cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Lij_Abel ኦርቶዶክሳዊ

የልዑል እግዚአብሔር፣ የቅድስት ድንግል ማርያም ወዳጅ፣ በቅዱሳን ተራዳይነት ያደኩ እኔ የተዋህዶ ልጅ ነኝ:: ሙዚቃ አልሰማም፣ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር ብቻ እዘምራለሁ !! - ሥርዓተ ቅዳሴ - ስብከት - መዝሙር ጥናት - መፅሐፍ - ገዳማት ይዳሰሱበታል!! እግዚአብሔር ይመስገን:: ሀሳብ አስተያየት በ @abelbeen ማካፈል ይሻላል ።

Show more
Advertising posts
1 896
Subscribers
+14324 hours
+1147 days
+41230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ፃድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በተወለዱበት ቤት አልኖሩምና እናት አባታቸው የሥጋ ዘመዶቻቸውም አላወቋቸውም፡፡ በበረሃ ብቻቸውን ኖሩ እንጂ፡፡ ነገር ግን ሰማያውያን ሁሉ ወዳጆቻቸው ሆኑ፤ እመቤታችን ወዳጄ ትላቸዋለች፡፡ ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ወገናችን ይሏቸዋል፡፡ መላእክትም ወዳጃችን እያሉ በክንፋቸው ያቅፏቸዋል፡፡ የአባታችን መዓዛቸው ጫካውን ይሞላው ነበር፡፡ በመንፈስ ቅዱስም ኃይል ወደፈለጉት ቦታ በፍጥነት እንደወፍ ይበራሉ፡፡ ስለተሰጣቸውም ጸጋ የበረሃ እንስሳት (አንበሳና ነብር)  ሁሉ ያገለግሏቸዋል፡፡ አባታችን ሁልጊዜ እንዲህ ይሉ ነበር፡-  
‹‹የሚጣፍጥ ምግብን መውደድ ኃጢአትን ያመጣል፣ ሞትን ያስከትላል፡፡ ክንፍ ያላቸው የሰማይ ወፎች እንኳን በመብል ምክንያት ይጠመዳሉ፣ ምግብ በመሻት ከምድር ላይ ይወድቃሉ በወጥመድም ይያዛሉ፡፡ የሰው ልጅም ምግብን በመውደድ በኃጢአት ይወድቃልና እኔስ ለሰውነቴ ምግብ መጠጥን አልፈልግም፤ ልብስም አልሻም ዕራቁቴን ከእናቴ ማኅፀን እንደወጣሁ እንዲሁ ዕረቁቴን ወደ መቃብር እመለሳለሁ እንጂ፡፡ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም በሞት በተለየሁ ጊዜ መብል መጠጥንና ልብስን ማን ያስከትልልኛል?›› 
አሉ፡፡ ዳግመኛም ‹‹ሰው ሊደርስ በማይችልበት በረሃ እኖራለሁ፣ ነጣቂ ተኩላዎችና አራዊቶች ባሉበት እነርሱ እንዲበሉኝ ሥጋዬን እጥላለሁ፤ ዳዊት በመዝሙር 
‹‹የጻድቃን ሥጋቸው ለዱር አራዊት ነው››
 እንዳለ እኔ
ክፉ አውሬዎች፣ ተናዳፊ እባቦችና ዘንዶዎች ወዳሉበት እገባለሁ ምግብም እሆናቸው ዘንድ እወዳለሁ››
 በማለት አባታችን ራሳቸውን ለሞት አሳልፈው ይሰጡ ነበር ነገር ግን አራዊቱ ሁሉ እየሰገዱላቸው ይገዙላቸው ከእግራቸውም በታች ይተኙ ነበር፡፡ እንደሚታዘዝ ደቀ መዝሙርም ይታዙላቸው ነበር፤ ለጸሎትም በሚቆሙበት ጊዜ አብረዋቸው ይቆማሉ፡፡ በፊታቸውም ይጫወታሉ፡፡ በአንደኛው ዕለት አባታችን ጸሎታቸውን እንደጨረሱ ሰማይ ተከፍቶ የእሳት ድንኳን ተገልጦ አርባእቱ እንስሳ የእግዚአብሔርን ዙፋን ተሸክመው ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ ማዕጠንት ይዘው፣ ቅዱሳን መላእክትና አለቆቻቸው በየነገዳቸው በዙሪያው ቆመው ጌታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአንድነት በሦስትነት እንዳለ ተገለጠላቸው፡፡ አባታችንም ይህንን ባዩ ጊዜ እጅግ ፈርተውና ደንግጠው መሬት ላይ ወደቁ፡፡ ጌታችንም ካጸናቸውና ካበረታቸው በኋላ ‹‹ዮሐንስ ቀለምሲስ እኔን እንዳየኝ አንተም እኔን ማየት የምትችልበትን ኃይል እሰጥሃለሁ፤ ወዳጄ ሆይ ምን ትሻለህ? የምትጠይቀኝስ ነገር ምንድነው? ልይህ ብለህ በለመንከኝ ጊዜ ተገልጥኩልህ፡፡ ሰማንያ ዓመት በጫካ ኖርክ፤ በረሃዎችን ዞርክ፤ ከአንበሶችና ነብሮች ከአራዊትም ጋር መኖርን አልፈራህም፤ ጨክነህ እስከ ሞት ድረስ ታገሥህ፡፡ የመረጥኩህ ወዳጄ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! ምን አደርግልህ ዘንድ ትወዳለህ?›› አላቸው፡፡ አባታችንም ይህንን ቃል ከጌታችን ሲሰሙ 
‹‹አምላኬ ሆይ ይህን ልታደርግልኝ አይገባኝም፡፡ በፊትህስ ሞገስን ካገኘሁ የገቦታን ሰዎች ማርልኝ፤ እነርሱ ኃጥአን ናቸውና አንተ ንስሓን ለማይሹ ጻድቃን አልመጣህምና ኃጥአንን ወደ ንስሓ ልትመልስ ነው እንጂ›› አሉት፡፡ ዳግመኛም ‹‹አቤቱ እንደ ክረምት ውኃ እንባቸውን እያፈሰሱ ጥርሳቸውን እያፋጩ በደይን የሚኖሩትን አስባቸው፤ ሰይጣን አስቷቸዋልና፤ በማወቅ ባለማወቅ በሠሩት ማራቸው፤ ይቅር በላቸው›› እያሉ ለመኑት፡፡ ጌታችንም ‹‹ወዳጄ ሆይ የለመንከኝን አልከለክልህም፣ እንደቸርነቴም ስምህን የጠሩትን መታሰቢያህን ያደረጉትን ኃጥአንን ምሬልሃለሁ፤ የለመንከኝንም ሁሉ አደርግልህ ዘንድ ቃል ኪዳንን ሰጥቼሃለሁ›› 
አላቸው፡፡ አባታችንም እጅግ ደስ ብሏቸው በግንባራቸው መሬት ላይ ወድቀው ጌታችንን ሲያመሰግኑት ቅዱሳን መላአክትና ሰማያውያን ቅዱሳን ሁሉም አብረው ተደስተው እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡
Show all...
🙏 10😍 2👏 1👌 1
✅ #የእምነትሽ_ፅናት ➡️ #ዘማሪት_ሲስተር_ሊድያ
@LijAbelOrthodoxawibot ይጋብዙ።
#Mezmur #መዝሙር #ቅድስት_አርሴማ ✅✅✅✅✅ ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Show all...
ዘማሪት_ሲስተር_ልድያ_New_Ethiopian_Orthodox_Mezmur_2022.m4a5.67 MB
8🙏 4😍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ሐምሌ ፮ እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ ለቅድስት አርሴማ በዓል በረከቷ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን።
Show all...
🙏 12 9👌 1
00:30
Video unavailableShow in Telegram
ይሄን ማለፍ አልቻልኩም❤
Show all...
6.89 MB
22🙏 8🥰 3👌 2
Photo unavailableShow in Telegram
ከፀድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ስዕለ አድኖ ስር ነብር እና አንበሳ ይታያል። ለመሆኑ ትርጉሙ ምንድነው ? እያሰላሰላችሁ እደሩ። ነገ ትንሽ ፅሁፍ ለማስቀመጥ እሞክረሰለሁ፣ እግዚአብሔር ይርዳን🙏🙏 መልካም አዳር
Show all...
🙏 11 6🤔 6👌 2🥰 1
🔹🔹🔹🔹🔹 ፆመ ሐዋርያት ዛሬ ተፈፀመ። ፆም ፀሎታችንን እግዚአብሔር ይቀበለን። አሜን🙏🙏
የምንናፍቃት ፆመ ፍልሰታ ነሐሴ ፩ ትጀምራለች።
Show all...
13🙏 7👌 3👏 2
🎙 #ርዕሰ_ባህታዊያን 📣 #ሊቀዘማሪ_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ @LijAbelOrthodoxawibot #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ #አቡዬ 🎥✍️✍️✍️✍️✍️✍️ ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Show all...
ርዕሰ_ባህታዊያን_ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ.m4a5.09 MB
7👏 4🙏 3👍 1👌 1
ጥያቄ ቁጥር ፵፬ ከሚከተሉት ውስጥ በትክክል ያልተዛመደው የቱ ነው?Anonymous voting
  • ምድረ ከብድ -- አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
  • ደብረ ምጥማቅ ፃድቃኔ -- እመቤታችን ቅድስት ማርያም
  • ሲሪንቃ -- ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ
  • መልስ የለም
0 votes
12👏 3🙏 3👌 3
Photo unavailableShow in Telegram
ሀምሌ ፭ አባታችን #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ለሰባት አመት ያክል ቆመው በትጋት ወደሰማይ አንጋጠው ሲፀልዮ ሰ ይ ጣ ን በፅናታቸው ተናዶ በቁራ ተመስሎ መቶ አይናቸውን ኣንቁሮ አ ጥ ፍ ቶባቸዋል በጠፋው ኣይናቸው ትጋታቸውን ሳያቋርጡ ለሁለት ሳምንት ያክል በጠፋ አይናቸው ሲፀልዮ ሀምሌ አምስት ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መታ የብርሀን አይን የሰጠቻቸው ቀን ነው::
Show all...
11🙏 7👌 2😍 2
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.