cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ትምርት ሚንስትር

Show more
Advertising posts
9 887
Subscribers
+224 hours
+427 days
+8730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ተጨማሪ ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በፖሊስ ድብደባ ተፈፀመባቸው። 10 ተማሪዎች መታሰራቸው ተገልጿል። ተማሪዎቹ የተራዘመ የመመረቂያ ግዜን በመቃወም ሰልፍ የወጡ ሲሆን ፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ እና እንግልት እንደፈፀሙባቸው ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ተማሪዎቹ ዛሬ ረፋድ 4:00 ሰዓት ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ አሪድ ግቢ ተነስተው ያሏቸውን ቅሬታዎች ለማሰማት ወደ መቐለ ከተማ ጎዳናዎች ሰላማዊ ሰልፍ አካሒደዋል። ተማሪዎቹ በተለያዩ ምክንያቶች ለዓመታት ትምህርታቸው ሲስተጓጎል ቆይቶ ዘንድሮ ለመመረቅ እየተጠባበቁ የነበረ ቢሆንም፤ ዩኒቨርሲቲው ሌላ ተጨማሪ ዓመት መማር እንደሚጠበቅባቸው መግለፁን ተከትሎ ተማሪዎቹ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ መገደዳቸውን ጠቁመዋል። ፖሊስ ጥይት በመተኮስ፣ በድብደባ እና በአፈሳ ሰልፉን በኃይል መበተኑን ተማሪዎቹ የገለፁ ሲሆን በተፈፀመባቸው ድብደባ አካላዊ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች መኖራቸው ታውቋል። 10 ተማሪዎችም መታሰራቸው ተገልጿል። #ዶቼቬለ ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇 ╔═══════════╗ https://t.me/temertminister https://t.me/temertminister
Show all...
👍 16 8🥰 3
"ዲግሪ ለመያዝ ስምንት ዓመት መቆየት ፍትሃዊ አይደለም! በዚህ ዓመት ልንመረቅ ይገባል!" የሚሉ ጥያቄዎችን የያዙ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዛሬ ጠዋት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው ተሰምቷል። "በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የባከነውን የትምህርት ጊዜ ለማካካስ የሚሰጠው ትምህርት የፌደራል መንግሥት ባሰቀመጠው መመሪያ መሰረት እንዲከናወን" የዩኒቨርሲቲውን አስተዳደር በተደጋጋሚ መጠየቃቸውን ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ተማሪዎቹ በጥር 2017 ዓ.ም ሊመረቁ እንደሚችሉ በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች እንደተነገራቸው ተሰምቷል፡፡ በክልሉ ከተማ በተለምዶ የተባበሩት የሚባለው አካባቢ ጥያቄዎቻቸውን ሰላማዊ በሆነ መንገድ እያቀረቡ የነበሩት ተማሪዎቹ በጸጥታ ኃይሎች መበተናቸው ተነግሯል። ፖሊስ አንዲት ሴትን (ተማሪ) ገፍትሮ አስፓልት ላይ ሲጥላት የሚያሳይ ቪዲዮ በማኅበራዊ ትስስር ገፆች ሲዘዋወር ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተመልክቷል፡፡ በተማሪዎቹ ላይ ጉዳት መድረስ አለመድረሱን ማረጋገጥ አልቻልንም፡፡ በጉዳዩ ላይ መቐለ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ትምህርት ሚኒስቴር የሚሉትን ወደፊት የምናደርሳችሁ ይሆናል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇 https://t.me/temertminister https://t.me/temertminister
Show all...
👍 6
👍 15👎 1 1
https://t.me/notcoin_bot?start=r_573809_33911258 🎁 +2.5k Notcoin as a first-time gift 🎁🎁🎁 +50k Notcoin if you have Telegram Premium @PremiumBot
Show all...
Notcoin

Probably nothing @notcoin

👍 5 1
- TONCOIN የምትሰሩበት NOTCOIN ቴሌግራም ለ ማስተዋወቅ አሁን ላይ በነፃ መሰብሰብ ትችላላቹ - ከ APRIL በፊት የተለያዩ ትዛዞችን በመፈፀም ከ 100ሺ -250ሺ NOTCOIN እየሰበሰባቹ BOOSTS እየገዛቹ በ TAP TAP እንዲሁም AUTO TAP ON በማረግ ከ BRONZE ወደ SILVER ከዛ GOLD እያደጋቹ መምጣት እና NOTCOIN መሰብሰብ ነው። - ክፍያ ስለሌለው በትርፍ ሰዓታቹ ሞክሩት ማብቂያው ጊዜ ትንሽ ስለሆነ ፍጠኑ!! - TELEGRAM PREMIUM የሆናቹ EARN ሚለው ውስጥ በመግባት TELEGRAM PREMIUM ሚለውን ነክታቹ 3Million NOTCOIN ማግኘት ትችላላቹ - NOTCOIN ያልጀመራቹ በዚ ሊንክ ትገባላቹ ⭐ Start ⭐ Invite your friends and get bonuses for each invited friend! 🎁 Your referral link: https://t.me/notcoin_bot?start=r_573809_33911258 - LINK ከነካችሁ በኋላ Let's Go ሚለውን ነክታቹ መጀመር ነው!! * ቴሌግራም በቅርቡ ለቻናል ባለቤቶች ለማስታወቂያ የሚከፍለውም በእነዚሁ በTONCOIN እና NOTCOIN ይሆናል። ⭐  Start ⭐
Show all...
👍 5 2👎 1
#MoH በውጤታችሁ ላይ ጥያቄ ያላችሁ የጤና መስክ ተመዛኞች ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ። ባለፈው ወር በትምህርት ሚኒስቴር እና በጤና ሚኒስቴር በጋራ የተሰጠውን የመውጫ እና የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዳችሁ #የጤና_መስክ ተመዛኞች ውጤት ከመጋቢት 04/2016 ዓ.ም ጀምሮ ኦንላይን እየተመለከቱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በውጤታችሁ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎች ያላችሁ ተመዛኞች ከመጋቢት 04/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት በስልክ ቁጥር 0118275936 በመደወል ወይም በኢሜይል አድራሻ [email protected] ብቻ ሙሉ ስም፣ ሙያ እና የፈተና መለያ ቁጥር (Username) በማስገባት ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡ የማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ ተመዛኞች ስም ዝርዝር ለክልል የጤና ተቆጣጣሪ አካላት የሚላክ በመሆኑ በየክልላችሁ በመሔድ የሙያ ሥራ ፍቃድ ማውጣት እንደምትችሉም ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡ 🙏Share share🙏 👇👇ለተጨማሪ መረጃ👇👇 https://t.me/temertminister https://t.me/temertminister
Show all...
👍 13 3
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሐኪሞች በመድኃኒት እጥረት ምክንያት ሕክምና መስጠት መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡ በሆስፒታሉ የመድኃኒት አቅርቦትና የሕክምና መስጫ መሣሪያዎች እጥረት ምክንያት ተገቢውን ሕክምና መስጠት መቸገራቸውን በሆስፒታሉ የሚሠሩ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የሕክምና ባለሙያዎች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ በተለይ ዝቅተኛ የገቢ ምንጭ ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ሕክምና ማግኘት አለመቻላቸውን የገለፁት ባለሙያዎቹ፤ "በአሁኑ ወቅት የመድኃኒት ዋጋ መወደድና ዩኒቨርሲቲው የተመደበለት በጀት አነስተኛ መሆን" ዋነኛ የችግሩ መንስዔ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም በጣም በቅናሽ ዋጋ ማግኘት የሚቻሉ እንደ አልኮል፣ መርፌና ምላጭ የመሳሰሉ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች ታካሚዎች ከሆስፒታሉ ውጭ ከሚገኙ ፋርማሲዎች እንዲገዙ በማድረግ ለከፍተኛ ወጪ እየተዳረጉ መሆኑን የሕክምና ባለሙያዎቹ ጠቁመዋል፡፡ የመድኃኒት ዋጋ በእጥፍ መጨመሩ፣ እንዲሁም የሁሉም የዩኒቨርሲቲዎች በጀት 50 በመቶ እንዲቀነስ መደረጉ ለመድኃኒት ግዥ የሚሆን በጀት እጥረት እንዲከሰት ማድረጉን የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጀማል አባፊጣ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡ ሪፖርተር የጤና ሚኒስቴርን ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካለትም፡፡ #ሪፖርተር 🙏Share share🙏 👇👇ለተጨማሪ መረጃ👇👇 https://t.me/temertminister https://t.me/temertminister
Show all...
2👍 1👏 1
Ministry of education®, [3/16/24, 6:30 PM] [Posted by 𝐄𝐥𝐢𝐲𝐚𝐬 🌒] [🖼 አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ትናንት መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ከኢትዮጰያ ንግድ ባንከ ኤ.ቲ.ኤም ማሽን የሌላቸውን ገንዘብ ወጪ ያደረጉ የተቋሙ ተማሪዎች በፍጥነት በቅሊንጦ ቅርንጫፍ በመቅረብ እንዲመልሱ አሳስቧል። ወጪ ያደረገውን ገንዘብ የማደመልስ ተማሪ ላይ ዩኒቨርሲቲው አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድና ተማሪዎቹ በሕግ እንደሚጠየቁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። በተመሳሳይ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከትክክለኛ ሒሳባቸው ውጪ ገንዘብ ወጪ ያደረጉ ተማሪዎች የራሳቸው ያለሆነውን ገንዘብ በአስቸኳይ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የትኛውም ቅርንጫፍ በመሔድ ተመላሽ እንዲያደርጉ በጥብቅ አሳስቧል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲስተም ችግር ምክንያት ዛሬ የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሞት እንደነበር መግለፁ ይታወቃል። 🙏Share share🙏 👇👇ለተጨማሪ መረጃ👇👇 https://t.me/Temhert_Minister1 https://t.me/Temhert_Minister1 https://t.me/Temhert_Minister1] አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ትናንት መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ከኢትዮጰያ ንግድ ባንከ ኤ.ቲ.ኤም ማሽን የሌላቸውን ገንዘብ ወጪ ያደረጉ የተቋሙ ተማሪዎች በፍጥነት በቅሊንጦ ቅርንጫፍ በመቅረብ እንዲመልሱ አሳስቧል። ወጪ ያደረገውን ገንዘብ የማደመልስ ተማሪ ላይ ዩኒቨርሲቲው አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድና ተማሪዎቹ በሕግ እንደሚጠየቁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። በተመሳሳይ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከትክክለኛ ሒሳባቸው ውጪ ገንዘብ ወጪ ያደረጉ ተማሪዎች የራሳቸው ያለሆነውን ገንዘብ በአስቸኳይ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የትኛውም ቅርንጫፍ በመሔድ ተመላሽ እንዲያደርጉ በጥብቅ አሳስቧል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲስተም ችግር ምክንያት ዛሬ የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሞት እንደነበር መግለፁ ይታወቃል። 🙏Share share🙏 👇👇ለtemertminister @temertminister @temertminister
Show all...
👍 3
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትላንት መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ምሽት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካጋጠመው የሲስተም ችግር ጋር በተገናኘ የማይገባ ገንዘብ ከኤ.ቲ.ኤም (ATM) ማሽን ወጪ ያደረጉየዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት ካሉ ወደ ባንኩ ቅርንጫፎች በመሄድ ገንዘቡን ተመላሽ እንዲያደርጉ አሳስቧል። 🙏Share share🙏 👇👇ለተጨማሪ መረጃ https://t.me/temertminister https://t.me/temertminister
Show all...
#Update ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውና ሌሎችም የተቋሙ አካላት በካሽ የወሰዱትን እና ለሌላ ሶስተኛ ወገን ያስተላለፉትን ገንዘብ እንዲመልሱ አስጠነቀቁ። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲስተም ላይ ካጋጠመው ችግር ጋር በተያያዘ በርካቶች ገንዘብ ያለገደብ ሲያወጡና ሲያስተላልፉ ነበር። በተለይም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አካላት ትላንት ካጋጠመው ችግር ጋር በተያያዘ ገንዘብ ወጭ ሲያደርጉና ወደ ሌላም ሲያስተላልፉ እንደነበር ተነግሯል። ይህንን ተከትሎ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ ያወጡና ያስተላለፉ እንዲመልሱ ተቋሞቻቸው እያሳሰቡ ይገኛሉ። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ባንኩ የተፈጠረዉን ችግር በተመለከተ ፦ * ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፤ * የመረጃ እና ደህንነት እንዲሁም ከሌሎች ከሚመለከታቸዉ ተቋማት ጋር በመሆን እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። በባንኩ የተፈጠረዉን የሲስተም መቋረጥ ምክንያት እንደ አጋጣሚ በመጠቀም ፦ ➡️ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ #በካሽ ወጭ ያደረጉና በማንኛዉም የባንኩ የድጅታል አማራጮች የተቀበሉ ➡️ ወደ 3ኛ ወገን ያስተላለፉ ተማሪዎች እና የዩንቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት የወሰዱትን እና የተላለፈላቸውም አካላት ገንዘቡን ተመላሽ እንዲያደርጉ አስጠንቅቀዋል። ገንዘቡ ተመላሽ የሚደረገው በአቅራቢያ ባለ የባንኩ ቅርንጫፍ መሆኑን አሳውቀዋል። ለመመለስ ፈቃደኛ ካልሆኑ ጉዳዩ የሕግ ተጠያቂነትን የሚያስከትል መሆኑንም እየገለጹ ናቸው። ገንዘብ ያወጡ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ስም ዝርዝር እንዳላቸውም ጠቁመዋል። 🙏Share share🙏 👇👇ለተጨማሪ መረጃ👇👇 @temertminister @temertminister
Show all...
👍 3