cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

🌱 ጉብዝናዬ ለታረደው በግ🐏

“እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስና በኀይል ቀባው፤ እርሱም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ በደረሰበት ሁሉ መልካም እያደረገ በዲያብሎስ ሥልጣን ሥር የነበሩትን ሁሉ ፈወሰ።

Show more
Advertising posts
283
Subscribers
+824 hours
+197 days
+3030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

LOADING
Show all...
4👍 2
📆 ነገ (#ሰኞ) ነው። ቀጠሮ አለን፥ 〽️ ቦታ እናት ቃለ ህይወት ቤተ/ክ 〽️ ሰአቱ 8:00 ሰአት ነው። *ሁኔታውን ሳይሆን ጌታን አክብሩ❕ “ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ 🙏ስለዚህ በሥጋችሁ #እግዚአብሔርን_አክብሩ።” — 1ኛ ቆሮንቶስ 6፥19-20 ጌታን አክብሩ ማለት እርሱን ማጉላት፣ ለእርሱ ክብርና ቦታ ስጥ ማለት ነው።
Show all...
🥰 3
1ኛ ቆሮንቶስ 15 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³ እኔ የተቀበልሁትንና ከሁሉ በላይ የሆነውን ለእናንተ አስተላልፌአለሁ፤ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚሉት ክርስቶስ ስለ ኀጢአታችን ሞተ፤ ⁴ ተቀበረ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተጻፈውም በሦስተኛው ቀን ተነሣ፤ ⁵ ከዚያም ለኬፋ ታየ፤ ቀጥሎም ለዐሥራ ሁለቱ ታየ፤ እንኳን አደረሳችሁ from Elisha
Show all...
🥰 1
🔰እንኳን ለትንሳኤው መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ!   ደግሞም ፋሲካው የእግዚአብሔር ነው! “ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ 👉ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ 👉እድፈትም ለሌለበት 👉ለማያልፍም ርስት #እንደ_ምሕረቱ_ብዛት 〽️ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ይህም #ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን #በእምነት #በእግዚአብሔር_ኃይል ❤ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።” —1ኛ ጴጥሮስ 1፥3-5   🙏ሞቶ አልቀረም፤ ተነስቷል!   🙏ምህረቱ የሚገባንን ቅጣት ከለከለ፤    ፀጋውና ፍቅሩ ግን የማይገባንን ሰጠን።    〽️ከጉብዝናዬ ዘላለም አበራ
Show all...
4
... የ🀄ጠለ 🪧PASSOVER  ፋሲካ (passing over)    🐏ፋሲካውን ፋሲካ ሊያደርግ የቻለው በጉ እንደሆነ ሁሉ  በውጭ መልክ መታለፋችንና በውስጥ ደግሞ መብላችን ሆኖ አገልግሏል ይህ በግ።     👉 - ዘጸአት 12፥4: የቤቱ ሰዎች ቍጥርም ለጠቦቱ የማይበቃ ቢሆን እርሱና ለቤቱ የቀረበው ጎረቤቱ እንደ ነፍሶቻቸው ቍጥር አንድ ጠቦት ይውሰድ፤ እያንዳንዱም እንደሚበላው መጠን ከጠቦቱ ይካፈሉ።      ▫በዋነኛነት የፋሲካው በግ ስጋ በእሳት ተጠብሶ መብላት እንዳለበትና መትረፍ እንደሌለበት እንመለከታለን። ለአሁኑ ግን ጥቂት ነገሮችን እንመልከት።  በጉ በየቤቱ ነበር የሚሆነው   ይህንንም ስንረዳ ጌታ ኢየሱስ ለሁሉም ቢታረድም መታረዱ ግን ሚሰራለት በግል ለተቀበሉት ብቻ ነው።   ጌታ ኢየሱስን በቡድን ልንቀበለው እንችልም በግል እንጂ።      ▫በመቀጠል ደግሞ የበጉ ምልክት ያለበት ቤት ውስጥ ደግሞ የሚበላው የበጉ ስጋ አለ።   እና ቤተሰቡ ይሰበሰብና በጋራ ይበላዋል  የቻለውን ያህል።  የመሰብሰባቸው ምክንያት በጉ እንጂ ምሽቱ ብቻ አልነበረም።    ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ከእግዚአብሔር ቁጣ ያመለጡት ሚጠለሉባትና  የመሰብሰቃቸው ዋና ምክንያት ቀጉ የሆነባት ናት ቤተ ክርስቲያን።     ▫በተረፈው የሚበሉት የተለያዩ ነገሮች ከእርሾ ነፃ የሆኑ ነገሮች አሉ እርሱም የክርስቶስን ንፅህና ይገልፅልናል።       🎚ይህም በግብፃዊያን አማልክት ላይ ከወረደው መቅሰፍት አስረኛው መሆኑ ነው።    🎚በግብፅ የነበሩት የእስራኤል ልጆች የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ተከትለው የመጀመሪያውን ፋሲካ አደረጉ። ሆኖም ከግብፃውያን መካከል አንዳቸውም እንዲህ አላደረጉም። በግብፅ በሙሉ፣ ምልክት ከሌለው፣ ደም ከሌለው የግብፃውያን በሮች ጀርባ፣ የበኩር ልጆች በመንፈቀ ሌሊት ሞቱ (ዘጸአት 12፡21–29)። "በግብፅ ውስጥ ታላቅ ዋይታ ሆነ፥ የሞተም የሌለበት ቤት አልነበረምና" (ቁጥር 30) ይህ አስከፊ ፍርድ በመጨረሻ የግብፅን ንጉስ ልብ ለወጠው፣ እናም የእስራኤልን ባሪያዎች ፈታ (ቁጥር 31-32)።   🎚 በእምነት የፋሲካውን በግ ደም በቤታቸው ያደረጉ እስራኤላውያን ለእኛ አርአያ ይሆናሉ። እስራኤላውያን ያዳናቸው የዘር ግንዳቸው ወይም ጥሩ አቋም ወይም ተወዳጅነት አልነበረም። ከሞት ነፃ ያደረጋቸው የበጉ ደም ብቻ ነው (ዮሐንስ 1:29 እና ራዕይ 5፡9–10)።   🎚በአጭሩ ሲጠቀለል "ሕይወትም ትንሳኤም ሰንበታችንም ኢየሱስ ነው በቃ። 🕎#ፋሲካችን_ክርስቶስ_ታርዶልናል! ...
Show all...
👍 1
  🎚#የእግዚአብሔር_ፋሲካ! ✝ፋሲካው የእግዚአብሔር ነው  ❣ እንኳን አደረሳችሁ።       💯share    share  share
Show all...
2
🪧PASSOVER   (passing over”) ፋሲካ ምንድን ነው?    ▫   #ፋሲካ (passing over  ወይንም ማለፍ ማለት ነው።)(በዕብራይስጥ pasach) በመጀመሪያ፦ እግዚአብሔር ከደሙ የተነሳ ማለፉንና፤ በሁለተኛም፦  እስራኤላውያን በመታለፋቸው ምክንያት ከግብፃውያን ባርነት ነፃ መውጣታቸውን የሚታወጅ መታሰቢያ ነው። 👉- ዘጸአት 12፥11: ፤ እርሱ #የእግዚአብሔር_ፋሲካ ነው።    ▫በመጀመሪያ ደረጃ  ይህ ፋሲካ የአይሁዳዊያን ሳይሆን የእግዚአብሔር እንደሆነ ከክፍሉ እንመለከታለን።  ይህንንም ምልክት የምንረዳው ከቃሉ ነው።  በተጨማሪም 📖 - ዘሌዋውያን 23፥2: ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ የተቀደሰ ጉባኤ ብላችሁ #የምታውጁአቸው #በዓላቶቼ፥ የእግዚአብሔር በዓላት፥ እነዚህ ናቸው።   ይህ በዓል የእግዚአብሔር ነው እግዚአብሔር በሚያደርገው መደሰት እንደማለት ነው በአሉ ለእኛ። በመቀጠል ደግሞ የእግዚአብሔር ፋሲካ የተባለበት ምክንያት በእርሱ መመሪያ ትዕዛዝ ስለሚከናወን ነው።     👉📖- ዘጸአት 12፥2: ይህ ወር የወሮች #መጀመሪያ_ይሁናችሁ፤ የዓመቱም መጀመሪያ ወር ይሁናችሁ።      ~በመቀጠልም የራሱን የሆነ ፋሲካን ለአይሁድ ሲሰጥ ይህ ፋሲካ መጀመሪያቸው እንዲሆን ነው ምክንያቱም ባበቁበት ህይወትን የጀመሩት ያኔ ነበር።   ወር እና አመት የነገሮች መቁጠሪያ ናቸው ካለበጉ በእግዚአብሔር ፊት ሚቆጠርልን እድሜ የለም ሚቆጠርልን ልጅነት የለም።        ~ይህም ወር በእኛ ሚያዝያ ሲሆን በእነሱ ኒሳን ይሆናል  ከነዓናዊያን ደግሞ አቢብ ብለው ይጠሩታል፤ #አቢብ የሚለው የቃሉ ትርጓሜ አዲስ ቡቃያ እሸት ማለት ነው።    🎴የፋሲካ በዓል፣ ከቂጣ በዓል ጋር፣ እስራኤላውያን እንዲያከብሩት በእግዚአብሔር ከታዘዙት በዓላት የመጀመሪያው ነበር (ዘጸአት 12)። በዛሬው ጊዜ የሚከበሩት መታሰቢያዎች ሴደር የሚባል ልዩ ምግብ የሚያካትቱ ሲሆን ይህም የፍልሰትን ልዩ ልዩ ገጽታ የሚያሳዩ ያልቦካ ቂጣ እና ሌሎች ምግቦችን ያቀርባል።    🎴ፋሲካ በብዛት በአይሁድ ከሚከበሩት በዓላት አንዱ ነው። ከሻቩኦት (የሳምንታት ወይም የጴንጤቆስጤ በዓል) እና ሱኮት (የዳስ በዓል) ጋር፣ ፋሲካ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ካሉት ከሦስቱ “የጉዞ” በዓላት አንዱ ነው። ካሉበት ተሰባስበው የሚያከብሩት ነው። ✝#ፋሲካችን_ክርስቶስ_ታርዶልናል❕ 🕎ይ🀄ጥላል... 👉ቴሌግራም ቻናል @GubznayeLEeyesus Z....A
Show all...
3