cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የተዋህዶ መዝሙሮች ✝✝✝

የኢትዮጵያ የሆነችዉ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮቿ እና አስተማሪ አጫጭር የስብከት ቪዲዬ ከፈለጉ ይህንን ቻናል ይቀላቀሉ

Show more
Advertising posts
1 254
Subscribers
+524 hours
+47 days
-430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

"ሰላምሽ ዛሬ ነው" ሰላምሽ ዛሬ ነው ኢየሩሳሌም ወደ አንቺ መጥቷልና አምላክ ዘለዓለም/፪/ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ዘመሩ ሕፃናት በኢየሩሳሌም አንቺ ቤተልሔም የዳዊት ከተማ የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ/፪/      አዝ ሆሣዕና እያሉ አመሰገኑት በኢየሩሳሌም አእሩግ ወሕፃናት/፪/   አዝ ኪሩቤል መንበሩን  የሚሸከሙት መስቀል ተሸክሞ ሆነን መድኃኒት/፪/   አዝ የኢየሱስን ሕማም ደናግል አይተው እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው/፪/     በማኅበረ ቅዱሳን መዘምራን https://t.me/orthodox_mezmur_1 https://t.me/orthodox_mezmur_1
Show all...
የተዋህዶ መዝሙሮች ✝✝✝

የኢትዮጵያ የሆነችዉ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮቿ እና አስተማሪ አጫጭር የስብከት ቪዲዬ ከፈለጉ ይህንን ቻናል ይቀላቀሉ

👍 7
#ኒቆዲሞስ (የዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት) ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ በነበረው በኒቆዲሞስ የተሰየመ ሰንበት ነው፡፡ የአይሁድ አለቆች አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን “ምልክት አሳየን” እያሉ ይፈታተኑት ነበር፡፡ ስለሞቱና ትንሣኤው በምሳሌ ቢነግራቸው አልገባቸውም፡፡ ሲያስተምር ብዙዎች ያምኑ ነበር፡፡ ለአይሁድ አለቆች ግን ጭንቅ ነበር፤ የታመሙ ሲፈወሱ ሕጋችን ተሻረ ይሉ ነበር፡፡ በዚህ ሁሉ ተአምራትና ትምህርት የአይሁድ አለቆች ክርስቶስን ለመክሰስ በሚፈልጉበት ወቅት ከአይሁድ አለቆች አንዱ ኒቆዲሞስ በቀን እንዳያደርገው አይሁድን ፈርቶ አንድም ጊዜ አላደርሰው ብሎ እንደ አይሁድ አለቆች ኢየሱስን መቃወሙን ትቶ በሌሊት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ሄደ፡፡ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በነፍስ የታመሙትን በቃሉ በሥጋ የታመሙትን በተአምራቱ ሲፈውስ፤ ኒቆዲሞስ ሰምቶና ተመልክቶ “መምህር ነኝ” ብሎ በመምህርነቱ ሳይኮራ አለቅነቱን መመኪያ ሳያደርግ፡፡ በልቦናው የተሳለውን እውነትን የመፈለግ ስሜት አንግቦ ጌታው መምህሩ ዘንድ በሌሊት ገሠገሠ ዮሐ.3÷1ደርሶም ምስክርነቱን እንዲህ ሲል መስጠት ጀመረ “መምህር ልታስተምር ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን፡፡ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርገውን ተአምራት ሊያደርግ የሚችል የለምና” ዮሐ.9÷24፣ የሐዋ.ሥራ 10÷38 በማለት መመስከር ሲጀምር ጎዶሎን የሚሞላ፡፡ አላዋቂነት በአዋቂነት የሚለውጥ፡፡ ከምድራዊ እውቀት ወደ ሰማያዊ ምስጢር የሚያሸጋግር አምላክ፡፡ “ዳግመኛ ያልተወለደ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማየት አይችልም” ዮሐ.3÷6 ,1ጴጥ.1÷23 በማለት የአይሁድ መምህር ለሆነው ኒቆዲሞስ ቢያስተምረው ስለዳግመኛ መወለድ ከመጽሐፍ ቢያገኘውም ምስጢሩ አልተገለጠለትምና “ሰው ከሸመገለ በኋላ ዳግመኛ መወለድ እንደምን ይቻላል? ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ወደ እናቱ ማኅፀን ተመልሶ መግባት ይችላልን?” በማለት ጥያቄ አቅርቧል፡፡ “እውነት እውነት እልሃለሁ ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ ወደ እግዝአበሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡ ኤፌ.5÷26 ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነውና፡፡ በማለት አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቢያስረዳው ምስጢሩ ከአቅሙ በላይ የሆነበት ኒቆዲሞስ እንደምን ይቻላል? በማለት ጠይቋል፡፡ አበ ብዙኀን አብርሃም ከአምላኩ ሞገስን አግኝቶ፤ የሰዶምና ገሞራ ጥፋት እንዳይደርስ እያማለደ ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገር እንደ ነበረ፤ ኒቆዲሞስም አላዋቂነቱን አምኖ ያልገባውን ምስጢር አምላኩን የመጠየቅ ዕድል በማግኘቱ ሲጠይቅ፣ ኢየሱስ ክርስቶስም “አንተ የእስራኤል መምህራቸው ነህ ግን ይህን ነገር አታውቅምን? በምድር ያለውን ስንነግራቸው ካላመናችሁ በሰማይ ያለውን ብንነግራችሁ እንደምን ታምናላችሁ? ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፡፡ ሙሴ ምድረ በዳ እባቡን እንደ ሰቀለ የሰው ልጅ እንዲሁ ይሰቀላል፡፡ ያመኑበት ሁሉ ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ እንዲኖር እንጂ እንዲጠፉ አይደለም…..” ዮሐ.3÷14፡፡ እያለ ለድኅነተ ዓለም እንደ መጣ ሰው በመብል፣ አምላኩን ከድቶ ልጅነቱን ትቶ ከእግዚአብሔር ቢለይም የሰው ልጅ ያጣውን ልጅነት ለመመለስ ስመ ግብርና ሀብተ ወልድን ለመስጠት መምጣቱን አስረዳው። “ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ፡፡ አመከርከኒ ወኢተረከ በዓመፃ በላዕሌየ፡፡ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመሕያው፡፡ ልቤን ፈተንከው በሌሊትም ጎበኘኸኝ ፈተንከኝም ምንም አላገኘህብኝም፡፡ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው” መዝ.16÷3 እንዳለ ቅዱስ ዳዊት ምስጢረ ሥጋዌን የድኅነት ምስጢር ገልጾለታል፡፡ በሌሊት ከአምላኩ ተምሮ ምስጢሩ የተገለጸለት ኒቆዲሞስ ፍርሃት ርቆለት ቀድሞ በአደባባይ ሄዶ መማርን የፈራ ምስጢሩ ሲገለጽለት አይሁድ በሰቀሉት ዕለት ሳይፈራ ከአርማትያሱ ዮሴፍ ጋር ቅዱስ ሥጋውን ገንዞ ለመቅበር በቃ “ወአልቦ ፍርሃት ውስተ ተፋቅሮትነ፡፡ ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል ማቴ.27÷58፣ 1ዮሐ.4÷18 እንዲል፡፡ ያመነ የተጠመቀ ይድናል፡፡ ያላመነ ያልተጠመቀ ይፈረድበታል ማር.16÷16፡፡ ባለው አማናዊ ቃል ኪዳን መሠረት አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አምላክነቱ አምነን ለመንግሥቱ ዜጋ እንድንሆን ለኒቆዲሞስ ምስጢሩን ጥበቡን የገለጸ አምላክ ለኛም ይግለጽልን፡ #ምስባክ፦ መዝ.16፥3 ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ፡፡ አመከርከኒ ወኢተረክበ ዓመፃ በላዕሌየ፡፡ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመ ሕያው፡፡ ትርጉም፦ በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ልቤንም ፈተንኸው÷ ፈተንኸኝ÷ ዐመፅም አልተገኘብኝም፡፡ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር #ወንጌል፦ ዮሐንስ 3፥1-12 "ከፈሪሳውያንም ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ። መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን አለው።.... #ቅዳሴ - ዘእግዝእትነ ማርያም [ጎሥዐ] ለመቀላቀል👇👇      @https://t.me/orthdoxswallper      @https://t.me/orthdoxswallper      🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊
Show all...
👍 2👌 1
ኒቆዲሞስ ኒቆዲሞስ ኒቆዲሞስ ክቡር ሌቱን በብርሃን የሚማር መምህር በጨለማው ግርማ ኮከብ የደመቀ በመከራው ፅናት ይህን ዓለም ናቀ መምህር ሆኖ ሳለ ከመማር ያልራቀ የትዕቢትን ጅረት በትህትና ተዋርዶ አደረቀ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የአቢ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ አዝ ፍርሃትን በሚጥል ፍፁም ፍቅር ያደረ ከመስቀል አውርዶ ጌታውን ቀበረ የመግነዙን በፍታ በሽቶ አከበረ ከመቅደሱ አንቀፅ ላይረሳ አምድ ሆኖ ታጠረ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የአቢ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ አዝ ለሊትም ለሊት ዕውቀትን ነገረች ህጉን ለሚያስበው ምክር አለኝ እያለች ከጨለማ ሀጢያት ነግታ ብርሃን ከአየች እንደ ኒቆዲሞስ ነፍስህም ተምራ ተመለሰች ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የአቢ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ ለመቀላቀል👇👇      @https://t.me/orthdoxswallper      @https://t.me/orthdoxswallper      🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊
Show all...
👍 6
ብፁዕ አቡነ ማር ማርያም ኢማኑኤል በአገልግሎት ላይ ሳሉ ጥቃት ተፈፀመባቸው "ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።" ~ ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕራፍ ፰: ፴፮ በተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች በሚዘዋወር ስብከታቸው የሚታወቁት ብፁዕ አቡነ ማር ማርያም ኢማኑኤል በአገልግሎት ላይ ሳሉ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ተገለጸ ! በአሦርያውያን ቤተ ክርስቲያን የአውስትራሊያ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ማር ማርያም ኢማኑኤል በተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች በእንግሊዝኛ እና ዐረብኛ ቋንቋዎች በሚያስተላልፉት ስብከት የሚታወቁ ሲሆን በሲድኒ በሚገኝ አንድ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ ሳሉ በአንድ ግለሰብ አማካይነት በስለት መወጋታቸው ተገልጿል። የኒው ሳውዝ ዌልስ ፖሊስም ጥቃቱን የፈፀመውን ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ተናግሯል። የኒው ሳውዝ ዌልስ የአምቡላንስ አገልግሎት በዕለቱ ጥቃቱ በደረሰበት ወቅት አራት ሰዎች ቆስለዋል ብሏል። ሊቀ ጳጳሱ የሕክምና እርዳታ ተደርጎላቸው በአሁኑ ወቅት በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተዘግቧል በዕለቱ በሠላሳዎቹ ውስጥ ከሚገኝ ወጣት በተጨማሪ በከባድ ሁኔታ ወደ ሆስፒታል የተወሰደው በሀምሳዎቹ ውስጥ የሚገኝ አንድ ሰው መኖሩንና በርካታ ቦታዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰበት ለመገንዘብ ተችሏል ። #ኦርቶዶክሳዊ https://t.me/orthdoxswallper https://t.me/orthdoxswallper
Show all...
👍 1
የሚያሳፍር ነገርም የስንፍና ንግግርም ወይም ዋዛ የማይገቡ ናቸውና አይሁኑ፥ ይልቁን ምስጋና እንጂ።” — ኤፌሶን 5፥4 ዲያቆን°°°°ሄኖክ ሐይሌ http://tiktok.com/@fiekr_yemariam_lij3
Show all...
👍 3 1
🔴 አዲስ ዝማሬ " ተናገር አለኝ " | Tenager Alegn | ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ (Official Video ) https://t.me/Abel_mekebeb https://t.me/Abel_mekebeb
Show all...
👍 1
#የሉም_ሞተዋል የሉም ሞተዋል ሲሉን ኖረን የሉም ጠፍተዋል ሲሉን በዝተን አለን በእግዚአብሔር ሁሉን አልፈን አለን በጌታ ሁሉን አልፈን ለካ ሰው ሰለሮጠ አይቀድምም ጉልበታም ስልታገለ አይጥልም ጎልያድ ወድቋል በዳዊት ጠጠር የኛ አምላክ ስሙ ከፍ ይበል ይክበር እግዚአብሔር ስሙ ከፍ ይበል ይክበር አዝ = = = = = በሚነድ እሳት መሐል ሆነን አልሞትንም ዛሬም አለን በዝተን ያልሰማ ሁሉ ይስማ ይግረመው ያመለክነው እግዚአብሔር እንዲህ ነው(፪) አዝ = = = = = ጨክነን እኛ ሰይፉን ባንመዝ በእጃችን ጦር ጉመድን ባንይዝ ይዋጋል ዝም አይልም እግዚአብሔር ልጆቹን ፈጥሮ አይሰጥም ለፍጡር(፪) አዝ = = = = = አሕዛብ ሥጋችንን ሊያጠፉ ቢደክሙ ብዙ ዘመን ቢለፉ ካሸናፊዎች ሁሉ በልጠን አልሞትንም ዛሬም አለን በዝተን(፪)
Show all...
4
🔴 አዲስ ዝማሬ " እኔ ደካማውን " ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ https://t.me/Abel_mekebeb
Show all...