cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

በእኔ እይታ

ሁሉም ሰው ለእራሱ ማለትም በእርሱ እይታ ትክክል ነው ።አንድ ነን እንጂ አንድ ዓይነት አይደለንም ስለዚህ ሁሉም ለእራሱ ትክክል ነው 👍👍👍👍👌👌👌👌👌💪💪💪 ይህ ቻነል አስተማር ትምህረት አዘል መልዕክቶች የሚተላለፍበት ቻነል ነው ለማነኛውም ዓይነት ሀሳብ እነ ጥያቄ @israelalexe or "Gaetu"ልታጋኙኝ 0955294580 ትችላለችሁ [email protected]

Show more
Advertising posts
208
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በአንድ ትልቅ አዳራሽ ውስጥ በርካታ ሰዎች ተሰብስበዋል፡፡  የውይይቱ መሪ ወደመደርክ ይወጣና ለእያንዳንዳቸው ፊኛ ይሰጣቸዋል፡፡  --------------------------- በመቀጠልም እላዩ ላይ ስማቸውን እንዲፅፉበት አዘዘ፡፡  ፅፈው እንደጨረሱም የሁሉንም ሰበሰበና አዘበራርቆ አስቀመጠው፡፡ እናም ሁሉም የእራሳቸውን ስም ያለበትን ፊኛ በ5 ደቂቃ ውስጥ ፈልገው እንዲያመጡ አዘዘ፡፡ --------------------------- ሁሉም በተጣደፈ መልኩ የእራሱን ፊኛ መፈለግ ጀመረ፡፡ ግማሹ ይገፋፋል፤ ግማሹ እርስ በርስ ይጋጫል፤ ክፍሉ ለዛ በሌለው ጫጫታ ተሞላ፡፡ 5 ደቂቃው እንዳለቀ ማንም የእራሱን ፊኛ ያገኘ አልነበረም፡፡  --------------------------- አሁን አወያዩ ሁሉም አንድ ፊኛ እንዲያነሳና ስሙ ለተፃፈበት ሰው እንዲሰጥ አዘዘ፡፡ በ2 ደቂቃ ውስጥ ሁሉም የእራሱን ፊኛ አገኘ፡፡ አወያዩ ቀጠለ፡፡ "ይህ በትክክለኛው ህይወታችን የሚፈጠር ነገር ነው፡፡ ሁሉም ሰው ደስታን ፍለጋ ይጣደፋል፡፡ ግን አያገኘውም፡፡ የእኛ ደስታ ሌሎችን በመርዳትና ደስተኛ በማድረግ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡  ሌሎችን በመርዳት ደስተኛ እንዲሆኑ ማድረግ  ከቻልን የእኛን ደስታ ማግኘት ቀላል ነው፡፡  ሰው መሆን ማለት ሌሎችን በመርዳት ደስተኛ ማድረግና በዚህም ውስጥ የራስን ደስታ መፍጠር ነው፡፡" ---------------------------@israelalexe መልእክቱ አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎች ይማሩበት ዘንድ like/copylink share ማድረግን አትርሱ!
Show all...
ሳታልፍ በፊት ኑር! በዚህ አለም የሚያረጋጋ ቃል ቢኖር አንዱ "ሁሉም ያልፋል" የሚለው ነው፤ ሀዘኑም ያልፋል፣ደስታውም ያልፋል፣ ንዴቱም ያልፋል፣ እርካታውም ያልፋል፤ ሌላውን ተወው አንተም እኔም እናልፋለን! በፍጥረት አለም ፀንቶ የሚኖር ነገር ቢኖር አምላክ ብቻ ነው። ታዲያ ለሚያልፍ ችግር ለምን አብዝተህ ትጨነቃለህ? ለሚያልፍ ቀን ለምን ራስህን ትጎዳለህ? ህይወትህን ነብስ ዝራበት፤ የምትወደውን ስራ፣ የምትወዳትን የራስህ ለማድረግ ተዘጋጅ፣ መንፈሳዊነትህን ሳትለቅ የምድርን በረከት ሁሉ አጣጥም፤ ሳታልፍ በፊት ኑር ወዳጄ! @israelalexe
Show all...
ዱካህን አስቀምጥ! ፨፨፨፨////////፨፨፨፨ መንገዱ የሚመራህን መንገድ አትከተል። በምትኩ ዱካ በሌለበት ቦታ ሂድና የእራስህን ዱካ አስቀምጥ። - Ralph Waldo Emerson የተለዩት ብቻ የተለየ ጀብድ ይፈፅማሉ፣ የተመረጡ ብቻ ያልተሞከረውን ይሞክራሉ፣ በእራሳቸው የሚተማመኑ ብቻ ህይወታቸውን በፈለጉት መንገድ ይመሩታል፣ ብርቱዎች ብቻ የእራሳቸውን አለም ይፈጥራሉ፣ ደፋሮች ብቻ ፍረሃታቸውን ፊትለፊት ይጋፈጣሉ። ዋናው ጉዳይ ህይወት ምርጫ እንደሆነች ማወቅ ብቻ ሳይሆን የመረጡትን ህይወት መኖር መቻል ነው። ቁብነገሩ ሃሳብ ላይ ሃሳብ መደረብ፣ በጭንቀት ላይ ጭንቀትን ማከል ሳይሆን በአንዱ ልዩ ሃሳብ እራስን ነፃ ማውጣት ነው። የእራስህ የግል አቋም ከሌለህ ሁሌም የአለም ባሪያና አቋም ያላቸው ሰዎች ተገዢ ነህ። ሃሳብህ ባሪያ አልያም ገዢ ያድግሃል። አዎ! ጀግናዬ...! ዱካህን አስቀምጥ! በአዲሱ ቀንህ የእራሴ የምትለውን፣ የምትኮራበትን፣ በልበሙሉነት የምታወራለትን ዱካ አስቀምጥ፣ የእራስህን አሻራ አሳርፍ፣ እራስህን በየቀኑ አድሰው። ዓለም ብትዘነጋህም አንተ ግን እለት እለት እራስህን አስታውስ፣ በአዳዲስ ፈተናዎች እራስህን አንፅ። ሮጠህ የምታመልጠው፣ ተደብቀህ የምትሸውደው ለውጥ እንደሌለ አስታውስ። በውዴታም ይሁን በግዴታ የህይወትህ ለውጥ ከበርህ አፋፍ ላይ ቆሞ ይጠብቅሃል። ያንተም ምርጫ የምትፈልገውን ማስገባት ወይም ሁሉም እንዲገባ መፍቀድ ነው። ፈልገህ ብትቀየር የገዛ ክብርህን በፍቃድህ ትጨምራለህ፣ ለምርጫ ተቸግረህ በለውጥ ማዕቀፍ ውስጥ ብትዋጥ ግን ከትርፍህ ጉዳትህ፣ ከሰላምህም ጭንቀትህ ይልቃል። አዎ! የእራስን ዱካ በማስቀመጥ ውስጥ ሸውደህ የምታመልጠው የፍረሃት መንገድ የለም፤ ሃላፊነት ለመውሰድ በመዘጋጀት ውስጥ ግዴለሽነት ተቀባይነት የለውም፤ በእራስ ውሳኔ በመፅናት መሃል ልፍስፍስነት ቦታ የለውም። በተለየው አቋምህ መፅናት ካለብህ እስከመጨረሻው መፅናት ይኖርብሃል፤ መዳረሻህን ካስቀመጥክ እስክትደርስበት ወደኋላ መመለስ የለም። ወደፊት የምትፈጥረው ማንነት በዛሬው ተስፋህ ላይ የተመሰረተ ነው፤ የህይወትህ ወሳኝ ቁልፍ 🔑 ዛሬ በእጅህ ላይ ያለችው አሁን ነች። አሸንፎ መገኘት ትናንትን ወይም ነገን ሰይሆን ዛሬን አሁንን ነውና አሁኑኑ የእራስህን ዱካ በማሳረፍ የህይወትህ አሸናፊ ሁን። @israelalexd
Show all...
ስማቹን አስቀይሩ ለእናንተ የማይመጥን፣ስራቹን የማይገልፅ፣አቅማቹን የማይስተካከል ስም ካላቹ አሁኑኑ አስቀይሩት፤ ያዕቆብ አታላይነቱን አልወደደውም ያዕቆብ ተብሎ ሲጠራ ትዝ የሚለው አታላይነቱ ነው ለዚህም ነው ስም ቀያሪውን አምላኩን ሲያገኘው ካልባረከኝ አለቅህም ያለው የያዕቆብ ትክክለኛ ስም እስራኤል ነበር ያዕቆብ የእርሱ ስም አልነበረም እናንተም የናንተ ባልሆነ ማንነት ጊዜያቹን አትጨርሱ አሁኑኑ የእናንተን እውነተኛ ማንነት እወቁት ያኔ በህይወታቹ ታሪክ መስራት ትጀምራላቹ @israelalexe @israelalexe @israelalexe @israelalexe
Show all...
እያለህ አጊጥበት! ፨፨፨፨/////፨፨፨፨ ዘላለም አብሮን የሚቆይ ነገር የለም፤ የእኔ የምንለው የገዛ አካላችን እንኳን አንድ ቀን ይከዳናል፤ ያረጃል፤ ያልፋል፤ ይጠፋል፤ እንዳልነበርም ይሆናል። የሆነው ሆኖ፣ የሆነው ላይቀየር፣ ያልሆንከውን ላትሆነው "እንደዚህ ቢሆን፣ እንደዛ ቢሆን ይሻለኝ ነበር" በማለት ማማረጥህንና ያለህን ማማረርህን አቁም። እንዳለህ ማመስገን ትችላለህ፤ ያለህን መውደድ፣ ማድነቅ፣ ማሞገስ፣ በእርሱም መኩራት ትችላለህ። ተጨማሪ ነገር እየፈለክ ያለህ እስኪወሰድ አትጠብቅ። አዎ! ጀግኒት..! ተፈጥሮ አስውቦሽ፣ ዋናውን ነገር ሰቶሽ ሳለ በሰው ሰራሽ በጊዜያዊ ቁስ ለማጌጥ አትሽቀዳደሚ። ተጨመሪ ቁስ የሚያስፈልግሽ ጊዜ እስኪደርስ ባለሽ ማማርን፣ በተሰጠሽ መዘነጥን ተለማመጂ። ዛሬ ያለሽ ሁሉ ጊዜው ያልፋል፤ ያረጃል፤ በጊዜው ግን በነፃነት ተጠቀሚበት፤ ውደጂው፣ ተቀበይው፣ ተደሰቺበት። አሁን ሁሉ ነገርሽ ሙሉ ነው፣ ውብ ነው ከጊዜ ቦሃላ ግን ላይሆን ይችላል። ሙሉና ውብ ሆነሽ ሳለ የጎደለሽና ያነሰሽ ነገር እንዳለ ተጨማሪ ነገር ከማሳደድ ብትቆጠቢ በእራስሽ እንድትኮሪ ያደርግሻል። አዎ! ጀግናዬ..! ከሌለ የለም፤ ካለፈም አለፈ፤ ከቀረም ይቀራልና እያለህ አጊጥበት፤ ድመቅበት፤ ታይበት። ዛሬ ሰውነትህን እንደፈለክ ማዘዝ ትችላለህ፤ ተነስ ስትለው የሚነሳ፤ ተቀመጥ ስትለው የሚቀመጥ፣ የፈለከውን የሚፈፅምልህ ብርቱና ጠንካራ ሰውነት አለህ። አንድ ቀን ግን ላትቆጣጠረው ትችላለህና በእጅህ እያለ ተጠቀምበት፤ ያሰብከውን ሁሉ በጊዜ ከውንበት። የሚያደምቅህን ተጨማሪ ጊዜያዊ ነገር ከምትፈልግ ባለህና በተፈጥሮዓዊ ነገር ደምቀህ ለመታየት ሞክር። ያለህን፣ የተሰጠህን፣ ያንተ ብቻ የሆነውን እያንዳንዱን ስጦታህን ተጠቀም፤ ኩራበት፤ አጊጥበት። የቀረብህን ጥቂት ነገር ፍለጋ ያለህን፣ የተሰጠህን ውድ ሰጦታም ዋጋ አታሳጣው። ✍️@israelalexe
Show all...
እራሳችሁን አስቀድሙ! ፨፨፨፨/////////፨፨፨፨፨ ሳታስቡት ኬት መጣ የተባለ እባብ ቢነድፋችሁና ቢጎዳችሁ የመጀመሪያ እርምጃችሁ ምን ይሆናል? እባቡን ገድሎ መበቀል ወይስ እራስን ለማዳን በፍጥነት ወደ ጤና ጣቢያ ማምራት? ከሁለቱ አንዱን ለመምረጥ ቀዳሚው ነገር ሚዛናዊ እይታ ይሆናል። እባቡን ብትገድሉት የእናንተን ጉዳትና ህመም ማስታገስ አትችሉም፣ በፍጥነት ወደ ጤና ጣቢያ በማምራት ብትታከሙ ግን በመርዙ ከመጎዳት እራሳችሁን ታድናላችሁ። የህይወት ታሪካችሁም ከዚ የተለየ አይደለም። ማንም በትናንትናችሁ ውስጥ ሊኖር ይችላል፣ ማንም ባልጠበቃችሁት ልክ ሊጎዳችሁ ይችላል፣ ምንም ነገር ሳታስቡት ገጥሟችሁም ይችላል ነገር ግን ያለፈ ጉዳታችሁን በበቀል ለመሻር፣ ዳግም የጎዳችሁንም በመጉዳት ለመመለስ የምትጥሩ ከሆነ በእባቡ ተነድፋችሁ መርዙ ውስጣችሁ እየተሰራጨ እባቡን ለመግደል እየታገላችሁ እንደሆነ እወቁ። አዎ! እራሳችሁን አስቀድሙ! መጀመሪያ እራሳችሁን አድኑ፣ አስቀድማችሁ በደህንነታችሁ እርግጠኛ ሁኑ፣ ባላችሁበት  ሁኔታ ሰላም ይሰማችሁ። ትናንታችሁ ጠባሳ የጣለባችሁ ሳያንስ ዛሬም እናንተው በፍቃዳችሁ ተጨማሪ ጠባሳ እራሳችሁ ላይ አትጣሉ። ከህመማችሁ ለመንፃት መተው ያለባችሁን ነገር ተዉ፤ ስለወደፊት ህይወታችሁ የሚገዳችሁ ከሆነ እስራታችሁን ፍቱ፣ በእርግጥም ህይወትን በሙላት መኖር ካሻችሁ የይቅርታ ልብ ይኑራችሁ። ሸክማችሁን አራግፉ፣ ለደህንነታችሁ ዋስተና አስቀምጡ፣ በምርጫችሁ ወደፊትን ተመልከቱ፣ ኋላ ከቀረውና ከተበላሸው ይልቅ የሚመጣውና ማስተካከል የምትችሉት ጉዳይ ላይ አተኩሩ። አዎ! ጀግናዬ..! ካለፈው ስህተትህ በላይ በመጪው መልካም ጊዜ ላይ ተደገፍ፣ በበቀል ጊዜያዊ ደስታን ከማግኘት በተሻለ በይቅርታህ ዘላቂን ሰላምህን አትርፍ። የህይወት መልካም ገጠመኞችም ሆኑ አስከፊ ገፆች ማለፋቸው አይቀሬ ነው፤ ነገር ግን አልፈው በአዲስ ክስተት ለመተካት የእኛን ፍቃደኝነት ይፈልጋሉ። ስህተተን በስህተት፣ ጥፋትንም በጥፋት አታርመውና ትናንትህ ትናንት፣ ታሪክህም ታሪክህ እንዲሆን ፍቀድለት። ባለፈው መጠፎ ጥላ የአሁኑን ውዱን ብሩህ ጊዜህን አታጨልመው። ካለፈው ትናንትህ በላይ ዛሬ ያለህበት አሁንህ የላቀ ዋጋ እንዳለው አስታውስ፣ ካለፍከው ታሪክ በላይ ከአሁን ቦሃላ የምትሰራው ታሪክ የህይወትህ ወሳኝ ምዕራፍ እንደሆነ ተገንዘብ። ✍️@israelalexe
Show all...
ዓለም እኮ ሰፊ ነች!💃 ዓለም እናንተ ስታጠቧት ትጠባለች፣ ሰፊነቷን ስትቀበሉና ስታዩላት ደግሞ በስፋቷ ልክ ታስተናግዳችኋለች፡፡ ☺ ቀና በሉ! ከሰፈራችሁ ውጪ ሌላ ሰፈር አለ! ከቡድናችሁ ውጪ ሌላ ቡድን አለ! ከመስሪያ ቤታችሁ ውጪ ሌላ መስሪያ ቤት አለ! በአካባቢች ካሉት ሰዎች ውጪም ሌሎች ሰዎች አሉ! አሁን ካላችሁ የገቢ ምንጭ ውጪ ሌላ የገቢ ምንጭ አለ! ከፈጣሪ የተሰጣችሁን ሰፊ ዓለማችሁን አታጥብቧት፡፡ ምርጫችሁ አንድና አንድ ብቻ እንደሆነ ስታስቡና በዚያ ዙሪያ ብቻ ስትሽከረከሩ ዓለማችሁ እሱ ብቻ እስከሚመስል ድረስ ትጠባላችሁ፡፡
Show all...
ውለታ ዋይ! ፨፨//////፨፨ ያለማንም አስገዳጅነት ገብቶሽ፣ ተረድተሽ፣ እያወቅሽ ለእራስሽ ውለታ ዋይ። ውለታሽ እንደማይመለስ አውቀሽ የምታደርጊው ነው፤ ውለታሽ እራስሽን ስለምትወጂ፣ ለእራስሽ ስለምታስቢና ስለምታዝኚ የምትፈፅሚው ተግባር ነው። እራሱን ለሚወድ ሰው ውለታ ደጋግሞ አስቦ፣ አውጥቶ አውርዶና ነገሮችን መርምሮ ለእራሱ የሚያደርገው ነገር አይደለም። እራስሽን የምትወጂ ከሆነ ለእራስሽ ውለታ ከመዋል በላይ ለእራስሽ ባለሽ ፍቅር እራስሽን ትማርኪያለሽ፤ ለእራስሽ በምትሰጪው ቦታ ክብርሽን ትገለጪያለሽ፣ ስለእራስሽ በምታስቢው ሃሳብ ህይወትሽን ታጣፍጪያለሽ። እግዚአብሔር አምላክ ለማንም ሳይሰጥ ላንቺ ብቻ የሰጠሽ ውድ ስጦታ አለ፣ ይህ ስጦታ ውዷ እራስሽ ነሽ። በማንነትሽ የምታዝኚበት ጊዜ አብቅቷል፣ በአንቺነትሽ አንገት የምትደፊበት፣ የምታቀረቅሪበት ወቅት ላይመለስ ሔዷል። አዎ! ጀግኒት..! ከስጦታዎች ሁሉ ለላቀው፣ ከአበርክቶት ሁሉ ለገዘፈው፣ ካለሽ ንብረትና ዝና በላይ ለሆነው ሰውነትሽ ውለታ ዋይ፤ ለንፁሁ ማንነትሽ በጎ ነገር አድርጊ፤ አምላክሽ መርጦ በሰጠሽ አንቺነትሽ ኩሪ፣ ተመቻቺ፣ ደስተኛ ሁኚ። መጥቶ ስላለመሔዱ እርግጠኛ የማትሆኚለትን ሰው በመጠባበቅ የተሰጠሽን ትልቅ ፀጋ አታርክሺ፤ ነገ ስላለመጥፋቱ ለማትተማኚበት ንብረትና ዝና ውዱን ሴትነትሽን አሳልፈሽ አትስጪ። በገዛ ባለቤቱ ያልተከበረ ማንም ቢመጣ ሊያከብረው አይችልም፤ የተሰጠውን ስጦታ በአግባቡ ያልጠቀመ ለሚያጣው ነገርም ማንንም መውቀስ አይችልም። ክብርሽ ልኬትሽ እንደሆነ አስታውሺ።  አዎ! ጀግናዬ..! የወዳጅህን ደጅ እየጠናህ፣ ከአካባቢህ ውለታ እየጠበክ፣ እራስህን እራሱን መርዳት እንደማይችል ምስኪን እየተመለከትክ የውድቀትህን ጊዜ ቆመህ አትጠብቅ። ያንተ ችግር ባንተ ልክ ግድ የሚሰጠው ሰው የለም። ለእራስህ ካንተ በላይ ማንም እንደማያዝንልህ እወቅ። አውቆ እራሱን የሚጎዳ ሰው የለምና ለእራስህ የምታደርገውን የትኛውንም ጠቃሚ ነገር እንደውለታ ሳይሆን እንደ ግዴታ ተመልከተው። ባለመጠንቀቅህ አደጋ ውስጥ ብትገባ፣ ባለማስተዋልህ ከነበረህ ክብር አንሰህ ብገኝ፣ ሳይገባህ ደጋግመህ ብታጠፋ ከገባህበት አደጋ የመውጣቱ፣ የነበረህን ክብር የማስመለሱና ከጥፋትህ የመማሩ ሃላፊነት የእራስህ ነው። ቀና በል፣ እራስህን ተመልከት፣ እራስህን ተንከባከብ፣ እራስህን ጠብቅ፣ ለክብርህ ከማንም በላይ ግድ ይኑርህ። ✍️@israelalexe
Show all...
ሲደብራችሁ ህይወታችሁ እንደዛው ሆኖ የሚቀር ይመስላችኋል አይደል??.. የማትቀየሩ.. ሁኔታው የማያልፍ.. ደግማችሁ የማትስቁ ይመስላችኋል አ?.. እንደዛ አይነት ቀኖች ደግሞ መከሰታቸው የማይቀር ነው ስለዚህ ለነዛ ቀናቶች ቀድማችሁ ተዘጋጁባቸው.. እያሟረታችሁ እንዳይመስላችሁ በራሳችሁ ላይ.. ከለቅሶ በኋላ ሳቅ እንዳለ የሚያወራ ሰው ካለቀሰ በኋላ ስቆ ስለሆነ ያለማልቀሻዋ ቀን መሳቂያዋ እንደማትመጣ ጠንቅቆ ያውቃል.. እኛ ዝግጁ እስከሆንን.. እስከበረታን.. ከአምላካችን ጋር ግንኙነት እስካላቆምን ድረስ የማናሸንፈው ችግር.. የማንወጣው መአት.. የማንፈነቅለው የስኬት ድንጋይ አይኖርም.. መኖርማ አለብን የምር ❤❤
Show all...
አቅማችሁን አስመልሱ! ፨፨፨፨///////////፨፨፨፨ ፈጣሪ የሰጣችሁ ማንነትና አቅም ምንም ነገር ለማለፍ የሚያስቸል ማንነትና አቅም ነው፡፡ ይህንን አቅማችሁን ለማወቅ ከፈለጋችሁ በብዙ ሁኔታዎች ከመጠላለፋችሁ በፊት የነበራችሁ ንቁ ማንነት፣ ትጋት፣ ግለትና ቀኑን የመጋፈጥ አቅም ለማስታወስ ሞክሩና ትደርሱበታቸላችሁ፡፡  ያንን የነበራችሁን አቅምና ጉልበት ከሚቦረቡሩና አቅመ-ቢስ ከሚያደርጉ ሁኔታዎች ራሳችሁን ካልጠበቃችሁ ቀስ በቀስ፣ “እኔም እንደዚህ ሁንኩኝ ???!!!" እስከምትሉ ድረስ የማትፈልጉት የወረደ የስሜት አቅመ-ቢስነት ደረጃ ላይ ራሳችሁን ታገኙታላችሁ፡፡ በዚህም መሰረት የየእለት አቅማችሁን የሚወስኑ ሶስት ሁኔታዎች፦ 1.  ትኩረት ትኩረታችሁን የጣላችሁበት ነገር በስሜታችሁ ላይ ከፍተኛ ጫናን ያስከትላል፡፡ ለምሳሌ በስራ ቦታ ወይም በምትኖሩበት አካባቢ በቅርባችሁ ካሉ ሰዎች መካከል ጥሩ ያልሆነን ነገር የሚያሳይዋችሁ ሰዎች ካሉና ሁል ጊዜ ትኩረታችሁን በእነሱ ላይ የምታደርጉ ከሆነ ቀስ በቀስ በዚያ አካባቢ የመሆን አቅማችሁ እየደከመ መሄዱ አይቀርም፡፡ በዚያ ምትክ ትኩረታችሁን ከእነሱ ላይ ስታነሱና ወደሌሎች ስታደርጉ አቅማችሁ ይመለሳል፡፡  2.  መጠባበቅ ከምን አይነት ሰው ምን አይነት ነገር እንደምትጠብቁ (Expect እንደምታደርጉ) የመለየትን ብልሃት ካላደበራችሁ የምትጠባበቁትን ነገር በማታገኙበት ጊዜ ሁሉ ስሜታችሁ እየደተጎዳና አቅም እያጣችሁ ትሄዳላችሁ፡፡ አብዛኛው የግንኙነት ቀውስ መንስኤው ከመጠባበቅ (Expectation) የሚመነጭ ነው፡፡ ከአንድ ሰው የምትጠብቁትን ነገር ሚዛናዊ ስታደርጉ ስሜታችሁ ከመጎዳት አቅማችሁ ደግሞ ከመድከም ይጠበቃል፡፡ 3.  ለውጥ ራሳችሁን አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ስታገኙት አቅም ከሚያሳጣችሁ ነገር አንዱ፣ መለወጥ የሚገባችሁንና የምትችሉትን ነገር በሚገባ ያለማወቅ ጉዳይ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሁኔታዎችን መለወጥ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሰዎችን መለወጥ፣ ወይም ደግሞ ምናልባት መለወጥ የሚገባን ራሳችንን ወይም አመለካከታችንን የሚሆንበት ጊዜ አለ፡፡ ለመለወጥ ከማትችሉት ሁኔታ ጋር መታገል፣ ፈጽሞ ለመለወጥ ፈቃደኝነቱ ከሌለው ሰው ጋር ጊዜን ማባከንና የመሳሰሉት ሁኔታዎች አቅምን ያደክማሉ፣ ሕይወትን ያዘባርቃሉ፣ ሰላምንም ይነሳሉ፡፡ በእነዚህ ሶስት ነገሮች ዙሪያ ብልሃትንና ጥበብን በማዳበር ምን ያህል ኃይል፣ ጉልበትና የመኖር ጉጉት እንደሚጨመርላችሁ አስቡት @israelalexe
Show all...