en
Feedback
WeMind Ethiopia

WeMind Ethiopia

Open in Telegram

Comprehensive Mental Health Resources Across Ethiopia

Show more
1 193
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-1030 days
Posts Archive
PDF |

ስጦታ ወግ (5ኛ ዙር) 🧠 የመወያያ ርዕስ፡ አልታመምኩም ህክምና አያስፈልገኝም 🎙 እንግዳ ዶ/ር ዮናስ ባህረጥበብ   👨🏽‍⚕️ ዝግጅት መሪ፡ ጋሻው አወቀ 📅 ቀን፡ ቅዳሜ ሚያዚያ 5 🕒 ሰዓት፡ 1፡00-3፡00 @Gashaw_Aweke

ዛሬ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ ለመሳተፍ https://t.me/Sitotapsy
ዛሬ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ ለመሳተፍ https://t.me/Sitotapsy

እኒህ በኢልቦለድ መጽፎቹ የሚታወቀው አሜሪካዊ ጋዜጠኛ ፔት ኤርሊ ቃላቶች ናቸው “አባባ፣ የምትወደው ሰው ራሱን ቢያጠፋ ምን ይሰማሃል?” ይህንን ጥያቄ ሲጠይቀኝ የኮሌጅ ልጄን ማይክ ይዤ ወደ ድንገተኛ ክፍል እየጣደፍኩ ነበር። በሚስጥር መልዕክቶች እየተላለፉለት እንደሆነ፣ ያልሆነ ነገር እንደሆነ እያሰበ ይጠራጠር እና ፈጣን የስሜት መዋዠቅ እያጋጠመው ነበር። ሆስፒታል ስንደርስ በጣም ጥሩ የሆነ እፎይታ ተሰማኝ። “ዶክተሮች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ያውቃሉ!” ብዬ ስላሰብኩ፡፡ ከአራት ሰዓታት በኋላ አንድ ዶክተር ማይክን ለአጭር ጊዜ ከጠየቀው በኋላ ሀኪሙ ምንም ሊረዳው እንደማይችል ገለጸ። ይህም ማይክ ምንም እንዳልታመመ እና ምንም አይነት መድሀኒት እንደማይወስድ አስረግጥቶ ስለተናገረ ነበር፡፡ ልጄ ምንም እንኳን የህመሙን ምልክቶች በግልጽ እየታየበት መሆኑን ዶክተሩ ቢረዳም፤ በራሱም ሆነ ለሌሎች “አደጋ ያደርሳል” ብሎ ስላላመነ ወደ ቤት ያለምንም እርዳታ ተመለሰ፡፡ በሚቀጥሉት 48 ሰዓታት ውስጥ ማይክ ጭራሹኑ ባሰበት። የገዛን ልጅ አእምሮው እየሸወደው እያየ ዝም ብሎ ማየት ያለውን ጭንቀት የሚረደው የደረሰበት ወላጅ ብቻ ነው። በእርግጥ አንድ ነገር ለማድረግ ሞከርኩ። ለማይክ መድሀኒቱ እንደሚረዳው በግልጽ ነገርኩት። እሱ ግን ምንም ችግር እንደሌለበት ነገረኝ። አስተሳሰብ እና በእይታው እንደተዛባ ላሳየው ሞከርኩ ግን አልተስማማም። በመጨረሻም ክኒኑን እንዲወስድ ለመንኩት …“እባክህ… ለእኔ ስትል … ለእኔ ብለህ መድሀኒቱን ውሰድልኝ!” … ግን አላደረገውም። "አልታመምኩም" እያለ ደጋግሞ ከመናገር ውጭ ፍንክች አልልም አለ። ከሰአታት አድካሚ ውይይት በኋላ መድሃኒቱን እንዲወስድ አለበለዚያ ከቤት እንዲወጣ ለማስፈራራት ሞከርኩ፡፡ ማስፈራራቱ ሁኔታውን የበለጠ አባብሶት ቁጭ አለ፡፡ ምንም አማራጭ እንደሌለኝ ሳውቅ፣ በመንገድ ላይ አንድ ነገር ይሆንብኛል ብዬ ፈርቼ፣ ራሴን አረጋግቼ ሌላ ዘዴ መፈለግ ግዴታዬ ነበር። በማግስቱ ጠዋት ተደብቄ በማይክ ቁርስ ላይ መድሀኒቱን ቁርሱ ላይ ለመጨመር ስሞከር ያዘኝ፡፡ እጅግ ተናደደ። በእኔ አመኔታ እያጣ እንደመጣ ነገረኝ፡፡ ግንኙነታችን የበለጠ የሻከረ መሰለኝ፡፡ ከ2 ቀን በኋላ ከፖሊስ ጣቢያ ተደወለልኝ፡፡ አንድ ቀን ጠዋት፤ ማይክ ከቤት አምልጦ ወጥቶ የሰው ቤት ሰብሮ በመግባት በፖሊስ ተያዘ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ቆሽሻለሁ ብሎ ስላሰሰበለ ለመታጠብ ፈልጎ ነበር ሰብሮ የገባው። እንደ እድል ሆኖ፤ የቤቱ ባለቤቶች ከከተማ ውጭ ነበሩ፡፡ እሱን ለመያዝ ስድስት ፖሊሶች መረባረብ ነበረባቸው። ማይክ በሁለት ከባድ ወንጀሎች ተከሰሰ፡፡ ውሎ አድሮ ልጄ የሁለት አመት የአመክሮ ጊዜ ተፈረደበት፡፡ እና በዚያ ጊዜ ውስጥ ማይክ ህጎቹን ተከተለ። በሕክምና ላይ ይገኛል፡፡ በቡድን ቴራፒዎች ላይ ይሳተፋል፤ መድሀኒቱን ይወስዳል፡፡ ማይክ ከአመክሮ ቦታው ከወጣ ከበርካታ ወራት በኋላ የሕመሙ ምልክቶች እንደገና መታየት ጀመሩ። ማይክ መድሃኒቱን መውሰድ እንዳቆመ ሳውቅ በጣም ደነገጥኩ። በብዙ ችግሮች ውስጥ እንዳሳለፈው ቢያውቅም፣ አሁንም መድሀኒቱን አቋረጠ። ወዲየውኑ ማይክን ስቆጣ ራሴን አገኘሁት “… እንዴት ይህንን አሁንም አደረክ? ትንሽ እንኳን አታስብም…? `````````````````````````````` ይህ የብዙ ቤተሰቦች ገጠመኝ እና እራስ ምታት ነው፡፡ ዶ/ር ዮናስ፤ እንዲህ አይነቱ ጉዳይ ሲገጥመን እንደቤተሰብ… እንደ አስተማሚ… ምን ማድረግ እንዳለብን በቴሌግራም በኦንላይን ትምህርት ይሰጣሉ፡፡ ሁሉም ሰው መሳተፍ ይችላል፡፡ ለመሳተፍ ይህንን ይጫኑ t.me/sitotapsy ቀን፡ ቅዳሜ ሚያዚያ 5 ሰዓት፡ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዯች፥ ኢድ ሙባረክ @gashaw_aweke
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዯች፥ ኢድ ሙባረክ @gashaw_aweke

Happy one year anniversary, MENTAL HEALTH ADDIS
+1
Happy one year anniversary, MENTAL HEALTH ADDIS

photo content
+1

የአንቲ ሳይኮቲክ የጎንዮሽ ጉዳት እና መፍትሔያቸው ያለ ሀኪም ትዕዛዝ የምንገዛቸውን መደሀኒቶች ጨምሮ ሁሉም መድሀኒቶች የየራሳቸው የጎንዮሽ ጉዳት አላቸው፡፡ አንቲ ሳይኮቲኮችም እንደማኝኛውም መድሀኒቶች የየራሳቸው የጎንዮሽ ጉዳት አላቸው፡፡ አብዛኛዎቹ የጎንዮሽ ጉዳቶች ቀላል እና ከጥቂት ጊዜ በኋላ በራሳቸው ጊዜ የሚስተካከሉ ናቸው፡፡ ሌሎቹ ታካሚን የሚያስቸግሩ ናቸው፡፡ ማርከሻ መድሀኒቶችን ወይም ማስተካክያዎችን በማድረግ ይስተካከላሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ጉዳታቸው ከፍ ያለ እና መድሀኒቱን ለመቀየር የሚያስገደድዱ ናቸው፡፡ የተለመዱትን የጎንዮሽ ጉዳቶች እና መፍትሔያቸውን ተራ በተራ ለመዳሰስ እሞክራለሁ፡፡ 1. የመጫጫን እና እንቅልፍ የሚል ስሜት (sedation/Somnolence) - ይህ አንድ ሰው የተወሰኑ አንቲ ሳይኮቲክ መድሀኒቶችን ሲጀምር ወይም መጠን ሲጨመርለት አንድ ጎንዮሽ ምልክት ነው፡፡ - የተለመደ ቢሆንም ሁሉም ታካሚዎች ላይ ላይከሰት ይችላል፡፡ - በአብዛኛው ይህ ምልክት ጊዜያዊ ነው፡፡ በራሱ ጊዜ ይስተካከላል፡፡ - ወይም አስፈላጊ ህክምና ከተደረገ በኋላ መሻሻል በሚመጣ ጊዜ መድሀኒቱ ስቀነስ እሱም ይቀንሳል፡፡ - ብዙ ታካሚዎች ቀስ በቀስ እየለተላመዱት ይመጣሉ፡፡ - እንደ ጥቅም የሚለውልበትም ጊዜም አለ፡፡ አንድ ታካሚ አለመረጋጋት ከገጠመው እንዲረጋጋ ለማድረግ ይጠቅማል፡፡ - እንቅልፍ ለሚያስቸግራቸው ታካሚዎች እንዲተኙ ያግዛችዋል፡፡ የመጫጫን ስሜት ከተሰማኝ ምን ላድርግ? 1. ይጠብቁ 2. ይጠብቁ 3. ይጠብቁ 4. ከሀኪምዎ ጋር ለመነጋገር አያመንቱ 5. ቀን ቀን እንቅልፍ የሚያስቸግረዎት ከሆነ እና ስራዎን በንቃት ለማከናዎን ከተቸገሩ ማታ ማታ እንዲወስዱት ወይም መጠኑን ከፋፍሉ አብዛኛውን ማታ ማታ እንዲወስዱት ሀኪምዎ ሊያዝ ይችላል፡፡ 6. እሰኪስተካከልልዎ ድረስ መኪና አይንዱ፣ ከባድ ማሽን ላይ አይስሩ 7. አልኮል ያስወግዱ፡፡ አልኮል ተጨማሪ የመጫጫን ስሜት ይፈጥራል፡፡ 8. ያም ሆኖ የማይስተካከል ከሆነ ሀኪምዎ መጠኑን ይቀንስልዎታል ወይም ወደሌላ ተስማሚ መድሀኒት ይቀይርልዎታል፡፡ ከሀኪምዎ ጋር ለመነጋገር ነፃነት ይሰማዎት፡፡ ይሁን እንጅ በራስዎ መድሀኒት ለመቀነስ ወይም ለመጨመር አይሞክሩ! t.me/Gashaw_Aweke ጋሻው አወቀ [ሳይካትሪ ፕሮፌሽናል]

የዓለም የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን
+3
የዓለም የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን

ክፍል 03 💊 ጸረ-ሳይኮቲክ (antipsychotic) መድሀኒቶች 💊  መድሀኒቶቹን ከመውሰድዎ በፊት ምን አይነት ምርመራ ይደረግለዎታል ■ የደም ግፊት፣ ክብደት፣ ሌሎች መድሀኒቶችን ይወስዱ እንደሆነ፣ የደም እና የሽንት ምርመራዎች...  እንደ አስፈላጊነታቸው ሊታዘዝልዎ ይችላል፡፡ ይህም ለእርሱ የተሻለውን መድሀኒት ለመምረጥ ነው፡፡ ■ ለምሳሌ የደም ግፊት ካለብዎ የደም ግፊት የመጨመር እድል የሌላቸውን መድሀኒቶች እንዲመረጥልዎት ይደረጋል፡፡ 💊 አንቲ ሳይኮቲክ መድሀኒቶችን በዋናነት በሁለት መክፈል ይቻላል [ በእኛ ሀገር ውስጥ የሚታዘዙትን ብቻ ለመጥቀስ እሞክራለሁ፤ ነገር ግን ሌሎች መድሀኒቶችም አሉ] 1. የመጀመሪያ ትውልዶች (first generation antipsychotics) 🔸  በክኒን መልክ የሚሰጡ (የመጀመሪያው ስም የመድሀኒቱ ስም ሲሆን በቅንፍ ያለው መድሀኒቱን የሚያቀርበው ፋብሪካ የሚሰጠው ስሞች ናቸው)   ■  በብዙ ግራም የሚሰጡ (low potent)   - chlorpromazine (Chloractil, Largactil)   - Thioridazine (Mellaril or Melleril) ■ በጥቂት ግራም የሚሰጡ (High potent)   - haloperidol (Haldol, Halkid)   -  trifluoperazine (Stelazine) ■  በመርፌ መልክ የሚሰጡ - fluphenazine decanoate (medicate) - haloperidol decanoate (Haldol Decanoate) 2. ሁለተኛ ትውልዶች (second generation antipsychotics) 🔸  በክኒን መልክ የሚሰጡ ■ ብዙውን ጊዜ የሚታዘዙ - Risperidone (Risperdal) - olanzapine (Zalasta, Zyprexa) - aripiprazole (Abilify, Arpoya) - quetiapine ■ ለህክምና አስቸጋሪ ለሆነ ህመም የሚታዘዝ - clozapine (Clozaril, Denzapine, Zaponex) 🔸 በመርፌ መልክ የሚሰጡ - ከሁለተኛዎቹ ትውልዶች በመርፌ መልክ የሚሰጡ መደሀኒቶች ቢኖሩም ነገር ግን በሀገራችን ብዙም የሉም፨ ፓሊፔሪዶል የሚባል  መድሀኒት በቅርቡ ወደ ሀገር የገባ ቢሆንም አገልግሎት ላይ ሲውል አይሰተዋልም [ በዋጋው ምክንያት ሊሆን ይችላል] 💊 በምንደን ነው የሚለያዩት? ■ የጎንዮሽ ጉዳት፡ የመጀመሪያዎቹ መድሀኒቶች ጠንከር የሚል የጎንዮሽ ጉዳት አላቸው፡፡ የመጀመሪያዎቹ ትውልዶች ሰውነት የመያዝ፣ እጅን የማንቀጥቀጥ… ምልክቶች ይበዛባቸዋል (ወደፊት ይብራራል) ■ ዉጤታማነት፡ ብዙውን ጊዜ ሁለተኛዎቹ ትውልዶች የተሻለ ውጤታማ ናቸው፡፡ ግን ይህ ህግ ለሁሉም ሰው አይሰራም - የመጀመሪያዎቹ ትውልዶች የተሻለ ለውጥ የሚያመጡላቸው ሰዎች አሉ፡፡ ■ አጠቃላይ ደህነነት፡ ሁለተኛዎቹ ትውልዶች የበለጠ ለታካሚ ተስማሚ ናቸው ■ ዋጋ፡ ሁለተኛዎቹ ትውልዶች በአንጻሩ ውድ ናቸው፡፡ በተለይ በመርፌ የሚወሰዱት ውድ ናቸው፡፡ የእዚህ ጽሑፍ አላማ ሾለ አንቲ-ሳይኮቲክ መድሀኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት እና መፍትሔ ግንዛቤ መስጠት ነው፡፡ ይቀጥላል ልብ ይበሉ! ጽሑፉ ግንዛቤ ማስጨበጫ ብቻ ነው፡፡ የሀኪምዎን ምክር አይተካም! t.me/Gashaw_Aweke ጋሻው አወቀ [የስነ አእምሮ ባለሙያ]

ክፍል 02 💊 ጸረ-ሳይኮቲክ (antipsychotic) መድሀኒቶች ለስኪዞፍሬኒያ የሚሰጡ መደሀኒቶች ጸረ-ሳይኮቲክ (antipsychotic) ይባላሉ፡፡ እነዚህ መድሀኒቶች በአእምሮ ህክምና ላይ በብዛት ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ እነዚህ መድሀኒቶች የሚያክሙት ህመሞች ውስጥ የሚጠቀሱት ■ ስኪዞፍሬኒያ፡ አረዳድ፣ ስሜት፣ የማገናዘብ አቅምን እና ባህሪን የሚጎዳ/የሚቀይር ስር የሰደደ ህመም ■ ከፍተኛ ድባቴ፡ ለረጅም ጊዜ የሚከሰት የሀዘን፤ ተስፋ የመቁረጥ፤ የባዶነት እና በህይወት ትርጉም የማጣት ህመም፡፡ ከድባቴ መድሀኒት በተጨማሪ እነዚህ መድሀኒቶች ሊታዘዙ ይችላሉ፡፡ ■ አንዳንድ የባይፖላር ህመሞች፡ ከልክ ባለፈ ደስታ፣ መነጫነጭ፣ በሀይል መሞላት እና ከልክ ባለፈ የሀዘን ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ውስጥ የሚገለባበጥ የስሜት ህመም፡፡ ■ ስኪዞአፌክቲቭ፡ ከላይ ያየናቸውን ህመም ምልክቶች አንድ ላይ የሚይዝ ህመም ■ አንዳነንድ የስብዕና ችግሮች 💊መድሀኒቶቹ የሚሰሩት እንዴት ነው? ■ በመሀለኛው የአንጎላችን ክፍል፣ ዶፓሚን የሚባል ንጥረ ነገር ከመጠን በላይ ሲበዛ ድምጽ መስማት እና ሰውን መጠራጠር የመሳሰሉ ሳይኮቲክ ምልክቶች ይከሰታሉ፡፡ ■ በውጨኛው የአንጎል ክፍላችን ውስጥ ይህ ዶፓሚን የተባለው ንጥረ ነገር ሲያንስ ራስን ከሰው መነጠል፣ ስሜት አልባ ፊት ማሳየት፣ ተነሳሽነት ማጣት… የመሳሰሉት ምልክቶች ይከሰታሉ፡፡ ■ አንቲ ሳይኮቲክ መድሀኒቶች ዝቅ ወይም ከፍ ያለውን የዶፓሚን መጠን በማስተካከል ምልክቶቹን ያክማሉ፡፡ 💊 ለመስራት ምን ያህል ጊዜ ይፈጅባቸዋል? ■ እንደ መድሀኒቶቹ አወሳሰድ ይለያያል፡፡ በክኒን መልክ የሚወሰዱት ለውጣቸው ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ሊጀምር ይችላል፡፡ ■ በመርፌ መልክ ለሳምንታት ወይም ለወር የሚሰጡት ቀስ በቀስ እያሉ ሊሰሩ ይችላሉ ■ በድንገተኛ ህክምና ለማረጋጊያ የሚሰጡት በተወሰዱ በትንሽ ጊዜ የመረጋጋት ስሜት ሊፈጥሩ ይችላሉ ■ ይሁን እንጅ ሳይኮቲክ ምልክቶችን ማስተካከል የሚጀምሩት ከቀናት ወይም ከሳምንታት በኋላ ነው የእዚህ ጽሑፍ አላማ ስለ አንቲ-ሳይኮቲክ መድሀኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት እና መፍትሔ ግንዛቤ መስጠት ነው፡፡ ይቀጥላል t.me/Gashaw_Aweke ጋሻው አወቀ (የስነ አእምሮ ባለሙያ)

ክፍል 01 የእዚህ ጽሑፍ አላማ ስለ አንቲ-ሳይኮቲክ መድሀኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት እና መፍትሔ ግንዛቤ መስጠት ነው፡፡ ጽሑፉ ረዘም ስለሚል በየክፍል እየከፋፈልኩ ለመልቀቅ እሞክራለሁ ከእውነት አፋች ምልክቶች (psychotic symptoms) ተኝታችሁ እየቃዣችሁ ነው እንበል፡፡ በአይን የማይታያችሁ ሰው የምታደርጉትን ነገር በሙሉ እየተከታተለ አስተያየት ሊሰጥ ወይም ሊሰድባችሁ ይችላል፡፡ የሆነ የሚያስፈራ አውሬ ወይም ጭራቅ የሚመስል ፍጥረት ሲያባርራችሁ ልታዩ ትችላላችሁ፡፡ የሆነ ጭውውው ያለ ገደል ውስጥ ልትወድቁ ስትሉ… ልታዩ ትችላላችሁ፡፡ ከእንቅልፋችሁ ስትነቁ የሚያባርራችሁ ነገር የለም፡፡ ኡፈይይይ…. ተመስገን… እንኳንም ቅዠት ሆነ ብላችሁ ታልፉታላችሁ፡፡ ከእውነት አፋች ህመሞቸ እንቅልፍ ሳይወስዳቸሁ በቁም እንደመቃዠት አድርጋችሁ ውሰዱት፡፡ ሳይኮቲክ ምልክቶች (psychotic symptoms) ካጋጠመን፣ አእምሯችን እውነታውን እና ምዕናቡን ለመለየት ይቸግረዋል፡፡ ታማሚው በእውን ያልተፈጠረን ድምጽ ሊሰማ ይችላል፡፡ የሚከታተለው ፖሊስ ወይም ሰው ሳይኖር ሰዎች እየተከታተሉት እና ሊያጠቁት እየፈለጉት ሊመስለው ይችላል፡፡ ይህን ለምሳሌ አነሳን እንጅ ሳይኮቲክ ምልክቶች ዘርፈ ብዙ ናቸው፡፡ ሳይኮቲክ ምልክቶች በብዙ የአእምሮ እና የነርቭ ህመሞች ላይ ይከሰታሉ፡፡ ሳይኮቲክ የአእምሮ ህመሞች (ለምሳሌ ስኪዞፍሬኒያ) ከባድ እና ስር ከሰደዱ የአእምሮ ህመሞች ውስጥ ይካተታሉ፡፡ እነዚህ ህመሞች በጊዜው ተገቢውን ህክምና ካላገኙ ታማሚውን ■ ከሰው ተራ ያስወጡታል ■ የማስታወስ፣ የማመዛዘን አቅሙን ይጎዱል፡፡ ስለዚህም ግለሰቡ አደጋ ላይ ሊወድቅ፣ መስራት ሊያቅተው እና ከስራ ሊባረ ይችላል (ጎዳና እስከመውጣት ሊያደርሱት ይችላሉ) ■ ራሱን እንዲያገል ያደርጉል ■ እውነታውን ከምዕናም መለየት እንዳይችል ያደርጉታል፡፡ ይህ አደጋ ላይ እንዲወድቅ ያደርጉታል፡፡ ■ ከፍተኛ ፍርሀት፣ ጭንቀት፣ ድብርት፣ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ይከቱታል ■ ከመስሪያ ቤት ሰዎች፣ ከቤተሰብ፣ ጓደኛ፣ እጮኛ… ጋር እንዳይግባባ ያድርጉታል፡፡ ■ ራሱን ወይም ሌሎቹን እንዲጎዳ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ አንድ ታካሚ የራሱን አይኑን አውጥቶታል፣ ሎላኛው ደግሞ እግሩን ቆርጧል ■ ስነ-ልቦናዊ ውጥረት ውስጥ ይከቱታል ■ የልብ ህመም፣ የስኳር ህመም፣ ሱስ እና የመሳሰሉትን ህመሞች ሊያስከትሉበት ይችላሉ፡፡ ■ እና ሌሎችም እነዚህም ምልክቶች ለማከም የሚሰጡ መድሀኒቶች ጸረ-ሳይኮቲክ (antipsychotic) ይባላሉ፡፡ t.me/Gashaw_Aweke ጋሻው አወቀ (የስነ አእምሮ ባለሙያ)

ማሪዋና እና የታዳጊዎች ጤና | ክፍል 03 | ዶ/ር ግርማ ማሞ ሀሺሽ በተማሪዎች ዘንድ በአስደንጋጭ ሁኔታ እየተበራከተ የመጣ የአእምሮ እና አካላዊ ጤናን በእጅጉ የሚጎዳ ሱስ አምጪ ንጥረ ነገር ነው፡፡ የጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት እና ታዳጊዎች ላይ በሀሺሽ ምክንያት የሚመጣን የጤና መታወክ ከመቀነስ አንጻር፤ ስጦታ የህክምና ማዕከል ከወላጆች/መምህራን ጋር የመከረበት እና የግንዛቤ የሰጠበጥ የጤና ፎረም ክፍል 03 እነሆ፡፡

ከዳኒ ትህትና ወደ ዳኒ ጭሷ በሀሺሽ ምክንያት የተበተነው ቤተሰብ

ሀሺሽ/ማሪዋና እና የታዳጊዎች ጤና | ዶ/ር ዮናስ ባህረጥበብ ሀሺሽ በተማሪዎች ዘንድ በአስደንጋጭ ሁኔታ እየተበራከተ የመጣ የአእምሮ እና አካላዊ ጤናን በእጅጉ የሚጎዳ ሱስ አምጪ ንጥረ ነገር ነው፡፡ የጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት እና ታዳጊዎች ላይ በሀሺሽ ምክንያት የሚመጣን የጤና መታወክ ከመቀነስ አንጻር፤ ስጦታ የህክምና ማዕከል ከወላጆች/መምህራን ጋር የመከረበት እና የግንዛቤ የሰጠበጥ የጤና ፎረም ክፍል 01 እነሆ፡፡

የዶ/ር ግርማ ትምህርቶች 01 ዶ/ር ግርማ ስለሱስ የተናገሩት ■ ማንም ሰው ሱሰኛ ለመሆን አቅዶ ሱስ አልጀመረም! ■ ሱስ መጥፎ ነው -- የሚያሳይህ የሚያብረቀርቀውን ነው፡፡ ■ የሱስ አደገኝነቱ እየ
የዶ/ር ግርማ ትምህርቶች 01 ዶ/ር ግርማ ስለሱስ የተናገሩት ■ ማንም ሰው ሱሰኛ ለመሆን አቅዶ ሱስ አልጀመረም! ■ ሱስ መጥፎ ነው -- የሚያሳይህ የሚያብረቀርቀውን ነው፡፡ ■ የሱስ አደገኝነቱ እየገደለህ እንኳን ክፋቱን እንዳታይበት ያደርግሀል፡፡ ■ ሱስ አእምሮህን ይቆጣጠረህና ለእኔ ብቻ ቅድሚያ ስጠኝ ይልሀል፡፡ ■ “ሰቀለ” ሲባል ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? … ልብስ መስቀያን አስቡት፡፡ አንድ ቀጭን ብረት ወይም እንጨት ላይ ልብሳችሁን ትሰቅሉበታላችሁ፡፡ አንድ ሱሰኛ “ሰቀለ” የሚባለው በሱሱ ምክንያት ከስቶ ከስቶ በአጥንት እና ቆዳ ብቻ ሲቀር ነው፡፡ ልብስ መስቀያ፡፡ አንድ እንዲሁ “ሰቃይ” የተባለለት ደንበኛዬ እንዲህ አለኝ፡፡ “‹ሰቀለ› መባል አሪፍነት ይመስለኝ ነበር፡፡ አሁን ሲገባኝ አሪፎቹስ የማይጠቀሙት ነበር”…. (ወረድ ባለ ድምጽ) የሚያሳዝነው ይህ ደንበኛዬ ከባነነ በኋላ ብዙ አብሮኝ መቆየት አልቻለም (አረፈ) ■ አእምሮህ የሱስ ጊዜያዊ ጥቅሙን ሊያስታውስ ይችላል፡፡ አንተ ግን ጉዳቱን አስብ፡፡ አንድ የምትወደው ምግብ ቀርቦልህ ቆሻሻ ብታገኝበት ትጥለዋለህ፡፡ ሱስን ከጊዜያዊ ጥቅሙ ይልቅ ቆሻሻነቱን አስታውስ፡፡ የተፋኸውን ምራቅ መልሰህ አትውጠውም፡፡ ያወጣኸውን ሱስ መልሰህ እንዳትገባበት፡፡ ■ ሱስን መውሰድ ያለብህ እንደ አለርጂ ነው- ከነካኸው ይቀሰቀስብሀል፡፡ አየህ ማኖ መንካት የለብህም፡፡ በተቻለ መጠን ራስህን ሱስ በሚገኝባቸው ቦታዎች እያዞርክ ራስህን አትፈታተነው፡፡

ጥቂት ወንበሮች ቀርተዋል በ0955346528 ወይም https://forms.gle/TVLJScFMPbf9MYG97 ቶሎ ይመዝገቡ መግቢያ #በነጻ
ጥቂት ወንበሮች ቀርተዋል በ0955346528 ወይም https://forms.gle/TVLJScFMPbf9MYG97 ቶሎ ይመዝገቡ መግቢያ #በነጻ

ራስህን አክብር ራስህን ካላከበርክ ማንም ሰው እንደማያከብርህ እወቅ፡፡ ራስህን ማክበርህን ለማወቅ ስለ ራስህም ሆነ ስለ ሃገርህ ሰዎች፣ ስለ ወገኖችህ የምትናገረውን ንግግር አጢነው፡፡ ራስህን ሳታከብ
ራስህን አክብር ራስህን ካላከበርክ ማንም ሰው እንደማያከብርህ እወቅ፡፡ ራስህን ማክበርህን ለማወቅ ስለ ራስህም ሆነ ስለ ሃገርህ ሰዎች፣ ስለ ወገኖችህ የምትናገረውን ንግግር አጢነው፡፡ ራስህን ሳታከብር ወገንህን ልታከብር አትችልም፡፡ ወገኑን የናቀ ሰው በቅድሚያ የናቀው ራሱን ነው፡፡ በሌላ ጎኑ፣ አለባበስህ፣ ለራስህ የምትሰጠው ትኩረት፣ የምትገኝባቸው ስፍራዎች፣ የምትመርጣቸው የጓደኛ አይነቶች ለራስህ የሰጠኸው ዋጋ ምልክቶች ናቸው፡፡ ንጹህ ነኝ ብለህ እያሰብክ ቆሻሻ ቦታ ራስህን ልታገኘው አትችልም፡፡ ጨዋ ነኝ ብለህ እያሰብh ራሳቸውን ከተራ ነገር ለማውጣት ከማይፈልጉ ሰዎች ጋር ማሳለፍ አትችልም፡፡ የምታደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ለራስህ የሰጠኸው ዋጋ ነጸብራቆች ናቸው፡፡ “ለራሳችን ያለንን ክብር አሳልፈን ካልሰጠናቸው በስተቀር ሰዎች ሊወስዱብን አይችሉም” - Mahatma Gandhi ይህንን አትዘንጋ፡- ሰዎች ከሰጠሃቸው መብት የበለጠ ምንም አይነት መብት በአንተ ላይ ሊኖራቸው አይችልም፡፡ እንዳይንቁህ ማድረግ አትችልም፣ ራስህን በማhበር ግን ንቀታቸውን ቦታ ልታሳጣው ትችላለህ፡፡ ስለአንተ ክፉ እንዳያወሩ ማድረግ አትችልም፣ ያወሩትን ክፉ ነገር ተቃራኒ በመኖር ግን ወሬአቸው ውሸት እንደሆነ የማሳየትን መብትህን ግን ሊወስዱብህ አይችሉም፡፡ አብረሃቸው ለማሳለፍና በማንነትህ ላይ ተጽእኖ እንዲያመጡ የፈቀድhላቸው ሰዎች ብቻ በማንነትህ ላይ ያለህን አመለካከት ይወስናሉ፣ ይህንን ደግሞ መቆጣጠር ትችላለህ፡፡