en
Feedback
📘📕ከመፅሐፍት መሐል📙📗

📘📕ከመፅሐፍት መሐል📙📗

Open in Telegram

☞ ይህ ቻናል መግቢያም ሆነ አጥር የለውም እንደ ሰው ለሚያስብ ብቻ ተከፍቷል። [ ° ° በየቀኑ የተለያዩ የስነፅሁፍ ስራዎች ሚቀርቡበት ቻናል ° ° ] ❖ ጥንታዊ ፍልስፍናዎች ❖ ሳይኮሎጂ ❖ አስደማሚ ታሪኮች ❖ አጫጭር ልብወለዶች ❖ ቁም ነገሮችና አጅግ በረካታ ሀሳቦችን ለናንተ ይቀርባል [ ° ° Others channel ° ° ] @Ethio_treca @Ethio_books33 @Yotor_Tereka

Show more
288
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
..... ከህመሞች ሁሉ ትልቁ ህመም ካንሰር ወይም ኤድስ ሊመስለን ይችላል። እውነቱ ግን #ከስብዕና_መዛባት የከፋ ህመም የለም። ውጫዊ መልክ የሰው የገፅ ሽፋን ነው። ስብዕና ግን የሰው እውነተኛ መልክ ነው። በየእለቱ አብረን የምንኖረው ሰው ቢኖር ፤ እውነተኛ የማያረጅ ዘላቂ ማንነታችን ስብእናችን ነው። በዓይናችን የማናየው እውነተኛ መልካችን በውስጥ ማንነታችን ውስጥ ተቀብሮ ያለው ስብዕናችን ነው።የስብዕና እኩልነት ፣ ጠባሳዎችና መዛባቶች ቤት ያፈርሳሉ ፣ አገር ይንዳሉ ግንኙነት ይመርዛሉ። ለማከው ለማዳን ብቻ ሳይሆን ለማየትና ህመሙን ለመረዳትም አዳጋች ነው። ስብዕና በልጅነት እንደተቦካ ሲሚንቶ ፣ በአዋቂነት ደግሞ እንደ ደረቀ አርማታ ነው። የብሱ ሰው ስብዕና እንደ ተቦካ ሲሚንቶ በልጅነት ጊዜ በትክክል የሚቀርፀው ካላገኘ ተንሻፎ እና ተዛብቶ ያድጋል። እድሜው ከገፋ በኋላ ደርቆ ስለሚጠነክር ብዙ ጊዜ ለመከራ መዶሻና ለምክር መጥረቢያ አዳግቶት አገር ያጠፋል። የልጅ ውበቱ በቀላሉ መሰራቱ.... ያዋቂ ክፋቱ ለመለወጥ አስቸጋሪ የሆነ ክፉ እውቀቱ ነውና። ✍🏾 ደራሲ ዶ/ር ምህረት ደበበ 📙 ሌላ ሰው ♦️ ❍✰ @FromBooks776 ✰❍ ♦️ ♡ ㅤ       ❍ㅤ         ⎙ㅤ        ⌲             ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

...ከዘንባባና ከሰሜናዊት ቆንጆዎች ሹሩባ ጥላ ሾር ላንዳፍታ እረፍ ፤ ጋደም በማለት እንደ ኩል ከጠራ ሰማይ ላይ የምታበራውን ሰሜናዊ ኮከብ በጠረፍ ጨረቃ በእፎይታ መመልከት ምነኛ ደስ ይል ይሁን? ሰላም ናፋቀኝ! ጦርነት በህይወት እና በቁስ ላይ የሚያስከትለው ጥፋት የበለጠ የሚያስጠላኝ ነገር በዚህ አለም ላይ ያለ አይመስለኝም። የሰው ልጅ በመካከሉ የሚፈጠሩትን ልዩነቶች በውይይትና በሰላም የሚፈታበት ቀን ናፈቀኝ። ለምንድን ነው የሰው ልጅ በሰላም የማይኖረው? ያለጦርነትም ሕይወት ልሡ አጭር ናት። ✍🏾 ደራሲ ፥ በዓሉ ግርማ 📙 ኦሮማይ ♦️ ❍✰ @FromBooks776 ✰❍ ♦️ ♡ ㅤ       ❍ㅤ         ⎙ㅤ        ⌲             ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

✥••┈┈┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈┈┈••✥ ✝ ​​እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ✝ ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም 🙏 አደረሳችሁ አደረሰን 🙏 ✥••┈┈┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈┈┈•
✥••┈┈┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈┈┈••✥ ✝ ​​እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ✝ ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም 🙏 አደረሳችሁ አደረሰን 🙏 ✥••┈┈┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈┈┈••✥

ቃልኪዳን መፅሀፍ በደራሲ ጌታቸው አያልቄ ተደርሶ በ 19890 G.C የመጀመሪያ እትም ታትሞ ለአንባቢያን የቀረበ ድንቅ የአገራችን መፅሀፍ ሲሆን ተወዳጅ በመሆኑም ለ 6 ጊዜዓት ለዕትም የበቃ ምርጥ ጥ
ቃልኪዳን መፅሀፍ በደራሲ ጌታቸው አያልቄ ተደርሶ በ 19890 G.C የመጀመሪያ እትም ታትሞ ለአንባቢያን የቀረበ ድንቅ የአገራችን መፅሀፍ ሲሆን ተወዳጅ በመሆኑም ለ 6 ጊዜዓት ለዕትም የበቃ ምርጥ ጥበብ የታየበት መፅሀፍ ነው ። እኛም መፅሀፉን በሚመጥን መልኩ ተጨንቀን ተጠበን በትረካ መልክ አዘጋጅተን ወደ እናንተ ልናቀርብ ዝግጅታችንን ጨርሰናል. በቅርቡ ወደ እናንተ ይዘን እንቀርባለን እስከዛው share , like , comment አድርጉልን።

< የተፈጥሮ የመገንዘብ አቅም ካልታከለበት የአዋቂነት መሠረት በመማር ብቻ አይመሰረትም። ብዙ ተምረው ምንም የማያውቁ ልሂቃን አሉና።> ✍🏾 ደራሲ ፥ ይስማዕከ ወርቁ 📙 ደህንነቱ ♦️ ❍✰ @FromBooks776 ✰❍ ♦️ ♡ ㅤ       ❍ㅤ         ⎙ㅤ        ⌲             ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

< የተፈጥሮ የመገንዘብ አቅም ካልታከለበት የአዋቂነት መሠረት በመማር ብቻ አይመሰረትም። ብዙ ተምረው ምንም የማያውቁ ልሂቃን አሉና።> ♦️ ❍✰ @FromBooks776 ✰❍ ♦️ ♡ ㅤ       ❍ㅤ         ⎙ㅤ        ⌲             ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

Repost from Yotor Books
ጸሎት ማድረግ የምችል አይመስለኝም። ሁልጊዜ ለጸሎት ስቆምም ሆነ ስንበረከክ የምለው ይጠፋኛል። ምስጋና ሳበዛ የጎደለኝ ትዝ ይለኛል። ጥያቄ ሳበዛ የተደረገልኝ በአይነ ሕሊናዬ ይመጣና ውለታ ቢስ የሆንኹ ይመስለኛል። ወዲያው ደግሞ ግሳንግስ ኃጢያቴ ትዝ ይለኝና የማመስገንም የመጠየቅም ሐሳቤ ይጠፋና ሀፍረቴ ይመጣል። ለማመጣጠን ስሞክር ደግሞ ጸሎቱን ትቼ ሾል የያዝኩ ይመስለኛል። በቃል ያጠናሁትን የተለመደ ጸሎት ባደርግ ይሻላል ብዬ ስጀምር ራሴን መጨረሻው ላይ አገኘዋለሁ። በንባብም ቢሆን ያው ነው። አንዳንዴ ለራሴ፦ ሰው እንዴት ከፈጣሪው ጋር መነጋገር ያቅተዋል? ከስንቱ የሰው አይነት ጋር እየተግባባሁ እንዴት ከአምላኬ ጋር መግባባት ያቅተኛል? እያልኩ በራሴ አዝናለሁ። ✍🏾 ደራሲ ፦ አለማየሁ ዋሴ እሸቴ 📙 ፦ ሚተራሊዮን ♦️ ❍✰ @Ethio_treca ✰❍ ♦️ ♡ ㅤ       ❍ㅤ         ⎙ㅤ        ⌲             ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

"ማንም ሰው የበላይም የበታችም አይደለም። ግን ደግሞ እኩልም አይደለም። በቃ! ሰዎች የተለያዩ ናቸው። አይወዳደሩም ፤ አይነፃፀሩም። አንተ አንተን ወይንም ራስህን ነህ። እኔ ደግሞ እኔን ነኝ። " •
"ማንም ሰው የበላይም የበታችም አይደለም። ግን ደግሞ እኩልም አይደለም። በቃ! ሰዎች የተለያዩ ናቸው። አይወዳደሩም ፤ አይነፃፀሩም። አንተ አንተን ወይንም ራስህን ነህ። እኔ ደግሞ እኔን ነኝ። " ••• ባግዋን ራጅኒሽ (ኦሾ) ♦️ ❍✰ @FromBooks776 ✰❍ ♦️ ♡ ㅤ       ❍ㅤ         ⎙ㅤ        ⌲             ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

✍ዓለማየሁ ገላጋይ ሰውየው ደስተኛ ህይወት እየመራ ነው ። በሄደበት ሁሉ ፈጣሪው ከጎኑ እንዳለ በፅኑ ያምናል ። ደግሞም እውነቱን ነበር ። በመንገዱ ሁሉ ፈጣሪው ከጎኑ መሆኑን የሚያረጋግጥበት አንድ ዘዴ ነበረው ። ሲጓዝ ከእርሱ የእግር ፈለግ በተጨማሪ ሌሎች ሁለት የጫማ ማህተሞችን አሸዋው ላይ ይመለከታል ። የፈጣሪው አንደሆነ አውቆ ደስ ይሰኛል ። ሰውየው ህይወት ድንገት ከደስታ ወደ መከራ ተለወጠ ። ችግርና ለቅሶ አብዝተው ጎበኙት ። በዚህ ጊዜ በመንገዱ ላይ መለሾ ብሎ ፈጣሪው ከጎኑ መኖሩን ለማረጋገጥ ቢሞክር ተጨማሪውን የጫማ ዱካ አጣው ። "በደስታዬ ጊዜ ከጎኔ የነበረውን አምላክ በመከራዬ ጊዜ አጣሁት ፣ እርሱም እንደሰው ችግሬን ላለመካፈል አፈግፍጎ እነሆ በመንገዴ ላይ የእኔ ብቻ የእግር ዳና ቀረ"አለ ። አማረረ ፣ ላገኘው ሁሉ የፈጣሪን በመከራ ጊዜ ከጂነት መሰከረ ። አንድ ቀን በሰውየው የመከራ ጉዞ ላይ ፈጣሪው እንዲህ የሚል ቃሉን ሰደደለት ። "በመከራ ጊዜ አንተን ስለተሸከምኩ ፣ ብቻውን የቀረው የእግር ዳና የአንተ ሳይሆን የእኔ ነው ። " ♦️ ❍✰ @FromBooks776 ✰❍ ♦️ ♡ ㅤ       ❍ㅤ         ⎙ㅤ        ⌲             ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

Repost from Yotor Tereka
ከአጋታ ክርስቲ በስራወቿ እንዲሁም በመጽሐፍ ሽያጭ ከፍተኛ ዝናን ካተረፉት ደራሲወች መካከል ግንባር ቀደም ናት። ዛሬ ደግሞ በቻናላችን የአጋታ ስራ የሆነውንና ታዋቂውን ክህደት የተሰኘውን መጽሐፍ በት
ከአጋታ ክርስቲ በስራወቿ እንዲሁም በመጽሐፍ ሽያጭ ከፍተኛ ዝናን ካተረፉት ደራሲወች መካከል ግንባር ቀደም ናት። ዛሬ ደግሞ በቻናላችን የአጋታ ስራ የሆነውንና ታዋቂውን ክህደት የተሰኘውን መጽሐፍ በትረካ ልናቀርብላችሁ ነው። የእንግሊዘኛው ርዕስ Unknown destination በመባል ይታወቃል። ቆንጆ የስለላ መጽሐፍ ነው። Yotor Terrka ን በመቀላቀል ይከታተሉ። https://t.me/+Reyc3bYs7AA3MTg0

🌿የህልም እንጀራ! ሆንግኮንግ/አሜሪካዊው ብሩስ ሊ (Bruce Lee) ታዋቂ አክተር፣ ብቁ የማርሻል አርት ባለሞያና አስተማሪ፣ እንዲሁም ሾመ-ጥር ፈላስፋ ነበር፡፡ ይህ ሰው አንድ ጊዜ ስለስኬቱ ምስጢር እንዲህ ሲል ተደመጠ፣ “አስር ሺህ አይነት የተለያዩ የካራቴ ምቶችን በአንድ ቀን ከተለማመደ ሰው ይልቅ እኔ የምፈራው አንድን አይነት የካራቴ ምት አስር ሺህ ጊዜ ደጋግሞ የተለማመደን ሰው ነው”፡፡ አንድ ቀን ተነስተን የተለያዩ ነገሮችን ስለሞከርን ብቻ የትም እንደማንደርስ አመልካች የሆነ ሃሳብ ነው፡፡ አስር ሺ አይነት ነገሮችን ከመሞካከር፣ ዓላማችንንና ግባችንን ከለየን በኋላ ያንን አንድን ነገር አስር ሺህ ጊዜ አድምተን ብንደጋግመውና ብንለማመደው ለምነገባበት ስኬት ወሰን አይኖረውም፡፡ የዚህ እውነታ ምስጢር ያለው በመነሳሳት (Motivation) እና በዲሲፕሊን (Discipline) መካከል ያለውን ልዩነት በማወቅ ነው፡፡ የተነሳሳን አንድ ቀን ከምናደርጋቸው አስር ሺህ የዘመቻ ስራዎች ይልቅ የያዝነውን አንድ ነገር በዲሲፐልን አስር ሺህ ጊዜ ብንደጋግመው የተሸለ ውጤትን እናገኛል፡፡ በመነሳሳት የጀመርነውን ነገር በዲሲፕሊን መቀጠልን እስከምንለምድ ድረስ ስኬት የህልም እንጀራ እንደሆነ ይቀራል!!!      ♦️ ❍✰ @FromBooks776 ✰❍ ♦️ ♡ ㅤ       ❍ㅤ         ⎙ㅤ        ⌲             ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ❗️ ---------------------------------- 🖌 Dr. Eyob Mamo ' • መማር ከባድ ነው፣ ሳይማሩ መኖርም ከባድ ነው፤ ➺ ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ❗️ • ራስን ከአቻዎች ግፊት መጠበቅ ከባድ ነው፣ በአቻዎች ግፊት ምክንያት ጤና-ቢስ ሕይወት ውስጥ መግባትም ከባድ ነው፤ ➺ ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ❗️ • ማፍቅር ከባድ ነው፣ አለማፍቀርም ከባድ ነው፤ ➺ ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ❗️ • በፍጹም ከማይፈልግህ ጓደኛ መለየት ከባድ ነው፣ ይህንን ጓደኛ ሲለማመጡ መኖርም ከባድ ነው፤ ➺ ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ❗️ • የትዳር ኑሮ ከባድ ነው፣ መፋታትም ከባድ ነው፤ ➺ ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ❗️ • በጤናማ አመጋገብና በስፖርት ራስን መጠበቅ ከባድ ነው፣ እንደፈለጉ በመመገብና ስፖርት ባለመስራት የመኖርም ውጤት ከባድ ነው፤ ➺ ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ❗️ • ከእጽ፣ ከማሕበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ሱሶች ታግሎ መላቀቅ ከባድ ነው፣ በእነዚህ ሱሶች ተዘፍቆ መኖርም ከባድ ነው፤ ➺ ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ❗️ • በገንዘብ አያያዝ ዲሲፕሊን ማዳበር ከባድ ነው፣ ከአባካኝነት የሚመጣ እዳም ከባድ ነው፤ ➺ ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ❗️ • ከሰዎች ጋር መግባባት ከባድ ነው፣ ከሰዎች ጋር አለመግባባትም ከባድ ነው፤ ➺ ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ❗️ • መወሰን ከባድ ነው፣ አለመወሰንም ከባድ ነው፤ ➺ ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ❗️ ትክክለኛውን ከባድ ለመምረጥ ያለህን ጉዞ ሚዛናዊ የሚያደርጉልህ ጥያቄዎች 👇 • ባሉኝ ምርጫዎች መካከል ለማመዛዘን በቂ ጊዜ ወስጄ አስቤበታለሁ❓ • ምርጫዬን የመዘንኩት ከወቅቱ ስሜት አንጻር ነው ወይስ ከወደፊቱ ውጤት አንጻር❓ • የምመርጠው የውጭ ግፊትን ተከትዬ ሳይሆን ህሊናዬን አድምጬ ነው❓ • የምመርጠውን ምርጫ የመረጥኩት ከጊዜው ከባድ ሁኔታ ለማምለጥ ነው ወይስ ነገ ከሚሰጠኝ ዘላቂ ውጤት የተነሳ ነው❓ ሕይወት በጥቅሉ ከባድ ነው፣ ስለዚህ የትኛውን “ከባድ” መምረጥ እንዳብህ በጥንቃቄ አስበህ ምረጥ❗️ ትክክለኛ ላልሆነው ከባድ ምርጫ 10 ከምትከፍል፣ ትክክል ለሆነው ከባድ ምርጫ 100 ብትከፍል ይሻላል‼️ -------------------------- ♦️ ❍✰ @FromBooks776 ✰❍ ♦️ ♡ ㅤ       ❍ㅤ         ⎙ㅤ        ⌲             ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

Repost from Yotor Books
የመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ " 888 " የተሰኘው መጽሐፍ ዛሬ ለንባብ በቅቷል :: @Ethio_treca
የመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ " 888 " የተሰኘው መጽሐፍ ዛሬ ለንባብ በቅቷል :: @Ethio_treca

💫ከማንም ሰው ጋር እውነተኛ ለመሆን ከመሞከርህ በፊት ከራስህ ጋር እውነተኛ ሁን፡፡ የምታስበውን ተናገር (አንድ አይነት ሰው ሁን)፣ የምትናገረውን ደግሞ ተግብር (የቃልህ ሰው ሁን)፡፡ በሃሳብህ፣ በንግግርህና በተግባርህ ላይ ለሚነሳ ለማንኛውም ጥያቄ ደግሞ ሙሉ ሃላፊነት በመውሰድ ለማስረዳት፣ ለመከላከልና ለማስከበር፤ ስህተት ከሆነ ደግሞ ይቅርታ ለመጠየቅ ዝግጁ ሁን፡፡ በዚህ ሃሳብ መሰረት የዛሬ ውሎህ እንዴት ነበር? ♦️ ❍✰ @FromBooks776 ✰❍ ♦️ ♡ ㅤ       ❍ㅤ         ⎙ㅤ        ⌲             ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

👉አንተ ካልሞትክ አይገድሉህም የሚያልቅልህ አለቀልኝ ያልክ ቀን ነው የምትሞተዉ ሞትኩ ብለህ የተቀበልክ ቀን ነዉ የምትሸነፈዉ ልብህ የተረታ ለት ነዉ።አፈር  ስለጨመሩብህ ብቻ ልትቀበር  አትችልምኮ አፈሩን ማራገፍ ካልቻልክ እንጂ ፤ ተስፋ ከቆረጥክ ወለል ብሎ የተከፈተዉም ሰፊም በር አይታይህም ብርታቱ ካለህ ግን ማንም የማያየዉን በስላሽ የተከፈተዉን የሰርጥ በር እንኳን ታየዋለህ። ቀድመህ ካልተሸነፍክ እሳት ዉስጥም ሆነህ ታበራለህ ከተሸነፍክ ግን አልጋ ላይ ሆነህም ታለቅሳለህ። ♦️ ❍✰ @FromBooks776 ✰❍ ♦️ ♡ ㅤ       ❍ㅤ         ⎙ㅤ        ⌲             ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

ሁሌም ማታ ወደ አልጋችን ስንሄድ ነገ እንደምንነሳ ምንም ማርጋገጫ የለንም ! #ነገር_ግን_ለመነሳት ✔ አላርም እንሞላለን ✔ ነገ ብለን ሰው እንቀጥራለን ✔ነገ የምናደርገውን ዛሬ እናስባለን ሰው በተስፋ ይኖራል ተስፋን የሰጠን ፈጣሪ ደግም የታመነ ነው ነገን በመልካም ያኖረናል !!! ወዳጄ__ሆይ ተስፋ እንዳለህ አምነህ ብዙ ነገር እያደረክ ተስፋ የለኝም የኔ ነገር አበቃ አትበል !!!! "ሁሉም ለበጎ ነው" ♦️ ❍✰ @FromBooks776 ✰❍ ♦️ ♡ ㅤ       ❍ㅤ         ⎙ㅤ        ⌲             ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

በገሀዱ ያሉትን ሰዎች ማፍቀር ይቸግራል። ምክንያቱም በገሀዱ ያለ አንድ ሰው ሀሳባቹህን ሁሉ አያሟላላቹህም። አፈጣጠሩም እንደዚያ አደለም። አንድ ሰው ወደዚህች ምድር የመጣው የማንንም ሀሳብ ሊያሟላ አደለም__የገዛ እራሱን ህይወት ለመኖር እንጂ።" #ኦሾ_ህያውነት ♦️ ❍✰ @FromBooks776 ✰❍ ♦️ ♡ ㅤ       ❍ㅤ         ⎙ㅤ        ⌲             ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

በሰዎች ዘንድ ተስፋ የሌለን ብንመስልም እንኳን ዋናው ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ተስፋችን ነው።ሕይወት ጠመዝማዛም ብትሆን ውብና ተስፋን የተሞላች ናት! በዚህ ዓለም ሁሉ ነገር አበቃ፤አከተመ ባልንበት ጊዜ የሚቀጥል የተሻለ እድል፤ የምናውቀውና የተለመደው በር የተከረቸመ ቢመስልም ወለል ብሎ የሚከፈት ሌላ በር፤ዙሪያችን ጭው ያለ በረሃ ቢሆንም የለመለመ መስክ የሆነ ስፍራ ላይ እንዳለ ተምሬያለሁ።ዕድል ፊቷን ያዞረችብን በመሰለን ጊዜ እንኳ ቢሆን አብዝቶ በትጋት መጓዝ እንጂ ተስፋ መቁረጥ አይገባም። ትጋት የተስፋ ልጅ ናት። ተስፋ ደግሞ በእኛና በፈጣሪ መካከል የእምነት ድልድይ ስለመኖሩ ማረጋገጫ ነውና !    #ከሰበዝ ♦️ ❍✰ @FromBooks776 ✰❍ ♦️ ♡ ㅤ       ❍ㅤ         ⎙ㅤ        ⌲             ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

🌿" የምትናገሩት ከሀሳቦቻችሁ ጋር ሰላም መፍጠር ሲያቅታችሁ ነው ። በልባችሁ ውስጥ ባለው ጭር ያለ ስፍራ መኖር ሳትችሉ ስትቀሩ፣ በከናፍሮቻችሁ ውስጥ ትኖራላችሁ ንግግርም አቅጣጫን የሚያዛንፍ ጊዜ ማሳለፊያ እና መደሰቻ ነው ...እናም በአብዛኛው ንግግራችሁ(ወሬያችሁ) ውስጥ የማሰብ ችሎታችሁ በከፊል ይሞታል ። ሃሳብስ በህዋ ላይ እንደምትበር ወፍ አይደለምን ? በፍርግርግ ብረት በተሰራ የቃላት መረብ ውስጥ ከተዘጋባትስ ክንፎቿን ትዘረጋ እንደሆን እንጂ ልትበር ትችላለችን...? በእናንተ መካከል ለብቻቸው መሆንን በመፍራት ወሬኞችን የሚፈልጉ አሉ ። ምክንያቱም የብቸኝነት ፀጥታ ለአይኖቻቸው እርቃኑን የቀረውን ራሳቸውን አጋልጦ ያሳያቸዋልና ሁሌ ከእሱ ለመሸሽ ይፈልጋሉ...ደግሞም ሳያውቁት ወይም ቀደም ብለው ሳያስቡበት የሚያወሩ እና በዚህ ንግግራቸው ራሳቸው እንኳን የማያውቁትን እውነት ገልጠው የሚያሳዩም አሉ... በውስጣቸው እውነትን የያዙ ፣ ነገር ግን በቃላት የማይናገሩትም አሉ ። እንደዚህ ባሉት ሰዎች ልብ ውስጥ የእውነት መንፈስ ዜማ በሚደረድር ትርታዊ ፀጥታ ውስጥ ይኖራል... ጓደኞቻችሁን በመንገድ ዳር ወይም በገበያ ቦታ ስታገኙዋቸው በውስጣችሁ ያለው መንፈስ ፣ ከናፍራችሁን ያንቀሳቅስ ፤ ምላሳችሁንም ይምራ ። የጽምፆቻችሁ ድምፅም ለጆሮዋቸው ጆሮ ይናገር..የወይንን ጣዕም ሁሌ እንደሚያስታውስ ሁሉ ፣ የጓደኞቻችሁ ነፍስ የልባችሁን እውነት ጠብቆ ያቆያል አይደለምን? ቀለሙ(ጣዕሙ) በተረሳ ጊዜ ግን ዕቃውም አይታወስም ። " ♦️ ❍✰ @FromBooks776 ✰❍ ♦️ ♡ ㅤ       ❍ㅤ         ⎙ㅤ        ⌲             ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ❗️ ---------------------------------- 🖌 Dr. Eyob Mamo ' • መማር ከባድ ነው፣ ሳይማሩ መኖርም ከባድ ነው፤ ➺ ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ❗️ • ራስን ከአቻዎች ግፊት መጠበቅ ከባድ ነው፣ በአቻዎች ግፊት ምክንያት ጤና-ቢስ ሕይወት ውስጥ መግባትም ከባድ ነው፤ ➺ ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ❗️ • ማፍቅር ከባድ ነው፣ አለማፍቀርም ከባድ ነው፤ ➺ ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ❗️ • በፍጹም ከማይፈልግህ ጓደኛ መለየት ከባድ ነው፣ ይህንን ጓደኛ ሲለማመጡ መኖርም ከባድ ነው፤ ➺ ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ❗️ • የትዳር ኑሮ ከባድ ነው፣ መፋታትም ከባድ ነው፤ ➺ ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ❗️ • በጤናማ አመጋገብና በስፖርት ራስን መጠበቅ ከባድ ነው፣ እንደፈለጉ በመመገብና ስፖርት ባለመስራት የመኖርም ውጤት ከባድ ነው፤ ➺ ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ❗️ • ከእጽ፣ ከማሕበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ሱሶች ታግሎ መላቀቅ ከባድ ነው፣ በእነዚህ ሱሶች ተዘፍቆ መኖርም ከባድ ነው፤ ➺ ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ❗️ • በገንዘብ አያያዝ ዲሲፕሊን ማዳበር ከባድ ነው፣ ከአባካኝነት የሚመጣ እዳም ከባድ ነው፤ ➺ ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ❗️ • ከሰዎች ጋር መግባባት ከባድ ነው፣ ከሰዎች ጋር አለመግባባትም ከባድ ነው፤ ➺ ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ❗️ • መወሰን ከባድ ነው፣ አለመወሰንም ከባድ ነው፤ ➺ ትክክለኛውን ከባድ ምረጥ❗️ ትክክለኛውን ከባድ ለመምረጥ ያለህን ጉዞ ሚዛናዊ የሚያደርጉልህ ጥያቄዎች 👇 • ባሉኝ ምርጫዎች መካከል ለማመዛዘን በቂ ጊዜ ወስጄ አስቤበታለሁ❓ • ምርጫዬን የመዘንኩት ከወቅቱ ስሜት አንጻር ነው ወይስ ከወደፊቱ ውጤት አንጻር❓ • የምመርጠው የውጭ ግፊትን ተከትዬ ሳይሆን ህሊናዬን አድምጬ ነው❓ • የምመርጠውን ምርጫ የመረጥኩት ከጊዜው ከባድ ሁኔታ ለማምለጥ ነው ወይስ ነገ ከሚሰጠኝ ዘላቂ ውጤት የተነሳ ነው❓ ሕይወት በጥቅሉ ከባድ ነው፣ ስለዚህ የትኛውን “ከባድ” መምረጥ እንዳብህ በጥንቃቄ አስበህ ምረጥ❗️ ትክክለኛ ላልሆነው ከባድ ምርጫ 10 ከምትከፍል፣ ትክክል ለሆነው ከባድ ምርጫ 100 ብትከፍል ይሻላል‼️ -------------------------- 📖 📖 📖 📖 ♦️ ❍✰ @FromBooks776 ✰❍ ♦️ ♡ ㅤ       ❍ㅤ         ⎙ㅤ        ⌲             ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ