en
Feedback
ጃን ያሬድ | Jan Yared

ጃን ያሬድ | Jan Yared

Open in Telegram

እግዚአብሔርን አመስግኑ ምህረቱ ለዘላለም ነውና!!! ማን ነው ህይወትን ማግኘት የሚፈልገው ማን ነው ጣፋጭ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል መማር የሚፈልገው  ማን ነው ስለ እመብርሀን ስለ ድንግል ማርያም መማር ማወቅ የሚፈልገው   እንግዲያውስ አሁንኑ ይፍጠኑ እና ይቀላቃሉ 

Show more
1 460
Subscribers
No data24 hours
-117 days
-2930 days
Posts Archive
እሷ ዓይነ ስውር በመሆኗ ከፍቅረኛዋ በቀእ እራሷን ጭምር የምትጠላ አንዲት ልጅ ነበረች። ፍቅረኛዋ ዓይነ ስውር መሆኗን ተቀብሎ ይወዳት ስለነበር፤ እሷም ዓይኔ ይብራልኝ እንጂ ዓለምን ብቻ ማየት ከቻለ
እሷ ዓይነ ስውር በመሆኗ ከፍቅረኛዋ በቀእ እራሷን ጭምር የምትጠላ አንዲት ልጅ ነበረች። ፍቅረኛዋ ዓይነ ስውር መሆኗን ተቀብሎ ይወዳት ስለነበር፤ እሷም ዓይኔ ይብራልኝ እንጂ ዓለምን ብቻ ማየት ከቻለኩ አንተን አገባሃለው ትለው ነበር። አንድ ቀን፧ አንድ የማታውቀው ሰው ጥንድ ዓይኖቹን ሰጣት፤ አሁን የወንድ ጓደኛዋን ጨምሮ ሁሉንም ነገር ማየት ትችላለችና ደስ አላት••• ፍቅረኛም እግሯ ስር ሆኖ “አሁን ዓለምን ስታዪ እና ስትመለከቺኝ የገባሽውን ቃል ጠብቀሽ ታገቢኛለሽ?” ብሎ ጠየቃት። ልጅቷ የወንድ ጓደኛዋም ዓይነ ስውር መሆኑን ስታይ ደነገጠች እና እሱን ለማግባት ፈቃደኛ ሳትሆን ቀረች°°° እሱም አምርሮ አለቀሰ እና ትቷት ሄደ፤ በኋላ እንዲህ የሚልደብዳቤ ጻፈላት°°° “ውድ ዓይኖቼን ብቻ ተንከባከቢልኝ” ••• ሞራል - ስንወድ እና ቃል ስንገባ፤ ምንም አይነት ሁኔታዎች ቢለዋወጡ እንደማንቀያየር እርግጠኛ ስንሆን ይሁን••• ፨፨፨ እናንተ ብትሆኑ ምን ታድርጉ ነበር? *** እናንብብ እንወያይ ነጻ እንውጣ

ስላለፈው ውሳኔያችሁ በጸጸት አትኑሩ! ከዚህ በፊት የወሰናችሁትን ውሳኔ አሁን ስትመለከቱት፣ “ምነው ባልወሰንኩት!” የሚያሰኝ ውሳኔ ከሆነ በዚህ ውሳኔ መሰረት እየተጸጸቱ መኖር ምንም አያዋጣም፡፡ በታ
ስላለፈው ውሳኔያችሁ በጸጸት አትኑሩ! ከዚህ በፊት የወሰናችሁትን ውሳኔ አሁን ስትመለከቱት፣ “ምነው ባልወሰንኩት!” የሚያሰኝ ውሳኔ ከሆነ በዚህ ውሳኔ መሰረት እየተጸጸቱ መኖር ምንም አያዋጣም፡፡ በታትነን እንመልከተው፡፡ 1. ምናልባት ትክክለኛውን ውሳኔ እያወቃችሁ የተሳሳተ ውሳኔ ወስናችሁ ሊሆን ይችላል፡፡ 2. ምናልባት በወቅቱ የነበራችሁን እውቀት፣ መረጃም፣ የኑሮ አቅምም ሆነ የስሜት ሁኔታ አሰባስባችሁ በተቻለ መጠን ትክክለኛ ነው ብላችሁ ያመናችሁበትን ውሳኔ ወስናችሁ ሊሆን ይችላል፡፡ 3. ምናልባት በሰው ተታላችሁ ወይም በሁኔታዎች ተወዛግባችሁ ምኑንም ሳታውቁት ወስናችሁ ሊሆን ይችላል፡፡ ዛሬ ለጸጸት የዳረጋችሁ ያለፈው ውሳኔ መንስኤ ከላይ ከተዘረዘሩት መካከልም ሆነ ከዚያ ውጪ፣ ዋናው ነገር ያለፈው ውሳኔ ዛሬ ያመጣባችሁን የጸጸት ስሜት አልፋችሁ ለመሄድ ያላችሁ ቁርጠኝነት ነው፡፡ መፍትሄዎች፡- 1. በትናንትናው ውሳኔ ዛሬ፣ በዛሬ ውሳኔ ደግሞ ነገ የመጸጸት ነገር እድሜ ልክ የሚከተል እውነታ መሆኑን አትዘንጉ፡፡ 2. በውሳኔያችሁ ስትጸጸቱ፣ እንደገና ማስተካከል የምትችሉትን የውሳኔውን ውጤት ለማስካከል ሞክሩ፡፡ 3. በውሳኔያችሁ ስትጸጸቱ፣ እንደገና ለማስተካከል የማትችሉትን የውሳኔ ውጤት ተቀበሉት፣ ትምህርታችሁን አግኙ፣ ብሰሉበት . . . እና ወደፊት ተራመዱ፡፡ 4. በውሳኔው ምክንያት ስለመጣው ችግር ከማሰላሰል ላይ ሃሳባችሁን አንሱና ስለወደፊት ራእያችሁና እቅዶቻቸው ማሰብ ጀምሩ፡፡ ፈጣሪ ጤና ይስጣችሁ!

Enjoy The Day!!! የዛሬዋ ቀን እንደገና ደግማ የማትመለስ ውብ የሆነች ቀን ነች! Enjoy it! በምንም ሁኔታም ሆነ በማንም ሰው ምክንያት በድብርት አታሳልፏት! ደስተኛ ለመሆን ወስኑ፡፡ በ
Enjoy The Day!!! የዛሬዋ ቀን እንደገና ደግማ የማትመለስ ውብ የሆነች ቀን ነች! Enjoy it! በምንም ሁኔታም ሆነ በማንም ሰው ምክንያት በድብርት አታሳልፏት! ደስተኛ ለመሆን ወስኑ፡፡ በምንም ሁኔታም ሆነ በማንም ሰው ምክንያት መራራ በመሆን አታባክኗት! የቀኑ መልካም ጎን ላይ በማተኮር አጣጥሟት! በምንም ሁኔታም ሆነ በማንም ሰው ምክንያት ተስፋ ቆርጣችሁ አትለፍባችሁ! ተስፋችሁን በፈጣሪ ላይ አድርጉና ቀና ብላችሁ ዋሉ! መልካም ቀን ለሁላችሁም! Source: Dr Eyob Mamo

🙏 ለመጸለይ ከፀሐይ ጋር ተነስ። ብቻህን ጸልይ። ብዙ ጊዜ ጸልይ። ብትናገር እግዚአብሔር ይሰማል። 🙏 በመንገዳቸው የጠፉትን ታገስ። ድንቁርና፣ ትዕቢት፣ ቁጣ፣ ቅናት እና ስግብግብነት የሚመነጩት ከ
🙏 ለመጸለይ ከፀሐይ ጋር ተነስ። ብቻህን ጸልይ። ብዙ ጊዜ ጸልይ። ብትናገር እግዚአብሔር ይሰማል። 🙏 በመንገዳቸው የጠፉትን ታገስ። ድንቁርና፣ ትዕቢት፣ ቁጣ፣ ቅናት እና ስግብግብነት የሚመነጩት ከጠፋች ነፍስ ነው። ምሪትን እንዲያገኙ ጸልይ። 🙏 ራስህን በራስህ ፈልግ። ሌሎች መንገድህን እንዲያበጁልህ አትፍቀድ። የአንተ መንገድ የአንተ መንገድ ብቻ ነው። ሌሎች አብረውህ ሊራመዱ ይችላሉ፤ ነገር ግን ማንም የአንተን መንገድ ሊሔድልህ አይችልም። 🙏 ለእንግዳ ዋጋ ስጥ። በጣም ጥሩውን ምግብ አቅርብላቸው፤ ጥሩውን አልጋ ስጣቸው እና በአክብሮት ያዛቸው። 🙏 ያንተ ያልሆነውን ከሰው፣ ከማህበረሰቡ፣ ከበረሃም ሆነ ከባህል አትውሰድ። ካላገኘህ ወይም ካልተሰጠህ ያንተ አይደለም። 🙏 በዚህች ምድር ላይ የተቀመጡትን ነገሮች ሁሉ አክብር- ሰዎችም ይሁኑ ተክሎች። 🙏 የሌሎችን ሃሳቦች፣ ምኞቶች እና ቃላት አክብር። ሲያወሩ በፍፁም አታቋርጥ፣ በጭራሽ አታላግጥ ወይም በስድብ አትመልስላቸው። የእያንዳንዱን ሰው እራሱን የመግለጥ መብት አትፈታተን። 🙏 ስለ ሌሎች በመጥፎ መንገድ በጭራሽ አትናገር። ያወጣኸው አሉታዊ ኃይል ወደ አንተ ሲመለስ ይበዛል። 🙏 ሁሉም ሰው ይሳሳታል። እና ሁሉም ስህተቶች ይቅር ሊባሉ ይችላሉ። 🙏 መጥፎ አስተሳሰብ የአዕምሮ፣ የአካል እና የመንፈስ ህመም ያስከትላል። ብሩህ ተስፋን ተለማመድ። ✍️ የፍልስፍና ሀሁ መፅሐፍ

የሰው ልጆች ችግራችን ዓለም በእኛ አዕምሮ ልክ እንድትጠብ ነው የምንጠብቀው። ነገር ግን አዕምሯችንን በዓለም ልክ ማስፋት ነው ያለብን! በአዕምሮህ የምትስለው ማፕ [ከምትፈልገው] ሪያሊቲ ጋር ማች ማድረግ አለበት። ስለዚህ የምትፈልገውን ሪያሊቲ በማጥናት ማፕህን አስፋ! ማንኛውንም ሃሳብ በአዕምሮህ በመደጋገም በአፅንኦት ካሰብከው እውን የሚሆን ከሆነ ለምን የሚጠቅምህን እና ሕልምህን የሚያሳካ ሃሳብን ደጋግመህ በአፅንኦት አታስብም? ለምን የሚያፈርስህ ሃሳብ ላይ ጊዜህን እያባከንክ የማትፈልገውን ውጤት ትሰበስባለህ??? በጥበብና በማስተዋል እናስብ!!! 😍✌️

አለማወቅ
አለማወቅ

መፍትሄ ! አብዛኞቻችን ሰኞን ላንወደው እንችላለን ከእንቅልፍ ከምንነሳበት ሰዓት ጀምሮ የተለመደው ንቃት ላይሰማን እንችላለን። ቀናችንን ደማቅ ለማድረግ ከፈለግን እነዚህን ሁለት ነገሮች ማድረግ ነው ያለብን። 1. ባለፈው ሳምንት ያሳካናቸውን ስራዎችና ያሳለፍናቸውን አሪፍ የደስታ ጊዜዎች ማሰብ። 2. የአሁኑም ሳምንት ከባለፈው የተሻለ እንደሚሆን ብዙ ነገር እንደምናሳካበት ማሰብና ይሄን ለማድረግ ሰኞ ላይ ከኛ ሚጠበቀውን ስራና ሀላፊነት በአሪፉ ከተወጣን እንደሆነ አምኖ መጀመር። የተዋበ ምሽት ተመኘን🙏 የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

እንዳንሳሳ ! ልብስ ቢቆሽሽ ይታጠባል፣ ትንሽ ጊዜ ከቆየ ደግሞ በሌላ ልብስ ይተካል ግን እስክንሞት ድረስ አንድ ልብስ ብቻ መልበስ ቢኖርብን የምናደርገውን ጥንቃቄ አስቡት እስኪ? ያ አንድ ልብስ እንዳይቆሽሽ ስንጠነቀቅ፣ ከቆሸሸብን ደግሞ ስናጥበው እንዳይሳሳ ስንጠነቀቅ፣ በቃ በተቻለን አቅም እኛ ሳናልቅ እሱ ቀድሞ እንዳያልቅ እንጠነቀቃለን። የተሰጠን ህይወት እንደዚህ ልብስ ነው፤ ሌላ ተቀያሪ የለንም። ታዲያ ለምንድነው ግድየለሽ የምንሆነው? ሰዎች ምን ይሉኛል ብለን የማንፈልገውን የምናደርገው? አንድ አይን ያለው ሰውኮ በአይን አይቀልድም! የተሰጠንን የህይወት ዘመን የምንፈልገውን ለማሳካትና በደስታ ለማጣጣም መጠቀም አለብን። ጣፋጭ ምሽት ተመኘን🙏 የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ለመማር ስንዘጋጅ ! "ተማሪ ካለ ሁሌም አስተማሪ አለ" እውነት ነው እኛ ለመማር ዝግጁ ከሆንን አይደለም ከሰው ከእንስሳው እና ከግዑዝ አካላት የምንማረው ትልቅ ጥበብ አለ ! በየሄድንበት በያለንበት ቦታ ሁሉ አካባቢያችንን እናስተውል ምን እየተከናወነ እንደሆነ በንቃት እንመልከት እያንዳንዷ ነገር ታላቅ እውቀትን ታላብሰናለች ! የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

<< ብቸኝነት ሌላ ሰውን የምታጡበት ሁኔታ ሲሆን፣ ለብቻ መሆን ግን ራሳችሁን የምታገኙበት ሁኔታ ነው! >>

የእናንተ ማንነት ያ ነው! እግዚአብሔር ማን እንደሆነ ራሱን ያውቃል። አምላክ መሆኑ እንዲሰማው የእናንተ ምስጋና አያሻውም። እግዚአብሔር ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ እናንተ እንድትነግሩት አይጠብቅም። እግዚአብሔር የሚፈልገው ማን እንደሆናችሁ ማንን መምሰል እንዳለባችሁ እንድታውቁ ነው። እርሱ የሚፈልገው በእናንተ ሀጥያት ስር (ውስጥ) የተደበቀውን እውነተኛ ሰዉ ነው። የእናንተ የአዕምሮ ችሎታ (IQ) የእናንተን ማንነት መለካት አይችልም: ይህን ማድረግ የሚችለው እግዚአብሔር ነው። የእናንተ እውነተኛ የአዕምሮ ችሎታ (IQ) <መንፈስ ቅዱስ > ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር የሆነውን ይዛችኋል። ክርስቶስ ውስጣችሁ አለ። የእናንተ ማንነትም ያ ነው። ✍ ዶ/ር ማይለስ ሙንሮ... ዳኜ መላኩ እንደተረጎመው።

ሁኔታዎች አይገድቡህ ! የሰው ልጅ በሁኔታዎች አይገደብም በከባድ ሁኔታዎች ውስጥ አልፎ ስኬታማ የሆነ ብዙ የጀግንነት ተግባሮችን የፈፀመ አለ ! በጥሩ ሁኔታዎች አልፎ ደግሞ የሰነፈም አለ ስለዚህ ላለህበት ቦታ ያሳለፍካቸውን ችግሮች ሰበብ አታድርጋቸው እንደውም የበለጠ በርታባቸው ! ደስ የሚል ቀን ተመኘን 🙏 የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

🌿#የህይወት_ድንቅ_መልህቆች 7ናቸው! ከሰው ጋር በሰላም ለመኖር፣ ከራሳችን ጋር ሰላም ለመፍጠር፣ በስኬት ጎዳና ላይ ወደ ፊት ለመገስገስ የሚረዱ ሰባት የህይወት ህጎችን እንሆ- 1.ከትላንትህ ጋር ሰላም ፍጠር፤ አሁንህን እንዳይረብሽ። 2. ሌሎች ሰዎች በአንተ ዙሪያ ስላላቸው ሀሳብ ያንተ ሀላፊነት አይደለም። 3. ጊዜ ማይሽረው ቁስል የለም። 4. ደስታ በማንም እጅ ላይ አይደለችም፤ በአንተ እጅ እንጂ። 5. እራስህን ከሌሎች ጋር አታነጻጽር፤ ሰዎች ላይም አትፍረድ፤ ያለፉበትን የህይወት ውጣ ውረድ አንተ አታውቅም። 6. አብዝተህ መጨነቅህን አቁም፤ ለጥያቄዎች ሁሉ መልስ ሊኖርህ አይጠበቅብህም። 7. ፈገግ በል በዓለም ላይ ያለው ችግር በሙሉ ያንተ አይደለም።

አባትና ልጅ ተያይዘው ሽርሽር ሲሄዱ ከ አማኑኤል ሆስፒታል አጠገብ ይደርሳሉ። አባት ለልጁ ይህ የእብዶች ሆስፒታል ነው ብሎ ያሳየዋል። ልጅም አባቱን ማነው ሚጠብቃቸው? ብሎ ይጠይቀዋል። አባትም በር ለይ የቆሙትን ሁለት ኮስማና ዘበኞች ያሳየውና እነርሱ ናቸው ይለዋል። ልጁም ይገረምና ይህ ሁሉ እብድ ተባብሮ ቢመጣባቸው ምን ያደርጋሉ ? ብሎ እንደገና ይጠይቀዋል። አባትም የኮረኮሩት ያህል ይስቅና፦  እብዶች ምን ጊዜም ቢሆን ሊተባበሩ አይችሉም፤ ብሎ መለሰለት። https://t.me/INSPIRING_ETHIOPIA https://t.me/INSPIRING_ETHIOPIA

እኩል መታየትና እኩል መሆን ይለያያል !! አለማወቅ
እኩል መታየትና እኩል መሆን ይለያያል !! አለማወቅ

"እኔ እማቀው አለማወቄን ነው!!" ራሳችንን ሁሉን እንደሚያቅ አድርገን የምንቆጥር ከሆነ ከሰዎች ፣ ከህይወት ፣ ከውድቀታችን መማር አንችልም። ምንም አንደማናውቅ እንወቅ. ይህን የምንለውም ለትህትና ሳይሆን እውነቱን እንረዳ ምንም አናውቅም እናውቃለን ያልነው ነገር ራሱ ስህተት ሊሆን ይችላል። " ለመማር የሚፈልግ አላዋቂነቱን ይረዳ join us our chanale