en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

Soressa KG and primary school

Open in Telegram
300
Subscribers
No data24 hours
+37 days
+2330 days
Posts Archive
ቀን 18/01/2017ዓ.ም ማስታወቂያ ለሶሬሳ ት/ቤት ተማሪዎችና ወላጆች በሙሉ ሰኞ መስከረም 20/01/2017ዓ.ም መደበኛው የትምህርት ፕሮግራም የሚቀጥል በመሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁሶቻቸውንና ምሳቸውን አሟልተው በመያዝ በሰዓቱ በት/ቤት በመገኘት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እናስታውቃለን። መምህራን፣ ሠራተኞችና መልዕክቱ የደረሳችሁ ወላጆች መልዕክቱን ላልሰሙ የት/ቤታችን ወላጆችና ተማሪዎች እንድታስተላልፉ ጭምር እናሳስባለን። ት/ቤቱ

የ2017ዓ.ም የሶሬሳ ቅድመ አንደኛ የመጀ/ እና መካ/ ደረጃ ት/ቤት የመጀመሪያ ቀን የመጀመሪያ ክፍለ ጊዜ ትምህርት አጀማመር

🌻🌻🌻ለሶሬሳ ት /ቤት መምህራን፣ ሠራተኞች፣ ወላጆችና ተማሪዎች በሙሉ 🌻🌻🌻 🌻እንኳን አደረሳችሁ🌻 2017 መልካም አዲሰ ዓመት ይሁንላችሁ አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የጤና፣ የፍቅርና የስኬት ዓመት እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን። ት/ቤቱ 💐🌼 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

ለሶሬሳ አፀደ ህፃናት የመጀ/ እና መካ/ ደረጃ ት/ ቤት ወላጆችና ተማሪዎች የ2017ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቅድመ መደበኛ እና መደበኛ ትምህርት ተማሪዎች የመማሪያ ክፍል ድልድል በት/ቤት ግቢ ውስጥ የተለጠፈ ሰለሆነ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን። ት/ቤቱ

ማስታወቂያ በደሴና አዲስ አለማየሁ አዳሪ ት/ቤቶች በ2017ዓ.ም ለመማር ለምትፈልጉ የ2015 እና 2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የወሰዳችሁ ተማሪዎች በ9ኛ እና 10ኛ ለመማር የምትፈልጉ ማሟላት የሚገባችሁን ነጥብ፣ የመመልመያ መስፈርትና የምዝገባ ጊዜውን የያዘ ደብዳቤ ያያዝንላችሁ ሰለሆነ በስራ ቀናት በት/ቤት እየተገኛችሁ በመመዝገብ በእድሉ እንድትጠቀሙ እናስታውቃለን። ሶሬሳ ት/ቤት

Desse and Hadis Alemayehu s school.pdf1.24 MB

የ2016 ዓ.ም የ6ኛ  እና 8ኛ ክፍል  ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ ።።።።።።   ነሐሴ 12/2016(ትምህርት ቢሮ) በአማራ  ክልል የ2016ዓ.ም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፍ ሆኗል። ከሰኔ 3_4/2016 እና ከሰኔ 13_14/2016 የተሰጠው ክልል አቀፍ የ8ኛ እና 6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት    ዛሬ ተገልጿል። ፈተናውን ከወሰዱት 132,225 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል 97,859(74.1%) ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል። በተመሳሳይ ፈተናውን ከወሰዱት 150,928 የ8ኛ ክፍል  ተማሪዎች መካከል 84,522(56%) ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት አስመዝግበዋል። ለፈተና ከተቀመጡት 82 የአይነ ስውር 6ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል 80(95.18%) ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን ፈተናውን ከወሰዱት 148 የ8ኛ ክፍል አይነስውር ተማሪዎች  መካከል 105(70.94%) ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት አስመዝግበዋል። 👉 በ2016 ክልል አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ሆኖ የተመዘገበው የ6ኛ ክፍል አማካይ ውጤት 100 ሲሆን የ8ኛ ክፍል ደግሞ 97 ሆኖ ተመዝግቧል። ተማሪዎችም በሁለት  አማራጮች ውጤታቸውን ማየት የሚችሉ ሲሆን ➊ በኮምፒውተር ወይም ስልካቸው ባለዉ የድር መፈለጊያ መተግበሪያ ( Web browser Application ) ላይ 👉 ለ8ኛ ክፍል ተፈታኞች https://amhara.ministry.et/#/result የሚለውን አድራሻ በመፃፍ እና 👉 ለ6ኛ ክፍል ተፈታኞች https://amhara6.ministry.et/#/result የሚለውን አድራሻ በመፃፍ በሚመጣው ቅጽ(form) ላይ               የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number) በማስገባት ዉጤት ይመልከቱ (Check your result) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ማየት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም  @emacs_ministry_result_qmt_bot   በሚለው የቴሌግራም ቦት ላይ በመግባት ተማሪዎች ውጤታቸውን መመልከት የሚችሉ ሲሆን በመጀመሪያ             👉start የሚለውን ይጫኑ!            👉በመቀጠልም ክፍልዎን ይምረጡ            👉ከዚያም ክልልዎን ይምረጡ            👉በመቀጠል የምዝገባ መለያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስምን በማስገባት ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ። ተማሪዎች ማንኛውም ከውጤት ጋር የተያያዘ ቅሬታ ካላቸው ማቅረብ ይችላሉ። ቅሬታቸውንም ለማቅረብ ➌በኮምፒውተር ወይም ስልካቸው ላይ ባለዉ የድር መፈለጊያ መተግበሪያ ( Web browser Application ) ላይ:- 👉 ለ8ኛ ክፍል ተፈታኞች https://amhara.ministry.et/#/complaint የሚለውን አድራሻ በመፃፍ እና 👉 ለ6ኛ ክፍል ተፈታኞች https://amhara6.ministry.et/#/complaint  የሚለውን አድራሻ በመፃፍ 👉 በሚመጣው ቅጽ(form) ላይ የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number)እና   የተማሪውን የመጀመሪያ ስም (First Name)በማስገባት 👉 የትምህርት ዓይነት አሳይ(Fetch course) የሚለውን ቁልፍ በመጫን 👉 ቅሬታ ማቅረብ የሚፈልጉበትን ይምረጡ 👉በመጨረሻም ሪፖርት (Add Complaint) የሚለውን  ቁልፍ በመጫን ቅሬታቸውን  ማቅረብ ይችላሉ ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ 1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/ 2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w 3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau 4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse ያግኙን YouTube

የተከበራችሁ የት/ቤታችን ተማሪዎች ወላጆች ከኢንተርኔት መለቀቅ ጋር ተያይዞ ተቋርጦ የነበረው የት/ቤታችን የቴሌግራም የመረጃ ልውውጥ የሚቀጥል መሆኑን እየገለፅን መረጃዎችን ዘወትር እንድትከታተሉ በአክብሮት እናሳስባለን። የ2016 ዓ.ም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት እስካሁን ያልመጣ ሲሆን እንደደረሰን በቴሌግራም ቻናላችን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን። በተመሳሳይ የ2017ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርት መጀመሪያ ጊዜ ቀኑ ሲቃረብ የምናሳውቅ ይሆናል።