en
Feedback
Bahir dar University Main Registrar

Bahir dar University Main Registrar

Open in Telegram

This is the Bahirdar University Main Registrar Official channel

Show more
India268 234The category is not specified
1 319
Subscribers
+224 hours
+127 days
+2030 days
Posts Archive
በ 2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ ተማሪዎች እንኳን ደስ ያላችሁ እያልን በመንግስት ተቋማት ገብታችሁ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 02/2015 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር የገለጸ በመሆኑ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን የመጀመሪያ ምርጫችሁ እንድታደርጉ እንጠይቃለን፡፡ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በአገሪቱ ካሉ አንጋፋና በመምህራንና በትምህርት ግብዓቶች በሚገባ የተደራጁ ተቋማት አንዱ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲው 115 የቅድመ ምረቃ (የመጀመሪያ ዲግሪ)፣ 200 የማስተርስ ዲግሪና 98 የፒ.ኤች. ዲ (ዶክትሬት ዲግሪ) ፕሮግራሞች ያሉት ተቋም ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲያችን የሕክምና ዶክትሬት ዲግሪን ጨምሮ በተለያዩ የህክምና ዘርፎች፣ በርካታ የኢንጂነሪንግ፣ አርክቴክቸርና የኮምፒተር ሳይንስ አማራጭ ፕሮግራሞች፣ ጂኦሎጂ፣ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ስልጠናዎች፣ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ዘርፍ፣ ሕግ፣ ገቨርናንስ፣ የተፈጥሮና ማህበራዊና ሳይንስ፣ ጋዜጠኝነት፣ የቋንቋ ጥናቶች፣ ትምህርትና ስነ ባሕርይ (ሳይኮሎጂ)፣ ስፖርት ሳይንስ፣ የእንስሳት ሕክምናን ጨምሮ በርካታ የግብርና ሙያ ስልጠናዎች፣ እንዲሁም ዩኒቨርሲቲያችን የሚታወቅባቸው የመሬት አስተዳደርና የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጥናትና ሌሎች በራካታ አማራጮች ያሉት ዩኒቨርሲቲ ነው፡፡ ግቢዎቻችን እጅግ ውብና ማራኪ ናቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በ2022 እ.ኤ.አ. በአለም አቀፍ የዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ አሰጣጥ መሰረት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቀጥሎ በኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ እና በአፍሪካ ደግሞ 66ኛ ደረጃ ላይ ያለ ዩኒቨርሲቲ ነው፡፡ ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ

ዋናውን የትምህርት ማስረጃ ለማሰራት ስትመጡ ማሟላት ያለባችሁ ማስረጃወች 1. Temporary Degree 2. Student Copy 3. Student Copy ያላወጣችሁ አመልካቾች ወጭ መጋራት የከፈላች
ዋናውን የትምህርት ማስረጃ ለማሰራት ስትመጡ ማሟላት ያለባችሁ ማስረጃወች 1. Temporary Degree 2. Student Copy 3. Student Copy ያላወጣችሁ አመልካቾች ወጭ መጋራት የከፈላችሁበትን ደብዳቤ እና ደረሰኝ ይዛችሁ መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡