cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የፀጋ ወንጌል

📌በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶች ይለቀቃሉ 📌ጥያቄዎች ከመፅሐፍ ቅዱስ አንፃር ይመለሳሉ 📌የእናንተ ድርሻ Share በማድረግ ሰው የእውነትን ወንጌል እንዲያውቅና እንዲረዳ ማድረግ ነው Group https://t.me/Graceofjesushighpriestgroup ሀሳብ እና አስተያየት +251985406785(@yabsen) +251953843618(@josi1423) ✍የጌታን ፀጋ ይብዛላቹህ

Show more
Advertising posts
531
Subscribers
-124 hours
-17 days
+830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

♦#የመስቀል_በዓል_እውን_መጽሐፍ #ቅዱሳዊ_ነውን?♦ ================================== ✍️የመስቀል በዓል በአብዛኛው በክርስትናው አለም ያልተለመደ ሲሆን በመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ በጥንት የቤተክርስቲያን ታሪክ የማይታወቅና እውቅና የለውም ነው። ✍️ መስቀል ሲነሳ መነሳት ያለበት እንጨቱ ሳይሆን የተሰቀለው ጌታና የመጣበት አላማ ሊሆን ይገባል። የተሰቀለውን ጌታና የመጣበትን አላማ ስተን የተሰቀለበት እንጨት ላይ ትኩረት ብናደርግ ሐይማኖታዊ ስርአትን ከመፈጸም ውጭ ደህንነትን ልንካፈል አንችልም። ከዚህ የተነሳ ሁላችንም ወደ መጽሐፍ ቅዱሱ ሀሳብ በትህትና ልብ ልንመለስ ያስፈልገናል። ✍1 ቆሮንቶስ 2፡15፤ መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል ✍ዮሐንስ 8 (John) 32፤ እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው። 📌የመስቀል ፍቺ:- ---------------- Greek: σταυρός Transliteration: staurós Pronunciation: stow-ros' በጥንቱ ገጽ የግሪክኛ ቋንቋ ይህ “መስቀል ተብሎ የተተረጐመው ቃል [ስታዉሮስ ] ማንኛውም ነገር የሚሰቀልበትን ወይም [ለአጥር የሚሆንን] እንጨት ወይም ቀጥ ያለ ምሰሶ ወይም ግንድ ያመለክታል። (Cross) “ክሮስ” የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል የተወሰደው "ክሩክስ" ከሚለው የላቲን ቃል ሲሆን በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች “መስቀል” (“የመከራ እንጨት” ) ተብሎ የተተረጐመው ነው። 📌የመስቀል አይነቶች ፦ ----------------- 👉1) ክሩክስ ኢሚሳ (ተ) = (Crux immissa) የላቲኖች መስቀል 👉2) ክሩክስ ኳዳርታ (+) = (Crux quadrata) የግሪኮች መስቀል 👉3) ክሩክስ ኮሚሳ (Crux commissa) (T) =ወይንም በተለምዶ የቅዱስ አንቶኒ መስቀል (St. Anthony’s cross) ተብሎ ይጠራል፡፡ 👉4) ክሩክስ ዲኩሳታ (Crux decussate) (X)= ወይንም በተለምዶ የቅዱስ እንድርያስ መስቀል (St.Andrew’s cross) ተብሎ ይጠራል። 📌መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?? -------‒----------------- ✍1 ቆሮንቶስ 1፡18 የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።..... 23፤ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥ ✍መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ኃይል የሚለው የመስቀሉን ቃል እንጂ የመስቀሉን እንጨት(ቅርጽ) እንዳልሆነ ልብ ልንል ይገባናል። ✍አንድ ሰው ሆዱን ቢታመም እና ሽሮፕ ቢታዘዝለት የሚያድነውን ሽሮፑን ደፍቶ ጠርሙሱን ያድናል ቢልና ይዞት ቢዞር ከበሽታው ሊፈወስ አይችልም። እንዲሁ የተሰቀለው ጌታ እንጂ የተሰቀለበት እንጨት ሊያድነን አይችልም። 📌በተሰቀለው በ ኢየሱስክርሰቶስ የተቆጠሩልን በረከቶች፦ ==================================== መጽሐፍ ቅዱስ በ1ኛ ቆርንቶስ 1፣23 ላይ " እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን" ይለናል። ከዚህም የተነሳ በሰቀለው በኢየሱስ ክርስቶስ፦ 👉የእግዚአብሔር ልጆች ሆነናል ዮሐ 1:12 👉-በተሰቀለው ደህንነት አግኝተናል። ዮሐ3:14-18 👉-በተሰቀለው ከሞት ወደ ሕይወት ተሻግረናል። ዮሐ 5:24 👉-በተሰቀለው ዘላለማዊ ስርየት አግኝተናል።ዕብ 9:22 👉-በተሰቀለው ለዘላለም ተቀድሰናል።ዕብ 10:10 👉-በተሰቀለው የዘላለም ፍጹማን ሆነናል። ዕብ 10:14 👉-በተሰቀለው የእድሜ ዘመን የሀጢያት ስርየት አግኝተናል ። ዕብ 10:17-18,ሮሜ4:5-6 👉- በተሰቀለው ከሕግ ርግማን ነጻ ወጥተናል ገላ3:13 👉-በተሰቀለው ከኩነኔ አምልጠናል። (ሮሜ 8:1) 👉-በተሰቀለው ከኃ ጢያትና ከሞት ሕግ ነጻ ወጥተናል። (ሮሜ 8፡2)። 📌መስቀል ሲነሳ መነሳት ያለበት እንጨቱ ሳይሆን የተሰቀለው ጌታና የመጣበት አላማ ነው። የተሰቀለበት እንጨት ላይ ትኩረት አድርገን የተሰቀለውን ጌታ አላማ ብንስት ሐይማኖታዊ ስርአትን ከመፈጸም ውጭ ደህንነትን ልንካፈል አንችልም። የተሰቀለውን ጌታ እንጂ የተሰቀለበትን አንሰብክም የተሰቀለበት እንጨት ከተሰቀለው ጌታ አላማ ውጭ ምንም ነው። ✍️1 ቆሮንቶስ 1 (1 Corinthians) 18፤ የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና። ✍️1 ቆሮንቶስ 1 (1 Corinthians) 23፤ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥ ✍ዮሐንስ 8 (John) 32፤ እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው። ✍ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ሰላም ለሁላችንም ይብዛ። https://t.me/Graceofjesushighpriest https://t.me/Graceofjesushighpriest
Show all...
የፀጋ ወንጌል

📌በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶች ይለቀቃሉ 📌ጥያቄዎች ከመፅሐፍ ቅዱስ አንፃር ይመለሳሉ 📌የእናንተ ድርሻ Share በማድረግ ሰው የእውነትን ወንጌል እንዲያውቅና እንዲረዳ ማድረግ ነው Group

https://t.me/Graceofjesushighpriestgroup

ሀሳብ እና አስተያየት +251985406785(@yabsen) +251953843618(@josi1423) ✍የጌታን ፀጋ ይብዛላቹህ

👍 5 4🔥 2💯 1
ኢየሱስ የተናገራቸው እና ዛሬም በህይወታችን ላይ ተግባራዊ የሚሆኑ አንዳንድ ታላላቅ እውነቶች እነሆ፡- - ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በእምነት ብቻ ይቀበለናል። - በእርሱ ካመንን ፈጽሞ አይጥለንም። - ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ይወደናል። - የእግዚአብሔር ፍቅር ስጦታ ነው። መዳናችንም ሆነ ሌላ ከእግዚአብሔር የምንቀበለው ሁሉ በእኛ ሥራ ሳይሆን በጸጋው (በቸርነቱ) ነው። - ሌሎች ሰዎችን መውደድ አለብን እንጂ ከእነሱ ጋር መወዳደር የለብንም። - የገባውን ቃል እናምናለን እርሱም ያዘጋጃል። https://t.me/Graceofjesushighpriest
Show all...
የፀጋ ወንጌል

📌በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶች ይለቀቃሉ 📌ጥያቄዎች ከመፅሐፍ ቅዱስ አንፃር ይመለሳሉ 📌የእናንተ ድርሻ Share በማድረግ ሰው የእውነትን ወንጌል እንዲያውቅና እንዲረዳ ማድረግ ነው Group

https://t.me/Graceofjesushighpriestgroup

ሀሳብ እና አስተያየት +251985406785(@yabsen) +251953843618(@josi1423) ✍የጌታን ፀጋ ይብዛላቹህ

👍 2
📌#ቀኝ_ዓይንህም_ብታሰናክልህ_ #አውጥተህ_ጣላት_ምን_ማለት_ነው? -------------------------------- 📌ማቴዎስ 5 (Matthew) 29፤ ቀኝ ዓይንህም ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት፤ ሙሉ ሰውነትህ በገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻልሃልና። 30፤ ቀኝ እጅህም ብታሰናክልህ ቆርጠህ ከአንተ ጣላት፤ ሙሉ ሰውነትህ በገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻላልና። ✍️በዚህ ክፍል ብዙ ቅዱሳን ግራ ከመጋባታቸው የተነሳ በተደጋጋሚ ጥያቄ ይጠይቃሉ። ክፍሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተራራው ስብከት ያስተማረው ሲሆን ንጉሱ ኢየሱስ ህግን መፈጸም ያቃታቸውን የእስራኤልን ህዝብ እየሰበከ ባለበት ሰዓት ያስተማረው ትምህርት ነው። 📌 ቅዱሳን የሚጠይቁት ጥያቄም 1)ቀኝ ዓይንህም ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት? 2)ቀኝ እጅህም ብታሰናክልህ ቆርጠህ ከአንተ ጣላት? ብሎ አስተምሯል ይህ ማለት ምን ማለት ነው??? 👉ኢየሱስ ክርስቶስ አይንህን አውጥተህ ጣላት እጅህንም ቆርጠህ ጣላት ሲል እያወራ ያለው ስለ አካላችን አይንና እጅን መቁረጥ ይሆን ወይስ የትምህርቱ ትክክለኛ ሀሳብ ምንድነው? መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ነገር ምን ያስተምረናል? 👉1)ማቴዎስ 5 (Matthew) 29፤ ቀኝ ዓይንህም ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት፤ ሙሉ ሰውነትህ በገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻልሃልና። ❤ ጌታ ኢየሱስ እያስተማረ ያለው የስጋ አይንህን አውጥተህ ጣል ሳይሆን አይንህን እንዲሳሳት ያደረገውን በአዕምሮህ ውስጥ ያለውን ክፉ ሀሳብ አውጥተህ ጣል ማለቱ ነው። 👉 2) ማቴዎስ 5፡30 ቀኝ እጅህም ብታሰናክልህ ቆርጠህ ከአንተ ጣላት፤ ሙሉ ሰውነትህ በገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻላልና። ቀኝ እጅህም ብታሰናክልህ ቆርጠህ ከአንተ ጣላት ሲል በእጅህ ሀጥያት በሰራህ ጊዜ የስጋ እጅህን ቆርጠህ ጣለው ማለቱ ሳይሆን በእጅህ እንድትሰርቅ ያደረገህን በአዕምሮህ ውስጥ ያለውን ክፉ ሀሳብ አውጥተህ ጣል ማለቱ ነው። ✍️2 ቆሮንቶስ 13 (2 Corinthians) 14፤ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን። https://t.me/Graceofjesushighpriest https://t.me/Graceofjesushighpriest
Show all...
የፀጋ ወንጌል

📌በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶች ይለቀቃሉ 📌ጥያቄዎች ከመፅሐፍ ቅዱስ አንፃር ይመለሳሉ 📌የእናንተ ድርሻ Share በማድረግ ሰው የእውነትን ወንጌል እንዲያውቅና እንዲረዳ ማድረግ ነው Group

https://t.me/Graceofjesushighpriestgroup

ሀሳብ እና አስተያየት +251985406785(@yabsen) +251953843618(@josi1423) ✍የጌታን ፀጋ ይብዛላቹህ

3
❤#የመንፈስ_ቅዱስ_ጥምቀትና #_የእሳት_ጥምቀት❤ ================================== ✍️በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና በእሳት ጥምቀት መካከል ያሉትን ልዩነቶች እንደሚገባ ካለማጥናት የተነሳ በብዙ ቅዱሳን መካከል ግራ መጋባቶች ይታያሉ። በአማኞችም ዘንድ ጌታ ሆይ በእሳት አጥምቀን የሚል ጸሎት በስፋት ይታያል (ይሰማል) እውን ይህ ጸሎት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነውን? 👉 የእሳት ጥምቀት አማኞችን የሚመለከት ነውን? 👉 መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና ስለ እሳት ጥምቀት ምን ያስተምረናል? 📌 መጽሐፍ ምን ይላል፦ ---------------- ሉቃስ 3 (Luke) 16፤ ዮሐንስ መልሶ፡— እኔስ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ነገር ግን የጫማውን ጠፍር መፍታት ከማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ ይመጣል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፤ 17፤ መንሹም በእጁ ነው፥ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፥ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፥ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል፡ አላቸው። ✍️በዚህ ቃል ውስጥ መጥምቁ ዮሐንስ ከእርሱ በኃላ የሚመጣውና በክብር የሚበልጠው ጌታ ኢየሱስ ስለሚያጠምቃቸው ሁለት አይነት ጥምቀቶች ይናገራል። ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና ስለ የእሳት ጥምቀት። ✍️በመቀጠልም ስንዴ እና ገለባ የሚል ቃል ይጠቀማል ስለ ስንዴ ሲያወራ በመንፈስ ቅዱስ በማጥመቅ በአንድ ጎተራ ውስጥ እንደሚያስገባቸው ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት እንደሚያቃጥለው ይናገራል። 📖 መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል፦ -------------------------- 📌 ሁለቱ ጥምቀቶች ምን ይመስላሉ 👉 1) የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ፦ ---------------------------- ✍️እውነተኛ አማኞች ሁሉ ባመኑበት ቅጽበት ጌታ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃቸዋል። ሰው በመንፈስ ቅዱስ ሲጠመቅ የክርስቶስ የአካል ክፍል (አጥንት እና ስጋው) ይሆናል። አማኞች የሚጠመቁትም በህይወት ዘመናቸው አንድ ጊዜ ብቻ ነው። ይህን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አገልጋዮች ማጥመቅ አይችሉም። ሉቃ 3:15-, ሐሥ 1:5,ገላ 3:27,1ቆሮ12:12 ,ኤፌ 5:30 kjv ✍️ዮሐንስ 12 (John) 24፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች። ✍️ኢየሱስ በዚህ ክፍል ራሱን በስንዴ ቅንጣት ይመስላል በእርሱ ሞትና ትንሳኤ ደግሞ ህይወቱን የሚካፈሉትን አማኞች ብዙ የስንዴ ፍሬ እንደሆኑ እናያለን። ከዚህ ጥቅስ ጋር በማገናኘት ወደ ጎተራው ያስገባቸው ስንዴዎች በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቃቸው እውነተኛ አማኞችን እንደሆነ ቃሉ በግልጽ ያስተምረናል። ✍️ጌታ ኢየሱስም ወደ ሰማይ ሊያርግ ባለበት ስዓት ሐዋርያቶቹን ከጥቂት ቀን በኃላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ ብሏቸው ነበር። በባለ ሃምሳ እለትም ይፈጸማል። ሐዋ. ሥራ 1 (Acts) 5፤ ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና፥ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኃላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ፡ አለ። በዚህ ጥቅስ ውስጥ የእሳት ጥምቀት አልተነሳም ምክንያቱም አማኞችን የሚመለከት አይደለምና። 📌 2) የእሳት ጥምቀት፦ ---------------- ✍️ይህ የእሳት ጥምቀት በክርስቶስ አምነው የዳኑትን ቅዱሳን የማይመለከት ሲሆን። በክርስቶስ ኢየሱስ የቤዛነት ስራ ያላመኑ ሙታን ሁሉ ከአዳም ጀምሮ እስከመጨረሻው ሰው በክርስቶስ ሳያምኑ የሞቱት ሁሉም በእሳት ጥምቀት ይጠመቃሉ። ይህ የእሳት ጥምቀት መለኮታዊ ፍርድን የሚያሳይ ሲሆን ጌታ ኢየሱስም የማያምኑትን ሙታን ሀሉ በእሳት ያጠምቃቸዋል።ሉቃ 3:16-17,ራዕ20:11-15 ✍️መጥምቁ ዮሐንስ በሉቃስ 3:16 በማይጠፋ እሳት ስለሚቃጠሉ ገለባዎች ይናገራል። በገለባ የተመሰሉትም በክርስቶስ በማመን ህይወት ያልተካፈሉትን የማያምኑ ሰዎችን የሚያሳይ ነው። አነዚህ የማያምኑ ሰዎችን በአለም መጨረሻ በነጩ ዙፋን ፍርድ ወደ እሳት ባህር በመጣል በእሳት ያጠምቃቸዋል። 👉 ስለዚህ በዚህ ቃል መሰረት የእሳት ጥምቀት እውነተኛ አማኞችን የሚመለከት አይደለምና በእሳትህ አጥምቀን ብሎ መጸለይ ትክክል አይደለም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረትም የለንም። ✍️ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። https://t.me/Graceofjesushighpriest https://t.me/Graceofjesushighpriest
Show all...
የፀጋ ወንጌል

📌በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶች ይለቀቃሉ 📌ጥያቄዎች ከመፅሐፍ ቅዱስ አንፃር ይመለሳሉ 📌የእናንተ ድርሻ Share በማድረግ ሰው የእውነትን ወንጌል እንዲያውቅና እንዲረዳ ማድረግ ነው Group

https://t.me/Graceofjesushighpriestgroup

ሀሳብ እና አስተያየት +251985406785(@yabsen) +251953843618(@josi1423) ✍የጌታን ፀጋ ይብዛላቹህ

💯 2👍 1🔥 1
✍ ጉዳዩ የመደረግ ነው ***************** ✍ የትኛውም ጤነኛ ወንድ ጧት ከቤቱ ሲወጣ ጡት ማስያዣ ማድረግ አስቦ አያውቅም ምክንያቱም የተደረገው ወንድ ነው!! 👉 ወንድ ስለሆነ ጺሙን ያበጥራል እንጂ ወንድ ለመሆን ጺሙን አያበጥርም!! እንዲሁ 📌 ጻድቅ ስለሆንክ መልካም ታደርጋለህ እንጂ ጻድቅ ለመሆን መልካም አታደርግም!! ✍ የትኛዋም ጤነኛ ሴት ጧት ከቤቷ ስትወጣ ጺም ማበጠር አስባ አታውቅም ምክንያቱም የተደረገችው ሴት ነው!! 👉 ሴት ስለሆነች ጡት ማስያዣ ታደርጋለች እንጂ ሴት ለመሆን ጡት ማስያዣ አታደርግም!! እንዲሁ ✍ በክርስቶስ የሆንን እኛ ጻድቅ ተደርገናል......ኃጢአት አናስብም!! 📌 ዳግመኛ የተወለድን እኛ አዲስ ፍጥረት ተደርገናል......አሮጌውን አናስብም!! ✍ ወንድ ሁሉ ወንድ ለመሆን ምንም አያደርግም ሴትም ሴት ለመሆን ምንም አታደርግም!! እንዲሁ 📌 ጻድቅ ተደርገናልና ጻድቅ ለመሆን ምንም አናደርግም!! 📌 ልጆች ተደርገናልና ልጆች ለመሆን ምንም ነገር አናደርግም!! 📌 ቅዱስ ተደርገናልና ቅዱስ ለመሆን ምንም አናደርግም!! ✍ ጉዳዩ የመደረግ እንጂ የማድረግ አይደለም!! 📌 በክርስቶስ ከተደረግነው ተነስተን እናደርጋለን እንጂ በራሳችን ለመደረግ አናደርግም!! እና ምን ልልህ ነው ✍️ በክርስቶስ ከሆንክ ጻድቅ አለመሆን በአዳም ከሆንክ ኃጢአተኛ አለመሆን አትችልም!! ✍️ በክርስቶስ ከሆንክ መጥፋት በአዳም ከሆንክ አለመጥፋት አትችልም!! https://t.me/Graceofjesushighpriest https://t.me/Graceofjesushighpriest
Show all...
የፀጋ ወንጌል

📌በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶች ይለቀቃሉ 📌ጥያቄዎች ከመፅሐፍ ቅዱስ አንፃር ይመለሳሉ 📌የእናንተ ድርሻ Share በማድረግ ሰው የእውነትን ወንጌል እንዲያውቅና እንዲረዳ ማድረግ ነው Group

https://t.me/Graceofjesushighpriestgroup

ሀሳብ እና አስተያየት +251985406785(@yabsen) +251953843618(@josi1423) ✍የጌታን ፀጋ ይብዛላቹህ

✍️ ጸጋ ብቻ...................ቻ!! ********************* ✍ ጸጋ ነጻ ስጦታ ነው፡፡ ስጦታው የሚሰጠው ደግሞ ስጦታው ላልተገባው፣ በራሱ ላልበቃ፣ በገዛ ክንዴ ይሄን አደረግኩ ማለት ለማይችል ኃጢአተኛ ሰው ነው፡፡ ጸጋ የሰጭውን ባለጠግነትና ፍቅር የሚያሳይ ለተቀባዩ የማይገባ ውድ ስጦታ ነው። ጸጋ እግዚአብሔር በምላሹ ምንም ሳይጠይቅ በክርስቶስ በኩል ለኃጢአተኛው ሰው ያደረገው ቸርነት፣ ያወረደው ምህረት፣ ያፈሰሰው ፍቅር፣ ያትረፈረፈው ሞገስ የሰጠው ሕይወት ነው፡፡ ሰው ድኅነትን ፍለጋ እንዳይባዝን፣ በላቤ እና በወዜ እንዳይል፣ አዋጥቼ ልዳን እንዳይል፣ ለፍቼ እና ሰፍቼ ልትረፍ እንዳይል እግዚአብሔር መዳንን ለሰዎች ሁሉ እንዲሁ በነጻ ሰጥቷል!! ✍ አዳምና ሔዋን እግዚአብሔር አትብሉ ካላቸው ዛፍ በመብላታቸው ሁለቱም ራቁታቸውን በሆኑ ጊዜ ከእግዚአብሔር ዓይን ለመሸሸግ ሞከሩ፤ እርቃናቸውን ለመሸፈን የቅጠል መሸፈኛ ሰፉ፤ ሆኖም እነሱ የሰፉት የሃይማኖት መሸፈኛ እርቃናቸውን ሊሸፍን አልቻለም። ሥራው የሰው ስለነበር በእግዚአብሔር ፊት አቅም አልነበረውም፡፡ እግዚአብሔር ግን ኃጢአት ሰርቶ እርቃኑን ለሆነ ሰው ንጹህ እንስሳ ያለጥፋቱ አርዶ ቁርበት አለበሰው፡፡ ሀፍረቱን ሸፈነለት። ለማይገባው አዳም ስጦታን ሰጠው፡፡ ጸጋ ይህ ነው!! ጸጋ ውብ የሆነ፣ የተቀባይን የአቅም ወሰን የጣሰ፣ የሰዎችን የመረዳት ድንበር ያለፈ የተትረፈረፈ ሰማያዊ ስጦታ ነው፡፡ 📌 ጸጋ በስራ የሚገኝ አይደለም፡፡ ሰው በመጾሙ፣ የቤተ ክርስቲያን ስርአቶችን በመፈጸም፣ በመጸለይ የሚያገኘው ደመወዝ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ለሰጠን የጸጋ ስጦታ እኛ ምላሽ ማዘጋጀትና መመለስ አንችልም፡፡ ስጦታ ሆኖ የመጣው ለዚህ ነው፡፡ ✍ ጸጋ በኢየሱስ ክርስቶስ የሆነ ያልተገባን በራሳችን ስራ የማንሸለምበት የእግዚአብሔር ሞገስ ነው፡፡ በጸጋ ከሆነ ግን ከሥራ መሆኑ ቀርቶአል፤ ጸጋ ያለዚያ ጸጋ መሆኑ ቀርቶአል። (ሮሜ 11፥6) ለሚሠራ፥ደመወዝ እንደ ዕዳ ነው እንጂ እንደ ጸጋ አይቈጠርለትም፤ (ሮሜ 4፥4) 📌 ጸጋ ከእግዚአብሔር የሆነ ስጦታ እንጂ በራሳችን ሰርተን የተሸለምነውም የምንሸለመውም አይደለም፡፡ ሰው ስራ ሲሰራ ስራው የድካሙ ውጤት ነውና ለሰራበት ደመወዝ ይከፈለዋል፡፡ ስራውን በአግባቡ ያልሰራ ሰው ግን ደመወዙ ይቀነስበታል፡፡ ይህ ማለት ደመወዝህ የሚወሰነው አንተ በምትሰራው ስራ ላይ ነው፡፡ ጸጋ ግን ለጸለይንበት፣ ለጾምንበት ወይም ቤተ ክርስቲያን ለሄድንበት የድካማችን ክፍያ አይደለም፡፡ ጸጋ ገና መጸለይ፣ መጾም ሳንጀምር እንዲያው የተሰጠን ስጦታ ነው፡፡ የዳንነው በጸጋው ነው፣ የቆምነው በጸጋው ነው የምንጨርሰው በጸጋው ነው!! ✍ ድነት በጸጋ ብቻ እንጂ ከጸጋ ውጭም ሆነ ሥራ ከጸጋ ጋር ተቀላቅሎ አይገኝም!! https://t.me/Graceofjesushighpriest https://t.me/Graceofjesushighpriest
Show all...
የፀጋ ወንጌል

📌በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶች ይለቀቃሉ 📌ጥያቄዎች ከመፅሐፍ ቅዱስ አንፃር ይመለሳሉ 📌የእናንተ ድርሻ Share በማድረግ ሰው የእውነትን ወንጌል እንዲያውቅና እንዲረዳ ማድረግ ነው Group

https://t.me/Graceofjesushighpriestgroup

ሀሳብ እና አስተያየት +251985406785(@yabsen) +251953843618(@josi1423) ✍የጌታን ፀጋ ይብዛላቹህ

✍ ያዳነን ጸጋ **************** ሕገ ልፋት ፣ ሕገ መድከም ሕገ መቅሰፍት ፣ ሕገ መርገም ሕገ ድንጋይ ፣ ሕገ ፊደል ሕገ ውገር ፣ ሕገ ግደል ሕገ ሀዘን ፣ ሕገ ፍርሀት ሕገ ቁጣ ፣ ሕገ መዓት የድንጋይ ፊደል፣ ጽላተ ሙሴ በመላዕክቱ እጅ፣ ሲወርድ ጊዜ በኩነኔ ስር፣ ረግጦ ገዝቶ የሰውን ጆሮ፣ በወስፌ በስቶ አድርግ አታድርግ፣ ከፍርድ አጀብ ጋ ሁሉን ከኃጢአት፣ በታች የዘጋ ሰርቶም ላይጸድቅ፣ ልፋት ስር ጥሎት ሕይወት የማይሰጥ፣ የሞት ግልጋሎት የማያነጻ ፣ ያዳምን በደል ክቡሩ ገዳይ፣ የድንጋይ ፊደል ሞቱ በስራ፣ የማይመከት ኮናኙ ፊደል፣ የሲናው ስብከት የሚፈጽመው፣ ጀግና ቢታጣ የተስፋው ጸጋ፣ ሰው ሆኖ መጣ ------------------------------------------ የምድር በጎች፣ ማንጻት ባይችሉ የሰውን ኃጢአት፣ መንቀል ከስሩ ታርዶ የሚያወርድ፣ ታላቅ ምህረት እግዚአብሔር ሰጠን፣ ከራሱ በረት እንደ ናሱ እባብ፣ ተንጠለጠለ ሁሉን ፈጽሞ፣ ተፈጸመ አለ ለአለም ሁሉ፣ ታረደ በጉ ፈጻሚ አግኝቶ፣ ተሸኘ ሕጉ ፊደሉ ትዕዛዝ፣ ሆኖ ሲገ'ለን ቃል ስጋ ሆኖ፣ በሞት አዳነን ከሲኦል ወ'ተን፣ ጽዮን ገብተናል በፊደል ሞተን፣ በቃል ድነናል ነጻ ያወጣን ፣ ከሞት መንጋጋ እርሱ ኢየሱስ ነው ፣ ያዳነን ጸጋ ✍ ጸጋ ትምህርት ሳይሆን ኢየሱስ የሚባል ሰው ነው!! ✍️ሔኖክ አሸብር https://t.me/Graceofjesushighpriest https://t.me/Graceofjesushighpriest
Show all...
የፀጋ ወንጌል

📌በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶች ይለቀቃሉ 📌ጥያቄዎች ከመፅሐፍ ቅዱስ አንፃር ይመለሳሉ 📌የእናንተ ድርሻ Share በማድረግ ሰው የእውነትን ወንጌል እንዲያውቅና እንዲረዳ ማድረግ ነው Group

https://t.me/Graceofjesushighpriestgroup

ሀሳብ እና አስተያየት +251985406785(@yabsen) +251953843618(@josi1423) ✍የጌታን ፀጋ ይብዛላቹህ

❤️#የቁስጥንጥንያ_የእምነት_ቀኖና❤️ ( በ381 ዓ.ም ) ================================== ✍️እኔ ሁሉን በሚችል ሰማይንና ምድርን፣ የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ አንድ አምላክ በሚሆን በእግዚአብሔር አብ አምናለሁ። ✍️እርሱ ብቻ የአብ ልጅ በሚሆን፣ ዓለም ሳይፈጠር ከአብ በተወለደ፣ ከአምላክ በተገኘ አምላክ፣ ከብርሃን በተገኘ ብርሃን፣ ከእውነተኛ አምላክ በተገኘ እውነተኛ አምላክ፣ በሕልውና ከአብ ጋር አንድ በሆነ፣ በተፈጠረ ሳይሆን በተወለደ፣ ሁሉ በእርሱ በሆነ፣ ስለ እኛ ስለ ሰዎች ስለ ድኅንነታችንም ከሰማይ በወረደ፣ በመንፈስ ቅዱስ ከድንግል ማርያም በተወለደ ሰው በሆነ፣ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመንም ስለ እኛ መከራ በተቀበለ ፥በተሰቀለ፣ በሞተ፣ በተቀበረም፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም እንደ ተጻፈ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ በተነሣ፣ ወደ ሰማይም በወጣ፣ በአብ ቀኝ በተቀመጠ፣ በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ዳግመኛ በክብር በሚመጣ፣ ለመንግሥቱም ፍጻሜ በሌለው በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ። ✍️ከአብና ከወልድ ጋር በሚሰገድለትና በሚከበር፣ ከአብ በሠረጸ ፣ በነቢያት በተናገረ፣ የሕይወት ጌታና ሰጪ በሆነ፣ በመንፈስ ቅዱስም አምናለሁ። ✍️የሁሉም በሆነች በአንዲት ቅድስት የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያንም አምናለሁ። በኃጢአት ስርየት እና በአንዲት ጥምቀትም አምናለሁ። የሙታንንም ትንሳኤና ገና የሚመጣውን ዓለም ሕይወትም እጠባበቃለሁ። አሜን!! ✍️ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። https://t.me/Graceofjesushighpriest
Show all...
የፀጋ ወንጌል

📌በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶች ይለቀቃሉ 📌ጥያቄዎች ከመፅሐፍ ቅዱስ አንፃር ይመለሳሉ 📌የእናንተ ድርሻ Share በማድረግ ሰው የእውነትን ወንጌል እንዲያውቅና እንዲረዳ ማድረግ ነው Group

https://t.me/Graceofjesushighpriestgroup

ሀሳብ እና አስተያየት +251985406785(@yabsen) +251953843618(@josi1423) ✍የጌታን ፀጋ ይብዛላቹህ

❤ #አሮጌው_ሰው_አልተሻሻለም❤ =============================== ✍እግዚአብሔር በክርስቶስ ስናምን የተሻሻሉ ወይም የተጠጋገኑ ሰዎች አላደረገንም ምክንያቱም አሮጌው ሰዋችን ሊሻሻል በማይችል ሁኔታ የተበላሸ ስለሆነ እግዚአብሔር እንጨት ላይ ጠርቆ አስወግዶታል። በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት አድርጎናል ይህ አዲስ ፍጥረት አሮጌ የሀጥያት፥ የአመጻ፥ የበሽታ ወዘተ ታሪክ የሌለው ታሪኩ ኢየሱስ የሆነለት ማንነት ነው። ✍ 2 ቆሮንቶስ 5 (2 Corinthians) 17፤ ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል። 📌 በክርስቶስ ላላችሁ ጸጋና ምህረት ይብዛላችሁ።
Show all...
📌#በክርስቶስ_ነህ_ወይስ_ጴንጤ_ነህ?📌 ** ✍ክርስቶስ የሞተልህ ጴንጤ እንድትሆን ሳይሆን በክርስቶስ እንድትሆን ነው!! ✍ እግዚአብሔር በክርስቶስ መሆንህን እንጂ ጴንጤነትህን አያውቀውም!! 📌 በክርስቶስ ሆነህ እንጂ ጴንጤ ሆነህ ባለመፍትሄ አትሆንም!! ✍ እግዚአብሔር ሁሉን በልጁ የማድረግ እንጂ ሁሉን ጴንጤ የማድረግ ሀሳብ የለውም!! 📌 በክርስቶስ በመሆንህ ሕይወት ይኖርሃል ጴንጤ በመሆንህ ኃይማኖት ይኖርሃል!! ✍️ ወልድ ያለው ሕይወት እንጂ ኃይማኖት የለውም!! 📌 የወንጌል እንቅፋትና የሰው ትልቁ ጥላት ኃይማኖት ነው!! ✍️ ኃይማኖት ነፍስ የወንጌሉን ብርሃን እንዳትረዳ የሚጋርድ ጥልቅ ጨለማ ነው!! 📌 ክርስቶስ ሕይወትን እንጂ ኃይማኖትን አልሰጠም!! ✍️ በኃይማኖት ነፃነት በክርስቶስ ባርነት የለም!! 📌 በኃይማኖት ዳንኩ የሚል በክርስቶስ ጠፋሁ የሚል የለም!! ✍️ በኃይማኖት መፅደቁ የሚሰማው በክርስቶስ ኩነኔ የሚሰማው የለም!! 📌 በኃይማኖት እርሱ ማለት በክርስቶስ እኔ ማለት የለም!! ✍️ በኃይማኖት የሚያርፍ በክርስቶስ የሚቅበዘበዝ የለም!! 📌 በኃይማኖት ድፍረት በክርስቶስ ፍርሀት የለም!! ✍ ኢየሱስ የእምነታችን ራስና ፈጻሚ እንጂ የክርስትና ኃይማኖት መስራች አይደለም!! 📌 ያመኑበትን ሁሉ ሕይወት ሰጣቸው እንጂ ኃይማኖት አልሰጣቸውም!! ✍️ ሕይወት ያለው ኃይማኖት የለውም!!..............ሕይወት ክርስቶስ ነው!! 📌 ጴንጤ መሆንህ በክርስቶስ የመሆንህ ዋስትና አይደለም!! ✍እናልህ ወዳጄ በክርስቶስ ነህ ወይስ ጴንጤ ነህ? 📍#በክርስቶስ_ነኝ!! 📍#In_Christ!! Join Telegram➬ https://t.me/Graceofjesushighpriest https://t.me/Graceofjesushighpriest
Show all...
የፀጋ ወንጌል

📌በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶች ይለቀቃሉ 📌ጥያቄዎች ከመፅሐፍ ቅዱስ አንፃር ይመለሳሉ 📌የእናንተ ድርሻ Share በማድረግ ሰው የእውነትን ወንጌል እንዲያውቅና እንዲረዳ ማድረግ ነው Group

https://t.me/Graceofjesushighpriestgroup

ሀሳብ እና አስተያየት +251985406785(@yabsen) +251953843618(@josi1423) ✍የጌታን ፀጋ ይብዛላቹህ