en
Feedback
Glory Consultancy

Glory Consultancy

Open in Telegram

Glory Consultancy Our services : -> English proficiency test payment -> Partial scholarship -> Visa appointment The cheapest Consultancy

Show more
The country is not specifiedEducation116 025
993
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
#college_research ኒው ዮርክ ዩኒቨርሲቲ (new york university) 🏛 የኒውዮርክ ዩኒቨርሲቲ በኒውዮርክ ከተማ የግል የምርምር ዩኒቨርሲቲ ሲሆን በ1831 በኒውዮርክ ግዛት ህግ አውጪ ቻርተርድ፣ NYU የተመሰረተ ነው ሲሆን በወቅቱ የግምጃ ቤት ፀሐፊ አልበርት ጋላቲን በሚመራው የኒውዮርክ ነዋሪዎች ቡድን ነው የተመሰረተው። 🌐 የአለም አቀፍ ደረጃ ፡ 42ተኛ (QS የአለም ደረጃዎች) ✅የመቀበል መጠን(acceptance rate) ፡ 21% 📝SAT ክልል(range) ፡ 1370 - 1540 📙 የACT ክልል(range) ፡ 31-34 📃የሁለተኛ ደረጃ GPA አማካይ 3.69 ነው። 💸የማመልከቻ ክፍያ(application fee)፡ 80$ 🎯በcommon app apply የምታደርጉ fee wavier ስላለ እሱን መጠቀም ትችላላችሁ ። 💵 አማካይ ዓመታዊ ወጪ : 77,632 ዶላር 💢ነፃ የትምህርት እድል ለinternational students ይሰጣል። 📮70 ዋሽንግተን ስኩዌር ደቡብ ኒው ዮርክ ፣ NY 10012 📧የመተግበሪያ ድህረ ገጽ(website)፡- www.nyu.edu የማመልከቻ ገደብ፡ January 5 በEA እና ED apply ማድረግ ይቻላል ? : አዎ ✅እንዴት ማመልከት እንደሚቻል፡- በ common app እና coalition app

#channel_navigation ውድ የቻናላችን ተከታታዮች በዚህ ቻናል ብዙዎቻችሁ እየተጠቀማችሁ እንደሆነ እንዲሁም የተለያዩ ቢሻሻሉ ብላችሁ የምታስቧቸውን ነገሮች ስታደርሱን ቆይታችኋል። እኛም የናንተን የተከታታዮቻችንን ተደራሽነት ለመጨመር በሚል በቻናላችን የሚለቀቁ የተለያዩ ይዘት ያሉዋቸውን መረጃዎች በቀላሉ ለማግኘት ይቻላችሁ ዘንድ #channel_navigation ያዘጋጀን መሆኑን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው። ይህ የchannel navigation በተለያየ ይዘት ከፋፍለን ያሰራጨናቸውን መረጃዎች እናንተ ለመፈለግ መድከም ሳይጠበቀባችሁ በቀላሉ መረጃዎቹን ማግኘት እንድትችሉ ታስቦ የተሰራ ነው። ለምሳሌ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የተሰሩ ሪሰርቾችን ለማግኘት " #college_research " ሰርች ባሩ ላይ በመፃፍ ወይም ሊንኩን በመንካት ማግኘት ትችላላችሁ። #college_application_tips - የተለያዩ ስለ college application የተፃፉ መረጃዎችን ለማግኘት። #college_research - የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የተሰሩ ሪሰርቾችን ለማግኘት። #useful_explanation - ጠቃሚ ነው ብለን የምናስባቸውን ፅሁፎች ለማግኘት ። #useful_materials - የተለያዩ ጠቃሚ የሆኑ በቻናላችን የተለቀቁ ፋይሎችን ለማግኘት። #update - የተለያዩ ጊዜያዊ የሆኑ ፕሮግራሞች ፣ ኢቨንቶችና መረጃዎችን ለማግኘት። #fun_fact - የተየለያዩ ዩኒቨርስቲዎችን የተመለከቱ አዝናኝና አስገራሚ መረጃዎችን ለማግኘት ። #motivation - የተለያዩ የማነቃቂ ንግግሮችን የተመለከቱ መረጃዎችን ለማግኘት ። #ADS - የተለያዩ ማስታወቂያዎች ለማግኘት ። #holiday_message - የተለያዩ የበአል መልእክቶችን ለማግኘት ። #fun_activity - የተለያዩ ፈገግ የሚያደርጉ ተግባራትን ለማግኘት ።

#useful_explanation 📑 የSAT ፈተና ማዕከላት በኢትዮጵያ 🏛 #አዲስ_አበባ_ዩኒቨርሲቲ አድራሻ፡ Law campus በተለምዶ 5ተኛ በር ተብሎ በሚጠራው መግቢያ ዋናው የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር Test center code፡ 77303 🏛 #ቢንጋም_አካዳሚ አድራሻ፡ አዲስ አበባ ሰፈረ-ሰላም አካባቢ፡ ኢትዮጵያ Test center code፡ 77300 🏛 #Intetational_community_school (ICS Addis) አድራሻ፡ አዲስ አበባ፡ ካርል አደባባይ Test center code: 77301 🏛 #ሳንፎርድ_ኢንተርናሽናል_ትምህርት_ቤት አድራሻ፡ አዲስ አበባ፡ ቀበና አካባቢ Test center code፡ 77308

#usefull_explanation #CDS / #Common_data_set ምንድነው ? 🎯በተለምዶው #CDS እየተባለ የሚጠራውና #common_data_set የሚል ፈቺ ያለው ይህ ፋይል በዋናነት ስለ አንድ ዩኒቨርስቲ ማንኛውንም አይነት መረጃ የሚሰጥና ዝርዝር ጉዳዪችን ሁሉ ጨምሮ የሚያሳይ ሰነድ/file ነው። 🎯ምናልባት በተለያዩ ድህረገጾች(website) ከሚወጡት መረጃዎች በምን ይለያል ? የሚል ጥያቄ ያስነሳ ይሆናል ነገር ግን ከነዚህ አይነት መረጃዎች ፈፁም ልዩ ነው። ምክንያቱም በራሱ በዩኒቨርስቲው የሚፃፉና ስለተደረጉት እያንዳንዱ ጉዳዮች ዝርዝር ነገር የሚገልጽ ነው። በ#CDS ውስጥ ከሚካተቱት ነገሮች መካከል ....... #General_Information , ይህም የትምህርት ቤቱን ስም ፣ አድራሻ ፣ po.box/ ፖ.ሳ.ቁ ፣ የemail አድራሻ ፣ ስልክ ቁጥር እና ሌሎች ተያያዥ ነገሮችን አካቶ የያዘ ነው። #Enrollment_And_Persistence, በዚህ ክፍል ደግሞ ቀደም ብሎ በነበረው አመት የተቀበሉዋቸውን የተማሪዎች ብዛት በፆታ ፣ በትምህርት ደረጃ (Undergraduate, Masters and PHD) ፣ በሀገርና በትምህርት አወሳሰድ የጊዜ ስሌዳ (የሙሉ ጊዜ ተማሪና የትርፍ ሰአት ተማሪ) ተከፋፍሎ የሚቀረብ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም በትምህርት ዘመኑ ስላሉ የተመራቂዎች ብዛትም ይገልጻል። #First_Time, #First_Year (#Freshman) Admission ይህ ክፍል ደግሞ ቀደም ብለው በነበሩት አመታት ዩኒቨርሲቲው ስለተቀበላቸው(accept) ፣ በተጠባባቂነት ስለሰየማቸው (wait listed) ተማሪዎች የሚገልጽ ሲሆን በዋናነት ግን ስለ መጀመሪያ ጊዜ አመልካቾች(first time applicants) እና first year/freshman አመልካቾች የሚገልጽ ነው። #Transfer_Admission: ይህም በዝውውር ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ስለመጡ ተማሪዎች ዳሰሳ የሚያደርግ ክፍል ሲሆን ምን ያህሉ accept ፣ reject ወይም wait list ተደረጉ የሚለውን የሚገልጽ ነው። 🎯ከዚህ በተጨማሪም በዚሁ ፋይል ውስጥ ትምህርት ቤቱ የሚፈልገው የትምህርት ውጤት መጠን (transcript)፣ የ standardized test ውጤት መጠን (SAT, ACT, ILTS) ፣ ስለተማሪዎች ህይወት ፣ ስለFinancial aid እና ስለሚሰጡት የትምህርት ፕሮግራሞች በግልጽ ተፅፏል። ይህም የተሟላ መረጃን ለማግኘት ያስችላል። 🎯የዩኒቨርሲቲዎችን #CDS/#common_data_set ለማግኘት የዩኒቨርሲቲውን ከፃፋችሁ በኋላ common data set/cds ብላችሁ አስከትላችሁ በመፃፍ search ብታደርጉ ማግኘት ትችላላችሁ። 🉑ለምሳሌ የምንፈልገው ዩኒቨርስቲ Harvard ቢሆን " Harvard common data set " ብሎ search በማድረገ ማግኘት ይቻላል።

#update ለ#Early_decision እና ለ #Early_action deadline 55 ቀናት ብቻ ቀሩት ! ስለዚህ ሙሉ applicationናችሁን ከቀኑ ጋር በማጣጣም ለመጨረስ ሞክሩ። በተጨማሪም r
#update ለ#Early_decision እና ለ #Early_action deadline 55 ቀናት ብቻ ቀሩት ! ስለዚህ ሙሉ applicationናችሁን ከቀኑ ጋር በማጣጣም ለመጨረስ ሞክሩ። በተጨማሪም recommendation letter ፣ transcript ማዘጋጀታችሁን እንዱሁም ለ #early_action ወይም #early_decision apply የምታደርጉበትን ዩኒቨርስቲ supplimental essay መፃፍም አትዘንጉ ። መልካም እድል !!

#usefull_explanation #college_application_tips common app #Honors_Section 🎯በመጀመሪያ Honour ማለት በማንኛውም ዘርፍ (በትምህርትም ሆነ ከትምህርት ውጪ) ያገኛችሁት ሽልማት ወይም አዋርድ ማለት ነው። ብዙ ተማሪዎችም በዚህ section ሰርተፊኬት ያገኙባቸውን ነገሮች ብቻ መጠቀስ እንዳለበትና ከዛ ውጪ ከሆነ ግን ተቀባይነት እንደሌለው ያስባሉ። ነገር ግን ይሄ ፍፁም የተሳሳተ ነው። ሰርተፊኬት ኖረውም አልኖረውም በ admission officers ፊት እኩል ነው። ይህም የሚሆነው ምንም አይነት ሰርተፊኬት ስለማያዩ ነው። (የ 50 አና 60 ሺ ተማሪዎችን ሰርተፊኬት ለማየት ጊዜ የላቸውም።) ስለዚህ እናንተ እንደ አዋርድ ወይም honor የምታስቡትን ማንኛውንም ነገር መፃፍ ይቻላል። (ከቤተሰብ ሽልማት ተሰጥቶኛል ማለት ግን አይቻልም። 😊) በመሆኑም ይህንን section ለመሙላት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ነጥቦች መመልከት ያስፈልጋል ; 🎯 ለእያንዳንዱ honor #ስሙን ፣ #አይነቱን( በአለም አቀፍ ፣ ሀገር አቀፍ ፣ በክልል/ ከተማ ደረጃ ፣ ክፍለከተማ ፣ ቀበሌ/ወረዳ ፣ ትምህርትቤት) # የተቀበላችሁበትን የክፍል ደረጃ መጠቀስ ይገባል። 🎯ያገኛችሁትን ሽልማት/አዋርድ ስትገልፁ ከላይ በተቀመጠው ቅደም ተከተል መሆን አለበት። ይህም ማለት ለምሳሌ በአለም አቀፍ ደረጃ ያገኛችሁት ሽልማት ካለ መጀመሪያ ቀጥሎ ሀገር አቀፍ .... እያላችሁ መፃፍ ያስፈልጋል። 🎯ስለሽልማቱም ለማብራራት የሚሰጣችሁን ክፍት ቦታ 100 ፊደላትን(character) ብቻ የሚያፅፍ በመሆኑ በሚገባ መጠቀም ይጠበቅባችኋል። ይህንንም ለማድረግ abbreviation (ምህፃረ ቃል/ አሳጥሮ መፃፍ) መጠቀም አሪፍ መንገድ ነው። #Example_ምሳሌ 🖍Winner of the National French Honor Society French Film Contest (2014-2015) Wrote script and played the main character in the short film, as well as assisted in editing (168 characters 😒😢) የሚለውን በ 🖍Winner of Nat'l French Honor Society Film Contest: Wrote script, played main char, asst. editor (95 characters 😁👍) መግለጽ ይቻላል። 🉑ስለሽልማቱ የበለጠ ጠቃሚ መረጃ ያለው ነገር ለመፃፍም ቀጥሎ ያሉትን ጥያቄዎች በተቻለ መጠን ለመመለስ ሞክሩ 💢ምን ያህል ሰዎች በውድድሩ ተሳትፈዋል ? ምን ያህሎቹስ ተመረጡ ?(ውድድር ከሆነ) 💢 ምን ያህል ሽልማት ተቀበልክ/ሽ 💢 ምን አይነት ሽልማት ነው ? (ትምህርታዊ ወይም ከዛ ውጪ) 💢 በማን ነው ሽልማቱ የተበረከተልክ/ሽ ? ⛎ብዙ ሽልማት ከተቀበላችሁና ለመዘርዘር ቦታ ካነሳችሁ addition section ላይ መፃፍ/ማስፈር ትችላላችሁ። ነገር ግን ሁሉም ሽልማቶች በሀይስኩል (#highschool/ 9-12) መሆን ይጠበቅበታል።

#usfull_explanation #College_application_tips ! #Personal_statement ( Essay ) 🎯 በጣም ልዪ አይነት የሆነ (formal) አፃፃፍ ማስወገድ ያስፈልጋል። ምክንያቱም ከ16 ና 17 አመት ልጅ የሚጠበቀውን አይነት አፃፃፍ admission Officerች ጠንቅቀው ስለሚያውቁ። 🎯 በተቻለ መጠን የፃፋችሁትን essay በዘርፉ ልምድ ባለው አስተማሪ ወይም ደግሞ ከዚህ በፊት scholarship ያገኙ ተማሪዎችን አግኝቶ ማስገምገም። (ኢትዮጵያ ውስጥ አብዛኛው አስተማሪ ስለ እንደዚህ አይነቱ ነገር እውቀቱ ስለሌለው ማሳየቱ ጥቅም አልባ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በቂ እውቀት አላቸው ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ ማሳየት ይመከራል።) 🎯 በምታሳዩበትም ግዜ ምንም አይነት ማብራሪያ ከናንተ አያስፈልግም። ምክንያቱም እነርሱው እራሳቸው essayን አንብበው የናንተን ማንነትና ልትሉት የፈለጋችሁትን ማወቅ ስላለባቸው። #Supplemental_Essay 🎯 ከዚህ በፊት በሌላ ተማሪዎች የተፃፈውን ፈፅሞ መገልበጥ የተከለከለና ትክክል ያልሆነ ነገር ነው። ምክንያቱም እያንዳንዱ college የናንተን ጥረትና እነርሱ ትምህርት ቤት ገብታችሁ ለመማር ያላችሁን ፍላጎት በግልጽ ማወቅ ስለሚፈልጉ ነው። 🎯 apply ለምታደርጉበት ዪኒቨርሲቲ ጠለቅ ያለ research መስራት ያስፈልጋል። ይህም ከዩኒቨርስቲው website ፣ ከተለያዩ ማህበራዊ ድረገጾች ፣ ከዚህ በፊት ከገቡ ተማሪዎችና ከተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች (social media) ሊሆን ይችላል። በ research ውስጥም ዋና ዋና ከግምት ውስጥ መግባት ካለባቸው ነገሮች መካከል መማር የምትፈልጉት የትምህርት ፕሮግራም(አይነት) በዩኒቨርስቲው መሰጠት አለመሰጠቱን እና ከትምህርቱ ጋር ተያያዥነት ያለው ፕሮፌሰርም መፈለግ critical ነገር ነው። 🎯 ለመልሳችሁ በተቻለ መጠን ቀጥተኛ ምላሽ ለመስጠት ሞክሩ። ይህም ሲባል ግን መልሳችሁን attractive በሆነ መልኩም ማቅረባችሁን ከግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል።

#useful_explanation #college_application_tips 🎖personal essay ላይ ማወቅ ያለብን ወሳኝ ነገሮች አድርግ(Dos) እና አታድርግ(Don't) ‼️ ሙሉ በሙሉ በፊደል አራሚ (spell checker) ላይ አትተማመን‼️ 🎯 በሰዋስው (grammar) ለማገዝ ትልቅ ግብአት ቢሆንም፣ ሁሉንም ነገር ያስተካክላል ማለትም ግን አይቻልም ። በተቻለ መጠን ብዙ ጊዜ ማረም ያስፈልጋል ። በመጨረሻው ደቂቃ ላይ ለማስገባት (submit) አያድርጉ። ምክንያቱም essay የተጣደፈ ይመስላል እና ጠቃሚ መረጃ ሊቀር ስለሚችል። የፊደል አጻጻፍ እና ሰዋሰዋዊ ስህተቶች essayን እንዲያበላሹት አትፍቀድ ። ለእያንዳንዱ ትምህርት ቤት ጥያቄ ትኩረት ስጥ ‼️ 🎯 በተቻለ መጠን ደግ መስለህ ለመታየት ሞክር! admission officers ትዕቢተኛ፣ አስመሳይ፣ ምሑር ወይም ባለጌ የሆኑ አመልካቾችን(applicant) ለመቀበል አይቸኩሉም። በአረፍተ ነገሩ ውስጥ ሁሉ አክባሪ ወይም ደግ በሃሪ ያለው ቃና ለማሳየት ሞክር። በተጨማሪም “የናንተ ኮሌጅ ስገባ” ከማለት ይልቅ “በዩኒቨርስቲያችሁ የመገኘት እድል ከተሰጠኝ” ብሎ ማለትም የበለጠ ተመራጭ ነው። 🎯 ከመጠን በላይ ድራማቲክ ለመሆን አትጣር። ምክንያቱም የምትፅፈው ስለ ግላዊ ባህሪህ እንጂ ድርሰት አይደለም ። ከዚህ በተጨማሪም ስለ ሌላ ሰው ወይም ስለ ሌላ ነገር ለመናገር ብዙ ጊዜ አታጥፋ ። ሁልጊዜ ትኩረቱን ወደ እራስህ ለመሰብሰብ ሞክር። 🎯 ከpersonal essy ጭብጥ(point) ጋር ምንም ያህል እንኳን ይስማማል ብለህ ቢታሰብም essayህን በታዋቂ ጥቅስ አትጀምር። ምክንያቱም admission officers የአንተን ቃል መስማት ይፈልጋሉ እንጂ የሌላ ሰው አይደለም። 🎯 admission officerችን ለመማረክ ብለህ ትልቅ ቃላትን አትጠቀም። ለ essay የተሳሳተ ድምጽ ያስቀምጣልና።

#useful_explanation #college_application_tips 📍#Early_action (EA) - ተማሪዎች ከመደበኛው የጊዜ ገደብ ቀድመው ለኮሌጅ እንዲያመለክቱ አስገዳጅ ያልሆነ የመግቢያ ሂደት ሲሆን፣ ብዙ ጊዜም በ #November መጀመሪያ አከባቢ deadline ያልቃል። ተማሪዎችም የ admission decision (የመግቢያ ማሳወቂያቸውን ) #December ውስጥ የሚቀበሉ ሲሆን እና ተቀባይነት ካገኙ (accepted ከተደረጉ) ወደዩኒቨርስቲው እንዲሄዱ አይገደዱም። 📍#Early_Decision_one(I) (ED I) - ተማሪዎች ከመደበኛው የጊዜ ገደብ ቀድመው ወደ ኮሌጅ እንዲገቡ አስገዳጅ የመግቢያ ሂደት ያለው ስርአት ሲሆን ፣ አብዛኛውን ጊዜ #በኖቬምበር (November) ውስጥ deadline ያበቃል። ተማሪዎች #በዲሴምበር (December) ውስጥ የመግቢያ ማሳወቂያዎችን(admission decision) የሚቀበሉ ሲሆን ተቀባይነት ካገኙ, ግዴታ ወደተቀበላቸው ዩኒቨርስቲ መሄድ ይጠበቅባቸዋል። 📍#Early_Decision_two (||) (ED II) - ተማሪዎች ወደ ኮሌጅ በጥር (#January) ወር ወደ መደበኛው የጊዜ ገደብ እንዲያመለክቱ አስገዳጅ የመግቢያ ሂደት ነው። ተማሪዎች በየካቲትበ(#February)ወር አጋማሽ ላይ የመግቢያ ማሳወቂያዎችን(admission decision) የሚቀበሉ ሲሆን ተቀባይነት ካገኙም ግዴታ ወደተቀበላቸው ዩኒቨርስቲ መሄድ ይጠበቅባቸዋል። 📍 #Restrictive_Early_Action (REA) ሂደት Early action የበለጠ ገዳቢ የሆነቢሆንም ነገር ግን ከ Early decision ያነሰ ነው። በ restrictive early action በመጀመሪያ ዙር apply የሚያደርጉ ተማሪዎች ተማሪዎች ለማንኛውም ED ትምህርት ቤት ማመልከት አይችሉም፣ ነገር ግን ለሌሎች EA ትምህርት ቤቶች ማመልከት ይችላሉ። 📍#Single_choice_early_action - ወደ ከፈተኛ ትምህርት ቤታቸው ተማሪዎች እንዲያመለክቱ የሚፈቅድ ሲሆን ተማሪዎች ለሌሎች ትምህርት ቤቶች በ EA ወይም ED ማመልከት አይችሉም። 📍#Regular_decision (RD) - አብዛኞቹ ተማሪዎች regular decisionን ይተገበራሉ፣ ብዙውን ጊዜ በጥር(#January) deadline ያለው ሲሆን፣ በመጋቢት(#March) መጨረሻ ወይም በሚያዝያ(#April) መጀመሪያ ላይ ማሳወቂያ(admission decision) ይደርሳቸዋል ። ተማሪዎች ተቀባይነት ወደተቀበላቸው ዩኒቨርስቲ የመሄድ ግዴታ የለባቸውም።

#useful_materials ሰላም የቻናላችን ተከታዮች ዛሬ ደሞ እንደተለመደው በapplication process ላይ የበለጠ መረጃዎችን ለማግኘትና የ ኮሌጅ ሊስት ለማውጣት ይረዳቹሀል ብለን ያሰብናቸውን ድህረገጾች ( website) ይዘንላችሁ መተናል። 1, #College_Vine ; ስለምትፈልጉት ኮሌጅ ማንኛውንም መረጃ የምታገኙበት website ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ስለሙሉ የ application process የረጅም አመት ልምድ ባላቸው ሰዎች የአንድ ለአንድ ነፃ ምክር አገልግሎትም የሰጣል። #for_free 2, #Big_Future ; ምንም ሳትጨናነቁና ሳትለፉ ስለምትፈልጉት ኮሌጅና ስራ መረጃን የምታገኙበት ዌብሳይት ሲሆን ከሃይስኩል(highschool) በኋላ ስላለው የትምህርት ህይወታችሁም plan ለማድረግ አሪፍ website ነው። #for_free 3, #College_Essay_Guy ; የ personal essayን ለመፃፍ ፣ ትክክለኛ የሆነ የ extracurricular activity አፃፃፍ ለመረዳትና ሙሉ በሙሉ የ college applicationኑን ከማስዋብ አንፃር ትልቅ መረዳትን እንድታገኙ የሚረዳ website ሲሆን የሚሰጧቸው አብዛኞቹ አገልግሎትም ነፃ ናቸው። #for_free

#useful_materials ሰላም የቻናላችን ተከታታዮች በዚህ ቪዲዮ የEarly action/ decision እና የ regular decision ልዩነት ጥልቅ በሆነ ማብራሪያ የተዳሰሰ ሲሆን እንድትመለከቱት ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን። የcommn app link 👇👇 https://t.me/common_app

#useful_materials 📩 ለኢትዮጵያውያንና አለም አቀፍ ተማሪዎች 100% የገንዘብ ፍላጎት የሚያሟሉ 20 የአሜሪካ ኮሌጆች 1. #Harvard_University – Need Blind. 2. #Yale_University –  Need Blind. 3. #Princeton_University – Need blind. 4. #MIT – Need blind. 5. #Amherst_College – Need blind. 6. #Williams_College – Need aware. 7. #California_Institute_of_Technology – Need aware. 8. #Swathmore_College – Need aware. 9. #Stanford_University – Need aware. 10. #Davidson_College – Need aware. 11. #Colgate_University – Need aware. 12. #Vassar_College – Need aware. 13. #University_of_Richmond – Need aware. 14. #Duke_University – Need aware. 15. #University_of_Pennsylvania-need blind 16. #Brown_University-need blind 17. #Dartmouth_College-need aware 18. #Vanderbilt-need blind 19. #Pomona_College -need blind 20. #University_of_Chicago-need blind Apply on common app

#useful_explanation 🏛#common_app ወይስ #coalition app??? ምንም እንኳን ሁለቱም ተመሳሳይነት ቢኖራቸውም - ከተግባራዊነት እና ከባህሪያት አንፃር- አመልካቾች በየትኛው apply እንደሚያደርጉ ከመምረጣቸው በፊት ሊያስቡባቸው የሚገቡ አንዳንድ ገጽታዎች አሉ። #የተሣታፊ_ኮሌጆች_ብዛት (number of participating colleges 🎯በ1975 የተመሰረተው የcommon app መተግበሪያ የተመሰረተው በአሜሪካ ሲሆን ከ900 በላይ በሆኑ ኮሌጆች ስራ ላይ ይውላል። 🎯የcoalition መተግበሪያ ግን በ2015 የተመሰረተ ሲሆን በ150 ኮሌጆች ብቻ ጥቅም ላይ ይውላል። #የቴክኒክ_ድጋፍ_ደረጃ(level of technical support) 🎯በዓመት ከ3 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት፣ የcommon app ለጊዜ ገደብ (deadline) ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥ ሲሆን እንደ አለመታደል ሆኖ፣ ይህ ማለት ተማሪዎች በጣም በሚፈልጉበት ጊዜ የቴክኒክ ድጋፍ በቀላሉ ላይገኝ ይችላል። በሌላ በኩል፣ የcoalition መተግበሪያ ግን ጥቂት ተጠቃሚዎች ያሉት በመሆኑ ወደ ውስጥ ሲገቡ ጥያቄዎችን ለመመለስ ተጨማሪ የቴክኖሎጂ ድጋፍ ሊኖረው ይችላል።

#ክፍል_አምስት ስኮላርሺፕ እና የገንዘብ ድጋፍ ይህ ዩኒቨርስቲ በጣም ትልቅና ታዋቂ ከመሆኑም በላይ ለነፃ የትምህርት እድል ለሚመርጣቸው ተማሪዎች በሚበጅተው በጀትም ይታወቃል። በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ
#ክፍል_አምስት ስኮላርሺፕ እና የገንዘብ ድጋፍ ይህ ዩኒቨርስቲ በጣም ትልቅና ታዋቂ ከመሆኑም በላይ ለነፃ የትምህርት እድል ለሚመርጣቸው ተማሪዎች በሚበጅተው በጀትም ይታወቃል። በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ተቀባይነት ያገኝ ተማሪ በአመት በአማካይ ከ $80,000 - $95,000 ሙሉ ወጪ ይደረግበታል። ይህም የምግብ ፣ የመኖሪያ ፣ የጤና ፣ ወርሀዊ የኪስ ገንዘብን የሚያጠቃልል ነው። በመሆኑም በ አራት አመት በሚኖረው አጠቃላይ የካምፓሱ ቆይታ $240,000 -$300,000 ለአንድ ተማሪ ብቻ ወጪ ያደርጋል።

#useful_explanation #Medicine ስለ ሜዲስን ትንሽ ልበላቹህ 📡 ጥሩ ውጤት ማምጣት እስከቻላችሁና ግቢያቹህ ሜዲስን እንደሚሰጥ እርግጠኛ እስከሆናቹህ ድረስ ያለምንም ጥርጥር ህክምና ማጥናት ትችላላቹሁ ሀገራችን ውስጥ እንደሚታወቀው ከፍተኛ የሆነ የሀኪሞች እጥረት ያለ ቢሆንም የስራ እድሉ ግን ብዙዎቻቹህ እንደምታስቡት እንደልብ አይደለም በተለይ በዚህ ወቅት በህክምና የተመረቁ ዶክተሮችን እንደድሮው መንግስት ሳይሆን ራሳቸው ናቸው ስራ ፈለገው የሚቀጠሩት ቢሆንም ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ የግል ስራ ለመስራት ጥሩ እድል አለው ። ምንም ጥያቄ የሌለው ነገር ሜዲስን ለመግባት ጥሩ ውጤት ሊኖራቹህ እንደሚገባ ነው ፤ ግቢ ስትገቡ በመጀመሪያው ሴሚስተር ጥሩ ግሬድ ሊኖራቹህ ግድ ይላል(50%) ፤ ኢንትራንስም ከ20% ዋጋ አለው የሜዲስን መግቢያ COC ደግሞ 30% ግቢያቹህ በሚቀበለው ኮታ ልክ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎቹን ሜዲስን በምርጫቸው እንዲማሩ ይደርጋል ፈጣሪ ረድቷቹህ ሜዲስን ለምትገቡ Full year Course 🧿 Pre-medical modules (16 weeks) 📌 Basic English Skills 📌 Communicative Skill 📌 Basic Writing skills 📌 Computer Application in Medicine 📌 Medical Psychology 📌 Medical Sociology and Anthropology 📌 Civics and Ethics ♨️ Vacation: 2 ▶️ Pre-clinical Year I (Year 1) 📌 Body structure, Organization and Functions – I 📌 Body structure, Organization and Functions – II 📌 Metabolic Homeostasis and Molecular Genetics 📌 Basic concepts of Disease and Therapy ♨️Vacation: 2 weeks 📌 Measurment of Health and Diseases 📌 Blood and Immunity 📌 Neoplasia and Molecular Basis of Cancer 📌 Musculoskeletal, Integumentary and Craniofacial Regions ▶️ Pre-Clinical Year II (Year 2) 📌 Cardioipulmonary System 📌 Nutrition, Metabolic diseases and the GIT 📌 Urinary system and Toxicology 📌 Infectious Disease ♨️Vacation: 2 weeks 📌 Determinents of Health and Disease and research Methodology 📌 Endocrinology and Reproduction 📌 Neurosciences and Behavior ▶️1. Clinical Year I (Year 3) 📌Clinical Methods 📌Medical ethics and law I Internal Medicine I 📌Surgery I Obstetrics and Gynecology I Paediatrics and Child Health I ▶️1. Clinical year II (Year 4 and 5) 📌Health Promotion and Disease Prevention 📌Health Management and Policy 📌Otorhinolaryngology (ENT) 📌Ophthalmology 📌Dentistry 📌Dermatology 📌Introduction to Gender ♨️Vacation: 2 weeks 📌 Paediatrics and Child 📌 Health I 📌Obstetrics and Gynecology II 📌 Diagnostic Radiology 📌 Medical Ethics and Law II 📌 Rural community Health Practice ♨️Vacations: 2 weeks 📌 Internal Medicine II 📌 Surgery II 📌 Psychiatry 📌 Emergency Medicine 💎 ይህ ከላይ የተጠቀሰው የትምህርት ካሪኩለም የጥቁር አንበሳ ሆስፒቲል ተማሪዎች የሚማሩበት የትምህርት ስርዓት ሲሆን ከዩንቨርሲቲዎች ጋር አንዳንድ መዋቅሮቹ ቢለያዩም ብዙ ነገሮቹ ግን ተመሳሳይ ናቸው 💰ስለ ስራ እድሉ እና ተያያዥ የህክምና ትምህርት መረጃዎችን በሌላ ጊዜ የምንዳስስላቹህ ይሆናል ። 💌 Caution በጣም ግን አደራ ልላቹህ የምፈልገው ነገር ፍሬሽማን ኮርስ ላይ ጥሩ ውጤት ስላመጣቹህ ብቻ አልያም ሜዲስን የመማር ዕድል ስላላቹህ ብቻ ወይም ቤተሰብ ደስ እንዲለው ብላቹህ ሜዲስን ለመግባት እንዳትወስኑ ምክንያቱም ይህ የትምህርት መስክ ከሁሉም በላይ OVER LOAD ስላለው ብዙ ተማሪዎች ትምህርቱን መቋቋም አቅቷቸው ከመጫርም በላይ ስለሚጨልሉ አቅማችሁን አውቃቹህ ከፍላጎታቹህ ጋር ለማስማማት ሞክሩ ፤ በተለይ በተለይ ሶስቱን ተከታታይ አመታት የሚሰጡት ኮርሶች ከምታስቡት በላይ ጫና ሊኖራቸው እንደሚችል አውቃቹህ ከወዲሁ አቅማችሁን ፣ ችሎታችሁን እንዲሁም ተነሳሽነታችሁን ፈትሹ

#college_research #ክፍል_አንድ የማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ተቋም (#MIT) በካምብሪጅ ፣ ማሳቹሴትስ ውስጥ የሚገኝ የግል የምርምር ዩኒቨርሲቲ ሲሆን ዓለም አቀፋዊ መሪ የሳይንስ እና የምህንድ
#college_research #ክፍል_አንድ የማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ተቋም (#MIT) በካምብሪጅ ፣ ማሳቹሴትስ ውስጥ የሚገኝ የግል የምርምር ዩኒቨርሲቲ ሲሆን ዓለም አቀፋዊ መሪ የሳይንስ እና የምህንድስና ተቋም ነው። በዓለም ላይ ካሉት በጣም ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ እንደሆነ የሚታሰበው ይህ ተቋም እ.ኤ.አ. በ1861 ከተቀላቀለበት ጊዜ ጀምሮ እውቀትን ለማሳደግ እና ተማሪዎችን በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ እና በተዛማጅ የስኮላርሺፕ ዘርፎች ለማስተማር ያለውን ቁርጠኝነት አጽንቷል። ማስተማር(teaching )እና ጥናት (research)- ከተግባራዊው ዓለም (practical world) ጋር በተዛመደ ሁኔታ እንደ መመሪያ መርህ ይዞ ያለ ተቋም ሲሆን አለምን በሳይንስና ቴክኖሌጂ የሚመሩ ተማሪዎችንም ማፍራት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል። MIT በ 1861 በማሳቹሴትስ ግዛት ውስጥ በኪራይ የነበረ ስፍራ ሲሆን በ 1863 ግን በመሬት ስጦታ ኮሌጅ መሆን ችሏል ። የ MIT መስራች እና የመጀመሪያ ፕሬዝዳንት ዊልያም ባርተን ሮጀርስ ሙሉ በሙሉ ለሳይንሳዊ እና ቴክኒካል ስልጠና የሚሰጥ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለማደራጀት ለዓመታት የለፋና ትልቅ ስራን የሰራ ሰው ቢሆንም የአሜሪካ የእርስ በርስ ጦርነት መቀስቀስ የትምህርት ቤቱን መክፈቻ እስከ 1865 አዘግይቶት ነበር፣ 15 ተማሪዎች ለመጀመሪያዎቹ ክፍሎች ሲመዘገቡ፣ ምዝገባውም በቦስተን የተካሄደ ነበረ። በመቀጠልም MIT በ 1916 ወደ ካምብሪጅ, ማሳቹሴትስ የተዘዋወረ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ግቢው የሚገኘው በቻርለስ ወንዝ አጠገብ ነው። MIT በፕሬዝዳንት ካርል ቲ ኮምፕተን (1930-48) አስተዳደር ጊዜ ከታዋቂ የቴክኒክ ትምህርት ቤትነት ወደ አለም አቀፍ የታወቀ የሳይንስ እና ቴክኒካል ምርምር ማዕከልነትም ሊለውጥ ችሏል።

#college_research #ክፍል_አንድ ዬል(#YALE) ዩኒቨርስቲ በአሜሪካ ከሚገኙ እውቅ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን በግሪጎሪያውያኑ የዘመን ቀመር 1701 የተመሰረተ የግል ዩኒቨርስቲ ነው።
#college_research #ክፍል_አንድ ዬል(#YALE) ዩኒቨርስቲ በአሜሪካ ከሚገኙ እውቅ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን በግሪጎሪያውያኑ የዘመን ቀመር 1701 የተመሰረተ የግል ዩኒቨርስቲ ነው። የግቢው መጠን 373 ሄክታር ሲሆን በሴሚስተር ላይ የተመሰረተ የአካዳሚክ የቀን መቁጠሪያንም ይጠቀማል። ዩኒቨርሲቲው በ2022 በአሜሪካ የምርጥ ኮሌጆች እትም #5 ደረጃ ላይ ተቀምጧል። የዩኒቨርስቲው የተማሪዎች ቆይታ ገደብ 4 አመት ሲሆን ለአንድ ተማሪ አመታዊ የዩኒቨርሲቲ ቆይታ ክፍያው $59,950 ነው። በኒው ሄቨን፣ ኮኔክቲከት የሚገኘው ዬል ዩኒቨርሲቲ፣ ከክፍል ውጪ እንደ ዬል ዊፈንፖፍስ (Yale Whiffenpoofs) ፣ ታዋቂው የካፔላ ቡድን እና የዬል ድራማቲክ ማህበር ካሉ የተማሪ ድርጅቶች ጋር በሚደርሱ ምርጥ የድራማ እና የሙዚቃ ፕሮግራሞችም ይታወቃል። የዬል ቡልዶግስ( Yale Bulldogs) በአይቪሊግ (Ivy Leage) ውስጥ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ተወዳዳሪ ሲሆን ከሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ጋር ባላቸው ፉክክር የታወቁ ናቸው። ተማሪዎች በዬል በሚቆዩበት ጊዜ ከ14 የመኖሪያ ኮሌጆች በአንዱ እንዲኖሩ የሚመደቡ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም እያንዳንዱ ኮሌጅ በኮሌጁ ውስጥ የሚኖሩ እና በመመገቢያ አዳራሾች ውስጥ ከተማሪዎች ጋር የሚበሉ መሪ እና ዲን አላቸው። ከዚህ በተጨማሪም በዩኒቨርሲቲው ያለው የባህል ማዕከላት ተማሪዎች በግቢው ውስጥ የባህል ማንነት ስሜት እንዲገነቡ ትልቅ ቦታ ይሰጣል። የዬል ዩኒቨርሲቲ በአሜሪካ ከሚገኙና ነፃ የትምህርት እድል ከሚሰጡ ጥቂት ዩኒቨርስቲዎች መካከል አንዱ ሲሆን አንድን ተማሪ የሚቀበሉት Acceptance rate 7% ነው። ይህም ወደዚህ ዩኒቨርሲቲ በስኮላርሽፕ የሚገቡ ተማሪዎችን የተመረጡና ተወዳዳሪ ተማሪዎች እንዲሆኑም ያደርጋል።