cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ግጥም ከብሶት አንደበት(@wubie m)

Death die with me

Show more
Advertising posts
200
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሎሚየን ልወርውር! ነገ ገብያ ልውረድ ማለዳ ማልጄ፣ ሎሚዬን ልሸምት ቶሎ ልቅደም ሄጄ፣ መጣጭ ሳይበዛበት ሳይወደድብኝ፣ ፈጥኘ ልወርውር ቆንጂት ሳቴድብኝ። መቼም ማርፈድ ነው ልምዴ ፥ መበለጥ፣ መቀደም ነው ገዴ፥ ስለዚህ ልወርውር! ደረቷን እንዳልስት አስቤ መሳትን፣ ውብ የሆነችውን አይኔ ያረፈባትን፣ ቀርቤ ላማትር መልሷን ልጠባበቅ ፤ በመራቄ ምክንያት መንገድላይ እንዳይደርቅ፤ ለኔ የቀሰርሽው ቀልብሽ ሳይሰረቅ። ሎሚየን ልወርውር! ልላከው ገምቸ ፣ ዋጋው ላልበለጣት በውድ ገዝቸ፣ ከእጅ እየነጠቀች መምጠጥ ላለመደች ፤ ዘንድሮን የዋለች አምናን ያልነበረች፤ ሎሚዬን ልወርውር ! ጥምቀቱን ሂደሻል መጣሁ ተሻምቸ ፣ እየተንደረደርኩኝ መሄድሽን ሰምቸ፣ ከታቦቱ ስደርስ አንችን እረሳሁኝ፣ ለካ ስጋዬን ነኝ አንችን ያ'ሳደድኩኝ። ✍️✍️wubie maralem https://t.me/wubiemlove
Show all...
ግጥም ከብሶት አንደበት(@wubie m)

Death die with me

👍 7👏 1
እንኳን   ለ፳፻፩፮ኛው ለአምላካችን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን በዓሉን የሰላም የፍቅር ያድርግልን
Show all...
ፍርጃ @ጋሻው የኋላሸት (ዘቢደር) በልቦናየ ተዳፍኖ  - የተቀየጥሽኝ በሀዘን - የተዋሃድሽኝ በፌሽታ፣ ትላንቴ ዛሬን ከቀማኝ - ትዝታ ይምከን ይገነዝ - የቁም ፍታቱ ይፈታ! አሁኔን ብቻ ልበርታ! በሰማይ በምድር - አክንፎ አገስግሶ - ከߴቅፍሽ ካልጣለኝ፣ በማበርታት ፈንታ - ተብትቦ ለጉሞ - ደካማ ካረገኝ፣ ታንቆ ይሙት ናፍቆት - እያጠወለገ አንቺን ካስናፈቀኝ! ይጨክን አንጀቴ! እንደ ሞት ልዘንጋሽ - የጎደለብኝን ስማስን ልሞላ፣ ታዛቢ ይውቀሰኝ - ልባል ልብ የበላ፣ መኖር ላይደገም! ለምን ከቁም ሞት ጋር - በቁሜ ልታደም? ከመላ ህዋሴ - ከደም ስሬ ሰርፆ - ከሕይወት ወለላ - አፍላ ፍቅር ቀስሞ፣ መርሳት ህያው ይሁን - ይለምልም ከራርሞ! ኑረትን በከንቱ - ዕድሜን ካለፋይዳ ከተቀራመቱ፣ ትዝታߴና ናፍቆት - ለወሬ አይትረፉ - ተረስተው ይሙቱ! (ለምጻትሽ ብቻ ለߴቅፍሽ ይበርቱ!)     -//-
Show all...
👍 4
🙏____ የሆነ የጎደለ ነገር እንዳለ ይሰማኛል ምንም መረጋጋት አልቻልኩም የማይታወቅ ድብቅ ስሜት በደምስሬ ሲርመሰመስ ሲሯሯጥ ሲፈራገጥ ይታወቀኛል ምናለ እንደ ወጥ ገንፍሎ ቢወጣልኝ ምን ያህል ደስ ባለኝ ነበር በቃ ውስብስብ ያለ ህይወት ____😴 ''እየገነፈለ ድንገት ሆድ የሚያስብስ ሒማ የሚያሳንስ አቅልን የሚበጥስ'' ስሜት አለ ውስጤ __ ውስጤ ይጨሳል ሆዴ ተቀጣጥሎ እንደ ሰው ፊት ደርሶ ይገርፈኛል በማይመከት ወላፈን ድኩም ሰውነቴን ያነደኛል በቃ እንደ ሰደድ እሳት እየተንቀለቀለ ትኩስ ትንፋሼን እያበዛ በጭሱ ሳምባዬን ይገርፈኛል ወላፈኑም ያለ ከልካይ ልፍስፍስ ጅስሜን ያቃጥለኛል '' 😴በቃ ያኮረፈ ስሜት ደስታን የሚሠውር ሣቅን የሚቀማ ልብን የሚያቆስል ሆድን የሚያደማ ስቃይን የሚያሳይ ፍዳን የሚያበላ ልብን የሚያቆሽሽ ዕምነት የሚያላላ ውስጤ ስሜት አለ __ ሁሉም ነገር ተዘበራርቋል ውል አልባ ማንነቴን ለመፈለግ ሳስብ ይደክመኛል ምክንያቱም :- መንገዴ ከመንገዱ ጋር ተለያይቷል ሀሳቤም ከሀሳቡ ጋር ተራርቋል ለዛ ነው የተረበሽኩት በቃ ውስብስብ ያለ ህይወት 🙏 የዘመን ድካም ልፋቱ በቀን ጎደሎ ሲበላሽ የሚኖርለት ሕይወቱ በሰው ባለጌ ሲኮላሽ ስታይ ምን ትላለህ ?? ተስፋ ታጣለህ በኑሮህ ለህይወት ምንም አትጓጓም የቱንም ያህል ብትጥር አቲዝም የደስታ ልጓም __😴 ለዛም ነው ብዙ ጊዜ ስሜቴን በፅሁፍ እንጂ በንግግር ለመግለፅ የሚከብደኝ ማንም የሚረዳኝ ያለ አይመስለኝም አለ አደል ውስጤ እንዲነው የሚሰማኝ 😭 የውስጣችን ስንኝ የልባችን ጩኸት የሆዳችን ዜማ የታፈነ ህመም ስቃይ ነው ሲሰማ _ ሁሉም ነገር ተዘበራርቋል ውል አልባ ማንነቴን ለመፈለግ ሳስብ ይደክመኛል ምክንያቱም :- መንገዴ ከመንገዱ ጋር ተለያይቷል ሀሳቤም ከሀሳቡ ጋር ተራርቋል ለዛ ነው የተረበሽኩት በቃ ውስብስብ ያለ ህይወት 🙏 ስለዚህ ! በቃ በዚች ስንኝ ሀሳቤን ልቋጭላችሁ መሰለኝ 👇 ህይወት እንዲሰምር ተስፋህ እንዲታደስ የሰይጣንን ዕምነት በጌታህ ስም ገርስስ በልብህ ዙፋን ላይ አምላክን ብቻ አንግስ ። 🙏
Show all...
እኔ አንችን ስወድሽ! እኔ አንችን ስወድሽ ቀናቶች ያውቃሉ፤ ሳላውቀው የሄድኩባቸው ጎዳናወች አሉ ፤ ብዙ እጾች ነበሩ ስላንች ለመስማት የተጎናተሉ፤ የፎነጨርኳቸው እልፍ ግንዶች አሉ፤ ውሸት እንዳይመስልሽ ፤ ብትጠይቂያቸው ይመሰክራሉ። አኔ አንችን ስወድሽ! ድንጋዮች ነበሩ ፣ የደነቋቆሩ፣ እንባየን ያቆሩ፣ ስጮህ የጠቆሩ ። እኔ አንችን ስወድሽ ! ፖሎች እኮ አቀዋል ፤ ስንደፋደፍልሽ ደግፈው አዝነዋል ፣ እንደተገተርኩኝ ማታወች አልፈዋል፤ እኔ አንችን ስጠብቅ አብረውኝ ነግተዋል። እኔ አንችን ስወድሽ! የተሸሸኩበት ጣሳወች ያቃሉ፤ አንሳት ይሉኛል ጌሾ እያቀበሉ፤ ደጋግሜ እንድልሽ ስላንች እያስማሉ፤ መለኪያወች ናቸው የተሸምኩሽን አንችን ያቀለሉ። እናማ ስወድሽ ! ቀን ከሌት አልመርጥም፤ ነጋ ፣መሸ አልልም፤ አመት አልደምርም ፤ ዘመን አልቀንስም ፤ በቃ ማሰብ ብቻ ፤ አንችን በመጠበቅ እንዳይኖረኝ አቻ፤ እስከመኖሬ ጫፍ እስከ ሞት መባቻ። እኔ አንችን ስወድሽ ! ጨርቄ ፣ማቄ አልልም፣ ጫማም አላጠልቅም ፣ መኪና አልጠይቅም፣ መዳንች ስመጣ ወዳንች ሳዘግም። አወ! አልፈልግም! አለኝ ምርኩዝ ነፋስ፣ አፍጥኖ የሚያደርስ፣ አለኝ! የሌት ህልም ፈረስ!!!! ✍️✍️✍️wubie maralem https://t.me/wubiemlove
Show all...
ግጥም ከብሶት አንደበት(@wubie m)

Death die with me

👍 5 1