cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Semu tube...2

#የ አላህ ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን #ትንሽ ሆና አባቷን ጀነት የምታስገባ #ወጣት ሆና የባሏን ግማሽ ዲን የምትሞላ እንዲሁም #እናት ሆና ጀነት በ እግሮቿ ስር የምትሆን ፉጡር ሴት ብቻ ናት!!! አላህዬ ለሰጠኸኝ ፀጋ ሁሉ አመሰግንሀለው በፉጥረትህ ስፉር ቁጥር ልክ ምስጋና ይገባህ ። ወደ ግሩፑ ይቀላቀሉን @Semuruhi ማንኛውም ሀሳብና አስታየት @Ruhihubi_bot @Fafuya1433 ያናግሩን።

Show more
Advertising posts
242
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
وَمَا جَعَلَهُ اللَّهُ إِلَّا بُشْرَىٰ لَكُمْ وَلِتَطْمَئِنَّ قُلُوبُكُم بِهِ ۗ وَمَا النَّصْرُ إِلَّا مِنْ عِندِ اللَّهِ الْعَزِيزِ الْحَكِيمِ አላህም (እርዳታውን) ለእናንተ ብስራትና ልቦቻችሁ በእርሱ እንዲረኩ እንጂ አላደረገውም፡፡ ድልም መንሳት አሸናፊ ጥበበኛ ከኾነው አላህ ዘንድ እንጅ ከሌላ አይደለም፡፡           https://t.me/Ruhihubi
Show all...
00:22
Video unavailableShow in Telegram
ህይወት ጦርነት ናት ለምን እጅህን ሰጠህ......
Show all...
ና አሰልቺ ሆነብኝ፡፡ ህይወቴም ያለ ኢንቲሳር፣ ያለ እማዬ፣ ያለ አብዱኬ፣ ያለ ጋሼ ምን ያህል አሰልቺና መራራ ሊሆን እንደሚችል አሰብኩ፡፡ የህይወቴን ጉዞ ያቀለሉልኝ እነሱ ናቸው፡፡ የሁሉም ነገር ውበት ሰው ነው፡፡ ሀዘንም … ደስታም …… ችጋርም …… ድሎትም ያለ ሰው ጎምዛዛ ነው፡፡ እንደዛ አሰብኩ፡፡ ያለአብዱኬ መንገዱ ራሱ ያስጠላል፡፡ የማልደርስ ቢመስለኝም ከአሰልቺው መንገድ በኋላ ቤቴ ደረስኩ፡፡ ቤት ስገባ ኢንቱ እራት አቀራርባ እየጠበቀችኝ ነበር፡፡ ገብቼ ልስማት ስጠጋ አይኗ መቅላቱን ልብ አልኩ፡፡ እማዬም አይኗ ቀልቷል፡፡ ‹‹ኢንቱዬ ምን የተፈጠረ ነገር አለ?›› ግራ እየተጋባሁ ጠየቅኳት፡፡ ወደ ትሪው እየተጠጋች ‹‹እንብላና እነግርሀለሁ፡፡›› አለች! ‹‹አብዱኬስ?›› ‹‹በልቷል!›› መብላት ጀመርን፡፡ በውስጤ ምን ተፈጥሮ ሊሆን እንደሚችል አውጠነጥናለሁ፡፡ የሚያረካ ግምት አልመጣልኝም፡፡ በልተን እንደጨረስን ኢንቱ ላይ አፈጠጥኩ፡፡ ‹‹ኢንቱዬ ምንድነው የሆናችሁት?›› በቀኝ እጇ ግራ እጇን እየዳሰሰች ‹‹ኢቦዬ …… አብዱኬ ……›› ‹‹አብዱኬ ምን ሆነ?!›› ከተቀመጥኩበት ተስፈንጥሬ ተነሳሁ፡፡ በልቷል ስትለኝ ጀምሮ እየሸከከኝ ነበር፡፡ ‹‹ተረጋጋ ምንም አልሆነም! ተቀመጥና እነግርሀለሁ!›› ልቤ አመታቱን ሲለውጥ እየተሰማኝ ነው፡፡ ከጎኗ ተቀመጥኩ፡፡ ‹‹አብዱኬ …… ታሰረ!›› ‹‹ለምን?›› ‹‹የተሰረቀ እቃ ተቀብለሀል ተብሎ!›› ‹‹የት ነው ያለው?›› ተነሳሁ፡፡ ‹‹ኢቦ አሁን እኮ ማታ ነው አያስገቡህም! እኛ እዛ ነበርን! ነገ አብረን እንሄዳለን …… ተረጋጋ!›› ጭንቅላቴን ይዤ ቁጢጥ አልኩ፡፡ በእኔ ሐጥያት እየተቀጣ እንደሆነ ተሰማኝ፡፡ ኢንቱዬ አቅፋኝ ፀጉሬን መዳበስ ጀመረች፡፡ ‹‹ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባል ብለዋል፡፡ በነፃ ሊለቀቅም እኮ ይችላል፡፡›› ‹‹ኢንቱዬ ስልኩ እኮ እኔ ጋር ነው ያለው!›› አውጥቼ አሳየኋት! ‹‹እና የእውነት ተቀብሏል ማለት ነው?›› ደነገጠች፡፡ ‹‹አዎ ኢንቱዬ ……›› ‹‹ለማንኛውም ስልኩን ደብቀው! ፖሊሶች ቤቱን ሊፈትሹ ሲመጡ ከተገኘ ለእሱ መጥፎ ነው፡፡›› መኝታችንን አነጣጥፈን ተጋደምን፡፡ ኢንቱ ትንሽ ቆይታ ተኛች፡፡ እኔን ግን እንቅልፍ ተጣላኝ፡፡ አብዱኬ እስርቤት ውስጥ እንዴት ይሆን ይሆን? መተውት ይሆን? ከአዕምሮዬ የሀሳብ ድር ያለ እረፍት ይመዘዛል፡፡ ከስምንት ሰዓት በኋላ እንቅልፍ ይዞኝ ጠፋ፡፡ ንጋት አስራ ሁለት ተኩል ገደማ ኢንቱ ከእንቅልፌ ቀሰቀሰችኝ፡፡ ‹‹ኢቦዬ …… ተነስ ይረፍድብናል፡፡ ለባብስ!›› በፍጥነት ተነስቼ ለባበስኩ፡፡ እማዬን ተሰናብተን ከጋሼና ከአባይዬ ጋር ወደ ኮልፌ ተጣደፍን፡፡ ፍርድ ቤቱ አንድ የጃጀ ቤት ውስጥ ነበር፡፡ ግቢ ውስጥ ቆመን መጠባበቅ ጀመርን፡፡ ሁለት ሰዓት ከሀያ አካባቢ አንድ ሎንቺን እጃቸው በካቴና የታሰሩ ሰዎችን ማውረድ ጀመረ፡፡ መሳሪያቸውን ያቀባበሉ ፖሊሶች ከግራና ከቀኝ በኩል በተጠንቀቅ ቆመዋል፡፡ አብዱኬ እጆቹ በካቴና እንደተጠፈነጉ ከመኪናው ወረደ፡፡ አባይዬ ስታየው አለቀሰች፡፡ እንባ እየተናነቀኝ ለሰላምታ እጄን አወዛወዝኩለት፡፡ አንገቱን እያዟዟረ እየፈለገን ነበር፡፡ ሲያየኝ ፈገግ አለ፡፡ የታሰሩ እጆቹን ከፍ አድርጎ ሰላም አለን፡፡ እስረኞቹ ከገቡ በኋላ ወደ ችሎት ክፍሉ ገባን፡፡ ዳኛዋ በተራ በተራ የሚገቡትን እስረኞች ክስና ምርመራ እያዳመጠች ቀጠሮ ትፈቅዳለች፡፡ አንዳንዶቹ ላይ ውሳኔ ትሰጣለች፡፡ የአብዱኬ ተራ ደርሶ ወደ ክፍሉ ገባ፡፡ መርማሪው ክሱን ማስረዳት ጀመረ፡፡ ‹‹ … ዋጋው 15 ሺህ ብር የሚጠጋ የሞባይል ቀፎ የስርቆት ወንጀሉን ከፈፀመው ከተከሳሽ ሰለሞን በላይ እኔ አሻሽጥልሀለሁ በማለት ተቀብሏል፡፡ በዚህም የሌባ ተረካቢ በመሆን ……›› አብዱኬ እዚህ ቦታ የቆመው ለእኔ ብሎ ብቻ እንደሆነ ተሰማኝ፡፡ እኔ እህቴን ማገዝ እንድችል ገንዘብ ማግኛ መንገድ ሊፈጥርልኝ በመሞከሩ ብቻ! አብዱኬ ለዳኛዋ፣ ለፖሊሶቹና ለመርማሪዎቹ ተጠርጣሪ ብቻ ነው፡፡ ለእኛ ህይወት ግን ትልቅ ትርጉም ያለው ወንድማችን ነው፡፡ ለጋሼና ለአባይዬ ደግሞ የምሽት ጧሪያቸው …… ጥላ ከለላቸው ነው፡፡ በእሱ መታሰር ስንት ጎሮሮ በረሀብ እንደሚደርቅ ያሰበ የለም፡፡ ዛሬ ቁርስ አልበላንም፡፡ አብዱኬ ባይታሰር ግን እንደምንበላ እርግጠኛ ነኝ፡፡ አብዱኬ ፖሊሶቹ ለማወጣጣት በሚል እንደደበደቡትና እሱ ግን የተባለውን ስልክ እንዳላየ ለዳኛዋ አስረዳ፡፡ ድምፁ ላይ ጥቂት እንኳን የፍርሀት ድባብ አልነበረም፡፡ ዳኛዋ ዳግም እንዳይመቱት ፖሊሶቹን አስጠነቀቀች፡፡ መርማሪው የአስራ አራት ቀን ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠየቀ፡፡ ዳኛዋ የስድስት ቀን ቀጠሮ ፈቀደች፡፡ ችሎቱ እንደተጠናቀቀ በእግራችን አብዱኬ ወደ ታሰረበት አጠና ተራ ወዳለው እስር ቤት ሄድን፡፡ የእስረኞቹ መኪና እስኪመጣ ዘገየ፡፡ ከመኪናቸው ወርደው ወደ ውስጥ ከገቡ በኋላ በሩ ለጠያቂዎች ተከፈተ፡፡ አስጠርተነው አባይዬ የቋጠረችለትን ምግብ ሰጠነው፡፡ ፈገግ ብሎ ‹‹ኢቦ ……›› አለ፡፡ ‹‹ወዬ ……›› ‹‹ሞባይል የሚባል አልተቀበልኩም እሺ? እሺ? በቅርቡ በነፃ እፈታለሁ፡፡›› በአይኑ አወራኝ፡፡ ለማለት የፈለገው እንደገባኝ እንዲያውቅ አንገቴን በአዎንታ እየወዘወዝኩ ‹‹እሺ ……›› አልኩ፡፡ ትንሽ አዋርተነው ብዙ ጠያቂ ስለመጣ ቦታ ለቀን ወጣን፡፡ ለታክሲ የምንከፍለው ብር ስላልነበረን ከአጠና ተራ እስከ አንፎ በእግራችን መመለስ ጀመርን፡፡ መንገድ አሳብረን …… እያወራን …… ከፀሐዩ ጋር እየታገልን …… መድረስ አይቀርምና ቤታችን ደረስን፡፡ ቤት ውስጥ ምንም የሚበላ ነገር አልነበረም፡፡ ፍራሹ ላይ ተቀምጬ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አሰብኩ፡፡ ማህሌት ጋር ከመደወል የተሻለ ሀሳብ ሊመጣልኝ አልቻለም፡፡ በኢንቱዬ ስልክ ደወልኩላት! ይጠራል ግን አታነሳም፡፡ ምህረት ጋር ደወልኩ፡፡ እሷም አታነሳም፡፡ ግራ ገባኝ፡፡ ሰላም አይደሉም ይሆን ብዬ ሰጋሁ፡፡ አሁን ከመተኛት ውጪ የመጣልኝ ሀሳብ የለም፡፡ ድካምና ረሀብን በእንቅልፍ መሸወድ! ኢንቱዬም ከጎኔ ተኛች፡፡ እማዬም ተኝታለች፡፡ በሩ ተዘግቶ ቤቱ ጨልሟል፡፡ ከምድር የተገለልን መሰለኝ፡፡ የሁሉም መከራ የኛ ቤት ላይ የወደቀ ይመስላል፡፡ በልቤ ‹‹ለምን?›› ብዬ ጠየቅኩ፡፡ ‹‹ለምን የማያባራ የመከራ ጎርፍ ይወርድብናል? እኛ ከሌሎች የሰው ልጆች በምን እንለያለን? ፈጣሪን ፍጠረን ብለነዋል? ለምን ፈጥሮን ችግር ላይ …… መከራ ስር ይጥደናል?›› ከራሴ ጋር ተጨቃጨቅኩ፡፡ የረሀብ መጥፎ ነገሩ እንቅልፍ እንዳትተኛ መከልከሉ ነው፡፡ እንቅልፍ እንዲወስደኝ ብታገልም በቀላሉ ማሸለብ አልቻልኩም፡፡ ‹‹ደሀ ጥሩ እንቅልፍ ይተኛል፡፡›› ያሉን ሽንገላ ቅኔ ነው ማለት ነው? ሲሞት ነው? ቶሎ ይሞታል ለማለት ነው? ይኸው አሁን ለምን እንቅልፍ አይወስደኝም? ምኔ ሀብታም ይመስላል? ፈጣሪ ላይ ያሉኝ ብሶቶች ሁሉ እንደአዲስ ሲገነፍሉ ተሰማኝ፡፡ ግን ለምን? ስለፈጣሪስ ለማን አቤት ይባላል? . ይቀጥላል … . @Ruhihubi
Show all...
ከተራራው ላይ ክፍል አስር (ፉአድ ሙና) . ‹‹ከሰማይ በላይ ያለኸው ፣ ነፍሴን ለስቃይ ፈጥረኸው፣ ለአፍታ ሊያርፍ ቢደገፍ፣ ምነው ምርኩዙን ቀማኸው፣ በሱም ቀናህ?›› *** እራት ከተበላ በኋላ አብዱኬ ትንሽ ተጫውቶ ሄደ፡፡ ትንሿ ጎጇችን ውስጥ ሶስታችን ብቻ ቀረን፡፡ እማዬ ተኝታለች፡፡ ከኢንቱዬ ፊት ለፊት ተቀምጬ አይን አይኗን እያየሁ እስክትነግረኝ መጠባበቅ ጀመርኩ፡፡ ፊቷ ላይ መከፋት ይነበባል፡፡ መከፋቷን በውሸት ፈገግታ ልትሸፍነው እየሞከረች ‹‹ምንድነው የምትቁለጨለጨው?›› አለችኝ፡፡ አይኖቼን ፊቷ ላይ እንደተከልኩ ‹‹ንገሪኛ!›› አልኩ፡፡ እንባዋ አይኗን ሞልቶ ለመፍሰስ መታገል ጀመረ፡፡ ሳግ ባጠረው ድምፅ ‹‹እነግርሀለሁ ……›› አለች፡፡ ፍራሹ ላይ ከጎኗ ተቀምጬ አቀፍኳት፡፡ ማልቀስ ጀመረች፡፡ እያለቀሰች ‹‹ኢቦዬ አልቻልኩም …… ሁሉም ከቁጥጥሬ ውጪ ሆነ!›› አለችኝ፡፡ በእጄ ፀጉሯን እየዳበስኩ በዝምታ እስክትቀጥልልኝ መጠበቅ ጀመርኩ፡፡ ‹‹ኢቦዬ …… እጄ ላይ ምንም ገንዘብ የለም፡፡ ነገ እንኳን ለምሳ የምቋጥርልህ ነገር የለኝም! ከስራ ተባርሬያለሁ፡፡ በቻልኩት አቅም ለመሸፈን ሞክሬያለሁ፡፡ ግን አሁን ከአቅሜ በላይ ሆነ፡፡ አታፍርብኝም አይደል?›› ጭምቅ አድርጌ አቀፍኳት፡፡ ‹‹ግን አይዞህ እሺ …… ብንራብም ይኼን ሳምንት ብቻ ነው፡፡ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ገንዘብ አገኛለሁ፡፡ እሺ?›› እንባዋን እየጠረገች ‹‹እሺ ኢቦዬ?›› አለች፡፡ ግንባሯን ሳምኳት፡፡ ‹‹ኢንቱዬ …… እንደዚህ በግልፅ ስትነግሪኝ እኮ ላንቺም ለእኔም ይቀላል፡፡ አትጨነቂ …… ደግሞ ለዚህ ሳምንት መፍትሔ አናጣም!›› ተንሰቀሰቀች፡፡ አቅፌ ላረጋጋት ሞከርኩ፡፡ ‹‹ኢንቱዬ …… እኔን እኮ ከረሀቡ በላይ የሚያመኝ አንቺ ከፍቶሽ ሳይ ነው፡፡ እኛ ለረሀብ አዲስ ነን እንዴ? ረሀቡንም መከራውንም መቋቋም የቻልኩት ግን አንቺን በማየት ነው፡፡ አንቺን ማየት …… ደስ ብሎሽ ማየት ከሁሉም በላይ ያጠነክረኛል፡፡ ኢንቱዬ በጣም እወድሻለሁ፡፡ በጣም! አትዘኚ! አብረን እናልፈዋን እሺ?!›› እንባዋን እየጠረገች ‹‹እሺ!›› አለች፡፡ ‹‹ፈገግ በያ!›› ‹‹እሺ›› ፈገግ ለማለት ሞከረች! ጎኗን እየነካሁ ስኮረኩራት መሳቅ ጀመረች፡፡ መኝታችንን አነጣጠፍኩና ተቃቅፈን ተኛን፡፡ ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ በእኔና በኢንቱ መካከል ትራስ ገብቷል፡፡ ኢንቱ ተዘርራ ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ሰጥማለች፡፡ በመካከላችን ያለው ትራስ የእማዬ ፍራሽ ላይ የነበረ ነው፡፡ ግራ ግብት አለኝ፡፡ ማታ ተቃቅፈን እንደተኛን ትዝ ይለኛል፡፡ ተነስቼ ለትናንትና አቅጄው የነበረውን ለመጨረስ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ ትንሽ ቆይታ ኢንቱዬ ነቃች፡፡ እየሳቀች መሀከላችን በነበረው ትራስ መታችኝ፡፡ ሳቋ እየተጋባብኝ ‹‹ይኼ ከየት መጥቶ ነው?›› አልኳት፡፡ ‹‹ፍቅረኛ ምናምን ጀምረሀላ!?›› በአይኖቿ ልታወጣጣኝ ሞከረች፡፡ ሳቅኩኝ! ‹‹ተናገራ የምሬን እኮ ነው፡፡›› ‹‹ኧረ ወፍ የለም!›› ‹‹እሺ ትናንት የተመቸችህ…… የሳምካት ወይም ብስማት ምናምን ያልካት ሴት የለችም?›› ‹‹ባይሆን የሚያምር ከንፈር አይቻለሁ፡፡ ግን ማንንም አልሳምኩም፡፡›› ‹‹ወረኛ አሳሳምህማ ልምድ ያለው ሰው አሳሳም ነበር!›› ‹‹የምን አሳሳም ነው?›› ግራ አጋባችኝ፡፡ ‹‹ማታ በእንቅልፍ ልብህ ስትስመኝ ነበር …… ለዛ ነው ትራሱን መሀል ላይ ያደረግኩት!›› ‹‹ማን እኔ? ምንሽን?›› ‹‹ከንፈሬን ነዋ! የሆነ ሰዓት ስባንን አይንህን ዘግተህ ……›› ሳቀች፡፡ ‹‹ቆይ እንዴት ይሆናል? ማለቴ እንዴት ከንፈርሽን አገኘሁት?›› ‹‹ብዙም ሩቅ አልነበረም …… ፊት ለፊትህ ነበር እኮ!›› ሳቀች፡፡ ‹‹ደግሞ አቅፈኸኝ ስለነበር በደመ-ነብስም አይጠፋህም!›› አፈርኩ! እሷ ትስቃለች፡፡ በትራስ እየመታች ሙድ ትይዝብኛለች፡፡ ‹‹ባይሆን እውነቱን ተናገር! ስመህ አታውቅም ማንንም?›› ‹‹ኢንቱዬ …… ማንንም አልኩሽ እኮ! ማንንም!›› ተነስቼ መለባበስ ጀመርኩ፡፡ ከቻልኩ ስልኩን ዛሬ እንደምንም ለመሸጥ አስቤያለሁ፡፡ ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ ስዘገጃጅ አብዱኬ መጣ፡፡ እጁ ላይ ሁለት ፓስቲ ይዟል፡፡ እንደሌላው ጊዜ ምድጃው ላይ የተጣደ ነገር ሲያጣ ‹‹ሻይ የለም እንዴ?›› አለ፡፡ ኢንቱዬ ፈገግ ብላ እያየችው ‹‹ዛሬ ሻይ ፎርፈናል!›› አለች፡፡ ‹‹አትነግሪኝም እንዴ!›› አኮረፈ! ‹‹በቃ እኛ ውጪ ‘ሚቀማመስ እንፈላልጋለን! ለእናንተ ስሪ!›› ከኪሱ ሀምሳ ብር አውጥቶ ሰጣት፡፡ ‹‹ኧረ አብዱኬ ……›› ኢንቱዬ በሀፍረት አንገቷን ሰበረች፡፡ ‹‹ምን ልትዪ ነው ደግሞ …… ወንድምሽ አይደለሁ እንዴ!?›› ‹‹እሱማ ነህ …… አበዛሁት ብዬ እኮ ነው፡፡ አላህ ይስጥልኝ …… መቼስ ምን እልሀለሁ ……›› ፓስቲውን ከሰጣት በኋላ ተሰናብተናቸው ወጣን፡፡ መንገድ ላይ እየሄድን አብዱኬን ከሌላው ጊዜ በተለየ ተመለከትኩት፡፡ መልዓክ መልዓክ መሰለኝ፡፡ በስስት እየተመለከትኩት ‹‹አብዱኬ ……›› አልኩት፡፡ ‹‹ኧ›› ‹‹ታውቃለህ ትምህርት ቤት ስማር ሁሉም በጣም Smart እንደሆንኩ ይነግሩኛል፡፡ ለእኔ ግን በጣም smart ማን እንደሆነ ታውቃለህ?›› ‹‹ማነው?›› ‹‹አንተ ነህ!›› ‹‹ምን ቀላቅለህ ቅመህ ነው?›› ‹‹ቀልዴን አይደለም አብዱኬ! እኔን Smart የሚሉኝ በሚታወቅ ቀመር ሂሳብ፣ ፊዚክስ ወይም ደግሞ በሽምደዳም ቢሆን ሌሎቹን ትምህርቶች በደንብ መረዳትና መስራት ስለምችል ነው፡፡ ይኼ የሚታወቅ ነገር ነው፡፡ ጥረት እንጂ ልዩ ጥበብ አይጠይቅም፡፡ ልዩ ጥበብ የሚጠይቀው ያልተፃፈን ነገር መረዳት ነው፡፡ የሰውን ልጅ መረዳት! የሰውን ጭንቀት ያለምንም ንግግር መረዳት! ከጭንቀቱ መፈወስ! ህይወትን መረዳት! ተቋቁሞ መኖር መቻል! ብዙ ሰው እኔን መሆን ይፈልጋል፤ እኔ ግን የምፈልገው አንተን መሆን ነው!›› ‹‹የእኔን Smart ልንገርህ?›› ‹‹ንገረኝ ……›› ‹‹የእኔ Smart ኢንቲሳር ናት፡፡ ለራስ ሳይጨነቁ ለሌላ ሰው የመኖር ምሳሌዬ ናት፡፡ ድሮ ስራ ስጀምር ገንዘብ እንዴት መጠቀም እንዳለብኝ አላውቅም ነበር፡፡ ሁሉንም ያስተማረችኝ እሷ ናት፡፡ የከፋኝ ቀን የምሄደው ወደሷ ነው፡፡ ከባድ የመሰለኝን አቅልላ ታሳየኛለች፡፡ ያጣሁ ጊዜ ያላትን በአቅሚቲ ታካፍለኛለች፡፡ አንዳንዴ ምናለ ከእሷ ጋር ከአንድ መሀፀን በወጣን …… የስጋም እህቴ በሆነች ብዬ እመኛለሁ፡፡ ኢቦዬ እህትህ በጣም በጣም ልዩ ሰው ናት!›› ‹‹እሷስ ልክ ነህ ልዩ ናት!›› ባጃጅ ተራ ደርሰን አንድ ሻይ ቤት ገባንና ፓስቲ በሻይ በላን፡፡ አለምባንክ ደርሰን ከአብዱኬ ጋር ልንለያይ ስንል እጄን ይዞ ‹‹ይኸውልሽ ኢቦ …… ችግር ሁሌም ያጋጥመናል፡፡ ግን ደግሞ ያልፋል፡፡ ገባሻ! ዛሬ ቢቸግረን ነገ እናገኛለን፡፡ አትጨነቅ!›› አለኝ፡፡ አሁን አሁን አብዱኬን በአንድ አመት እንደምበልጠው መርሳት ጀምሬያለሁ፡፡ ታላቅ ወንድሜ …… ታላቅ ወንድሜ ይመስለኛል፡፡ ከአብዱኬ ጋር ተለያይተን ወደ ትምህርት ቤት ገባሁ፡፡ ቀኑን ሙሉ በቻልኩት መጠን ስልኩን ለመሸጥ ለብዙ ተማሪዎች ሳሳይ ዋልኩ፡፡ በርካሽ ስምንት ሺህ ድረስ ልሸጥላቸው ብዙዎችን አጠያየቅኩ፡፡ የሚደፍር አልተገኘም፡፡ ባዶ እጄን ወደ ቤት መግባት ቀፈፈኝ፡፡ ማህሌትን ላስቸግራት አሰብኩና ወደ ማታ ደወልኩላት፡፡ ስልኳ ዝግ ነበር፡፡ ማታ ቤተል ቤተ-መፅሀፍት ከአቤላ ጋር ተቀምጬ አብዱኬ ስለዘገየብኝ ለመደወል ሞከርኩ፡፡ ስልኬ ካርድ አልነበረውም፡፡ በአቤላ ስልክ ደወልን፡፡ ስልኩ ዝግ ነው፡፡ ግራ ገባኝ፡፡ ትንሽ ጠብቄው ሲቆይ ወደ ቤት ሄድኩ፡፡ ለብቻዬ ስለሆንኩ ነው መሰል መንገዱ በጣም ረዥም
Show all...
ደስታ ማለት ወዳጆቼ ሁሉን ነገር ማግኘት ማለት አይደለም፣ አላህ በሠጠህ ነገር መደሠት ነው፣ እሱ በወደደልህ ነገር መርካት ነው፣ ❤️❤️❤️اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وآله وصحبه أجمعين ❤️❤️❤️ በተሰጠን ነገር ተደስተን እና ረክተን የምንኖር በሰለዋት የፈካ፣ በካህፍ የደመቀ በዱዓ የተዋበ ጁምዓ ይሁንልን ።
Show all...
🌿🌟🌿🌟🌿🌟🌿🌟🌿🌟🌿🌟🌿🌟🌿🌟🌿 የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- 🌿(( ﺇِﻥَّ ﻓِﻲ ﺍﻟْﺠُﻤُﻌَﺔِ ﺳَﺎﻋَﺔً ﻟَﺎ ﻳُﻮَﺍﻓِﻘُﻬَﺎ ﻋَﺒْﺪٌ ﻣُﺴْﻠِﻢٌ ﻳَﺴْﺄَﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻋَﺰَّ ﻭَﺟَﻞَّ ﻓِﻴﻬَﺎ ﺧَﻴْﺮًﺍ ﺇِﻟَّﺎ ﺃَﻋْﻄَﺎﻩُ ﺇِﻳَّﺎﻩُ ‏)) 🌟((ጁሙአ ቀን አንዲት ሰአት አለች በዛች ወቅት ላይ አንድ ባሪያ አላህን ከመልካም ነገር እየጠየቀ አይገናኝም አላህ ያን ነገር ቢሰጠው እንጂ ።)) 🌿የውመል ጁሙዐህ የሰዎች ሁሉ አባት ጀነት የገባበትና ከርሷም የወጣበት ቀን ነው፣ አንድ ቀንም እንደሚመልሰው አላህ ቃል ገብቶለታል፣ 🌟ዛሬ አንተ መመለስህ የሚረጋገጥበት ቀን እንዲሆን ከፈለግክ እጅህን ወደ አላህ ዘርጋ፣ምናልባትም ዱዐ የማይመለስባት ወቀት ገጥማህ የዱንያ የአኺራህ መሻትህ ይሞላልህ ይሆናልና ★ያ አላህ★ በል.......... 🌟ያ አላህ የክብር ሀገር የሆነችውን ጀነት ያለ ሂሳብና ያለ ቅድመ ቅጣት ከሚገቡት አድርገን💚🥹                     🌿💚🌿መልካም ጁመዐ💚🌿💚
Show all...
01:00
Video unavailableShow in Telegram
00:22
Video unavailableShow in Telegram
ህይወት ጦርነት ናት ለምን እጅህን ሰጠህ......
Show all...
ውስጥ?›› ፈገግ አለችና ‹‹አቤላ ከፈቀደልን ካንተ ጋር የሆነ ቦታ ደርሰን እንድንመጣ ፈልጌ ነበር!›› አለች፡፡ አቤል እየሳቀ ‹‹ምን ጣጣ አለው …… ብቻ እንደትናንትናው ብዙ በር ያለበት ቤት አስገብተሽው እንዳይጠፋ!›› አለ፡፡ አቤላን ተሰናብተን መኪናዋ ውስጥ ገባን፡፡ መኪናው ውስጥ ያለው ጠረን ደስ ይላል፡፡ ‹‹እሺ …… ወዴት ነን?›› አልኳት ቀበቶዋን የምታስረውን ማህሌትን እየተመለከትኩ! ‹‹you will see it! …… አንድ ቦታ እወስድሀለሁ …… unfortunetly ለዛሬ ጥናት ያልፍሀል፡፡ I hope you won’t get mad! yeah?›› ‹‹እሺ ግን ይኼን ያህል ጊዜ የሚወስደው ምን ቢሆን ነው?›› ‹‹please be patient!›› ሳቀች፡፡ መኪናዋን በአርባ ሜትሩ በኩል እያካለበች ጦርሀይሎችን አልፋ …. ቶታልን ዞራ …. ሞቢል ጋር የሚገኘው ካልዲስ ኮፊ ግቢ ውስጥ ቆመች፡፡ አስተናጋጁ ሲመጣ ለእኔም ለእሷም አዘዘች፡፡ ምን እንደምፈልግ አልጠየቀችኝም፡፡ የመኪናውን መስታወቶች ዘጋቻቸው፡፡ ‹‹አብርሽዬ …… እስኪ just tell me ምን የጎደለኝ ይመስልሀል?›› ‹‹እኮ አንቺ?›› ‹‹yeah እኔ!›› ‹‹አትቀልጂ ባክሽ! ምንም ነዋ! ምንም ነው የጎደለሽ!›› ሳቅ አለች፡፡ ‹‹I was የአምስት አመት ህፃን ምናምን ነገር when my mom dies! Dad single parent ሆኖ ነው ያሳደገኝ!›› ‹‹እናትሽ ሞታለች እንዴ? ይቅርታ አላወቅኩም ነበር!›› ‹‹Its okay! Its okay! Feel free!›› ‹‹ወንድምም ሆነ እህት የለኝም፡፡ I am the only one! …… Dad is በጣም busy! ስራውን ቤት ሳይቀር ነው የሚሰራው! Somedays በጣም ብቸኝነት ይሰማኝ ነበር፡፡ ለኔ ብሎ ድጋሚ አላገባም! He is married to his work! የኛን ቤት ስታይ ይህን ገምተሀል?›› ‹‹በፍፁም! በፍፁም አልገመትኩም!›› ‹‹So እኔም እንዳንተ ፈጣሪ ከኔ ጋር መልካም ግንኙነት የለውም ማለት እችላለሁ አይደል?›› ሳቀች፡፡ ‹‹የኛ እኮ በሁሉም ነው! አንቺ እኮ በአንዱ ብትከፊ ሌላ መፅናኛ አለሽ!›› ‹‹ሀብታም ነን I know! ሰው ግን የለኝም! Even በእሱም ቢሆን አላማርርም!›› አስተናጋጁ ምግቡን ይዞ መጣ፡፡ ፒዛ ነበር፡፡ እየበላን ማውራት ጀመርን፡፡ ‹‹Okay let’s play a game እስኪ አይንህን ጨፍንና ስለእኔ ጥሩ ጥሩ ጎኔን ንገረኝ!›› አይኔን ጨፍኜ ስለማህሌት አሰብኩ፡፡ ‹‹ማህሌት …… ቀላ ያለች፣ አይኖቿ ትላልቅ፣ ፀጉሯ ረዥም፣ ሁሌ ቀሚስ የምትለብስ ……›› ‹‹No! No! Come on! ግለፀኝ አይደለም ያልኩህ! ፈጣሪ ለእኔ የሰጠኝን መልካም ፀጋ ቁጠርልኝ!›› ‹‹እሺ …… ማህሌት ቅን ነች! ደግ ነች! በጣም ቆንጆ ናት! ጎበዝ ተማሪ ናት! አባት አላት! የምግብ ችግር የለባትም ማለቴ የሀብታም ልጅ ናት! ጥሩ ጓደኞች አሏት! በቃ!›› ‹‹Okay open your eyes. አንተ ስለኔ ሰባት ጥሩ ነገር ቆጥረሀል፡፡ አሁን የኔ ተራ ነው፡፡›› አይኖቿን ጨፈነች፡፡ አይኗን ስትጨፍን የበለጠ ታምራለች፡፡ ከንፈሮቿ ያሳሳሉ፡፡ ‹‹አብርሽ …… በራሱ ይተማመናል! በጣም Genius ነው፡፡ በጣም የምታምር Smart እህት አለችው፡፡ እናቱ በህይወት አሉ፡፡ በጣም ቆንጆ ነው፡፡ amazing friends’ አሉት! በጣም ግልፅ ነው! ጥሩ ስነ-ምግባር አለው! ጤነኛ ነው!›› አይኗን ከፈተች፡፡ ‹‹So እኔ ዘጠኝ ቆጠርኩ! አሸነፍኩህ ማለት ነው!›› ዘጠኝ መልካም ነገር አለኝ? አስቤው አላውቅም ነበር፡፡ ክላክስ እያደረገች ‹‹ፈጣሪን ምን አድርግልኝ ብለኸው ታውቃለህ?›› አለችኝ፡፡ ‹‹አባቴን አትርፍልኝ ብዬው አውቃለሁ …… ገደለው! እህቴ ላይ መከራ አታብዛባት አልኩት …… ደራረበባት! እማዬን አሽልልኝ አልኩት …… ህመሟን ጨመረው! በጠየቅኩት ቁጥር ተቃራኒው እየሆነ ነው፡፡ ስለዚህ ተውኩት! አትድረስብኝ አልደርስብህም ብዬ ማለት ነው!›› ‹‹ጎበዝ አድርገኝ አላልከውም …… ጎበዝ አደረገህ! ጤናዬን አደራ አላልከውም …… ጤነኛ አደረገህ! Why don’t you see መልካም መልካሙን?›› አስተናጋጁ ትኩስ ነገር ይዞልን መጣ፡፡ ‹‹የቆምኩበት ቦታ ከባድ ነው ሚቾ!›› ‹‹what you just call me? ሚቾ! Wow! ወድጄዋለሁ! ሁሌ እንደሱ ጥራኝ!›› አለችና ማኪያቶዋን እየማገች ስለ ተስፋ፣ ስለ ፈጣሪና ስለህይወት ያላትን አመለካከት ታስረዳኝ ጀመረች፡፡ አብራርታ ስትጨርስ ‹‹እስኪ ያንተን ንገረኝ!›› አለች፡፡ ‹‹እኔ ስለ ረሀብ ነው የማስበው! ገና ስለምግብ ነው የምጨነቀው! በባዶ ሆዴ ደግሞ አንቺ ያልሽው አይነት ተስፋም፣ ህይወትም፣ ፈጣሪም …… ሊያፈላስፉኝ አይችሉም፡፡ ፍልስፍናዬ ረሀብ ነው፡፡ ፍልስፍናዬ የእህቴ ስቃይ፣ የእናቴ ህመም ነው፡፡›› አይኔ እንባ ሞላ፡፡ ብርጭቆዋን ዳሽ ቦርዱ ላይ አስቀምጣ ጭምቅ አድርጋ አቀፈችኝ፡፡ አንገቴን ደረቷ ስር ቀብሬ አነባሁ፡፡ ስረጋጋ ሂሳብ ከፈለችና መኪናዋን አስነሳች፡፡ ጨልሞ ነበር፡፡ ወደ ሰፈር እየተመለስን ‹‹ሚቾ …… ሐዋርያት ማለት ግን ምን ማለት ነው?›› አልኳት፡፡ ፈገግ አለች፡፡ ፈገግ አልኩኝ፡፡ ‹‹Okay …… ሐዋርያት የእምነቱ ተከታዮች የምንጠራበት ስያሜ ነው፡፡ ቤተክርስትያናችን ደግሞ ሐዋርያዊት ነው የምትባለው!›› ‹‹እሺ ሐዋርያዊት ማለት ምን ማለት ነው? ጥያቄዬ እሱ ነበር! ማለቴ ስለእምነቱ!›› ‹‹ሐዋርያዊት is a religion በአንድ አምላክ የሚያምን …… በእየሱስ ስም ጥምቀት የሚያምን …… ሐይማኖታዊ ስርዓቱ የሚከበርበት or የሚተገበር እምነት ነው!›› ‹‹ምንድነው ለየት የሚያደርገው?›› ‹‹ያው እኛ አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ አንድ ናቸው ብለን እናምለን፡፡ like ስላሴ አንድም ሶስትም በሚባለው አናምንም! አብ፣ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ አንድ አካል ብለን እናምናለን፡፡ ሌላው ደግሞ ቀን መርጠን የምናከብረው በዓልም የለም፡፡ plus ስናገባ ቀለበት አናደርግም! እንደምታየው አንገቴና እጄ ላይም ምንም አይነት ጌጣ ጌጥ የለም፡፡ ጆሮዬም አልተበሳም!›› ‹‹ኦው ይገርማል ›› አንገቴን በግርምት እየነቀነቅኩ ጆሮዋንና አንገቷን ተመለከትኩ፡፡ ጆሮዋም አልተበሳም፡፡ እጇም ሆነ አንገቷ ላይ ጌጥ የለም፡፡ ወደ ቤተ-መፅሀፍቱ ስንደርስ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አልፎ ነበር፡፡ በሩ ጋር አውርዳኝ ተሰናብታኝ ሄደች፡፡ ወደ ቤተ-መፅሀፍቱ ስገባ አቤላ እየሳቀ ያየኛል፡፡ አንገቴን ሰብሬ ከፊትለፊቱ ተቀመጥኩ፡፡ ትንሽ ማንበብ ፈልጌያለሁ፡፡ መፅሀፌን ከፍቼ ንባቤ ላይ ሰመጥኩ፡፡ አቤላ በየመሀሉ እየሳቀ ይመለከተኛል፡፡ ሶስት ሰዓት ተኩል ሊሆን ሲል አብዱኬ መጣ፡፡ ከቤተ-መፅሀፍቱ እየወጣን አቤላ የአብዱኬን ትከሻ እየነቀነቀ ‹‹አባቴ ኢቦ ማህሌትን አፈፍ አድርጎልሻል!›› አለው፡፡ ‹‹አቤላ ደሞ ምንሼ ነው? ነገር አብርድ እንጂ! ሰላማዊ ግንኙነት ነው ያለን!›› ‹‹እሱ ጦርነት ነው አላለ!›› አብዱኬ ጣልቃ ገባ፡፡ ‹‹ታውቂያለሽ አብዱኬ ሲዞሩ አምሽተው አሁን ነው ላይብረሪ የገባው! የት እንደነበሩ እንኳን ምንም አልነገረኝም!›› ‹‹ላይብረሪ ስለነበርን ነዋ! ካፌ ነበርን በቃ ስናወራ ምናምን! ምንም አዲስ ነገር የለውም!›› ‹‹ለምን አቤላን ትታችሁት ሄዳችሁ?›› መመለስ አልቻልኩም፡፡ ዝም ስል ሁለቱም ጮክ ብለው ሳቁ፡፡ ከአቤላ ጋር ተለያይተን ወደ ቤት ሄድን፡፡ ኢንቱዬና እማዬ መምጣታችንን በጉጉት ሲጠብቁ ነበር፡፡ ከሌላ ጊዜው ትንሽ አርፍደናል፡፡ የቀረበው እ
Show all...
ራት ትንሽ ነበር፡፡ኢንቱ ‹‹እኔ በቃኝ!›› አለች፡፡ እኔ መብላቴን ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ በአብዱኬ ምስክርነት አሳምኛቸው መብላት ጀመሩ፡፡ በልቤ ዛሬ ኢንቱዬ እውነቱን እንድትነግረኝ ተመኘሁ፡፡ . ይቀጥላል … . @Ruhihubi
Show all...