cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሰላም (Peace) ፈጣን ወታደራዊ የሚዲያ ቻናል ዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ መረጃዎችን በዚህ ቻናል ያገኛሉ

እየተዝናናን እንማማር

Show more
Advertising posts
629
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሬዲዮ ወደ አድማጭ ጆሮ ለመግባት ከፍተኛ ፍጥነት አለው ወደ አድማጭ የተለያዩ መረጃዎችን የማድረስ ልዩ ችሎታ ስላለው የህብረተሰቡንና የብዝሃነት ልምድ በመቅረፅ ሁሉም ድምፅ የሚናገርበት የሚወከልበት እና የሚሰማበት መድረክ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። ዛሬ የዓለም የሬዲዮ ቀን ነው፤ የሬዲዮ ጋዜጠኛ የሆናችሁ ሁሉ ዛሬ የናንተም ቀን ነው እንኳን አደረሳችሁ 📻❤ የሬዲዮ ጋዜጠኛ እንድሆን ያስመኘኝ ኢትዮጵያ ሬዲዮ ነው የልጅነት ፍፁም የማይረሱ ልዩ ትዝና ትውስታ አለብኝ #ሬዲዮ #ውስጤ ነው❤ ሬዲዮ ማዳመጥ የጀመርኩት መቼ ላይ እንደሆነ በውል አላስታውስም ግን በጣም ልጅ እያለሁ ነበር ማዳመጥ አሀዱ ብዬ የጀመርኩት። ልጅ ሳለሁ በሬዲዩ የሚመስጡኝ እና መቼም ልዘነጋቸው የማልችላቸው ዝግጅቶች አሉ እንደነሱ መሆን እሻለሁ ብዬ ነው ያደኩት በተለይ ነብሱን ይማረውና አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛው ጋሽ ደምሴ ዳምጤ ፣ የወጣቶችን ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ ጋዜጠኛ ብርሃዩ ገብረማርያም ከመፅሐፍ አለም ከዘጋጅና አቅራቢያ ጋዜጠኛ ደጀኔ ጥላሁን ከኢትዮጵያን እንቃኛት ጋዜጠኛ አስቻለሁ ጌታቸው እና የልጆች ጊዜ ፕሮግራም እንዲሁም ዜና ፋይሎችን እከታተል ነበር። አሁን ላይ በኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት የሬዲዮ ፕሮግራም ክፍል ውስጥ የሬዲዩ ጋዜጠኛ ሆኜ በምወደው ሙያ ውስጥ በመኖር ላይ እገኛለሁ📻 በነገራችን ላይ እንደ ጋሽ ደምሴ ዳምጤ ሀገር ወዳድና ሀገራዊ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ብቻ መዘገብ እንዳለብኝ እመኝ ነበር። ፈጣሪ ይመስገን በሠራኋቸው መስሪያ ቤቶችም ሆነ በማህበራዊ ትስስር ገፆቼ ከሀገሬ ውጪ የባህርማዶ ስፖርታዊ መረጃዎችን አድርሼ አላውቅም! ሙሉ ትኩረቴና ፍላጎቴ የሀገሬን ስፖርት በመረጃ በመላው አለም ተደራሽ ማድረግ ላይ ነው። በቱይ በማንኛውም ጉዳይ ላይ የሴቶች ተሳትፎ ለማሳደግና ለለማጎልበት ትኩረት በመስጠት ለመሥራት ሁሌም ዝግጁ ነኝ አንድ ቀን የእራሴ የሬዲዮ ጣቢያና ፕሮግራም ይኖረኛል ብዬ ተስፋ አድርጌያለሁ ያደኩትም ይህን እየተመኘሁ ነውና 📻 #ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ👏
Show all...
አሁን ላይ ነፃ ኢንተርኔት መጠቀም ባንችልም በጣም በቅናሽ በሚባል ሁኔታ fast server መጠቀም እንችላለን. ምን መሠላችሁ ....... ቴሌ አዲስ የጀመረው የ social media package አለ አይደል ?? -ዕለታዊ በ 10 birr 1.5 gb telegram and whatsapp package(for 24 hour) -ሳምንታዊ በ 55 birr -ወራዊ 80 birr እንደ ምርጫችን እንገዛለን ከዛ እንዴት የገዛነውን " ለ telegram and whatsaap ብቻ የተገደበን ጥቅል ለሌሎች browsers መጠቀም እንደምንችል step by step በ photo አሳያችኋለሁ. It works for apps መጀመሪያ social media package መግዛታቹህን እንዳትዘነጉ and then dawnloud http injector from play store
Show all...
የአማራ ክልል መንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ስልጠና ለገቡ ሰልጣኞች አቀባበል ተደረገ *** የአማራ ክልል መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ስልጠና ለገቡ ሰልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ተደረገላቸው።  በስነ-ስርዓቱ ላይ የክልሉ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው፣ የምስራቅ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሃመድ ተሰማ ፣ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሀኑ በቀለ እንዲሁም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደስየ ደጀን ተገኝተዋል። በስነስርዓቱ ላይ አቶ ደሳለኝ ጣሰው፤ የተሃድሶ ሰልጣኞች ውግንናችሁን ለሕገ-መንግስቱ እና ለህዝብ መሆኑን አምናችሁና ተቀብላችሁ ስለመጣችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። ሌተናል ጄኔራል ብርሀኑ በቀለ በበኩላቸው፤ ሀገርና ህዝብን ለመካስ ዳግመኛ ያገኛችሁትን ዕድል በአግባቡ በመጠቀም ለሀገራችሁ ዘብ መቆም አለባችሁ ሲሉ አሳስበዋል። "ይሄን የሰላም ጥሪ ተቀብላችሁ ወደ ሰላም በመምጣታችሁ ጀግኖች ናችሁ" ያሉት ሌተናል ጀኔራል መሀመድ ተሰማ  በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚጥሩ ኃይሎችን ለመታገል ዳግመኛ እድል አግኝታችኋልና በአግባቡ ልትጠቀሙበት ይገባል ብለዋል። የተሃድሶ ሰልጣኞች የክልሉን ህዝብ እንዲሁም ሀገራቸውን ለመጠበቅ ቃል መግባታቸውንም የአማራ ክልል ፖሊስ መረጃ ያመለክታል። የኛ Tik Tok👇 👉  tiktok.com/@selam_peace2 የቴሌግራም የሚዲያ ቻናል 👉 https://t.me/ethiotubes1 የቴሌግራም ሀገራዊ የመወያያ ቻናል 👉 https://t.me/ethiotubes993 የፌስቡክ ፔጅ ቁጥር...1 👉 https://www.facebook.com/Ethio-Tubes-military-studio-101838698467272/
Show all...
የአማራ ክልል መንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ስልጠና ለገቡ ሰልጣኞች አቀባበል ተደረገ *** የአማራ ክልል መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ስልጠና ለገቡ ሰልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ተደረገላቸው።  በስነ-ስርዓቱ ላይ የክልሉ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው፣ የምስራቅ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሃመድ ተሰማ ፣ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሀኑ በቀለ እንዲሁም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደስየ ደጀን ተገኝተዋል። በስነስርዓቱ ላይ አቶ ደሳለኝ ጣሰው፤ የተሃድሶ ሰልጣኞች ውግንናችሁን ለሕገ-መንግስቱ እና ለህዝብ መሆኑን አምናችሁና ተቀብላችሁ ስለመጣችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። ሌተናል ጄኔራል ብርሀኑ በቀለ በበኩላቸው፤ ሀገርና ህዝብን ለመካስ ዳግመኛ ያገኛችሁትን ዕድል በአግባቡ በመጠቀም ለሀገራችሁ ዘብ መቆም አለባችሁ ሲሉ አሳስበዋል። "ይሄን የሰላም ጥሪ ተቀብላችሁ ወደ ሰላም በመምጣታችሁ ጀግኖች ናችሁ" ያሉት ሌተናል ጀኔራል መሀመድ ተሰማ  በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚጥሩ ኃይሎችን ለመታገል ዳግመኛ እድል አግኝታችኋልና በአግባቡ ልትጠቀሙበት ይገባል ብለዋል። የተሃድሶ ሰልጣኞች የክልሉን ህዝብ እንዲሁም ሀገራቸውን ለመጠበቅ ቃል መግባታቸውንም የአማራ ክልል ፖሊስ መረጃ ያመለክታል። የኛ Tik Tok👇 👉  tiktok.com/@selam_peace2 የቴሌግራም የሚዲያ ቻናል 👉 https://t.me/ethiotubes1 የቴሌግራም ሀገራዊ የመወያያ ቻናል 👉 https://t.me/ethiotubes993 የፌስቡክ ፔጅ ቁጥር...1 👉 https://www.facebook.com/Ethio-Tubes-military-studio-101838698467272/
Show all...
በየትኛውም የሀገሪቱ የሚገኙ የመከላከያ ይዞታዎች ህጋዊነታቸው ተረጋግጦ መከበር እንዳለባቸው ተጠቆመ በምስራቅ ኢትዮጵያ ጎዴ ከተማ የሚገኘው ወታደራዊ ካምፕ ከእድሜ ጠገብነቱ ጋር ተያይዞ የሰራዊቱን ቀደምት ታሪክ በሚያወሳ መልኩ በውስጡ የሚገኙ የተለያዩ መገልገያዎችና ሀውልቶች ቅርስነታቸው ተጠብቆ ለትውልድ መተላለፍ አለባቸው ሲሉ የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼ ተናግረዋል ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼ በጎዴ ወታደራዊ ካምፕ በመገኘት ከዞኑ አስተዳደርና ከጎዴ ከተማ ከንቲባ ጋር በመሆን የካምፑን ህጋዊ ይዞታ በማረጋገጥ የራሱ የሆነ ካርታ መሰራት እንዳለበት የጋራ ምክክር አድርገዋል የሼበሌ ዞን አስተዳደር አቶ አደን አህመድ በበኩላቸው አሁን ላይ የምናየው ነገር ሁሉ ሠራዊቱ በትክክልም የህዝብ ልጅ እንደሆነ የሚያስመሰክር መሆኑን ጠቁመው ህዝቡም ለመከላከያ ያለውን የተዛባ አመለካከት ቀይሮ ተባብሮ እየሰራ መሆኑን አክለዋል ሠራዊቱ በተለየ ሁኔታ የህብረተሰቡን ቀልብ መግዛት የቻለው ባለፈው የዘነበው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ ለህይወቱ ሳይሰስት ባደረገው መልካም ነገር መሆኑን ገልፀው በርካታ ዜጎችን ከነ-ንብረታቸው ከመታደጉም ባሻገር ከሚበላው ቀንሶ እያካፈለ የነፍስ አድን ስራ በመስራቱ ህዝባዊነቱን ስላሳየ አሥፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነን ብለዋል የጎዴ ከተማ ከንቲባ አቶ አብዱላሂ አሊ ሀጂ ከልጅነት እስካሁን ባለኝ እድሜ ሰራዊቱ በቀጠናው ለረጅም ዘመን ግዳጅ እየተወጣ የቆየ በመሆኑ ካምፑ የተረጋገጠ በመሆኑ ይዞታነቱን እናስጠብቃለን ሲሉ ገልፀዋል የጎዴ ከተማም ይሁን የኢትዮጵያ እድገት የሚፋጠነው ደምበራችን በአስተማማኝ ሲጠበቅ በመሆኑ እንደ አስፈላጊነቱ ለሠራዊታችን ተጨማሪ ቦታ በመስጠት አብሮነታችንን በማጠናከር ከጎኑ ሆነን እንሠራለን ብለዋል።
Show all...
መምህርት ሊያ የ5ኛ ክፍል አስተማሪ ነች ሊያ ተማሪዎቿን አንድ በአንድ የምትከታተል ብርቱ መምህር ነች ከተማሪዎቿ አንዱ ኒክ ይባላል ኒክ አያወራም: ከተማሪዎች ጋር አይጫወትም: ልብሱ ዝብርቅርቅ ያለ ነው: ክፍል ውስጥ አይሳተፍም - መምህር ሊያ በኒክ ደስተኛ አይደለችም መምህር ሊያ የተማሪዎችን የቤት ስራ እና ፈተና ባረመች ጊዜ ሁሉ የኒክን ፈተና በትልቁ ኤክስ (X) የምታደርግ እና በብስጭት ስንፍናውን የምትፅፍ ሆነች - አልወደደችውም በትምህርት ቤቱ ህግ ደግሞ የእያንዳንዱን ተማሪ የቀድሞ አመታት የውጤት ፋይሎችን ማየት ግዴታ ስለሆነ መምህርት ሊያም ይህንኑ ስታደርግ የሁሉንም ፋይል አይታ የኒክ መጨረሻ ላይ ቀረ አነበበችው : ተገረመች : ደነገጠች ! **** የአንደኛ ክፍል መምህሩ "ኒክ በጣም ጎበዝ ተማሪ ነው! ፀባዩም ሸጋ ነው: ንፁህ እና ብሩህ ተማሪ ነው" የሁለተኛ ክፍል መምህሩ "ኒክ ጎበዝ ተማሪ ነው: ነገር ግን በዚህ አመት እናቱ በጠና ስለታመመች በውጤቱ ቀንሷል" የሶስተኛ ክፍል መምህሩ "ኒክ በእናቱ ሞት ተጎድቷል: አባቱም በሀዘን ተጎድቶ ትኩረት የሚሰጠው ሰው የለም" የአራተኛ ክፍል መምህሩ "አባቱን በሞት የተነጠቀው ኒክ በዚህ አመት ብሶበታል: ብቸኛ ነው: ከማንም ጋር አያወራም: ውጤቱም ወርዷል" *** እለቱ የገና ዋዜማ ነው: ተማሪዎች ለመህራኖቻቸው ስጦታ የሚሰጡበት እለት ነው - ሁሉም ተማሪዎች ለመምህርት ሊያ የሚያምሩ ስጦታዎችን እየሰጡ ነበር ኒክ በስተመጨረሻ መጣ - በእጁ ጌጣቸው የረገፈ አምባር እና ሊያልቅ ቂጡ ላይ የደረሰ ሽቶ ይዟል: የእናቱ የእጅ አምባር እና ሽቶ ነበር - ተማሪዎች ይህንን አይተው ሳቁ : መምህሯ ግን ተማሪዎቹን ፀጥ አሰኝታ አምባሩን አጠለቀችው : ሽቶውን ተቀባች : ኒክን አቀፈችው "ዛሬ እናቴን ትመስያለሽ : እናቴን እናቴን ትሸቻለሽ" አላት : ተማሪዎች ከሄዱ በኃላ ለሰአታት ብቻዋን አለቀሰች ** ከዚያ ጀምሮ መምህርት ሊያ ኒክን ተከታተለችው: ኒክ ጎበዘ: አመቱ መጨረሻ ላይ ጥሩ ውጤት አመጣ በትምህርት ቤቱ ውስጥ "የመምህራን ምርጫ" ተብሎ ለመጠራት የበቃው ኒክ በትምህርቱ ጎበዝ: በፀባዩ ምስጉን እና በባህሪው ደግሞ ተግባቢ እና ደስተኛ ሆነ ብዙ አመታት አለፉ: በእነዚህ አመታቶች ሁሉ በገና እለት ዋዜማ መምህርት ሊያ የቤቷ በራፍ ላይ "በህይወቴ ሁሌም ምርጧ አስተማሪ ነሽ! ኒክ" የሚል ፅሁፍ ታገኛለች ኒክ ተመረቀ: ዶክተር ሆነ: በስራው የታወቀ ሀኪም ሆነ ከእለታት በአንዱ ቀን "መምህርት ሆይ! ጥሩ እጮኛ አገኘሁኝ! እናት እና አባት እንደሌለኝ ታውቂያለሽ:: ስለዚህ የሰርጌ ቀን ከጎኔ ቁሚልኝ! ኒክ" የሚል ደብዳቤ ደረሳት ** በሰርጉ ቀን የእናቱን አምባር አድርጋ እና ሽቶውን ተቀብታ ከጎኑ ቆመች : ዳረችው በሰርጉ መሃል እጁን ይዛ ወደ አዳራሹ ሲገቡ "መምህርት ሊያ ህይወቴን በተለየ መልኩ እንድረዳ እና እንድመለከት ስላደረግሽ አመሰግንሻለሁኝ" አላት መምህርት ሊያ እንዲህ አለች 👇🏾 “ዶ/ር ኒክ! አንተ ነህ ሰዎችን እና ይህችን አለም የማይበትን መነጽር እንድቀይር ያደረግከኝ: አመሰግንሃለሁ!" ❤️🙌🏼 by Zemelak Endrias
Show all...
👍 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.