cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

🇪🇹 ETHIOPIA ZENA 🇪🇹

ሰላም ሰላም እንዴት ነችሁ ይህ ቻናል የተለያዩ አዳዲስ ዜናዎች በፍጥነት የሚቀርብበተ እንዲሁም የተለያዩ አዝናኝ ቪዲዮዎች ፣አስተማሪ የሰዎች ንግግሮች በፅሁፍ የሚገኝበትቻናል ነው ቻናላችንን ይቀላቀሉ join channel 👇👇👇👇 @ethiopia02 መረጃዎችን ለመላክ @mikiyasj ለአስተያዬት👉 @Lifiisgood02

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
179
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
126ኛ የአድዋ ድል በዓል በነገው ዕለት “አድዋ ለኢትጵያዊያን ህብረት፤ ለአፍሪካ የነጻነት ጮራ!” በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል! 126ኛ የአድዋ ድል በዓል በነገው ዕለት “አድዋ ለኢትጵያዊያን ህብረት፤ ለአፍሪካ የነጻነት ጮራ!” በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡ የዘንድሮውን የአድዋ ድል በዓል እንደሁል ጊዜው በድምቀት ለማክበር በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ የበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ አስታውቋል። የአከባበሩም ሁኔታ እንደተለመደው የፌዴራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስተ የሥራ ሃላፊዎች፣ አባት አርበኞች እና መላው የከተማዋ ነዋሪ በሚገኝበት በእግር ጉዞና በተለያዩ ደማቅ ዝግጅቶች ከሚኒሊክ አደባባይ እስከ አድዋ ድልድይ ይከናወናል ተብሏል፡፡ በዚሁ መሰረት በማለዳ በሚኒሊክ አደባባይ በሚደረገው የመክፈቻ ዝግጅት ተጀምሮ ወደ ሌላኛው ታሪካዊ ቦታ ወደ አድዋ ድልድይ በእግር ጉዘ የሚቀጥል ይሆናል መባሉን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል፡፡ በመጨረሻም አድዋ ድልድይ ጋር በሚደረጉ የተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚጠናቀቅ የበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ አስታውቋል። @ethiopian02 @mikiyasj
Show all...
ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በትግራይ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም ጠየቀ! በትግራይ የሚንቀሳቀሰው ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፖርቲ በክልሉ ሁሉን አካታች የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት ጠየቀ።አሁን ላይ በትግራይ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የህዝቡን ድህንነት እና ህልውና ማረጋገጥ አልቻለም የሚለው ዓሲምባ ዴሞክራስያዊ ፖርቲ፥ በትግራይ ያለው ዘርፈ ብዙ ችግር ለመፍታት ሁሉም የፖለቲካ ፖርቲዎች፣ ሲቪክ ማሕበራት እና ሌሎች ያካተተ ሁሉን አቀፍ የሽግግር አስተዳደር እንዲመሰረት ጥሪ አቅርቧል።በቅርቡ የትግራይ ነፃነት ፖርቲ እና ሳልሳይ ወያነ ትግራይ የተሰኙ ሁለት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፖርቲዎች በተመሳሳይ በትግራይ የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት ጠይቀው እንደነበር ይታወሳል። [DW] @ethiopia02 @mikiyas8
Show all...
ሱማሌ ክልል በተከሠተው ድርቅ ከ683 ሺሕ በላይ የቤት እንስሳት ሞተዋል! በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል በተከሠተው ድርቅ ምክንያት እስካሁን ከ683 ሺሕ በላይ የቤት እንስሳት መሞታቸውን የክልሉ አደጋ ሥጋት አመራር ቢሮ ለአዲስ ማለዳ ገለጸ።በዚህም እስከ ጥር 30/2014 ባለው ጊዜ ብቻ 683 ሺሕ 465 የቤት እንስሳት መሞታቸውን ነው ቢሮው ያሳወቀው። የቢሮው የቅድመ ማስጠንቀቂያ ቡድን ኃላፊ በሽር አረብ እንደገለጹትም፣ 32 ሺሕ 729 ግመሎች፣ 188 ሺሕ 242 ከብቶች፣ 442 ሺሕ 628 ፍየሎች፣ እንዲሁም 19 ሺሕ 866 አህያዎች በድርቁ ሳቢያ በክልሉ የሞቱ የቤት እንስሳት ናቸው። የቦረና ዞን አጎራባች በሆነው ዳዋ ዞን የሞቱት የቤት እንስሳት ብቻ ከ447 ሺሕ በላይ ሲሆኑ፣ በአፍዴራና ሸበሌ ዞኖችም እንዲሁ ብዙ የቤት እንስሳት ማለቃቸውን ተናግረዋል። Via Addis Maleda @ethiopia02 @mikiyas8
Show all...
የአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ፣ ኢትዮጵያን በተመለከተ አዲስ ረቂቅ ህግ ያወጣ ሲሆን ረቂቅ ህጉ በኢትዮጵያ ግጭትን እያባባሱ በሚገኙ አካላት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የሚያዝ ነው ተብሏል። “የኢትዮጵያ የመረጋጋት፣ የሰላምና የዲሞክራሲ ህግ” በሚል ስያሜ የተዘጋጀው ረቂቅ ህግ፤ በዋናነት በአሜሪካ የኒውጀርሲና ካሊፎርኒያ ግዛት ተወካዮች በጋራ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ሁኔታዎች እስኪሟሉ ድረስ ለሀገሪቱ መንግስት የሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ እንዲቋረጥና አሜሪካን ለኢትዮጵያ የምታደርገው የደህንነትና ፀጥታ ትብብር እንዲቆም ይደነግጋል።በአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የፀደቀው ረቂቅ ህጉ በቀጣይ ለምክር ቤቱ ቀርቦ ከፀደቀ ብቻ ነው ተግባራዊ የሚደረገው፤ ህጉ ለኢትዮጵያ ምንም አይነት እርዳታም ሆነ ብድር እንዳይሰጥ የሚጠይቅ ነው። ይህ ረቂቅ ህግ በኢትዮጵያ ሰላም ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ድርድሩን በማይቀበሉና ግጭቱ እንዳይቆም በሚፈልጉ፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት በሚፈጽሙ፣ መከራን በሚያስፋና በማናቸውም ጠብ አጫሪ ወገኖች የጦር መሳሪያ በሚሸጡ አካላት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ያስችላል ተብሏል።ለሰብአዊ እርዳታዎች ካልሆነ በስተቀር እንደ የአለም ባንክና አለማቀፍ የገንዘብ ድርጅትን የመሳሰሉ አለማቀፍ ተቋማት ለኢትዮጵያና ኤርትራ መንግስታት የገንዘብ እርዳታዎችንም ሆነ ብድሮችን እንዳይሰጡ፤ የአሜሪካ መንግስትም ጫና እንዲያደርግ ረቂቅ ህጉ ይጠይቃል። በዚህ ረቂቅ ህግ ላይ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰብአዊ ወንጀሎች ጦር ወንጀልና ዘር ማጥፋት በኢትዮጵያ መካሄድ አለመካሄዱን መርምሮ እንዲያሳውቅ፤ ግጭቱን የሚያባብሱ ማናቸውም አካላት ተጠያቂነት ያለባቸው መሆኑን እንዲያውቁ እንዲደረግም በረቂቅ ህጉ ተመልክቷል። [Addis Admass] @ethiopia02 @mikiyas8
Show all...
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከመስቀል አደባባይ፤ ወይብላ ማርያም እና ባንዲራ ጋር ተያይዞ ለተነሱት ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ:- 👉በመጀመርያ በመስቀል አደባባይ የፕሮቴስታንት አማኞች የጠየቁት የገቢ አሰባሰብ ፕሮግራም ፍቃድ ሰጥተናል፡፡ 👉ፕሮግራሙ ሊካሄድ አንድ ቀን ሲቀረው አንድ ከፕሮግራሙ ጋር ግንኙነት በሌለው ሰው እንወርሳለን የሚል ሃሳብ ተንፀባረቀ፡፡ 👉ይህም በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ቁጣ የፈጠረ በመሆኑ ግንኙነት ስናደርግ ይህን ያለው ከፕሮግራሙ ጋር ግንኙነት የሌለው ሰው መሆኑን ነግረናቸው ፤ ነገር ግን በዚህም ወገን ያለው አባባልና እሱን መሰረት አድርጎ የተፈጠረውን ስሜት ሁለቱም ሃይ ሊባሉ ይገባል አልናቸው፡፡ 👉ነገር ግን ጉዳዩ ጠንከር እያለ ሲሄድ በፕሮግራሙ እለት ተገኝተን ይሄ አደባባይ የሁላችንም ነው በማለት ማንም ወራሽ እና ተወራሽ እንደሌለ የሚጠቁም መልእክት አስተላለፍን 👉ይህ አባባል በዛ መድረክ ሲነገር የመጀመርያ አልነበረም፤ ሌሎችም ተናግረዋል፡፡እኔ ራሴ ደጋግሜ በተለያዩ ፕሮግራሞች ተናግርያለሁ፡፡ 👉ስለዚህ ጉዳዩን አሁን እንዲባባስ ያደረገው የተጫጫኑ ስሜቶች በመኖራቸው ምክንያት ነው፡፡ 👉ስለዚህ ጥያቄው ሲገፋ ያልነው በህጋዊና ሰላማዊ መንገድ እንፍታ ነው ያልነው፡፡ በመረጃና በማስረጃ መፍታት የሚቻልባቸው ብዙ አማራጮች አሉ፡፡ 👉ከአደባባይ ጋር በተያያዘ የውጪ ብቻ ሳይሆን የራሷ የራሷ የኢትዮጵያ ልምድም ጭምር አለ፡፡ 👉ግንኙነት ለማድረግ ከመጀመርያው አንስቶ ብዙ ጥረት ተደርጓል ፤ከመጀመርያው የፓትርያርኩ መታመም አንስቶ በተለያዩ ምክንያቶች ተራዝሟል፡፡ 👉እኔ በግሌ ፓትርያርኩ ጋር በመሄድም ጉዳየን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ እንፍታ ብዬ አነጋግርያለሁ፡፡ ልዩነት አልነበራቸውም፡፡ ይህንን ሃሳባችሁን በደብዳቤ አስገቡልን አሉን ይህንንም አድርገናል፡፡ 👉ከዚህ ቀደም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ እኛ ወደነሱ እሄዳለን፤ እነርሱም ወደእኛ እየመጡ በርካታ ጉዳዮችን ፈትተናል፡፡ 👉ዛሬ እንኳን ግንኙነት ቀጠሮ አለ ስለተባለ የተወሰነው እዚህ ሆነን ጉባኤውን እናስኪድ ሌሎቻችን ደግሞ እዛ እንሂድ ብለን ተከፋፍለን ነው የሄዱት፡፡ እኛ ከሃይማኖት ጋር ፉክክር የምናደርግ መሪዎች አይደለንም!! 👉ወይብላ ማርያም ጋር የተከሰተው ክስተት አሳዛኝና መሆን ያልነበረበት ጉዳይ ነበር፡፡እኛም ከልባችን አዝነናል። 👉በምንም መንገድ ታቦት ውጪ ማደር አልነበረበትም፡፡ ጉዳዩ አሁን በህግ ተይዟል፡፡ እውነታውን አውቀን በህግ ተጠያቂ እስካላደረግን ድረስ ይቅርታ ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ 👉ከባንዲራ ጋር ተያይዞ የሚነሱ የተለያዩ ሃሳቦች አሉ፡፡ ይህ ጉዳይ የብሄራዊ ምክክር አጀንዳችን ይሆናል፡፡ በዚህ ምክንያት ጥልም ግጭትም በፍፁም አንፈልግም፡፡ ሰውም እንዲሞት አንፈልግም!! ጉዳዮችን ሁሉ ከፖለቲካ ዝንባሌ ጋር ማያያዝም ተገቢ አይደለም ማለታቸውን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ @ethiopia02 @mikiyas8
Show all...
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጅማ ዞን ጌራ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮችን ማሳ በመጎብኘት ላይ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበጋ መስኖ የለሙ የስንዴ ማሳዎችን እንዲሁም የቡና ልማትን ነው በመጎብኘት ላይ የሚገኙት። ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋርም የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በመስክ ጉብኝቱ ላይ መገኘታቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል። @ethiopia02 @mikiyas8
Show all...
ሲአይኤ አሜሪካውያንን በሚስጥር እየሰለለ ነው ሲሉ ሴናተሮች ከሰሱ! ሁለት የአሜሪካ ሴናተሮች ሲአይኤ አሜሪካውያንን በሚስጥር እየሰለለ ነው ሲሉ ወነጀሉ።የአሜሪካው የስለላ ተቋም ሲአይኤ ከዚህ ቀደም እንዳደረገው ሁሉ አሁንም ዜጎቹን እየሰለለ ነው ብለዋል።ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ ሲአይኤ ዜጎች እየሰለለ እንደሆነ የተናገሩት ሴናተሮች ሮን ዋይደን እና ማርቲን ሄይንሪች ናቸው።ሁለቱ ዴሞክራቶች ሲአይኤ ስለዘረጋው የዜጎች የስለላ መረብ ለደኅንነት አመራሮች በደብዳቤ ገልጸዋል። አሜሪካ ውስጥ መንግሥት የዜጎችን የግል መረጃ በስለላ ይሰበስባል የሚል ክስ ሲሰማ የመጀመሪያው አይደለም። ሲአይኤ እና ብሔራዊው የደኅንነት ተቋም ኤንኤስኤ አገር ውስጥ ስለላ እንዳያካሂዱ እአአ በ1947 የወጣው ሕግ ያግዳቸዋል።ከአሜሪካ ውጭ ግን መረጃ መሰብሰብ ይችላሉ።እአአ በ2013 የቀድሞው የሲአይኤ ሠራተኛ ኤድዋርድ ስኖውደን ሲአይኤ የአሜሪካውያንን የግል መረጃ ከተንቀሳቃሽ ስልካቸው እና ከበይነ መረብ እንቅስቃሴያቸው እየሰለለ እንደሆነ ለዓለም አጋልጧል። ስለላ ይደረግባቸው ከነበሩት 90 በመቶው ተራ የአሜሪካ ዜጎች መሆናቸውን የስኖውደን የዋሽንግተን ፖስት ሐተታ ይጠቁማል።የወቅቱ ከፍተኛ የደኅንነት አመራሮች ሲአይኤ አሜሪካውያንን እየሰለለ እንደሆነ አናውቅም ሲሉ በምክር ቤት ፊት መካዳቸው ይታወሳል።ኋላ ላይ ግን በአሜሪካ ፍርድ ቤት ፕሪዝም የተባለው የሲአይኤ የዜጎች ስለላ ሕገ ወጥ ተብሏል።ሁለቱ ሴናተሮች እንደሚሉት ሲአይኤ አሁንም በተራ አሜሪካውያን ላይ ሁለት የመረጃ መሰብሰቢያ መዋቅሮች ዘርግቷል። ይህንን ስለላ የሚያከናውነውም ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ ነው።ሲአይኤ ከዘረጋቸው ሁለት መዋቅሮች አንደኛውን ባለፈው ሳምንት ለሕዝብ ይፋ ቢያደርገም ሁለተኛውን የደኅንንት መረጃ ለመጠበቅ ሲል ይፋ ከማድረግ ተቆጥቧል።ሁለቱ የኒው ሜክሲኮ ሴናተሮች ሲአይኤ ሁለተኛውን መዋቅር ይፋ አለማድረጉ "ኢ-ዴሞክራሲያዊ የሆነና የስለላ ተቋሙን ተአማኒነት የሚያሳጣ ነው" ብለዋል።አሜሪካውያን ለምን እንደሚሰለሉ፣ የተሰበሰበው መረጃ ምን ያህል እንደሆነም ይፋ እንዲደረግ ጠይቀዋል። Via BBC @ethiopia02 @mikiyas8
Show all...
የዓለም ጤና ድርጅት 33.5 ሜትሪክ ቶን የህክምና ቁሳቁሶችን ወደ ትግራይ ክልል ማጓጓዝ ጀምሬያለሁ አለ! የዓለም ጤና ድርጅት 33 ነጥብ 5 ሜትሪክ ቶን የሚገመት አስፈላጊ የሆኑ መድሃኒቶችን እና የህክምና ቁሳቁሶችን ወደ ትግራይ ክልል ማጓጓዝ መጀመሩን አስታወቀ።የድርጀቱ የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት በትዊተር ገጹ ባሰፈረው ጽሁፍ፤ “በቀን 10 ሜትሪክ ቶን የህክምና ቁሳቁስ ወደ ትግራይ ክልል ይገባል” ብሏል።በዚሁ መሰረት በዛሬው እለት 10 ሜትሪክ ቶን የህክምና ቁሳቁሶችን በአውሮፕን ወደ ትግራይ ክልል መግቱን አስታውቋል።የዓለም ጤና ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ የተመድ ድርጅቶች በትግራይ ክልል ከፍተኛ የሆነ የህክምና ቁሳቁሶች እጥረት እንዳለ ሲገልጹ መቆየታቸው አይዘነጋም። Via Alain @ethiopia02 @mikiyas8
Show all...
ፌደራል መንግሥቱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተጠሪነትን ወደ ከተማዋ አስተዳደር ሊያዛውር እንደሆነ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን ተጠሪነቱን ለመረከብ ጥናቶችን አጠናቆ ለመንግሥት እንዳቀረበ የከተማዋ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ ቀንዓ ያዴታ ትናንት ለከተማዋ ምክር ቤት ጉባዔ ተናግረዋል። በተለያዩ አዋጆች ላይ የተደረጉ ጥናቶች የኮሚሽኑ ተጠሪነት ለከተማዋ አስተዳደር መሆን እንዳለበት የሚያመለክቱ እንደሆኑ ቀንዓ አብራርተዋል። ከንቲባ አዳነች ከቀንዓ ማብራሪያ ቀደም ብለው፣ የፖሊስ ኮሚሽኑ ተጠሪነትና አደረጃጀት እንደገና መስተካከል እንዳለበት ለምክር ቤቱ ተናግረው ነበር። የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን ተጠሪነት ሙሉ በሙሉ ለፌደራል መንግሥቱ የተሰጠው በ1997 ዓ.ም ነበር። @ethiopia02 @mikiyas8
Show all...
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ባለፉት ሁለት ሳምንታት 86 በረራዎችን በማድረግ ከ110 ሚሊየን በላይ የአበባ ዘንግ ወደተለያዩ ሀገራት ማጓጓዙን አስታወቀ። እንደ ዓየር መንገዱ ገለፃ የአበባ ዘንጎቹን በዋናነት ከኢትዮጵያ ወደ ተለያዩ ሀገራት ቢያጓጉዝም፥ በተጨማሪም ምርቱን ከኬንያ፣ ኢኳዶር፣ ኮሎምቢያና ሚያሚ (ዩናይትድ ስቴትስ) ወደ ተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት አጓጉዟል።አየር መንገዱ “የፍቅረኞች ቀን” (የቫለንታይን ደይ) በሚውልበት በዚህ ወር የሙቀት መቆጣጠሪያ በተገጠመላቸው ዘመናዊ እቃ ጫኝ አውሮፕላኖቹ ነው የአበባ ምርቶችን ወደተለያዩ የዓለም ሀገራት በማጓጓዝ ላይ የሚገኘው። @ethiopia02 @mikiyas8
Show all...