cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ነአምን media

<< ነአምን በአሐዱ አምላክ እግዚአበሔር!>> ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ #ትምህርቶች #ዝማሬዎችና #ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ስነ-ፅሁፎች የሚለቀቁበት ቻናል ነው። ለሁሉም መረጃና አስተያየትና በቻናሉ ላይ ለመፃፍና ለመሳተፍ @theofloss ያናግሩን መረጃውንም ያካፍሉን።

Show more
Advertising posts
267
Subscribers
No data24 hours
-27 days
-1430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

(በፍጹም ምግባርና በፍጹም ሃይማኖት በውስጥና በውጪ ያጌጠች ለኾነች ለአርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ ወደ ኋላ ባለመመለስ ሰማዕትን በኾነች ጊዜ ዐለንጎች (መግረፊያዎች) ሥጋዋን ማሳመም አልቻሉም፤ ነጣቂዎች አናብስትም የእግሯን ዐቧራ ላሱ) ይላል። 💥እኔም ከበረከቷ ለመሳተፍ ይህንን ጻፍኩ። እናንተም ከበረከቷ ትሳተፉ ዘንድ በአስተያየት መስጫው ላይ ደስ ያላችሁን ሰላምታና ውዳሴ አቅርቡላት። ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ +++ join & share +++ 👇👇👇👇👇👇👇👇 @neamn_media @neamn_media @neamn_media
Show all...
#እንኳን_አደረሳችሁ_አደረሰን መስከረም 29 በክርስቶስ ስም አንገቷን ለሰይፍ የሰጠችው፤ ታኅሣሥ 6 ቅዳሴ ቤቷ የኾነው የቅድስት አርሴማ ተጋድሎ በቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ❖ ❖✔💥 ስለ ቅድስት አርሴማ ተጋድሎ ቀደምት ሊቃውንት መስክረዋል፤ ሥዕሏን ሥለዋል፤ መልክእ ደርሰውላታል፤ የዚኽች ቅድስት ሰማዕት አባቷ ቴዎድሮስ እናቷ አትኖስያና ይባላሉ፤ በብፅዐት ያገኟት ልጅ በመኾናቸው በተወለደች በሦስት ዓመቷ በእመቤታችን ስም በታነጸች ቤተ ክርስቲያን አድጋለች። 💥 እጅግ መልከ መልካም ነበረች። ቅዱስ ጳውሎስ “ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ፤ የተጋባች ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንድታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች።” (1ኛ ቆሮንቶስ 7፥34) ያለውን አስባ ራሷንም በድንግልና ሕይወት ለክርስቶስ ለይታ ነበር። ከ284- 305 በሮም የነገሠው ከሓዲው ድዮቅልጥያኖስ መልኳ ውብ የኾነች ድንግል ሊያገባ ፈልጎ ቆንጆ መርጠው ያመጡለት ዘንድ አገልጋዮቹን አዘዛቸው፡፡ ❖✔💥 እነርሱም በፍለጋቸው በሮሜ አገር ባለች ቤተ ክርስቲያን ቅድስት አርሴማን በማግኘት ሥዕሏን ሥለው ለንጉሡ ላኩለት፡፡ ርሱም በእጅጉ ተደስቶ እንዲያመጧት በማዘዝ ወደ ሰርጉም እንዲመጡ ለመኳንንቱ ላከ፡፡ ❖✔💥 ርሷና ዐብረዋት የነበሩትም ደናግል ይኽነን በሰሙ ጊዜ በማዘን ጌታችን በወንጌል “በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ” (ማቴዎስ 10፥23) ያለውን አስበው ድንግልናቸውን ይጠብቅላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በመለመን ከሮም ተነሥተው በስዉር የንጉሥ ድርጣድስ ግዛት ወደነበረችው ወደ አርመን ሸሽተው ኼደዋል፡፡ 💥 ቅድስት አርሴማም ወደ አርመንያ ሀገር በገባች ጊዜ ከሓድያኑ በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነትን የሚያምኑትን ክርስቲያኖችን ላይ መከራን ሲያጸኑባቸው ተመለከተችና አምላካችን ክርስቶስ "ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።" (ማቴ 10:32-33) ያለውን በማሰብ “እኔ በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነትን የማምን ክርስቲያን ነኝ” በማለት መሰከረች፡፡ ❖✔💥 የመልኳን ደም ግባትም በማየት ንጉሥ ድርጣድስም ለራሱ ስለተመኛት አምልኮቷን እንድትተው፣ ክርስቶስን እንድትክድ በብዙ ሽንገላን ሊሸነግሏት ቢሞክሩም አልኾነላቸውም፤ ከዚያም ፈርታ ትክዳለች ብለው በማሰብ ክርስቲያኖች ለአናብስት ወደሚጣሉበት አደባባይ በመውሰድ የተራቡ አናብስትን ሲለቅቋቸው ነቢዩ ዳንኤል እንዳደረገው በጸሎቷ ኀይል አናብስቱ ወደ ንጉሡ ወታደሮች በመወርወር ብዙዎችን ገድለዋል፤ ከዚያም ከሥሯ ተንበርክከው ሰግደውላታል፡፡ ❖✔💥 ንጉሡ በዚኽ ባይኾንለት በግድ ለጣዖታቱ እንድትሰግድ አሳስሮ አማልክቱ ወዳሉበት ቤተ ጣዖት ሲወስዳት፤ በመስቀል ምልክት ብታማትብ በጣዖታቱ ላይ ዐድረው ሰዎችን የሚያስቱ አጋንንት እየጮኹ ሲወጡ ጣዖታቱ በመላ እየተሰባበሩ ወድቀዋል፤ ከዚያም በረኀብ ለመቅጣት ወደ እስር ቤት ቢያኖሯት መልአኩ ኅብስትን እንደ ኤልያስ መግቧታል፡፡ ❖✔💥 ከዚያም ንጉሡ ወዳለበት እየጐተቱ ወሰዷት፤ “ወተንሥአ ንጉሥ እማዕከለ ዐውድ ወአኀዛ ከመ ያብኣ ውስተ ጽርሑ ለአርሴማ ድንግል ወሶቤሃ ኀደረ ኀይለ እግዚአብሔር ላዕለ አርሴማ ቅድስት ወገደፈቶ ውስተ ምድር” ይላል፤ ንጉሡ ይዞ ወደ እልፍኙ ሊያስገባት ከአደባባይ ተነሥቶ ድንግል አርሴማን በያዛት ጊዜ፤ ዳዊት ጎልያድን በእግዚአብሔር ኃይል እንዳሸነፈ ቅድስት አርሴማም እላይዋ ላይ ባደረው የእግዚአብሔር ኀይል በምድር ላይ ጣለችው፤ ያን ጊዜ በዐፍረት ኾኖ ራሷ ይቈረጥ ዘንድ አዘዘ። 💥 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ ላይ "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።" (ሮሜ 8:35-36) እንዳለ ያደረሱባት መከራ ሁሉ ከክርስቶስ ፍቅር ሊለያት አልቻለም። 💥 ከዚያም የክብር ባለቤት ጌታችን እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምን አስከትሎ ተገለጸላት። በቅዱስ መጽሐፍ ላይ “አንተም አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ፥ ለሚወድዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆነ እወቅ፤” (ዘዳግም 7፥9) እንደሚል ስሟን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ምሕረትን እንደሚያደርግ ቃል ኪዳንን ከገባላት በኋላ መስከረም 29 በ290 ዓ.ም. አንገቷን ተቈርጣ የሰማዕታትን አክሊል ተቀዳጅታለች። 💥 አስቀድሞ በኢሳይያስ ዐድሮ "እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና፦ በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።" (ኢሳ 56:4-5) ብሎ እንደተናገረ በስሟም ቤተ ክርስቲያን ታንጾ ታኅሣሥ 6 ቅዳሴ ቤቷ ሲከበር፤ የከበረ ሰውነቷ ዛሬ ድረስ በአርመን አለ፡፡ ❖✔💥 በኢትዮጵያና በመላው ዓለም ብዙ አብያተ ክርስቲያናት በስሟ እየታነጹ ከክርስቶስ አምላኳ በተቀበለችው አማናዊ ቃል ኪዳንም ብዙ ሕሙማን እየተፈወሱ በረከቷን እያገኘን እንገኛለን፡፡ ታቦቷ ካለባቸው እጅግ ብዙ በረከት ካላቸው የሰማዕቷን ገድል ከተረጎምኩባቸው ቦታዎች መኻከል በደቡብ አፍሪካ በረስተንበርግ፤ በዱባይ እና በአውሮፓ ስኮትላንድ ግላስኮ፤ በሰሜን አሜሪካ ቨርጂንያ መካነ ሰማዕት የቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ይገኛሉ፨ ❖✔💥 ካመሰገኗት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀደምት ሊቃውንት ውስጥ ሊቁ አርከ ሥሉስ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የሚጠቀሱ ሲኾኑ፦ ❖✔💥 ሊቁ አርከ ሥሉስም ይኽነን የቅድስት አርሴማ ተጋድሎ ሲመሰክር፡- ✍️ “በጾታ ኅሩያን ዕደው እንዘ ተኀብሪ ጾታ እንበለ ትፍርሂ ምንተ ብልኀተ ኲያንው ወሰይፍ ልሳነ መንታ ዘፈጸምኪ ስምዐ በእንተ ኢየሱስ ንጉሠ ኤፍራታ ሰላም ለኪ አርሴማ ምስለ እምኪ አጋታ ወለደናግል ሰላም ምስሌኪ ዘሞታ” (በተመረጡ ወንዶች ወገንነት ተባብረሽ ኹለት አፍ ያለው ሰይፍንና የጦሮችን ስለትን ምንም ሳትፈሪ የኤፍራታ ንጉሥ ስለሚኾን ስለ ኢየሱስ ምስክርነት የፈጸምሽ አርሴማ ከእናትሽ ከአጋታ ጋር ሰላምታ ላንቺ ይገባል፤ ካንቺ ጋር የሞቱ ለኾኑ ደናግል ሰላምታ ይገባል) በማለት በኅብረት አመስግኗቸዋል፡፡ ❖✔💥 ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን ታላቅ መጽሐፉ ላይ፦ ✍️“ሰላም ለአርሴማ ቅድስት ከመ በቀልት ዘይመስል ቆማ ወዘከለላ ዘመንፈስ ግርማ ዘፈጸመት ገድላ በጻማ ወበመንግሥተ ሰማይ ዐቢይ ስማ”፡፡ (ገድሏን በሥቃይ የፈጸመች፤ የመንፈስ ግርማ የጋረዳትና ቊመቷ እንደ ዘንባባ የሚመስል ለምትኾን ለቅድስት አርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ በመንግሥተ ሰማይም ስሟ ታላቅ ነው) በማለት ያወድሳታል፨ ❖✔💥 እኔም በዚኽ ጽሑፌ ላይ ሊቁ አርከ ሥሉስ ለቅድስት ጣጡስ ሰማዕት በሰጣት ምስጋና ለሰማዕቷ አርሴማ በመስጠት አመስግኜያት ጽሑፌን አበቃለሁ፨ ❖✔💥 “ሰላም ለአርሴማ ሥርጉተ አፍኣ ወውስጥ በምግባር ፍጹም ወበሃይማኖት ስሉጥ አመ ኮነት ሰማዕተ እንበለ ተምያጥ አሕምሞ ሥጋሃ ኢክህሉ አስዋጥ ወጸበለ እግራ ለሐሱ አናብስት መሠጥ”
Show all...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! 🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷 🌹🌷🌹🌷🌹 እንኳን ለዘመነ ጽጌ በሰላም አደረሳችሁ። በኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተክርስቲያን በዕለቱ የሚቀርበውን እጅግ ጥልቅ ምስጢር የያዘውን የመጀመሪያው ሳምንት የጽጌ ማኅሌትን በአንድ ልብ በአንድ ቃል ለማመስገን ይረዳን ዘንድ ይህ ስርዓተ ማኅሌት በነአምን media እንደሚከተለው ቀርቧል። 🌸 እንኳን አደረሳችሁ🌸 +++ join & share+++ 👇👇👇👇👇👇 @neamn_media @neamn_media @neamn_media
Show all...
+++ join and share +++ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @neamn_media @neamn_media @neamn_media
Show all...
👍 1
- የ“at least” ክርስትና - | ጃንደረባው ሚዲያ - መስከረም 2016 ዓ.ም | ✍🏽 ቀሲስ ታምራት ውቤ እንደጻፉት (በእውነታ ላይ የተመሠረተ ምናባዊ ጽሑፍ) በቅርብ በቅዱስ ጋብቻ አንድ ከሆኑ ጥንዶች ጋር ስለ ክርስትና ሕይወታቸው አባታችንን ለማወያየት ፈልገው በቤታቸው ተገናኘን፡፡ በውይይታችን ከተነሡት በርካታ ጉዳዮች የዘመኑን የክርስትና ሕይወት አጉልቶ የሚያሳዩ ሁለት ነጥቦችን እነሆ፡- የመጀመሪያው ከእንግዶቹ የተነሣው ሐሳብ “ከአንዳንድ ወንድምና እኅቶች ጋር ስለ መንፈሳዊ ሕይወት ስንመካከር በክርስትና ሕይወት ስንኖር ‘at least’ እነዚህ የመሰሉ ነገሮችን ልንፈጽም እንደሚገባ ነግረውናል፡፡ እርስዎስ ምን ይመክሩናል?” በማለት አባታችንን በጠየቋቸው ጥያቄ ውይይታችንን ጀመርን፡፡ አባታችን በተቀመጡበት ትንሽ በዝምታ ከቆዩ በኋላ እንዲህ ሲሉ ጀመሩ፡፡ “የጌታ እግዚአብሔር ፈቃዱ የተገለጠባቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት በኅሊናዬ ለመዳሰስ ሞከርኩ፡፡ እናም ላገኘው ያልቻልኩት ነገር ቢኖር ‘ቢያንስ (at least)’ በሚል ቀዳሚ ቅጽል የተቀመጠን ትእዛዝ ነው፡፡ መንግሥተ እግዚአብሔርን ለመውረስ የተቀመጠ ‘አነስተኛ መሥፈርት (minimum requirement)’ ምን እንደሆነ ማወቅ ብችል ብዬ አሁንም ለማሰብ ሞከርኩ፤ ግን አሁንም መልስ ማግኘት አልቻልኩም፡፡” አሉን ትክዝ ባለ ድምፅ፡፡ ሙሉውን ያንብቡ
Show all...
✝✝✝ እሱን አንተ አስብበት ✝✝✝ በድሮ ጊዜ ነው አንድ በእድሜ የገረጀፈ አሞራ ሌጁን ይጠራና ምክር ቢጤ የአባትነቱን ይለግሰዋል :- ልጄ ይህን የምመክርህ ምክር በልብህ አኑረው በመሬትና በዛፍ ላይ አርፈህ ሳለህ ማንኛውም ሰው ወደመሬት ጎንበስ ሲል ካየህ መብረር እንዳለብህ እወቅ ምክንያቱም ጎንበስ ያለው ድንጋይ አንስቶ አንተን ሊመታ ነው>> አለው። ልጅም ምክሩን ሲሰማ ቆይቶ ጥያቄ ጠየቀ :- << እሺ አባዬ ግን እኮ አስቀድሞ ድንጋይ በብብቱ ወይም በኪሱ ይዞ ጎንበስ ሳይል ቢመታኝስ?>> << አይ ልጄ እኔ የራሴን ዘመን መከርኩህ እሱንማ አንተው አስብበት በኔ ዘመን እንዲህ አይነት ክፋት የለም ነበር >> አለው። *** ወዳጄ! ቤተክርስቲያናችን ጥንታዊት፣ ታሪካዊት፣ ብሔራዊትና አማናዊት ናት። በዚች ቤተክርስቲያን ስንነኖር የተማርነውና የምንማረው ከንፁህ ምንጭ የተቀዳ ቃለ እግዚአብሔር እንደክፍለዘመኑ ሥልታቸውን እየቀያየሩ ከሚያስቱ መናፍቃን ለመጠበቅ የአባቶቻችንን ጥበብ ከእኛ ዘምንጋ በማዋሐድ መትጋት አለብን። በቅዱስ መጽሐፋችን << ዘመኑን ዋጁ >> ተብሎ ተጽፏልና! +++ join & share +++ 👇👇👇👇👇👇👇👇 @neamn_media @neamn_media @neamn_media
Show all...
እንግዲህ ንግስት ሄሌና ምንም እንኳ ቀደም ሲል ከፍ ያለ ክርስቲያናዊ መንፈስ የነበራት ቢሆንም በነዚህ ሁኔታዎች ነው በልጇ ላይ አምላኳ ያደረገውን ከፍ ያለ ክብርና በረከት ያደነቀችው፡፡ በዚህም በክርስትና ዕምነት የተመሰጠችው ንግስት ሄሌና ኢየሩሳሌምን ለመጎብኘት ተጓዘች፡፡ በዚያም ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል አስቆፍራ በማውጣት (በጎልጎታ) ዕውነተኛውን መስቀል በሰራው ተአምራት፣ ሁለቱ ወንጀለኞች ከተሰቀሉባቸው መስቀሎች በመለየት (ታሪኩን በየአመቱ የምንሰማው ነው) የክርስትና ምልክት የሆነውን መስቀል ለአለም ክርስቲያኖች ያበረከተቸው፡፡ በዚህም ሳታበቃ መስቀሉን ባገኘችበት ጎልጎታና በሌሎቹ የተቀደሱ ቦታዎች ላይ ቤተጣኦቶችን አፈራርሳ ቤተክርስቲያን ለማሳነጽ የበቃች፤ በዚህም የቅድስና ክብር የተሰጣት ናት፡፡ ለዚህ ስራዋም በተከታዮቿ ዘንድ የውዳሴ መዝሙር ለእሷና ለልጇ ታላቁ ቆስጠንጢኖስ ተደርሶላቸዋል፡፡ አጭሩን የምስጋና ግጥም እንደሚከተለው ተርጉሜዋለሁ! “ቆስጠንጢኖስ ንጉስ ሄሌና እናቲቱ፤ የኢየሱስን መስቀል ሞት የሞተበቱ፤ የአማኞች መሳሪያ የጠላት ሰቀቀን፤ በፈጣሪ ፈቃድ ይኼው አገኙልን፤ በፍቅር ተገልጦ ጦሩን የሰበቀ፤ በጠላት ሜዳ ላይ ፍርሃት የለቀቀ፡፡” የሚል ድንቅ ውዳሴ! በመሰረቱ በንግስት/ቅድስት ሄሌና ታሪክ ላይ የተለያዩ ሃሳቦች ይነሳሉ፡፡ በትውልድ ቀኗ፣ በኅልፈቷ፣ በወላጆቿ፣ በትውልድ ቦታዋ ወዘተ. ላይ ከፍ ያሉ ክርክሮች አሉ፡፡ +++join & share+++ 👇👇👇👇👇👇👇👇 @neamn_media @neamn_media @neamn_media
Show all...
+++ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሠላም አደረሳችሁ +++ የመስቀል በዓል በሀገራችን የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ መከበር ከጀመረ ከ1600 ዓመት በላይ ሆኖታል፡፡ ቃሉ ነጠላና ጥምር ሲሆን የተለያዩ ትርጉሞች አሉት፡፡ ለምሳሌ ነጠላ ፍችውን ብንመለከት- የአማርኛ መዝገበ ቃላት፣ ከሳቴ ብርሃን ተሰማ 1951 ዓ.ም ላይ “የክርስቶስ መስቀል በሁለት ረዣዥም እንጨት እጅና እግሩ የተከነቸረበት ከራሱ እስከ እግሩ ወራጅ ግንድ ከቀኝ እጁ ወደ ግራ እጁ ከአግዳሚውም ግንድ በአራት ማዕዘን ተመሳቅሎ የሚታየው መስቀለኛ ዕንጨት” በማለት ሲፈታው፣ አማርኛ መዝገበ ቃላት የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል፣ 2001 ዓ.ም ደግሞ 1. “መስቀል- ቀጥ ባለ እንጨት አናት አካባቢ ሌላ አጠር ያለ እንጨት በማጋደምና ሁለቱን በማያያዝ የሚዘጋጅ በጥንት እስራኤላዊያንና ሮማውያን ጊዜ ወንጀለኞችን አሰቃይቶ ለመግደል ያገለግል የነበረ የሰው መስቀያ፤ 2 “… ከብረት ከእንጨት …የሚዘጋጅ፣ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል፣ ምሳሌ የክርስትና እምነት ተከታዮች ምልክት፣ 3. የክርስቶስ መስቀል ከተቀበረበት ቦታ መገኘቱን ምክንያት በማድረግ መስከረም 17 ቀን የሚከበር በዓል” በማለት ሶስት ትርጎሞች ይሰጠዋል፡፡ ቃሉ ከሌላ ቃል ጋር ተጣምሮ ሲመጣ ደግሞ ህማማተ-መስቀል “የክርስቶስ ልዩ ልዩ መከራው በጥፊ መመታቱ፣ መታሰሩ፣ መገረፉ፣ ግንድ መሸከሙ፣ ራቁቱን መሰቀሉ፣ አክሊለ ሶክ በራሱ ላይ መቀዳጀቱ ይኸንን የመሳሰለ ልዩ ልዩ መከራው …” ቀራንዮ መስቀል- “በቀራንዮ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዋነኛው የቀራንዮ መስቀል”፤ ዕርፈ መስቀል – “ማንካ፣ ቀሳውስት ለሚቆርቡ ምዕመናን ደሙን የሚያቀብሉበት ማንካ፣ በቤተ ክርስቲያን የሚኖር …” በሚል በከሳቴ ብርሃን መዝገበ ቃላት ላይ የተፈቱ ሲሆን “የመስቀል ወፍ፣ የመስቀል አበባ” ወዘተ. የሚሉም አሉ፡፡ ለመግቢያ ያክል ይህን ካልን በቅድመ ክርስቶስ መስቀል ምን ትርጉም እንደነበረው በአጭሩ ተመልክተን ወደተነሳንበት ርዕሰ ጉዳይ አልፋለሁ፡፡ በቅድመ ክርስቶስ ዘመን የመስቀል ትዕምርትነት የቅጣት፣ የወንጀለኞች መቅጫና የመግደያ መሳሪያ ነበር፡፡ በግሪኮችና በሮማውያን ዘመን በሺ የሚቆጠሩ ወንጀለኞችና እስረኞች በመስቀል ላይ ተሰቅለው ተገድለዋል፡፡ ለምሳሌ ታላቁ አሌክሳንደር ከትሮይ ከተማ ውድቀት በኋላ ሁለት ሺ የሚሆኑ ትሮኒያውያንን በዚሁ መንገድ እንዲገደሉ እንዳደረገ ታሪክ ይመሰክራል፡፡ በሮማውያን ዘመንም ለብዙ ዘመናት በዚህ ሁኔታ ቀጥሎ ነበር፡፡ ቡድሃዎች ደግሞ ከዚህ በተለየ መልኩ መስቀልን እንደየህይወት ዛፍ እና የመንፈስ ምግብነት ያዩት ነበር፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎችም እንደ ጣኦት ተደርጎ ይቆጠር ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ የምንመለከተው ግን ስለንግስት ሄሌና ታሪክ አብዝተን፣ በእሷ ምክንያት ስለሚነሱ ሰዎች ደግሞ በስሱ ይሆናል፡፡ ቅድስት/ንግስት ሄሌና/ዕሌኒ ማናት? በመግቢያው ላይ ስለመስቀል ፍች ትንሽ ማለቴ ለዚህኛው ርዕሴ ማካሄጃ እንዲሆነኝ በማሰብ ነው፡፡ ንግስት ሄሌና/ዕሌኒ በኋላ ቅድስት ሄሌና በላቲንኛ ደግሞ ፍላቪያ ኢዮሊያ ሄሌና አውጉስታ በመባል የምትጠራ ሲሆን የታላቁ ቆስጠንጢኖስ እናት ናት፡፡ በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም የትውልድ ቦታዋን የተመለከተው አፈታሪክ “እንግሊዝ፣ ሄሌኖፖሊስ ቢታንያ ሆኖ የዘር ግንዷ ከኤዥያ ይመዘዛል” የሚል ነው፡፡ “ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች ነው” የሚሉም አሉ፡፡ የትውልድ ዘመኗንም እንዲሁ በተጠጋጋ ግምት ከ246 -250 ዓ.ም መካከል ባለው አስምረው ህልፈተ ህይወቷ በ330 ዓ. ም በአሁኑ ጊዜ ስታንቡል በምትባለው በቱርክ እንደሆነ የሚናገሩ አሉ፡፡ ቅድስናዋ በሮማ ካቶሊክ፣ በምስራቅ ኦርቶዶክስ፣ በኦሬንታል ኦርቶዶክስ፣ በአንጀሊካ እና ሉተራን ቤተ ክርስቲያኖች ዕውቅና ተሰጥቶታል፡፡ ከላይ በተጠቀሰው ዘመን የተወለደችው ንግስት ሄሌና፣ የሮማ ጄኔራል የነበረውንና በኋላ ንጉስ የሆነውን ክሎረንስን አግብታ፣ በ274 ዓ.ም ቆስጠንጢኖስ የተባለ ወንድ ልጅ ወለደች፡፡ በ292 ዓ.ም ግን ከባሏ ጋር ተፋታ (ንጉሱ ለዘሯ ሲል ቴዎዶራን በማግባቱ) ለብዙ አመታት ከነበራት ክብር ዝቅ ብላ ኖረች፡፡ በ306 ዓ.ም ግን ንጉስ ክሎረንስ ሲሞት፣ ሰራዊቱ በአባቱ ምትክ ቆስጠንጢኖስን ተክቶ አነገሰው፡፡ ይህ ሁኔታም ንግስት ሄሌናን ወደቀድሞ ክብሯ እና ማዕረጓ እንድትመለስ አደረጋት፡፡ በሀገራችንም በመካከለኛው ዘመን በዚህ ስም የምትጠራ ኢትዮጵያዊት ንግስት እንደነበረች ታሪክ ያስረዳል፡፡ በታላቁ ቆስጠንጢኖስ እናትና በኢትዮጵያዊቷ ንግስት እሌኒ መካከል ያለው የዘመን ልዩነት ግን እጅግ የተራራቀ ነው፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያዊቷ በ16ኛው ክ.ዘ፣ ቅድስት ሄሌና ደግሞ በ3ኛው ክ.ዘ መጨረሻና በ4ኛው ክ.ዘ መጀመሪያ ላይ የኖሩ ናቸውና፡፡ ጉዳዩ ከተነሳ አይቀር ስለኢትዮጵያዊቷ ንግስት ዕሌኒ ትንሽ ብል መልካም ይመስለኛል፡፡ በሚያዚያ 1522 ዓ.ም (እንደነቤኪንግሃም) የሞተችው ንግስት ዕሌኒ (ሄንዝ የተባለ ጸሃፊ 1520 ይላል) የሃድያ ንጉስ የነበረው የንጉስ መሃመድ ልጅ ስትሆን በኋላ ክርስትናን ተቀብላ ከአጼ ልብነ ድንግል ጋር ተጋብታ የኖረች ጠንካራ ሴት ነበረች፡፡ በህይወት ዘመኗ በመንግስት አስተዳደር ላይ ተጨባጭ ሚና የነበራት፣ ለብዙ ነገስታትም አማካሪ ሆና ያገለገለች (ቢያንስ ለዘርዓ ያዕቆብ፣ ከሌላ ሚስት ለተወለደው የእንጀራ ልጇ በዕደ ማርያምና ለአጼ ናኦድ) ታላቅ ፖለቲከኛ ነበረች፡፡ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የተወለደችበትን በትክክል ባታስቀምጥም ሞቷ በ1522 ዓ.ም ነው ከሚሉት ጋር ትስማማለች፡፡ ቤተክርስቲያኗ ለንግስት ዕሌኒ ዕውቅና የምትሰጣት በመልካም ክርስቲያንነቷና ሃይማኖተኛነቷ ብቻ ሳይሆን በተለይ በሥላሶች ላይና በቅድስት ማርያም ንጽህና ላይ በጻፈቻቸው መጻህፍት ትልቅ ዋጋ ከመስጠት አኳያም ነው፡፡ ይሄ እግረመንገድ የተነሳ ስለሆነ ወደዋናው ነጥብ ልመለስ! ንግስት ዕሌኒ መስቀሉን ለመፈለግ ካነሳሷት ምክንያቶች አንዱ- ወደዚህ ርዕስ ከመግባታችን በፊት ስለታላቁ ቆስጠንጢኖስ አንድ የታሪክ ሁነት መግለጽ የግድ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ለመስቀሉ መገኘት ትልቅ ፋይዳ አለውና! ንጉስ ቆስጠንጢኖስ እንደነገሰ ከሶስት አቅጣጫ ከሶስት የተለያዩ ወገኖች ጋር ጦርነቶች ሊያደርግ ተነሳ፡፡ ውጊያውን ከማድረጉ በፊት ግን ስለማሸነፉ ልቡን ጥርጣሬ ወረረው፡፡ እንዲህ የልቡ ጥርጣሬ ከፍ ባለበት በሙሉ የቀትር ሰአት ግን አንድ በብርሃን የተሞላ መስቀል ከሰማይ ወደ ንጉሱ ቀረበ፡፡ በዚህ በከዋክብት ብርሃን በተሞላ መስቀል ላይም “በዚህ ምልክት ተዋጋ” የሚል ጽሁፍ ተመለከተ፡፡ በዚህ ጊዜ ንጉሱ ፈጥኖ በሰማይ ላይ የተመለከተውን መስቀል የሚመስልና የሚያክል እንዲሰራ በማዘዝ ከሰራዊቱ ቀድሞ እንዲመራ አደረገ፡፡ በመስቀሉ ኃይልም በቁጥር ከሱ ሰራዊት የሚበልጥ ጦር የነበራቸውን ጠላቶቹን አሸነፈ፡፡ በሌላ በኩል ንጉሱ በስጋ ደዌ በሽታ ይሰቃይ ስለነበር ወደአቡነ ሲልቨስተር (Bishop Sylvester) ቀርቦ ሲያማክራቸው፣ በክርስቲያን ወግ መሰረት አጥምቀውት ተፈወሰ፡፡ ከዚህ በኋላ ነው በ325 ዓ.ም በቤተክርስቲያን ላይ የተነሳውን ክርክር ተመልክቶ ከአለም ዙሪያ 318 ሊቃነ ጳጳሳትን በመጥራት “ኢየሱስ ክርስቶስ ወልድ ፍጡር ነው፤ ሁለት ባህርይ እንጅ አንድ አይደሉም” ብሎ የተነሳውን አርዮስን በኒቂያ ጉባኤ ላይ አስወግዞ ከቤተክርስቲያን እንዲለይ ያደረገውና ስርአትንና ኃይማኖትን የሚመለከቱ ሃያ ያህል ቀኖናዎች እንዲሰሩ ያደረገ ነው፡፡
Show all...
ብዙ ሰው "ያሰብኹት ሁሉ ምንም ሊሳካልኝ አልቻለም" እያለ ያጉረመርማል፤ "እግዚአብሔርማ እኔን ሳይተወኝ አልቀረም!" እያለ ፈጣሪውን ያማርራል። "ይሰጠኛል" ሳይሆን "አገኘዋለሁ" ብሎ ይጀምርና ሳይሆን ሲቀር በእጁ የነበረውን የነጠቀው ያህል አምላኩ ላይ ያለቅሳል። ስታቅድ ያላስታወስከውን አምላክ ያቀድከው ሲፈርስ ስሙን እየጠራህ ስለምን ትወቅሰዋለህ? በሕይወትህ መቼ ቦታ ሰጠኸው? እንደ ፈቃዴ ካልሆነ አልህ እንጂ መቼ "እንደ ፈቃድህ ይሁን" ብለህ ጸለይህ? ባላማከርከው ለምን ተከሳሽ ታደርገዋለህ? ልሥራ ብለህ በተነሣህበትም ቀን እንዲሁ በግዴለሽነት ስሙን ጠርተህ እንደ ሆነም ራስህን መርምር? በትክክል ጸልየህና በመንገድህ ሁሉ ይመራህ ዘንድ ፈቅደህ ከጀመርህ ግን ግድ የለም እረኛህን እመነው። አንተ እንደ ሎጥ ከመረጥኸው እና ለጊዜው የገነት አምሳል ሆኖ ከሚታይህ ነገር ግን እግዚአብሔር ከማይከብርበት ከለምለሙ ሰዶምና ገሞራ ይልቅ፣ አሁን ብዙም ለአይን የማይስበው በኋላ ግን ወተትና ማር የሚያፈሰው ለልጅ ልጆችህም ርስት የሚሆነው እግዚአብሔር የሚሰጥህ ከነአን ይሻልሃል። (Deacon Abel Kassahun Mekuria) +++join & share+++ 👇👇👇👇👇👇👇 @neamn_media @neamn_media @neamn_media
Show all...
“አንድ ምንም እውቀቱና ልምዱ የሌለው ሰው ዝም ብሎ መሬት ስለ ቆፈረ ብቻ ወርቅ አያገኝም፡፡ ከዚያ ይልቅ ምንም ረብሕና ጥቅም የሌለውን ድካም ያተርፋል እንጂ፡፡ ባስ ካለም የቆፈረው ጉድጓድ ተደርምሶበት ሕይወቱን ሊያጣ ይችላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት እንደሚነበብና እንዴት መረዳት እንዳለበት ያለወቀ ሰውም ይህን ሰው ይመስላል፡፡” ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ +++ join & share +++ 👇👇👇👇👇👇👇👇 @neamn_media @neamn_media @neamn_media
Show all...
👍 1