cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Freshman and remedial

📌ለfreshman እና ለremedial ተማሪዎች ✔️Freshman module📚 ✔️ Remedial module📚 ✔️Note📒 ✔️ Ppt📑 ✔️Mid and final exam📜 ✔️Freshman exa📄 ✔️Remedial exam🧾 ⤵️ ሁሉንም በአንድ ላይ የምታገኙበት ቻናል 👇👇

Show more
Ethiopia5 236The language is not specifiedEducation38 014
Advertising posts
3 339
Subscribers
+624 hours
+467 days
+27930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🖊 በቀጣይ ዩኒቨርሲቲ የምትገቡ የ ማህበራዊ ሳይንስ(social science) ተማሪዎች የ መጀመሪያው ሴሚስተር ላይ ስለምትወስዷቸው ኮርሶች መረጃ። 🥰 የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የመጀመሪያ አመት የመጀመሪያው ሴሚስተር ላይ የምትወስዷቸው ኮርሶች👇 💠 Communicative English Skill I 💠 Economics 💠 Geography 💠 Maths(Social) 💠 Civics and Moral Education 💠 Global Trends 💠 Physical Fitness 🙌 አሁን ደግሞ ስለ እያንዳንዱ ኮርስ መጠነኛ የሆነ ገለፃ ወይም ጅንጀና እናድርግ። ⚡የተወሰኑት ኮርሶች ከnatural ጋር ተመሳሳይ ስለሆነ ባለፈው ፖስት ያረግነውን ማየት ትችላላችሁ➡️ here 💻 Economics 📚 ግቢ ላይ ብዙ ሰቃይ ተማሪዎች Economics ን አይሰሩትም🙇‍♂️። 3.7 or 3.8 ያላቸው ልጆች Economics ን B- ምናምን ነው የሚያመጡት። ምን ልላችሁ ፈልጌ ነው ግቢ ላይ የ Economics ትምህርት ፈተናዎች ወይም ጥያቄዎች conceptual ናቸው። ስለዚህ Economics ን ስታነቡ አትሸምድዱ። በቻላችሁት መጠን ሳይንሱን ለመረዳት ሞክሩ ፡ ተግባራዊ እውነታውን ተረዱ።ከኛ ጋር ከሆናችሁ ደሞ እመኑን A+ ታመጣላችሁ 😎 💻 Maths (Social) 📚 ከ መጠነኛ ለውጥ ( modification) ውጭ 11 እና 12 የተማራችሁት ነው። 📚 በይበልጥ ፈተና ሲውጣ Basic ነገር ነው የሚያወጡት Module ማንበብ ለዚ ግዜ በጣም ወሳኝ ነው Module በደምብ ሳታነቡ Reference እንዳገልጡ አደራ Defintion , Properties , Exercises ..... module ላይ ያለውን በደምብ ያዙ የሚሰጣቹ Course outline ላይ ያለውንም ነጥብ በደምብ ተመልከቱ ምን ላይ ማተኮር እንዳለባቹ ይረዳቹሀል:: 💻 Civics and Moral Education 📚 ዩኒቨርሲቲ ላይ የሚሰጠው የ Civics and Moral Education ኮርስ ፤ Highschool ና pre paratory ከሚሰጠው ኮርስ ጋ በፍፁም አይገናኝም። ግቢ ላይ ያለው የ Civics ኮርስ ለተማሪዎች የሚያስቸግር ከባድ ኮርስ ነው። ይህ ኮርስ በተለይ ስለ Ethics ና Morality ምንነት በስፋት ያትታል። ከ Ethics ጋ የተያያዙ የ ሞራል ፍልስፍናዎችን ና ንድፈሀሳቦችን በስፋት ይዳስሳል። በተለይ ስለ Normative ና non-normative Ethics, Teleological Ethics, Ethical Egoism and psychological Egoism, Altruism, Utilitarianism, Quality over quantity Ethics, Quantity over quality Ethics, Act and Rule Utilitarianism, Virtue Ethics, Meta Ethics በጣም በስፋት ይዳስሳል። እንዲሁም ደግሞ ስለ state, government ና citizenship ምንነት በስፋት ያጠናል በተለይ ስለ pluralist state, capitalist state, Leviathan state, Patriarchal state, minimal state, developmental state,social-democratic state, collectivized state, totalitarian state, religious state ና ስለ Citizenship በጣም በስፋት ያጠናል። አይዞዓቹ እኛ አለንላችሁ 🥸 🥸 የ ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች first semester course እነዚህ ናቸው። በቀጣይ የእነዚህን ኮርሶች መፅሀፍ በ pdf እንለቅላችሗለን። ⭐️ADVANCED FRESHMAN COURSE
Show all...
👍 10🙏 4
❓ግቢ ውስጥ Grade እንዴት ነው ሚሰራው 🤔 ⭐️ GPA or CGPA ምን ማለት ነው ላላችሁኝ 😍 ጉድ የማያልቅበት ትምህርት ሚንስተር የሚያወጣው አዲስ ህግ እስካልኖረ ድረስ የሁሉም ግቢዎች grading system ተመሳሳይ ነበር በእያንዳንዱ ሴሚስተር ⏺️ Out of 20 or 30% Test, Quizzes , group work or Assignment ⏺️ Out of 20 or 30 % MID EXAM ⏺️ Out of 50% Final Exam ለእያንዳንዱ ኮርስ የሶስቱ ድምር ውጤት ሴሚስተር መጨረሻ ላይ ይደመርና ለጠቅላላ ኮርሶቹ ተካፍሎ ግሬድ ይሰራላቹሃል ። የስድስቱም ኮርሶች ድምር Garde ከተሰራ በኋላ የምታስመዘግቡት ውጤት የትምህርት መስክ ለመምረጥ ትምህርት ሚኒስተር ባወጣው range ልክ value ይኖረዋል ። ⛔ GPA ማለት በሁሉም ሴሚስተር የምታስመዘግቡት ግሬድ ማለት ነው ⛔ CGPA ማለት Average Grade ማለት ነው። 🔔 በመጀመሪያው ሴሚስተር የተጠቀሱትን አምስት የትምህርት መስኮች join ለማድረግ የምትፈልጉ ተማሪዎች ለውድድር የሚታየው first semister GPA ብቻ ይሆናል ፤ የተቀሩትን የትምህርት መስኮች join ማድረግ የምትፈልጉ ተማሪዎች ግን የሚያዝላቹህ የሁለቱም ሴሚስተር Average or CGPA ይሆናል ማለት ነው። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስተር አለ የተባለው ወይም ትላንት Post ያደረኩላቹህ 20% entrance , 30% PRE-FEILD ምናምን የተባለውን ነገር በሁሉም ዩንቨርሲቲዎች ላይ በዚህ ዓመት ተግባራዊ ሆነም አልሆነ የመጀመሪያ ሴሚስተር ግሬድ ግን ማንኛውንም የትምህርት መስክ ለመምረጥ ትልቁን ድርሻ ይይዝላቹሃል ፡ ስለሆነም 20%ቷ እውን ከሆነች entrance exam ስለተበላሸብኝ ብላቹህ ተስፋ አትቁረጡ ፤ ሲጀመር 20% ምናምን የተባለው ጉዳይ የሚኒስተር መስሪያ ቤቱ ማህተምና የክብርት ሚኒስተሯ ፊርማ ስላረፈበት አስደንግጦኝ Post አደረኩላቹህ እንጂ እስካሁን 100% እርግጠኛ ሆኖ ለማውራት የሚያስደፍር ማረጋገጫ ከበላይ አካላት አልደረሰንም ፤ ትምህርት ሚኒስተርም ተማሪው ሁለት ልብ ሆኖ እየጨለለ ባለበት ባሁኑ ወቅት ምንም አይነት ማስተባበያ አልያም ማረጋገጫ አለመስጠቱ አስከፍቶኛል ። ለማንኛውም ግን በውስጥ መስመር ብዙ ተማሪዎች የዩንቨርሲቲ ግሬድ calculation አልገባንም ባላችሁኝ መሰረት ከአራት ወራት በፊት post ያደረኩላችሁን በድጋሚ ለማስታወስ እገደዳለሁ For instance AAU first semister coursoch እነዚህ ናቸው ብንልና የኮርሶቹም ECTS እንደሚከተለው ቢሆን ♨️Critical thinking...... #5Ects ♨ Psychology........... #5Ects ♨️ General Physics. #5Ects ♨ English .............. #5Ects ♨️Geography ..........#5Ects ♨️Mathematics......# 6Ects ♨️Physical fitness (pass or fail) ✍️Total credit hours #31Ects ተማሪ አለባቸው ደብድባቸው እርገጣቸው😂 የተባለ ተማሪ በመጀመሪያው ሴሚስተር ያስመዘገበው ውጤት 1) Critical thinking-------> 77 🔫✂B+ 2) Psychology ---------->82 🔫✂A- 3) Gen' Physics --------->59.9🔫✂C 4) Mathematics---------->42 🔫✂D 5) English ------------>68 🔫✂B- 6) Geography ------------->64 🔫✂C+ ነው ብንል የተማሪ ሙጃን ግሬድ እንደሚከተለው ማወቅ ይቻላል በቅደም ተከተል calculate ማድረግ 🔍 Credit hour × grade 5×3.5 =17.5 5×3.75 =18.75 5×2 =8 6×1 =6 5×2.75 =13.75 5×2.5 = 12.5 Total sum=76.5 Semister grade = Total sum÷Total credit hour 76.5÷31=2.467GPA ስለዚህ ተማሪ ሙጃ በመጀመሪያው ሴሚስተር የሰራው ግሬድ 2.46 ነው ማለት ነው ። Status of first year students in the first semister ፤ የአንደኛ አመት ተማሪዎች በመጀመሪያው ሴሚስተር የሚያስመዘግቡት ግሬድ እንደሚከተለው ወደ ቀጣዩ ሴሚስተር Pass or Fail ያስብላቸዋል GPA Status 1.75-4.00 ➡️Promoted 1.50-1.75 ➡️Warning 1.00-1.50 🔫Academic dismissal( ለአንድ ዓመት ላግ ) 0.00-1.00 ❌Complete dismissal ከትምህርት ዓለም ሙሉ በሙሉ ላግ 😤) ከዚህ ውጭ ደግሞ በአንድ ሴሚስተር ሶስት ኮርሶች የፈሉበት ተማሪ ሴሚስተር ላግ ይኖርበታል ምናምን የሚባልም ነገር አለ ቢሆንም ግን የኛ ቤተሰቦች ሁሉም ለሜዲስን ስለሚቸክሉ F ምናምን እንደማያሳስባቸው ይሰማኛል 🧛‍♂️ ከላይ የጠቀስኩላቹህ የግሬድ አሰራር ካልገባቹህ ደግማቹህ አንብቡትና በድጋሚ ካልገባቹህ ባቅራቢያቹህ የሚገኙ ነባር ተማሪዎችን refer አድርጉ ። Join and share⭐
Show all...
👍 9
Photo unavailableShow in Telegram
#update #Result #Remedial #Exit_Exam የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና እና የሪሚዲያል ማጠቃለያ ፈተና ውጤቶች መቼ ይፋ ይደረጋሉ? ቲክቫህ ዩንቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴር አመራር አገኘሁት ብሎ ያጋራው መረጃ👇 📌 የሪሚዲያል ተማሪዎቹ ውጤት ከሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ቀናት በጣም ከዘገየ እስከ #ሰኞ ሰኔ 24/2016 ዓ.ም ይፋ ይሆናል። 📌 የመውጫ ፈተና ውጤት በቀጣይ ቀናት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ማስመረቅ ከመጀመራቸው #በፊት ይፋ ይደረጋል።
Show all...
👍 7🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
#Update የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና ውጤት ከመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ይፋ እንደሚደረግ ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ሰምቷል። የፈተናው ውጤት መቼ ይፋ እንደሚደረግ በርካታ ተማሪዎች ጥያቄያቸውን አድርሰውናል። የፈተናው ውጤት መቼ ይገለፃል ስንል የጠየቅናቸው የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር፤ "በቅርቡ፥ ከመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ቀናት" ሲሉ መልሰውልናል። የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና ከሰኔ 3-11/2016 ዓ.ም መሰጠቱ ይታወሳል።
Show all...
🙏 4👍 2
✅ practice practice practice it❗
Show all...
👍 3
✅ PHYSICS FOR PRE-REMEDIAL PROGRAM STUDENTS EXAM PRACTICE IT ❗❗❗
Show all...
👍 2
Maths 2015 remedial exam @freshman_remedial
Show all...
👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
ይለማመዱ! የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የኦንላይን የመፈተኛ ፕላትፎርም አጠቃቀምን ይለማመዱ! ፕላትፎርሙን እንዴት መጠቀምና እንዴት ፈተናውን መውሰድ እንደሚቻል ለማሳየት በትምህርት ሚኒስቴር እና በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተዘጋጀን የአራት ደቂቃ ገላጭ ቪዲዮ በተከታዩ ሊንክ በመግባት ይመልከቱ፡፡ ራስዎን ለፈተናው ያዘጋጁ! ቪዲዮውን ይመልከቱ 👇 https://www.youtube.com/watch?v=PdAu-FI-Q5M
Show all...
👍 3
በበይነ መረብ (Online) የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና በተመለከተ የተሰጠ ማብራሪያ በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በበይነ መረብ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወረቀት አልባ በማድረግ የዲጂታል ጉዞውን አንድ ምዕራፍ ጀምሯል። ይሄንንም ጉዞ የተሳካ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡ ለተፈታኞች በክላስተር የተዘጋጀው ማስፈንጠሪያ (URL) ከፈተናው በፊት ገብተው የሚለማመዱበት ሲሆን የፈተናው እለት ደግሞ መፈተኛ ይሆናል። ስለሆነም ከዚህ በታች በምትፈተኑበት የፈተና ክላስተር ፊትለፊት በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ በመግባት መለማምድ ትችላላችሁ፡፡  እስካሁን username እና password ያለገኘ ተፈታኝ ካለ፣ ከዚህ በፊት ለትምህርት ቢሮዎች ስለተላከ፣ ከየትምህርት ቤቱ አስተባባሪዎች ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ክላስተር አንድ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር፡ https://c2.exam.et  ሲዳማ ብሄራዊ ክልል፡ https://c2.exam.et ትግራይ ብሄራዊ ክልል፡ https://c2.exam.et ክላስተር ሁለት ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፡ https://c3.exam.et ጋምቤላ ህዝቦች ክልል፡ https://c3.exam.et አማራ ብሄራዊ ክልል፡ https://c3.exam.et ክላስተር ሶስት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል: https://c4.exam.et ሀረሪ ብሔራዊ ክልል: https://c4.exam.et አፋር ብሔራዊ ክልል: https://c4.exam.et ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል - 1 • አዳማ ከተማ: https://c4.exam.et • አጋሮ ከተማ: https://c4.exam.et • አምቦ ከተማ: https://c4.exam.et • ምሥራቅ አርሲ: https://c4.exam.et • ምዕራብ አርሲ: https://c4.exam.et • አሰላ ከተማ: https://c4.exam.et • ባሌ: https://c4.exam.et • ባቱ ከተማ: https://c4.exam.et • ቤሾፍቱ ከተማ: https://c4.exam.et • ቦረና: https://c4.exam.et • ቡሌ ሆራ ከተማ: https://c4.exam.et • ቡኖ በደሌ: https://c4.exam.et • ዶዶላ ከተማ: https://c4.exam.et • ምሥራቅ ባሌ: https://c4.exam.et • ምሥራቅ ቦረና: https://c4.exam.et • ጉጂ: https://c4.exam.et • ምሥራቅ ሐረርጌ: https://c4.exam.et • ምዕራብ ሐረርጌ: https://c4.exam.et • ሆለታ ከተማ: https://c4.exam.et • ሆሮ ጉዱሩ: https://c4.exam.et • ኢሉባቦር: https://c4.exam.et ክላስተር አራት ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር: https://c5.exam.et ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል - 2 • ጅማ: https://c5.exam.et • ጅማ ከተማ: https://c5.exam.et • ቄለም ወለጋ: https://c5.exam.et • ማያ ከተማ: https://c5.exam.et • መቱ ከተማ: https://c5.exam.et • ሞጆ ከተማ: https://c5.exam.et • ሞያሌ ከተማ: https://c5.exam.et • ነጆ ከተማ: https://c5.exam.et • ነቀምት ከተማ: https://c5.exam.et • ሮቤ ከተማ አስተዳደር: https://c5.exam.et • ሰንዳፋ በኬ: https://c5.exam.et • ሻኪሶ ከተማ: https://c5.exam.et • ሻሸመኔ ከተማ: https://c5.exam.et • ሸገር ከተማ: https://c5.exam.et • ሸኖ ከተማ: https://c5.exam.et • ምስራቅ ሸዋ: https://c5.exam.et • ሰሜን ሸዋ (ኦሮሚያ): https://c5.exam.et • ደቡብ ምዕራብ ሸዋ: https://c5.exam.et • መዕራብ ሸዋ፡ https://c5.exam.et • ምስራቅ ወለጋ፡ https://c5.exam.et • መዕራብ ወለጋ፡ https://c5.exam.et • መዕራብ ጉጂ፡ https://c5.exam.et • ወሊሶ ከተማ፡ https://c5.exam.et     
Show all...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችል ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ይፋ አድርጓል። በንቅናቄው ተፈታኝ ተማሪዎችን ለፈተና ለማዘጋጀት ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት መርሐግብር በትምህርት ቤቶች ይሰጣል። በማጠናከሪያ ትምህርቱ የተማሪዎችን የመማር ብቃትና የሥነ-ልቦና ዝግጅት ለማሳደግ እንደሚሠራ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ገልፀዋል። ይህን ሥራ አንዳንድ ክልሎች ቀደም ብለው መጀመራቸው የሚያበረታታ ተግባር መሆኑን ጠቅሰዋል። ንቅናቄው ውጤታማ እንዲሆን የክልል ትምህርት ቢሮዎች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በጎ ፈቃደኞች፣ የተቋማት ባለሙያዎች፣ ወዘተ በማሳተፉ እንዲሠሩ ጥሪ አድርገዋል።
Show all...
👍 8 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.