en
Feedback
ዶ/ር ዳዊት መስፍን (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት)

ዶ/ር ዳዊት መስፍን (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት)

Open in Telegram

**ጠቅላላ የማህፀንና ፅንስ ጉዳዬችን ማማከር** - ቅድመ ወሊድ - ስለ ወሊድ አገልግሎት - ስለ መካንነት ምርመራ እና ህክምና - በተለያዩ ምክንያቶች ከማህፀን ለሚወጣ ደም እና ፈሳሽ ምክንያና ህክምና - ለወር አበባ መዛባት ምክንያት እና መፍትሄ - ስለቅድመ ካንሰር ምርመራና የምክር አገልግሎት... 0911138054📞

Show more
5 833
Subscribers
-224 hours
-127 days
-4030 days
Posts Archive
💥 ድንግልና Vs ሀይመን (Hymen)💥 📌 ሀይመን (Hymen) የሴት የመራቢያ አካል ወደ ሆነው ማህፀን መግቢያ /vagina/ በር ላይ ያለ ስስ እና መለጠጥ የሚችል አካል ሲሆን 📌 ከሰው ሰው የተለያየ አይነት ቅርፅ ሊኖረው ይችላል፤ አንዳንዶች ላይ በተፈጥሮ የሌለ ሲሆን አንዳንዶች ላይ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ የማህፀን መግቢያውን (Vagina) ደፍኖ ሊገኝ ይችላል። 📌 ሀይመን (Hymen) በሰው ልጅ ላይ ብቻ የሚፈጠር አካል ሳይሆን በተለያዩ እንስሶች ላይም ይገኛል ለምሳሌ እንደ ፈረስ፣ ዝሆን፣ አሳ ነባሪ ፣ ቺምፓንዚ እና የመሳሰሉት 📌 ሀይመን (Hymen) የሰው ልጅ ፅንስ 5 ወር ላይ እያለ የሚፈጠር አካል ሲሆን ፥ ከወሊድ በፊት ወይም ከወሊድ በውሀላ ቀዳዳው ይከፈታል። በጊዜ ሂደት የተለያየ የቀዳዳ መጠኖችንም ይይዛል። 📌 ሀይመን (Hymen) ሊወጠርና ሊቀደድ የሚችል አካል ሲሆን፤ ይህም በተለያዩ ድርጊቶች ሊሆን ይችላል። እነኚህም :- የግብረ ስጋ ግንኙነት፣ የወር አበባ መፀዳጃ(Tampons) መጠቀም፣ የጣት የማህፀን ምርመራ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ( የፈረስ ግልቢያ፣ ሳይክል፣ ስፕሊት… ) ፣ በመራቢያ አካል አካባቢ የሚደርሱ አደጋዎች እና የመሳሰሉት ሊሆኑ ይችላሉ። 💥 ድንግልና Vs የድንግልና ምርመራ(Virginity Test)??💥 📌 በአለም ጤና ድርጅት (WHO, 2018) በወጣ መረጃ መሰረት ከዚህ በፊት በጤና ተቋማት ውስጥ ድንግልናን ያመለክታል ተብሎ የሚታሰበውን የሴት ልጅ አካል (Hymen) አለ ወይም የለም ፣ ተገርስሷል ወይስ አልተገረሰሰም የሚለውን ለማወቅ የሚደረገው ምርመራ(Virginity Test) ከአካሏ(Hymen) የአፈጣጠር ሁኔታ እና በእንቅስቃሴዎች ምክንያት በመራቢያ አካል ላይ በሚደርሱ ጫናዎች በሚፈጠር የቅርፅ ለውጥ ምክንያት አለ ወይም የለም ብሎ በእርግጠኝነት መናገር የማያስችል መሆኑ ተረጋግጧል 📌 በተጨማሪም ወሲባዊ ጥቃት በደረሰባቸው ሴቶች ላይ ምርመራውን ማድረግ ከፍተኛ የሆነ የህመም ስሜት እንዲሁም የመጀመሪያውን የጥቃቱን ጊዜ አይነት ስሜት ቀስቃሽ ሁኔታ መፍጠር የሚያመጣ ሲሆን ሴቲቱ ለህይወቷ የሚያሰጋ ደረጃ ላይ ለምሳሌ እንደ ደም መፍሰስ እና የመሳሰሉት አደጋዎች መኖራቸው ለማረጋገጥ እና ህክምና ለመስጠት ካልሆነ በስተቀር በምርመራው ሀይመን(Hymen) በድርጊቱ ተገርስሷል( ድንግል አይደለችም) ወይም አለ( ድንግል ነች) ማለት በፍፁም አይቻልም ወይም አያስደፍርም። 📌 እንደ WHO መረጃ የድንግልና ምርመራ የሴትን ልጅ የፆታዊ እኩልነት የጣሰ የምርመራ አይነት የሚል ሲሆን ይህም ሴቶች ላይ ብቻ ያነጣጠረ እና የወንዱን ድንግልና ከጥያቄ ውስጥ የማያስገባ ነው፤ ይህ ደሞ ኋላ ቀር ያረጀ ያፈጀ አስተሳሰብ ይለዋል። 📌 ከዚህም ጋር ተያይዞ የ1964ቱን World Medical Association’s Declaration of Helsinkiን በማጣቀስ ጤና ባለሙያዎች ይህንን የድንግልና ምርመራ(Virginity test) ማድረግ “መጀመሪያ ሰው ላይ ጉዳት አታድርስ - first, do no harm” የሚለውን ህግ ስለሚጥስ ለተጠያቂነት ይዳርጋል ይላል። 👉 አስተውል!! 📌 በመጀመሪያ ግንኙነት ደም አላየህም ማለት ሚስትህ/ጓደኛህ ድንግል ነች አይደለችም የሚለውን አይነግርህም 📌 ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሴቶች (~63%)ቱ በመጀመሪያ ግንኙነት ምንም አይነት ደም አይኖራቸውም 📌 ባለቤትህ/ ጓደኛህ ድንግል መሆኗን ለማወቅ እሷን መጠየቅ ብቻ በቂ ነው!! 💥መልካም ምሽት!!💥

💥ድንግልና(Virginity)💥 📌 ድንግልና ባለማችን ላይ ይህ ነው የሚባልና ሁሉንም ሊያስማማ የሚችል ትርጓሜ የሌለው ቃል ሲሆን ይህም የሆነበት ምክንያት በጊዜ ለውጥ ፣ ከቦታ ቦታ፣ ከማህበረሰቡ
+3
💥ድንግልና(Virginity)💥 📌 ድንግልና ባለማችን ላይ ይህ ነው የሚባልና ሁሉንም ሊያስማማ የሚችል ትርጓሜ የሌለው ቃል ሲሆን ይህም የሆነበት ምክንያት በጊዜ ለውጥ ፣ ከቦታ ቦታ፣ ከማህበረሰቡ ባህል እና ሀይማኖት አንፃር የተመሰረተ እይታ ስላለው ነው። 📌 በደፈናው ሲተረጎም ግን ከዚህ በፊት ግንኙነት አድርጋ የማታውቅ እንስት “ድንግል” የሚለው ስያሜ ይሰጣታል። 📌 ድንግልና በማህበረሰቡ የተሰጠው የባህል እና የሀይማኖት ትርጓሜ እንጂ ምንም አይነት በሳይንስ ወይም በህክምና ጥበብ ትርጓሜ ሊሰጠው የሚችል ወይም በምርመራ ታይቶ ሊረጋገጥ የሚችል ነገር አይደለም።

🌟አንዲት እርጉዝ እናት መቼ ነው ግፊት አለባት የሚባለው?🌟 💡 አንዲት እርጉዝ እናት ግፊት አለብሽ የምንለው ግፊቷ ከ 140 በ 90 በላይ ሲሆን ይህም ማለት የላይኛው ግፊት(systolic) ከ 140 እና ከዛ በላይ የታችኛው(Diastolic) ከ 90 እና ከዛ በላይ ከሆነ ፤ ይህም በአንድ ጊዜ ሳይሆን በሁለት ጊዜ ልኬት በ4 ሳዓታት ልዩነት መሆን አለበት። 💡 የእርግዝና ጊዜ ግፊት ለመባል ግፊቱ የተከሰተው ከ 20 ሳምንት(ከ 5 ወር) በውሀላ መሆን ይኖርበታል። 🌟አንዲት እርጉዝ ሴትን በእርግዝና ጊዜ ለግፊት የሚያጋልጧት ነገሮች ምንድን ናችው?🌟 💡 በቤተሰብ የደም ግፊት ከነበረ በእናት ወይም በእህት 💡 በልጅነት እድሜ የተከሰተ እርግዝና ከ 20 አመት በታች 💡 እድሜ ገፍቶ የተከሰተ እርግዝና ከ 40 አመት በላይ 💡 ባለቤቷን ከቀየረች ይህም ማለት በፊት ሌላ ባል ኖሯት አሁን ደግሞ አዲስ ባል ካገባች በተለይ አሁን ያገባችው ባለቤቷ በፊት የነበረው ሚስት እርግዝና ላይ ግፊት ኖሯት ከነበረ 💡 ከእርግዝና በፊት ግፊት ከነበረ 💡 በበፊት እርግዝና ግፊት ከነበረ 💡 ከፍተኛ የሰውነት ውፍረት 💡 ሌሎች የስኳር እና የኩላሊት ህመሞች ከመፀነሷ በፊት ከነበረ 💡 መንታ እና ከዛ በላይ እርግዝና ካለት ተጠቃሽ ናቸው። 🌟በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የደም ግፊት መጨመር ምልክቶች ምንድን ናቸው?🌟 💡 ከፍተኛ የሆነ የራስ ምታት, ይህም በራስ ምታት መድሀኒት የማይመለስ እና የማይቆራረጥ 💡 አይን ብዥ ማለት፣ መጨለም 💡 ጨጓራ በሚያመን ቦታ እና በላይኛው ቀኝ የሆዳችን ክፍል ከፍተኛ የሆነ ህመም 💡 የሰውነት ማበጥ በተለይ በፊታችንና በአይናችን ዙሪያ ፣ ሆዳችን እና እግራችን 💡 በላብራቶሪ የሚታዩ የላብራቶሪ ችግሮች በተለይ የደም ውጤት ላይ፣ የጉበት ምርመራዎች ላይ፣ እና የኩላሊት ምርመራዎች ላይ ችግር ካለ 💡 የሽንት መጠን መቀነስ ካለ እና ላብራቶሪ ላይ የኘሮቲን መጠን ከጨመረ 💥💥 ከላይ ላሉት ስሜቶች የህክምና እርዳታ ካላገኘሽ 👇👇 💡 እራስን መሳት 💡 አረፋን መድፈቅ ፣ ማንቀጥቀጥ 💡 እስከ ህይወት ህልፈት 🌟በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት ግፊትን እንዴት መከላከል ይቻላል?🌟 💡 ቅድመ ወሊድ ክትትል:- ይህም ግፊቱን በቶሎ እንዲገኝ እና መድሀኒትም ካስፈለገ ለመጀመር፣ ክትትልም መጨመር ካስፈለገ እንዲጨመር፣ ሀኪም ቤትም ገብተሽ ተኝተሽ መታከም ካስፈለገሽ ለመወሰን ይረዳል። 💡 የበፊት እርግዝናሽ ላይ ግፊት ተከስቶ ከነበረ እና በዚህኛው ላይ ግፊቱ ከፍተኛ እንዳይሆን ወይም ቀድሞ ከዘጠኝ ወር በፊት በመምጣት ፅንሱ ላይ እና እናትየው ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ገና ከ3 እስከ 4 ወር አካባቢ ሊጀመርልሽ የሚችል መድሀኒት ይኖራል። 💡 ከላይ የዘረዘሩትን የግፊቱን ምልክቶች በማስተዋል እና ቶሎ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ችግሩ ወደ ከፋተኛ ደረጃ ደርሶ እናትም ላይ ፅንሱም ላይ ችግር ሳያደርስ ቶሎ መከላከል ይቻላል። 🌟ህክምናው🌟 💡 ህክምናው የሚሆነው እንደተከሰተው የእርግዝና ላይ ያለ የግፊት አይነት ሲሆን፤ 💡 ከዘጠኝ ወር በፊት ከሆነ እንደየ ግፊቱ አይነት በጣም አጭር የቅድመ ወሊድ ክትትል ቀጠሮዎችን በመስጠት እና ለደም ግፊት የሚሆኑ መድሀኒቶችን በመስጠት ወይም ደግሞ ሆስፒታል በመግባት አልጋ ይዘሽ ፅኑ የሆነ ክትትል ላንቺም ለፅንሱም እየተደረገ ህክምናው ሊሰጥሽ ይችላል። 💡 ሀኪምሽ ከፍተኛ የግፊት ደረጃ ላይ ከሆንሽ እና ከላይ የተጠቀሱት የግፊት ምልክቶች ካሉሽ በመድሀኒት ግፊትሽን በማስተካከል ሊከሰቱ የሚችሉትን አደጋዎች ባንቺ ላይ( ደም መፍሰስ፣ ማንቀጥቀጥ፣ እራስ መሳት እና ሞት ሳይከሰት) በፅንሱም( ውሀው ማነስ፣ ፅንስ መቀንጨር፣ ህይወት ማለፍ) ሳይኖር መቆጣጠር ይቻላል። 💡 ሀኪምሽ አሁንም እርግዝናው ላይ እንደተከሰተውን የግፊት አይነት በመለየት ፣ እንዳሳየሽው የግፊት ምልክት እና የላቦራቶሪ ውጤቶች መሰረት መቼ እንደምትወልጂ ይወስናል። ⚠️ አስተውይ:- ይህ በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት ግፊት እድሜ ሲገፋ ከሚከሰተው ግፊት በዋነኝነት የሚለየው ግፊቱ የሚገናኘው ከእንግዴ ልጁ ጋር ስለሆነ ነው። ስለዚህ ግፊቱ የሚጠፋው ልጁ ሲወለድ እና እንግዴ ልጁ ሲወጣ ብቻ ነው!⚠️

🌟በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት ግፊት (Hypertension in pregnancy)🌟🌟 💡 ይህ የእርግዝና ጊዜ ግፊት 10% የሚሆነው እርግዝና ላይ የሚከሰት ሲሆን 💡 እርጉዝ እናት ላይ ከፍተኛ ችግ
+2
🌟በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት ግፊት (Hypertension in pregnancy)🌟🌟 💡 ይህ የእርግዝና ጊዜ ግፊት 10% የሚሆነው እርግዝና ላይ የሚከሰት ሲሆን 💡 እርጉዝ እናት ላይ ከፍተኛ ችግር ከሚፈጥሩት እና ለሞት በመዳረግ ከሚታወቁት ከማህፀንና እንግዴ ልጅ ደም መፍሰስ እና ኢንፌክሽን ቀጥሎ በሶስተኛነት የእናት ሞትን በማምጣት ይታወቃል።

📌 ይህ የወንዶች መከላከያ ከዘር ፍሬ የሚወጣውን የዘር ህዋስ(sperm) የሚያጓጉዘውን የዘር ፈሳሽ ቱቦ (vas deference) በመቁረጥ እና በማሰር የሚከናወን ነው። 🔍 እውነታዎች 👉 99% (1 ወይም 2 ሴቶች ከ 1000ሴቶች በ1 ዓመት ውስጥ) እርግዝና ሊከሰትባቸው ይችላል፤ ይህም እጅግ አስተማማኝ መከላከያ መሆኑን ያሳያል 👉 በቀላሉ ሊሰራ የሚችል ኦፕሬሽን ነው፤ በቀላል ማደንዘዣ አልጋ የማያሲዝ ⁃ ከኦፕሬሽኑ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ችግር እጅግ አናሳ ነው ⁃ ለሴት ትቦ መቋጠር ከሚወጣው ገንዘብ አንፃር ሲታይ እጅ አነስተኛ ወጪ ነው ሚያስወጣው ⁃ ከኦፕሬሽኑ በውሀላ ምንም አይነት የግንኙነት ብቃት ማነስ አይኖርም ወይም ደግሞ ይህ ነው የሚባም የዘር ፈሳሽ ማነስ አይኖርም 📌 ቫሴክቶሚ(Vasectomy) ከተሰራ በውሀላ ግንኙነት ለ 2 እስከ 4 ወር አይፈቀድም ይህም የሆነበት ዋነኛው ምክንያት በተቆረጠው በላይኛው ትቦ ውስጥ የዘር ህዋሶች ሊኖሩ ይችላሉ እናም ሙሉ ለሙሉ ለመጥራት በትንሹ ከ 2 እስከ 4 ወር ይፈጃል። በመጨረሻ ሊረጋገጥ የሚችለው የዘር ፈሳሽ ምርመራው ምንም የዘር ህዋሶች ከሌሉት ብቻ ይሆናል፤ ስለዚህ እስከጊዜው ድረስ ተጨማሪ መከላከያ መጠቀም ግድ ያስፈልጋል። 📌 ልክ ከኦፕሬሽኑ በውሀላ የሚጠበቁ ህመሞች ⁃ መድማት አንዳንዴ ደም መቆጠር ከዘር ማቀፊያው ስር ⁃ አንዳንዴ እንደማንኛውም ኦፕሬሽን ኢንፌክሽን መፈጠር ⁃ የተወሰነ የዘር ፍሬ ማቀፊያ (scrotum) ማበጥ እና ህመም መሰማት 📌 ከቆይታ በውሀላ ሊከሰቱ የሚችሉ ሁኔታዎች ⁃ አንዳንዴ ዘላቂ የሆነ ህመም ⁃ በዘር ፍሬ ማቀፊያ ውስጥ እብጠቶች ⁃ አለመሳካት እና እርግዝና መከሰት ⁃ ሀሳብን መቀየር እና ከ እደገና አባት ለመሆን መፈለግ 💥 አንድ ጊዜ ቫሴክቶሚ(Vasectomy) ከተሰራ በውሀላ ከንደገና ልጅ እንዲኖረን ብንፈልግ ይቻላል መመለስ??💥 ⁃ ቫሴክቶሚ(Vasectomy) ከተሰራ በውሀላ ለመመለስ ከንደገና ኦፕሬሽን ማድረግ ሊያስፈልግ ቢችልም ተመልሶ የማስረገዝ ብቃት ግን አጠያያቂ ይሆናል፤ ይህም የሆነበት ዋናው ምክንያት ከመጀመሪያው ሰርጀሪ ይልቅ ከበድ ያለ እና የመሳካት እድሉም ዝቅተኛ ስለሆነ ነው። ⁃ የተሻለ የሚባለው የመመለሻ መንገድ ከዘር ፍሬዎቹ ላይ የዘር ህዋሶችን በናሙና መውሰድ ሲሆን ፤ የተወሰዱትን ደግሞ IVF(Invitro Fertilization) በተባለ ዘመናዊ የህክምና መንገድ ውጭ ላይ ከሴት እንቁላል ጋር በማቀላቀል ወደ ማህፀን የመክተት መንገድ ይሆናል። ዶ/ር ዳዊት መስፍን(የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት)

💥ቫሴክቶሚ(Vasectomy)💥 📌 ይህ የወንዶች የወሊድ መከላከያ መንገድ ሲሆን በቀላል የኦፕሬሽን ሂደት ወይም የዘር ፍሬ አቃፊው አካባቢ ብቻ በሚሰጥ ማደንዘዣ የሚከናወን ነው። 📌 የወሊድ መቆ
+2
💥ቫሴክቶሚ(Vasectomy)💥 📌 ይህ የወንዶች የወሊድ መከላከያ መንገድ ሲሆን በቀላል የኦፕሬሽን ሂደት ወይም የዘር ፍሬ አቃፊው አካባቢ ብቻ በሚሰጥ ማደንዘዣ የሚከናወን ነው። 📌 የወሊድ መቆጣጠሪያ መንገዱ ዘላቂ ፣ ችግር የማያመጣ እና እጅግ አስተማማኝ የሚባል የወሊድ መከላከያ ሲሆን ባል የልጅ ፍላጎቱ ሲያበቃ ወይም ሲቆርጥለት የሚወሰን ይሆናል

እና ጭንቀት መካንነትን ያመጣል❓❓ 👉 ጥናቶች አሁንም እንደሚያሳዩት እርግዝና አልፈጠር ያላቸው ሴቶች ላይ እናም ይህ ነው የሚባል ጭንቀት የሌላቸው ውስጥ ጭንቀት አለመኖር በራሱ ብቻውን እርግዝና እንዲፈጠር አያደርግም ፤ ነገር ግን ጭንቀትን መቀነስ ለእርግዝና የሚደረጉ ህክምናዎች ላይ አዎንታዊ ተፅዓኖ እንዳለው ያሳያል 👉 የስነ ልቦና ተፅዓኖ የሚያመጣቸው ድብርት እና ጭንቀት ሀይፖታለመስ (Hypothalamus) የተባለውን የጭንቅላታችንን ክፍል በማነቃቃት ቫሶፕሬሲን(Vasopressin) እና ኮርቲኮትሮፒን ሪሊዚንግ ሆርሞን(Corticotropin releasing hormone) የተባሉ ንጥረ ነገሮች እንዲመነጩ ያደርጋል ፤ ኮርቲኮትሮፒን ሪሊዚንግ ሆርሞንም (Corticotropin releasing hormone) በበኩሉ ፒቱታሪ (Pituitary) ከተባለ የጭንቅላት ክፍል አድሪኖኮርቲኮትሮፒክ ሆርሞንን (Adrinocorticotropc hormone) እንዲመነጭ ያደርጋል። ይህ የመነጨው ንጥረ ነገረ‍ ኩላሊታችን ላይ የምትገኝ አድሬናል ኮርቴክስ (Adrenal Cortex) የተባለች አካልን በማንቃት ኮርቲሶል (Cortisol) እና ግሉኮ ኮርፒኮይድ (Glucocorticoid) የተባሉ ንጥረ ነገሮች እንዲመነጩ ያደርጋል። የኮርቲሶል (Cortisol) መጨመር እንቁላል በትክክል እድገቱን እንዳይጨርስ እና እንቁላል መለቀቅን የሚያዘገይ ሲሆን የግሉኮ ኮርፒኮይ (Glucocorticoid) መጨመር ደግሞ ሀይፖታለመስ (Hypothalamus) የተባለውን የጭንቅላት ክፍል በትክክል ስራውን እንዳይሰራ እና ለወር አበባ እና እርግዝና የሚጠቅሙ ንጥረ ነገሮችን ወይም ጎናዶትሮፒንስ (Gonadotropins) በትክክል እንዳይለቀቁ ያደርጋል። በዚህ ምክንያት እርግዝና እንዳይፈጠር ጫና ይፈጥራል ማለት ነው። ጭንቀት እና ድብርት በተጨማሪ የሚያመጡት ችግሮች:- 💥የእንቅልፍ ሂደታችንን ያበላሻሉ ይህም ብዙ መተኛት ወይም ትንሽ መተኛት 💥አመጋገባችንን ማበላሸት ይህም አለመመገብ ወይም ብዙ መመገብ 💥ጤናማ እንቅስቃሴ አለማድረግ ይህም ሙሉ ለሙሉ እንቅስቃሴ አለማድረግ ወይም ከመጠን በላይ ማድረግ 💥ለአልኮል እና ሲጋራ ለመሳሰሉ ሱሶች መጋለጥ 💥ለግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎት ማጣት በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው ጭንቀትን ሙሉ ለሙሉ ማጥፋት ቢከብድም እንዴት መቀነስ ይቻላል? ጨንቀትን ለመቀነስ የሚጠቅሙ ብዙ መንገዶች ያሉ ሲሆን ከነኚህ የሚከተሉት ይጠቀሳሉ 📌የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ 📌የስነ ልቦና ሀኪምን ማማከር 📌ሙዚቃ ማዳመጥ 📌የማሳጅ አገልግሎትን መሞከር 📌መፅሀፍቶችን ማንበብ 📌በተመሳሳይ ችግር ውስጥ ያሉ ሰዎች ጋር ሀሳብን መለዋወጥ 📌ዮጋ(Yoga) እና ሜዲቴሽን(Meditation) ይጠቀሳሉ 👉 ስለዚህ ጭንቀትን ሙሉ ለሙሉ ማጥፋት ቢከብደም፤ ከላይ የተጠቀሱትን ነገሮች በመጠቀም ለመቀነስ መሞከር በጭንቀት ምክንያት የምንወስናቸውን ውሳኔዎች እና የህክምና ሂደቶች ከማበላሸት እንቆጠባለን። ዶ/ር ዳዊት መስፍን(የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት)

💥ጭንቀት እና እርግዝና💥 እርግዝና አለመከሰት ጭንቀትን ያመጣል ፤ ጭንቀትስ እርግዝናን ይከለክል ይሆን?🤔 👉 ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከ8 እጮኛሞች (ወይም 12% ከሚሆኑት የተጋቡ ባልና ሚስት)
+1
💥ጭንቀት እና እርግዝና💥 እርግዝና አለመከሰት ጭንቀትን ያመጣል ፤ ጭንቀትስ እርግዝናን ይከለክል ይሆን?🤔 👉 ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከ8 እጮኛሞች (ወይም 12% ከሚሆኑት የተጋቡ ባልና ሚስት) 1ኛዎቹ እርግዝና ባለመከሰት ወይም የተፈጠረ እርግዝና ባለመሳካት ሁኔታ ውስጥ ይኖራሉ 👉 እርግዝና አለመፈጠር እንዳለ ሆኖ ባለትዳሮቹ የሚሰማቸውን ስሜት ለቤተሰብ ፣ ለጓደኛ በተለያዩ ምክንያቶች እኚህም በመሳቀቅ፣ ጥፋተኝነት ስሜት በመሰማት እና አነስተኛ የሆነ የራስ መተማመንን በማዳበር ምክንያት ጭንቀታቸውን አለማጋራት ከፍተኛ ለሆነ የስነ ልቦና ተፅዓኖን ይዳርጋቸዋል። 👉 ይህም የስነ ልቦና ተፅዓኖ ላልተፈለገ ድብርት ፣ ጭንቀት ፣ እራስን አለመንከባከብ እና ጥራት ያለው ኑሮን እንዳንኖሩ ያደርጋል

እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በዓሉ የደስታ፣ የሰላም ፣ የፍቅር፣ የጤና እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ!! ዶ/ር ዳዊት (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስ
እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በዓሉ የደስታ፣ የሰላም ፣ የፍቅር፣ የጤና እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ!! ዶ/ር ዳዊት (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት)

📌 የቀዶ ጥገና ቁስል መመርቀዝ(ኢንፌክሽን) በ3 አይነት ሁኔታ መክፈል የምንችል ሲሆን እነኙህም 👉 የላይኛው የቆዳ ሽፋን ብቻ በተህዋሲያን ሲጠቃ (superficial incisional surgical site infection) 👉 ከቆዳ ስር ባለው ስብ ላይ የተነሳ መመርቀዝ ( deep incisional surgical site infection) 👉 የውስጠኛው አካሎቻችን (ለምሳሌ:- በማህፀን) ላይ እና በማህከላቸው የተነሳ መመርቀዝ(ኢንፌክሽን) ( Organ/space infection) 💥ለቀዶ ጥገና ቁስል መመርቀዝ(ኢንፌክሽን) የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ምን ምንድን ናቸው?💥 📌 ብዙ ጊዜ ሆስፒታል ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች ከቀዶ ጥገና በውሀላ መቆየት 📌 በተለያዩ ምክንያቶች ደም ማነስ ካለ 📌 የሰውነትን የበሽታ መቋቋም የሚቀንሱ ነገሮች ካሉ:- እንደ HIV/AIDS, ማንኛውም አይነት የካንሰር በሽታ እና የካንሰር መድሀኒት መውሰድ 📌 የምግብ እጥረት ተጠቂ መሆን 📌 የስኳር በሽታ ካለ 📌 አልኮል አዘውትሮ መጠጣት እና ትምባሆ አጫሽ መሆን 📌 የግፊት፣ የኩላሊት እና የጉበት በሽታ ካለ 📌 በሆስፒታል ውስጥ በቀን ውስጥ የሚሰራው የኦፕሬሽን ብዛት 📌 የተሳራው የኦፕሬሽን አይነት 💥የቀዶ ጥገና ቁስል መመርቀዝ(ኢንፌክሽን) ምልክቶች ምን ምንድን ናቸው?💥 📌 ቁስሉ ላይ ከፍተኛ የሆነ ህመም ወይም መጠዝጠዝ 📌 ኦፕሬሽን የተሰራበት ቦታና አካባቢው መቅላት 📌 ኦፕሬሽን የተሰራበት ቦታና አካባቢው መሞቅ 📌 የቁስሉ ቦታ ማበጥ ከላይ ያሉትን አስተውለን ወደ ጤና ተቋም ካልሄድን 📌 ኦፕሬሽን ከተሰራበት ቦታ ፈሳሽ መውጣት ፤ ፈሳሹ ውሀ ወይም መረቅ የመሰለ ፈሳሽ መውጣት ሲበረታ እና መመርቀዙ ሲያል ደግሞ መግል ያለው ፈሳሽ መውጣት መጀመር 📌 ምን አልባት ኢንፌክሽኑ የውስጠኛው አካሎቻችን ላይ እና በማህከላቸው የተነሳ ከሆነ - መግል በውስጥ ላይ መጠራቀም ይህም ሆድ መነፋት ፣ ከፍተኛ የሆድ ህመም ፣ ትኩሳት ፣ ማንቀጥቀጥ፣ ሙሉ ሰውነት ጤና ማጣት ፣ መጫጫን 📌 በሽታው ሲቀጥል እና ካልታከመ ደግሞ ኦፕሬሽኑ አካባቢ ብቻ የነበረው ኢንፌክሽን በደም በመሰራጨት ሰውነት ሙሉ ማጥቃት እና በመጨረሻም መታከም ወደማይችልበት ደረጃ ደርሶ ለሞት ሊዳርግ ይችላል። 💥ከላይ ያሉት ምልክቶች ካሉ ምን ላድርግ?💥 📌 ከኦፕሬሽን በውሀላ ያለ የቆዳ ኢንፌክሽን ምልክቶች ካሉ :- በተቻለ አቅም ኦፕሬሽን ወደ ተደረግንበት ሆስፒታል መሄድ እና የሀኪም እርዳታ ማግኘት ያስፈልገናል 📌 ቁስሉ ፈሳሽ ካለው በቤት ውስጥ በተለያየ መንገድ ለማከም መሞከር ወይም ደግሞ ይድንልኛል ብሎ የተለያዩ አንቲባዮቲኮችን(Antibiotics) መውሰድ ከፍተኛ ለሆነ አደጋ ስለሚያጋልጥ ከዛ አይነት ድርጊት መቆጠብ 💥የቀዶ ጥገና ቁስል መመርቀዝ(ኢንፌክሽን) ህክምና ምን ይመስላል?💥 📌 የቀዶ ጥገና ቁስል መመርቀዝ(ኢንፌክሽን) እንደ ቁስሉ ያመጣው ምልክቶች ህክምናው ሊለያይ ይችላል። 📌 የኦፕሬሽን ቁስሉ ክፍተት ፈጥሮ ፈሳሽ ወይም መግል የሚወጣው ከሆነ :- ቁስሉ በተወሰነ ሁኔታ ወይም እንደ መግሉ መጠን ሙሉ ለሙሉ ተከፍቶ በጥሩ ሁኔታ መግሉ እስኪጠፋ እና ቁስሉ የመዳን ምልክት እስኪያሳይ ድረስ መፀዳት ያስፈልገዋል። የቁስሉ አፀዳድ የሚወሰነው እንደ ኢንፌክሽኑ መጠን ይሆናል። 📌 የቀዶ ጥገና ቁስል መመርቀዝ(ኢንፌክሽን) በሰውነታችን ላይ እንደ ትኩሳት ፣ ማንቀጥቀጥ ፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ የጤንነት ስሜት አለመሰማት እና የነጭ የደም ህዋስ መጠን መጨመር እስካላመጣ ድረስ ያለምንም አንቲባዮቲክስ(Antibiotics) ቁስሉን ብቻ በማፅዳት መተከም ይችላል፤ ነገር ግን ከላይ የተጠቀሱት ስሜቶች ካሉ አንቲባዮቲክስ(Antibiotics) ከቁስል ማፅዳቱ ጋር ግድ ያስፈልጋል። 📌 ሶስተኛው አይነት የቀዶ ጥገና ቁስል ኢንፌክሽን ካለ ይህም ማለት የውስጠኛው አካሎቻችን ላይ እና በማህከላቸው የተነሳ መመርቀዝ( Organ/space infection) ወይም በውስጥ ላይ መግል ቋጥሮ ከሆነ ግዴታ ከንደገና ኦፕሬሽን ተገብቶ መግሉን ማውጣት እና መግሉን ያመጣው ነገር ተለይቶ ታይቶ እንዳስፈላጊነቱ ኦፕሬሽን ማስተካከያ ሊደረግ ያስፈልጋል። ይህ በመድሀኒት ብቻ መታከም የማይችል እና ግዴታ ኦፕሬሽን የሚያስፈልገው ይሆናል። 💥ኢንፌክሽኑን እንዴት ልከላከል?💥 📌 ከኦፕሬሽኑ ከ 2 ቀን በውሀላ በንፁህ ውሀ እና ሳሙና መታጠብ እና በደረቅ ንፁ ጨርቅ ማድረቅ 📌 ሲያደርቁ አለመፈግፈግ 📌 ከፍተኛ ቦርጭ በተለይ ቁስሉ ላይ የሚተኛ አይነት ካለ በመቀነት ወደላይ ማሰር፤ ምክንያቱም ቁስሉ ላይ ከተኛ ለኢንፌክሽን እና ቁስሉ እንዲመረቅዝ ስለሚያደርግ 📌 የምታደርጊውም የውስጥ ልብስ ወይም ፓንት ከቁስሉ ጋር ለ1 ለ 2 ቀን አለማነካካት 📌 ከሀኪም የታዘዘ መድሀኒት ካለ በአግባቡ መጠቀም 📌 የአካልን እና ወሰውነትን ንፅህና መጠበቅ 📌 በተቻለ አቅም የተመጣጠነ ምግብ መመገብ 🍀መልካም ቀን ተመኘሁ🍀

💥የቀዶ ጥገና ቁስል መመርቀዝ(ኢንፌክሽን)💥 📌 የቀዶ ጥገና ቁስል መመርቀዝ(ኢንፌክሽን) ማለት ቀዶ ጥገና ከተሰራልን በውሀላ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ቁስሉ በበሽታ አምጪ ተህዋሲያን ሲጠቃና የተለ
+2
💥የቀዶ ጥገና ቁስል መመርቀዝ(ኢንፌክሽን)💥 📌 የቀዶ ጥገና ቁስል መመርቀዝ(ኢንፌክሽን) ማለት ቀዶ ጥገና ከተሰራልን በውሀላ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ቁስሉ በበሽታ አምጪ ተህዋሲያን ሲጠቃና የተለያዩ ምልክቶችን ማሳየት ሲጀምር ነው።

📌 ይህ መድሀኒት በውስጡ ሌቮኖጀስትሬል( Levonorgestrel) የተባለ ንጥረ ነገር የያዘ ሲሆን ፤ በተሻለ ሁኔታ ስራውን የሚሰራው ግንኙነት በተደረገ በተወሰኑ ሰዓታት ውስጥ ቢወሰድ ሲሆን ይህ ማለት ሰዓቶች በተቆጠሩ ቁጥር እርግዝናን የመከላከል አቅሙም እየቀነሰ እየቀነሰ የሚሄድ ይሆናል። 📌 ብዙን ጊዜ የ72 ሰዓቱ መድሀኒት ተብለው በየፋርማሲ ውስጥ የምናገኛቸው ሁለት አይነት ሲሆኑ አንደኛው Plan B One-step ( አንድ ፍሬ ብቻ የያዘ Levonogestrel 1.5 mg ሲሆን ) ሌላኛው እና አሁን ላይ ከገበያ እየወጣ ያለው ደግሞ ሁለት ፍሬ የያዘ Plan B የተባለው ሲሆን ይህም በ12 ሰዓት ልዩነት ውስጥ የሚወሰዱ ሁለት ፍሬ የያዘ ነው። 💥 መቼ ነው ፓስት ፒል(የ72 ሰዓት ድንገተኛ የወሊድ መከላከያ) መጠቀም ያለብን?💥 👉 በየቀኑ የሚወሰዱ የወሊድ መከላከያ ኪኒኖችን እረስተን ከሆነ ወይም ቀን ካሳለፍን 👉 ኮንዶም ከተቀደደ 👉 ምንም አይነት የወሊድ መከላከያ የማንጠቀም ከነበረ 💥 በምን ያህል ሰዓታት ውስጥ ነው ጥንቃቄ ከጎደለው ግንኙነት በውሀላ ፖስት ፒልን መውሰድ ያለብኝ?💥 👉 ፖስት ፒል እርግዝና በተሻለ መንገድ መከላከል የሚችለው በ72 ሰዓት ውስጥ ቢወሰድ ሲሆን ነገር ግን አወሳሰዱ ግንኙነት በተደረገ ጥቂት ሰዓቶች እና ሰዓት በሄደ ቁጥር የመድሀኒቱ የመከላከል ብቃት እየቀነሰ ይሄዳል። 💥 ፖስት ፒልን እንደዋና የወሊድ መከላከያ ሁሌ መውሰድ እችላለሁ? 💥 👉 ፖስት ፒልን ከአንድ ጊዜ በላይ በወር አበባ ጊዜ መውሰድ የሚቻል ቢሆንም ነገር ግን የተለያዩ የጎንዮሽ ችግሮች ስላሉት እንደ ዋና የወሊድ መቆጣጠሪያ ተደጋግሞ ባይወሰድ ይመከራል 💥 ፖስት ፒል እንዴት ነው እርግዝናን የሚከላከለው?💥 📌 ፖስት ፒል እርግዝና በተለያዩ መንገዶች ሊከላከል ይችላል፤ ይህም የመከላከል ብቃት የሚወሰነው ግንኙነት ከተደረገ በምን ያህል ሰዓታት ውስጥ ነው የተወሰደው እና በወር አበባ ዑደት ጊዜ መቼ ነው የተወሰደው የሚለው ወሳኝነት አለው። ይሁንና መድሀኒቱ በሚቀጠሉት መንገዶች እርግዝናን ይከላከላል:- 👉 እንቁላል ከእንቁላል ከሚለቀቅበት ቦታ(Ovary) እንዳይለቀቅ ወይም መለቀቁ እንዲዘገይ ያደርጋል:- እንቁላል ከመለቀቁ በፊት ከተወሰደ 👉 የወንድ ዘር(sperm) የሴቷን እንቁላል እንዳያገኝ የማህፀን በር ፈሳሽን ያወፍራል በዛም የወንድ ዘር በበቂ ሁኔታ እንዳይጓዝ ይከለክላል። 📌 የሰውነት ክብደት ያላቸው ሴቶች በተለይ BMI(Body Mass Index) ከ 30 በላይ የሆነ እና እንቁላል ከተለቀቀ በውሀላ ግንኙነት የሚያደርጉ ሴቶች ፖስት ፒል እርግዝናን የመከላከል አቅሙ አናሳ ስለሚሆን በማህፀን የሚቀበረውን ሉፕ(IUCD) ቢጠቀሙ ይመከራል። 📌 ፖስት ፒልን ከተጠቀምሽ በውሀላ ወደ ዘላቂ የወሊድ መከላከያ ለመዘዋወር ከፈለግሽ ትወስጂ ከነበረው መከላከያ (ለምሳሌ :- ቾይዝ) በተጨማሪ ለ7 ቀን ተጨማሪ መከላከያ መጠቀም ለምሳሌ ኮንዶም መጠቀም አልያም ደግሞ ግንኙነት አለማድረግ ያስፈልጋል። 💥 ፖስት ፒል ሊያስከስት የሚችላቸው የጎንዮሽ ችግሮች ምንድን ናቸው?💥 👉 መድሀኒቱን ከወሰድሽ በውሀላ በሳምንቱ ወይም በወሩ የተዛባ ከማህፀን የሚወጣ ደም ማየት 👉 ፖስት ፒል ከሌሎች የወሊድ መከላከያዎች አንፃር ሲታይ ከማህፀን ውጭ እርግዝና የማስከተል እድል ያለው ቢሆንም ያ እድል ግን ከ1% ያነሰ እና ከጥቅሙ ጋር ሲነፃፀር ጥቅሙ የበዛ ነው። 👉 ጊዜያዊ የሆኑ የጎንዮሽ ችግሮች:- እራስ ምታት፣ ማቅለሽለሽ ማስታወክ፣ የጡት ህመም፣ መጫጫን እና አንዳንዴም የሆድ ቁርጠት ሊሆኑ ይችላሉ። 💥የተሳሳቱና ማስተዋል ያለብን ነጥቦች💥 👉 ይህ መድሀኒት ጥንቃቄ ለጎደለው ግንኙነት እርግዝናን ለመከላከል ይወሰድ እንጂ ለአባላዘር በሽታ HIV/AIDSን ጨምሮ ምንም አይነት መከላከል አያደርግም። 👉 ይህ መድሀኒት በሌላ ስሙ MORNING AFTER PILL ይባል እንጂ ሁል ጊዜ ጠዋት እስኪመጣ ጠብቀን መዋጥ የለብንም 👉 ፖስት ፒል ወስደሽ ድንገት ብታረግዢ ፤ ፖስት ፒሉ ምንም አይነት ፅንሱ ላይ የሚያመጣው የአፈጣጠር ችግር ሆነ አደጋ አይኖርም 👉 ፖስት ፒል የተፈጠረ እርግዝናን ለማቆመረ አይጠቅምም ወይም ደግሞ የተፈጠረን እርግዝና ለማስወረድ አይጠቅምም 👉 ፓስት ፒል መጠቀም ምንም አይነት መካንነትን ወይም ደግሞ እርግዝና መከልከልን አያመጣም ፤ ፓስት ፒል በሰውነት ውስጥ ለተወሰኑ ቀናት ብቻ የሚቆይ መድሀኒት ነው። 💥ጥንቃቄ💥 👉 ፖስት ፒል በተፈጥሮ የሚመጣውን ፔሬድሽን በአንድ ሳምንት ጊዜ ሊያራዝም ወይም ሊያዛባው ስለሚችል ፔሬድሽን ከምትጠብቂበት ቀን ከ1 ሳምንት በላይ ከዘገየ የእርግዝና ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ ነው፤ እርግዝና ተከስቶ ሊሆን ስለሚችል 👉 ፖስት ፒል እንቁላል እንዳይለቀቅ ሊያዘገይ እና ከወንድ ዘር ጋር እንዳይገናኝ ሊያደርግ የሚችለው ለ5 እስከ 7 ቀን ነው ፤ የወንድ ዘር sperm cell ደግሞ በሴት ልጅ መራቢያ አካል ውስጥ ከግንኙነት በውሀላ ሊቆይ የሚችለው ለ 5 ቀን ነው ስለዚህ ፖስት ፒል ከወሰድሽ በውሀላ ባሉት ሰዓታት ውስጥም ከንደገና ግንኙነት ካደረግሽ ተጨማሪ ፓስት ፒል ብትወስጂ ይመከራል ምክንያቱም ከ 5 ቀን በላይ በሰውነትሽ ውስጥ የሚቆዩ የወንድ ዘር ህዋሳት ስለሚኖሩ እርግዝና ሊከሰት ስለሚችል። 👉 ፖስት ፒል ወስደሽ በ2 ሰዓታት ውስጥ አስታውኮሽ መድሀኒቱ ቢወጣ - ተጨማሪ ሌላ መውሰድ አትዘንጊ ✨መልካም ዕለተ ሰንበ✨

💥 ፓስት ፒል(የ72 ሰዓት ድንገተኛ የወሊድ መከላከያ)💥 📌 ይህ መድሀኒት plan B , Plan b one step ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ጥንቃቄ የጎደለው ግንኙነት ከተደረገ በውሀላ በ72 ሰዓት ው
+1
💥 ፓስት ፒል(የ72 ሰዓት ድንገተኛ የወሊድ መከላከያ)💥 📌 ይህ መድሀኒት plan B , Plan b one step ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ጥንቃቄ የጎደለው ግንኙነት ከተደረገ በውሀላ በ72 ሰዓት ውስጥ የሚወሰድና እርግዝና እንዳይፈጠር የሚያደርግ መድሀኒት ነው።

ጥር (January) በአለም አቀፍ ደረጃ ስለ ማህፀን በር ጫፍ ካንሰር የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር ተብሎ የተሰየመ ሲሆን ፤ ዘንድሮ ከታች ያለውን መሪህ መልእክት ያነገበ ነው:- “ አስቀድሞ በመመርመር
+1
ጥር (January) በአለም አቀፍ ደረጃ ስለ ማህፀን በር ጫፍ ካንሰር የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር ተብሎ የተሰየመ ሲሆን ፤ ዘንድሮ ከታች ያለውን መሪህ መልእክት ያነገበ ነው:- “ አስቀድሞ በመመርመር የማህፀን በር ካንሰርን መከላከል እና ማከም ይቻላል” “ Cervical Cancer Can be prevented and treated if caught early” እኔም ከዚህ በፊት ስለማህፀን በር ካንሰር በዚህ ቴሌግራም ቻናሌ ላይ የፃድኩትን ፅሁፍ ማስፈንጠሪያውን በመጫን ታነቡ ዘንድ ጋበዝኩ! መልካም ቀን!👇👇 👌 Part I - ስለማህፀን በር ጫፍ ካንሰር (Cervical Cancer) ማወቅ ያለቦት ነጥቦች። https://t.me/DrDawitMOBGYN/161 👌 Part II- የማህፀን ጫፍ ካንሰርን እንዴት መከላከል ይቻላል? https://t.me/DrDawitMOBGYN/167

👆👆👆የጥያቄውን መልስ እሁድ ስለ ፖስት ፒል (የ72 ሰዓቱ የወሊድ መቆጣጠሪያ መድሀኒት) በዚህ ቻናል ላይ Post በሚደረገው ፅሁፍ ላይ አብሮ ይብራራል።…. መልካም ቀን!!

“… ግንኙነት አደረግንና የ72 ሰአቱን ወሰድኩ እናም በንጋታው እንዲሁ ድጋሚ በስሜት ተነሳስተን አደረግን እና ከዛ አልወሰድኩም እንዴት ነው ማለት መድሀኒቱን በወሰድኩ በ24 ሰአት ውስጥ ነው ግንኙነት ያደረግነው እናም ታረግዛለሁ ወይስ … ”
Anonymous voting