MAKO TTC CENTER
Open in Telegram
Centering Soul Cultivating charisma Maintaining Balance!
Show more5 746
Subscribers
No data24 hours
-127 days
-11930 days
Posts Archive
5 746
FDP Training: 3 days package
ኑ በማኮ የተርቢያ የስልጠና እና የኮቺንግ ማዕከል ውስጥ ሁለንተናዊ ለውጥን እንጎናፀፍ!
5 746
ንቁ እና ብቁ እናት
-በእያንዳንዱ ልጆቿ መሃከል ላለው ልዩነት እውቅና በመስጠት ሁሉንም በራሱ ቋንቋ ታናግራለች
- በእያንዳንዱ ልጆቿ ውስጥ ያለውን ዓቅም በመለየት ማደግ ለሚገባው ዘር በቂ ኩትኮታ ታደርጋለች
-ልጆቿ የእሷ የስሜት ነፀብራቅ መሆናቸውን ስለምታውቅ ከነሱ እንዲመነጭ የማትፈልገውን ስሜት ከሷ እንዲያገኙ አታረግም
-የእሷ ሁለንተናዊ ጤንነት ለልጆቿ መሰረታዊ ቀለብ መሆኑን ስለምትገነዘብ እራሷን እና ጤናዋን በማስጠበቅ ልጆቿን ታከብራለች
-ለአካላቸው መጎልበት እና መፋፋት ከምትለፋው እኩል ወይንም በላይ ለስሜታቸው ጤና እና ለአዕምሯቸው ሰላም ይበልጥ ትተጋለች
ማኮ የተርቢያ፣የትሬኒንግ እና ኮቺንክ ማዕከል
5 746
በእያንዳንዳችን ውስጥ የአንዳችን ፈውስ አለ!
መኖር በህይወት በመቆየት የሚለካ ቀላል ነገር አይደለም፤ መኖር በዓላማ እና በትኩረት የታጀበ ከደመነፍስ የራቀ እውነት ነው። መኖር መገኘትን፣ማስተዋልን እና መከታተልን ያዘለ ከአኗኗሪነት በላይ የመሆን አቅም ነው!
ስለዚህ :
-አብረን መኖራችን አንዳችን ላንዳችን መኖራችንን አያሳይም!
-ትኩረታችንን ላላገኘ እና ማስተዋለለችንን ላልቸርነው ሰው ኑረንለታል ልንል አንችልም!
-ቅርበት በሜትር የሚለካ ሳይሆን በስሜት የሚመነዘር ነው!
-መኗኗር ቦታን ከመጋራት ከፍ ያለ ልብ እና ጆሮን የመከፈት ሂደት ነው!
በመሆኑም ኑሯችን ጥራት መመዘኛ ካለው መመዘኛው የአጋራችንን የልብ ትርታ ማድመጥ በመቻል እና ባለመቻላችን የሚለካ ይሆናል!
ማኮ የተርቢያ የስልጠና እና የኮቺንግ ማዕከል !
5 746
ሁሉም ነገር የራሱ ምርጥ እና የመጨረሻ ገፅታ አለው! ሴትነስ እውቀት፣ ትኩረት እና ጊዜ ሲያገኝ ምርጡ እና የመጨረሻው ገፅታው ምን ይመስል ይሁን?
ሚዛናዊ አኗኗር እና እይታ የሴትነት መሰረታዊ ሃሳብ ነው፤ ግርማ ሞገስ እና ስላም ያላብሳል
በዚህ ስልጠና ውስጥ :
-የባህሪያችንን እና የስሜታችንን መነሻ በመዳሰስ የህይወት ማነቋችን ከየት እንደጀመረ እንረዳለን
-ከሴትነት ሚዛን መሳት ምን እንደሚመስል እና እንዴት ወደ ትክክለኛው ቦታችን መመለስ እንደምንችል እንማማራለን
-የሴትነትን የኃይል ሚዛን በማስጠበቅ ግንኙነቶቻችንን እንዴት ማሳመር እንደምነችል እናያለን
-በአዕምሮ ንቁ፣ በስነልቦና ብቁ፣ በመንፈስ ጠንካራ እና በስሜት በሳል የሆነችውን ሴት ለመሆንም ካለንበት ቦታ አብረን ጉዞ። እንጀምራለን!
-ሳይንሳዊ እና መንፈሳዊ መነሻዎች ላይ በመደገፍ ካለንብት አንድ ደረጃ ከፍ እንላለን!
ኑ በማኮ የተርቢያ፣ የስልጠና እና የኮቺንግ ማዕከል እንገናኝ!
