cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም።

Show more
Advertising posts
1 512Subscribers
-324 hours
-57 days
+1830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ነገር ክርስቶስ ክፍል 3 ባለፈው ቅኝታችን ጠቅለል ባለ መልኩ ኢየሱስን ፈጣሪ ያለ ወንድ ጣልቃ ገብነት ከሴት ብቻ እንደፈጠረው አይተን እንደነበረ ታስታውሳላችሁ ዛሬ ደግሞ ዝርዝር ውስጥ ገብተን የኢየሱስን ፍጡርነት እንቃኝ። “ስለዚህ ወደ ዓለም ሲገባ፦ መሥዋዕትንና መባን አልወደድህም ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ፤”   — ዕብራውያን 10፥5 በዚህ አንቀጽ ላይ እንደምንመለከተው ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም ስገባ ሥጋን አዘጋጀህልኝ ብሎ እንደተናገር ልብ በል! ሥጋን አዘጋጀህልኝ ሲል ሥጋን ፈጠርከልኝ እያለ እንደሆነ ልብ ይላል! ምክንያቱም በባይብል አዘጋጅ የሚለው ቃል ፈጠረ በሚል ተለዋዋጭ ሆኖ ይመጣል! “ቀኑ የአንተ ነው ሌሊቱም የአንተ ነው፤ አንተ ፀሓዩንና ጨረቃውን አዘጋጀህ።”   — መዝሙር 74፥16 ፈጣሪ በዘፍጥረት 1:14 እና በዘፍጥረት 1:16 እንዲሁም በመዝሙር 136:7 ላይ  ፀሓይንና ጨረቃን ፈጥሮ እያለ አዘጋጅ በሚል የተቀመጠው አዘጋጅ የሚለውን ቃል ፈጠረ ለሚለው ቃል ተለዋዋጭ እንደሆነ ልብ ይላል! ታዲያ የኢየሱስ ሥጋው ፍጡር መሆኑን ከተመለከተን ሥጋ ብቻውን ግዑዝ ነገር እንጂ ሕያው አይደለምና የግድ ሕይወት ያስፈልገዋል ስለዚህም ነው ኢየሱስም ሕይወት የተቀበለው። “አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና።”   — ዮሐንስ 5፥26 ኢየሱስ ከፈጣሪ ሕይወትን ሳይቀበል በፊት ምን ነበረ? ግልጽ ነው ግዑዝ ሥጋ ብቻ ነበር ለዛውም ነው እንደ ማነኛውም ሰው ከፈጣሪ ዘንድ ሕይወት ተቀብሎ ሕያው የሆነው። ኢየሱስ ፈጣሪ ነው ለምትሉ በሙሉ ግልጽ ጥያቄ! :-አንደኛ ለኢየሱስ ሥጋን የፈጠረለት ፈጣሪ ማን ነው? ኢየሱስ ራሱ ፈጣሪ ከሆነ የኢየሱስን ሥጋ የፈጠረው ማን ነው? ፈጣሪን ፈጣሪ ፈጠረው እያላችሁን ነው?? :-ሁለተኛ ለኢየሱስ ሕይወትን የሰጠው ፈጣሪ ማን ነው? ፈጣሪ ጥንትም ዘልዓለምም ሕያው ነው እንጂ ከጊዜ ቦኋላ ሕይወት ይቀበላልን?? []]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]] [ይቀጣላል ___ኢንሻ አሏህ] []]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]]] ✍ ሙከሚል ሙሥሊም  ልጅ https://t.me/wada_islam
Show all...
የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም።

የነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) ነቢይነት ክፍል 4 በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነው! وَيَقُولُ الَّذِينَ كَفَرُوا لَسْتَ مُرْسَلًا ۚ قُلْ كَفَىٰ بِاللَّهِ شَهِيدًا بَيْنِي وَبَيْنَكُمْ  [ ሱረቱ አል- ረዕድ፥ - 43 ] እነዚያም የካዱት ሰዎች «መልክተኛ አይደለህም» ይላሉ፡፡ «በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ በአላህ በቃ በላቸው። ወዳጄ ሁሌም እንደምለው ስለ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) ነቢይነት ለማወቅ በመጀመሪያ እነዚያ በጥላቻ የተሞሉ የውሸት ጓንዳዎች ያጠለቁልህን የሻገተ መነጽርህን አውልቀህ ጣለውና ረጋ ሰከን ባለ ስሜት በጥንቃቄ አጥና! ያኔ እውነቱ ፍንትው ብሎ ታገኘዋለህ። በክፍል ሦስት ቅኝታችን ቁርአንን ነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) ከአለማቱ ጌታ ከአላህ ዘንድ የተቀበሉት መሆኑን ቁርአኑንም ከተቀበሉ በኋላ ቁርአን የፈጣሪ ቃል አይደለም የሚሉ ሰዎችን እንግዲያስ ቁርአን የፈጣሪ ቃል ሳይሆን የነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) ድርሰት ነው ካላችሁ እስቲ እናንተም የቁርአንን አምሳያው አምጡ ብሎ (ተሐዲ) አቅርቦላቸው ማምጣት አለመቻላቸውን አይተን ነበር። ይህም የሚያሳየው አንድም ቁርአን እውነተኛ የፈጣሪ ቃል መሆኑን ቁርአንን የተቀበሉት ነቢይ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) እውነት የፈጣሪ ነቢይ መሆናቸውንና ቁርአን ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) ከተሰጣቸው ትላልቅ ተአምራት ዋነኛው መሆኑን ያሳያል። አንድ ነቢይ ለእውነተኛ ነቢይነቱ እንደ ማስረጃ ሆነው ከሚቀርቡ ነገራቶች ውስጥ አንዱ ተአምር ማሳየት እንደሆነ ይታወቃል። ነቢዩ ሙሐመድም (ሰዐወ) እውነተኛ የፈጣሪ ነቢይ እንደመሆናቸው የተሰጣቸው ተአምር ቁርአን ብቻ ሳይሆን ብዙ ናቸው። እስቲ ዛሬ ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) ከፈጣሪ ዘንድ ከተሰጣቸው ከቁርአን ቀጥሎ ካሉ ትላልቅ  ተአምራት ውስጥ አንዱን እንመልከት። ነቢያች ነቢይ ሆነው በተነሱበት ጊዜ የቁረይሽ ሰዎች ነቢዩ ሙሐመድን እስቲ አንተ እውነተኛ የአላህ ነቢይ ከሆንክ ተአምር አሳየን አሉት ነቢዩ ሙሐመድም ጨረቃን ለሁለት በመካፈል ትልቅ ተአምር አሳይቷቸዋል። اقْتَرَبَتِ السَّاعَةُ وَانشَقَّ الْقَمَرُ (ሱረት አል-ቀመር - 1) ሰዓቲቱ (የትንሣኤ ቀን) ተቃረበች፤ ጨረቃም ተገመሰ፡፡ أَنَّ أَهْلَ مَكَّةَ سَأَلُوا رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم أَنْ يُرِيَهُمْ آيَةً، فَأَرَاهُمُ انْشِقَاقَ الْقَمَرِ‏. አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረ.ዐ) እንደተረከው የመካ ሰዎች የአላህን መልዕክተኛ (ﷺ) ተዓምር እንዲያሳዩአቸው ጠየቁት፣ እሳቸውም ጨረቃን ለሁለት በመክፈል አሳያቸው። (📚 ቡኻሪ መጽሐፍ 61, ሐዲስ ,141) በሌላም ዘገባ እንዲህ ተዘግቧል! ኢብኑ ሙጥዕም ከአባቱ ይዞ انْشَقَّ الْقَمَرُ عَلَى عَهْدِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم حَتَّى صَارَ فِرْقَتَيْنِ عَلَى هَذَا الْجَبَلِ وَعَلَى هَذَا الْجَبَلِ فَقَالُوا سَحَرَنَا مُحَمَّدٌ فَقَالَ بَعْضُهُمْ لَئِنْ كَانَ سَحَرَنَا مَا يَسْتَطِيعُ أَنْ يَسْحَرَ النَّاسَ كُلَّهُمْ በነቢዩ ዘመን ጨረቃ በዚህ እና በዚያ ተራራ ላይ ሁለት እስክትሆን ድረስ ተሰንጥቃ ታየች፣ ቁረይሾችም ‟ነቢዩ በእኛ ላይ አስደግሞብን ነው” አሉ፣ ከፊሎቹ ደግሞ ‟በእኛ ላይ አስደግሞብን ከሆነ ሁሉም ሰው ላይ ማስደገም አይቻለውም” አሉ። (📚ትርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ, 341) ተጨማሪ ማስረጃ ከፈለክ ! Sahih al-Bukhari, 3868 Sahih al-Bukhari, 4867 Sahih Muslim, 2802 Sahih Muslim, 2803 ወዘተ... ተመልከት ታላቁ አሊም ኢብኑ ከሲር ይህን ሐዲስ ሲያብራራ እንዲህ ብሏል! انشقَّ القمرُ بمكةَ حتى صار فرقتَينِ فقال كفارُ قريشٍ لأهلِ مكةَ هذا سحرٌ سحرَكم به ابنُ أبي كبشةَ انظروا  السُّفَّار فإن كانوا رأوا ما رأيتُم فقد صدق وإن كانوا لم يرَوا مثلَ ما رأيتُم فهو سِحرٌ سحركم به قال فسُئل ا السُّفَّارُ قال وقدِموا من كل وِجهةٍ فقالوا رأَينا. በመካ ጨረቃ ሁለት እስክትሆን ድረስ ተከፈለች፣ የቁረይሽ ካፊሮች ለመካ ነዋሪዎች ይህ ኢብኑ አቢ ከበሻ (ሙሐመድ) ያስደገመባችሁ ድግምት ነው፣ ከውጪ የሚመጡትን ተጓዢዎች ስለ ነገሩ ጠይቁአቸው፣ እናንተ የተመለከችሁን ነገር እነርሱም ከተመለከቱ በእርግጥም እውነት ነው፣ ያልተመለከቱ ከሆነ ደግሞ ድግምት ነው አሏቸው። ከዚያም ከሁሉም አቅጣጫ የመጡትን ተጓዦች ጠየቁ እነርሱም ‟አዎ አይተናል” ብለው መሰከሩ። (📚አል-ቢዳያ ወኒሃያ ለኢብኒ ከሲር 3/119) ይህ ክስተት እንዲሁ ተረት ተረት ሳይሆን በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በስጋ ዓይናቸው የተመለከቱት ክስተት ነው። ወደ ዋናው ነጥቤ ስመለስ አንድ ሐሰተኛ ነቢይ ጨረቃን የሚያክል ግዙፍ ፍጥረት ለሁለት መካፈል ይችላልን?? በጭራሽ አይችልም። ታዲያ ነቢዩ ሙሐመድ ይህን ማድረግ እንዴት ቻሉ? መልሱን ለራስህ!! [[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[ [[ይቀጥላል,, ኢንሻ አላህ   ]] [[                                   ]] [[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[[ ✍ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ https://t.me/wada_islam
Show all...
የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም።

3🔥 1
አሥ ሠላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ ያ ጀመዓህ! "የተደበቀው እውነት" የሚለው ስድስተኛው መጽሐፌ በገበያ ላይ ውሏል። "የተደበቀው እውነት" የሚያውጠነጥነው ስለ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" መምጣት በተውራት እና በኢንጂል ተነግሮ የመጽሐፉ ሰዎች ይህንን እውነት እንዴት እንደደበቁት የሚገልጥ እና የሚያጋልጥ ነው። ዝርዝሩን መጽሐፉ ላይ ያንብቡ እና ለሎች የሂዳያህ ሠበብ እንዲሆን አስነብቡ! መጽሐፉን መርካርቶ አንዋር መሥጂድ ኢሥላማዊ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ያገኙታል፥ የበለጠ ለመረጃ +251920781016 ዐብዱ ብለው ይደውሉ! መጽሐፉ ተደራሽነት እንዲኖረው ባለው የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ሼር በማድረግ ሠበቡል ሂዳያህ ይሁኑ! ወጀዛኩሙላህ ኸይራ! ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom
Show all...
👍 2
ኢሥላም የተማረኩ ሴቶችን አስገድዳችሁ ድፈሩ ይላልን? ለቀጣፊ ክርስቲያን ወገናችን መልስ 🎙ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ። https://t.me/mukamil12
Show all...
🔖 ኢየሱስ ምንድን ነው? በኡስታዝ ወሒድ ዑመር እና በፓስተር ኃይሉ ዮሐንስ መካከል የተደረገ ውይይት t.me/hidayaislam
Show all...
👍 1
“እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤”   — ዕብራውያን 5፥7 የዝንብ እግር ይዛ በር ክፈቱልኝ አለች አሉ። ራሱን ማዳን ተስኖት አምላኬ  ሆይ እባክህ ከሞት አድነኝ እያለ አቤቱታ ሲያቀርብ የነበረውን ኢየሱስን ሺህ ጊዜ ኢየሱስ ያድናል ብትል የሰው መሳለቂያ ትሆን ይሆናል እንጂ ማን ይሰማካል?🙈 ✍ ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ። https://t.me/wada_islam
Show all...
የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም።

6👍 4🔥 2
መጦ አይችሉምን? በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነው የረመዳንን ወር ጦም መጦም ከእሥልምና መሰረቶች ውስጥ አንዱ ነው። አምላካችን አሏህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُتِبَ عَلَيْكُمُ الصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጦም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈ በናንተም ላይ ተጻፈ (ተደነባ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡ [2:183] ይህም የጦር ወር የረመዳን ወር ነው። شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ ۚ فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ ۖ وَمَن كَانَ مَرِيضًا أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِّنْ أَيَّامٍ أُخَر  (እንድትጦሙ የተጻፈባችሁ) ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (እውነትን ከውሸት) ከሚለዩም ገላጮች (አንቀጾች) ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡ ከእናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጡመው፡፡ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነም ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን (በልኩ) መጦም አለበት፡፡ [2:185] ይህን የረመዳን ወር ጦምን መጦም በሁሉም ሙሥሊም ላይ ግዴታ ነው ዑዝር ካለው ሰው በስተቀር ዑዝር ያለው ሰው ረመዳን ላይ ያልጦማቸውን ቀኖች ቆጥሮ ከረመዳን ቦኋላ መጦም አለበት። ይህ ሆኖ ሳለ አንዳንድ ጥራዝ ነጠቅ ወገኖቻችን በእሥልምና ሴቶች ከባሎቻቸው ፍቃድ ውጭ የረመዳን ጦምን መጦም አይችሉም ብሎ ይቀጣጥፋሉ። ለዚህ ቅጥፈታቸው የሚያቀርቡት ሐዲስ ቦኻሪ ላይ ያለን ያልተሟላ ዘገባን በመጥቀስ ነው። لا تَصُومُ الْمَرْأَةُ وَبَعْلُهَا شَاهِدٌ إِلا بِإِذْنِهِ ሚስት ቦሏ እያለ ከእርሱ ፍቃድ ውጭ መጦም አትችልም። [ቦኻሪ 5192] ይህ ሐዲስ አንድም ነቢዩﷺ የተናገሩት ሙሉ ቃላቸውን አልያዘም ሆኖም ግን በዚህ ሐዲስ ላይ የትኛው ሀይለ ቃል ነው ሚስት ከባሏ ፍቃድ ውጭ ግዴታ ጦምን መጦም አትችልም የሚለው?? ቅጥፈት አይሰለቻችሁም?? ቅሉ ግን ሐዲሱ የሚናገረው ስለ "ሱና" ጦሞች እንጂ ስለ ግዴታው የረመዳን ወር ጦምን አይደለም። ከላይ ያለውን ሐዲስ በተሟላ መልኩ ቲርሚዚ ዘግቦታል። የተሟላው ሐዲስ እነሆ   أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لاَ تَصُومُ الْمَرْأَةُ وَزَوْجُهَا شَاهِدٌ يَوْمًا مِنْ غَيْرِ شَهْرِ رَمَضَانَ إِلاَّ بِإِذْنِهِ ‏ "‏ አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦"ነቢዩ"ﷺ እንዲህ አሉ፦ "አንዲት ሴት ከረመዷን ወር ውጪ ባሏ እያለ ከእርሱ ፈቃድ በስተቀር አንድ ቀን መጦም አትችልም"። [ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 101] ምን ትፈልጋለህ?? የሱና ጦም መጦም ምንዳን የሚያስገኝ ሥራ ቢሆንም የሱና ጦም አለመጦም ግን አያስጠይቅም። ሚስቶች በባሎቻቸው ላይ መብት እንዳላቸው ሁሉ ለባሎችም በሚስቶቻቸው ላይ መብት አላቸው። ለምሳሌ ሚስት ግዴታ ያልሆነውን የሱና ጦም ስትጾም ቦሏን ሳታስፈቅድ ከሆነ ባሏ ግን ያንን የሱና ጦም የማይጦም ከሆነ ምናልባት እርሷ ጦም ላይ ኹና ባሏ ግንኙነት ማድረግ ልፈልግ ይችላል ስለዚህ ሚስት የሱና ጦም መጦም በፈለገች ጊዜ ባሏን ማስፈቀድ አለባት። በጣም የሚገርመው ደግሞ ሚስት የሱና ጦም መጦም ፈልጋ ባሏን ብታስፈቅደውና ባሏ ባይፈቅድላት ራሱ ሦስት አጅር (ምንዳ) ታገኛለች! :-አንድም ጦሙን ለመጦም በማሰቧ እንደጦመች ይቆጠርላታ። ስራ የሚመዘነው "በኒያ" ነውና። ቦኻሪ መጽሐፍ 1,ሐዲስ 1 :-ሁለትም ባሏን እሺ ብላ በመታዘዟ ምንዳን ታገኛለች እንደውም ባሏን እሺ ብላ በመታዘዟ ምክንያት የገነት በሮች ተከፍቶላት በፈለግሽው በር ግቢ ትባላለች። [ሙስነድ አሕመድ 1661] (ሰሒሑል ጃሚዕ 660] :-ሦስትም ከሀላል ባሏ ጋር ግበረ ሥጋ ግንኙነት በማድረጋቸው ምክንያት "ምንዳን" ያገኛሉ። [ኢማሙ ሙሥሊም 1006 ።] ግዴታ ያልሆነውን ባይጦሙት ቅጣት የሌለበትን የሱና ጦም ለመጦ ባሏን ማስፈድ ነው ጉዳት ወይስ ባሏን እሺ ብላ በመታዘዟ ምክንያት ከላይ የጠቀስናቸውን ሁሉ ትሩፋት ማግኘት ነው የሚሻለው?? ወገኖቼ ሆይ እሥልምናን እና ሙሥሊሙን ለመተቸትና ለማብጠልጠል ቀንና ለሊት ከምትፍጨረጨሩ እሥልምናን በሰከነ መንፈስ አጥንታችሁ ወደዚህ ብርሃን ወደ ሆነ እምነት እንድትመጡ አሏህ ጤነኛ አዕምሮ ይስጣችሁ። ولله اعلم ✍ ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ። https://t.me/wada_islam
Show all...
የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም።

👍 3
አሥ-ሠላሙ ዐለይኩም ሙሥሊም እኅትና ወንድሞቼ ዒድ ሙባረክ እንኳን አደረሳችሁ! ተቀበል አሏሁ ሚና ወሚንኩም🌴
Show all...
4
ነገር ክርስቶስ ክፍል 2 በክፍል አንድ ቅኝታችን ኢየሱስን አምላካችን አሏህ ያለ አባት ከሴት ብቻ ኹን በሚለው ቃሉ እንደፈጠረው አይተናል። ባይብልም ላይ ስንመለከተው ኢየሱስን ፈጣሪ ያለ አባት ከሴት ብቻ እንደፈጠረው ተቀምጧል። ሉቃስ 1:26-32 “እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።”   — ሉቃስ 1፥31 “እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤”   — ሉቃስ 1፥32 ከእነዚህ አንቀጾች የምንረዳው ነገር! ፨አንደኛ እነሆ ትፀንሻለሽ ሲል ኢየሱስ ከሴት ማህጸን ተጸንሶ ካለ መኖር ወደ መኖር እንደመጣ እንረዳለን። ፨ሁለተኛ ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ ሲል ፈጣሪ ጾታ እንደሌለው ግልጽ ነገር ቢሆንም ኢየሱስ ግን ጾታ ያለው ወንድ ልጅ እንደሆነ እንረዳለን። ፨ሦስተኛ ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ ሲል ፈጣሪ ጥንትም የነበረና አዲስ ስምም የሚወጣለት እንዳልሆነ ግልጽ ነገር ቢሆንም! ለኢየሱስ ግን እንደ ማነኛውም ሰው ከጊዜ ቦኋላ ስም እየወጣለት እንደሆነ እንረዳለን። ፨አራተኛ እርሱም ታላቅ ይሆናል ሲል ፈጣሪ ጥንትም ዘልዓለምም ታላቅ እንደሆነ ግልጽ ነገር ቢሆንም! ኢየሱስ ግን ከጊዜ ቦኋላ ታላቅ ይሆናል እየተባለ እንደሆነ እንረዳለን። ፨አምስተኛ የልዑል ልጅም ይባላል ሲል ፈጣሪ ልዑል እንደሆነ ግልጽ ነገር ቢሆንም! ኢየሱስ ግን የልዑል ልጅ ተባለ እንጂ ልዑል እንዳልሆነ እንረዳለን። ፨ስድስተኛ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል ሲል! ለፈጣሪ በምንም መልኩ አባት እንደሌለው ግልጽ ነገር ቢሆንም! ኢየሱስ ግን የዳዊት ልጅ እንደተባለ እንረዳለን። ፨ሰባተኛ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል ሲል ለኢየሱስ የዳዊትን ዙፋን የሚሰጠው አምላክ እንዳለ ግልጽ ነው። ኢየሱስ አምላክ ቢሆንም ኖሮ ከሌላ አካል የዳዊትን ዙፋን አይቀበልም ነበር። ስለዚህም ለኢየሱስ የዳዊትን ዙፋን የሰጠው ነው አምላክ እንጂ የዳዊትን ዙፋን የተቀበለው ኢየሱስ አምላክ እንዳልሆነ እንረዳለን። ይቀጥላል----- ኢንሻ አሏህ ✍ ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ https://t.me/wada_islam
Show all...
የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም።

8👍 5