en
Feedback
ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ: የህጻናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት እና ረ. ፕሮፌሰር (Ass. Prof. Of Pediatric Surgery)

ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ: የህጻናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት እና ረ. ፕሮፌሰር (Ass. Prof. Of Pediatric Surgery)

Open in Telegram

@ ከ18 አመት በታች ለሆኑ ህፃናትና ታዳጊዎች(0911441651) ✅️የኩላሊት እና የሽንት ቱቦ ቀዶ ህክምና ✅️የብልት አፈጣጠር ችግር ✅️የዘር ፍሬ አቀማመጥ ችግር ✅️የግርዛት አገልግሎት ✅️ጠቅላላ የአንጀት ቀዶ ህክምና ✅️የሰገራ መውጫ አፈጣጠር ችግር ✅️የማህፀን አፈጣጠር ችግር ✅️የካንሰር ቀዶ ህክምና ✅️ማንኛውንም የህፃናት ቀዶ ህክምና አገልግሎትን እንሰጣለን

Show more
Ethiopia10 904The category is not specified
1 788
Subscribers
+124 hours
+57 days
+2030 days

Data loading in progress...

Tags Cloud
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Incoming and Outgoing Mentions
---
---
---
---
---
---
Attracting Subscribers
December '24
December '24
+262
in 1 channels
November '24
+447
in 0 channels
Get PRO
October '24
+106
in 0 channels
Get PRO
September '24
+25
in 0 channels
Get PRO
August '24
+30
in 0 channels
Get PRO
July '24
+6
in 0 channels
Get PRO
June '24
+14
in 1 channels
Get PRO
May '240
in 1 channels
Get PRO
April '24
+4
in 1 channels
Get PRO
March '24
+12
in 1 channels
Get PRO
February '24
+7
in 1 channels
Get PRO
January '240
in 1 channels
Get PRO
December '230
in 0 channels
Get PRO
November '230
in 2 channels
Get PRO
October '23
+11
in 1 channels
Get PRO
September '23
+32
in 0 channels
Get PRO
August '23
+16
in 0 channels
Get PRO
July '23
+38
in 0 channels
Get PRO
June '23
+39
in 0 channels
Get PRO
May '23
+67
in 0 channels
Get PRO
April '23
+38
in 0 channels
Get PRO
March '23
+11
in 0 channels
Get PRO
February '23
+13
in 0 channels
Get PRO
January '23
+45
in 0 channels
Get PRO
December '22
+72
in 0 channels
Get PRO
November '22
+248
in 0 channels
Get PRO
October '22
+347
in 0 channels
Get PRO
September '22
+173
in 0 channels
Get PRO
August '22
+143
in 0 channels
Get PRO
July '22
+69
in 0 channels
Get PRO
June '22
+198
in 0 channels
Get PRO
May '22
+335
in 0 channels
Get PRO
April '22
+156
in 0 channels
Get PRO
March '22
+79
in 0 channels
Get PRO
February '22
+1
in 0 channels
Get PRO
January '22
+6
in 0 channels
Get PRO
December '21
+213
in 0 channels
Date
Subscriber Growth
Mentions
Channels
21 December0
20 December0
19 December0
18 December+1
17 December0
16 December+1
15 December0
14 December+1
13 December0
12 December+1
11 December+2
10 December+1
09 December+255
08 December0
07 December0
06 December0
05 December0
04 December0
03 December0
02 December0
01 December0
Channel Posts
🔊 #ህፃናት ላይ #ቶንሲል_በኦፕራሲዮን_መወጣት ያለበት ጊዜ መቼ ነው❓️ 👉👉 በዝህ በክረምት ወቅት ብዙ ወላጆች የልጆቻቸው ቶንስል በኦፕሬሽን እንዲወጣ ያደርጋሉ :: ምክንያቱ ምንድነው❓️ ቶንስል በኦፕሬሽን መውጣት ያለበትስ መቼ ነው ❓️ 👉👉 ህፃናት ላይ የሚከሰት ቶንስል ህመም ከታች ያሉትን ምልክቶች ካሳየ በኦፕራሲዮን ቢወጣ ይመከራል❗️ 1. ቶንስል እና አዴኖይድ በከፍተኛ ሁኔታ ማበጥ(adenotonsilar hypertrophy) እና ይሄንን ተከትሎ ሌሎች ችግሮችን ካመጣ ለምሳሌ 🔹 ከፍተኛ ማንኮራፋት 🔹ለመዋጥ መቸገር, 🔹 ለንግግር እና አፍ ለመፍታት ጋር ችግር ካመጣ... 🔊 ከፍተኛ ማንኮራፋት ከምን ይመጣል❓️ 👉 በቶንስል እብጠት 👉 በአዴይድ እብጠት 👉 ሌሎች እባጮች 👉 የነርቭ ችግሮች 👉 ከፍተኛ ውፍረት ሊመጣ ይችላል 🔊 ከከፍተኛ ማንኮራፋት ጋር ተያይዞ የሚመጡ ችግሮች ከተከሰቱ 🔹 የእድገት መቀነስ 🔹 ክብደት አለመጨመር/መቀጨጭ ችግር 🔹 በእንቅልፍ ሰአት ላይ ከፍተኛ ትንፋሽ ማጠር ካለ ወይም ለመተንፈስ መቸገር እና ትንፋሽ ማቆራረጥ ካለ 🔹 ማንኮራፋቱ በከፍተኛ ሁኔታ እንቅልፍን የሚረብሽ - በተደጋጋሚ መባነን 🔹 የባህሪ ለውጥ (ቀን ላይ መንቀዥቀዥ እና አለመራጋጋት(ADHD) ወይም እንክልፍ ካለ 🔹 የትምርት አቀባበል ችግር ካለ 🔹 የሳምባ ግፊት እና የልብ ችግር ካመጣ 🔹 ምግብ ፍላጎት መቀነስ እና ኪሎ ያለመጨመር ችግር ካለ 🔹 ማታማታ አልጋ ላይ ሽንት መሽናት/ማማለጥ 2. የፓራዳይዝ ክራይቴርያን( Paradise criteria ) ካሟላ 🔹 ተደጋጋሚ የቶንሲል ህመም ከተከሰተ 🔹 በዝህ /በባለፈው ዓመት ውስጥ 7 ጊዜ በላይ ሀኪም ያየው የባክቴርያ ቶንስል ኢንፌክሽን ከተከሰተ 🔹 ወይም በባለፈው ዓመት ከ 5 ጊዜ በላይ የቶንስል ኢንፌክሽን ከተከሰተ 3. ከአንድ ጊዜ በላይ መግል እና ፈሳሽ የያዘ የቶንስል ኢንፌክሽን ( #Peritonsilar_Abcess) 4. ካንሰር መስል ምልክቶች ከታዩ 5. ለብዙ ፀረ ባክቴርያ(Antibiotics) መድሃኒቶች አለርጂ ካለ እና በመድሃኒት ማከም ካልተቻለ 6. በቶንስል ኢንፌክሽን ምክንያት febrile seizure የሚባለው ህፃናት ላይ የሚከሰት ራስ መሳት እና የማንቀቀጥ ችግር በተደጋጋሚ የሚከሰት ከሆነ ❤️ ጠቃሚ መረጃ ነው ብለው ካሰቡ ለሌሎችም ወላጆች እንዲደርስ በ ቅንነት #share ያድርጉት ‼️🙏 አዘጋጅ: ዶ/ር ፋሲል መንበረ (በቅዱስ ጳዑሎስ ሆስፒታል የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር) ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ እንሰራለን!!!      ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ:      የህፃናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም   Dr. Saleamlak Tigabie:     MD, Pediatric Surgeon, FCS-ECSA(at DCSH) , WU, Dessie, Ethiopia   👉ለበለጠ መረጃ ፣ ቀጠሮ ለመያዝ እና ነፃ የምክር አገልግሎት : ከስር ያሉ አድራሻዎችን መጠቀም ይቻላል! 📱0911441651 👉Gmail: saleamlaksati@gmail.com 👉@DrSaleamlak(በግል ለማናገር፣ ፎቶ ለመላክ)     https://t.me/DrSaleamlakT https://www.facebook.com/ዶር-ሳለአምላክ-ጥጋቤ-Pediatric-Surgeon-100878625359706/

2
+1
No text...
492
3
🔊 የዳይፐር ሽፍታ ሕክምናው ምንድነው❓️ ክፍል 2 ❤️ ሰላም ውድ ቤተሰቦቻችን 👋👋 👉 በትላንትው ፅሁፋችን ስለ ዳይፐር ሽፍታ ምንነት ምክንያት እና መከላከያ መንገዶችን አይተናል :: ዛሬ ደሞ መፍትሄዎቹን/ሕክምና መንገዶቹን ይዘን መተናል:: 👉 በመጀመሪያ በ ክፍል 1 ላይ የተገለፁትን መከላከያ መንገዶች መጠቀም:: 👉 ሽፍታው አንዴ ከተከስተ በተለያየ ምክንያት እና መንገድ ስለሚመጣ ሕክምናው እንደየምክንያቱ ይለያያል 👉 በቆዳ መቆጣት የመጣ ከሆነ በ zinc oxide, steroid ወይም በቫዝሊን እና በመሳሰሉት ማከም ይቻላል 👉 ተቅማጥ ካለ በደንብ ማከም እና ማዳን 👉 በኢንፌክሽን የመጣ ከሆነ በሀኪም የሚታዘዙ ለ ኢንፌክሽን መድሃኒቶችን መጠቀም ለምሳሌ አንቲባዮትክስ ወይም አንትፈንጋል ክሬሞችን መጠቀም 👉 በቀን ዉስጥ ቢያንስ 1 - 2 ሰአት ክፍት ማድረግ ፀሐይ ማሞቅ እና ቆዳው እንዲደርቅ ማድረግ 👉 ሽንት እና ሰገራ እረጅም ሰአት ዳይፐር ላይ እንዳይቆያ ማድረግ (ቶሎ መቀየር) 👉 ስናፀዳ ለብ ያለ ዉሃ መጠቀም 👉 ሰውነታቸውን ለማድረቅ በወፍራም ጨርቅ አለመጥረግ 👉 ሰውነታቸው ሳይደርቅ ሌላ ዳይፐር አለማድረግ ❤️ ጠቃሚ መረጃ ነው ብለው ካሰቡ ለሌሎችም ወላጆች እንዲደርስ በ ቅንነት #share ያድርጉት ‼️🙏 አዘጋጅ: ዶ/ር ፋሲል መንበረ (በቅዱስ ጳዑሎስ ሆስፒታል የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር) 👨‍ ❤️ ጠቃሚ መረጃ ነው ብለው ካሰቡ ለሌላውም እንዲደርስ #share ያድርጉት ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ እንሰራለን!!!      ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ:      የህፃናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም   Dr. Saleamlak Tigabie:     MD, Pediatric Surgeon, FCS-ECSA(at DCSH) , WU, Dessie, Ethiopia   👉ለበለጠ መረጃ ፣ ቀጠሮ ለመያዝ እና ነፃ የምክር አገልግሎት : 📱0911441651 👉Gmail: saleamlaksati@gmail.com 👉@DrSaleamlak(በግል ለማናገር፣ ፎቶ ለመላክ)     https://t.me/DrSaleamlakT https://www.facebook.com/ዶር-ሳለአምላክ-ጥጋቤ-Pediatric-Surgeon-100878625359706/
582
4
+2
No text...
396
5
የህፃናት የዳይፐር ሽፍታ(diaper rash) ምክንያቱ ምንድነው❓️ መፍትሄውስ❓️ 🤔  "ባክህ እኛ አሁን የጨነቀን #የዳይፐር ዋጋ እንጂ የዳይፐር ሽፍታ አይደለም ❗️"  እንደማትሉኝ ተስፋ አረጋለው 😁😁 🔊  እኔም ወላጅ ነኝና መንግስት የዳይፐር ዋጋውን   እንዲያስብበት እና መፍትሄ እንዲሰጥ በዚሁ አጋጣሚ ወላጆችን ወክዬ ጥሪዬን አቀርባለሁ❗️ እንደው ድንገት ከሰማኝ ብዬ ነው እንጂ... 🔊 ወደ ዛሬው ርዕሳችን ስገባ የዳይፐር ሽፍታ በጣም ብዙ ህፃናት ላይ የሚከስት እና በቀላሉ ሊታከም እና ሊድን የሚችል የቆዳ ህመም ነው :: ሆኖም ግን በቶሎ ካልታከመ አልፎ አልፎ ለከፋ የቆዳ ኢንፌክሽን ሊያጋልጥ እና ሕፃኑን ሊጎዳ ይችላል❗️ 👉👉  የዳይፐር ሽፍታ  ምክንያቱ ምንድነው? 🔹 የዳይፐር ሽፍታ የሚከሰትበት 3 ዋና ዋና መንገዶች/ምክንያቶች አሉ :: እነሱም ✔️ 1. #የቆዳ መቆጣት (Irritation) 👉 ረጅም ሰአት የቆየ የሽንት የሰገራ ወይም በዳይፐር ኬሚካል ካለ 👉 አዲስ ምግብ ከተጀመረ ✔️2. #ኢንፌክሽን 👉  ሽንት እና ሰገራ የቆዳን PH በመቀየር ለፈንገስ(candida/yeast) እና ለባክቴርያ  ኢንፌክሽን ሊያጋልጡ ይችላሉ 👉 በተለይ እንደ ዉሃ ያለ ጠቅማጥ ካለ ✔️3.  #አለርጂ 👉 አንዳንድ ህፃናት በተፈጥሮ ለተለያዩ አይነት ዳይፐሮች ወይም ለዋይፐር አለርጂ ሊኖራቸው ይቺላል:: ስለዚህ የሚመቻቸውን መርጦ መጠቀም የወላጅ ተግባር ነው :: 🔊🔊 #ምልክቱ ምንድነው❓️ 📌 ዳይፐር ያለበት ቦታ ለይቶ የሚከሰት ቀያይ ሽፍታ 📌 በመቀጠል ከፍ ከፍ ብሎ የሚወጣ በጣም የቀላ እና የ ተላላጠ ቆዳ ሊታይ ይችላል 📌 በመቀጠል ሊደማ እና ከፍተኛ ህመም ሊያመጣ ይችላል :: 🔊🔊 ስለዚህ የዳይፐር ሽፍታን በምን እንከላከልው❓️ 🔺 ልጅዎን አንዳንዴ ከዳይፐር ነፃ የሆነ ጊዜ ይስጡት 🔺 ሰገራ/ሽንት ካለው ወድያው ዳይፐሩን መቀየር 🔺 አንድን ዳይፐር 2-3 ሰአት በላይ አለመጠቀም 🔺 ሌላ ዳይፐር ከመቀየር በፊት ለብ ባለ ዉሃ የልጅዎን ቆዳ ቀስ ብለው ያፅዱት በመቀጠል 🔺 እንዲደርቅ ጊዜ ይስጡት 🔺 ቆዳው ከደረቀ በዋላ በወፍራሙ ቫዝሊን ይቀቡት እና ቀጣዩን ዳይፐር ያድርጉለት :: 🔺 ቆዳውን ለማድረቅ በ ፎጣ አይሞዥቁ ከዛ ይልቅ ለስ ለስ ባለ ፎጣ ጫን ጫን ማድረግ እና ማድረቅ ይቻላል:: 🔊🔊 ሕክምናውስ ምን ይመስላል❓️ በምን ይድናል❓️ ይቀጥላል..... ❤️ ጠቃሚ መረጃ ነው ብለው ካሰቡ ለሌሎችም ወላጆች እንዲደርስ በ ቅንነት #share ያድርጉት ‼️🙏 አዘጋጅ: ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር) ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ እንሰራለን!!!      ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ:      የህፃናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም   Dr. Saleamlak Tigabie:     MD, Pediatric Surgeon, FCS-ECSA(at DCSH) , WU, Dessie, Ethiopia   👉ለበለጠ መረጃ ፣ ቀጠሮ ለመያዝ እና ነፃ የምክር አገልግሎት ከስር የሚገኙትን አድራሻዎች መጠቀም ይቻላል: 📱0911441651 👉Gmail: saleamlaksati@gmail.com 👉 @DrSaleamlak (በግል ለማናገር፣ ፎቶ ለመላክ)     https://t.me/DrSaleamlakT https://www.facebook.com/ዶር-ሳለአምላክ-ጥጋቤ-Pediatric-Surgeon-100878625359706/
493
6
+2
No text...
426
7
ክፍል 2 - የህፃናት የቆዳ አለርጂ (Atopic dermatitis) የህፃናት የቆዳ አለርጂ (Atopic dermatitis) ከሌሎች የቆዳ ህመሞች በምን ይለያል ❓️ 👉 የህፃናት የቆዳ አለርጂ (Atopic dermatitis) ከሌሎች የቆዳ ህመሞች የሚለየው 1. ምልክቱ ሁሌም ሄድ መጣ የሚል ይሆናል 2. ከፍተኛ ማሳከክ እና የቆዳ ድርቀት ይኖረዋል 3. በተወሰኑ የምግብ አይነቶች በቀላሉ ሊባባስ ወይም ልነሳሳ ይችላል 4. ዳይፐር ቦታ ላይ አይከሰትም 5. ሀኪም በሚያዛቸው ክሬሞች (topical steroid) ቶሎ የመጥፋት ባህሪ ይኖረው እና በድጋሚ ይመጣል 🔊 የቆዳ አለርጂ መከላከያ ዘዴዎቹ ምን ምን ናቸው❓️ 👉 ህፃናት የእናት ጡት ወተት ብቻ እስከ 6 ወር ማጥባት ከዛ ከምግብ ጋር ቢያንስ ለ 1 ዓመት መቀጠል 👉 እናት በእርግዝና ወቅት omega 3 እና omega 6 ያላቸውን ምግቦች በብዛት እንድትመገብ ማድረግ ለምሳሌ 🔹 አሳ 🔹 የአሳ ዘይት 🔹 አቦካዶ 🔹 ለውዝ 🔹 ወተት 👉 ህፃናት 6 ወር በፊት ተፈጥሯዊ የሆኑ ቦታዎች እና ነገሮችን እንዲነኩ ማድረግ ለምሳሌ የቤት እንስሳት፣ አፈር፣ አትክልት... (NB: ይሄ መረጃ ቅርብ ጊዜ በወጡ ጥናቶች የተደገፈ ነው) 🔊 የህፃናት የቆዳ አለርጂ (Atopic dermatitis) የሚድን ነው ወይስ አይድንም? 👉 አለርጂ አንድ ልጅ ላይ ከተከሰት ተፈጥሯዊ(genetic) ስለሆነ በቀላሉ ላይድን ይችላል ሆኖም በቤት ውስጥ ሕክምናዎች እና ሀኪም በምያዛቸው መድሃኒቶች መቆጣጠር እና መቀነስ ይቻላል❗️ 👉 ብዙዎቹ ህፃናት ላይ ከ6 ዓመት በዋላ እየቀነሰ ሄዶ ይጠፋል የተወሰኑት ግን በዛው ሊቀጥልባቸው ይቺላል 🔊 ቤት ውስጥ ማድረግ ያለብን ጥንቃቄዎች ምን ምን ናቸው❓️ 👉 በተደጋጋሚ በሳሙና ሰውነትን አለማጠብ 👉 ሰውነታቸውን ካጠብ በዋላ ውሃው ሳይደርቅ የቆዳ ማለስለሻዎችን መጠቀም 👉 በሳምንት 1 ቀን ብቻ ሰውነት ማጠብ 👉 ካጠቡ በዋላ ዉሃ ከሰውነት ሳይደርቅ ወዲያው የቆዳ ማለስለሻ ቅባቶችን መቀባት 👉 ሰውነታቸው ስናጥብ መታሻ መጠቀም የለብንም 👉 ጠንካራ እና ሽታ ያላቸውን ሳሙናዎች አለመጠቀም 👉 ሰውነትን ማለስለሻ(Moisturizer effect and gentle cleanser) ያላቸውን ሳሙናዎች መጠቀም 👉 ለልብስ ማጠብያ የተዘጋጁ ሳሙናዎችን ለሰውነት አለመጠቀም 👉 አለርጂ የሚያስነሱ ነገሮችን መለየት እና ማስወገድ 👉 አለርጂ የሚያስነሱባቸውን ምግቦች መለየት እና እንዳይመገቡ ማድረግ (ለምሳሌ: እንቁላል ወተት ለውዝ ብርቱካን ቾኮሌት...) 👉 የሚለበሱትን ልብስ ከጥጥ የተሰራ ማድረግ 👉 ከፍተኛ ሙቀትን ማስወገድ 👉 ላብ እንዳይበዛ ልብስ ብዙ አለመደራረብ 👉 አለርጂ የሚቀንሱ ምግቦች ማስለመድ እነሱም 🔹 አሳ እና አሳ ዘይት 🔹 ዝንጅብል 🔹 ነጭ ሽንኩርት 🔹 እርድ 🔹 አትክልቶች 🔊 ዋነኛው መፍትሄ ግን 👇👇👇 ❤️  የሰውነት ድርቀት መከላከል እና የቆዳ ማለስለሽ የሆኑ ቅባቶችን ጠዋት እና ማታ መቀባት 🔹 የወይራ ዘይት 🔹 ፓራፊን ዘይት 🔹 የኮኮናት ዘይት 🔹 ኦልቬራ ጄል 🔹 ቫዝሊን እና የመሳሰሉትን የቆዳ ማለስለሻ መጠቀም 🔊 #አስተውሉ ❗️ ላንዱ ልጅ የሰራው የቆዳ ማለስለሻ ሌላው ልጅ ላይሰራ ይቺላል ስለዚህ የሚመቻቸውን መምረጥ ከወላጅ የሚጠበቅ ነው :: 👉አዘጋጅ:  ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር ) ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ እንሰራለን!!!    👉ከጨቅላ ህፃናት እስከ 18 ዓመት ታዳጊዎች ለማንኛውም የህፃናት ቀዶ ህክምና  መረጃ ለማግኘት፣ ቀጠሮ ለመያዝ እና ነፃ የምክር አገልግሎት : 📱0911441651 👉Gmail: saleamlaksati@gmail.com 👉@DrSaleamlak(በግል ለማናገር፣ ፎቶ ለመላክ)     https://t.me/DrSaleamlakT https://www.facebook.com/ዶር-ሳለአምላክ-ጥጋቤ-Pediatric-Surgeon-100878625359706/
649
8
ህፃናት ላይ የሚከሰት የቆዳ አለርጂ ( #Eczema) መንስኤው እና ሕክምናው ምንድነው? ክፍል 1 👉 አሁን አሁን ከተማ አካባቢ የቆዳ አለርጂ የሌለበት ህፃን ማግኘት ብርቅ እየሆነ መቷል:: 👉 የቆዳ አለርጂ ( #Eczema ) በተደጋጋሚ በህፃናት ላይ የሚታይ የቆዳ ህመም ሲሆን በተደጋጋሚ ሄድ መጣ እያለ የብዙ ህፃናትን ጤና እና እንቅልፍ ሰዓት ይረብሻል :: 👉 🌍 በአለም  ከመቶ ህፃናት ውስጥ ሰላሳው በዚህ ችግር እንደሚጠቁ ጥናቶች ያሳያሉ። በተለይ በተለይ ደሞ ከተማ አካባቢ የሚኖሩ ህፃናት ላይ ችግሩ ጎልቶ ይታያል 🔹 የቆዳ አለርጂ አጋላጭ ምክንያቶች(Risk factors) ምን ምን ናቸው 👉 በዘር ግንድ ውስጥ አለርጂ ካለ 👉 ለምሳሌ በአባት እናት እህት ወይም ወንድም ላይ አለርጂ ካለ 👉 ሌሎች የአለርጂ አይነቶች ካሉ 🔹 የአፍንጫ አለርጂ 🔹 የአይን አለርጂ 🔹 የሳይነስ አለርጂ 🔹 አስም 🔹 የአየር ቧንቧ አለርጂ 👉 የላም ወተት ከ6 ወር በፊት መጀመር 👉 የጣሳ ወተት ከ6 ወር በፊት መጀመር 👉 በከተማ አካባቢ መኖር 👉 ቀዝቃዛ አካባቢ መኖር 👉 ቤት ውስጥ የሚያጨስ ሰዉ ካለ 👉 ፀረባክቴርያ(Antibiotics) በጨቅላነት እድሜ መውሰድ 👉 በኦፕራስዮ(C-section) መወለድ 👉 ከፍተኛ የሆነ የወሊድ ክብደት     (Higher birth weight) 🔹 የቆዳ አስም በምን ምክንያት ይከሰታል? ✔️ ቆዳ ተፈጥሮአዊ የበሽታ መከላከያችን ነው :: ከውጪ የሚመጡ ባእድ ነገሮችን ወደሰውነታችን እንዳይገቡ ይከላከላል። ✔️ የሠውነት  ርጥበትን ይጠብቃል ✔️ ከኢንፌክሽን ይከላከላል 🔷 በዚህ በቆዳ አስም  በተጠቁ ህፃናት ላይ ግን ቆዳቸው እነዝህን ሌላይ የተዘረዘሩትን ተግባራት ማድረግ ይሳነዋል 🔷 ይህም ዋናው ምክንያቱ በዘር የሚመጣ ሲሆን በዚህ ችግር የተጠቁ ህፃናት ቤተሰባቸውም(ታላቅ ወይም ታናሽ ወንድም/እህት) ላይም ተመሳሳይ ችግር ያለበት ሰው ይኖራል። 🔷 የቆዳ አለርጂ ምልክቶች ምንድናቸው❓️ 👉 የቆዳ አስም (Atopic Dermatitis )  አብዛኛውን ጊዜ በመጀመሪያው አንድ አመት እድሜ ውስጥ ይጀምራል።ምልክቶቹም 📌 ዱብ ዱብ ያሉ የሰውነት ሺፍታዎች 📌 ማሣከክ ( በተለይ ምሽት ላይ ) 📌 የቆዳ መቅላት 📌 መቁሰልና ውሀ መቋጠር 📌 የቆዳ ድርቀትና መሰነጣጠቅ 📌 የቆዳ መሻከር( ብርጭቆ ወረቀት መምሰል) 🔹 በየትኛው የሰውነት ክፍል ይታያል❓️ በተለይ በለጋ እድሜ ላይ ያሉ ህፃናት ላይ     🔸በጭንቅላት ቆዳ     🔸በፊታቸው ላይ     🔸 ክንዳቸው ላይ የሚወጡ ሽፍታዎች ይታያሉ። (extensor surface) 📌  ከፍ ያለ እድሜ ያላቸው ልጆች እና አዋቂዎች ላይ በውስጥ መዳፍ በኩል ከፍ ብሎ ክንዳቸው ላይ (flexor area ) ይታያል። በተጨማሪ እግራቸው ላይ ይታያል ጥያቄዎች 👉 ከሌሎች የቆዳ ህመሞች በምን ይለያል 👉 የቆዳ አለርጂ እንዳይከሰት እንዴት እንከላከል❓️ 👉 ቤት ውስጥ መደረግ ያለበት ጥንቃቄስ ምንድነው❓️ 👉 የቆዳ አለርጂ በራሱ ሊጠፋ ይቺላል ወይስ አብሮ የሚኖር ህመም ነው? 👉 ዘላቂ መፍትሄው እና ሕክምናው ምንድነው? ይቀጥላል.... 👉አዘጋጅ:  ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር ) ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ እንሰራለን!!!    👉ከጨቅላ ህፃናት እስከ 18 ዓመት ታዳጊዎች ለማንኛውም የህፃናት ቀዶ ህክምና መረጃ ለማግኘት፣ ቀጠሮ ለመያዝ እና ነፃ የምክር አገልግሎት : 📱0911441651 👉Gmail: saleamlaksati@gmail.com 👉@DrSaleamlak(በግል ለማናገር፣ ፎቶ ለመላክ)     https://t.me/DrSaleamlakT https://www.facebook.com/ዶር-ሳለአምላክ-ጥጋቤ-Pediatric-Surgeon-100878625359706/
605
9
+2
No text...
506
10
https://t.me/DrSaleamlakT
https://t.me/DrSaleamlakT
646
11
"ዶክተር ቦርጭ ነው እያልኩ ሳላውቅ ልጄን ለ2 ዓመት አሰቃየሁት!" (ከቀዶ ህክምና በኋላ የወላጅ እናት ንግግር ነበር) 👉ይህ በምስሉ የሚታየው በተለምዶ "ቦርጭ ነው" እየተባለ ሳይታወቅ የቆየ፣  ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ የነበረ፣  ከጊዜ በኋላ መጠኑ በመጨመሩ እና  ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተኛ ህመም ያስከተለ ከአንጀት የደም ስር የተነሳ ከ2 ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝን የሆድ እቃ እጢ ሲሆን በቀዶ ጥገና ሙሉ በሙሉ መውጣት ችሏል። 👉ልጁም በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛል። ✍✍ችግሩን በመረዳት እና ከፍተኛ ቀዶ ህክምና እንደሚያስፈልገው አውቃችሁ የላካችሁ የጤና ባለሙያዎች ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን! 👉👉በዚህ ህክምና የተሳተፋችሁ ሁሉ እናመሰግናለን!! ማስታወሻ: 👉 በህፃናት ላይ የሚከሰቱ ማንኛውም የጤና ችግሮች በሚመለከታቸው የጤና ባለሙያዎች ታይተው ተገቢውን ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ የሁሉም ወላጅ ሐላፊነት ሊሆን ይገባል። 👉 በተፈጥሮ እና ከጊዜ በኋላ የሚመጡ የጤና ችግሮች በማህበረሰባችን የአመለካከት ችግር እንዲሁም የአንዳንድ የጤና ባለሙያዎች እውቀት ማነስ እና የግንዛቤ እጥረት ምክንያት በተገቢው ጊዜ እና ቦታ ህክምና ማግኘት አልቻሉም። 👉ስለዚህ ይህን ለማስተካከል የሁሉም አካላት ሐላፊት ሊሆን ይገባል። ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ እንሰራለን!!!   አዘጋጅ:    ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ:      የህፃናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም   Dr. Saleamlak Tigabie:     MD, Pediatric Surgeon, FCS-ECSA(at DCSH) , WU, Dessie, Ethiopia   👉ለበለጠ መረጃ ፣ ቀጠሮ ለመያዝ እና ነፃ የምክር አገልግሎት : 📱0911441651 👉Gmail: saleamlaksati@gmail.com 👉@DrSaleamlak(በግል ለማናገር፣ ፎቶ ለመላክ)     Click here Facebook
682
12
+3
No text...
510
13
ልጄ የ4 ዓመት ከ8 ወር ነው፡፡ ነገር ግን ከ3 ወር በፊት ይታመምና ሀኪም ቤት ስወስደው በአልትራሳውን የሐሞት ጠጠር እንዳለበት አወኩኝ እና ለ8 ቀን አኪም ቤት ተኝቶ ህክምና አድርጎ ከወጣ አሁን 2 ወር አለፎታል ነገር ግን ክትትል አለው፡፡ ትናንት ሀኪሞች ቀዶ ጥገና ማድረግ እንዳለበት ነገሩኝ እናም ሐሞቱን አብሮ እንደሚወጣ ነው የነገሩኝ የሐሞቱ መውጣት ጉዳት አይኖረውም ወይ? (የወላጅ ጥያቄ) 👉 የሐሞት ከረጢት መውጣት የሚያመጣው የራሱ ችግር ቢኖረውም ህክምናው አስፈላጊ ስለሆነ ከጉዳቱ ጥቅሙ የጎላ ነው ። 👉ስለሆነም መታከሙ የግድ የተሻለ ነው ። ✍ጥያቄ: 1 : የሃሞት ጠጠር በህፃናት እንዴት ይታከማል? 👉ልጅዎ የሃሞት ጠጠር ካለበት ነገር ግን ህመም ወይም ማስታወክ ያሉ ምልክቶች ከሌለ ህክምና ላያስፈልጋቸው ይችላል። 👉ክትትል ግን ያስፈልገዋል። 👉 በኋላ ላይ ምልክቶች ከታዩ ወደ ሕክምና መውሰድ አለበዎት። 👉ልጅዎ  የሐሞት ጠጠር ምልክት ካለበት፣ ብቸኛው እና ውጤታማው ሕክምና ሐሞትን ከጠጠሩ ጋር በቀዶ ጥገና ማስወገድ ነው። ✍ጥያቄ:2: የሐሞት ጠጠር ምልክቶች በህፃናት ምንድን ናቸው? 👉ብዙውን ጊዜ ሰዎች የሐሞት ጠጠር ቢኖራቸውም ነገር ግን ምንም ምልክት የላቸውም። 👉የሐሞት ጠጠር ምልክቶችን ካሳየ(if it is symptomatic) የሐሞት ከረጢቱ ከጠጠሩ ጋር መወገድ አለበት። 👉ምልክቶቹ ብዙውን ከምግብ በኋላ ይነሳሉ ፣ በተለይም ስብ ወይም ቅባት የበዛባቸው ምግቦች። 👉ምልክቶቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ: 👉👉በላይኛው ቀኝ ሆድ ላይ ህመም 👉👉ማቅለሽለሽ 👉👉ማስታወክ 👉👉 ትኩሳት(በተለይ ኢንፌክሽን ከፈጠረ) ✍ጥያቄ: 3: ባይታከም ምን ችግር ያመጣል? 👉ለሞት የሚያደርስ ኢንፌክሽን ሊያስከት ይችላል። 👉 ጠጠሮቹ ወደ ሐሞት ቱቦ በመንቀሳቀስ የሐሞት ፍሰት ሊዘጋ ይችላል። ከዛም የጉበት መድከምን(Hepatic Failure) ያስከትላል። ✍ጥያቄ : 4: ድንገተኛ የሕክምና እንክብካቤ መቼ ያስፈልጋቸዋል? 👉የሐሞት ጠጠር ያለበት ልጅ ከሚከተሉት ምልክቶች አንዱን ካጋጠመው አፋጣኝ የሕክምና ክትትል ያስፈልጋቸዋል። 👉👉በጣም ኃይለኛ የሆድ ህመም 👉👉ህጻኑ ምቾት ሊሰማው አይችልም 👉👉ቢጫ መሆን (በዓይን እና በቆዳ ውስጥ ቢጫ ቀለም ያለው ቀለም) 👉👉ከፍተኛ ትኩሳት ወይም ከፍተኛ ቅዝቃዜ ካለው በአፋጣኝ የድንገተኛ ህክምና ያስፈልገዋል!!! ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ እንሰራለን!!!   አዘጋጅ:    ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ:      የህፃናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም   Dr. Saleamlak Tigabie:     MD, Pediatric Surgeon, FCS-ECSA(at DCSH) , WU, Dessie, Ethiopia   👉ለበለጠ መረጃ ፣ ቀጠሮ ለመያዝ እና ነፃ የምክር አገልግሎት : 📱0911441651 👉Gmail: saleamlaksati@gmail.com 👉@DrSaleamlak(በግል ለማናገር፣ ፎቶ ለመላክ)     https://t.me/DrSaleamlakT https://www.facebook.com/ዶር-ሳለአምላክ-ጥጋቤ-Pediatric-Surgeon-100878625359706/
705
14
+3
No text...
540
15
2) ቀዶ ጥገና(Surgery) 👉አንጀት ከተበሳ ወይም ከበሰበሰ 👉አንጀቱ በፊንጢጣው ከወጣ 👉ችግሩ የተከሰተው ከአንድ ወር በታች በሆነ ጨቅላ ህፃን ከሆነ 👉በውሀ ችግሩን ለማስተካከል ካልተሳካ ወይም 👉መንስኤው መነሻ ነጥብ(lead point) ካለው ቀዶ ጥገና አስፈላጊ ነው። 👉 የቀዶ ጥገና ሐኪሙ የታሰረውን የአንጀት ክፍል ነፃ ያደርጋል ፣ እንቅፋቱን ያስወግዳል እና አስፈላጊ ከሆነ የሞተውን የአንጀት ሕብረ ሕዋስ ያስወግዳል። 👉ቀዶ ጥገና ለአዋቂዎች እና ለከባድ ሕመምተኞች ዋናው ሕክምና ነው። ✍✍በአንዳንድ ሁኔታዎች intussusception ጊዜያዊ ሊሆን ይችላል እና ያለ ህክምና ሊመለስ ይችላል። ✍ጥያቄ -7: ለማንኛውም ከዶክተርዎ ምን አይነት ጥያቄ ሊጠየቁ ይችላሉ? 👉የልጅዎ ሐኪም የሚከተሉትን ጨምሮ በርካታ ጥያቄዎችን ሊጠይቅዎት ይችላል። 👉ልጅዎ የሆድ ህመም ወይም ሌሎች ምልክቶች መታየት የጀመረው መቼ ነው? 👉የልጅዎ ህመም ቀጣይነት ያለው ይመስላል ወይንስ እየመጣ የሚሔድ ነው? - 👉ህመሙ በድንገት የሚጀምር እና የሚሔድ ነው? 👉ልጅዎ ማቅለሽለሽ, ማስታወክ ወይም ተቅማጥ አጋጥሞታል? 👉በልጅዎ ሰገራ ውስጥ ምንም አይነት ደም አስተውለዋል? 👉በልጅዎ ሆድ ውስጥ እብጠት ወይም መነፋት አስተውለሃል? ✍ጥያቄ -8: እስከዚያው ድረስ ምን ማድረግ ይችላሉ? 👉ከመታየቱ በፊት ምልክቶችን ለማከም ለልጅዎ ያለሀኪም ማዘዣ መድሃኒት አይስጡ። 👉ምልክቶቹን ካዩ ለልጅዎ ምንም የሚበላ ነገር አይስጡ። 👉 ለአስቸኳይ የሕክምና እርዳታ ወደ ሆስፒታል ይውሰዱ!!!!!! ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ እንሰራለን!!!   አዘጋጅ:    ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ:      የህፃናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም   Dr. Saleamlak Tigabie:     MD, Pediatric Surgeon, FCS-ECSA(at DCSH) , Dessie, Ethiopia   ተጨማሪ አድራሻ:      🩺ባቲ ጠቅላላ ሆስፒታል        👉ለበለጠ መረጃ ፣ ቀጠሮ ለመያዝ እና ነፃ የምክር አገልግሎት : 📱0911441651 👉Gmail: saleamlaksati@gmail.com 👉@DrSaleamlak(በግል ለማናገር፣ ፎቶ ለመላክ)     https://t.me/DrSaleamlakT https://www.facebook.com/ዶር-ሳለአምላክ-ጥጋቤ-Pediatric-Surgeon-100878625359706/
582
16
ሰላም ዶክተር የ6 ወር ልጅ አለኝ።  ያለማቋረጥ ያለቅሳል ፣ ይፈራገጣል አልፎ አልፎም ያስታውከዋል። ካካ ሲል ደም የቀላቀለ ነው! ከጀመረው አሁን 12 ሰዓት አለፈው! በጣም ጨንቆኛል ምን ሊሆን ይችላል? እባክህ በአስቸኳይ እርዳታህን እፈልጋለው!( የወላጅ ጥያቄ) 👉ህፃናት  ላይ ከሚከሰቱ የአንጀት ችግሮች አንዱ አንጀት በአንጀት ውስጥ የመግባት ችግር ነው! 👉ይህም Intussusception በመባል ይታወቃል። 👉አንጀት ወደ አንጀት በመንሸራተት የሚከሰት ከባድ በሽታ ነው። 👉ይህ ችግር ብዙ ጊዜ ምግብን ወይም ፈሳሽን በአንጀት ውስጥ እንዳያልፍ ያግዳል። 👉 በተጎዳው የአንጀት ክፍል ላይ ያለውን የደም አቅርቦትን ያቋርጣል። 👉ይህም ወደ የአንጀት መበስበስ ወይም ሞት ፣ የሆድ እቃ መቁሰል  እና የአንጀት መበሳት ሊያስከትል ይችላል። 👉በመጨረሻም እስከ ሞት ድረስ የሚያደርስ ከባድ ህመም ነው። 👉ከ3 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት በጣም የተለመደው የአንጀት መዘጋት መንስኤ ነው። 👉በልጆች ላይ የአብዛኛውን ጊዜ መንስኤው ወይም ምክንያቱ አይታወቅም። 👉በአዋቂዎች ላይ ምንም እንኳ  በጣም አልፎ አልፎ ቢከሰትም አብዛኛውን ጊዜ እንደ የአንጀት እጢ ያሉ የጤና ችግሮች ውጤት ነው። 👉በልጆች ላይ አንጀቱ ብዙውን ጊዜ በትንሽ አሠራር ወይም ህክምና ወደ ቦታው ሊመለስ ይችላል። 👉በአዋቂዎች ወይም እድሜአቸው ከፍ ላለ ህፃናት ውስጥ ብዙውን ጊዜ ችግሩን ለማስተካከል ቀዶ ጥገና ያስፈልጋል። ✍ጥያቄ -1: ምልክቶች ምን ምን ናቸው? 👉ምልክቱ በልጆች እና በአዋቂዎች ሊለያይ ይችላል። 👉ከዚህ በፊት ሙሉ ጤናማ የነበረ ህፃን የመጀመሪያው ምልክት በድንገት  በሆድ ህመም ምክንያት ከፍተኛ ማልቀስ ሊሆን ይችላል። 👉 የሆድ ህመም ያለባቸው ህጻናት ሲያለቅሱ ጉልበታቸውን ወደ ደረታቸው ይጎትቱታል። 👉ብዙ ጊዜ ሲጀምር በየ15 እና 20 ደቂቃው ህመሙ ይመጣል እና ይሄዳል። 👉እየቆየ ሲሔድ  ረዘም ላለ ጊዜ ይቆያል። 👉ሌሎች ተደጋጋሚ ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ: 👉👉ደም እና ንፍጥ የተቀላቀለ ካካ- አንዳንድ ጊዜ በመልኩ ምክንያት currant Jelly ሰገራ ይባላል። 👉👉ማስታወክ 👉👉የሆድ  እብጠት ወይም የሆድ መነፋት 👉👉ድካም ወይም የሰውነት መዛል 👉👉ተቅማጥ ✍✍ሁሉም ህፃናት ሁሉም ምልክቶች ይኖሩታል ማለት አይደለም። 👉አንዳንድ ጨቅላ ሕጻናት ግልጽ የሆነ ህመም የላቸውም 👉አንዳንድ ልጆች ደም የቀላቀለ ካካ ላይኖራቸው ይችላል ወይም 👉በሆድ ውስጥ እብጠት ላይኖራቸው ይችላል። 👉አንዳንድ ትልልቅ ልጆች ህመም ይኖራቸዋል ነገር ግን ሌላ ምንም ምልክት ላይኖራቸው ይችላል። 👉በአዋቂዎች ላይ እምብዛም ስለማይገኝ እና የሕመሙ ምልክቶች ብዙውን ጊዜ ከሌሎች ህመም ምልክቶች ጋር ስለሚደራረቡ ለመለየት የበለጠ ፈታኝ ነው። 👉በጣም የተለመደው ምልክት የሚመጣ እና የሚሄድ የሆድ ህመም ነው። 👉ማቅለሽለሽ እና ማስታወክም ሊከሰት ይችላል። 👉 አንዳንድ ጊዜ ሰዎች የሕክምና ዕርዳታ ከመፈለጋቸው በፊት ለሳምንታት ያህል ምልክቶች ይታያሉ። ✍ጥያቄ-2: ወደ ህክምና መሔድ ያለባቸው መቼ ነው? 👉ይህ ችግር ድንገተኛ የሕክምና እንክብካቤ የሚያስፈልገው አደገኛ ህመም ነውና 👉እርስዎ ወይም ልጅዎ ከላይ የተዘረዘሩት ምልክቶች  ከታዩ ወዲያውኑ ለሕክምና ዕርዳታ ወደ ጤና ተቋም መሔድ ያስፈልጋል። 👉በጨቅላ ህጻናት ላይ የሆድ ህመም ምልክቶች በተደጋጋሚ ጉልበቶቹን ወደ ደረቱ በመሳብ እና ማልቀስ ሊያካትቱ እንደሚችሉ ያስታውሱ። ✍ጥያቄ-3: መንስኤው ምን ሊሆን ይችላል? 👉አንጀት  ረጅም ቱቦ ቅርጽ ያለው የሰውነት ክፍላችን ነው። 👉በintussusception የሚፈጠረው አንዱ የአንጀት  ክፍል - ብዙውን ጊዜ ትንሹ አንጀት - በአቅራቢያው ባለው የአንጀት ክፍል ውስጥ ሲሸራተት ነው። 👉 ይህ አንዳንድ ጊዜ ቴሌስኮፒ ተብሎ ይጠራል ምክንያቱም ሊሰበሰብ የሚችል ቴሌስኮፕ አንድ ላይ ከሚንሸራተቱበት መንገድ ጋር ተመሳሳይ ነው። 👉በአዋቂዎች  የሚከሰተው በአንጀት ውስጥ ያልተለመደ እድገት ያለው እብጠት ሲኖር ነው። ለምሳሌ እንደ polyp ወይም ዕጢ (መነሻ ነጥብ ወይም lead point ይባላል)። 👉ያልተለመደ የሞገድ መሰል የአንጀት እንቅስቃሴ ይህን ሊያስከትል ይችላል። 👉በአብዛኛዎቹ ሁኔታዎች ግን ምክንያቱ አይታወቅም። 👉በልጆች ላይ በአብዛኛው በበልግ እና በክረምት ወቅት ይከሰታል። 👉 ይህ ችግር ያለባቸው ልጆች የጉንፋን ምልክቶች ወይም የአንጀት ኢንፌክሽን ምልክቶች ስለሚኖሯቸው አንዳንዶች በዚህ ሁኔታ ውስጥ ቫይረስ ሚና ሊጫወቱ እንደሚችሉ ይጠራጠራሉ። 👉በአዋቂዎች አብዛኛውን ጊዜ  የሚከተሉት ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ: 👉👉ፖሊፕ ወይም ዕጢ 👉👉በአንጀት ውስጥ ጠባሳ (መጣበቅ) 👉👉ከቀዶ ጥገና በኋላ ✍ጥያቄ-4 : ህክምና ባይደረግላቸው ሊከሰት የሚችሉ ችግሮች ምን ምን ናቸው? 👉ችግር የተከሰተበት የአንጀት ክፍል የደም አቅርቦትን ሊያቋርጥ ይችላል። 👉ሕክምና ካልተደረገለት የደም እጦት የአንጀት ግድግዳ እንዲሞት ያደርጋል። 👉 ይህም የአንጀት ግድግዳ መበሳት ሊያመራ ይችላል። 👉ይህም የሆድ እቃ ቁስለት (Peritonitis) ያስከትላል። 👉ይህ ቁስለት ለሕይወት አስጊ የሆነ ሁኔታ ሲሆን በአስቸኳይ ሕክምና ያስፈልገዋል። 👉የሆድ እቃ ቁስለት ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ: • የሆድ ህመም ወይም ሲነካ ከፍተኛ ህመም መሰማት • የሆድ እብጠት • ትኩሳት • ማስመለስ • የሰውነት መቀዝቀዝ ወይም ከፍተኛ ሙቀት • ደካማ እና ፈጣን የልብ ምት • ቀርፋፋ እና ጥልቀት የሌለው ወይም በጣም ፈጣን የሆነ ያልተለመደ አተነፋፈስ • መፍዘዝ ወይም እራስን መሳት ✍ጥያቄ-5: ህመሙ በምን ምርመራ ይረጋገጣል? 👉የእርስዎ ወይም የልጅዎ ሐኪም የችግሩን ምልክቶች ታሪክ በመጠየቅ እና በአካል ምርመራ ይጀመራል። 👉ምርመራውን ለማረጋገጥ  የሚከተሉትን ሊያዝዝ ይችላል- • የሆድ አልትራሳውንድ ወይም የሆድ ዕቃ ምስል • የደም ምርመራ ✍ጥያቄ-6: ሕክምናው ምንድነው? 👉የድንገተኛ የሕክምና ያስፈልጋለ። 👉ከፍተኛ የሰውነት ፈሳሽ ማነስ ካለ መተካት አለበት። 👉እንዲሁም በደም እጥረት ምክንያት የአንጀት ክፍል ሲሞት ሊከሰት የሚችለውን ኢንፌክሽን ለመከላከል አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ያስፈልጋል። 👉 የሕክምና አማራጮች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ- 1) በውሃ ወይም የአየር መመለስ። 👉ይህ ህክምና በህፃናት ላይ 90% የሚሆነውን  ችግር ሊያስተካክል ይችላል። 👉እናም ምንም ተጨማሪ ህክምና ላያስፈልገው ይችላል። 👉አንጀት ከተቀደደ (የተቦረቦረ) ከሆነ ይህ አሰራር መጠቀም አይቻልም። 👉 ይህ ህክምና  የሚደረገው በultrasound የተደገፈ ቢሆንም እንኳ የቀዶ ጥገና ሐኪም ማማከር እና እንዲወስን ማድረግ  አስፈላጊ ነው 👉ይህ የሆነበት ምክንያት በዚህ  ህክምና አማካኝነት አንጀት የመቀደድ ወይም የአንጀት መበሳት አደጋ ሊያጋጥም ይችላል።
476
17
+5
No text...
418
18
የግርጌ ማስታወሻ: 👉ልጆችን ለማስገረዝ የጤና ተቋማትን ብንጠቀም መልካም ነው። 👉ከዚህ የከፋ ችግር ሊያስከትል ስለሚችል የባህል ግርዛትን እንከላከል! ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገ+2
የግርጌ ማስታወሻ: 👉ልጆችን ለማስገረዝ የጤና ተቋማትን ብንጠቀም መልካም ነው። 👉ከዚህ የከፋ ችግር ሊያስከትል ስለሚችል የባህል ግርዛትን እንከላከል! ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ እንሰራለን!!!   አዘጋጅ:    ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ:      የህፃናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም   Dr. Saleamlak Tigabie:     MD, Pediatric Surgeon, FCS-ECSA(at DCSH) , WU, Dessie, Ethiopia   👉ለበለጠ መረጃ ፣ ቀጠሮ ለመያዝ እና ነፃ የምክር አገልግሎት : 📱0911441651 👉Gmail: saleamlaksati@gmail.com 👉@DrSaleamlak(በግል ለማናገር፣ ፎቶ ለመላክ)     https://t.me/DrSaleamlakT https://www.facebook.com/ዶር-ሳለአምላክ-ጥጋቤ-Pediatric-Surgeon-100878625359706/
540
19
✍ጥያቄ-8: የቀዶ ጥገናው ውጤት ምን ይመስላል? 👉ከቀዶ ጥገናው በኋላ አብዛኛዎቹ ልጆች በፊንጢጣ ውስጥ ሰገራ ማሳለፍ ይችላሉ። 👉ከጊዜ በኋላ ሊሻሻሉ የሚችሉ ችግሮች የሚከተሉትን ያካትታሉ:    👉👉ተቅማጥ   👉👉ሆድ ድርቀት   👉👉ሰገራ ማንጠባጠብ   👉👉የመጸዳጃ ቤት ስልጠና መዘግየት 👉ህጻናት ከቀዶ ጥገና በኋላ በተለይም በአንደኛው አመት ውስጥ የአንጀት ኢንፌክሽን (enterocolitis) የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ ነው። 👉የenterocolitis ምልክቶች ከተከሰቱ ወዲያውኑ ዶክተርዎን ያማክሩ- 👉👉ከፊንጢጣ ደም መፍሰስ 👉👉ተቅማጥ 👉👉ትኩሳት 👉👉የሆድ መነፋት 👉👉ማስታወክ ✍ጥያቄ -9: ከቀዶ ጥገና በኋላ የአኗኗር ዘይቤ እና የቤት ውስጥ እንክብኬቤ ምን መምሰል አለበት? 👉ልጅዎ ከቀዶ ጥገና በኋላ የሆድ ድርቀት ካለበት, ከሚከተሉት ውስጥ አንዱን መሞከር እንዳለብዎ ከሐኪምዎ ጋር ይወያዩ 👉👉ከፍተኛ ፋይበር ያላቸውን ምግቦች ማዘውተር 👉👉ዝቅተኛ ፋይበር ያላቸውን ምግቦች ይቀንሱ 👉👉በቂ ፈሳሽ እንዲወስድ ያድርጉ 👉👉አካላዊ እንቅስቃሴን ማበረታታት( ዕለታዊ እንቅስቃሴ መደበኛ የአንጀት እንቅስቃሴን ይረዳል።) 👉👉 የሰገራ ማለስለሻ መድኃኒት  በሐኪም ትዕዛዝ መሠረት መጠቀም ይቻላል!!! ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ እንሰራለን!!! አዘጋጅ ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ:     የህፃናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም Dr. Saleamlak Tigabie:     MD, Pediatric Surgeon, Assist. Prof. Of Pediatric Surgery, FCS-ECSA (at DCSH), WU, Dessie ተጨማሪ አድራሻ:      🩺ባቲ ጠቅላላ ሆስፒታል ለበለጠ መረጃ እና ነፃ የምክር አገልግሎት : 📱0911441651 👉@DrSaleamlak https://t.me/DrSaleamlakT https://www.facebook.com/ዶር-ሳለአምላክ-ጥጋቤ-Pediatric-Surgeon-100878625359706/
584
20
ልጄ ከተወለደ 20 ቀኑ ነው። ካካ ሲል በጣም ይጨናነቃል፣ በሦስት ቀን አንዴ ነው ካካ የሚለው፣ ሆዱ ይነፋል፣ አልፎ አልፎ ያስታውከዋል። የመጀመሪያው ካካ በ2ኛ ቀኑ ነበር የወጣለት! ችግሩ ምን ሊሆን ይችላል?(የወላጅ ጥያቄ) 👉በጨቅላ ህፃናት ከሚያጋጥሙት የተለመዱት የአንጀት ችግሮች ውስጥ  Hirschsprung's Disease(HSD) ወይም የአንጀት ነርቭ ችግር አንዱ ነው። 👉ይህ ችግር በትልቁ አንጀት፣ አልፎ አልፎም ቢሆን በትንሹ አንጀት ላይ ተፅዕኖ ያለው እና ሰገራን ለማለፍ ላይ ችግር የሚፈጥር በሽታ ነው። 👉ሁኔታው ህፃኑ በተወለደበት ጊዜ  በአንጀት ጡንቻዎች እና ግድግዳዎች  ውስጥ የነርቭ ሴሎች በማጣት ምክንያት የሚከሰት ችግር ነው 👉እነዚህ የነርቭ ሴሎች ከሌሉ  የአንጀት ጡንቻዎች በትክክል ስለማሰሩ  አንጀት ካካ ለማንቀሳቀስ የሚረዳውን አቅም ያጣል 👉እናም ወደ ኋላ ተመልሶ የአንጀት መዘጋት ሊያስከትል ይችላል። 👉ይህ  በሽታ ያለበት አዲስ የተወለደ ሕፃን ብዙውን ጊዜ ከተወለደ በኋላ ባሉት ቀናት ውስጥ የአንጀት መንቀሳቀስ ችግር ያጋጥመዋል። 👉ችግሩ መለስተኛ ሲሆን በልጅነት ጊዜ ውስጥ በሽታው ላይገኝ ይችላል። 👉እድሜአቸው ከፍ እስኪል ድረስ ሊቆይ ይችላል። 👉ያልተለመደ ቢሆንም በአዋቂዎች ላይ የመገኘት እድል አለው። ✍ጥያቄ-1: ምልክቶቹ ምን ምን ናቸው? 👉የዚህ በሽታ ምልክቶች እንደ ሁኔታው ​​ክብደት ይለያያሉ። 👉 ብዙውን ጊዜ ምልክቶቹ ከተወለዱ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ይታያሉ፣ 👉 ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ለአመታት ምልክቶቹ ላይታዩ ይችላሉ። 👉በተለምዶ በጣም ግልፅ ምልክት አዲስ የተወለደ ልጅ ከተወለደ ከ24-48 ሰአታት ውስጥ ካካ አለማድረጉ ነው። 👉አዲስ በተወለዱ ሕፃናት ላይ ሌሎች የሚከተሉትን ምልክቶችን ሊያካትቱ ይችላሉ- 👉👉 የሆድ መነፋት 👉👉ማስታወክ : አረንጓዴ ወይም ሐሞት የመሰለ ነገር 👉👉የሆድ ድርቀት ወይም ማማጥ ፣ ካካ ሲል መጨናነቅ 👉👉 ተቅማጥ 👉👉የመጀመሪያው ካካ መዘግየት 👉በትልልቅ ልጆች ላይ የሚከተሉትን ምልክቶችን ሊያካትት ይችላል: 👉👉 የቆየ ሆድ መነፋት(abdominal distension) 👉👉ሥር የሰደደ የሆድ ድርቀት(constipation) 👉👉ተደጋጋሚ የአንጀት ኢንፌክሽ(Enterocolitis)- ትኩሳት፣ የተለየ ሽታ ተቅማጥ፣ የሆድ መነፋት 👉👉የእድገት ውስንነት(Failure to thrive) ✍ጥያቄ-2: መንስኤዎቹ ምን ምን ናቸው? 👉የዚህ ችግር መንስኤ ምን እንደሆነ ግልጽ አይደለም። 👉 አንዳንድ ጊዜ በቤተሰብ ውስጥ የሚከሰት እና በአንዳንድ ሁኔታዎች ከጄኔቲክ  ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል። 👉ይህ ችግር የሚከሰተው በታችኛው የአኝጀታችን ክፍል ውስጥ ያሉ የነርቭ ሴሎች ሙሉ በሙሉ ሳይፈጠሩ ሲቀሩ ነው። 👉 በአንጀት ውስጥ ያሉ ነርቮች ምግብን በሆድ ውስጥ የሚያንቀሳቅሱትን የጡንቻ መኮማተር እና መላላትን ይቆጣጠራሉ። 👉ይህ ሒደት ከሌለ ሰገራ በትልቁ አንጀት ውስጥ ይቆያል። ✍ጥያቄ-3: የትኞቹ ህፃናት የበለጠ ተጠቂ ይሆናሉ? 👉ይህ ችግር ያለበት ወንድም ወይም እህት መኖር 👉 ወንዶች ከሴቶች የመያዝ እድላቸው ከፍ ያለ ነው። 👉ሌሎች በዘር የሚተላለፉ ሁኔታዎች መኖር   ለምሳሌ Down syndrome (ዳውን ሲንድሮም) ✍ጥያቄ-4: ተያያዥ ችግሮቹ ምን ምን ናቸው? 👉ይህ በሽታ ያለባቸው ህጻናት enterocolitis ለተባለ ከባድ የአንጀት ኢንፌክሽን ይጋለጣሉ 👉Enterocolitis ለሕይወት አስጊ ሊሆን ስለሚችል ፈጣን ህክምና ያስፈልገዋል። ✍ጥያቄ-5: በምን ምርመራ መረጋገጥ ይችላል? 👉የታሪክ እና የአካል ምርመራ በኋላ ይህ ችግር መሆን እና አለመሆኑን ለማረጋገጥ  ከሚከተሉት ምርመራዎች ውስጥ አንዱን ወይም ከዚያ በላይ ሊሰራላቸው ይችላል። 1) የሆድ ራጅ     👉የአንጀት መዘጋት መኖር አለመኖሩን ያሳያል!     👉የአንጀት ኢንፌክሽን እና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ለማየት ይረዳል 2) Barium enema: 👉ባርየም የሚባል ማቅለሚያ በመጠቀም የሚሰራ የሆድ ራጅ ነው። 👉ባሪየም ወይም ሌላ የንፅፅር ማቅለሚያ በፊንጢጣ ውስጥ በተገጠመ ልዩ ቱቦ ውስጥ ወደ አንጀት ውስጥ ይገባል። 👉ባሪየም ይሞላል እና የአንጀትን ቅርፅ ይይዛል 👉ይህም ትልቁ አንጀት እና የፊንጢጣ ጥርት ያለ ምስል ይፈጥራል 👉ብዙውን ጊዜ ነርቭ በሌለበት ጠባብ የአንጀት ክፍል እና ከጀርባው ባለው ጤነኛ ፣ግን ብዙ ጊዜ እብጠት(ሰፋ ባለው) የአንጀት ክፍል መካከል ግልፅ ልዩነት ያሳያል ። 👉እናም ችግሩን በቀላሉ ማየት ይቻላል 3) Biopsy(ባዮፕሲ): 👉ይህ የመጨረሻው የማረጋገጫ ምርመራ ነው። 👉ከአንጀት ግድግዳ ናሙናን በመውሰድ ለመለየት በጣም ትክክለኛው መንገድ ነው። 👉ከዚያም የነርቭ ህዋሶች መኖር አለመኖራቸውን መረጋገጥ ይኖርበታል። ✍ጥያቄ-6: ሕክምናው ምን ይሆን? 👉የነርቭ ሴሎች የጎደለውን የአንጀት ክፍል ለማለፍ ወይም ለማስወገድ በቀዶ ጥገና ይታከማል። 👉ይህንን ለማድረግ ሁለት መንገዶች አሉ-      1) በአንድ ጊዜ የሚሰራ ቀዶ ህክምና ወይም     2) በሁለት ደረጃ የሚሰራ ቀዶ ህክምና( መጀመሪያ ጊዜአዊ የሰገራ መውጫ በሆድ በኩል መስራትና ናሙና መውሰድ፣ ሁለተኛው ቀዶ ህክምና ችግር ያለበትን የአንጀት ክፍል በማውጣት በጤነኛ የአንጀት ክፍል መተካት) ✍ጥያቄ-7: የቅድመ ቀዶ ጥገና የሚደረጉ ህክምናዎች ምን ምን ናቸው? 👉ይህ  በሽታ ሕክምናው በቀዶ ሕክምና  ነው። 👉ይሁን እንጂ ከቀዶ ጥገና በፊት ግምት ውስጥ መግባት ያለባቸው በርካታ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች አሉ። 👉የመጀመርያው ቅድሚያ የሚሰጠው በተለይ የአንጀት መዘጋት(intestinal obstruction) እና የአንጀት ኢንፌክሽን(enterocolitis) ያለባቸው ህፃናት: 👉👉በደም ስር የሚሰጥ በቂ ፈሳሽ መውሰድ አለባቸው! 👉👉 እንዲሁም የኢንፌክሽን መድኃኒት መውሰድ ይገባቸዋል። 👉👉በፊንጢጣ አንጀታቸው መታጠብ አለበት 👉👉ጊዜአዊ ሰገራ መውጫ መስራት(Colostomy)ሊያስፈልግ ይችላል። ይቀጥላል.... ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ እንሰራለን!!! አዘጋጅ ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ:     የህፃናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም Dr. Saleamlak Tigabie:     MD, Pediatric Surgeon, Assist. Prof. Of Pediatric Surgery, FCS-ECSA (at DCSH), WU, Dessie ተጨማሪ አድራሻ:      🩺ባቲ ጠቅላላ ሆስፒታል ለበለጠ መረጃ እና ነፃ የምክር አገልግሎት : 📱0911441651 👉@DrSaleamlak https://t.me/DrSaleamlakT https://www.facebook.com/ዶር-ሳለአምላክ-ጥጋቤ-Pediatric-Surgeon-100878625359706/
698