cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

University of Gondar(UoG)Atse Tewodros Compus Student Union 2015 E.C

ውድ የግቢያችን ተማሪዎች ሰላምና ፍቅር ከእናንተ ጋር ይሁን እያልን ማንኛውንም ወቅታዊ መረጃዎች በዚህ ቻናል የምታገኙ መሆኑን እናሳውቃለን::ለሌሎችም እንዲደርሳቸው ሼር አድርጉላቸው!!!! ማንኛውንም ጥያቄና መረጃ በዚህ አድርሱን 👉👉 https://t.me/+5NelehOUNtthNDA0 (0918759849)

Show more
Advertising posts
833
Subscribers
No data24 hours
-27 days
-730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ለሪሜዲያል ተማሪዎች በሙሉ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ በ2015 ዓ፣ም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሪሜዲያል ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁ ተማሪዎች፦ 1. የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ 200 እና በላይ 2. ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ 150 እና በላይ 3. የዓይነ ስዉራን ተማሪዎች ማለፊያ ነጥብ 100 እና በላይ መሆኑን እየገለዕን ዉጤታችሁን ከታች በተቀመጠዉ ሊንክ እየገባችሁ ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን፣፣ ከግቢ ዉጪ http፡//213.55.79.200 ከግቢ ዉስጥ http፡//10.139.8.79 ለልህቀት እንተጋለን! ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ሐምሌ 22/2015 ዓ.ም
Show all...
Notice for Remedial students you can see your grade via this portal http://213.55.79.200
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
" ተፈታኞች በአካልም ይሁን በስነልቦና እራሳችሁን ዝግጁ አድርጉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መርሃ ግብርን ይፋ አድርጓል። በዚህም ፥ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሐምሌ 16 እና 17/2015 ዓ.ም ወደተመደቡበት ተቋም ይገባሉ። ሐምሌ 18/2015 ዓ.ም ገልጻ ይሰጣቸዋል። ከሐምሌ 19 እስከ 21/2015 ዓ.ም ፈተናቸውን ይወስዳሉ። ከሚቀጥለው ቀን ጀምሮ ተማሪዎች ወደመጡበት ይመለሳሉ። የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች  ደግሞ ሐምሌ 22 እና 23/2015 ዓ.ም ወደተመደቡበት ተቋም ይገባሉ። ሐምሌ 24/2015 ዓ.ም ገለጻ ይሰጣቸዋል። ከሐምሌ 25 እስከ 28/2015 ዓ.ም ፈተናቸውን ይወስዳሉ።  ከሚቀጥለው ቀን ጀምሮ ተማሪዎች ወደመጡበት ይመለሳሉ። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናውን በሚውስዱበት ጊዜ የፈተናውን ህግና ስርዓት እንዲያከብሩ በጥብቅ አሳስቧል። ተፈታኝ ተማሪዎች ለፈተናው ግልጋሎት ከሚሰጡ የፅህፈት መሳሪያዎች እርሳስ፣ ላጲስ፣ መቅረጫ እና ስክቢቶ ውጭ ወደ ፈተና ክፍል ይዞ መግባት ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑን እንዲያውቁት ብሏል። ተማሪዎቹ ከቤታቸው ሲወጡ፦ - መታወቂያ ፣ - አድሚሽን ካርድ - የት/ቤት ዩኒፎርም መያዛቸውን እንዳይረሱ ፤ ወላጆችም ይህንን እንዲያስታውሷቸው ጥሪ ቀርቧል። ወደ መፈተኛ ተቋማት ቆሎ፣ ጭኮ፣ በሶ የመሳሰሉ ደረቅ ምግቦችን ይዞ መግባት የሚፈቀድ ሲሆን የቴክኖሎጂ ውጤቶች፣ አይፓድ፣ ላፕቶፕ የመሳሰሉ እንዲሁም ማንኛውም ጌጣጌጥ ይዞ መግባት ፈፅሞ የተከለከለ ነው። ለኢንትራንስ ተፈታኞች👇 https://t.me/ATC_UEE ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Show all...
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሐምሌ 19 ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይሰጣል። የተፈታኝ ተማሪዎች መብቶች፦ ➭ ከፈተና ጥያቄ ውጪ ማንኛውንም ያልተረዳውን ነገር ጠይቆ የመረዳት መብት አላቸው። ➭ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የምግብ፣ የህክምና አገልግሎት፣ የማደሪያ ክፍል፣ ፍራሽ እና ትራስ የማግኘት መብት አላቸው። ➭ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ያለውን የቤተ መፅሐፍት፣ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የሻወር፣ የካፍቴሪያዎች፣ የሚኒ ሱፐር ማርኬቶች፣ የተለያዩ ሱቆች እንዲሁም የመናፈሻና መዝናኛ አገልግሎቶችን የመጠቀም መብት አላቸው። ➭ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የጋራ የደህንነት ጥበቃ የማግኘት መብት አላቸው። ➭ በፈተና ሰዓት መፈተኛ ክፍል ገብቶ ብርሃናማ የመፈተኛ ቦታ፣ ወንበርና መፃፊያ ጠረጴዛ የማግኘት መብት አላቸው። ➭ ፈተና ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀድሞ ስለፈተናው ገለጻ (ኦሬንቴሽን) የማግኘት መብት አላቸው። የተፈታኝ ተማሪዎች ግዴታዎች፡- ➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከልና መፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ ይዞ የመገኘት ግዴታ አለበት። ➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ የትምህርት ቤት ወይም የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት አለበት። ➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ግቢ ከመግባቱ በፊትና ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባቱ በፊት ሙሉ አካላዊ ፍተሻ የመፈተሽ ግዴታ አለበት። ➤ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢና በመፈተኛ ክፍል የተከለከሉ ዕቃዎችን መያዝ የለበትም። ➤ ማንኛውም ተፈታኝ እርሳስ፣ ላጲስና የእርሳስ መቅረጫ ይዞ መገኘት አለበት። ➤ ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብን የማክበር ግዴታ አለበት። ➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከል/በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የፈተና አስፈጻሚዎች የፈተና አስተዳደር ሥራን ውጤታማ ለማድረግና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚያደርጉትን ጥረት የመተባበር ግዴታ አለበት። ➤ ማንኛውም ተፈታኝ ፈተና ከመጀመሩ በፊት መፈተኛ ክፍል የመገኘት ግዴታ አለበት። ➤ ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ለፈታኙ የማሰረከብ ግዴታ አለበት። ➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደተመደበበት ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ጨርቅ ይዞ የመምጣት ግዴታ አለበት። ለተፈታኝ ተማሪዎች የተፈቀዱ ነገሮች፦ ➣ አዲስ ወይም ቀድሞ ለመማር እና ለማጥናት ሲጠቀሙበት የነበሩ ማስተወሻ ደብተር፣ የትምህርት መፅሐፍ፣ መንፈሳዊ/ኃይማኖታዊ መፅሐፍት፣ ባዶ ወረቀት ➣ ደረቅ ምግቦች (ጩኮ፣ በሶ፣ ዳቦ ቆሎ፣ ቆሎ….) ➣ ገንዘብ (ብር) ➣ የልብስ ወይም የእጅ ቦርሳ፣ የግል ልብስ፣ ጫማ ➣ የግል ንጽህና መጠበቂያዎች (ሳሙና፣ ሞዴስ፣ የጥርስ ብሩሽ፣ የጥርስ ሳሙና፣ ፎጣ፣ ሶፍት፣ ሻምፖ፣ ኮንዲሽነር፣ ሎሽን፣ ቻፕስቲክ፣ የጸጉር ቅባት፣ የፊት ቅባት) ለተፈታኝ ተማሪዎች የተከለከሉ ነገሮች፦ ➣ ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡ ➣ ማንኛውንም ዓይነት ስለት እና ሹልነት ያላቸውን ብረታ ብረቶችና ጠንካራ ፕላስትኮች ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው። ➣ ማንኛውም ድምጽ የሚቀዳ፣ ፎቶ የሚያነሳ፣ ቪዲዮ የሚቀርጽ፣ ከቴሌ መስመርም ሆነ ከቴሌ መስመር ውጭ መልዕክት በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል የግል ዕቃ/መሳሪያ/የቴክኖሎጂ ውጤት፣ ስልክ፣ አይ-ፓድ፣ ታብሌት፣ ኮምፕዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ጃኬት እና ሌሎች ማንኛቸውም ፎቶ፣ ምስል እና ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ ዙሪያ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡ ➣ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የግል ፍላሽ ዲስክ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ሲዲ፣ ሚሞሪ፣ ሚሞሪ ሪደር፣ ኦ-ቲጂ ኮንቨርተርና መሰል ዕቃዎችን ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡ ➣ ማንኛውም አደንዛዥ እጾች (ጫት፣ ሲጋራ፣ በሐኪም ማዘዣ የሌለው መድኃኒት)፣ ህክምና መስጫ መርፌ መያዝ ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡ ➣ ማንኛውም ዓይነት የአልኮል መጠጥ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡ ➣ ማንኛውም ዓይነት የአንገት ሐብል፣ የጸጉር ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ የጣት ቀለበት፣ የእጅ አንባር፣ አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡ (ከልሙጥ የጋብቻ ቀለበት በስተቀር) ➣ ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት የተከለከለ ነው፡፡ ➣ ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ይዞ መውጣት ተከለከለ ነው፡፡ ➣ በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ማስቲካ መያዝም ሆነ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡ ➣ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን መጮህ ወይም በጣም ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው። ለኢንትራንስ ተፈታኞች👇 https://t.me/ATC_UEE ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Show all...
በተማሪዎቻችን ውጤት ደስ ብሎናል እንኳን ደስ አላችሁ! ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ በዚህ ዓመት በተተገበረው አገር ዓቀፍ የመውጫ ፈተና ተማሪዎቻችን ከፍተኛ ውጤት አስመዝግበዋል። ይህም በሀገራችን ከሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ዩኒቨርሲቲያችን ቀዳሚ አድርጎታል። በገለልተኛ አካል አስፈትኖ ይህን ውጤት ማግኘት የበለጠ የሚያበረታታና ለነገ ተስፋ የሚሰጥ ጅማሮ ነው። ይህ ውጤት የተማሪዎቻችን፣ የመምህራንና መላ የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ ፣ የወላጆች፣ አቅፎና ደግፎ እዚህ ያደረሳቸው የጎንደር ሕዝብ እና የቅርብ አጋሮቻችን የረጅም ጊዜ ድካምና ልፋት ውጤት ነው። ከምንም በላይ የሁሉም የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ ሥራን በሙያዊነት፣ በተቆርቋሪነት እና በጋራ የመሥራት መንፈስ ውጤት ነው። አገር የሚፈርሰውም የሚሠራውም በትምህርት ነውና ለጥራት ከምንጊዜውም በላይ ተግተን እንሠራለን። "ሰው የዘራውን ያጭዳል" ነውና ሁላችንም የድካማችን ፍሬ ማየት በመብቃታችን እንኳን ደስ አለን። ሙያዊ ሆኖ መስራት ምላሹ ብዙ ነው! ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ዶክተር አሥራት ዓጸደወይን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሐምሌ 09/2015 ዓ.ም
Show all...
በአገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ዩኒቨርሲቲያችን በግምባር ቀደምትነት ተማሪዎችን በማሳለፉ እንኳን ደስ አለን፤ እንኳን ደስ አላችሁ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ በአገር ዓቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በተተገበረው እና በዩኒቨርሲቲያችን ባሉ 8 ኮሌጆች፣ 2 ኢንስቲትዩቶችና 1 ትምህርት ቤት ስር በሚገኙ 73 ትምህርት ክፍሎች ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል። በአጠቃላይ ካስፈተናቸው 3,089 ተማሪዎች ውስጥ 2,760(89.35%) ተፈታኞች በብቃት አልፈዋል። ፈተናውን ከወሰዱ 73 ትምህርት ክፍሎች መካከል 34 ትምህርት ክፍሎች ሙሉ በሙሉ (100%) አሳልፈዋል። ከአጠቃላይ ተፈታኞች መካከል በመደበኛ መርሐግብር ካስፈተናቸው 2,919 ተማሪዎች 2,703 (92.6%) ያለፉ ሲሆን ቀሪዎቹ 170 ተማሪዎች በተከታታይ መርሐግብር ተፈተነው 57(33.53%) ፈተናውን በብቃት አልፈዋል። ይህም ውጤት በአገሪቱ ካሉ አቻ ተቋማት ቀዳሚ ያደርገዋል። በዚህም መላው የዩኒቨርስቲያችን ማህበረሰብና አጋሮቻችን ከፍተኛ ኩራትና ደስታ ተሰምቷቸዋል። የተገኘው ስኬት አበረታችና ለቀጣይ ትልቅ ኃላፊነትን የሰጠን ነው። ስለሆነም ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ወላጆች፣ የቴክኒክ ረዳቶች፣ የአስተዳደር ሠራተኞች፣ ትምህርት ሚኒስቴርና ሌሎች አጋር አካላት እንዲሁም መላ የትምህርት ቤተሰቡ በትብብር ያስመዘገባችሁት ውጤት በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እንወዳለን። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ለልህቀት እንተጋለን! ህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግኝኙነት ዳይሬክቶሬት ሐምሌ 09/2015 ዓ.ም
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
#UniversityofGonder 🎉 በአገር ዓቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በተተገበረው የመውጫ ፈተና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በአገሪቱ ካሉ አቻ ተቋማት ቀዳሚ ሆኗል። የጎንደር ዩንቨርሲቲ በአጠቃላይ ካስፈተናቸው 3,089 ተማሪዎች ውስጥ 2,760(89.35%) ተፈታኞች በብቃት ማሳለፍ የቻለ ሲሆን ፈተናውን ከወሰዱ 73 ትምህርት ክፍሎች መካከል 34 ትምህርት ክፍሎች ሙሉ በሙሉ (100%) አልፈዋል። ይህንን ስኬት አስመልክቶ ዩኒቨርሲቲው ለተማሪዎቹ፣ ለመምህራን፣ ለወላጆች፣ ለቴክኒክ ረዳቶች፣ ለአስተዳደር ሠራተኞች፣ ለትምህርት ሚኒስቴርና ለሌሎች አጋር አካላት እንዲሁም ለመላ የትምህርት ቤተሰቡ ምስጋና አቅርቧል። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Show all...
ውጤት አሁን ይፍ ሁኗል እየገባችሁ ማየት ትችላላሁ መልካም ውጤት
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.