ የባህርይ ነው።       ሶስቱም ፍፁማዊ አምላኮች ሲሆኑ የየራሳቸው መለኮታዊ አካልና ስልጣን እንዳላቸው ይታመናል። እንዲሁም አንዱ ከአንዱ አይበልጥም፥ አንዱም ከአንዱ አይነጠልም፤ የሚል አስተምህሮት አለው።       ርዕሱን በቀጣዮቹ ንዑስ ክፍሎች አንድ በአንድ እየተነተንን የምናየው ሲሆን ነገሩን ይበልጥ ለመረዳት ግን ከእምነቱ ታሪካዊ አመጣጥ እንጀምር ዘንድ ወደድኩ።ለመሆኑ የሥላሴ አስተምህሮት ታሪካዊ አመጣጥ ምን ይመስላል? ታሪካዊ ዳራው የሚነግረን እውነታ ምንድነው? ቀጣዩ ርዕስ ለእነዚህና መሰል ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጠናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ------------------------------Ω-------------------------------------- https://t.me/muhammed6964 ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
ሙሐመድ የንፅፅር ማህደር

የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደኾነች ቃል ኑ፡፡(እርሷም) አሏህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአሏህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፣በላቸው። እምቢ ቢሉም፦እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው።3:64 መልካም የማንበብና የማነፃፀር ጊዜ ይሁንሎ!

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته አላህ ካለ ኢድ እሮብ ነው
Show all...
﴿ٱلْمَالُ وَٱلْبَنُونَ زِينَةُ ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا ۖ وَٱلْبَٰقِيَٰتُ ٱلصَّٰلِحَٰتُ خَيْرٌ عِندَ رَبِّكَ ثَوَابًۭا وَخَيْرٌ أَمَلًۭا﴾ ገንዘብና ወንዶች ልጆች የቅርቢቱ ሕይወት ጌጦች ናቸው፡፡ መልካሞቹም ቀሪዎች (ሥራዎች) እጌታህ ዘንድ በምንዳ በላጭ ናቸው፡፡ በተስፋም በላጭ ናቸው፡፤ ----------------------------------------- [ الكهف]-(46 : 18)
Show all...
👍 5
﴿وَقُلِ ٱلْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَن شَآءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَآءَ فَلْيَكْفُرْ ۚ إِنَّآ أَعْتَدْنَا لِلظَّٰلِمِينَ نَارًا أَحَاطَ بِهِمْ سُرَادِقُهَا ۚ وَإِن يَسْتَغِيثُوا۟ يُغَاثُوا۟ بِمَآءٍۢ كَٱلْمُهْلِ يَشْوِى ٱلْوُجُوهَ ۚ بِئْسَ ٱلشَّرَابُ وَسَآءَتْ مُرْتَفَقًا﴾ «እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ» በላቸው፡፡ እኛ ለበደለኞች አጥሯ በእነሱ የከበበ የኾነችውን እሳት አዘጋጅተናል፡፡ (ከጥም) እርዳታንም ቢፈልጉ እንደ ዘይት ዝቃጭ ባለ ፊቶችን በሚጠብስ ውሃ ይረዳሉ፡፡ መጠጡ ከፋ! መደገፊያይቱም ምንኛ አስከፋች! ----------------------------------------- [ الكهف]-(29 : 18)
Show all...
👍 5