ዶ/ር ዳዊት መስፍን (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት)
Open in Telegram
**ጠቅላላ የማህፀንና ፅንስ ጉዳዬችን ማማከር** - ቅድመ ወሊድ - ስለ ወሊድ አገልግሎት - ስለ መካንነት ምርመራ እና ህክምና - በተለያዩ ምክንያቶች ከማህፀን ለሚወጣ ደም እና ፈሳሽ ምክንያና ህክምና - ለወር አበባ መዛባት ምክንያት እና መፍትሄ - ስለቅድመ ካንሰር ምርመራና የምክር አገልግሎት... 0911138054📞
Show more5 833
Subscribers
-224 hours
-127 days
-4030 days
Posts Archive
ዶ/ር ዳዊትን በአካል ቀርቦ ህክምና ለማግኘት ከፈለጉ የሚቀጥሉት ሆስፒታሎች ይጎብኙ 👇👇
💥ማክሰኞ እና ሀሙስ💥 ከ 8 ሰዓት ጀምሮ
🫴 Washington Hospital
አድራሻ :- Bole Rwanda -
💥ረቡዓ(እሮብ)💥ከ 8 ሰዓት ጀምሮ
🫴 Medstar Speciality Clinic
አድራሻ:- 22 አካባቢ , ውሀ ልማት- ከcapital hotel ከፍ ብሎ ባለው ድልድይ በስተቀኝ 50ሜትር
🟢Medstar Speciality Center🟢
ዛሬ በ8፡00 ሰዓት በማህፀን እና ፅንስ ሀኪማችን ስለፅንስ እና ማህፀን ህመሞ መፍትሄ ሊሰጥዎ ሰዓት ብቻ እየተጠበቀ ነው፤ ይምጡ መፍትሄ ያግኙ
🆘የሚያገኙት አገልግሎት 🆘
🟢 ከእርግዝና ጊዜ ለሚከሰቱ ህመሞች ህክምና እና የመረጃ አገልግሎት
🟢 የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ
🟢 የወር አበባ መዛባት ችግሮች እና ህክምናው
🟢 የመካንነት ምርመራ እና ህክምና - ለወንድም ለሴትም
🟢 ከማህፀን ወይም ከብልት ለሚወጣ ግክክለኛ ያልሆነ ፈሳሽ ፣ ማሳከክ ህክምናዎች እና የምክር አገልግሎት
🟢 አዲስ ትዳር ለመመስረት ፍላጎት ላላቸው የአባላዘር ምርመራ የHIV/AIDS ምርመራን ጨምሮ
🟢 ቅድመ ወሊድ ምርመራ እና የምክር አገልግሎት
🟢 በተደጋጋሚ ለሚከሰት ውርጃ ምርመራ እና ህክምና
🟢 ባረጡ እናቶች ላይ ለሚከሰት የማህፀን ፈሳሽ እና የደም መፍሰስ ምርመራ እና ህክምናዎች
🟢 የተለያዩ የካንሰር ምርመራዎች
🟢 የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎቶች
አድራሻ :- አዲስ አበባ, 22 አካባቢ ከ Capital Hotel ከፍ ብሎ ባለው ድልድይ በስተቀኝ 50 ሜትር, ዘወትር እሮብ ከ 8 ሰዓት ጀምሮ
👉 ወሲብ መፈፀሚያ አካል ዝግጁ አለመሆን - ለወንዶች
👉 ጭራሹኑ ስሜት ማጣትንና ፍላጎት አለመኖር - በወንድም በሴትም
👉 የመጨረሻው እርካታ ላይ አለመድረስን፣
👉 የሌላውን ስሜት ሳይጠብቁ ፈጥኖ መርካትን፣ - ፍላጎት አለመኖርን፣
👉 የዘር ፈሳሽን ፈጥኖ ማፍሰስ- ለወንዶች - ይህ የወሲብ ስሜት ከፍተኛ ከመሆን፣ ዘር ፍሬዬ ፈጥኖ ሊፈስብኝ ነው ብሎ ሃሳብ ውስጥ መግባት እና ፍቅረኛዬን በወሲብ ማርካት አልችልም በሚል ስሜት መራቢያ አካል ዝግጁ አለመሆን ጋር የተያያዙ ችግሮች ጋር የተያያዘ ነው ። በቀላሉ በስነልቦና ሀኪም ድጋፍ መፍትሄ ሊያገኝ ይችላል
👉 ሴቶች ጋር የግንኙነት ሀሳቡ ሲመጣ እና በግንኙነት ጊዜ የሚወጡ ጠቃሚ የሆኑ የመራቢያ አካል ፈሳሽ አለመመንጨት - ይህም በግንኙነት ጊዜ ህመም መፍጠር
💥ሀኪም እንዴት ሊረዳህ/ሽ ይችላል?💥
👉 ጥልቅ ውይይት በማድረግ ሙሉ ታሪክሽን/ህን ይወስዳል። ተጨማሪ አካላዊ ምርመራ ያደረወጋል
👉 ተጨማሪ የላብራቶሪ ምርመራዎች - ደም ፣ ሽንት እና ሆርሞን እንደ አስፈላጊነቱ ተጨማሪ ከፍ ያሉ ምርመራዎችን ያደርጋል
💥መፍትሄዎች💥
👉 የስነ ልቦና ሀኪም ማማከር :- ጭንቀት፣ ፍርሃትን፣ ውጥረትን፣ ድብርትን፣ ስጋትንና ቀድሞ ተሸናፊ የመሆን ስነ ልቦናዊ ችግሮች ካሉ
👉 ለስንፈተ ወሲብ እንደምክንያትነት የሚጠቀሱ በሽታዎችን ሀኪም ጋር ጥብቅ ክትትል በማድረግ በቁጥጥር ስር ማድረግ :- ለምሳሌ ስኳር ፣ ግፊት
👉 ለሌላ ህመም ተሰጥተው ስንፈተ ወሲብ የሚያመጡ መድሀኒቶችን ከሀኪም ጋር በመነጋገር ለመቀየር መሞከር እና መፍትሄ መፈለግ
👉 የወንድ ብልት ዝግጁ የሚያደርጉ መድሀኒቶች :- ለምሳሌ - ሲልደናፊል(ቫያግራ) ። እነኚህ ለስንፈተ ወሲብ መፍትሄ የሆኑ መድሀኒቶች ቢሆኑም ፤ መድሀኒቶች ከሀኪም ትዓዛ ውጪ መውሰድ የራሳቸው የሆነ አደጋዎች ሊያመጣ ይችላል። በተለይ በተለይ የልብ ህመም ያላቸው ፣ ምክንያቱ ያልታወቀ እራስ ምታት ያለባቸው፣ ግፊት ያለባቸው፣ የጨጓራ ህመም ፣ የደም ካንሰር ፣ እንዲሁም ለሌሎች በሽታዎች ለምሳሌ እንደ ግፊት የመሳሰሉት መድሀኒት የሚወስዱ ከሆነ እና የመሳሰሉት ያለባቸው ሰዎች ያለሀኪም ትዓዛዝ ከወሰዱ ከጥቅሙ አደጋው የከፋ ይሆናል። በተጨማሪም ቫያግራ አዘውትሮ መውሰድ ሱስ ስለሚያመጣ ከሱ ውጪ ግንኙነት ማድረግ አለመቻልን ሊያስከስት ይችላል
👉 የሆርሞን መተካት ህክምና - በሆርሞን እጥረት ምክንያት ለተከሰተ ስንፈተ ወሲብ
👉 በኛ ሀገር ባይኖሩም እንደ :- ቫኪዩም ዲቫይሽ፣ ብልት ላይ የሚወጉ መርፌዎች ፣ በቀዶ ጥገና ሰው ሰራሽ ብልት ማቆሚያ፣ የደም ስር ችግር ከሆነ በቀዶ ጥገና ማስተካከል
💥አስተውል/ይ💥
👉 ስንፈተ ወሲብ ሊታከም እና ሊድን የሚችል የጤና ችግር ነው
👉 በጥንዶች እና በባለትዳሮች መሀከል ያለ ግልፅ ውይይት እና ህክምናን የመሻት ፍላጎት ችግሩ ተሸፋፍኖ ሊያመጣ ከሚችላቸው አላስፈላጊ ማህበራዊ ቀውሶች እንደ አላስፈላጊ ምክንያት በመደርድ ፍቺ ውስጥ መግባትን እና በኑሮ ዘመን ለተፈጠሩ ህፃናት የወላጆች ፍቅር አግኝተው ማደግንና ሳይችሉ ተበታትነው መቅረትን ይከላከላል።
👉 የወንድ ብልት መጠን ማነስ ወይም የሴት ብልት መስፋት ከስንፈተ ወሲብ ጋር አይገናኝም - ዋናውና አስፈላጊው ነገር በነፃነት ስሜትን ሰብስቦ፣ የተቃራኒ ፆታን ስሜት ተረድቶና ተቀብሎ ለወሲብ ዝግጁ መሆን ብቻ ነው።
💥መልካም እለተ ሰንበት💥
ስንፈተ ወሲብ
ክፍል - 2
💥ምልክቶች💥
👉 ለግብረ ስጋ ግንኙነት ፈፅሞ ዝግጁ አለመሆንን - በወንድም በሴትም
👉 የሴትም ሆነ የወንድ ብልት አለመነቃቃት ወይንም ደግሞ ለግንኙነት ዝግጁ ካለመሆን ጋር የቀጥታ ቁርኝት ያለው
👉 በወንድም ሆነ በሴት ላይ ሊከሰት ይችላል :- የወሲብ አካል(ብልት) ዝግጁ አለመሆን ችግር በስፋት በወንዶች ላይ የሚከሰት ሲሆን፣ ከሚፈፀመው የወሲብ ግንኙነት ደስታ ማጣትና የመጨረሻው እርካታ ላይ አለመድረስ ግን የሁለቱም የወንድም የሴትም ችግር ይሆናል፡፡
👉 ስንፈተ ወሲብ መፍትሄ ያለው የስነ ልቦና፣ የአካላዊና የአዕምሯዊ ጤና ችግሮች ውጤት ነው
👉 የስንፈተ ወሲብ ችግር በአገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ በመሄድ ላይ ነው፡፡ ለምሳሌ በየዓመቱ ግልፅ ምክንያት ሳይቀመጥላቸው የሚፈርሱ ትዳሮች እየጨመሩ እንደሆነ የሚያሳዩ መረጃዎች አሉ፡፡ እነኚህም አብዛኞቹ ከስንፈተ ወሲብ ጋር የተገናኙ እንደሆነ ይገመታል - ይህ ነው የተባለ ጥናት ባይኖርም
👉 ምክንያቶቹን በሁለት መክፈል ይቻላል እነኚህም :-
📌 አንደኛ- ተፈጥሯዊ በሆነ የአፈጣጠር ችግር ማለትም በክሮሞዞን፣ የሴትነትና የወንድነት መገለጫ በሆኑት የኦቫሪና የቴስትሮን አፈጣጠር ችግር ምክንያት የሚፈጠር፣
📌 ሁለተኛው - ከውልደት በኋላ በዕድገት ሂደት በአካላዊ፣ በስነ ልቦናዊ ፣ በአዕምሯዊና በአካባቢያዊ ምክንያቶች የሚፈጠር የስንፈተ ወሲብ ችግር ፡
💥መንስኤ💥
👉 ስነ አዓምሮ ችግሮች
👉 የስኳር ህመም
👉 የሰውነት ኮሌስትሮል መጨመር
👉 የደም ግፊት
👉 የልብ ህመም
👉 የኩላሊት ህመም
👉 የነርቭ ህመም
👉 እድሜ ሲጨምር - ስንፈተ ወሲብ የመከሰት እድል ይጨምራል 👉 ይህም የተለያዩ ከእድሜ ጋር ተያይዘው የሚመጡ በሽታዎች ስለሚጨምሩ እና የሆርሞን መጠንም እየቀነሰ የሚሄድ ስለሆነ ነው
👉 አልኮል፣ ሲጋራ ፣ ጫት እና የተለያዩ ሱሶች
👉 የሆርሞን መዛባቶች :- ቴስቴስትሮን
👉 አደጋዎች:- በተለይ ወገብ አካባቢ የሚደርስ የአከርካሪ አጥንት ስብራት ምክንያት የነርቭ መጎዳት
👉 የአባላዘር በሽታዎች
👉 በብልት አካባቢ የሚደረጉ ኦፕሬሽኖች- የነርቭ እና የደም ቧንቧ አደጋ ከተፈጠረ
👉 ስቴሮይድ መድሀኒቶችን መጠቀም:- ለጡንቻ ማፈርጠም እና የመሳሰሉት የሚወሰዱ መድሀኒቶች - ይህ የሰውነትን የመራቢያ ሆርሞኖችን ያዛባሉ
👉 የስራ ጫናዎች - እነኚህ የሰውነትን መድከም የአዓምሮ መዛል ስለሚያመጡ - ግንኙነት ደግሞ የአዓምሮን ሰላም፣ መረጋጋት እና ምቾትን ስለሚፈልግ ለስንፈተ ወሲብ ምክንያት ሊሆን ይችላል
👉 የስነልቦና መዛባት(መቃወስ) - ይህ ጭንቀት፣ ድብርት ፣ በጥንዶች መሀከል ያሉ ግጭቶች ፣ በቤተሰብ ውስጥ ጫና እና ችግር፣ ሀዘን የመሳሰሉት
👉 ከቴክኖሎጂ ጋር ተያይዘዞ የሚመጡ የወሲብ ቀስቃሽ ፊልሞች እና ምስሎች አብዝተው የሚመለከቱ - ይህንን አይነት ምስሎችን ወይም ፊልሞችን የሚያበዙ ሰዎች የሚያዩትን ነገር ወደ ጋህዱ አለም ሲያመጡት ለስነ አዓምሮ ጭንቀት መጋለጥ አልችልም ወደሚል ስሜት ውስጥ በግባትን እና የስነልቦና ጫናን መጋለጥ
👉 ሴቶች ቀደም ሲል የነበራቸው ጥሩ ያልነበረ የወሲብ ግንኙነት አሁን ላይ ፍራቻን መጫር እና ከነጭራሹ ወሲብን መጥላት ሊያመጣ ይችላል
👉 ለረጅም ጊዜ ሳይክል መንዳት
👉 ሌላ ህመም ወይም በሽታዎች የሚሰጡ አንዳንድ መድሀኒቶች :- ለምሳሌ - ለአዓምሮ ህመም፣ ለግፊት እና ለመሳሰሉት
👉 ሰውነትን ሽባ የሚያደርግ የነርቭ በሽታ - ለምሳሌ ፓርኪንሰንስ
… ክፍል -2 … የስንፈተ ወሲብ ምክንያቶች እና መፍትሄያቸው ይዳሰሳል ….ነገ በተመሳሳይ ሰዓት ይጠብቁ….
💥ሰንፈተ ወሲብ💥
ክፍል - 1
ምንድን ነው?
👉 በሁለት ጥንዶች መሀከል በግንኙነት ሰዓት ከፍላጎት ጀምሮ እስከ ግንኙነት ማብቂያው ድረስ ያለው ሂደት ውስጥ የሚከሰት ምንም አይነት እክል የሚገልፅ የህመም አይነት ነው።
ዘወትር ረቡዕ ከ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ዶ/ር ዳዊትን በመሀል አዲስ አበባ ፤ ውሃ ልማት ፤ ካሳንችስ Capital Hotel'ን አለፍ እንዳሉ ከሚያገኟት ድልድይ በስተቀኝ 50 ሜትር ብቻ ሲጓዙ ያገኙናል። MED-STAR SPECIALTY CLINIC.
📌 ለማንኛውም የማህፀን እና ፅንስ ጥያቄዎ ሳይታክት መልስ እንደሚሰጠው ሁሉ በፊት ለፊት ህክምና ለመስጠት ተዘገጃጅተን የእርሶን መምጣት ብቻ በመጠበቅ ላይ ነን።
ምን ምን አገልግሎት ነው የሚሰጠው ?
🧬 የማህፀን ጫፍ ቅድመ ካንሰር ምርመራ (Cervical Cancer Screening)
🧬 ከማህፀን ለሚነሱ ካንሰሮች ምርመራ እና ናሙና መውሰድ
🧬 በማህፀን እና በማህፀን ዙሪያ ለሚወጡ እጢዎች ምርመራ
🦠 ለአባለዘር በሽታዎች ምርመራ እና ህክምና
🦠 ከማህፀን ለሚወጡ ከተፈጥሮ ለተለዩ ፈሳሾች ህክምና
👭የመካንነት ህክምና እና ምርመራ
👫 የቅድመ ወሊድ የምክር አገልግሎት እና ምርመራ
🤰🏼የወሊድ ክትትል እና የምክር አገልግሎት
🤱🏼የድህረ ወሊድ ክትትል
🩸 የሆርሞን ምርመራ
🌡 የታይሮይድ ምርመራ
🩻 የማህፀን ራጅ ምርመራ
🔬 የእጢ ምርመራ በስነደዌ ስፔሻሊስት(Pathologist)
💉 የጡት ካንሰር ምርመራ
📍የት ካሉ ? 🏩
ዶ/ር ዳዊትን በመሀል አዲስ አበባ ፣ ካሳንችስ ፣ ውሃ ልማት Capital Hotel'ን አለፍ እንዳሉ ከሚያገኟት ድልድይ በስተቀኝ 5⃣0⃣ ሜትር ብቻ ሲጓዙ MED-STAR SPECIALITY CLINIC'ን ያገኛሉ ታዲያ እነደመጡ እኔ ነኝ ተረኛ እኔ ነኝ ምገባው ኧረ ሲስተር አስቀድሚኝ ቢሮ ጥዬ ነው የመጣሁት ፤ ኧረ ልጄን ከትምህርት ቤት አላመጣሁም ለኔ ቅድሚያ ይሰጠኝ እንዳይሉ በ 0920807650 ወይም 011-6-35-42-80 📞 በመደውል ቀድመው ቀጠሮ ያስይዙ።
📆 መቼ ካሉ ? ። 📅
ዘውትር ረቡዕ / እሮብ ከሰዓት ከ 8:00 ጀምሮ ።
በሜድ ስታር እንገናኝ 👨🏽⚕👨👩👧👦🤰🤱
እናንተን ያወያያል ፣ የህክምና እውቀታችሁን ያሳድጋል እንዲሁም ጥንቃቄ የሚያሻቸውን ነገሮች በውይይት ፕሮግራማችን እያነሳን እየተማማርን እንቀጥላለን።
ለዛሬ ደግሞ ስለ ድህረ-ወሊድ🤱 ምን ያህል ያውቃሉ ? ምን ምን አይነት ጥንቃቄስ ያሻል 🤔 ? የወለደች እናት በ Zero ሻማ 💡 ባለው ክፍል ብትሆን ይሻላል ወይስ በደንብ ብርሃን 🌕 በሚገኝበት ክፍል ውስጥ ?
ሀሣቦን ያጋሩን።
መልካም ዕለተ ሰንበት!🍀☘🍀☘
👉 የቆዳ ሸንተረሮች በእርግዝና ላይ በሁሉም አይነት የቆዳ ከለር ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ የሚከሰት የቆዳ ለውጦች ሲሆኑ፤ በመጀመሪያ ልጅ እርግዝና ላይ ገዝፈው የሚታዩ ሲሆን በተለይ ሶስተኛው መንፈቅ ላይ (ከ 7ወር በውሀላ) በይበልጥ እይታቸው ይጨምራል።
👉 ብዙን ጊዜ እነኚህ ምልክቶች በሆድ ላይ ገዝፈው ይታዩ እንጂ በጭን፣ መቀመጫ እና በጡት ቆዳ ላይም ይወጣሉ።
💥ለምንድን ነው የቆዳ ሸንተረር የሚከሰተው?💥
የቆዳ ሸንተረር የሚከሰትባቸው ምክንያቶች ይህ ነው የሚባል ትክክለኛ ምክንያት ባይኖርም የብዙ ምክንያቶች ውጤት ነው ተብሎ ግን ይታሰባል። እነኚህም:-
👉 የሆድ ቆዳ ለውጥ - ፅንሱ ባደገ ቁጥር የሆድ ቆዳሽን እየወጠረው እና እየለጠጠው ስለሚሄድ በተጨማሪም ያንቺም የሰውነት ኪሎ መጨመር የራሱ የሆነ አስተዋፅዎ ይኖረዋል
👉 በውጥረቱም ምክንያት ቆዳ እንዲለጠጥ የሚጠቅሙ collagen(ኮላጅን) የተሰኙ ንጥረ ነገሮች ስራቸውን በትክክል አለመስራት እና መቆራረጥ ወይም መሰባበር እንደምክንያትነት ይጠቀሳል
👉 በእርግዝና ጊዜ በሚኖሩ ወይም በብዛት በሚለቀቁ ንጥረ ፈሳሾች ምክንያት አንዱ የሸንተረሮቹ መንስኤ ሆኖ ይጠቀሳል
👉 ጥቂቶቹ ደግሞ በዘረመል ችግር (genetic alteration in connective tissues) ምክንያት ሊከሰቱ ይችላል።
💥 ለቆዳ ሸንተረር የሚያጋልጡ ነገሮች ምን ምንድን ናቸው?💥
👉 ለቆዳ ሸንተረር የሚያጋልጡ ነገሮች የተወሰኑት ያለንን ሁናቴ በማስተካከል መቅረፍ የሚቻሉ ሲሆኑ ፤ የተወሰኑት ደግሞ መቅረፍ የማይቻሉ አይነት ሊሆኑ ይችላሉ።
👉 ባብዛኛው ለቆዳ ሸንተረር እንዳጋላጭ ሁኔታ የሚጠቀሱት:-
📌 በእርግዝና ላይ ከፍተኛ የሆነ የሰውነት ኪሎ መጨመር እና
📌 ፅንሱ ከፍተኛ ወይም ትልቅ ኪሎ ከሆነ ነው
👉 ሌላ ተጠቃሽ አጋላጭ ምክንያቶች ተብለው የሚጠቀሱት ደግሞ:- የቀደመ እርግዝና ላይ ሸንተረሩ ተፈጥሮ ከነበረ ፣ በቤተሰብ ከነበረ እና እርግዝና በልጅነት የተፈጠረ ከነበረ ናቸው።
💥 ምልክቶች
👉 ብዙን ጊዜ በግራ እና በቀኝ በኩል እኩል የሚከሰቱ ሲሆን
👉 ስፋታቸው ከ ትንሽ ሚ.ሜትር እስከ ሴ.ሜትር ሊሆኑ ይችላሉ
💥 ነጣ ያለ የቆዳ ቀለም ያላቸው ሰዋች ላይ
👉 በመጀመሪያ ላይ ወደ ቀይ እና ሀምራዊ ቀለም ያላቸው የቆዳ ሸንተረሮች መታየት ይጀምራሉ
👉 ጊዜው በሄደ ቁጥር ከለራቸው ወደ ነጣ ያለ የቆዳ ሸንተረር ይቀየራል
💥 ጠቆር ያለ የቆዳ ቀለም ያላቸው ሰዋች ላይ
👉 ሸንተረሩ ጠቆር ያለ ግራጫ ወይም ጠቆር ያለ ሰማያዊ ከለር ሊይዝ ይችላል
💥 ህክምናው ምን ይመስላል?
👉 የቆዳ ሸንተረር በህይወት ላይ የሚያመጣው ምንም አይነት የሆነ አስጊ ሂኔታ የለም ፤ በዚህም ምክንያት ሁሉም በቆዳ ላይ የሚከሰት ሸንተረር ህክምና አያስፈልገውም።
👉 ህክምናው ሙሉ በሙሉ ሸንተረሩን ማጥፋት አይችልም፤ ነገር ግን የሸንተረሩን ከለር መቀነስ እና አካባቢው ካለው የቆዳ ሁኔታ ጋር ለማመሳሰል መሞከር ይሆናል።
👉 የተለያዩ የህክምና ዘዴ አይነቶች ሲኖሩ ከነኚህም ውስጥ ቆዳ ላይ የሚቀቡ ቅባቶች እና የጨረር ወይም የሌዘር ህክምና አይነቶች ተጠቃሾች ናቸው።
👉 መድሀኒቶቹ (የሚቀቡትም ሆኑ የጨረር ህክምናዎቹ) በእርግዝና ወቅት በፍፁም መጠቀም አይፈቀዱም፤ ይህም የሆነበት ምክንያት ለፅንሱ ካላቸው ጉዳት ነው።
💥 ቀድሞ መከላከል ይቻል ይሆን?
👉 🧴🧴በአለም ላይ ብዙ አይነት የኮስሞቲክ ውጤቶች እንደ ክሬም፣ ሎሽን፣ ቅባቶች እንዲሁም በተጨማሪ መድሀኒቶች እና የመሳሰሉት ከእርግዝና በፊትም ሆነ በእርግዝና ላይ የቆዳ ሸንተረር ይጠቅማሉ ተብለው የተሞከሩ ቢሆንም ከውጤት አንፃር ግን ምንም አይነት አመርቂ ውጤት አላመጡም።
🌼መልካም ምሽት🌼
💥 የቆዳ ሸንተረር (Striae Gravidarum)💥
👉 የቆዳ ሸንተረር ከ52 እስከ 90% በሚሆኑ ሰዎች ላይ የሚከሰት በቆዳ ላይ የሚወጡ ሸንተረሮች ሲሆኑ እነኚህም የተለያዩ አይነት ከለሮች - ቀላ ያሉ፣ ወደ ወይንጠጅ የሚሄዱ፣ ነጣ ያሉ ወይም ጠቆር ያለ ከለር የያዙ ሊሆኑ ይችላሉ።
💥የፎሊክ አሲድ እጥረት ምን ችግር ሊያመጣ ይችላል?
* በእርግዝና ወቅት የፎሊክ አሲድ እጥረት ካለ የአከርካሪ አጥንት ክፍተት (neural tube defect) ሊያመጣ ይችላል፡፡ ይህም የጭንቅላት ሽፋን በትክክል አለመሰራት ወይም ክፍተት እና የጀርባ አጥንት ክፍተት ሊያመጣ ይችላል።
💥ችግሩን እንዴት መከላከል ይችላል?
* ፎሊክ አሲድ ከማርገዝ 2 ወር በፊት እና ከተረገዘ በኃላ ለመጀመሪያው 1 ወር መውሰድ ችግሩ የመከሰቱን እድል በ 70% ይቀንሳል፡፡
* በመሆኑም በተለይ የሚከተሉት ከፍተኛ ተጋላጭ የሆኑ ሴቶች 4 mg በየቀኑ እንዲወስዱ ይመከራል፡፡ እነኚህም:-
1️⃣ ከዚህ እርግዝና በፊቱ ችግሩ የነበረባቸው ወይንም በቤተሰብ ችግሩ ተከስቶ ከነበረ
2️⃣ ቫልፕሮይክ አሲድ (valproic acid) እና ካርባማዜፒን (carbamazepine) የተባሉ የሚጥል በሽታ መድሀኒቶችን የሚወስዱ ሴቶች
🧿** ሌሎች ሴቶች እንደየ አስፈላጊነቱ ከ 0.4 – 0.8 mg ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ መውሰድ የሚኖርባቸው ሲሆን ከእርግዝና በፊት የሐኪም ምክር ማግኘትና አስፈላጊውን ክትትል ማድረግ ተገቢ ይሆናል፡፡
🧿 ፎሊክ አሲድ ከመውሰድ ባሻገር እርግዝና ሲከሰት በመጀመሪያዎቹ 20 ሳምንታት የአፈጣጠር ችግር መኖር አለመኖሩን በአልትራሳውንድ በመታየትና ችግሩ የተገኘባት እርጉዝ ሴትም ከማህፀንና ጽንስ ሐኪሟ ጋር የችግሩን መጠን ማወቅ አስፈላጊ ይሆናል፡፡
🧿ፎሊክ አሲድ በውስጣቸው የያዙ ምግቦች
🥜🫘ጥራጥሬዎችን :- ሽምብራ፣ ባቄላ ፣ ምስር፣ የበቀለ አኩሪ አተር ፣ ማሽላ
🐟🐠 ዓሳዎችን ፣
🍄 እንጉዳዮችን ፣
🥦🥒🥬🧅አትክልቶችን :- ስፒናች፣ ፓርሴል፣ ጎመን፣ ሰላጣ፣ ብሮኮሊ፣ ቀይ ሽንኩርት፣
🥑🥭🍌ፍራፍሬዎችን:- አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ ሙዝ፣ እንጆሪ
🫕 🥛🍳አይብ፣ ወተት እና እንቁላል አስኳል
🥓🥩🍗የስጋ ተዋፅዎች :- ጉበት፣ የዶሮ ስጋ
💥ፎሊክ አሲድ እና እርግዝና💥
ፎሊክ አሲድ (Folic acid) ፕሮቲኖች እና የቀይ የደም ህዋስ ንጥረ ነገር የሆነውን Hemoglobin ሄሞግሎቢንን ለመፍጠር አስፈላጊ የሆነ የቫይታሚን አይነት ሲሆን፤ በሌላ ስሙም ቪታሚን ቢ 9 (vitamin B₉) በመባል በባለሙያዎች ይጠራል፡፡
💥የፎሊክ አሲድ እጥረት ምን ችግር ሊያመጣ ይችላል?
* በእርግዝና ወቅት የፎሊክ አሲድ እጥረት ካለ የአከርካሪ አጥንት ክፍተት (neural tube defect) ሊያመጣ ይችላል፡፡ ይህም የጭንቅላት ሽፋን በትክክል አለመሰራት ወይም ክፍተት እና የጀርባ አጥንት ክፍተት ሊያመጣ ይችላል።
💥ችግሩን እንዴት መከላከል ይችላል?
* ፎሊክ አሲድ ከማርገዝ 2 ወር በፊት እና ከተረገዘ በኃላ ለመጀመሪያው 1 ወር መውሰድ ችግሩ የመከሰቱን እድል በ 70% ይቀንሳል፡፡
* በመሆኑም በተለይ የሚከተሉት ከፍተኛ ተጋላጭ የሆኑ ሴቶች 4 mg በየቀኑ እንዲወስዱ ይመከራል፡፡ እነኚህም:-
1️⃣ ከዚህ እርግዝና በፊቱ ችግሩ የነበረባቸው ወይንም በቤተሰብ ችግሩ ተከስቶ ከነበረ
2️⃣ ቫልፕሮይክ አሲድ (valproic acid) እና ካርባማዜፒን (carbamazepine) የተባሉ የሚጥል በሽታ መድሀኒቶችን የሚወስዱ ሴቶች
🧿** ሌሎች ሴቶች እንደየ አስፈላጊነቱ ከ 0.4 – 0.8 mg ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ መውሰድ የሚኖርባቸው ሲሆን ከእርግዝና በፊት የሐኪም ምክር ማግኘትና አስፈላጊውን ክትትል ማድረግ ተገቢ ይሆናል፡፡
🧿 ፎሊክ አሲድ ከመውሰድ ባሻገር እርግዝና ሲከሰት በመጀመሪያዎቹ 20 ሳምንታት የአፈጣጠር ችግር መኖር አለመኖሩን በአልትራሳውንድ በመታየትና ችግሩ የተገኘባት እርጉዝ ሴትም ከማህፀንና ጽንስ ሐኪሟ ጋር የችግሩን መጠን ማወቅ አስፈላጊ ይሆናል፡፡
🧿ፎሊክ አሲድ በውስጣቸው የያዙ ምግቦች
🥜🫘ጥራጥሬዎችን :- ሽምብራ፣ ባቄላ ፣ ምስር፣ የበቀለ አኩሪ አተር ፣ ማሽላ
🐟🐠 ዓሳዎችን ፣
🍄 እንጉዳዮችን ፣
🥦🥒🥬🧅አትክልቶችን :- ስፒናች፣ ፓርሴል፣ ጎመን፣ ሰላጣ፣ ብሮኮሊ፣ ቀይ ሽንኩርት፣
🥑🥭🍌ፍራፍሬዎችን:- አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ ሙዝ፣ እንጆሪ
🫕 🥛🍳አይብ፣ ወተት እና እንቁላል አስኳል
🥓🥩🍗የስጋ ተዋፅዎች :- ጉበት፣ የዶሮ ስጋ
ይህንን ሰለ ማህፀን እና ፅነስ መወያያ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ፤ ብዙ ያተርፋሉ! መልካም ጊዜ! 👇👇
