cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ahmed Habib Alzarkawi

Hello World

Show more
Advertising posts
21 084
Subscribers
-424 hours
-347 days
-25930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ዱባይ የተፈጠረውን ጉድ ሰማችሁ....🇦🇪 🤔 ባለፉት ጥቂት ቀናት ዱባይ ላይ ከፍተኛ ውድመትና ኪሳራ ያደረሰው ንፋስ የቀላቀለው ዝናብ ተፈጥሯዊ ዝናብ ሳይሆን አቧዋራው በራሱ ጊዜ ተነስቶ sand storm በበረሃማ አካባቢዎች ብዙ ግዜ ይከሰታል አጋጣሚ ሆኖ ይህ ንፋስ ልክ እነሱ ደመና ላይ ርጭት ሲጀምሩ ንፋሱም ተነሳ ሁለቱ ሲገናኙ በጣም አደገኛ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ ሀገሪቱን አደጋ ላይ ጥሏታል እናም (Cloud Seeding Technology) በመጠቀም በራሳቸው ላይ የፈጠሩት ችግር ነው አላህ ይጠብቀን ከተፈጥሮ ጋር መሟገት በጥንቃቄ ማየትን ይፈልጋል አላህ ይድርስላቸው። Ahmed Habib Alzarkawi
Show all...
👍 58 2
በተፈራው መሰረት ኢራን በእስራኤል ላይ ከፍተኛ የሆነ የሚሳኤልና የአጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች ጥቃት ከፍታለች ። ቀይ ባህርና ሜድትራኒያን ቀጠና ውጥረት ውስጥ ገብቷል ። በቀጥታ ስርጭቶች እየታየ እንዳለው እስራኤል እንዲሁም አጋሮቿ እንግሊዝና አሜሪካ የኢራንን ጥቃት ሙሉ በሙሉ ኢላማቸውን ከመምታት እንዲከሽፉ መከላከል እየተቻላቸው አይደለም ። ጆ ባይደን ኢራን ላይ ያለንን ጦር መሳሪያ በሙሉ እንጠቀማለን ሲሉ የዛቱ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ ዓለም ለኒውክሌር ጦርነት ከምንግዜውም በላይ ቀርባለች ሲሉ ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች እየዘገቡ ይገኛሉ።
Show all...
👍 76🙏 6🏆 5🆒 2 1
እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ። አደረሰን። የሀዘኖቻችን ሁሉ ማብቂያ ፣የስኬቶቻችን ሁሉ መጀመሪያ ፣የፍላጎቶቻችን ሁሉ ማግኛ ፣ የደስታዎቻችን መዘውተሪያ ኢድ አላህ ያድርግልን !!!ኢድ ሙባረክ!
Show all...
👍 43 8🙏 6
😭😭😭
Show all...
👍 41🕊 8
ፆመኛ በባዶ ሆድ እጁ ላይ ሙስበሃ ብቻ የያዘ ንፁሃን መግደል ጀግንነት የሚመስላቸው ሰው መሳይ አውሬዎች 😭😭 ለሻሂዶች አላህ ጀነተል ፊርደውስ ይወፍቃቸው 🤲🤲
Show all...
👍 65
በአሜሪካ በብዙ ግዛቶች እንዲሁም በፖርቹጋል ሙሉ የፀሃይ ግርዶሽ (Full solar eclipse) ተከስቷል። ይህ ክስተት የሚከሰተው ጨረቃ ፀሀይን ሙሉ ለሙሉ ስትሸፍናት ነው።
Show all...
👍 28 1🙏 1
አላህ ሱ.ወ ሁላችን ፆምን ከሚቀበላቸው ሌይለቱል ቀድር ከሚወፍቃቸው ያድርገን ዱዓ ዚክር በማድረግ ቁርአን በመቅራት ላይ እንበርታ ..🙏
Show all...
🙏 64👍 31 16😁 2
ቀይ መስመር!!! ''አብሱማ'' በሚል ርዕስ የተሰራው በአፋር ባህል አኗኗር ዙሪያ የሚያጠነጥነው ይህ የፍቅር ፊልም ገና በማስታወቅያው የአፋርን ባህል እምነት የማይወክሉ ድርጊቶች እና ብዙ ጋጠወጥና የጥላቻ ቃላቶች ተጠቅመዋል። ይህ ፊልም የአፋር ህዝብን እንደህዝብ የሚያጠለሽና የአፋርን ህዝብ ባህል እምነትና እሴትን ጥላሸት የሚቀባ በመሆኑ በአስቸኳይ የሚመለከታቸው አካላቶች ፊልምሙን ሊያስቆሙ ይገባል። የማይሆን ከሆነ ጉዳዩን ወደ ህግ እንወስደዋለን።
Show all...
👏 58👍 50 11
“ሙሽራ መስሎ ወጥቶ ቀረብኝ…” ለእናት የልጅን መርዶ መስማት ምን ያህል ከባድ እንደሆነ መገመት አይከብድም። በቅጽበት ምን እንደሚፈጠር በማይታወቅበት ጦርነት ውስጥም ቢሆን ልጅን ማጣት የሚያደርሰው የልብ ስብራት በቀላሉ አይሽርም። እኝህ በእስራኤል የቦምብ ጥቃት ልጃቸውን ያጡ ፍልስጤማዊ እናትም “ማታ አብረን ራት በልተናል፤ ጠዋት ሲወጣም እንደ ሙሸራ አምሮበት ነበር” እያሉ በመብሰክሰክ ሀዘኑ መሪር ሆኖባቸዋል። እስራኤል ባለፉት 24 ስአታት በጋዛ በፈጸምችው ጥቃት በጥቂቱ 76 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁም አለማቀፉ ጫና ከ32 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወት የቀጠፈውን ጦርነት እንደማያስቆመው ነው የተናገሩት። አል ዐይን
Show all...
👍 28 5🥰 4🕊 4
ተይዟል!! ከሚሌ -- አዳይቱ ከሚሌ--ኤልዉሃ ከሚሌ --ጭፍራ በሚወስዱ መንገዶች ጨለማን ተገን በማድረግ በጦር መሳሪያ የታገዘ ዝርፊያ ሲያካሄድ የነበረው ዘራፊ/ሽፍታ በሚሌ ወረዳ ፖሊሶች ክትትል ከሌሊቱ 7:00 ሰአት ዝርፊያ እየፈፀመ እጅ ከፍንጅ ተይዞ በቁጥጥር ስር ውልዋል። ይሄ ዘራፊ በነዚህ መንገዶች ተሽከርካሪዎችን በጦር መሳሪያ በማስፈራራት እየዘረፈ ሲያስቸግር የነበረ ሌባ ነው። በቀጣይ ክትትሉ ተጠናክሮ ዘራፊዎችን ለህግ የማቅረብ ስራ እንደሚሰራ የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር Bilae Acmad አያይዘው ተናግረዋል። Ahmed Habib Alzarkawi
Show all...
🙏 57👍 48 8🥰 1