cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወ9 ሒክማ መስጂድ ጀመዓ

{ وَمَنۡ أَحۡسَنُ قَوۡلٗا مِّمَّن دَعَآ إِلَى ٱللَّهِ وَعَمِلَ صَٰلِحٗا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ ٱلۡمُسۡلِمِينَ } ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው? (ሱረት አል-ፉሲለት 33)

Show more
Advertising posts
463
Subscribers
No data24 hours
+57 days
+1830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ክፍል ሰባ ሰባት #77 📅  በእለተ ረቡዕ   ሚያዝያ 23/ 2016 الأربعاء شوال  ٢٢/ ١٤٤٥  Wednesday May   01/ 2024 ከመግሪብ እስከ ኢሻ በኡስታዝ ሙስጠፋ አደም በሳሪስ ሒክማ መስጂድ የተሰጠ የቁርኣን ተፍሲር ትምህርት።     መሰል ትምህርቶችንና ተጨማሪ መልዕክቶችን ለመከታተል ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉ። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/Hikmamesjid https://t.me/Hikmamesjid
Show all...
👍 3
🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰 ረሱል (🤍) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿خيرُ الأصحابِ عندَ اللهِ خيرُكم لصاحبِه، وخيرُ الجيرانِ عندَ اللهِ خيرُكم لجارِه﴾ “አላህ ዘንድ መልካም ጓደኛ ማለት ለጓደኛው መልካም የሆነው ነው። አላህ ዘንድ መልካም ጎረቤት ማለት ለጎረቤቱ መልካም የሆነው ነው።” 📚 ሶሂህ አልጃሚ: 3270
Show all...
3
🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰 السلام عليكم ورحمة الله وبركات! ኢንሻአላህ ዛሬ ሚያዝያ 17/2016 ባለን ፕሮግራም መሰረት ከመግሪብ እስከ ኢሻ በኡስታዝ ሙስጠፋ አደም አማካኝነት የሚሰጠው የቁርኣን ተፍሲር ትምህርት ሱራህ  አል-ሙናፊቁን (የመናፍቃን  ምዕራፍ)  ሲሆን ፕሮግራማችንን በማስተካከል፣ያልሰሙትን በማሰማት እና ቤተሰቦቻችንን በመጋበዝ በጊዜ እንድንገኝ ሁላችንም ተጋብዘናል። 📚 وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ ወደ አሏህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው!? 🏷መቅረት ባይቻልም በስራ ጫና እና የቦታ እርቀት ገድቧችሁ ዛሬን መምጣት ለማትችሉ እህትና ወንድሞች በዚህ ቴሌግራም ቻናል ቀጥታ ትምህርቱን በድምፅ የምናስተላልፍ በመሆኑ ለብዙሀኑ ይደርስ ዘንድ ሼር በማድረግ ሰወችን ወደ ቻናሉ እንዲቀላቀሉ ያድርጉ። 👉አድራሻ:- ሳሪስ አል-ሒክማ መስጂድ 🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰 https://t.me/Hikmamesjid https://t.me/Hikmamesjid
Show all...
👍 3
🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰 ረሱል (🤍) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إِذَا قَرَأَ ابْنُ آدَمَ السَّجْدَةَ، فَسَجَدَ اعْتَزَلَ الشَّيْطَانُ يَبْكِي يَقُولُ: يَا وَيْلِي، أُمِرَ ابْنُ آدَمَ بِالسُّجُودِ، فَسَجَدَ، فَلَهُ الْجَنَّةُ، وَأُمِرْتُ بِالسُّجُودِ، فَأَبَيْتُ، فَلِي النَّارُ﴾ “የአደም ልጅ ሱጁድ ሲያደርግ ሸይጣን እያለቀሰ ይሄዳል። እንዲህም ይላል፦ ወይኔ! እሱ ሱጁድ እንዲያደርግ ታዘዘ ሱጁድ አደረገ፤ በመሆኑም ጀነት የሱ ሆነች። እኔ ግን ሱጁድ እንዳደርግ ታዘዝኩ እምቢ አልኩ ስለሆነም ጀሀነም እጣፋንታዬ ሆነ።” 📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 81
Show all...
🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰 "በህይወትህ ሶብረኛ መሆን ከቻልክ የምትፈልጋቸው ነገሮች በሙሉ ግዜያቸውን እየጠበቁ ወዳንተ ይመጣሉ፡፡         በፍቅር አለም ውስጥም ትልቁን ዋጋ ሚያስከፍለው ትእግስት ነው፡፡ መሶበር ይከብዳል፡፡ ያ' ግዜ ሲያልፍ ግን ምንፈልገውን እናገኛለን፡፡መራራውን ግዜ አልፈህ ጣፋጩን ፍሬ ትበላ ዘንድ ሶብረኛ ሁን፡፡ ሶብረኞች ከ ጉልበተኞች ይበልጣሉና፡፡"
Show all...
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ኡስታዝ ዛሬ ቀጥታ ወደትምህርቱ የገባ ባለመሆኑና ዝናብ እየዘነበ በመሆኑ የጥራት ችግር ይኖራል በሚል ቀጥታ መተላለፍ ባለመቻሉ ይቅርታ እንጠይቃለን
Show all...
👍 1🥰 1👏 1
🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰 السلام عليكم ورحمة الله وبركات! ኢንሻአላህ  ዛሬ ማክሰኞ ሚያዝያ 22/2016 ባለን ፕሮግራም መሰረት ከመግሪብ እስከ ኢሻ  በኡስታዝ ኢንጂነር ጅብሪል አክመል አማካኝነት የኪታቡ ተውሂድ ደርስ(ትምህርት)የሚሰጥ በመሆኑ ፕሮግራማችንን በማስተካከል፣ያልሰሙትን በማሰማት እና ቤተሰቦቻችንን በመጋበዝ በጊዜ እንድንገኝ ሁላችንም ተጋብዘናል። 📚ኪታቡን ይዞ መምጣት እንዳትረሱ ""እዉቀት ለሰዉ ልጅ ብርሀን ነዉ።   ➡️"እዉቀት ለመቅሰም ወደ ኃላ ማለት አይገባንም እስልምና እምነታችን በእዉቀት ላይ የተመሰረተ ዲን (ሀይማኖት ) ነዉ እና።ለዱንያም ለአሄራም ከማይጠቅሙን ነገሮች ቢዚ ከመሆን  እራሳችን እንቆጥብ""     👉አድራሻ:- ሳሪስ ሒክማ መስጂድ
Show all...
👍 2 1
🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰 🔐 ሴት ልጅ ባሏ በሀሳብ ቢቃረናትም ሸሪዓን በሚጥስ ነገር እስካላዘዛት ድረስ ባሏን የመታዘዝ ግዴታ አ ለባት!! ————— ይህ ነጥብ ብዙዎች ዘንድ የተዘነጋ ነጥብ ነው። ሚስት ባሏን መታዘዝ ግዴታ የሆነባት ባል የርሷን ሀሳብ በማይነቅፍ ነገር ሲያዛት ብቻ ሳይሆን በዋነኝነት የርሷን ሀሳብ በሚነቅፋት ነገር ሲያዛት ነው። የሀሳብ ልዩነት በሌለው ነገርማ ማንኛውም አካል በአንድ ነገር ላይ ተነጋግሮ የሀሳብ ልዩነት እስከሌለ ተስማምቶ ይጓዛል። አብሮ መጓዝ የማይቻለው የሀሳብ ልዩነት ሲፈጠር ነው። በባልና ሚስት መካከልም መለያየቱ የሚፈጠረው በዋነኝነት የባልን ትእዛዝ አለማክበር ሲከሰት ነው። ➤ ሚስት የሀሳብ ልዩነት ሲፈጠር ባሏን የማትታዘዝ ከሆነ አላስፈላጊ ንትርኮችና ጭቅጭቆች ይፈጠራሉ!!። ይህ ማለት ደግሞ በመካከላቸው የነበረው ፍቅርና መተሳሰብ በአጭር ጊዜ ይሻክራል። ይህ ደግሞ በትዳራቸው ውስጥ ከባድ አደጋ ይሆናል። እህቶች ሆይ! የሚከተለውን የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ንግግር ልብ ብላችሁ አንብቡት:- قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: «إذا صلت المرأة خمسها وصامت شهرها وحفظت فرجها وأطاعت زوجها قيل لها ادخلي الجنة من أي أبواب الجنة شئت» . ورواه ابن حبان في صحيحه عن أبي هريرة رضي الله عنه، والحديث صححه الألباني في الجامع الصغير. አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- “ሴት ልጅ አምስት ወቅቷን ከሰገደች፣ የረመዷን ወሯንም ከፆመች፣ ብልቷንም (ከዝሙት) ከጠበቀች፣ ባሏን ከታዘዘች በፈለግሽው የጀነት በር ግቢ ትባላለች።” [ኢብን ሂባን በሶሂሃቸው የዘገቡት ሲሆን አልባኒም በጃሚዑ ሰጊር ሶሂህ ነው ብለውታል] 🌷 እህቶቼ ሆይ! ይህ ቀላል ነገር አይደለምና ልዩ ትኩረት ስጡት!!። የባልን ትእዛዝ ላለማክበር የተቀመጠው መስፈርት አንድ ነገር ብቻ መሆኑን አስተውሉ እሱም "ሸሪዓን በሚጥስ ነገር ካዘዘ አለመታዘዝ ነው" በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ግን ብዙ ጊዜ እህቶች ዘንድ የሚስተዋለው ነገር ባል (አላህ ይጠብቀንና) ሸሪዓን በሚጥስ ነገር ሲያዛቸው ይታዘዙትና ሀሳባቸውን በሚቃረን ነገር ሲያዛቸው ደግሞ አለመታዘዛቸው ነው። መልእክተኛው (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሴት ልጅ ባሏን መታዘዟን በተመለከተ ከታላላቅ ዒባደዎች "ከሶላት፣ ብልቷን ከዝሙት ከመጠበቅ፣ የረመዷን ወርን ከመፆም" ጋር አያይዘው ነው ጀነት ለመግባቷ እንደ ሰበብ የጠቀሱት። ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚየህ (ዐለይሂ ረህመቱላህ) ሴት ልጅ የባሏን ሀቅ አስመልክተው የአላህንና የመልእክተኛውን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሐቅ ከማክበርና ከመጠበቅ ጋር በማያያዝ እንዲህ አሉ:- قال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله تعالى: "ليس علي المرأة بعد حق الله ورسوله أوجب من حق الزوج." (مجموع الفتاوى: 32/260) "በአንዲት ሴት ላይ ከአላህና ከመልክተኛው ሀቅ በመቀጠል ከባሉዋ ሀቅ በላይ ግዴታ የለባትም።" [መጅሙዕ አል-ፈታዋ 32/260] قال الإمام ابن تيمية رحمه الله:- (المرأة المتزوجة طاعتها لزوجها أفضل من طاعتها لأبويها) مجموع الفتوى 10-428 ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚየህ (ረሂመሁላህ) ባለ ትዳሯ ሴት ባሏን የመታዘዝ ደረጃው ምን ያህል እንደሆነም እንዲህ ሲሉ ይገልፃሉ:- “ባለ ትዳሯ ሴት ለባለቤቷ መታዘዟ ወላጆቿን ከምትታዘዘው ይበልጥላታል።” [መጅሙዕ አል-ፈታዋ 10/428] ## አንዳንድ ወላጆች አላህን ፍሩ ልጆቻቹ ከዳራቹ በኋላ የባሌ ሀቅ ባሌ ፍቃደኛ አይደለም ባሌ አያስደስተውም  ስትል የምትሉት ነገር በጣም የከፋ ነገር ነው። ልክ እንደናንተው የሱም ሀቅ አለው እንደውም የበለጠ ሀቅ። منقول
Show all...
🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰 በሚገጥምህ ነገር ከማማረር እና ከማዘን ይልቅ ምን ሊያስተምረኝ ነው በል። የአንድ ነገር መጨረሻ የሌላ ነገር መጀመሪያ ነውና!
Show all...
👍 1
🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰 በሚገጥምህ ነገር ከማማረር እና ከማዘን ይልቅ ምን ሊያስተምረኝ ነው በል። የአንድ ነገር መጨረሻ የሌላ ነገር መጀመሪያ ነውና!
Show all...