en
Feedback
ዶ/ር ዳዊት መስፍን (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት)

ዶ/ር ዳዊት መስፍን (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት)

Open in Telegram

**ጠቅላላ የማህፀንና ፅንስ ጉዳዬችን ማማከር** - ቅድመ ወሊድ - ስለ ወሊድ አገልግሎት - ስለ መካንነት ምርመራ እና ህክምና - በተለያዩ ምክንያቶች ከማህፀን ለሚወጣ ደም እና ፈሳሽ ምክንያና ህክምና - ለወር አበባ መዛባት ምክንያት እና መፍትሄ - ስለቅድመ ካንሰር ምርመራና የምክር አገልግሎት... 0911138054📞

Show more
5 833
Subscribers
-224 hours
-127 days
-4030 days
Posts Archive
👉 🚗 የመኪና ቀበቶ ላንቺ የሚጠቅሙሽ ሁለት አይነት ክፍሎች ያሉት ሲሆን እንኚህም የጭን ቀበቶ ክፍል (lap belt) እና የትከሻ ቀበቶ( shoulder belt) ተብለው ይታወቃሉ። ❓እንዴት አድርጌ የመኪና ቀበቶ ልታጠቅ❓ ⚠️ የታችኛውን የቀበቶ ገመድ ወይም የጭን ቀበቶ ወደፊት ከወጣው የሆድሽ ክፍል ታች ጭንሽ ላይ በሁለቱ በግራና ቀኝ የሚነኩ የዳሌ አጥንቶች ላይ አድርጊ ⚠️ በሰያፍ የሚደረገውን የቀበቶ ገመድ ከላይ በትከሻሽ ፊት ላይ ባለው ማጭድ በምትመስለው አጥንት (clavicle) መሀል ላይ በማሳረፍ እናም በደረትሽ መሀል ወይም በጡቶችሽ መሀል ወደታች አድርጎ ማሰር። ⚠️ ቀበቶው በምንም ሁኔታ ሊላላብሽ ወይም እጅግ በጣም ሊያጠብቅሽ አይገባም። ⚠️ ወንበርሽን በተቻለ አቅም ቀጥ ለማድረግ ሞክሪ ወደ ውሀላ አትዘቅዝቂው፤ ይህ የጭን ቀበቶሽ በአደጋ ጊዜ ማህፀንሽ ላይ ጫና እንዳይፈጥር እና አደጋ እንዳይፈጥር ይረዳል። ወንበርሽን ግን ሙሉ ለሙሉ ወደ ውሀላ ፈቀቅ አድርጊው ነገር ግን እግርሽ መርገጫዎቹን መርገጡን እርግጠኛ ሁኚ። ⚠️ ሁል ጊዜ እርጉዝ ሆነሽ መኪና ስትነጂ በደረትሽ አጥንት እና በመሪው መሀከል ያለው እርቀት 30 ሳንቲም ሜትር እና ከዛ በላይ በሆነ እርቀት ውስጥ መሆን አለበት። ነገር ግን መሪው ሆድሽን እንዳይነካሽ ወደ ደረትሽ አቅጣጫ አድርጊው። ⚠️ መኪናሽ በአደጋ ጊዜ የሚወጣ የአየር ፊኛ(Air bag) ካለው በአደጋ ጊዜ የሚወጣ እንዲሆን አድርጊው። ማስተዋል ያለብሽ 💥 ማንኛውም አደጋ ቢደርስ ትንሽም እንኳን ብቶን ፣ አንቺ ምንም የነካሽ ነገር እራሱ ባይኖር ሀኪምሽ ጋር ሄደሽ ምርመራ ማድረግ ተገቢ ነው። 💥 በቀን ከ5 እና 6 ሰዓት በላይ አታሽከርክሪ - መንዳት እራሱን የቻለ ድካም ስለሚያመጣ፤ በመሀል እረፍቶችን ውሰጅ በዛም ጊዜ እግሮችሽን አፍታቺ አወጣጥሪ ይህ እግርሽ እንዳያብጥ እና ደም መርጋትን ይቀንሳል። በመሀል በመሀልም ተመገቢ ፣ ፈሳሽም ውሰጂ 💥 አላስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር በመጨረሻዎቹ ወራት ላይ መኪና ባታሽከረክሪ መልካም ነው፤ ከ36 ሳምንት በውሀላ ደግሞ አለስፈላጊ ጉዞዎችንም መቀነስ ይኖርብሻል። 💥 ፅንሱ ጊዜው ገፍቶ ምናልባት መንዳት ከከበደሽ ሆድሽ ላይ ጫና ካለው፣ በትክክል መሪ ማዞር እና በእግር የሚረገጡትን በትክክል መንካት የሚከብድሽ ከሆነ - ያንቺና የልጅሽ ህይወት ስለሚበልጥ በፍፁም አትንጂ 💥 ማንኛውም አይነት የማቅለሽለሽ፣ የማስታወክ ፣ የማዞር፣ የመድከም ስሜት ካለሽ ወይም የጤናማነት ስሜት ካልተሰማሽ በፍፁም አትንጂ እየነዳሽም ከሆነ አቁሚ- ቅድሚያ ለህይወትሽ እና ለልጅሽ 💥 በተቻለሽ አቅም በፍጥነት አትንጂ፣ ፈጣን የሆኑ መጠማዘዞችንም አታድርጊ፣ 💥 በመጨረሻም በተቻለሽ አቅም ሀሳብሽን ከሚሰርቁ ነገሮች ለምሳሌ:- ስልክ እያወሩ ወይም text እየፃፉ መንዳት፣ የመኪናሽ ሬድዮ ወይም መዝናኛ እየነካኩ መሄድ፣ ሜካፕሽን እያስተካከልሽ መንዳት ፣ እየበላሽ ወይም እየጠጣሽ መንዳት ከመሳሰሉት ተጠበቂ።

💥የመኪና አነዳድ ጥንቃቄ ለእርጉዞች💥 👉 🚗 በእርግዝና ጊዜ ምንም ቢሆን ልጅሽ በማህፀንሽ ውስጥ የተጠበቀ ቢሆንም በመኪና በምትጓዢበት ጊዜ ግን ከመኪና ጥንቃቄዎች ውስጥ በቀዳሚነት የሚጠቀሰውን
+4
💥የመኪና አነዳድ ጥንቃቄ ለእርጉዞች💥 👉 🚗 በእርግዝና ጊዜ ምንም ቢሆን ልጅሽ በማህፀንሽ ውስጥ የተጠበቀ ቢሆንም በመኪና በምትጓዢበት ጊዜ ግን ከመኪና ጥንቃቄዎች ውስጥ በቀዳሚነት የሚጠቀሰውን የመኪና ቀበቶን መታጠቅን ምንጊዜም ቢሆን መዘንጋት የለብሽም።

🤰ብዙን ጊዜ የሆድ ድርቀት የሚከሰተው እርጉዟ ሴት 7 ወርን ስታልፍ ሲሆን ይህም ፅንሱ በከፍተኛ ፍጥነት እድገት የሚያሳይበት እና ጫና የሚያመጣበት ጊዜ ስለሆነ ነው። 🤰በእርግዝና ወቅት ከሌላ ጊዜው በተለየ አንዲት እናት ለሆድ ድርቀት የምትጋለጥበት ዋና ምክንያት ከእርግዝናው ጋር ተያይዞ በሚኖር የአካል ለውጥ እና የንጥረ ፈሳሾች (Hormones) ለውጥ ምክንያት ነው። 📌 በእርግዝና ጊዜ የሆድ ድርቀት እንዲኖር ከሚያደርጉ ዋና ዋና ምክንያቶች ውስጥ ጥቂቶቹ:- 🔥 በሰውነት ውስጥ ያለው የፕሮጀስትሮን (progesterone)የተባለው ንጥረ ቅመም በብዛት መገኘት የአንጀት አካል እንዲላላ እና ምግብ በዝግታ ረጅም ጊዜ እየቆየ እንዲዘዋወር ማድረግ እና ለድርቀት ማጋለጥ 🔥 በእርግዝና ጊዜ ሞቲሊን(motility) የተባለች የአንጀት እንቅስቃሴን የምትጨምር ንጥረ ቅመም መቀነስ 🔥 በእርግዝና ጊዜ በአንጀት ውስጥ ውሀ በከፍተኛ ሁኔታ ወደሰውነት መግባት ወይም መመጠጥ በዛም ምክንያት ሰገራ እንዲደርቅ መሆን 🔥 በእርግዝና ጊዜ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ - ከእርግዝናው እድገት ጋር እና ጫና በተያያዘ 🔥 በእርግዝና ጊዜ የምንወስዳቸው ንጥረ ነገሮች ውስጥ እንደ አይረን(iron) ፣ ካልሲየም(calcium) የመሳሰሉት ጥቅማቸው የጎላ ቢሆንም ለድርቀት የማጋለጥ ሁኔታ 🔥 እርግዝናው በገፋ ቁጥር አንጀት ላይ ያለው ጫና እየጨመረ መሄድ - ሰገራ አንጀት ውስጥ ለብዙ ጊዜ እንዲቆይ ማድረግ እና ለድርቀት ማጋለጥ 🔥 የነፍሰጡሯ አመጋገብ - አነስተኛ ፋይበር ባለው ምግብ መሞላትም ለሆድ ድርቀት እንደ ምክንያትነት ከሚጠቀሱ ነገሮች ውስጥ ይጠቀሳል። ፋይበር ያላቸው ምግቦች የሚባሉት እንደ :- ባቄላ፣ አቮካዶ፣ ማንኛውም የአትክልትና ፍራፍሬ አይነት( ብሮኮሊ፣ አፕል፣ ሙዝ፣ ምስር፣ ስንዴ፣ ፋንዲሻ፣ ድንች፣ ጎመን ፣ ቆስጣ ፣ ሰላጣ…የመሳሰሉት)። 🔥 በእርግዝና ጊዜ ፈሳሽ በበቂ ሁኔታ አለመጠጣት 👉 ስለዚህ ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች የሆድ ድርቀት ሲኖር - ሰገራ ለመውጣት መቸገር ፣ እና ብዙ ማማጥ ሊያስከትል ይችላል። 👉 ይህ ብዙ ሰገራን ለማውጣት የሚደረግ ማማጥ ደግሞ በሰገራ መውጫ አካባቢ ያሉ ደምን ወደ ልብ የሚመልሱ ቧንቧዎች ላይ ጫና እንዲኖር ማድረግ ያመጣል ይህም የፊንጢጣ እብጠት/ኪንታሮት (Haemorrhoids) ሊያስከትል ይችላል።(👌 በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የፊንጢጣ እብጠት - ኪንታሮት ( Haemorrhoids) https://t.me/DrDawitMOBGYN/274) 📌 የሆድ ድርቀትን እንዴት እንቀንስ? ⁃ 🔑 ፋይበር የበዛበትን ምግብ አዘውትሮ መመገብ። የታሸጉ ምግቦችን የምትመገቢ ከሆነ የፋይበር ምግብ መጠን በቀን 25 ግራምና ከዛ በላይ መሆን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው። ⁃ 🔑 ፈሳሽ የመውሰድ አቅማችንን በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር ⁃ 🔑 በተቻለን አቅም በእርግዝና ጊዜ ሊደረጉ የሚችሉ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ - በሀኪም እና ባሰልጣኝ በተደገፈ ሁኔታ ( 👌 እንቅስቃሴ በእርግዝና ጊዜ - https://t.me/DrDawitMOBGYN/47 ) https://youtu.be/Tl7HvYoI-5E ⁃ 🔑 ከላይ የተጠቀሱት የህክምና መንገዶች ለውጥ ካላሳዩ በሀኪም ትዓዛዝ ብቻ! የሚታዘዙ መድሀኒቶች ስለሚኖሩ የማህፀንና ፅንስ ሀኪም ማማከሩ ተገቢ ነው። እነኚህም መድሀኒቶች በህክምናው እንደሚከተለው ይከፈላሉ :- bulk forming agents, stool softeners , laxatives(lubricant, osmotic and stimulant) 🌼መልካም ጊዜ🌼

💥የሆድ ወይም የሰገራ ድርቀት በእርግዝና ጊዜ💥 📈📊ጥናቶች እንደሚያሳዩት በእርግዝና ወቅት ከ 11 እስከ 38% የሚሆኑት ነፍሰጡር እናቶች የሆድ ድርቀት የሚያጋጥማቸው ሲሆን ያም ማለት የሰገራ
+4
💥የሆድ ወይም የሰገራ ድርቀት በእርግዝና ጊዜ💥 📈📊ጥናቶች እንደሚያሳዩት በእርግዝና ወቅት ከ 11 እስከ 38% የሚሆኑት ነፍሰጡር እናቶች የሆድ ድርቀት የሚያጋጥማቸው ሲሆን ያም ማለት የሰገራ መቆየት ወይም ደግሞ ሰገራን ማሶጣት መቸገርን የመሳሰሉትን ያካትታል።

🌼🌼እንኳን አደረሳችሁ!🌼🌼 አዲሱ አመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ እና የብልፅግና ይሁንልን!! አገራችን ኢትዮጵያ🇪🇹 ሰላም የምትሆንበት ሰርተን የምናድግበት አመት ይሁንልን!! አሜን!!🙏�
🌼🌼እንኳን አደረሳችሁ!🌼🌼 አዲሱ አመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ እና የብልፅግና ይሁንልን!! አገራችን ኢትዮጵያ🇪🇹 ሰላም የምትሆንበት ሰርተን የምናድግበት አመት ይሁንልን!! አሜን!!🙏🏽🙏🏽 ዶ/ር ዳዊት መስፍን (የማህፀንና ስፔሻሊስት)

ጥያቄ ፣ ሀሳብ እና አስተያየት ካለዎ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇ይጫኑ!! https://t.me/+9xiri5o68zZkNGM0
ጥያቄ ፣ ሀሳብ እና አስተያየት ካለዎ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇ይጫኑ!! https://t.me/+9xiri5o68zZkNGM0

👉 በእርጉዝ እናቶች ላይ ጠንከር ብሎ ይምጣ እንጂ ይህ የፊንጢጣ እብጠት በሁሉም ሰው ላይ ሊከሰት የሚችል ህመም ነው። ❓❓ለምንድን ነው የሚከሰረው❓❓ 👉 እርግዝናሽ ጊዜው በጨመረ ቁጥር ወደ ማህፀን ዙሪያ እና ወደ ፅንሱ አካባቢ የሚሄደው የደም ፍሰት ከወትሮው በተለየ ይጨምራል። በተጨማሪም ፅንሱ በታችኛው የአንጀትሽ ክፍል ላይ ከፍተኛ የሆነ ጫና ማሳድር ይጀምራል፤ ይህ የደም መመለስን እና ለሆድ ድርቀት እንደ ምክንያትነት ሊጠቀስ ይችላል። 👉 ከሰገራ መውጫ የአንጀት ክፍል (Rectum and anus) ከሚባሉት ክፍሎች ደም ወደልብ የሚመልሱ የደም ቧንቧዎች አንጀት ላይ እየተፈጠረ ባለው ጫና ምክንያት ከፍተኛ የሆነ ግፊት ይፈጠራል፤ ይህም በፊንጢጣ መውጫ ላይ ከፍተኛ የሆነ ደም የቋጠሩ እብጠቶች እንዲኖሩ ያደርጋል። 👉 ይህ ሁሉም እናቶች ላይ የሚከሰት ሳይሆን በተለይ የሰገራ ድርቀት እና ሽንት ቤት ብዙ የሚያስምጣቸው እርጉዞች ላይ በርትቶ ይከሰታል። 👉 ስለዚህ የሆድ ድርቀት ከፍተኛ በሆነ ሁኔታ ለፊንጢጣ እብጠት(Haemorrhoid) የማጋለጥ እድሉ ከፍተኛ ነው። (በእርግዝና ላይ ስለሚከሰት ሆድ ድርቀት ምንነት እና መፍትሄዎች ከ2 ቀን በውሀላ በዚሁ ዋናው የቴሌግራም ቻናል ላይ https://t.me/DrDawitMOBGYN ይጠብቁ።) 💥የህመሙ ምልክቶች💥 📌 የፊንጢጣ መውጫ ላይ እብጠት ፤ ያም ከፍተኛ የሆነ የህመም ስሜት ያለው 📌 ቦታው ላይ ማሳከክ እና ማቃጠል 📌 ሰገራ ሲወጣ ከፍተኛ የሆነ ህመም አንዳንዴም ደም መኖር 📌 ህክምና ካልተገኘ ደግሞ :- ከፍተኛ የሆነ ኢንፌክሽን መፈጠር፣ የደም መርጋት እና የሰገራ መውጫ መውጣት ሊያመጣ ይችላል። ❓❓ህክምናው ምንድን ነው❓❓ 🔑 የመጀመሪያው እና ዋነኛው ህክምና በውስጣቸው ብዙ ፋይበር ያላቸውን ምግቦች መመገብ ማዘውተር ነው። እነኚህም:- አቮካዶ፣ ብርቱካን፣ አፕል፣ ሙዝ (ፍራፍሬዎች በብዛት) ፣ ጎመን፣ አተር፣ ምስር፣ የአበባ ጎመን፣ ባቄላ፣ ስኳር ድንች፣ እና የመሳሰሉትን መመገብ ድርቀትን ይከላከላል 🔑 በተቻለሽ መጠን ብዙ ፈሳሽ መጠጣት ይህ ድርቀትን ይከላከላል 🔑 ወደ መፀዳጃ ቤት የምንሄድበትን ጊዜ በቀን ውስጥ በመወሰን ሰውነታችንን ማለማመድ 🔑 ኪሏችንን ለመቀነስ መሞከር 🔑 ለረጅም ሰዓት አንድ ቦታ አለመቀመጥ ፤ ይህ የደም ቧንቧዎቹ ላይ ያለውን ጫና ይቀንስልናል 🔑 ቀዝቃዛ በረዶ ቦታው ላይ ማድረግ ይህ የደም ቧንቧዎቹ እንዲኮማተሩ እና ህመም እንዲቀንስ ያደርጋል። 🔑 በቀን ሶስት ጊዜ ለ10 ደቂቃ ያክል በጣም በማያቃጥል ለብ ባለ ውሀ ውስጥ ቁጭ ማለት 🔑 ብዙን ጊዜ የፊንጢጣ እብጠትን የሚያባብሰው ነገር የሆድ ድርቀት ስለሆነ በምግቡ የማይስተካከል ከሆነ ሰገራን የሚያለሰልስ መድሀኒት ሀኪምሽ ሊፅፍልሽ ይችላል፤ ይህም ማማጥን ስለሚቀንስ እብጠት እንዲቀንስ ወይም እንዳይኖር ያደርጋል። ( እነኚህ መድሀኒቶች የሰውነትሽን ፈሳሽ በሰገራ መልክ ስለሚያወጡ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው እና በሀኪም ትዓዛዝ ብቻ መወሰድ ይኖርባቸዋል።) 🔑 በታቻለ አቅም ሰገራን ለማፅዳት ለስለስ ያሉ ሶፍቶችን ፣ ውሀን ወይም baby wipes የመሳሰሉትን መጠቀም መልካም ነው። 🔑 በተቻለ መጠን በእርግዝነ‍ኣ ጊዜ የሚመከሩትን የሰውነት እንሴዎች ማድረግ ፤ ይህ የሆድ ድርቀትን ይቀንሳል። 🔑 በተጨማሪም ሀኪምሽ በፊንጢጣ አካባቢ የሚፈጠር ማቃጠል እና ማሳከክ ስሜት ካለ የሚፅፍልሽ የሚቀባ ክሬም ሊኖር ይችላል ፤ በተጨማሪም በፊንጢጣ የሚገባም መድሀኒት ሊፃፍልሽ ይችላል። 🍀መልካም ዓለተ ሰንበት🍀

💥በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የፊንጢጣ እብጠት ( Haemorrhoids) 💥 👉 ይህ በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የፊንጢጣ እብጠት ከ25 - 35% የሚሆኑ እርጉዝ እናቶች ላይ ይከሰታል። በአንዳንድ የ
+1
💥በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የፊንጢጣ እብጠት ( Haemorrhoids) 💥 👉 ይህ በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የፊንጢጣ እብጠት ከ25 - 35% የሚሆኑ እርጉዝ እናቶች ላይ ይከሰታል። በአንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ በተለይ ከሶስተኛው መንፈቅ በውሀላ ይህም ማለት ከ 28ሳምንት በውሀላ እስከ 85% የሚሆኑት እርጉዞች ላይ ሊከሰት እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ።

ጥያቄ ፣ ሀሳብ አስተያየት ካለዎ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇ይጫኑ!! https://t.me/+9xiri5o68zZkNGM0
ጥያቄ ፣ ሀሳብ አስተያየት ካለዎ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇ይጫኑ!! https://t.me/+9xiri5o68zZkNGM0

❓❓ለምንድን ነው በእርግዝና ጊዜ ወገብ የሚያመው❓❓ 👉 ብዙን ጊዜ በእርግዝና ጊዜ የወገብ ህመም በተረገዘው ፅንስ እድገት ምክንያት የሚከሰት ነው። ልጅሽ ባደገ ቁጥር ወገብሽን እያጠፈው በሆድሽ ላይ የሚገኙትን ጡንቻዎች እያሳሳ እያሳሳ እና አቋቋምሽን እየቀየረው ይመጣል ይህም የታችኛው የወገብሽ ክፍል ላይ ጫና እንዲበዛ ያደርጋል። 👉 ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በእርግዝናው ምክንያት የሚፈጠር የሰውነት ክብደት መጨመር ስለሚኖር ይህም በራሱ ወገብ አካባቢ ያሉ መገጣጠሚያዎች ላይ ተጨማሪ ጫና እንዲፈጠር ይሆናል፤ እነኚህ ተደማምረው የወገብ ህመም ስሜት እንዲኖርሽ ያደርጋል። 👉 በመጨረሻዎቹ የመውለጂያ ጊዜያት እና በወሊድ ጊዜ ደግሞ ሰውነታችን የሚያመነጨው ሪላክሲን(relaxin) የተባለው ሆርሞን በዳሌ አካባቢ ያሉ መገጣጠሚያዎች ከወትሮ በተለየ መሳሳብ እና መለጠጥ እንዲችሉ ያደርጋል ይህም በራሱ በታችኛው የወገብ ክፍል ላይ የህመም ስሜት እንዲኖር ያደርጋል ማለት ነው። ❓❓እንዴት የወገብ ህመምን መከላከል ወይም መቀነስ እችላለሁ❓❓ 👉 🤔 ማስተዋል ያለብሽ ነጥቦች! 🔑 ከመሬት የተቀመጠ እቃ ስታነሺ ቁጢጥ ብለሽ ይሁን ወገብሽን ቀጥ አድርጊው 🔑 ከባድ እቃዎች በፍፁም አታንሺ 🔑 ወደ ውሀላ እቃ ለማንሳት ስትፈልጊ ወገብሽን አታዙሪ፤ እግሮችሽን በመጠቀም ለመዞር ሞክሪ 🔑 የምታደርጊያቸው ጫማዎች ከፍ ያለ ሶል ያላቸው መሆን የለባቸውም በጣምም ለጥ ያሉ መሆን የለባቸው፤ የሚደሉ እና የስፖርት አይነት ቢሆኑ ይመከራል 🔑 ስትቀመጪ ወገብሽ እንዳይታጠፍ ትራስ ከታች ወገብሽ ጋር አድርጊ ፤ ይህ ቀጥ ያደርግሻል 🔑 ለረጅም ጊዜ የምትቆሚ ከሆነ አንድ እግርሽን ከፍ ማድረግ እያቀያየርሽ፤ ይህ ወገብሽ ላይ ያለውን ጫና ይቀንሳል 🔑 በፋብሪካ የሚሰሩ የእርጉዝ ሴት የሆድ መደገፊያዎችን መጠቀም ከተገኘ 🔑 ገበያ ላይ ለእርጉዞች የተሰራ ረጅም ትራስ መጠቀም ከተገኘ ካሌለ አንድ ትራስ በጉልበቶችሽ መሀል እና አንዱን ሆድሽ ጋር በማድረግ መጠቀም ትችያለሽ 🔑 ህመም ከተሰማሽ ወገብሽ ላይ ቀዝቀዝ ያለ ወይም ሞቅ ያለ ነገር ማድረግ፤ በፎጣም ሊሆን ይችላል ህመሙን ለመቀነስ፣ ለረጅም ጊዜ ባይሆን ይመከራል 🔑 ማሳጅ መደረግ በባለሙያ 🔑 ዋና መዎኘት - ህመሙን ሊቀንስ ይችላል 🔑 በጣም ህመሙ ካቅም በላይ ከሆነ ፓራሴታሞል መጠቀም 👉 የወገብ ህመም ከፍተኛ ከሆነ እና በላይ ካሉት የማይመለስ ከሆነ ምን ሊያመለክተን ይችላል? ⚠️ ያለጊዜ የመጣ የምጥ ህመም - በተለይ ከማህፀን የሚወጣ ፈሳሽ ወይም ደም ካለ ⚠️ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን - ሽንት ቶሎ ቶሎ ማለት፣ ማቃጠል ፣ እና ትኩሳት ካለ 👉 👩‍⚕️👨‍⚕️ስለዚህ ከፍተኛ የሆነ የወገብ ህመም ካለ የማህፀን ሀኪምሽን ማማከር እንዳትረሺ። 🍀መልካም ጊዜን ተመኘሁ🍀

💥የወገብ ህመም በእርግዝና ጊዜ💥 👉 የወገብ ህመም በእርግዝና ጊዜ በሁሉም እናቶች ላይ በሚባልበት መልኩ እርግዝናው ሶስተኛውን መንፈቅ ከገባ በውሀላ ጊዜ ጀምሮ የሚያስቸግራቸው አንዱ የእርግዝና
+1
💥የወገብ ህመም በእርግዝና ጊዜ💥 👉 የወገብ ህመም በእርግዝና ጊዜ በሁሉም እናቶች ላይ በሚባልበት መልኩ እርግዝናው ሶስተኛውን መንፈቅ ከገባ በውሀላ ጊዜ ጀምሮ የሚያስቸግራቸው አንዱ የእርግዝና ህመም ነው።

የተለያዩ ምክንያቶች እንደምክነ‍እያት የሚጠቀሱ ሲሆን ከነዚህም:- ⁃ 💥 ከአንድ በላይ ፅንስ ማርገዝ ለምሳሌ መንታ እና ሆድ እጅግ መለጠጥ ⁃ 💥 ከአንድ ጊዜ በላይ ማርገዝ ⁃ 💥 ውፍረት ⁃ 💥 የማህፀን መጠን እጅግ የሚጨምሩ ነገሮች : የእንሽርት ውሀ መብዛት፣ የፅነሱ ኪሎ ትልቅ መሆን ⁃ 💥 የጄኔቲክስ ጋር የተገናኘም ሊሆን ይችላል ምልክቶች ⁃ 💥 እስከወሊድ ድረስ ምንም የሚስተዋል ነገር ላይኖር ይችላል ከዛን በውሀላ ግን ⁃ 💥 የሆዳችን ቆዳ መርገብ ⁃ 💥 ከጎዜያት በውሀላ መሀሌ ለመሀል ክፍተት ያለ ነገር መምሰል ⁃ 💥 ሲቆይ እና በእንቅስቃሴ ካልተደገፈ እና ካልተስተካከለ ስናስል፣ ወይም ከባድ ነገር ስናነሳ ወይም ሽንት ቤት ስንሆን በክፍተቱ እብጠት ማስተዋል እና ተመልሶ እብጠቲ ወደ ውስጥ መግባት (Hernia የምንለው ማለት ነው) ህክምናው እንዴት ነው? ⁃ 💥 ባብዛኛው ጊዜ ይህ ክፍተት በራሱ የሚዘጋ እና ህክምና የማያስፈልገው ነው። ⁃ 💥 ከወሊድ በውሀላ ይህ ክፍተት እስኪዘጋ ድረስ የተወሰኑ እንቅስቃሴችን ባናደርግ መልካም ነው፤ ለምሳሌ sit up, crunch የመሳሰሉትን ምክንያቱም የውስጠኞቹ የሆዳችን አንጀት በእንቅስቃሴ ጊዜ በክፍቱ አብጦ ሊወጣ ስለሚችል ⁃ 💥 የሚከተሉትን ስፖርቶች መስራት ◦ 🔑 Deep transverse abdominals muscle activation እንቅስቃሴ ( YouTube ቪዲዮውን ተመልከች) https://youtu.be/pUSDRGg1u_Q ◦ 🔑 Pelvic tile እንቅስቃሴ ( YouTube ቪዲዮውን ተመልከች) https://youtu.be/1o8tNEthajU https://youtu.be/sNcmGhLI4Hk https://youtu.be/gmqjLD_hJ-c እንዴት መከላከል ይቻላል? ⁃ 💥 እርግዝና ከመከሰቱ በፊት ለሆድ ጡንቻ ማጠንከሪያ የሚሆኑ ሰፖርቶችን መስራት ( እነኚህ ስፖርሮች በባለሙያ የታገዙ ቢሆኑ መልካም ነው።) 🍀መልካም ቀን ተመኘሁ!🍀

የእምብርት እና የሆድ ክፍተት (diastasis recti) ይህ ችግር አንዲት ሴት በእርግዝና ጊዜ በሚፈጠርባት የሆድ መወጠር ምክንያት ከፊት ለፊት ሆድ ላይ የሚገኙት የሆድ ሽፋን ጡንያዎች መሳሳት እ
+2
የእምብርት እና የሆድ ክፍተት (diastasis recti) ይህ ችግር አንዲት ሴት በእርግዝና ጊዜ በሚፈጠርባት የሆድ መወጠር ምክንያት ከፊት ለፊት ሆድ ላይ የሚገኙት የሆድ ሽፋን ጡንያዎች መሳሳት እና መለያየት ይፈጠራል። ይህ ሁሉም እናቶች ላይ የሚከሰት ሳይሆን የተወሰኑት ላይ ነው።

💥የውሸት እርግዝና (Pseudocyesis)💥 👉 ማርገዝ ለአንድ ጥንዶች ወይም ወላጆች እጅግ በጣም ደስታን የሚጭር ጊዜ ሲሆን በተለይ ደግሞ ታስቦ እና ታቅዶ የተረገዘ እርግዝና የበለጠ ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ ግን ሴቶች pseudocyesis (በጣም በትንሹ ደግሞ ወንዶች ላይ 🤔… Couvade syndrom የሚሰኘው ) ሳያረግዙ ከብዙ ነገሮች አንፃር አርግዣለሁ ብሎ ማሰብ በታሪክ አዲስ ክስተት አይደለም። ❓❓ምን ይሆን ምክንያቱ❓❓ 👉 ባብዛኛው ጊዜ ይህ አይነት አርግዣለሁ ብሎ እራስን ማሳመን ምክንያቱ ይህ ነው መባል የማይቻም ሲሆን ነገር ግን የሚከተሉት ነገሮች እንደ መላምት ይጠቀሳሉ:- 📌 እጅጉን ማርገዝ መፈለግ ይህ ከብዙ ነገሮች አንፃር የመጣ ፤ ለምሳሌ 🔑 ብዙ ጊዜ ለማርገዝ ሙከራ እየተደረግ እንቢ ሚላቸው ሴቶች ላይ 🔑 በተደጋጋሚ ውርጃ የሚያጋጥማቸው 🔑 ወደ ማረጥ እየቀረቡ ነገር ግን ማርገዝ የሚፈልጉ ላይ 📌 እጅጉን ማርገዝ አለመፈለግ ነገር ግን ሁሌም አርገዣለሁ ብሎ መጠርጠር እና ማሰብ 👉 እነኚህ ከላይ የተጠቀሱት ሁናቴዋች ወይም ስሜቶች ሴቲቱ በአካሏ ላይ የእርግዝና ምልክቶች ያሉ እንዲመስላት ያደርጋል። 👉 በነኚህ ምልክቶች ምክንያት የሴቲቱ ጭንቅላት እርግዝና እንዳለ በማመን እርግዝና ላይ ከመጀመሪያ ጀምሮ አስተዋፅዎ ያላቸውን በጭንቅላት የሚመነጩ ንጥረ ቅመሞች እንዲመነጩ በማድረግ ትክክለኛ የሚመስሉ የእርግዝና ምልክቶች እንዲሰሟት ያደርጋል። 💥ሊታዩ የሚችሉ ስሜቶች💥 📌 የወር አበባ የተዛባ መሆን ፤ በጣም ማነስ ወይም እስከጭራሹ አለማየት 📌 ጡት መጨመር እና የህመም ስሜት፤ አንዳንዴም ወተት እስከማውጣት መድረስ 📌 ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ 📌 ሆድ እያበጠ እና እየጨመረ መምሰል 📌 እንቅስቃሴ ያለ መምሰል እና ኪሎ መጨመር 📌 ምጥ አለኝ ብሎ ሆስፒታል እስከመሄድ እስከመድረስ ሊሆኑ ይችላሉ 💥ሊደረጉ የሚችሉ ምርመራዎች💥 📌 የእርግዝና ምርመራ:- የሽንት እርግዝና ምርመራ እርግዝና እንደሌለ ያሳያል 📌 አልትራሳውንድ:- ምንም አይነት ፅንስ እንደሌለ ያሳያል ህክምናውስ❓❓ ⁃ ብዙን ጊዜ እርግዝና ለሚፈልግ እና በጣም ለጓጓች ሴት እርግዝና የለሽም ማለት በጣም የሚያበሳጭ ነገር ስለሚሆን በተቻለ አቅም ስላለው ሁኔታ ተረጋግቶ እና አረጋግቶ መንገር ተገቢ ነው። ⁃ ቢቻል በስነልቦና ሀኪም ቢነገራቸው እና ቀጣይ ያሉ ክትትሎች ቢያደርጉ ይመከራል።

ጊዜው 1945 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ቤውላ ሃንተር ትባላለች። በትውልድ አሜሪካዊት የሎሳንጀለስ ነዋሪ ስትሆን በአለም ረጅም ጊዜ የፈጀውን እርግዝና በመያዝ ስሟ በ ታይም መፅሄት ሰፍሯል። ቤውላ
+2
ጊዜው 1945 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ቤውላ ሃንተር ትባላለች። በትውልድ አሜሪካዊት የሎሳንጀለስ ነዋሪ ስትሆን በአለም ረጅም ጊዜ የፈጀውን እርግዝና በመያዝ ስሟ በ ታይም መፅሄት ሰፍሯል። ቤውላ እንደ ሀኪሟ ዶ/ር ቤልዝ ገለፃ period መጨረሻ ያየችው February 10 ሲሆን እርግዝናዋ አንድ እርጉዝ ትወልዳለች ተብላ ከምትጠበቅበት 40 ሳምንት(280 ቀን) ከ 100 ቀናት በላይ በመቆየት በ 375ኛው ቀን ይህም ማለት 1 አመት ከ 10 ቀን በማሳለፍ February 21 ፔኒ ዲያና የተባለች የ3.14 ኪ.ግ. ጤናማ ሴት ልጅ መገላገሎን Time Magazine ዘግቧል። 18 እርግዝና…❓❓❓

💥 የማህፀን ሞኝ እጢዎች (uterine fibroids) ከማህፀን የመሀከለኛው ክፍል ወይም ከማህፀን ጡንቻ ላይ የሚነሱ እጢዎች ናቸው። 💥 ብዙን ጊዜ እጢ ስንል በጭንቅላታችን የሚመጣው መጥፎና የካንሰርነት ባህርይ ያለው ነገር ቢሆንም እነኚህ uterine fibroids ወይም የማህፀን ሞኝ እባጮች ግን የካንሰርነት ባህሪ የሌላቸው እና ወደ ካንሰር የመቀየር እድላቸውም እጅግ በጣም አናሳ እና ጥናቶችም እንደሚያሳዩት በዚህ እጢ ከታከሙ 580 ሴቶች አንዷ ብቻ ይህ እጢ ወደ ካንሰር ሊቀየርባት እንደሚችል ያሳያሉ። 💥 የማህፀን ሞኝ እጢዎች (uterine fibroids) አንዲት ሴት በመውለጃ ዘመኗ ላይ የሚከሰቱ የእጢ አይነቶች ሲሆኑ በተለይ ደግሞ ከ 30 እስከ 40 አመት እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሴቶች ላይ አብዝተው ይከሰታሉ። 💥 እነኚህ እጢዎች ብዙን ጊዜ የህመም ስሜት ስለሌላቸው ነው እንጂ እስከ 70% የሚሆኑ ሴቶች ይህ እጢ በማህፀናቸው ላይ ተብሎ ይታሰባል። 👉❓❓ይህ እጢ ለምን ይከሰታል❓❓ የማህፀን ሞኝ እጢዎች (uterine fibroids) ለምን እንደሚከሰቱ እርግጥ የሆነ ጥናት ባይኖርም መላምቶቹ ግን የሚያሳዩት በማህፀን ጡንቻ ውስጥ የሚገኙ የዘረመል ችግር ያለባቸው የጡንቻ ህዋሶች Estrogen የተሰኘው ንጥረ ነገር(hormone) ሲነካቸው ከቁጥጥር ውጪ በሆነ መንገድ ስለሚራቡ እና ወደ እጢነት ስለሚያድጉ ነው። 👉❓የዚህ እጢ ምልክቶች ምንድን ናቸው❓ 💥 ባብዛኛው ጊዜ ምንም አይነት ምልክት የሌላቸው ሲሆን ለሌላ ህመም በሚደረግ የአልትራሳውንድ ምርመራ እንደ ድንገት ሊገኙ የሚችሉ እጢዎች ናቸው። ነገር ግን ከዛ ባለፈ ህመሙ የሚሰማቸው ሴቶች የሚከተሉትን ምልክቶች ሊያሳዩ ይችላሉ:- 🔑 የወር አበባ ለውጥ 📌 የወር አበባ መብዛት እና መቆየት ካለበት ጊዜ በላይ አሳልፎ ከቆየ 📌 የወር አበባ ህመም 📌 የደም ማነስ ምልክት:- ብዙ ደም ከመፍሰስ የመጣ 🔑 የወገብ ህመም እና ከእንብርት በታች የህመም ስሜት፣ በተለይ በግንኙነት ጊዜ ሊብስ የሚችል 🔑 ሽንት እንቢ ማለት ወይም ቶሎ ቶሎ ማለት 🔑 የሰገራ ድርቀት፣ እና የሆድ ህመም 🔑 በሆድ ላይ ቀስ ብሎ እየጨመረ የሚሄድ እብጠት ማስተዋል 🔑 በተደጋጋሚ ውርጃ መከሰት 🔑 እርግዝና እንዳይፈጠር መከልከል 👉❓እነኚህ እባጮች/እጢዎች መቼ ነው ህክምና የሚያስፈልጋቸው❓ 💥 ብዙን ጊዜ ምንም አይነት ህመም ከሌላቸው በጊዜ ሂደት አንዲት ሴት ስታርጥ ወይም የወር አበባ ማየት ባቆመች ጊዜ መጠናቸው እየኮመሸሸ እና እያነሰ ስለሚመጣ በመድሀኒትም ሆነ በቀዶ ህክምና መታከም አያስፈልግም፤ ነገር ግን አንዲት ሴት :- 💥 በእጢው ምክንያት የመጣ የወር አበባ መዛባት ፣ በብዛት ካለ እና ደም ማነስ ካመጣባት 💥 ከፍተኛ የሆነ ህመም ካላት (ከእጢው ጋር የተገናኘ) 💥 እጅግ መጠኑ የበዛ እጢ ከሆነ 💥 እርግዝና ከከለከላት ወይም ደግሞ እርግዝና ተከስቶ ለውርጃ እንደምክንያት ከሆነ (ሌሎች እርግዝና የሚከለክሉ ወይም ውርጃን የሚያመጡ ነገሮች ሁሉ ከተጣሩ በውሀላ) 👉❓ሊሰጡ የሚችሉ ህክምናዎች❓ 📌 የመድሀኒት ህክምና:- ይህ ህክምና የሚፈሰውን የደም መጠን ለመቆጣጠር የሚሰጥ ህክምና ነው። 📌 ኦፕሬሽን :- ይህ እጢውን በኦፕሬሽን የማውጣት ህክምና ሲሆን ፤ በተጨማሪ ግን የተለያዩ የኦፔሬሽ አይነቶችም ሊኖሩ ይችላሉ። 📌 ማህፀንን እስከነ እጢው ማውጣት:- ይህ ኦፕሬሽን ሴቲቱ ወልዳ የጨረሰች ከሆነች ወይም ደግሞ እጢውን ለማውጣት በሚደረግ ኦፕሬሽን ጊዜ ከፍተኛ ደም መፍሰስ ካለ ማህፀን ማውጣት የሴቲቱን ህይወት የሚያተር አንዳች አማራጭ ሆኖ ሲገኝ የሚደረግ ኦፕሬሽን አይነት ነው። 🍀መልካም ጊዜን ተመኘሁ!🍀

የማህፀን ሞኝ እጢዎች (Uterine fibroids) 💥 ትክክለኛ የአማርኛ ትርጓሜ ባይኖራቸውም Uterine fibroids የማህፀን ሞኝ እባጮች/እጢዎች ብንላቸው ካላቸው ባህሪ ጋር ያስኬዳል ብዬ አ
+2
የማህፀን ሞኝ እጢዎች (Uterine fibroids) 💥 ትክክለኛ የአማርኛ ትርጓሜ ባይኖራቸውም Uterine fibroids የማህፀን ሞኝ እባጮች/እጢዎች ብንላቸው ካላቸው ባህሪ ጋር ያስኬዳል ብዬ አስባለሁ።