cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ፈዘኪር-አስታውስ

«ስለ ዱንያዊ ጉዳይ አዋቂ ሁኖ ስለ አኼራዊ ጉዳይ የማያውቅ የሆነን ሰው አላህ ይጠላዋል»። ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ምንጭ፦📔ሶሒሁል ጃሚዕ (1879)

Show more
Advertising posts
761
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-3030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

➯የቀኑ ⓷ቱ ሐዲሶች ፡፡፡።፡፡፡፡።።።።።።።።።።   []ክፍል:-⓵⓼⓶ [] 1) «ዱዓው ተቀባይነት እንዲኖረውና እንዲሁም ችግሩ እንዲፈታለት የፈለገ ሰው፤ የሌሎችን ችግር ይፍታ»። ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ምንጭ:-📒ሙሰነድ አህመድ (4749) 2)«ዱዓ የተከሰተን አደጋ ለማስወገድ ይጠቅማል እንዲሁም ገና ያልተከሰተን አደጋ ይከላከላል፣ ስለዚህ የአላህ ባሪያዎች ሆይ አደራችሁን ዱዓ በማድረግ ላይ ተበራቱ»። ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ምንጭ፦📒ሶሒሁል ጃሚዕ (3409) 3) «ሙስሊም ወንድሙ ክብሩ እንዳይነካ  እንዳይታማ፣ የተከላከለ፤ አላህ የውሙል ቂያማ ከፊቱ(ከርሱ) እሳት ይከላከልለታል»። ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) 📒ቲርሚዚ ዘግበውል ቴሌግራም ቻናሉን ተቀላቀሉ
Show all...
👍 2
ውድ ወንድሜ! አንተንም ይመለከታል ወንዶች ነበሩ ሰይፍ እያሽኮረመሙ በጀነት ፍቅር ህይወታቸውን ያሳለፋ።አንተ ሴት እያሽኮረምምምክ ጌታህ ዘንድ እጅግ የተወደደውን ጀምዕ ሰላት ታሳልፍለህ ምነኛ ክስረት ነው ። በጎን የአንዷን እህት ህይወት እያበላሸህ በጎን እራሷን አስከብራ የተቀመጠችውን ትመኛለህ አልሰማህንም አላህ (ሱ.ወ) በተከበረ ቃሉ ያለውን መጥፎቹ ሴቶች ለመጥፎቹ ወንዶች መጥፎቹም ወንዶች ለመጥፎቹ ሴቶች የተገቡ ናቸው።ጥሩዎቹም ሴቶች ለጥሩዎቹ ወንዶች ጥሩዎቹም ወንዶች ለጥሩዎቹ ሴቶች የሚገቡ ናቸው ።(አል-ኑር:26) አንተ ካልተቃናህ ማን ሊመራው አንተ ካልበረታህ ማን ሊቆም ለዲህ እስኪ ተመልከት ከጀግኖቹ ጎራ ለሰይፍ አንገታቸው የተንሰራራ ለዲናቸው ሲሉ አንገታቸውን ያሰሉ ታድያ የት ነክ ጀግናው? ጀነትን ስትል ስሜትህን የገታሀው!
Show all...
በሀራም ግንኙነት ውስጥ ሆና ትላላች እኔ ማግባት ምፈልገው ዲን ያለውን መልክ ያለውን ሀብት ያለውን እያለች ታማርጣለች። ""ድንጋይ ሆነሽ ከቀረብሽ ሊቀርብሽ የሚችለው ዶማ ብቻ ነው"" ምትሰሚ ከሆነ በደንም ስሚኝ እህቴ... ጊዜሽን ስብዕናሽን ውድነትሽን አሟጦ ጨርሶ ፤ expair date የደረሱበትን ዕቃ መግዛት ሚፈልግ አለን ብለሽ ታስቢያለሽ? በፍፁም በማይረባ ነገር ግን አላህ አልቆ ፈጥሮሽ መች በዚህ አበቃና ከፍ አድርጎሽ በስምሽ የቁርዐን ምዕራፍ ሰቶሽ እንዴታ ነው እህቴ ይህን ሁሉ ክብር መገፍተርሽ። አትዘኝ ሰው ዳግም ባይፈልግሽ ልዕልና የተገባው ጌታሽ ግን ከነወንጀልሽ ይፈልግሻል ተጎንብሰሽ ይቅርታን ብትማፅኚው ደግሞ ያልቅሻል። ሱብሀነላህ አላህ ሁሌም ጥራት የተገባው ይሁን 🤲
Show all...
#ሚዛን 🔹ሚስት ባሏ ድሃ በሆነ ወቅት ትታወቃለች። 🔹ባል ሚስቱ በታመመች ጊዜ ይታወቃል። 🔹ወንድምና እህት በውርስ ጊዜ ይታወቃሉ። 🔹ጓደኛ በችግር ወቅት ይታወቃል። 🔹ሙእሚን በፈተና ወቅት ይታወቃል።
Show all...
🙏 2
~ነገሮች እንዳይሳኩልን ከሚያደርጉና በስኬት ፊት ከሚቆሙ እንቅፋቶች መካከል አንደኛው ወንጀል ነው ይላሉ ኢማም ኢብኑል ቀይም። አንድን ሀሳብ ለማሳካት ተነስቶ በተደጋጋሚ ሞክሮ አልሳካለት ያለ ሰው ሱስ የሆነበት ያልተላቀቀው ኃጢአት አለና እሱን ይተው ይላሉ ዑለሞች። በ ወንጀላችን ምክኒያት ያጣናቸውን ፀጋዎችን እስኪ ቁጭ ብለን እንቁጠር!?
Show all...
:::::::ህይወት ሚስጥር ናት:::::::☜ ☞⇡በሕይወትህ ምን እደሚጠብቅህ ፣ምን   እንደሚያጋጥምህ አታውቅም። ሁሉንም ነገር ለመቀበል እራስህን ዝግጁ አድርግ። ደግም ሲያጋጥምህ አመስግን፣ ክፉም ሲያጋጥምህ ታጋሽና አመስጋኝ ሁን ። ከችግርም ጋር ምቾት  አለና እራስህን አፅናና። ይቺ ምድር የፈተና ቦታ መሆኗን ላፍታም አትዘንጋ። አላህም እንዲህ ይለናል፦ كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَنَبْلُوكُم بِالشَّرِّ وَالْخَيْرِ فِتْنَةً ۖ وَإِلَيْنَا تُرْجَعُونَ 📖 አል-አንቢያ: 35 📖 ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ ለመፈተንም በክፉም በበጎም እንሞክራችኋለን፡፡ ወደኛም ትመለሳላችሁ፡፡ «አስታውስ! አላህ ከታጋሾች ጋር መሆኑን። አላህን በኸይር ጠርጥረው ኸይር ይሰጥሃል። وَلَسَوْفَ يُعْطِيكَ رَبُّكَ فَتَرْضَىٰ         📖አል ዱሃ :5📖 ጌታህም ወደ ፊት (ብዙን ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል፡፡ ትደሰታለህም፡፡ እናም አላህ እዳለው፦ فَاصْبِرْ صَبْرًا جَمِيلًا       📖 አል-መዓሪጅ:5📖 መልካምንም ትዕግስት ታገሥ፡፡ وَاللَّهُ يُحِبُّ الصَّابِرِينَ       📖አሊ-ዒምራን:146 📖 አላህም ትዕግስተኞችን ይወዳል፡፡ #ሼር_ያድርጉ
Show all...
➪ት.....ዳ.....ር ➥ንቃ ለማለት ነው። 〰️〰️〰️〰️〰️〰️ አርባ ሽማግሌ ደጋግመህ ብትልክም፡ ቆንጆ ለማገኘት ብትለፋ ብትደክም፡ አጋር አታገኝም ለሰው ሆነህ ሸክም፡ ---------- ዘንጠህ ብትወጣ ፈክተህ እንደ አበባ፡ ምላስህ ቢሾልም እንደ ጃርት ወለባ፡ ዲሀ ነው ከተባልክ ክብርህ ነው ገለባ፡ ------------------------------- ሸጋው ተንቀሳቀስ ወንድም አለም ንቃ፡ ፀዳልህ ቢያበራ ቢዋብ ከጨረቃ፡ መልክ የሚጠቅምበት ያ ዘመን አበቃ። ---------------------------------------------- መስራትን ካልወደድክ ከወሬ አስበልጠህ፡ መኖር አይቻልም ራስክን ለውጠህ፡ ለውጥ ከቶ አይመጣም ሁሌም ተቀምጠህ፡ ይልቅ ሳትዋረድ ራስህን ሽጠህ.. ስንፍናህን በይድ በትጋት ቀጥቅጠህ፡ --------------------------------------- በዱንያ ውደታው ትውልዱ ሀይሏል፡ ገንዘብ የሌለው ሰው አውሬ ነው ተብሏል፡ 40 እና 50ሽ ነው መህሩም ተቆልሏል፡ 〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️ ገንዘብ ለሌለው ሰው ትዳር አስፈርቷል፡ ግን ገንዘብ ያለውም እያገባ ፈቷል፡ አልገባንም እንጂ የሆነ ግፍ መጥቷል፡ መልክህ ሸጋ ሆኖ ቢጠፋ አንተን መሳይ፡ ማንም አይፈልግህ ስራህን ሳታሳይ፡ ---------------------------------- ➪በል እንጂ....!! ጉልህ ስህተትህን ሳታርም ቀስበቀስ፡ በደል አይሆንም ወይ ሁሌ ሴትን መውቀስ!? 〰️〰️〰️〰️〰️〰️ 🖋ስማ....!! ይህን ሁሉ ነገር የምጎነጉነው፡ በግጥም ቢገባህ የማሽሞነሙነው፡ ወንዱ ተንቀሳቀስ ንቃ ለማለት ነው። ------------------------------ ...🖋ገጠሬው ኑረዲን ----------------------------------
Show all...
ሰው ሲሄድ የምትሄዱ፤ ሰው ሲቆም የምትቆሙ ደካማ ፍጡር አትሁኑ። ሕይወታችሁን በማንም ላይ፣ ከማንም አንፃር አትመስርቱ። ከአላህ በታች በራሳችሁ ተማመኑ። ራሳችሁን ቻሉ። ስትወጡ ሁሌም ቢስሚላህ ተወከልቱ ዐለሏህ በሉ። መመካት በአላህ ብቻ በቃ።
Show all...
☑️ የአሹራ ቀን ፃም በተመለከተ   〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 አቢ ቀታዳ አል አንሷርይ አላህ መልካም ስራው ይውደድለትና እንዲህ አለ። የአላህ መልእክተኛ ስለ አሹራ ቀን መፃም ተጠይቀው እንዲህም አሉ፦ 【ያለፈውን አንድ አመት ወንጀል ያብሳል】ብለዋል። 📚(ሙስሊም ዘግቦታል።) ◼️መቼ ነው የሚጀመረው⁉️ 〰〰〰〰〰〰〰〰〰 የአሹራ ቀን ፃም የሚጀመረው፦ አሁን ያለንበት የሙሀረም ወር አስረኛው ቀን ላይ ነው። ይህም ማለት የፊታችን ጁሙአ  ነው። ◼️እንዴት ነው የሚፃመው⁉️ 〰〰〰〰〰〰〰〰〰 📍 ነገር ግን አህለል ኪታቦችን ለመሀለፍ ዘጠነኛውን ቀን መፃም የፈለገ (በላጩም ይህ ነውና) የፊታችን ሐሙስ ቀን 9  ይጀምርና ጁሙአ  ቅዳሜ  በተከታታይ ይፃማል ማለት ነው። 📍 ዘጠነኛው ቀን መጨመር ያልተመቸው ደሞ አስረኛውና አስራ አንደኛው ቀን ማለትም ጁሙአንና ቅዳሜ መፃም ይችላል። 📍 አስረኛው (የአሹራውን ቀን) ብቻ እንጂ ከፊትም ሆነ ከኋላ ማስከተል ያልቻለ ችግር የለውም አስረኛውን ቀን ብቻውን መፃም ይችላል። አንዳንድ ኡለማዎች አስረኛው ቀን ብቻውን ከፊት ወይም ከኋላ ሳያስከትሉ መፃም የተጠላ ነው ቢሉም ትክክለኛው ግን ያለምንም መጠላት መፃም ይችላል የሚለው ነው። አቅም አግኝቶ የመፃም ፍላጎት ካለው ግን ሶስቱንም ቀናቶች 9ኛው, 10ኛውና, 11ኛው ማለትም ( ሀሙስ፣ ጁሙአና   ቅዳሜ ) መፃም እንደሚችል ኡለማዎች ገልፀዋል። 📖አላህ በሰላም ያድርሰን ፃመውም ከሚቀበላቸውና ያድርገን
Show all...
☑️ የአሹራ ቀን ፃም በተመለከተ   〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 አቢ ቀታዳ አል አንሷርይ አላህ መልካም ስራው ይውደድለትና እንዲህ አለ። የአላህ መልእክተኛ ስለ አሹራ ቀን መፃም ተጠይቀው እንዲህም አሉ፦ 【ያለፈውን አንድ አመት ወንጀል ያብሳል】ብለዋል። 📚(ሙስሊም ዘግቦታል።) ◼️መቼ ነው የሚጀመረው⁉️ 〰〰〰〰〰〰〰〰〰 የአሹራ ቀን ፃም የሚጀመረው፦ አሁን ያለንበት የሙሀረም ወር አስረኛው ቀን ላይ ነው። ይህም ማለት የፊታችን ጁሙአ  ነው። ◼️እንዴት ነው የሚፃመው⁉️ 〰〰〰〰〰〰〰〰〰 📍 ነገር ግን አህለል ኪታቦችን ለመሀለፍ ዘጠነኛውን ቀን መፃም የፈለገ (በላጩም ይህ ነውና) የፊታችን ሐሙስ ቀን 9  ይጀምርና ጁሙአ  ቅዳሜ  በተከታታይ ይፃማል ማለት ነው። 📍 ዘጠነኛው ቀን መጨመር ያልተመቸው ደሞ አስረኛውና አስራ አንደኛው ቀን ማለትም ጁሙአንና ቅዳሜ መፃም ይችላል። 📍 አስረኛው (የአሹራውን ቀን) ብቻ እንጂ ከፊትም ሆነ ከኋላ ማስከተል ያልቻለ ችግር የለውም አስረኛውን ቀን ብቻውን መፃም ይችላል። አንዳንድ ኡለማዎች አስረኛው ቀን ብቻውን ከፊት ወይም ከኋላ ሳያስከትሉ መፃም የተጠላ ነው ቢሉም ትክክለኛው ግን ያለምንም መጠላት መፃም ይችላል የሚለው ነው። ↪️ አቅም አግኝቶ የመፃም ፍላጎት ካለው ግን ሶስቱንም ቀናቶች 9ኛው, 10ኛውና, 11ኛው ማለትም ( ሀሙስ፣ ጁሙአና   ቅዳሜ ) መፃም እንደሚችል ኡለማዎች ገልፀዋል። 📖አላህ በሰላም ያድርሰን ፃመውም ከሚቀበላቸውና ያድርገን
Show all...
ኢብኑ ተይሚያ የተውሂድ የሱና ቻናል

➡️ በቻናላችን የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች ➲የአቂዳ ኪታቦች ➲የፊቅህ ግንዛቤዎች ➲የሱና ኡለማዎች ፈትዋ ➲ወቅታዊ ምክሮች ➲የቁርአን ቂርአትና ሌሎችም http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru