cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ማህበር

ይህ የአዲስአበባ ሙስሊም ወጣቶች ማህበር Official የቴሌግራም ቻናል ነው !

Show more
Advertising posts
248
Subscribers
-124 hours
-17 days
-330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከ/ም/ቤ ፕሬዝደንት ክቡር ዶር ሸይኽ ሱልጧን አማን በባህሬን The Accounting and Auditing Organization for Islamic Financial Institutions (AAOIFI) የሸሪዓ ቦርድ ጉባኤ ላይ ተሳትፈዋል። በባህሬን ማዕከላዊ ባንክ የሚደገፈው የሒሳብ አያያዝ እና ኦዲት ድርጅት ኢስላሚክ የፋይናንስ ተቋማትThe Accounting and Auditing Organization for Islamic Financial Institutions (AAOIFI) 22ኛውን የAAOIFI አመታዊ የሸሪዓ ቦርድ ጉባኤ በ19-20 ሻዋል 1445 ሂ.አ/ ከኤፕሪል 28-29 2024 በክራውን ፕላዛ ሆቴል አዘጋጅቶ በዛሬዉ እለት ተጠናቋል። መቀመጫዉን ባህሪን ያደረገዉ The Accounting and Auditing Organization for Islamic Financial Institutions (AAOIFI) ለሁለት ቀናት ባካሄደዉ ኮንፈረንስ ከተለያዩ ዓለማት የተገኙ ታዋቂ የሸሪዓ ሙሁራን፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ውሳኔ ሰጪዎች፣ መሪዎች እና ሌሎች የኢስላማዊ ፋይናንስ ኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ጋር የፓናል ውይይቶች የተካሄዱ ሲሆን በዚህ ኮንፈረንስ ላይ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ክቡር ዶር ሸይኽ ሱልጧን አማን ተሳታፊ ነበሩ። የAAOIFI አመታዊ ኮንፈረንስ በአለም አቀፍ ኢስላማዊ ፋይናንስ ኢንደስትሪ ውስጥ በጣም አስፈላጊ ከሆኑት ስብሰባዎች አንዱ ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን በዚህ አመትም ከ1000 በላይ የአለም ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ነበሩ። በዚህ ሰፊ ዳሰሳ በተካሄደበት ታላቅ ኮንፈረንስ ላይ ክቡር ፕሬዝደንቱ መገኘታቸዉ ለተቂምና ለሀገር ያለዉ ፋይዳ ድርሻዉ ከፍተኛ መሆኑ እሙን ነዉ። ለሁለት ቀናት እየተካሄደ የነበረዉ ኮንፈረንስ በዛሬዉ እለት ተጠናቋል።
Show all...
https://youtu.be/i613_dCrB7Y #የአባቶቻችንን መስዋትነትና የአሁኑ ትውልድ ሀላፊነት!HarunMedia
Show all...
#የአባቶቻችንን መስዋትነትና የአሁኑ ትውልድ ሀላፊነት!||HarunMedia||

Join this channel to get access to perks:

https://www.youtube.com/channel/UCp39OPJjq5ipnFbtXYDCpKQ/join

Photo unavailableShow in Telegram
አስቸኳይ ህክምና ለወንድማችን ያሻዋል ውዱ የአፋሩ ወንድማችን ሳዲቅ Saddik Badru Al Afari ምክንያቱ በግልፅ በማናውቀው ምክንያት በአፋር ክልል ለእስር ከተዳረገ ወራት አልፏል:: ይህ ወንድማችን በአካል ባናውቀውም በማህበራዊ ሚዲያ ለዲናቸው ከሚለፉ ወንድሞች ቀድሚው ነበር:: በእስር ላይ መሆኑ ሲያሳዝነን አሁን ደግሞ በእስር ላይ ሆኖም ለከፍተኛ የደም ግፊት በሽታ ተጠቅቶ ህመም ላይ መሆኑን ሰምተናል:: በእስር ላይ ያሉ እስረኞችን ጤንነት ማስጠበቅ የመንግስት ኃላፊነት ነው:: ወንድማችን አስቸኳይ ህክምና እንዲያገኝ የሚመለከታቸው የአፋር ክልል የእስር ቤት ኃላፊዎች ሊያደርጉ ይገባል:: በደግነቱ የምናውቀው የአፋር ህዝብ ለዚህ ውድ ወንድማችን የተለመደ ድጋፉን ሊያደርግለት ይገባል:: ወንድማችችን ሳዲቅ አላህ ሙሉ አፊያውን ይመልስለት:: ካለበት እስርም ይፈርጀው Saddik Badru Al Afari
Show all...
ልዩ የወዳጅነት የእግር ካስ ውድድር በአወሊያ ት/ቤት ሜዳ በይፋ ተጀመረ‼ ዛሬ 19/08/2016 የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት የሙስሊም ወጣቶች ሊግ "ወጣት ሙስሊም ራሱን በስፖርት ሊያጠናክር ይገባል።" በሚል መሪ ቃል  የእግር ኳስ ውድድር አድርጓል። ዛሬ በተደረገው የመጀመሪያ ዙር የእግር ኳስ ውድድር የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ሊግ አመራሮች ከመላው አዲስ አበባ የተወጣጡ የአወሊያ ጀመዓዎች ጋር ልዩ የወዳጅነት ፕሮግራም አድርገዋል። መግቢያው ቀለል ባለ ዳዕዋ ተጀምሯል። የመጨረሻው ውጤት 2 ለ 2 ተጠናቋል። ጨዋታው በጣም ከባድ እና አዝናኝ ነበር። በፕሮግራሙ ላይ የተሳተፉ በሙሉ ይህ ጅምር ወደፊት በሰፊው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ውይይት የተደረገ ሲሆን በቀጣይ የሚደረግ የእግር ኳስ ውድድር ይፋ እንደሚያደርጉ ተገልፇል። ይህ ጅምር ሙስሊሙ ማህበረሰብ በስፖርታዊ ውድድር ራሱን ሊያጠናክር የሚያስችለው እንደመሆኑ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ ሰፊ ስራዎች እንዲሰራ ሀሳብ ተሰጥቷዋል።
Show all...
👍 1
ኡስታዝ ሙባረክ ኸድርን እንተባበር‼️ ••••••••••••••••••••••••••••••••••••• 🔹በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አቡል ኸይር መስጂድ በኡስታዝነት የሚታወቀው ሙባረክ ኸድር ያለወንጀሉ በግፍ የ10 አስር አመት ፅኑ እስራት ተፈረዶበት በቃሊቲ ማረሚያ ታስሮ ይገኛል። ይህ ወንድማችን እስካሁን እስከታሰረበት ድረስ ከፍተኛ ችግር እየገጠመው ይገኛል። በተለይ ከክፍለ ሀገር ድረስ ቤተሰቦቹ እየተመላለሱ እየተጉላሉ ይገኛል። በመሆኑም ለወንድማችን በፍጥነት ከእስር እንዲፈታ ዱዓ እንድታደርጉለት እየጠየቅን በገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ የምትፈልጉ በኡስታዝ ሙባረክ ኸድር በግሉ በተከፈተው የባንክ አካውንት ቁጥሮች ከስር አስቀምጠናል። •ንግድ ባንክ 1000081251243 •አዋሽ ባንክ 01336195412200 •ኦሮሚያ ህብረት ባንክ 1025300010427 •ዳሽን ባንክ 5210003297007 #ፍትህ_ለኡስታዝ_ሙባረክ_ኸድር @የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ማህበር https://www.facebook.com/100063462439332/posts/pfbid02UCfeNZTMg2QiKEfpcwtPVwF9nCrjbJREAVwjsECEfJZZfuzAnzyU3CAn3SWNxaLyl/?app=fbl https://www.facebook.com/100063462439332/posts/pfbid02KF3azGRgVQTcWXi8GHb1iV1E3KfnPACgbad3PAwAApsgNMVnpMBXn5QTwFfg17Pcl/?app=fbl
Show all...
የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ማህበር

አሳዛኝ ዜና‼ 10 አመት‼ የፍትህ ያለ‼ ይህ ወጣት ኡስታዝ ሙባረክ ከድር ይባላል ከሀላባ ዞን ከአስር አመት በፊት አዲስ አበባ በመሄድ ንፋስ ስልክ ለፍቶ ክ/ከ/ወረዳ 11 የሚገኘው አቡል ኸይር መሰጂድ ህጻናትን ቁረአን ከመስቀረት እሰከ በወረዳው መጅሊስ ምክትል ሰብሳቢ በመሆን ለረዥም አመታት እያገለገለ እያለ...

ይሄን ልጅ አስታወሳቹት ? ግንቦት 25 /2015 በታላቁ አንዋር መስጂድ በሸገር ሲቲ በፈረሱ መስጂዶች ለተቃውሞ በወጡ ወንድሞች ላይ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ የጥይት ናዳ መስጂዱ ላይ በነበሩ ሙስሊሞች ላይ ከፀጥታ ሀይሎች ተተኩሷል ። ብዙዎችም ሸሂድ ሆነዋል ። አንዳንዶቹ ደግሞ ደግሞ አካላቸውን አጥተዋል ። ከነዛ ውሰጥ አንዱ ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ልጅ ነው ። በሰዓቱ በጥይት ተመቶ እጁን ለሸሀዳ አዘጋጅቶ ሰዎች ይዘውት ሲሮጡ የሚያሳይ ፎቶ ሲዘዋወር ነበር ። አብዛኞቻችን የሞተ ሁሉ መስሎን ነበር ። ዛሬ ከወራቶች ህክምና በኃላ ደህና መሆኑን በቲክቶክ ፔጁ ላይ ትላንት ቪዲዮ አጋርቷል ። ወደ አኼራ የሄዱትንም ወንድሞቻችንን መልዕክ አስተላልፏል ።(ሆስፒታል ከገባ ቀን ጀምሮ ከጎኑ ለነበሩ በዱዓመ ያሰቡትን ሙስሊም እህቶ ወንድሞቹንም አመሰግኗል ..!) አልሐምዱሊላህ የቀረው ቀርቶ ወደ አላህ የሄደውም ሄዶ ዛሬ እዚህ ላይ ደርሰናል ። ሸሂዶቻችንን እንዳልረሳናቸው ተስፋ አደርጋለው ፤ በዱዓችን እንዳልዘነጋናቸውም ተስፋ አደርጋለሁ ፤ አሁንም ለሸሂድ ወንድሞቻችን ዱዓ ማድረጋችንን አንርሳ ። አንረሳቹም ሸሂዶቻችን !!!
Show all...