ets&len📷💃
Open in Telegram
@ets4123 Model photo📷 Bezi Chanel west Music🔊🔊 Ye Fker Tekesoche😍😍 Tiktok video😂😂 Memes😛😋 All of you want are here just join us feta becha💃💃💃 comment 👉👉👉 @model_etsub_28 😍😍😍😍 @lenaw16
Show more383
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-530 days
Posts Archive
383
HBD yene wed wendem
Yene meskine😊
Yene asetewaye🥰
Nefffffffff amete nurelegne
Fetari yasebekewen yasakaleke 🎂🎂🥂🥂🍸🍸🍸🍸🎂🎂🥰🥰🥰🥰
383
ጊዜ ጊዜን እየተካ፤
ልጅነት አልቋል ለካ፤
ምነው ቢቀር እንደራቀኝ፤
ላይመለስ ባይናፍቀኝ፤
ያለፍኩትን ልጅነቴን ሳስታውሰው፤
ተመኘው ብችል ስቤ ልመልሰው፤
በእናት ጉያ በእናት እቅፍ ማለት ዘና፤
በአባት ተግሣፅ በአባት ምክር መሆን ቀና፤
............
383
እጎዳብሻለሁ
:
:
የሱ ነገር በቃኝ ባፍንጫዬ ይውጣ፣
ፍቅሩን በማለቴ ለምንስ ልቀጣ፣
ብለሽ የላክሺብኝ ወቀሳሽ ደርሶኛል፣
ካጠፋሁት አንፃር እንደውም ያንሰኛል።
ባፍንጫሽም ልውጣ ይበለኝ አምናለሁ፣
ግን ፍቅሬ ...
ከልብሽ ከወጣሁ እጎዳብሻለሁ።
383
💔 ሂጂ ፈቅጃለሁ ❤️🔥
የውስጤን ላይ ሸማ #አንቺው ጀምረሽው
በሰፊው ልቤ ላይ ባጭር #ከቀጨሽው😔
……………………ደርቢው አልልም!
ድሮም #አጭር ነገር ከሰው ላይ #አያምርም!!
እውነቴን ነው ውዴ
ለሰው ልጆች ሁሉ
ያልተመለሰልን ብዙ ጥያቄ አለ
አንቺም #ካልተመቸሽ
የልቤ ላይ ሸማ ላንቺ #ካልተባለ
መሄድ ትችያለሽ!🤷♂
#አልከለክልሽም !
ለኔ የሞተብሽ ስሜትሽ ካየለ
ግን #ማወቅ ያለብሽ?
ገፍቶ #በመሄድ ላይ ብዙ #መውደቅ አለ😒
እውነቴን ነው ውዴ❤️
በዚች ዓለም ስኖር መገፋት #ቢኖርም
በፍቅር #መረገጥ ሽንፈት #አይወክልም🙏
ደሞ ይሄን #ስልሽ
#እንዲገባሽ እንጂ #እንድትመጪ አደለም!🙌
ሂጂ #ፈቅጃለሁ☹️
በኳታኙ እግርሽ #እንዳሻሽ ሁኝበት💁♂
ድሮም መሄድ እንጂ መምጣት #አታውቂበት😏
ስለዚህ ፍቅሬ❤️
ጥለሽኝ ብትሄጅም😟
#መነሳቴ አይቀርም መቃብር ፈልፍየ
በፍቅር ዓለም ውስጥ
#ከሞት በኃላ ነው 'ሚኖረው #ትንሳኤ 🙌
@ets4123
383
ከፍቅር በላይ❤️
አፍቅሮኛል እያልሽ ያወጋሽው ወሬ
ስንት ጆሮ አልፎ ከኔም ደርሷል ዛሬ።
በኔ መውደድ ታስሮ መላወስ ከብዶታል
ያልሺውም ንግግር ከጆሮዬ ገብቷል።
ከራሴው ሳትሰሚ ሳታውቂው እርግጡን
የብብትሽን ጣልሽ ስታልሚ ቆጡን።
ሁሉን ሰምቻለው ማን ምንስ እንዳለኝ
አንቺ አፍ እንዳለሽ እኔም ጆሮ አለኝ።
ምንም ይሁን ምንም
ስሜን ስላጠፋሽ አላዘንኩብሽም
እውነቱ ግን ይህ ነው እኔ አላፈቅርሽም
እኔስ አልወድሽም።
እርግጥ ነው አልክድም...
ከቤትሽ ፊት ለፊት ከዋርካው ጥላ ስር ሁሌ እቀመጣለው
ዕድል ያልቀናኝ ለት ያላየውሽ እንደው ጭንቄን አምጣለው
ያየውሽም ከሆን እንደ ረጋ ወተት በደስታ እናጣለው።
እርግጥ ነው አልክድም...
ያ የሰፈራችን ጠብደሉ ጎረምሳ በጨዋታ መሀል ሲሰድብሽ ስሰማ
በጣም ተናድጄ ፈንክቼው ሮጬያለው ጠብቄ ጨለማ።
ደግሞም የሆነ ጊዜ በመንገድ እያለፍሽ አንዱ ጓደኛችን የለከፈሽ ለታ
ደም ፋላቴ መቶ አዝንቤበታለው የቡጢ ጋጋታ።
እርግጥ ነው አልክድም...
ሳገኝሽ ስቄያለው ሳጣሽም ከፍቶኛል
አንቺን ብቻ እያየው በመንገድ ሳቀናም ስልክ እንጨት ገጭቶኛል
ትረፍ ሲለኝ ከላይ መኪናም ስቶኛል።
እርግጥ ነው አልክድም...
ጎኔና ፍራሼ የገጠሙ ጊዜም በህልሜ አይሻለው
ስምሽን ሲጠሩት የጠሩኝም መስሎኝ ስንቴ አቤት ብያለው
አዝነሽ ያየው ቀንም ደም እንባ አልቅሻለው።
ይህንም አልክድም...
ምንም ቢሆን ምንም
እኔ አንቺን አልወድም።
አፍቅሮኛል ብለሽ ስሜን ስላጠፋሽ አላዘንኩብሽም
እውነት እውነት ስሚኝ አላፈቀርኩሽም።
ይህ ፍቅር አይደለም
ይህ መውደድ አይደለም
ለጓደኞችሽም ዳግም ስታወጊ
ከዚህ የተሻለ ሌላ ቃል ፈልጊ።
አፍቅሮኛል ብለሽ ፍቅሬን አትግደዪ
ከፍቅር በላይ ነው ያፈቀረኝ በዪ
ከመውደድ በላይ ነው የወደድከኝ በዩ።
@ets4123
