en
Feedback
Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

Open in Telegram

Addis Ababa, Ethiopia Con-Site is a Comprehensive Construction Filed Works and Materials Reference Catalogue for Architects, Engineers, Consultants and Customer service. t.me/ConsitesolutionBot ☜|]Comments Construction Solution Official Service

Show more
3 584
Subscribers
No data24 hours
-57 days
+5330 days
Posts Archive
የኤሌክትሪክ አገልግሎት በኪሎ ዋት እስከ 95 ብር ገባ ከመስከረም ወር ጀምሮ በመጪዎቹ 3 ወራት የኤሌክትሪክ አገልግሎት በኪሎ ዋት እስከ 95 ብር ድረስ ጭማሪ ሊደረግበት ነው
የኤሌክትሪክ አገልግሎት በኪሎ ዋት እስከ 95 ብር ገባ
ከመስከረም ወር ጀምሮ በመጪዎቹ 3 ወራት የኤሌክትሪክ አገልግሎት በኪሎ ዋት እስከ 95 ብር ድረስ ጭማሪ ሊደረግበት ነው

ይህ የምታዩት መንገድ በቁጥር 1 የኮሪደር ልማት የተገነባ ነው። 🔹የሚገኘው 4 ኪሎ ከመንግሥት ኮምኒኬሽን ፅ/ቤት ወደፒያሳ መስመር በግምት 800 ሜትር ርቀት ላይ ነው። ከተመረቀ ገና ሁለት ወር ስ
+1
ይህ የምታዩት መንገድ በቁጥር 1 የኮሪደር ልማት የተገነባ ነው። 🔹የሚገኘው 4 ኪሎ ከመንግሥት ኮምኒኬሽን ፅ/ቤት ወደፒያሳ መስመር በግምት 800 ሜትር ርቀት ላይ ነው። ከተመረቀ ገና ሁለት ወር ስለመሙላቱም እርግጠኛ አይደለሁም። ግን የህዝብ ገንዘብ ወጥቶበት ሳያገለግል ከጥቅም ውጪ ሆኗል። በጋዜጠኛ ፍሬው አበበ

🔺የ ኮንስትራክሽን ውሎችን ለሌላ መልቀቅ (Assignment) ምን ማለት ነው? ውሎችን ለሌላ መልቀቅ (Assignment) ዋናው ተቋራጭ የግንባታ ውሉን ስራ በሙሉ እንዲፈጽምለት ለአንድ ሶስተኛ ወገ
🔺የ ኮንስትራክሽን ውሎችን ለሌላ መልቀቅ (Assignment) ምን ማለት ነው?
ውሎችን ለሌላ መልቀቅ (Assignment) ዋናው ተቋራጭ የግንባታ ውሉን ስራ በሙሉ እንዲፈጽምለት ለአንድ ሶስተኛ ወገን ለሆነ ሲያስተላልፍ ነው፡፡ (የፍ/ህ/ቁ 3201(1) ይሄውም ከንኡስ ተቋራጭነት ጋር ሁኔታው አንድ አይነት ሲሆን በዋናነት ልዩነቱ ዋናው ተቋራጭ ለሌላ ተቋራጭ(ለንኡስ ተቋራጩ) የሚያሰራው ሙሉውን የግንባታ ስራ ነው፡፡ 🚧በዚህ ውል ውስጥ ሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች ተቋራጮች ናቸው፡፡ ❤ለምሳሌ "ሀ" የተባለ ተቋራጭ "ለ" ከተባለ አሰሪ ጋር የኮንስትራክሽን ውል ገባ እንበል የግንባታ ስራው ደግሞ ትምህርት ቤት ቢሆን እና ሁለት ብሎክ መማሪያ ህንጻ እና አንድ ሽንት ቤት ግንባታ ቢሆን እንበል፡፡ 💫እንግዲህ ዋናው ተቋራጭ "ሀ" ከግንባታ ስራው ውስጥ አንዱን ብሎክ መማሪያ ክፍል "ሐ" ለተባለ ተቋራጭ በውል ሰጥቶ ቢያስገነባው በ "ሀ" እና "ሐ" መካከል የሚደረገው ውል የንኡስ ተቋራጭነት ውል ይባላል ማለት ነው፡፡ 💫በሌላ በኩል ምናልባት ዋናው ተቋራጭ "ሀ" ሁሉንም ግንባታ ማለትም ሁለት ብሎክ መማሪያ ህንጻ እና አንድ ሽንት ቤት "መ" ለተባለ ተቋራጭ በውል ሰጥቶ ቢያስገነባው በዋናው ተቋራጭ "ሀ" እና "መ" በተባለው ተቋራጭ መካከል የተደረገው ውል በንኡስ ተቋራጭነት ሳይሆን ውሎችን ለሌላ መልቀቅ (Assignment) በሚለው የህግ ክፍል የሚጠቃለል ይሆናል ማለት ነወ፡፡ ጀኔራል ኮንዲሽኖች ንኡስ ተቋራጭነትን በምን ሁኔታ ያስቀምጡታል? 🚧ፒፒኤ 2011 ስለ ንኡስ ተቋራጭነት አስመልክቶ በክሎስ 14 ላይ አስቀምጧል፡፡ 💫በዚህም የንኡስ ተቋራጭነት ውሉ በጽሁፍ መሆን እንዳለበት እና ይሄውም የቫሊዲቲ መስፈርት ስለመሆኑ ይገልጻል፡፡ 💫ንኡስ ተቋራጮች በዋናው የኮንስትራክሽን ውል ላይ ያልታወቁ ( Non nominated) የሆኑ እንደሆነ ዋናው ተቋራጭ ሌሎች ንኡስ ተቋራጮችን የግንባታ ስራ ለማሰራት የአሰሪውን የጽሁፍ ፈቃድ ማግኘት ይኖርበታል በሚል ያስቀምጣል፡፡ 💫የንኡስ ተቋራጭነት ውሉም ከዋናው ውል ጋር የተጣጣመ እና በዋናው ውል ጭምር የሚገዛ እንደሚሆን ክሎስ 14.3 ላይ ተቀምጧል፡፡ 💫ዋናው ተቋራጭ የአሰሪው መስሪያ ቤት ሳይፈቅድለት የንኡስ ተቋራጭነት ውል የገባ እንደሆነ አሰሪው ፎርማል ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልገው ውልን ማቋረጥ እንደሚችል ክሎስ 14.8 ያስቀምጣል፡፡ 💫ሌላው ንኡስ ተቋራጩ የግንባታ ስራ ለማከናወን ብቃት የሚያንሰው እንደሆነ አሰሪው መስሪያ ቤት ወይም መሀንዲሱ ዋናውን ተቋራጭ ሌላ ብቃት ያለው ንኡስ ተቋራጭ እንዲያመጣ ወይም ስራውን በራሱ እንዲያከናውን ሊጠይቀው እንደሚችል ክሎስ 14.9 ይገልጻል፡፡ 🚧ፊዲክ ሬድ ቡክ 1999-በዚህ ጀኔራል ኮንዲሽን ክሎስ 4.4 ላይ ዋናው ተቋራጭ ሙሉውን የግንባታ ስራ ለንኡስ ተቋራጭ መስጠት እንደማይችል ተቀምጧል፡፡ 💫እንዲሁም በስፔሻል ኮንዲሽን ላይ በሌላ ሁኔታ ካልተቀመጠ በስተቀር ንኡስ ተቋራጩ በዋናው የኮንስትራክሽን ውል ላይ ስሙ የተጠቀሰ በሆነ ጊዜ በንኡስ ተቋራጭነት ለማሰራት የመሀንዲሱን ፈቃድ መጠየቅ አይጠበቅበትም፡፡ 💫ሆኖም የታሰበው ንኡስ ተቋራጭ አዲስ እና በዋናው ውል ስሙ ያልተጠቀሰ የሆነ እንደሆነ በቅድሚያ የመሀንዲሱን ፈቃድ ማግኘት አስፈላጊ ይሆናል፡፡ 💫ዋናው ተቋራጭ ለመሀንዲሱ በተለይ ንኡስ ተቋራጩ የሚሰራውን የግንባታ ስራ መጀመሪያ ቀን/ኮመንስመንት ዴት/ ተብሎ የታሰበውን ጊዜ ከ28 ቀን ባላነሰ ጊዜ ማስታወቅ ሲኖርበት ንኡስ ተቋራጩ በትክክል በሳይት ላይ ስራ የጀመረበትንም ቀን ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ 💫Nominated subcontractors በሚመለከት በክሎስ 5.1 ላይ ትርጉም ተሰጥቶታል፡፡ በዚህም መሰረት ኖምኔትድ ሰብ ኮንትራክተር የሚባለው በዋናው የኮንስትራክሽን ውል ላይ ኖምኔትድ ሰብ ኮንትራክተር መሆኑ የተገለጸ እንደሆነ ወይም ኢንጅኒየሩ ለተቋራጩ ንኡስ ተቋራጭ መርጦለት እንዲያሰራው ያዘዘው የሆነ እንደሆነ ነው፡፡ ለኖምኔትድ ሰብ ኮንትራክተሩ ክፍያ የሚፈጸምለት በንኡስ ተቋራጭነት ውሉ አግባብ በመሀንዲሱ በሚሰጥ የክፍያ ሰርተፍኬት መሰረት ሲሆን ክፍያውን የሚፈጽመውም ዋናው ተቋራጭ ስለመሆኑ ክሎስ 5.3 ላይ ተቀምጧል፡፡

RC-PIPE (ኮንክሪት ቱቦ) ባለ 100 ሚ.ሜ ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

የመስከረም_ወር_2017_ዓ_ም_የሀራጅ_ሽያጭ_ማስታወቂያ.PDF3.25 MB

"ካዛንችስ እና አዋሬ ውስጥ ከህንፃዎች ቤቶች እና አንዳንድ በደንብ ከተያዙ መኖርያ ቤቶች በቀር ሁሉም ፈራሽ ናቸው" በቅርብ ቀናት ካዛንችስ ከስድስተኛ ፖሊስ ጣብያ ጀርባ ያለው አካባቢ ሙሉ በሙሉ ሊ
"ካዛንችስ እና አዋሬ ውስጥ ከህንፃዎች ቤቶች እና አንዳንድ በደንብ ከተያዙ መኖርያ ቤቶች በቀር ሁሉም ፈራሽ ናቸው" በቅርብ ቀናት ካዛንችስ ከስድስተኛ ፖሊስ ጣብያ ጀርባ ያለው አካባቢ ሙሉ በሙሉ ሊፈርስ ታስቧል። Via~መሠረት ሚዲያ

እባካችሁ ለሴፍቲ ትኩረት እንስጥ 🥶🥶

እባካችሁ ለሴፍቲ ትኩረት እንስጥ 🥶🥶

☀️ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺሕ 499ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
☀️ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺሕ 499ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

💠ቁ.04 መልስ:-
= 600 ÷ (0.4 * 0.2) = 7500 ብሎኬት ብዛት ያስፈልጋል አለጁንታ እነዚህ ባለ 20 ብሎኬቶች ለውጫዊው ግድግዳ ግንባታችን ጥቅም ላይ ይውላሉ

🔺የ ኮንስትራክሽን ውሎችን ለሌላ መልቀቅ (Assignment) ምን ማለት ነው? ሀሳባችሁን አድርሱን የቴሌግራም/መልዕክት መስጫ ቦት ተጠቀሙ! t.me/unitysupplydbot • ••☜|] ❤ምላሽ እ
🔺የ ኮንስትራክሽን ውሎችን ለሌላ መልቀቅ (Assignment) ምን ማለት ነው?
ሀሳባችሁን አድርሱን የቴሌግራም/መልዕክት መስጫ ቦት ተጠቀሙ!
t.me/unitysupplydbot • ••☜|] ❤ምላሽ እንሰጣለን!
የቴሌግራም ቻናል ድህረ-ገፃችን ላይ ጠቃሚና ወቅታዊ የስራ መረጃዎችን ስለምንለቅ ቻናሉን join አድርጉት👇
http://t.me/con_site_solution ❤🚧🏗
ለሌሎችም ተያያዥ ስራ ላላቸው ባልደረቦቻችሁ አጋሩ!

🔺ጥያቄ? ጉርሻ🚧 600ካሬ ሜትር × 2 ሜትር ግድግዳ ለመገንባት ስንት ባለ20 hollow blocks ያስፈልጋል?? @consite
Anonymous voting

🔺አብዛኛዎቻችን ቤት ውስጥ የኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች ገጠማ ፣ ሶኬቶች፣ሲዊቾች፣ ውበት ዲዛይኑ፣ አጠቃቀማችን በምን መልኩ ነው? ከመሬት ወይም ከወለል ያላቸው ከፍታ ምን ያህል ቢሆን ይመረጣል?? በኮ
+1
🔺አብዛኛዎቻችን ቤት ውስጥ የኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች ገጠማ ፣ ሶኬቶች፣ሲዊቾች፣ ውበት ዲዛይኑ፣ አጠቃቀማችን በምን መልኩ ነው? ከመሬት ወይም ከወለል ያላቸው ከፍታ ምን ያህል ቢሆን ይመረጣል?? በኮንስትረክሽን ህንፃ ግንባታ ውስጥ ስለየኤሌክትሪክ አክሰሰሪዎች ገጠማ የተቀመጠ ድንጋጌ ምን ይላል??? ማታ ይጠብቁን እናየዋለን.. .)
የቴሌግራም ቻናል ድህረ-ገፃችን ላይ ጠቃሚና ወቅታዊ የስራ መረጃዎችን ስለምንለቅ ቻናሉን join አድርጉት👇
http://t.me/con_site_solution 👈❤🚧🏗
ለሌሎችም ተያያዥ ስራ ላላቸው ባልደረቦቻችሁ አጋሩ! ሃሳባችሁን ልታደረሱን ከፈለጋችሁ የቴሌግራም/መልዕክት መስጫችን ቦት
t.me/unitysupplydbot 🔺☜|] ❤ይጠቀሙ! ምላሽ እንሰጣለን
ሰናይ ጊዜ!🤚

አንድ የስራ ተቆጣጣሪ ባለሞያ የኮለን ኮንክሪት ከመሞላቱ በፊት ፎርምወርክ ስራው ላይ መሟላታቸውን ማረጋገጥ የሚገባው መሰረታዊ ነጥቦች:- 🏗
[Elements of good Column formwork finish] 1.ጥብቅ መሆኑን/Formwork rigidity/ ⚡️የተዘጋጀው ፎርምወርክ የራሱን ክብደት/self weight/፣የብረቱን ክብደት፣የርጥብ ኮንክሪቱን ክብደት፣ የኮንክሪት ሰራተኞች፣ የንፋስ ግፊት፣ የስራ መሳሪያዎችና ሌሎች ሊያጋጥሙ የሚችሉ ጫናዎችን የሚቋቋም ሆኖ በቂ ጥንካሬ ኖሮት መሰራቱን ማረጋገጥ የመጀመሪያ ስራ ይሆናል። 2.የፎርምወርክ ጥራት/Quality of formwork material/ ⚡️ለፎርምወርክ ስራ ጥቅም ላይ የዋለው እቃ ያልተጣመመ፣ ያላበጠና ያልጎበጠ ፣ወጥነት ያለው ፣ያልተቀደደና ጥሩ ጥንካሬና የመሸከም አቅም ያለው መሆኑን ማረጋገጥ ሌላ አስፈላጊ ስራ ነው። 3.አቀባዊ ሊኛ/Vertical alignment/ ⚡️የተዘጋጀው ኮለን ፎርምወርክ ዲዛይኑ እንደሚጠይቀው ልክ በሚገባ ወደላይ ቀጥ ማለቱን ማረጋገጥ አለበት። 4.አግድም ሊኛ/Horizontal alignment/ ⚡️የተዘጋጀው ኮለን ፎርምወርክ ዲዛይኑ እንደሚጠይቀው ከሌሎች ኮለኖች አንጻር ያለው አቀማመጥ፣ ከታወቀ መነሻ በሚገባ ወጥነት ያለው ሆኖ መቀመጡን ማረጋገጥ አለበት። 5.የኮለን ወርድና ስፋት ልክ/Design dimension/ ⚡️በዲዛይኑ መሰረት የኮለኑን ወርድና ስፋት ከፎርምወርኩ አቀናንሶ ትክክል መሆኑን ማረጋገጥ። 6.ከመነሻው ያለው ርቀት/Distance from reference/center to center/ ⚡️ከታወቀ መነሻ በመነሳት አንዱ ኮለን ከሌላው ኮለን ርቆ የተቀመጠው በዲዛይኑ መሰረት መሆኑን ማረጋገጥ። 7.መሃል ገጠምነት/Eccentricity/ ⚡️ተንጠልጣይ ወለል/Suspended floors/ በሚኖራቸው ግንባታዎች ላይ የላይኛው ወለል ኮለን ከታችኛው ወለል ኮለን ጋር ሴንተራቸው ፍፁም መሃል ገጠም/eccentric/ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው። 8.ከብረቱ ያለው ተገቢ ርቀት /Concrete cover/ ⚡️ለኮንክሪት ሽፋን ዲዛይኑ የሚጠይቀው ተገቢ መጠን፣ በፎርምወርኩና በብረቱ መሃል በልዩ ጡብ/Spacers/ መለየቱን ማረጋገጥ ሌላው በጣም አስፈላጊው ነጥብ ነው።