cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኦርቶዶክሳዊ ፕሮፋይሎች

ንዒ ርግብየ(21) ልጄ ሆይ እንዳትሆን#መናፍቅ ታሪክህና ሀይማኖትህን እወቅ በዚህ ቻናል ውስጥ የምታገኙት *የቅዱሳን ስዕሎች *ኦርቶዶክሳዊ የስልክ ጥሪዎች *የንግስ በዐል ጥሪዎች *መንፈሳዊና የንግስ ጉዞዎች *መዝሙሮች *ሀይማኖታዊ ቪዲዮዎች #ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲያጋሩ በልዑል እግዚአብሔር ስም ጥሪዬን አስተላልፋለሁ @kidanamhrat ማርያምን ዝም ብላችሁ join በሉ

Show more
Advertising posts
295
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ቅድስት ስላሴ @kidanemeherte
Show all...
2
✞#ታኅሣሥ_፮✞ ✞#ቅድስት_አርሴማ_ድንግል✞ ✞✞✞✞✞✞ https://t.me/kdusan_melaekt        ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   
Show all...
🙏 1
#ታኅሣሥ_፮✞ ✞ቅድስት አርሴማ ድንግል✞ =>እናታችን ቅድስት አርሴማን በምን እንመስላታለን? እርሷ በአድማስ ላይ ተቀምጦ እንደሚያበራ እንቁ ናትና ክብሯ ብዙ ነው:: መድኃኒታችን ክርስቶስ በወንጌል እንዳለው "በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትምና" (ማቴ. 5:11) የሰማዕቷ ሕይወት በፊታችን እንደ ብርሃን ተገልጦ ይታያል:: *ቅድስት አርሴማ እንደ ልጅ ወላጆቿን በመታዘዝ ደስ ያሰኘች ቡርክት ናት:: *ቅድስት አርሴማ ይሕ ቀረሽ የማይሏት ውብ ናት:: *ቅድስት አርሴማ ድንግል ናት:: *ቅድስት አርሴማ ባሕታዊት ጻድቅ ናት:: *ቅድስት አርሴማ ኃያል ሰማዕት ናት:: ¤ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ: +አበው በትውፊት እንደ ነገሩን ከሆነ ቅዱሱ ጐርጐርዮስ የታላቁዋ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ትልቅ ወንድም ነው:: በዜና ሰማዕታት ተጽፎ እንደሚገኘው በዚያ የመከራ ዘመን ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሦስት ኃላፊነቶች ነበሩበት:- 1.ቅድስት አርሴማን ጨምሮ ደናግሉን ማጽናት 2.ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ ማጥናት 3.የሚመጣውን መከራ ለመቀበል ራሱን ማዘጋጀት:: +ቅዱሱ 3ቱንም ኃላፊነቶች በሚገባ በመወጣቱ ከራሱ አልፎ ለሌሎቹ አርአያ መሆን ቻለ:: ያቺን ንጽሕት አርበኛ ቅድስት አርሴማንም አጽንቶ የደናግሉ መሪ አደረጋት:: መከራው ገፍቶ እስከ መጣበት ጊዜ በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ሆነው ይጸልዩ: ይጾሙ: ገዳማዊ ሥራንም ይሠሩ ነበር:: +ለዚህም ነው ቅድስት አርሴማና ቅዱስ ጐርጐርዮስ ጻድቃን የምንላቸው:: በሁዋላ ግን ማሕደረ ሰይጣን ዲዮቅልጢያኖስ በመልኩዋ ተማርኮ ቅድስት አርሴማን ካላገባሁ በማለቱ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ድንግሏን አርሴማን ጨምሮ ክርስቲያኖችን ይዞ ወደ አርማንያ ተሰደደ:: +በአርማንያም በአንድ ገዳም ውስጥ ተደብቀው በጾምና በጸሎት ለጥቂት ጊዜ ቆዩ:: ነገር ግን ረሃብ ፈጃቸው:: የሚላስ የሚቀመስ ነገር በአካባቢው ባለ መኖሩ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ወደ ከተማ ለመውጣት ተገደደ:: +በዚያም በድርጣድስ ቤተ መንግስት ውስጥ ባርነት ተቀጠረ:: በሚያገኛት ገንዘብም ወገኖቹን ይረዳ ነበር:: መከራው ግን አለቀቃቸውም:: ርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ቅዱሳኑ ወደ አርማንያ መሔዳቸውን ስለ ሰማ ይዞ እንዲልክለት ድርጣድስን ላከው:: +ድርጣድስ ግን ቅድስት አርሴማን ባያት ጊዜ ከውበቷ የተነሳ መታገስ ባለመቻሉ "ካላገባሁሽ" አላት:: ድንግሊቱ ግን "እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ: አይሆንም" አለችው:: ሊያስፈራራት ሞከረ:: ዐይኗ እያየ ደናግሉን ጨፈጨፋቸው:: +አልሳካልህ ቢለው በአደባባይ በግድ ሊያገባት ቢሞክር እጁን ጠምዝዛ በሰው ሁሉ ፊት መሬት ላይ ጣለችው:: እጅግ ስላፈረ አስገረፋት: አሰቃያት: ዐይኗንም አወጣ:: በመጨረሻም አንገቷን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት:: +ከነገር ሁሉ በሁዋላ ድርጣድስና ባለሟሎቹ ለአደን በሔዱበት ርኩስ መንፈስ ወደ አውሬነት (እሪያነት) ቀየራቸው:: +የንጉሡ እንስሳ (አውሬ) መሆን በአርማንያ ታላቅ ድንጋጤን ፈጠረ:: የንጉሡ እህት ስታለቅስ በራዕይ "ለእመ ኢያዕረግምዎ ለጐርጐርዮስ አልብክሙ ድኂን-ጐርጐርዮስን ከተቀበረበት ካላወጣችሁት አትድኑም" አላቸው:: ወዲያውም ቆፍረው አወጡት:: +ቅዱሱ እንደ ወጣ ዕረፍትን አልፈለገም:: ለ15 ዓመታት ቀባሪ አጥቶ የተበተነውን የቅድስት አርሴማንና የሰማዕታቱን አጽም ሰብስቦ በክብር አኖረው:: ድርጣድስና ባለሟሎቹንም ወደ በርሃ ሒዶ ፈወሳቸው:: +የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ አጽም በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ከሌሎች ሰማዕታት አጽም ጋር ኢትዮዽያ እንደ መጣ አባቶቻችን በትውፊት ነግረውናል:: ለዚህም ይመስላል ቡርክቷ እናታችን ከሌሎች ሃገራት ለይታ ለኢትዮዽያውያን ልዩ ፍቅር ያላት:: በዋናው ገዳሟ (ወሎ /ኩላማሶ/ : ስባ : ውስጥ የሚገኝ ነው) ጨምሮ ስሟ በተራበት ሁሉ ኃይልን ታደርጋለችና:: +ነገር ግን ወንድሞቼና እሕቶቼ በቅድስቷ እናታችን ስም የሚነግዱ ሥጋውያን ሰዎች በዝተዋልና እንጠንቀቅ:: የሰማዕቷ ክብር ብዙ ነውና በሕልም ላይ ብቻ አንታመን:: አባ እንጦንስ እንዳሉት "በሕልሙ የሚታመን ሰው ከንቱ ነውና::" (መዝ. 75:5) +በዚህ ዕለት ከሰማዕቷ ጋር የመንፈስ እናቷን ቅድስት አጋታን ልናስባት ይገባናል:: ይህች እናት እመ-ምኔት ስትሆን ቅድስት አርሴማን ታስተምራት: ታጸናት: ከጐኗም ትቆምላት ነበር:: ረሃቧን: ጥሟን: ስደቷን: መከራዋንም ሁሉ አብራት ተሳትፋለች:: በፍጻሜውም አብራት ተሰይፋለች:: +ይህች ዕለት ለቅድስት አርሴማና ለተከታዮቿ ሰማዕታት የፍሰትና የቅዳሴ ቤት መታሰቢያ ናት:: ✞✞✞✞✞✞ https://t.me/kdusan_melaekt        ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   
Show all...
ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

#ቅዱሳን_መላዕክት እንኳን ወደ ቅዱሳን መላዕክት መንፈሳዊ ቻናል በደህና መጡ። ማህበሩ ምዕመናን ባሉበት ሆነው በየዕለቱ መንፈሳዊ ትምህርቶች እና ዝማሬዎች እንዲደርሳቸው ይጥራል ፤ የቅዱሳን በዓላት እና ወቅታዊ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጉዳዮችን ይዳስሳል፤ መረጃዎችን እና ጥቆማዎችን ወደእናንተ ያደርሳል። እርሶም ይህን መንፈሳዊ ቻናል ይቀላቀሉ ዘንድ ተጋብዘዋል! ግሩፕ:- @zmare_melaekt

#በዓታ_ለእግዝእትነ_ማርያም https://t.me/kdusan_melaekt        ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   
Show all...
#በዓታ_ለእግዝእትነ_ማርያም ††† ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ (አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር:: ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች "ልጅ የላችሁም" በሚል ይናቁ ነበር:: ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ:: እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም:: የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው:: አንድ ቀን እርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች:: "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን ሳይቀር በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች:: ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ:: ለ40 ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ:: በ40ኛው ቀን ሁለቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- *ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጀሮ ገብታ: በማሕጸኗ ስትደርስ አየ:: እርሷ ደግሞ:- *የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለ7 ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ:: በ7ኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው:: እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ:: እንደ ሥርዓቱም አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች:: "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ . . . ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ:: (ቅዳሴ ማርያም) ††† "ለጽንሰትኪ በከርሥ:: እንበለ አበሳ ወርኩስ:: ወለልደትኪ እማሕጸን ቅዱስ . . ." "ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማሕጸንም ቅዱስ ነው . . ." (መጽሐፈ ሰዓታት፣ ኢሳ. 1:9) "ኢያቄም ወሐና ወለዱ ለነ ሰማየ:: ሰማዮሙኒ አስረቀት ለነ ፀሐየ::" "ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱልን:: ሰማያቸው ደግሞ ፀሐይን አወጣችልን (ወለደች-አስገኘችልን)" የዓለማችን ወላጆች ነቢያት ሐዋርያትን: ጻድቃን ሰማዕታትን ወልደው ከብረዋል: ተመስግነዋል:: ኢያቄምና ሐና ግን ፍጥረት ሁሉ በአንድነት ቢሰበሰብ በእግሯ የረገጠችውን ትቢያ እንኳ መሆን የማይችል: የሰማይና የምድር ንግሥት: የእግዚአብሔርን እናት: እመቤታችን ማርያምን ወለዱልን:: ኢያቄም ወሐና ለእግዚአብሔር የሥጋዌ አያቶቹም ተባሉ:: ቅዱሳኑ እስኪያረጁ ድረስ በመካንነት አዝነው ፀልየዋል:: ንጽሕናቸውና ደግነታቸው ተመስክሮላቸው ድንግል ማርያምን አግኝተዋል:: እመቤታችን ነሐሴ 7 ቀን ተጸንሳ ግንቦት አንድ ቀን ተወልዳለች:: ከአዳም ስሕተት በኋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተወለደች የመጀመሪያዋ ሰው ድንግል ማርያም ሆናለች:: (ኢሳ. 1:9) ††† የእመቤታችን የዘር ሐረግ:- *አዳም-ኖኅ-አብርሃም-ይስሐቅ-ያዕቆብ= *በእናቷ:- ሌዊ-ቀዓት-እንበረም-አሮን-ቴክታና በጥሪቃ-ሔኤሜን-ዴርዴን-ቶና-ሲካር-ሔርሜላና ማጣት-ሐና:: *በአባቷ በኩል:- ይሁዳ-ፋሬስ-ሰልሞን-ቦኤዝ-እሴይ-ዳዊት-ሰሎሞን-ሕዝቅያስ-ዘሩባቤል-አልዓዛር-ቅስራ-ኢያቄም ይሆናል:: ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም: በሊባኖስ ተራራ ከ2,023 ዓመታት በፊት ተወልዳለች:: ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ድንግል እመ ብርሃንን ከወለዱ በኋላ ለ3 ዓመታት እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ: ነዳያንንም ሲጠግኑ ኖሩ:: በእነዚህ ዓመታትም ቅድስት ሐና ድንግል ማርያምን ከእቅፏ አውርዳት አታውቅም:: ቅዱሳን መላእክትም ዘወትር እየመጡ ያጫውቷት ይንከባከቧትም ነበር:: 3 ዓመት በሞላት ጊዜም በቅድስት ሐና አሳሳቢነት ብጽዓታቸውን (ስዕለታቸውን) ይፈጽሙ ዘንድ ተዘጋጁ:: እንደ ሥርዓቱ የሚዘጋጀውን (መባውን) ይዘው ወደ ቤተ መቅደስ ሲደርሱ አበው ካህናትና የመቅደሱ አገልጋዮች ሁሉ ሊቀበሏቸው ወጡ:: ሕዝቡ: ሊቃነ ካህናት ቅዱሳን ዘካርያስና ስምዖን: ኢያቄም ወሐና ከድንግል ማርያም ጋር ቆመው ሳሉም ሊቀ መላእክት ፋኑኤል ከሰማይ ወርዶ ረቦ ታየ:: ከቅዱስ ዘካርያስ ጀምሮ ሁሉም ሰው ሕብስትና ጽዋዑን ለመቀበል ቀረበ:: ግን መልአኩ ራቀ:: ድንግል ማርያም በቀረበች ጊዜ ግን ከመሬት አፈፍ አድርጐ አንስቶ: ክንፉን ጋርዶ ሰማያዊውን ማዕድ መገባት:: በዚህ ደስ የተሰኙ ካህናትና ሕዝቡ እየዘመሩ በታኅሣሥ ሦስት ቀን ወደ ቤተ መቅደስ አስገብተዋታል:: አማናዊት መቅደሰ መለኮት ድንግል ማርያም ወደ ኦሪቱ ቤተ መቅደስ በገባችበት ዕለት ጸሎታችን እንድትሰማን እንደ ሊቃውንቱ:- "ማርያም አንቲ ሰዋስው ዘምድረ ሎዛ:: ዲቤኪ ትዕርግ ጸሎትየ ከመ ጼና ሠናይ መዓዛ:: ኀበ ለነፍስየ ታሰስል ትካዛ" እንላለን:: (አርኬ) https://t.me/kdusan_melaekt        ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   
Show all...
ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

#ቅዱሳን_መላዕክት እንኳን ወደ ቅዱሳን መላዕክት መንፈሳዊ ቻናል በደህና መጡ። ማህበሩ ምዕመናን ባሉበት ሆነው በየዕለቱ መንፈሳዊ ትምህርቶች እና ዝማሬዎች እንዲደርሳቸው ይጥራል ፤ የቅዱሳን በዓላት እና ወቅታዊ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጉዳዮችን ይዳስሳል፤ መረጃዎችን እና ጥቆማዎችን ወደእናንተ ያደርሳል። እርሶም ይህን መንፈሳዊ ቻናል ይቀላቀሉ ዘንድ ተጋብዘዋል! ግሩፕ:- @zmare_melaekt

#ሃያ_አራቱ_ካህናተ_ሰማይ እንኳን ለ24ቱ ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ እና ቅዱስ አዝቂር ሰማዕት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥራቸው በነገድ መቶ (100): በክፍለ ነገድ አሥር (10) አድርጓቸዋል:: አቀማመጣቸውንም በሦስት ሰማያትና በ10 ከተሞች (ዓለማት) አድርጓል:: ††† መላእክት ያሉባቸው ከተሞች ከታች ወደ ላይ "ኤረር: ራማና ኢዮር" ይባላሉ:: አሥሩ ክፍለ ነገድ ደግሞ ከነ አለቆቻቸው ይህንን ይመስላሉ:- 1."አጋእዝት" (የቀድሞ አለቃቸው ሳጥናኤል: አሁን የተረፉት በቅዱስ ሚካኤል ሥር ናቸው) 2."ኪሩቤል" (አለቃቸው ኪሩብ) 3."ሱራፌል" (አለቃቸው ሱራፊ) 4."ኃይላት" (አለቃቸው ሚካኤል) 5."አርባብ" (አለቃቸው ገብርኤል) 6."መናብርት" (አለቃቸው ሩፋኤል) 7."ስልጣናት" (አለቃቸው ሱርያል) 8."መኳንንት" (አለቃቸው ሰዳካኤል) 9."ሊቃናት" (አለቃቸው ሰላታኤል) 10."መላእክት" (አለቃቸው አናንኤል) ናቸው:: ††† ከእነዚህም:- *አጋእዝት: *ኪሩቤል *ሱራፌልና *ኃይላት መኖሪያቸው በኢዮር (በ3ኛው ሰማይ) ነው:: *አርባብ: *መናብርትና *ስልጣናት ቤታቸው ራማ (2ኛው ሰማይ) ነው:: *መኳንንት: *ሊቃናትና *መላእክት ደግሞ የሚኖሩት በኤረር (በ1ኛው) ሰማይ ነው:: መላእክት ተፈጥሯቸው እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ ነው:: አይራቡም: አይጠሙም: አይዋለዱም: አይሞቱም:: ተፈጥሯቸውም ረቂቅ ነው:: ተግባራቸውም ዘወትር "ቅዱስ: ቅዱስ: ቅዱስ" እያሉ ፈጣሪያቸውን ማመስገን ነው:: ምግባቸውም ይሔው ነው:: ዕረፍት ብሎ ነገርን አያውቁም:: "አኮቴቶሙ ዕረፍቶሙ: ወዕረፍቶሙ አኮቴቶሙ" እንዲል:: በተጨማሪም መልአክ ማለት ተላላኪ (አገልጋይ) ነውና ከፈጣሪ ወደ ሰው ልጆች ለምሕረትም: ለመዓትም ይላካሉ:: ምሕረትን ያወርዳሉ:: ልመናን ያሳርጋሉ:: ቅጡ ሲባሉም ይቀጣሉ:: ስነ ፍጥረት (አራቱ ወቅቶች) እንዳይዛቡ ይጠብቃሉ:: *ዘወትርም ስለ ሰው ልጆች ያማልዳሉ:: (ዘካ. 1:12) *ምሥጢርን ይገልጣሉ:: (ዳን. 9:21) *ይረዳሉ:: (ኢያ. 5:13) *እንዳንሰናከል ይጠብቃሉ:: (መዝ. 90:11) *ያድናሉ:: (መዝ. 33:7) *ስግደት ይገባቸዋል:: (መሳ. 13:20, ኢያ. 5:13, ራዕ. 22:8) *በፍርድ ቀንም ኃጥአንን ከጻድቃን ይለያሉ:: (ማቴ. 25:31) *በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ሕይወትና ድኅነት ሲባል ከፈጣሪያቸው የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ሲጠብቁና ፈቃዱን ሲፈጽሙ ይኖራሉ:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚህች ዕለት የሃያ አራቱን ቅዱሳን ካህናተ ሰማይን መታሰቢያ ታደርጋለች:: እኒህ ቅዱሳን መላእክት በነገድ 10 ሲሆኑ መጠሪያቸው "ሱራፌል" : መኖሪያቸውም በኢዮር ነው:: ነገር ግን ሃያ አራቱ አለቆቻቸው ተመርጠው በመሪያቸው በቅዱስ ሱራፊ አለቅነት በጽርሐ አርያም ያገለግላሉ:: በቀናች ሃይማኖት ትምሕርት ሁሉም ቅዱሳን መላእክት ለእግዚአብሔር ቅርብ ቢሆኑም: በነጠላ የቅዱስ ሚካኤልን ያህል: በነገድ ደግሞ የኪሩቤል (አራቱ እንስሳ) እና የሱራፌልን (ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ) ያህል ቅርብ የለም:: ††† ሃያ አራቱ ቅዱሳን ካህናት ሥራቸው:- 1.እንደ ሞገድ ከአንደበታቸው ምስጋና እየወጣ: ጧት ማታ ፈጣሪያቸውን ይቀድሱታል:: (ኢሳ. 6:1, ራዕይ 4:11, 5:11) 2.የሥላሴን መንበር ያለ ማቋረጥ ያጥናሉ:: (ራዕይ 5:8) 3.የሰው ልጆችን: በተለይም የቅዱሳንን ጸሎት በማዕጠንታቸው ያሳርጋሉ:: (ራዕይ 8:3) 4.የረከሱትን ይቀድሳሉ:: (ኢሳ. 6:6) 5.ዘወትርም ለሰው ልጆች ምሕረትን ሲለምኑ ይኖራሉ:: (ዘካ. 1:12) ስለ እነዚህ ቅዱሳን ካህናት (ሱራፌል) ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ብዙ ይላል:: ለምሳሌ:- ዐቢይ ነቢይ ወልዑለ ቃል ኢሳይያስ ፈጣሪው ተቀይሞት በነበረበትና ዖዝያን በሞተበት ወራት: ግሩማን ሆነው ሥላሴን "ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ" እያሉ ዙሪያውን ከበው ሲያመሰግኑ ሰምቷል:: ከእነርሱም አንዱ (ሱራፊ) መጥቶ በጉጠት እሳት ከንፈሩን ዳስሶ ከለምጹ አንጽቶታል:: (ኢሳ. 6:1) አቡቀለምሲስ የተባለ ቅዱስ ዮሐንስም በራዕዩ በግርማ: በአምሳለ አረጋዊ ተመልክቷቸዋል:: (ራዕይ 4:4) አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን የመሰሉ ቅዱሳን ሊቃውንት ደግሞ በጣዕመ ምስጋናቸው ሲገልጿቸው:- "ካህናተ ሰማይ ቅውማን በዐውዱ:: አክሊላቲሆሙ ያወርዱ:: ቅድመ መንበሩ እንዘ ይሰግዱ:: ይርዕዱ:: ከመ ኢይዝብጦሙ ሶበ ይበርቅ ነዱ::" ብለዋል:: (መጽሐፈ ሰዓታት) ትርጉሙም "በፈጣሪ መንበር ዙሪያ የሚቆሙ የሰማይ ካህናት አክሊለ ክብራቸውን አውርደው በመንበሩ ፊት ይሰግዳሉ:: መብረቀ መለኮቱ በተገለጠ ጊዜም በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ::" ነው:: ግሩም ባሕርየ ሥላሴን ሊቋቋመው የሚችል ፍጡር የለምና:: ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ በምስጋናቸው: በማዕጠንታቸውና በምልጃቸው ክቡራን ናቸውና ዘወትር ልናከብራቸው ይገባናል:: የረከሰ ማንነታችንን ይቀድሱ ዘንድ: በምልጃቸውም ዘንድ እንድንታሰብ: ጸሎታችንንም ያሳርጉልን ዘንድ እንለምናቸው:: ††† ኅዳር 24 ቀን ዓመታዊ በዓላቸው ነው ማለት በየወሩ በ24 ወርኀዊ በዓላቸው መሆኑን ያሳያልና ዘወትር ልናስባቸው ይገባል:: በተለይ ያዘነን ልብ ደስ ያሰኛሉና እንደ ሊቃውንት እንዲህ ብለን እንጠራቸዋለን:: "ሰላም ለክሙ ካህናተ ሕጉ ወትዕዛዙ:: ለእግዚአብሔር ቃል ዘጶዴሬ ሥጋ አራዙ:: እምነቅዐ አፉክሙ ሐሴት ዘኢይነጽፍ ዉሒዙ:: ኪያየ ኅዙነ ወትኩዘ ልብ ናዝዙ:: ወበክንፍክሙ ብርሃናዊ ዐውድየ ሐውዙ::" (አርኬ ዘኅዳር 24) ††† ቅዱስ አዝቂር ካህን ††† ††† ከዜና ካህናት ወደ ዜና ካህናት እንለፍ:: ቅዱስ አዝቂርን የመሰሉ ካህናት ምንም ሥጋ ለባሽ ቢሆኑም ሥልጣናቸውና ግብራቸው ሰማያዊ ነውና መላእክትን ይመስላሉ:: አንድም በስልጣናቸው ከመላእክት ይበልጣሉ:: "ካህናትየ ይቤሎሙ:: ወእምኩሉ ፈድፋደ አክበሮሙ:: ዘኢተገብረ ለመላእክት ተገብረ ለካህናት::" ትርጉም "አገልጋዮቼ አላቸው:: ከሁሉ በላይ አከበራቸው:: ለመላእክት ያልተደረገ ለካህናት ተደረገ::" እንዳለ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ:: (መጽሐፈ ቅዳሴ) ቅዱስ አዝቂርም የናግራን (አሁን የመን) ክርስቲያን ሲሆን በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በንጹሕ የክህነት አገልግሎቱ ሰውንም: ክርስቶስንም ደስ ያሰኘ አባት ነው:: አሕዛብን: አረማውያንን ሁሉ ድል ነስቶ መንጋውን ጠብቋል:: በቁጥርም አብዝቷል:: ገርፈው ቢያስሩት በቃሉ ስልጣን የብረት በሮችን ከፍቶ አሕዛብን ሲያጠምቅ ተገኝቷል:: ሊገድሉት ሲወስዱት በየመንገዱ ይሰብክ ነበር:: ገዳዮቹ በርሃ ላይ ውኃ ጥም እንዳይገድላቸውም በአንዲት ገበታ ላይ ዝናም አዝንሞ 700 ወታደሮች ከነ ፈረሶቻቸው አጥግቧል:: በመጨረሻም አይሁድ በድንጋይ ሲወግሩት ድንጋዮቹ እየተመለሱ አናት አናታቸውን ብሏቸዋል:: ያን ጊዜ በብስጭት አንገቱን ቆርጠውታል:: አብረውም ቅዱስ ኪርያቅ ወዳጁንና 48 ተከታዮቹን ሰይፈዋል:: ††† አምላከ ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ ከምስጋናቸው ሐሴትን: ከማዕጠንታቸው በጐ መዓዛን ያውርድልን:: በረከታቸውንም ያብዛልን:: https://t.me/kdusan_melaekt        ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   
Show all...
ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

#ቅዱሳን_መላዕክት እንኳን ወደ ቅዱሳን መላዕክት መንፈሳዊ ቻናል በደህና መጡ። ማህበሩ ምዕመናን ባሉበት ሆነው በየዕለቱ መንፈሳዊ ትምህርቶች እና ዝማሬዎች እንዲደርሳቸው ይጥራል ፤ የቅዱሳን በዓላት እና ወቅታዊ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጉዳዮችን ይዳስሳል፤ መረጃዎችን እና ጥቆማዎችን ወደእናንተ ያደርሳል። እርሶም ይህን መንፈሳዊ ቻናል ይቀላቀሉ ዘንድ ተጋብዘዋል! ግሩፕ:- @zmare_melaekt

#ሃያ_አራቱ_ካህናተ_ሠማያት https://t.me/kdusan_melaekt        ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   
Show all...
ላልተመለሰው ፀሎትህ አመስግን! ለዛሬ መድረስ ቀላል አይደለም! ሀብታም ወይ ደሀ ስለሆንክ አይደለም ይሄ ቀን የተጨመረልህ፤ ጎበዝ ወይ ሰነፍ ስለሆንክ አይደለም፤ ዕድለኛ ስለሆንክ ብቻ ነው ለዛሬ የደረስከው! ዛሬ ያንተ ቀን ነው፤ ያንተ ባይሆንማ ትንፋሽህ ተቋርጦ ይሄን ፅሁፍ እንኳን ማንበብ አትችልም ነበር። ለማመስገን የምትፈልገው ሁሉ እስኪሟላ አጠብቅ፤ ወዳጄ እንደውም ላልተመለሰው ፀሎትህ ሳይቀር አመስግን! እስትንፋስ ያለው ሁሉ ፈጣሪውን ያመስግን! የምስጋና ምሽት ይሁንላችሁ🙏 https://t.me/kdusan_melaekt        ❍ㅤ         ⎙          ⌲         ♡   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ      ˡᶦᵏᵉ   
Show all...
ቅዱሳን መላዕክት Kdusan melaekt

#ቅዱሳን_መላዕክት እንኳን ወደ ቅዱሳን መላዕክት መንፈሳዊ ቻናል በደህና መጡ። ማህበሩ ምዕመናን ባሉበት ሆነው በየዕለቱ መንፈሳዊ ትምህርቶች እና ዝማሬዎች እንዲደርሳቸው ይጥራል ፤ የቅዱሳን በዓላት እና ወቅታዊ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጉዳዮችን ይዳስሳል፤ መረጃዎችን እና ጥቆማዎችን ወደእናንተ ያደርሳል። እርሶም ይህን መንፈሳዊ ቻናል ይቀላቀሉ ዘንድ ተጋብዘዋል! ግሩፕ:- @zmare_melaekt