cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ከፍልስፍና ዓለም ™

" አዋቂ ሰው ማለት ፍላጎቱን የመግታት እውቀቱ ከፍተኛ የሆነ ማለት ነው በሕይወት ዝቅተኛው ደረጃ ራስን በፍላጎት አጥር ውስጥ ማስቀመጥ ነው አብዛኛው የሰው ልጅ በብዙ ፍላጎትና በጥቂት እውቀት የተሞላ ነው ፤ አዋቂነት ግን ብዙ እውቀትና ጥቂት ፍላጎት ብቻ ይበቃታል አርተር ሾፐንሀወር

Show more
Advertising posts
5 859Subscribers
+3524 hours
+1937 days
+67330 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViewsSharesViews dynamics
01
https://theconversation.com/could-consciousness-all-come-down-to-the-way-things-vibrate-103070
2180Loading...
02
https://www.psypost.org/where-does-consciousness-come-from-it-could-all-be-vibrations/
260Loading...
03
ከበደ ሚካኤል ቀለል ባሉት ተራኪ ግጥሞቻቸው ከአገር በቀል እውቀት እስከ ፈረንጆቹ ፍልስፍና አንድም ሳይቀራቸው እውቀት ለማስተላለፍ ሞክረዋል። ‘ብርሃነ ሕሊና’ በሚል ርዕስ በ1933ዓም ከዛሬ ስምንት አስርት ዓመታት በፊት ባሳተሙት መጽሃፍ በአርስቶትል አንደበት እንዲህ ብለው ነበር፥ አሪስቶት አሪስቶት የሚባል ፈላስፋው መምህር ከሊቆች መካከል ቆሞ ሲያስተምር የወዳጅን ነገር ጠቅሶ ሲነግራቸው እንዲህ ሲል በምክሩ አስጠነቀቃቸው። ስሙኝ ልንገራችሁ ወዳጆቼ ሆይ ምንም ወዳጅ የለም በዚህ ዓለም ላይ። ለዚህ ላርስቶት ለትልቁ ሊቅ ወዳጆችህ ያንተን እውቀት በመናቅ ሲያሙህ ሰማናቸው ብለው ቢነግሩት እንኳን ማማት እና እሌለሁበት ቢደበድቡኝም አልቀየማቸው አሚታ አይጎዳኝም ሲል መለሰላቸው። እኛም እንደ አሪስቶት ምንም ባንሆን ሊቅ ይገባናል ዞትር አሚታን መናቅ አርስቶት= አርስቶትል ወይም ኤርስቶትል አሚታ= ሃሜት ስለሰው ክፉ ወሬ
6673Loading...
04
For those interested
8620Loading...
05
Media files
8202Loading...
06
ከሀሳብ አይደለም ከስልቱ ነው
1 0692Loading...
07
በአሉ ግርማን በ"የቀይ ኮኮብ ጥሪ" በኩል እንደታዘብነው socialist realism:- እንደ አንድ የኪነት ስልት በ1932 አካባቢ ተጀመረ ይላሉ...ጥበብ ፤ ለሰውልጅ ነፃነትን ደስታንና ዲሞክራሲን ለማስፈን የሚተጋውን የጭቁኑ ህዝብ ትግል ማገልገል መቻል አለበት ከሚል አዝማሚያ የተነሳ ይመስላል ...didactic use of literature, art, and music to develop social consciousness in an evolving socialist state.[1] socialist realism ጭቁኑን ትግል የሚያንፀባርቅ የጥበብ ስልት ተደርጎ ሊታይ ይችላል።The primary theme of Socialist Realism is the building of socialism and a classless society.In portraying this struggle, the writer could admit imperfections but was expected to take a positive and optimistic view of socialist society and to keep in mind its larger historical relevance.[2] በrealism እና በ socialist realism መካከል ያለው ልዩነት realism የህይወትን ነፀብራቅ ሊያሳየን ይሞክራል...ጥበብ የገሃዱ አለም ነፀብራቅ ነው በሚል መፈክር።"Realism is the attempt of art to capture life as realistically as possible."[3] በአንፃሩ ለsocialist realism ጥበብ የሰፊው ህዝብ ትግል ነፀብራቅ ነው።"Socialist realism differs from critical realism, not only in being based on a concrete socialist perspective, but also in using this perspective to describe the forces working towards socialism from the inside."[4] በዚህ መነሻነት ለኔ በአሉ ግርማ realist ደራሲ የሚለው ነገር አያስማማኝም socialist realismን የሚከተል ደራሲ ነው(ለኔ በአሉን ደራሲ ነው ብዬ ራሱ መጥራት ይቸግረኛል፤ በተለየ በ"የቀይ ኮኮብ ጥሪ" ውስጥ እልም ያለ የደርግ ፕሮፓጋንዲስት ሆና እንታዘበዋለን) በ"የቀይ ኮኮብ ጥሪ" ውስጥ የታዘብናቸው አብይ የስነፅሁፍ ህፀፆች 1 የጥበብ አረዳድ... በአሉ ስነፅሁፍን ለውበቱ ሳይሆን የራሱን ሀሳብና አመለካከለት ማንፀባረቂያ መንገድ አድርጎ ነው የተጠቀመው የራሱን ብቻ ሳይሆን በጊዜው ገዢ የነበረውን የፖለቲካ አስተሳሰብ ለመስበክም ይጋጋጣል...በመሰረቱ አንድ ጥበብ ውበት የሚኖረው ለጥበብነቱ የዋለ ጊዜ ነው ፤ ጥበብ የሆነ አይነት ዘርፍን ማገልገል ስትጀምር ጥበባዊ ለዛዋ ይሞታል....በአሉ በአተራረኩ የተወጣለት ቢሆንም አለማው ጥበባዊ ለዛ ሳይሆን የጭቁኑን ህዝብ ትግል ወይም የአብዮቱን "ቅዱሳዊነት" ማስተጋባት ነው። ጥበባዊ ለዛን ብለው ለሚመጡ አንባቢያን በጥበብ ስም ፖለቲካዊ ንትርክን ያጠጣ...አንዳንዴ የጥበባዊ ውበቱ አይሎብን ፖለቲካዊ ጥዝዛውን ችለን የምንቀበላቸው ስራዎች ይኖራሉ የበአሉ ግን ፅንፍ ይወጣል....በጣም ቋቅ ያለኝና በአሉ እልም ያለ ፕሮፓጋንዳስት ነው ያስባለኝ ..."ያብዮትና ያገር ፍቅር ከማንኛውም ፍቅር ይበልጥ ጠንካራ ነው። "(ገፅ-101)...ሚለው አባባል ነው፤ እንዴት አይተውት በአሉን የሚያንቆለጳጵሱት ስል ተገረምኩ 2 የንዑስ ታሪኮች ነገር በዚህ የቀይ ኮኮብ ጥሪ በሚለው ድርሰት ውስጥ ከዋናው ጭብጥ ጋር ፍፁም ግንኙነት የሌላቸው ሌሎች ንዑስ ታሪኮች እናነባለን... የድርሰቱ ዋና ጭብጥ በፍቅር ተጎዳ አሽከር እንዴት የአብዮቱን ጥሪ(የቀይ ኮኮብ ጥሪ) እንደተቀበለ ፤ እንዲሁም ይህ ሰው የአብዮቱን አደራ በመወጣትና የቀድሞ አሳዳሪዎቹ የዋሉለት ውለታ በፈጠረበት ስሜት መካከል የሚኖረው ጡዘት ነው....ነገር ግን በአሉ ትዝብቱን፣ ፖለቲካዊ አስተሳሰቡና ፕሮፖጋንዳውን ለማስተላለፍ ከዋናው የታሪክ ፍስት ጋር ትስስር የሌላቸው ሌሎች ተዳባይ ታሪኳችን ያስነበብናል...ይሄ የድርሰቱን ውበት ባያሌው አጉድፎታል ሲጀመርም ድርሰት ከተባለ ማለት ነው ከአላስፈላጊ ንዑስ ታሪኮች በተጨማሪ አላስፈላጊ ገፀባህርያትም ወዲያ ወዲህ ሲሉ ይታያሉ....ለምሳሌ ጌታቸው ሸዋሉል በድርሰቱ ውስጥ ተደጋግሞ ይነሳል ብዙ የገፅ ሽፋንም ተሰጥቶታል ነገር ግን ከዋናው የታሪክ ጭብጥ ጋራ ያለው ትስስር እጅግ የላላ ነው ለመፃፍ ባለኝ ስልቹነት የተነሳ ያልጠቀስኳቸው የበአሉ እልፍ ስህተቶች በ"የቀይ ኮኮብ ጥሪ" መፅሐፍ ውስጥ ታዝቢያለው መፅሐፉን ጨርሼ ስከድን እዚህ መፅሐፍ ላይ ያባከንኩት ጊዜ ፀፀተኝ... የተሻለ እይታ አለኝ የሚለንን ለማድመጥ ዝግጁ እንደሆንን ይሰመርበትና... [1] [2] Encyclopedia Britannica [3] social realism literature: studysmarter.com.uk [4]critical realism and socialist realism: springer.com ✡אומנות
1 1537Loading...
08
Media files
1 0361Loading...
09
አያን ሂርሲ አሊ ትባላለች። ከአራቱ ሞገደኛ ኢአማንያን ከዶዊክንስ ከሂችንስ ካሃሪስ እና ዴኔት ጋር በአቻነት የምትወሳ ነበረች። ወዳጃችን ሂችንስ ነፍሱ በአፀደ ገነት ትረፍና በሞት ከተለየን ቆየ። አያን ደግሞ ባሳለፍነው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ ገደማ ጥላን ላሽ ብላለች። ከኢአማኝነት ወደ ሐይማኖተኝነት የተቀየሩ ምሁራኖች ጥቂት አይባሉም። ግን "ለምን? ለምን? ለምን?" አለ በስንቱ። እኔ ደግሞ እዚህ ተጎልቼ "እንዴት ነው አንድ የተማረ የተመራመረ የሚባል ሰው በአንድ ወቅት ያለምንም ጥርጣሬ ሽንጡን ገትሮ ሲሟገትለት የነበረን አመለካከት በአንዴ አሽቀንጥሮ በተቃራኒው ጎራ መሰለፍ የሚችለው?" እያልኩ እጠይቃለሁ። መጨረሻዬን አሳምርልኝ እንጂ ሌላ ምን ይባላል።
1 3041Loading...
10
የዛሬውን አለምአቀፍ የመፅሀፍት ቀን በማስመልከት ማንኛውንም አይነት classic የልቦለድ፣የፍልስፍና፣የታሪክ ወይም የግጥም (ቧለቲካም ቢሆን)መፅሐፍት በስጦታ ልታበረክቱልኝ የምትሹ ካላችሁ አጋጣሚው እንዳያመልጣችሁ ስል በአክብሮት አሳስባለሁ። "10 መፅሃፍ ለሚሰጠኝ ሰው መንግስተ ሰማይ ስገባ ከሚኖረኝ የወይን እርሻ እኩሌታውን ልሰጠው ቃል እገባለሁ"ብሏል አንዱ😁..... #ማሳሰቢያ—self-help እና መሰል መፅሀፍትን አያካትትም።
1 5995Loading...
11
For those of you interested
1 3440Loading...
12
ገጣሚ በዕውቀቱ ስዩም የክብር የእንግዳ የሆነበት አንጋፋው የኪነጥበብ ምሽት አርብ ይካሄዳል! ~   ~   ~   ~   ~   ~   ~   ~   ~ በታላቁ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሚዘጋጀው የኪነ-ጥበብ መርሃ ግብር የወሩን ድንቅ የኪነጥበብ ምሽቱን ከፍ ባለ ዝግጅት አርብ ሚያዚያ 18/2016 ዓ.ም ያካሂዳል። በዕለቱም ደራሲና ገጣሚ በውቀቱ ስዩም የክብር እንግዳ ሆኖይገኛል። እንዲሁም በአራት ሳምንታት የኪነጥበብ ዝግጅቶች ቀርበው የተመረጡ ልዪ ግጥሞች ፣ ወግ ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ተሰናድተው እናንተ ውድ ታዳሚዎቻችንን በባህል ማዕከል አዳራሽ ከቀኑ በ 11: 30 ጀምሮ ይጠብቃችኃል ። በተጨማሪም ባህል ማዕከሉ ከኢንፊኒክስ ሞባይል ጋር በመተባበር በቀኑ የታለንት ውድድር በማካሄድ አሸናፊዎችን አጓጊ ሽልማቶችን ይሸልማል። #ማስታወሻ :- ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም የምትፈልጉ በአሁን ሰዓት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የስነ ጽሑፍ አፍቃሪያን መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው ።
1 4041Loading...
13
የካንት ዓመት ዛሬ ሚያዝያ 14 2016 (April 22, 2024) የታላቁ ፈላስፋ የኤማኑኤል ካንት ሶስት መቶኛ የልደት ቀን ነው።በተጨማሪም የፈረንጆቹ 2024ዓም  “የካንት መታሰቢያ ዓመት” ተብሎ ተሰይሟል። ጀርመናዊው ፈላስፋ ዛሬ በሩሲያ ግዛት ስር በምትተዳደረው የያኔዋ ኮኒግስበርግ የዛሬዋ ካሊኒንግራድ ተወለደ። ካንት ከትውልድ መንደሩ ሳይወጣ ዓለምን በመፅሃፍት ንባብ ጠንቅቆ የተረዳ ተረድቶም በስራዎቹ ተፅእኖ መፍጠር የቻለ ሰው ነው። ካንት ከተራው ሰው ርቆ ጥቂት የዩኒቨርሲቲ ምሁራን የሚያወጉት ተምኔታዊ ፍልስፍና ብቻ ሳይሆን ተራውን ሰው እለት ተእለት ስለሚያሳስቡት የስነምግባር የሰላም እና የፖለቲካ ህይወት የተፈላሰፈ እና ዛሬም ድረስ ፋይዳቸው ያልደበዘዙ ሃሳቦችን ያቀረበ ነው። ካንት ለእውቀት ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጥ ሰው ነበር። “ለማወቅ ድፈር፤ የራስህን ህሊና ለመጠቅም ወኔው ይኑርህ።” ይላል ካንት። ይሄ አባባሉ ከእሱ ዘመን ባልተናነስ ዛሬ ላይ ሰዎች በስማ በለው በሚነዱበት እና በሚተራረዱበት ዘመን እንደ መሪ ምርኩዝ ነው። ካንት የሰው ልጆች ሰላም በጣም ያሳስበው ነበር። ዘላቂ ሰላም እንዴት ማስፈን ይቻላል በሚል ብዙ አሰላስሏል። አገራዊ ሰላም ያለ አስተዳደር ነፃነት እንደማይገኝ ገልጿል። ሁለት ወገኖች በድብቅ እያሴሩ እና እየተጠራጠሩ ዘላቂ ሰላም እንደማያሰፍኑ አስረድቷል። ሰላም የሞራል ልእልና እና ምክንያታዊነት ይሻል። የሞራል ልሽቀት እና የድንቁርና አረም የዋጠው ህዝብ ለተሻለ ማህበራዊ እድገት ሊንቀሳቀስ አይችልም። ከጦርነት ማንም አያተርፍም። ይሄንን በዘመናችን ደጋግመን በተግባር አይተነዋል፤ አሁንም እያየነው ነው። እኛም ካንትን ስናስብ ለሰላም ዋጋ የሚሰጡ ፖለቲከኞችን ይስጠን፤ ከመንጋነት ወጥቶ ቆም ብሎ የሚያስብ ትውልድ ይምጣ እያልን በመፀለይ ነው። ቀጥሎ ሃውልቱን ለማድመቅ የተከተበች ሃሳቡ ናት። “ሁሌም ባሰላሰልኩ ቁጥር እነዚህ ሁለት ነገሮች አእምሮዬን በአድናቆት እና አግራሞት ይሞሉታል ይላል ካንት ቀና ስል በከዋክብት የደመቀው የሰማያት ትንግርት እና በዓይነ ልቦና ስመለከት በውስጤ የታተመው የምግባር ህግ ናቸው!
1 5377Loading...
14
Media files
1 2411Loading...
15
THE SWEETEST TABOO If I tell you If I tell you now Will you keep on Will you keep on loving me If I tell you If I tell you how I feel Will you keep bringing out the best in me You give me, you give me the sweetest taboo You give me, you’re giving me the sweetest taboo Too good for me There’s a quiet storm And it never felt like this before There’s a quiet storm That is you There’s a quiet storm And it never felt this hot before Giving me something that’s taboo (Sometimes I think you’re just too good for me) You give me the sweetest taboo That’s why I’m in love with you You give me keep giving me the sweetest taboo Sometimes I think you’re just too good for me I’d do anything for you, I’d stand out in the rain Anything you want me to do, don’t let it slip away There’s a quiet storm And it never felt like this before There’a a quiet storm I think it’s you There’a a quiet storm And it never felt this hot before You’re giving me something that’s taboo You give me the sweetest taboo That’s why I’m in love with you You give me, keep giving me the sweetest taboo Sometimes I think you’re just too good for me You’ve got the biggest heart Sometimes I think you’re just too good for me Every day is Christmas, and every night is new years eve Will you keep on loving me Will you keep on, will you keep on Bringing out the best in me I hope so, I really do
1 77610Loading...
16
Media files
1 3881Loading...
17
Media files
1 5142Loading...
18
April 21, 753 BC: the date traditionally chosen for the mythical founding of Rome by Romulus. Happy birthday Rome !
4400Loading...
19
ስለ ሲልቨስተር ስታሎን ወይም ራምቦ እያነበብኩ ነበር። ድሮ ገና በረንዳ አዳሪ ሆኖ በልጅነቱ ፖርን ላይ ሰርቷል። እኔም ጎግልን ጠየቅኩት፦ Which famous actors starred in adult film industry? ከዚያማ በፎቶ ላይ የሚታዩትን ዘረዘረልኝ—ማርሊን ሞንሮ፣ አርኖልድ ሽዋዚንገር፣ ጆን ሃም፣ ማት ለብላንክ፣ ሄለን ሚረን፣ ካሜሮን ዳያዝ ወዘተ ወዘተ። ከሁሉም የገረመኝ የጄኪ ቻን ነው። ጄኪ በካራቴ ጥበቡ እያሳቀ ጭምር ሲያስደምመን እንጂ፣ በእግሮቹ መሀል ያለው አካሉን የህይወት እንጀራ ሲጋግርበት ማሰብ አልቻልኩም!!!😕
1 6882Loading...
20
ብፅዓት ስዩም ባስረሳኝ ❤️
1 4252Loading...
21
Media files
1 6681Loading...
22
የእብዲያኖስ እና የደዲበስ የጠላ ቤት ንትርክ . . . እ:- አንዳአንዴ እያበድኩ ያለሁ ይመስለኛል። አዲስ ነገርን በመሻት አነባለሁ አነባለሁ ነገር ግን የመፅሐፉን የመጨረሻ ገፅ አንብቤ ስከድን የማወቅ ጉጉቴን የሚያጠረቃ ነገር አጣለሁ። i already knew this'ኮ ምናምን እላለሁ፤ በፊት የማወቀውን የማስታወስ ያህል ይሆንብኛል....ለነገሩ ህይወት ራሱ ለኔ ያነበቡትን መፅሐፍ እንደገና ማንበብ፤ ያዩትን ፊልም እንደገና መከለስ ነው የሆነብኝ ልክ እንደ ouroboros ሆኛለው...ይሄን ነገር'ኮ አውቀዋልው እላለሁ፤ መቼ አወኩት ይሄን ነገር?! ማን ነገሮኝ አወኩት?! ይዘባረቅብኛል እና ይህንን ምን ትለዋለህ? በ reincarnation ታመናለህ? ደ:- አሁን ማመን አቁሜአለሁ በፊት  አምን ነበር። ምን በበፊት ህይወቴ አንስታይንን ነበርኩ ልትለኝ ነው?! ሃሃሃ እ:- ወሬውን ተውና የጠየኩህን መልስ ደ:- አመንኩ አለማመንኩ የሚቀየር ነገር ስለማይኖር ነዋ...ሞቼ ድጋሜ መወለዴን አመንኩ ከዛስ? በኔ ላይ የሚፈጠረው ልዩነት ምንድነው? የገብርኤል የፀጉር ወርቃማ ነው የጊዮርጊስ ጦር ጫፍ ላይ መስቀል አለ እንደማለት ያለ ከህልውናችን ጋር የማይገናኝ መደናቆር ስለሆነብኝ ወይም ደሞ በምክንያታዊነት ሊብራራ የማይችል ስለሆነብኝም ሊሆን ይችላል....ሲቀጥል "ከሞት በኃላ ምንድነው ያለው?!" ብዬ መመናፈስ አቋሚያለው Confucius የሚላት ነገር አለች we must not focus on the afterlife, because we know so little of it, and we must focus on everyday life. እኔም አሁኔን ለመኖር እየጣርኩ ነው። እ:-ጥሩ ማምለጫ ነች ኧኧ፤ እኔም እንደሱ ለመሆን እየሞከርኩ ነበር። ግን ቅዠቱ ሊለቀኝ አልቻለም every were i go እብደቱ ይከተለኛል... ምንም አዲስ የማገኘው ነገር የለም። የእውቀት ሀሳቦች ፣ ሁኔታዎች ፣ ሰዎች አዲስ አይሆኑብኝም...ምንም አዲስ ነገር በማላገኝበት ሁኔታ የመኖር ትርጉሙ ምንድነው? ደ:- ሁሌ የሚያጋጥምህ ነገር ነው ወይስ አልፎ አልፎ እ:- በየለቱ የሚያጋጥመኝ ነገር አይደለም። አንዳንዴ ለረጅም ወራት ፈታ ይሰጠኝና የጠፋ ይመስለኛል....አንዳንዴ ደሞ በሳምንት ውስጥ ሶስቴ የሚገኝበት ሁኔታ ይኖራል ሁሌም ግን ሊጀምረኝ ሲል ራሴን ያዞረኛል አለ አይደል ሊጥለኝ ሁላ ይሞክራል። ደ:- ዲዮቶቭስኪን እየሆንሽ ነዋ ዘመዴ ልዩነቱ እሱ ይጥለዋለ አንተን አይጥልህም ሃሃሃ...ብቻ ይሄንን ተረትህ እንዳምህ አትጠብቅ አይደል? እ:- ሀጠራው መቼ እመነኝ አልኩህ...ከሰማኸኝ በቂዬ ነው...በእርግጥ ምክንያታዊ ለሆነ አእምሮ ለመቀበል የሚከብድ ነገር ነው I'm beyond rationality ደ:- ዋኣይ መኣልቲ ምን ጀመርክ ዘመዴዋ.."beyond rationality" የሚባል ነገር የለም እውነትም ጨርቅህን ጥለሃል ይልቅ ፒኗን ፉት በልበት ውልቅ ነው የሚልልህ ሃሃሃ እ:- አለመኖሩን እንዴት አወክ? ደ:- ነገሮችን ከምክንያታዊነት ውጪ በተሟላ መልኩ ማብራራት ስለማንችል ...ሲቀጥል አንተ ነህ አለ ያልከው መኖሩንም ልታስረዳኝ የሚገባው አንተ ነህ እ:- የማስረዳህ በምክንያታዊነት ነው? ከምክንያታዊነት ውጪ የሆነ ነገር አለ ብዬ በምክንያት ነው የማስረዳህ? this is a pradox....ለኔ genius የሆነ ሰው ካንት ነው Noumenon እና phenomena ብሎ ለማብራራት ሞክሯል Noumenon እንግዲህ በአጭሩ the thing-in-itself እንደማለት ነው.... እውነታን የምናውቀው በስሜት ህዋሳት በኩል በሚገባ መረጃ ብቻ ነው ኮምፒዩተር 0s and 1s ብቻ እንደሚያቀው ሁሉ የኛም አእምሮ የስሜት ህዋሳት ከሚነግሩት ውጪ ማወቅ አይችልም ይህ ደሞ ነገሮች በሚመስሉን መልኩ እናውቃቸዋለን እንጂ ነገሮቹ ባላቸው ትክክለኛ ህልውና ልናውቃቸው አንችልም ይህ እውነታ(the thing-in-itself) ከኛ አእምሮ የራቀ ነው ይላል ውዱ ካንት ፤ ፕሌቶ ራሱ form የሚለው ነገር ጥሩ እይታ ነበር ተሳለቁበት እንጂ ፈላስፋ ነን ባዮች....የካንትና የፕሌቶ ችግር እንደዚህ አይነት ሀሳብ እያሰቡ ራሳቸውን ፈላስፋ ብለው ይጠራሉ ደ:- እሺ ከምክንያታዊነት ባሻገር አለ ያለከውን ሀሳብ በምክንያታዊ አለም ውስጥ ሆነህ እንዴት ልታስበው ቻልክ እ:- through imagination, i think...አልበርት አንስታይን "Imagination is more important than knowledge. Knowledge is limited. Imagination encircles the world.” የሚላት ነገር ሁሌ እንደነካችኝ ነው። እውነት እውነታ የምንለውን ነገር ሁሌ በreason ብቻ የሚገኝ ነው እንላለን ግን ምክንያታዊነት(እወቀት) ውሱን ነው። ምናብ ግን ገደብ የለውም አንስታይን ይቀጥላል logic will get you from A to B imagination take you everywhere...እኔን logic እና reason ይገድቡኛል philosophy እና science ይጠቡኛል በልኬ የተሰፋው "ምናብ" ነው...እንዳልኩ እያበድኩ ይመስለኛል አእምሮዬ real ከምንለው ነገር ጋር መስማማት ተስኖታል....አናቴን ለሁለት ፈንክቼ ውስጡን እድታይ ማድረግ ብችል ደስ ይለኝ ነበር......ሰው ራሱ እንደዛው ይመስለኛል ብናገረው አልታመንም፣ ይሳቅብኛል ፣እንደ እብድ እታያለው በሚል ፍራቻ የማይናገረው ብዙ ነው....ባናምናቸውም ቢያንስ ጆሮ ብንሰጣቸው የተወሰነ relief ያገኙ ነበር...ምስኪን እብዶች ደ:- ለዚህ ነዋ ተረት የምትፅፈው ፣ ተረት የምታነበው፣ ከረዱ ጋር ቁጭ ብለህ carton network የምታየው ሃሃሃ አንተ እውነትም ለይቶልሃል፤ ቆሌታም እብድ ነህ እ:- ኢየሱስ ራሱ እንደ ህፃናት ካልሆናቹ ገለመሌ ይል የለ ያው ወደ የ"እግዚአብሔር መንግስት" ያስገባል የሚለውን ትተህ እንደህፃነት መሆን የተሻለ የማሰብ ነፃነት ይሰጣል እንደማለት ብለህ ያዘው....ደሞ ተረት ውስጥ'ኮ ጥሩ የምናብ ከፍታ አለ ምክንያታዊነትና እውነታ በተረት ውስጥ ቦታ ባይኖራቸውም...ሲቀጥል fantasy ደስ ይለኛል... ግን reality ላንተ ምንድነው? ደ:- እንደዚህ አይነት ጥያቄ በመጠየቅ የማጠፋውን ጊዜ ቀንኛለው። ህይወቴ አጭር ናት'ኮ እውነት ምንድነው? እውነታ ምንድነው? ቅብርጥሶ በሚል የማያባራ ጥያቄ ውስጥ በመዘፈቅ አጭር እድሜዬን የበለጠ አላሳጥርም...የኔ ፍልስፍናም፣ ሀይማኖትም፣ ሳይንስም "አሁንን የመኖር ጥበብ" ይባላል የኔ ሶስቱ ስላሴዎች ደስታ ሰላምና ነፃነት ናቸው ስለሰውልጅ ነፃነት፣ ስለሰውልጅ ሰላም፣ ስለሰውልጅ ደስታ ግድ አይሰጠኝም ስለራሴ ነፃነት ፣ ስለራሴ ደስታና ስለራሴ ሰላም ነው የምጨነቀው....ለጨዋታው ድምቀት ግን ለኔ reality በ sense organ'ኖቼ feel የማደርገው ነገር ነው... ለአይኔ ቆንጆ ሴት ፣ ለጆሮዬ ውብ ሙዚቃ፣ ለአፍጫዬ የአንገቷ ስር ጣፋጭ ጠረን፣ ለምላሴ የክንፎ ውስጥ ንጥር ቂቤ ፣ ለቆዳዬ የእንቡጥ ገላ እቅፍ ይሄ እኔ የማውቀው እውነታ ነው ከዚህ ውጪ እውነትን አላወቅም... አንተሆዬ ደሞ አይንና ጆሮ ውሸታም ናቸው እያልኸኝ ነው ስለዚህ ከዚህ በዘለል አትጠይቀኝ የማብራራው ነገር አይኖርም ይልቅ ያንተን ነገር አጫውተኝ ለውጪው ሳታስብ እየጠጣህ ሃሃሃ
1 2837Loading...
23
እ:-The Matrix የሚለው movie አይተኸዋል? ደ:- እ አዎ አይቼዋለው እ:- cypherን ነው የመሰልከኝ ለሆነ comfort ብሎ እንዳንተ እውነታውን ይክዳል ልክ እንዳንተ ብሽቅ አሳማ ነው....Ignorance is bliss የሚል ነገር አለችው ልክ እንዳንተ ደደብነቱን አምኖ ይቀበላል ደ:- ሃሃሃ ጭራሽ ነው የማንገናኘው እሱ'ኮ ቢያንስ  የቱ እውነት የቱ ውሸት እንደሆነ ያውቃል እኔ የማወቀው ይሄንን አለም ነው ሌላ እውነታ ስለመኖሩም የማወቅበት ምንም መንገድ የለም ታዲያ ለምንድነው እርባና ቢስ በሆኑ ጥያቄዎች ውስጥ ተጥጄ እድሜዬን የማጠፋው?! እ:- እውነትም ከህይወት ጋር በፍቅር ወድቀሃል ሃሃሃ...ግን'ኮ philosophy ሁሌ እንዳነበብክ ነው ደ:- አንተም ብትሞክረው ይሻልሃል የማያዛልቅ እብደት ውስጥ ከምትልከሰከስ...ቆይ ለምን ያቺን ደንደሷሟን አትገነድሳትም አይኗ አይህ ላይ ሲላወስ ታዝቢያለው'ኮ በአንድ'ዜ እብደህ ጥሎህ ይተን ነበር ሃሃሃ....ካልክስ በእርግጥ ለኔም ህይወት 80% ስቃይ ነው ግን በ20 %ቱ 80ውን ለማጣፋት የሌለ ካልኩለስ እሰራለው አለሁ 20>80 ሃሃሃ....ፍልስፍና የማነበውማ ደስ ስለሚለኝ ነው የተለየ እወቀት ፈልጌ አይደለም እንደው በሀሳብ መጫወታቸው ያዝናናኛል...ሲቀጥል እንዳልኩህ ደስ የሚለኝን በማድረግ ነው የምኖረው ነገሩ የግርቢጥ ቢሆንም...ፍልስፍና ርባና ቢስ የቃላት ጨዋታ ቢሆንም ግን ውብ ነው ለውበቱ ስል አነባለሁ እ:- የሚገነድስ ይገንድስህ አቦ....ግን ጥሪያለው'ኮ እኔም እንዳንተው በድድብና ውስጥ ምቾትን ለማፋፋም አይነት ነገር...በእርግጥ እኔም እንዳንተው ደደብ ነኝ ካንተ የምለ'የው ድድብና ላይ በከፈትኩት አመፅ ነው...ነገር ሁሉ እንደ ህፃን ከመሆን ይጀምራል...አንተን የሚያስኮንንህ ድድብናህን በአሜንታ መቀበልህ ነው...እንዳንተ በህይወት በረከቶች ውስጥ መጥፋትን ሞክሪያለው ግን ነፍስያዬ አሻፈረኝ አለች... 100% ህይወት ስቃይ ለሆነችብን ማጣፊያው ላጠረን ምን መልስ ይኖርሃል ደ:- at the end of the day እኔም አንተም ሟች ነን ማወቅህ ወይም አለማወቄ የሚፈጥረው ልዩነት የለም....ግን'ኮ ቀላል ነው ለምን ራስህን አትገልም...100% ስቃይ ውስጥ ሆነህ እንዴት እስካሁን ኖርክ?!....እንደ'ኔ ግን ለመሞት ስለምትደርስ መኖርህን ጠበቅ ብታረግ ባይ ነኝ እ- ስለፈራሁ ነው እስካሁን ያለሁት....አእምሮ ሁሌም አለማው ህይወትን ማስቀጠል ነው ስለ መሞት ማሰብ አይፈልግም አእምሮ ስለማያወቀው ነገር ማስብ ያስፈራዋል....መኖርን ፈልጌ ሳይሆን መሞትን ፈርቼ ነው እዚ ያለሁት በእርግጥ ማድረጌ አይቀርም በፊት ጀምሮ ከፎቅ ላይ መዝለል ያምረኝ ነበር አለ አይደል ለትንሽ ሰከንድም ቢሆን የመብረረን ለማጣጣም...ግን ስቃይን ለማምለጥ ሳይሆን እንዲሁ አዲስ ነገር ይኖር ይሆን በሚል ጉጉት ወደ ብሄረ ሞታን በጥድፊያ መጓዜ አይቀርም....ራስንን መግደልን የሚያበረታታ motivational speaker ቢኖር እስኳሁንም አልቆይም ነበር ሃሃሃ ደ:- ለማንኛውም መሄጃህ እስኪደርስ እየጠጣህ...ምሬትን በምሬት እናጣፋ . . . © የንጋት ኮኮብ
1 6186Loading...
24
Picture a perfect society. What does it look like? - Joseph Lacey https://youtube.com/watch?v=wyHLLzmNje0&si=jx_U26KwLIqq2yhT
1 2291Loading...
25
ነገ መሳተፍ የምትፈልጉ ከስምንት ጀምሮ 5 ኪሎ አፄ ናዖድ ትምህርት ቤት 2 ተኛ ፎቅ መገኝት ትችላላችሁ !
1 3820Loading...
26
Weakness is a great thing, and strength is nothing. When a man is just born, he is weak and flexible. When he dies, he is hard and insensitive. When a tree is growing, it's tender and pliant. But when it's dry and hard, it dies. Hardness and strength are death's companions. Pliancy and weakness are expressions of the freshness of being. Because what has hardened will never win." —Andrei Tarkovsky (Stalker-1979)
1 52911Loading...
27
ሃሳብ ➕ Epigenetics የአስተሳሰባችን መሰረት የዘርሀረጋዊ ነገሮችን መቀየር ይቻለዋል ይለናል ኢፒጄኔቲክስ Spiritual Science ,above genetics Epigenetics is the future as we're more than our genetic makeups ሳይንስ ለሁለት ይከፈላል መንፈሳዊ ሳይንስ ና አካላዊ ሳይንስ Science➾ Spiritual Science n Physical Science , መንፈሳዊ ሳይንስን ጥቂቶች ለራሳቸው በማስቀረት Occulted ,ለብዙሃን በዘመናዊ የትምህርት ተቋሞች ለዘመናት የተሰጠው የትምህርት አስተምህሮ በአካላዊው Physical Science ያተኮረ በመሆኑ ነገሮችን ከሚታየው ባሻገርም ለማወቅ አስቸጋሪና አሁን ለደረስንበት ውጥንቅጥ ድርሻው የላቀ ነው። ይበልጥ genetics  የዘረመል ነገሮችን ያካተተው ሳይንስ መገኘት ና ከአርያን የበላይነት እሳቤ ካላቸው ውስጥም መግባቱ ከጥቅሙ ብዙ ጉዳቶችን አስከትሏል ይባላል በእርግጥም Eugenics turned into genetics... ነገርግን አሁን ጊዜውም ነውና መንፈሳዊ ሳይንሳዊ ነገሮችን ያካተተው ጥንታውያን ለዘመናት የተጠቀሙበት ለእኛ አዲሱ Epigenetics ኢጲጄኔቲክስ ማለት ከጄኒትክስ በላይ ማለት ሲሆን ዘርፍ በጣም የሚገርሙ ነገሮችን ይዟል ፣ ይኸውም የሰው ልጅ የተሰራበት ዘረመል ኮዱ dna codes ብቻ ሳይሆን: የሰው ልጅ አካባቢው ሃሳቡ ዘረመል ኮዱን dna codes የመስራት አቅም አለው ይለናል ይኸው ሃሳብ የከበረ ታላቁ ፋጥረት እንደሆነ እና በአካባቢያችን ባለው ነገሮች ውስጣዊ የዘረመል ኮዳችንን ኮድ ዲኮድ  ማድረግ እንደሚቻል ነው ! ማለትም በዘር ሃረግ ና በቤተሰብ የሚመጣ በሽታዎች እርግማኖች ወዘተረፈ የአስተሳሰባችንን መሰረት በማስተካከል መቀየር እንችላለን ማለት ነው። Humans have the power how their genes can be expressed in their body but not the ultimate power
1 6973Loading...
28
Media files
1 5021Loading...
29
እዚ ሙቀት ላይ... ታክሲ ውስጥ 4 የሚይዘው ወንበር ላይ 3 ሴቶች መሀል ተቀምጠህ ወሬያቸውን እየሰማ እንደመሄድ ገሀነም አለ ወይ😭😭 ጌታ ሆይ ገልብጠን ወይ አጋጨን 😭😭🙏
1 7774Loading...
30
እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠው እውቀት የለም!!! ———————————————— (በብሩህ አለምነህ) የትናንቱን የፀሐይ ግርዶሽ ተከትሎ «የሰው ልጅ እንደዚህ ዓይነት እውቀት የተሰጠው ከእግዚአብሔር ነው» የሚሉ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው። እንደዚህ የምታምኑ ሰዎች እስቲ እነዚህን ጥያቄዎች መልሱ፣ " ❶ ለምንድን ነው ህፃን ልጅ ዕውቀት የሌለው? ❷ ለምንድን ነው ያልተማረ ሰው እውቀት የማይኖረው? ❸ እግዚአብሔር እውቀት የሚሰጠው የሰው ልጅ ልክ ሲያድግና ሲማር ጠብቆ ነው እንዴ? " የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር የተሰጠው ምንም ዓይነት እውቀት የለውም። "ተሰጠው" ለማለት ክስተቱ የዕድሜና የመማር (በት/ት የማለፍ) ቅድመ ሁኔታዎች ሳይኖሩት "ቅፅበታዊ" መሆን አለበት ‐ just like injection ወይም "መገለጥ" – ክስተቱም በድንገት ካለማወቅ ወደ ማወቅ ከተቀየረ "ዕውቀት ተሰጠው" ልንል እንችላለን። ሆኖም ግን፣ በጥረትና በሂደት የተገኘን ነገር «ስጦታ» ልንለው አንችልም። "" የሰው ልጅ ከ15 ዓመት በላይ በት/ቤት ቆይቶ እና ለዘመናት በትውልድ ቅብብሎሽ የተከማቹ ዕውቀቶች ላይ ተመራምሮ በልፋቱ ያገኘውን እውቀት «እግዚአብሔር ሰጥቶት ነው» ማለት ግን ለሰው ልጅ ጥረትና ድካም እውቅና መንፈግ ነው። --- እኔ ግን ይህን እላለሁ! ይህ ሐሳብ ትንሽ ችግር አለበት። በመጀመሪያ እግዚአብሔር የተባለው ማን ነው? በመቀጠልም ዕውቀት ከውጭ የሚመጣ ብቻ፣ ሰውም ንጹህ ወረቀት ነበር (tabula rasa) የሚል ትርጉም የሚሰጥ ነውና ትክክል አይደለም። ከዚህ ጽሑፍ የሚጠበቀው ተፈጥሮንና እግዚአብሔርን መነጠል ነበር። © ብሩህ አለምነህ
1 82213Loading...
31
ልጅነት - ሰሎሞን ዴሬሳ (Replay) https://www.clubhouse.com/room/xVlwaJn3?utm_medium=ch_room_pxr
1 5673Loading...
32
You[all] grow up with actors[pretenders], you learned their craft and you learnt it well, But i grew up with soldiers, i learned how to die [and how to kill] a long time ago. ~ Ned ✡היופי המזויף של החיים
1 6391Loading...
33
what is real?!
1 7291Loading...
34
..... መርዘኛው ሬዲዮ ጣቢያ ባለፈው ዓመት ግንቦት 12 ቀን በፈረንሳይ የተሰማው ዜና ዓለምን በግርምት ያንቀጠቀጠ ነበር። በዘረኛነት መርዝ ተመርዞ መቶ ሺዎችን ያስገደለው የወንጀል ተጠርጣሪ ከ-26 ዓመታት መሰወር በኋላ እጁ ሲያዝ እስከዚያ ጊዜ ድረስ ተሰውሮ መቆየቱ አስገራሚ ሆነ። መቶ ሺዎች እንዲገደሉ በገንዘቡም ፥ በዕውቀቱም ፥ በድርጊቱም የተካፈለው ሃብታም ሰው 26 ዓመታት ሙሉ አየሁት የሚል መጥፋቱ ፥ በገንዘቡ መጋረጃ እየተጋረደ መቆየቱ ዓለምአቀፍ የወንጀለኛ ተከታታዮችን ጭምር የሚያዋርድ ነበር። መቶ ሺዎች በዘር ተለይተው በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ ከጦር መሣሪያ እስከ ፕሮፓጋንዳ ያመቻቸው ሰው ፤ እዛው እየተከታተልኩት ነው ከሚለው ኢንተርፖል መሥሪያቤት አጠገብ ይኖር ነበር። የሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ ዋና ተጠያቂ ፍሊሲዮን ካቡጋ ከ-26 ዓመታት መሰወር በኋላ እጁ ተያዘ። ፍሊሲዮን ካቡጋ በዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድቤት ቀረበ። በታንዛኒያ አሩሻ በሚገኘው የሩዋንዳን የዘር ፍጅት ለሚያየው የዓለም አቀፍ ፍርድቤት ቅርንጫፍ ጉዳዩ እንዲታይ ተወሰነ። ክሱም በሂደት ላይ ነው። ካቡጋ ለ-26 ዓመታት ሥሙን ለውጦ ፥ ከሚያውቁት ሰዎች ፊት ተሰውሮ ኖረ ፤ በርግጥ ወንጀለኛ ህሊናውን ሊሸሸው አይችልም። ከዘመድና ከወዳጅ እርቆ ፥ ከሩዋንዳ እግሩን ነቅሎ የሚንደላቀቅበትን አዱኛ በሽሽግ እየተጠቀመ ሰነበተ ፤ ግን ከፍርድ ሊያመልጥ አልቻለም። በ-60 ዓመቱ ለሰራው ወንጀል በ-87 ዓመቱ በሕግ አደባባይ ቁም ተባለ። ፍሊሲዮን ካቡጋ ሐብታም ነበር። ግን ሃብቱን ለጭካኔና ለአረመኔያዊ ድርጊት ተጠቀመበት። ከባለ ስልጣኖች ጋር ቀረቤታ ነበረው። ግን ቅርርቡን የሩዋንዳን ሕዝብ ለማስጨፍጨፍ ፥ ሩዋንዳንም ለመበተን ተጠቀመበት። በይፋ የተገለፀ ስልጣን ባይኖረውም ገንዘቡን ተግኖ ከፊት ባስቀደማቸው ተባባሪዎቹ ሕግን በእጁ አደረገ። ነጋዴውና ባለሐብቱ ካቡጋ ከሹማምንተ በላይ አዛዥ ሆኖ ፥ ሩዋንዳውያንን በዘር ከፋፍሎ አንዱ ሌላውን እንዲያጠፋው በብርቱ ሰራ። በካቡጋ መሪነት ፥ በመንጋ ተባባሪዎቹ ትጋት ሩዋንዳ ነደደች ፤ ሩዋንዳውያን ተጨፈጨፉ። ግን ውጤቱ ካቡጋ እንዳሰበው ሊሆን አልቻለም። ፍሊሲዮን ካቡጋና ተባባሪዎቹ ሊያጠፏቸው የፈለጓቸው ቱትሲዎች አልጠፉም። ካቡጋ የሚፈልገው የመንግሥት ሥልጣን ወደ ቱትሲዎችም ተላለፈ። ካቡጋ እንዳሻው ከጨፈረባት ሩዋንዳ በእግሬ አውጪኝ ሽሽት አምልጦ ተሰደደ። ራሱን ለውጦ ከአዳኞቹ እጅ ለመዳን ከአንዱ አገር ወደሌላው ተቅበዘበዘ። የሽምግልና ዕድሜውን በፍርሃት አርጩሜ እየተጠበጠበ ፥ ጥላውን እየሸሸ ሰነበተ። በየጓዳውና በየስርቻው ለመተንፈስ እስኪቸግረው ቆየ። በመጨረሻም የሸሸውን ውርደት ፥ የሸሸውን ፍርድ ሊጋፈጥ እጁ ተይዞ ወኸይኒ ወረደ። ካቡጋ ሲያዝ ዕድሜና ጤንነቱን መከታ አድርጎ ለመዳን ፈለገ። ምንግዜም ግፈኞች ፈተና ላይ ሲወድቁ ይብረከረካሉ። በሌላው ላይ የፈረዱትን ስቃይ በራሳቸው ሲደርስ የመዳኛቸውን ሰበብ ያበዛሉ። ካቡጋም 'ሸምግያለሁ ጤንነቴም ተጓድሏልና ተውኝ' አለ። ብዙ ጊዜ በጉልምስና ወቅት የተሰራ ግፍ በሽምግልና ጊዜ እንዳራጣ ብድር በመቶ ተባዝቶ ይቆያል። ጉልበት በደከመበት ፥ ዓይን በማያጠራበት ፥ አንደበት በጎለደፈበት ጊዜ በርክቶ ይፋረዳል ፤ ሽምግልና የጉልምስናን ክፉ ሥራ ይፈትነዋል ፤ ውርደት ፥ ችግር ፥ ህመም ፥ ሞት እየተንኳተቱ ይደርሳሉ። ይሄም በውጭ ሀገር ሰዎችም ሆነ በአገራችን ሰዎች በተደጋጋሚ ሲደርስ በዕድሜያችን አይተነዋል። ፍሊሲዮን ካቡጋም ይኸው ዕጣ ነው የደረሰበት ፤ በ-87 ዓመቱ ወደ ወኸይኒ ቤት። ይቀጥላል ..... © ተስፋ
1 7104Loading...
35
ይቀጥላል ..... © ተስፋ
10Loading...
36
Media files
1 5740Loading...
37
ክሩዝ ሚሳየል ሲባል ሰምታችኋል ክሩዝ ሚሳየል አብራሪ የሌለው አነስተኛ አውሮፕላን ነው ማለት ይቻላል። ባለ ቱርቦፋን ሞተሩ እና 6.25 ሜ የሚረዝመው ክሩዝ ሚሳየል፣ 2.61ሜ. የክንፍ ርዝመት ሲኖረው፣ በከፍተኛ ደረጃ ተቀጣጣይ የሆኑ እስከ 450 ኪ.ግ. የሚመዝኑ ቦምቦችን ተሸክሞ፣ ከ800-1600 ኪ.ሜ ርቀት፣ በሰዓት 880 ኪ.ሜ በሆነ ፍጥነት (cruising speed ) መምዘግዘግ እና ኢላማውን መምታት የሚያስችል አቅም አለው። አንድ ክሩዝ ሚሳየል በጠቅላላው 1450 ኪ.ግ ክብደት ሲኖረው፣ ከዚህ ውስጥ 65 ኪ.ግ የሚሆነው የሞተሩ ክብደት ሲሆን ወደ 450 ኪ.ግ የሚሆነው ደግሞ የሚጭነው ነዳጅ ክብደት ነው። solid rocket booster የተባለው አስወንጫፊው አካል ደግሞ 250 ኪ.ግ የሚሆነውን ክብደት ይይዛል። የታቀደለትን ኢላማ በመምታት በኩል ክሩዝ ሚሳየል ባለ ንስር አይን መሳሪያ ነው። 1000 ኪ.ሜ ከተምዘገዘገ በኋላ እንኳን የተላከበት የማይረሳው ይህ መሳሪያ፤ “It can fly 1,000 miles and hit a target the size of a single-car garage.” የሚል ምስክርነት ተሰጥቶታል። ይህም ብቻ አይደልም፤ ክሩዝ ሚሳየል ከራዳር እይታ ውጪ በሆነ ዝቅተኛ ከፍታ መጓዝ ስለሚችል በቀላሉ ሊመታና ሊከሽፍ አለመቻሉ መሳሪያውን እጅግ ተወዳጅ እና ተመራጭ ያደርገዋል። ይህን መሳሪያ ኢላማውን በተገቢው መንገድ እንዲመታ የሚያግዙ አራት የተለያዩ የቴክኖሎጂ ስርዓቶች (systems) አሉ። እነሱም…. IGS - Inertial Guidance System Tercom - Terrain Contour Matching GPS - Global Positioning System DSMAC - Digital Scene Matching Area Correlation በመባል ይታወቃሉ። እነኚህ አራት የቴክኖሎጂ ስርዓቶች የተለያየ ሚና ሲኖራቸው ክሩዝ ሚሳይሉ ከተተኮሰበት ቅጽበት ጀምሮ ኢላማውን በትክክል እስኪመታ ድረስ በመተባበር ይሰራሉ። የነዚህ የቴክኖሎጂ ስርዓቶች ዋነኛ ሚና የሚሳየሉን ፍጥነት መቆጣጠር፣ ሚሳይሉ የሚምዘገዘግበት መልከዓምድር በመለየት የሚሳይሉን የጉዞ መንገድ እና ሁኔታ መቀየስ፣  የሚሳየሉን የጉዞ ሁኔታ መከታተልና ሚሳይሉ የታቀደለትን ኢላማ በአግባቡ መምታቱን ማረጋገጥ ነው። ክሩዝ ሚሳየሎች በዓይነታቸው ብዙ ሲሆኑ፤ ከባህር ሰርጓጅ መርከቦች፣ ከተዋጊ አውሮፕላኖች እንዲሁም ከምድር ላይ ሊተኮሱ ይችላሉ። እነኚህን መሳሪያ የታጠቁ ሀገራትን ለወዳጅነት እንጂ ለጠብ የሚያጫቸው የለም። እንደው ከአቅም በላይ በሆነ ገፊ ምክንያት ከነዚህ ሀገራት ጋር ወደ ጠብ ውስጥ ቢገባ እንኳን ሁለቴ እና ሶስቴ የኃይል ሚዛንን ማስላትን ይጠይቃል። ምክንያቱም የታጠቁት መሳሪያ ባህር ተሻግሮ የሚያዳፍነው ክሩዝ ሚሳየል ነውና! ሶስተኛ የአለም ጦርነት ስለሚነሳ ከወዲሁ ለጠቅላላ ዕውቀት 😁
1 7579Loading...
38
Media files
1 5130Loading...
Show all...
Could consciousness all come down to the way things vibrate?

A resonance theory of consciousness suggests that the way all matter vibrates, and the tendency for those vibrations to sync up, might be a way to answer the so-called 'hard problem' of consciousness.

1🔥 1🤣 1
Show all...
Where does consciousness come from? It could all be vibrations

The "hard problem" of consciousness examines how subjective experiences arise from physical processes. A resonance theory suggests that all matter, showing synchronized vibrations, possesses a basic level of consciousness that amplifies through complex interactions and information exchanges.

ከበደ ሚካኤል ቀለል ባሉት ተራኪ ግጥሞቻቸው ከአገር በቀል እውቀት እስከ ፈረንጆቹ ፍልስፍና አንድም ሳይቀራቸው እውቀት ለማስተላለፍ ሞክረዋል። ‘ብርሃነ ሕሊና’ በሚል ርዕስ በ1933ዓም ከዛሬ ስምንት አስርት ዓመታት በፊት ባሳተሙት መጽሃፍ በአርስቶትል አንደበት እንዲህ ብለው ነበር፥ አሪስቶት አሪስቶት የሚባል ፈላስፋው መምህር ከሊቆች መካከል ቆሞ ሲያስተምር የወዳጅን ነገር ጠቅሶ ሲነግራቸው እንዲህ ሲል በምክሩ አስጠነቀቃቸው። ስሙኝ ልንገራችሁ ወዳጆቼ ሆይ ምንም ወዳጅ የለም በዚህ ዓለም ላይ። ለዚህ ላርስቶት ለትልቁ ሊቅ ወዳጆችህ ያንተን እውቀት በመናቅ ሲያሙህ ሰማናቸው ብለው ቢነግሩት እንኳን ማማት እና እሌለሁበት ቢደበድቡኝም አልቀየማቸው አሚታ አይጎዳኝም ሲል መለሰላቸው። እኛም እንደ አሪስቶት ምንም ባንሆን ሊቅ ይገባናል ዞትር አሚታን መናቅ አርስቶት= አርስቶትል ወይም ኤርስቶትል አሚታ= ሃሜት ስለሰው ክፉ ወሬ
Show all...
9👍 1
For those interested
Show all...
👍 1
ከሀሳብ አይደለም ከስልቱ ነው
Show all...
👍 7🥰 2
በአሉ ግርማን በ"የቀይ ኮኮብ ጥሪ" በኩል እንደታዘብነው socialist realism:- እንደ አንድ የኪነት ስልት በ1932 አካባቢ ተጀመረ ይላሉ...ጥበብ ፤ ለሰውልጅ ነፃነትን ደስታንና ዲሞክራሲን ለማስፈን የሚተጋውን የጭቁኑ ህዝብ ትግል ማገልገል መቻል አለበት ከሚል አዝማሚያ የተነሳ ይመስላል ...didactic use of literature, art, and music to develop social consciousness in an evolving socialist state.[1] socialist realism ጭቁኑን ትግል የሚያንፀባርቅ የጥበብ ስልት ተደርጎ ሊታይ ይችላል።The primary theme of Socialist Realism is the building of socialism and a classless society.In portraying this struggle, the writer could admit imperfections but was expected to take a positive and optimistic view of socialist society and to keep in mind its larger historical relevance.[2] በrealism እና በ socialist realism መካከል ያለው ልዩነት realism የህይወትን ነፀብራቅ ሊያሳየን ይሞክራል...ጥበብ የገሃዱ አለም ነፀብራቅ ነው በሚል መፈክር።"Realism is the attempt of art to capture life as realistically as possible."[3] በአንፃሩ ለsocialist realism ጥበብ የሰፊው ህዝብ ትግል ነፀብራቅ ነው።"Socialist realism differs from critical realism, not only in being based on a concrete socialist perspective, but also in using this perspective to describe the forces working towards socialism from the inside."[4] በዚህ መነሻነት ለኔ በአሉ ግርማ realist ደራሲ የሚለው ነገር አያስማማኝም socialist realismን የሚከተል ደራሲ ነው(ለኔ በአሉን ደራሲ ነው ብዬ ራሱ መጥራት ይቸግረኛል፤ በተለየ በ"የቀይ ኮኮብ ጥሪ" ውስጥ እልም ያለ የደርግ ፕሮፓጋንዲስት ሆና እንታዘበዋለን) በ"የቀይ ኮኮብ ጥሪ" ውስጥ የታዘብናቸው አብይ የስነፅሁፍ ህፀፆች 1 የጥበብ አረዳድ... በአሉ ስነፅሁፍን ለውበቱ ሳይሆን የራሱን ሀሳብና አመለካከለት ማንፀባረቂያ መንገድ አድርጎ ነው የተጠቀመው የራሱን ብቻ ሳይሆን በጊዜው ገዢ የነበረውን የፖለቲካ አስተሳሰብ ለመስበክም ይጋጋጣል...በመሰረቱ አንድ ጥበብ ውበት የሚኖረው ለጥበብነቱ የዋለ ጊዜ ነው ፤ ጥበብ የሆነ አይነት ዘርፍን ማገልገል ስትጀምር ጥበባዊ ለዛዋ ይሞታል....በአሉ በአተራረኩ የተወጣለት ቢሆንም አለማው ጥበባዊ ለዛ ሳይሆን የጭቁኑን ህዝብ ትግል ወይም የአብዮቱን "ቅዱሳዊነት" ማስተጋባት ነው። ጥበባዊ ለዛን ብለው ለሚመጡ አንባቢያን በጥበብ ስም ፖለቲካዊ ንትርክን ያጠጣ...አንዳንዴ የጥበባዊ ውበቱ አይሎብን ፖለቲካዊ ጥዝዛውን ችለን የምንቀበላቸው ስራዎች ይኖራሉ የበአሉ ግን ፅንፍ ይወጣል....በጣም ቋቅ ያለኝና በአሉ እልም ያለ ፕሮፓጋንዳስት ነው ያስባለኝ ..."ያብዮትና ያገር ፍቅር ከማንኛውም ፍቅር ይበልጥ ጠንካራ ነው። "(ገፅ-101)...ሚለው አባባል ነው፤ እንዴት አይተውት በአሉን የሚያንቆለጳጵሱት ስል ተገረምኩ 2 የንዑስ ታሪኮች ነገር በዚህ የቀይ ኮኮብ ጥሪ በሚለው ድርሰት ውስጥ ከዋናው ጭብጥ ጋር ፍፁም ግንኙነት የሌላቸው ሌሎች ንዑስ ታሪኮች እናነባለን... የድርሰቱ ዋና ጭብጥ በፍቅር ተጎዳ አሽከር እንዴት የአብዮቱን ጥሪ(የቀይ ኮኮብ ጥሪ) እንደተቀበለ ፤ እንዲሁም ይህ ሰው የአብዮቱን አደራ በመወጣትና የቀድሞ አሳዳሪዎቹ የዋሉለት ውለታ በፈጠረበት ስሜት መካከል የሚኖረው ጡዘት ነው....ነገር ግን በአሉ ትዝብቱን፣ ፖለቲካዊ አስተሳሰቡና ፕሮፖጋንዳውን ለማስተላለፍ ከዋናው የታሪክ ፍስት ጋር ትስስር የሌላቸው ሌሎች ተዳባይ ታሪኳችን ያስነበብናል...ይሄ የድርሰቱን ውበት ባያሌው አጉድፎታል ሲጀመርም ድርሰት ከተባለ ማለት ነው ከአላስፈላጊ ንዑስ ታሪኮች በተጨማሪ አላስፈላጊ ገፀባህርያትም ወዲያ ወዲህ ሲሉ ይታያሉ....ለምሳሌ ጌታቸው ሸዋሉል በድርሰቱ ውስጥ ተደጋግሞ ይነሳል ብዙ የገፅ ሽፋንም ተሰጥቶታል ነገር ግን ከዋናው የታሪክ ጭብጥ ጋራ ያለው ትስስር እጅግ የላላ ነው ለመፃፍ ባለኝ ስልቹነት የተነሳ ያልጠቀስኳቸው የበአሉ እልፍ ስህተቶች በ"የቀይ ኮኮብ ጥሪ" መፅሐፍ ውስጥ ታዝቢያለው መፅሐፉን ጨርሼ ስከድን እዚህ መፅሐፍ ላይ ያባከንኩት ጊዜ ፀፀተኝ... የተሻለ እይታ አለኝ የሚለንን ለማድመጥ ዝግጁ እንደሆንን ይሰመርበትና... [1] [2] Encyclopedia Britannica [3] social realism literature: studysmarter.com.uk [4]critical realism and socialist realism: springer.com ✡אומנות
Show all...
3😁 2👍 1
አያን ሂርሲ አሊ ትባላለች። ከአራቱ ሞገደኛ ኢአማንያን ከዶዊክንስ ከሂችንስ ካሃሪስ እና ዴኔት ጋር በአቻነት የምትወሳ ነበረች። ወዳጃችን ሂችንስ ነፍሱ በአፀደ ገነት ትረፍና በሞት ከተለየን ቆየ። አያን ደግሞ ባሳለፍነው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ ገደማ ጥላን ላሽ ብላለች። ከኢአማኝነት ወደ ሐይማኖተኝነት የተቀየሩ ምሁራኖች ጥቂት አይባሉም። ግን "ለምን? ለምን? ለምን?" አለ በስንቱ። እኔ ደግሞ እዚህ ተጎልቼ "እንዴት ነው አንድ የተማረ የተመራመረ የሚባል ሰው በአንድ ወቅት ያለምንም ጥርጣሬ ሽንጡን ገትሮ ሲሟገትለት የነበረን አመለካከት በአንዴ አሽቀንጥሮ በተቃራኒው ጎራ መሰለፍ የሚችለው?" እያልኩ እጠይቃለሁ። መጨረሻዬን አሳምርልኝ እንጂ ሌላ ምን ይባላል።
Show all...
😁 7👍 5👌 2🙏 1

😁 25👍 3