cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ያሬዳውያን መንፈሳዊ የቅዱስ መርቆሬዎስ እና የቅድስት አርሴማ ማኅበር

ንሴብሖ ለእግዚአብሔር “ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው፥ ጥበብንም ያበዛል፤ ጽድቅንም አስተምረው፥ እውቀትንም ያበዛል።” — ምሳሌ 9፥9 “ድንጋጤ በድንጋጤ ላይ ይመጣል፥ ወሬም ወሬውን ይከተላል፥ ከነቢዩም ዘንድ ራዕይን ይሻሉ፤ ከካህኑም ዘንድ ትምህርት፥ ከሽማግሌዎችም ዘንድ ምክር ይጠፋል።” — ሕዝቅኤል 7፥26 በ https://www.tiktok.com/@yaredaweyan

Show more
Advertising posts
6 410
Subscribers
+8424 hours
+3717 days
+1 37330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Repost from N/a
Show all...
🛑ድንግል ቃል ኪዳንሽ / ዘማሪት መቅደስ ማርዬ/ mekdes marye/Ethiopia Orthodox mezmur

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱአምላክ አሜን 🚶‍♂️እንኳን ደህና መጡ👋የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የድሮና አዳዲስ መዝሙራት ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን like share subscribers በማድረግ ይጎብኙ።👥 ✅...

🙏 2
Repost from N/a
#ግንቦት_9 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ዘጠኝ በዚች ቀን የጻድቅ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ እናት #ቅድስት_ዕሌኒ አረፈች፣ ታላቁ አባት #አቡነ_ብፁዕ_አምላክ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅድስት_ዕሌኒ_ንግሥት ግንቦት ዘጠኝ በዚች ቀን የጻድቅ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ እናት ቅድስት ዕሌኒ አረፈች። ይቺም ቅድስት በፊት የአንድ ነጋዴ ሰው ሚስት ነበረች እርሱም በነገረ ሠሪ ንጽሕት ሁና ሳለች ወደ ባሕር ጣላት። የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ፈቃድም ሮሐ ከሚባል አገር ደርሳ የበራንጥያ ንጉሥ ቊንስጣ አገኛት። ውበቷንና ደም ግባቷንም አይቶ አገባት። ለክርስቲያን ነገሥታት መጀመሪያቸው የሆነውን ቈስጠንጢኖስን ወለደችው ምግባርንና ሃይማኖትን በማስተማር በመልካም አሳደገችው። ልጇም በነገሠ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ሒደሽ የክብር ባለቤት የሆነ የክርስቶስን መስቀል ግለጪ የከበሩ ቦታዎችንም ሥሪ የሚላትን በሕልሟ አይታ እንዴት እንዳየች ይህን ለልጇ ነገረችው እርሱም ከብዙ ሠራዊት ጋራ ሰደዳት።  በደረሰችም ጊዜ የክብር ባለቤት ስለሆነ ስለ ጌታችን መስቀል መረመረች አዳኝ የሆነ መስቀሉንም ሁለቱ ወንበዴዎች ከተሰቀሉባቸው መስቀሎች ጋራ አገኘችው። የክብር ባለቤት የክርስቶስ መስቀል የትኛው እንደሆነ ታውቅ ዘንድ በወደደች ጊዜ ከራሱ በላይ ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉሥ ነው የሚል በእንጨት የተቀረጸበት ጽሑፍ ያለው እንደሆነ የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ ቅዱስ መቃርስ ነገራት። ከዚህ በኋላ ከእርሱ ምልክት ታይ ዘንድ ፈለገች የሞተ ሰውም አግኝታ መስቀሎችን በበድኑ ላይ አኖረች አልተነሣም። ከዚህ በኋላ ሦስተኛውን መስቀል በላዩ አኖረች። ያን ጊዜ ምውት ተነሣ ሃይማኖቷም ጸና ደስታዋም በዛ። ከዚህ በኋላም ዜናቸው በመስከረም ወር በዐሥራ ሰባት የተጻፈ በከበሩ ቦታዎች ውስጥ አብያተ ክርስቲያናትን ትሠራ ዘንድ ጀመረች። ለአባ መቃርስም በከበሩ ቦታዎች ሁሉ አብያተ ክርስቲያናትን እንዲሠራ ብዙ ገንዘብ ሰጠችው። ከዚህ በኋላ ወደ ልጇ ተመልሳ የሆነውን ሁሉ ነገረችው የከበረ መስቀል በመገኘቱ እጅግ ደስ አለው። ይቺም ቅድስት በጎ ገድሏን ከፈጸመችና እግዚአብሔርንም ከአገለገለች በኋላ ስለ ካህናትም ልብስና ቀለብ ለአብያተ ክርስቲያናትና ለገዳማት ብዙ ጉልቶችና ርስቶችን ለድኆችና ለምስኪኖችም እንዲሁ ከሠራችና ከተከለች በኋላ በሰላም አረፈች መላ ዕድሜዋም ሰማንያ ሆነ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #አቡነ_ብፁዕ_አምላክ በዚህች ቀን ታላቁ አባት አቡነ ብፁዕ አምላክ ዕረፍታቸው ነው፡፡ እኚህ ጻድቅ የአባታቸው ስም ቅዱስ አፍቅረነ እግዚእ ሲሆን የእናታቸው ስም ደግሞ ቅድስት ማርያም ዘመዳ ሲባሉ በ1425 ዓ.ም መስከረም አንድ ትግራይ ክልል ልዩ ስሙ መከዳ በተባለ ቦታ ተወለዱ። እስከ ሰባት ዓመታቸው በእናትና አባታቸው ቤት ከኖሩ በኋላ በስምንት ዓመታቸው ወደ ደብረ ቢዘን ገብተው የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ሲማሩ በገዳማዊ ኑሮ ሲያገለግሩ ቆይ እስከ 25 ዓመታቸው ከቆዩ በኋላ በዛው በደብረ ቢዘን በ25 ዓመታቸው መነኵሰዋል። ከዚያም ወደ ደብረ ዳሞ ገዳም ገብተው ለአምስት ዓመታት ካገለገሉ በኋላ በድጋሚ በእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ ኤርትራ አገር ወደ መጀመርያ ወደ መሰረቱ ገዳም ደብረ ኰዳዱ ሔደው በአንድ ዋሻ ውስጥ ገብተው ሕማማተ መስቀልን በማሰብ በአንድ ሺህ ችንካሮች እራሳቸው ቸክረው ለ30 ዓመታት ሲጋደሉ ኖሩ። በዛው አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ለአብሃም እንደተገጹ ለእርሳቸውም በአንድነትና በሦስትነት ታኅሣሥ አንድ ቀን ተገለጡላቸው። እርሳቸው ሥላሴ መሆናቸው ለማረጋገጥ የቆሙበት ድንጋይ ለሦስት ቦታ ተከፈለ፤ እንደ ገና ደግሞ ተመልሶ ወደ አንድ ተለወጠ። በዚህ የተገለጡላቸው ሥላሴ እንደሆኑ አረጋገጡ ቃል ኪዳን ከገቡላቸው በኋላ መጨረሻ የሚያርፉበት ቦታ ነግረዋቸው ተሰወሩ ከዚያም ወደ ሁለተኛ ወደ መሰረቱት ገዳም ደብረ ምዕዋን ገብተው ብዙ ከተጋደሉ በኋላ ግንቦት 9 ቀን 1501 ዓ.ም በ76 ዓመታቸው ከእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ተቀብለው ዐርፈዋል። አጽማቸውም እስካሁን በዛው በደብረ ምዕዋን ይገኛል። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎትና ምልጃ ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት እና #ገድለ_ቅዱሳን)
Show all...
ናሁ ሰማን(Nahu seman)

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 🚶‍♂️እንኳን ደህና መጡ👋 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የቅዱሳን ስንክሳር የድሮና አዳዲስ መዝሙራት ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን like share subscribers በYouTube✅

https://www.youtube.com/@nahu-seman-zema25

በማድረግ ይጎብኙ።

Repost from N/a
ድንግል ቃል ኪዳንሽ      ድንግል ቃል ኪዳንሽ ሰውሮኛልና      ሳይታሰብ ወጣሁ ከአዳጋች ፈተና      ጸጋና ሞገስን ካንቺ በማግኜቴ      ሳመልጠው ተቆጨ ነደደ ጠላቴ ልዩ ስጦታዬ የመስቀሉ ቃል በማዕከለ ምድር አንቺ ነሽ ድንግል ከጣሪያዬ በታች ይዤሽ ብገባ በላይም ሆንሺልኝ ለነፍሴ አምባ    መነጠቂያ ምህዋሬ    ጠላት መምቻ ጽኑ በትሬ    የዓይኔ ስዕል ፅላሎቴ    መቅረዜ ነሽ እመቤቴ   */አዝ* ኪዳንሽ ተተክሎ ከፊት ለፊቴ ቀስቱን እያጠፈ ፀንቷል ጉልበቴ ከድንገተኛ ሞት ከአስፈሪ አደጋ ተሰውሬያለሁኝ ስላለሽ ከኔ ጋ    መደገፊያ መልህቄ    የሀይማኖት ድርብ ትጥቄ    ከሰይፍና መሰንዘሪያ    ስምሽ ሆነኝ መከለያ    */አዝ* የፋራን ተራራ መሸሸጊያዬ     ከሳዖል ፍላፃ ነሽ ማምለጫዬ ንጉሡ የፃፈሽ የክብር ፊደሌ ወደ ርስቱ መግቢያ ተስፋ መሰላሌ    የምህረት መቀነቴ    ፈትለ ፅሩይ ሞጣዕቴ    ሠረገላ ማማ ክንፌ    መዝገቤ ነሽ ምዕራፌ     ✥•┈•●◉ ናሁ ሰማን-ዜማ ◉●•┈•✥ ╭✥◉●•┈•✨◍❀◍●✨◉●•┈•✥╮ /╭✧✞ @Nahuseman256✞ ✧╮\ \╰✧ ✞ @Nahuseman256 ✞✧/ ╰✥◉●•┈•🌿◍❀◍●🌿◉●•┈•✥
Show all...
Repost from N/a
††† እንኳን ለእናታችን ቅድስት እሌኒ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† እሌኒ ንግሥት ††† ††† ቅድስት እሌኒ የታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ እናቱና እግዚአብሔር ለበጐ አገልግሎት የጠራት ቡርክት ሴት (ንግሥት) ናት:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- የቅድስቲቱ ሃገረ ሙላዷ ሮሃ (ሶርያ) አካባቢ ነው:: ነገዷ ከእሥራኤል ዝርዋን እንደሆነም ይነገራል:: ጣልያኖች "Helena" : በእንግሊዝኛው "Helen" ይሏታል:: እኛ ደግሞ "እሌኒ" እንላታለን:: ትርጓሜው "ጥሩ ምንጭ" : አንድም "ውብና ደግ ሴት" ማለት ነው:: ቅድስት እሌኒ በመልካም ክርስትና አድጋ እንደ ቤተ ክርስቲያን መተርጉማን ተርቢኖስ የሚባል ነጋዴ አግብታ ነበር:: ወቅቱም ዘመነ ሰማዕታት ነበር:: በማይሆን ነገር ጠርጥሮ ባሕር ላይ ጥሏት ንጉሥ ቁንስጣ አግኝቷታል:: እርሱም የበራንጥያ (የኋላዋ ቁስጥንጥንያ) ንጉሥ ነበር:: ቅድስት እሌኒ ከቁንስጣ የተባረከ ልጅን ወለደች:: ቆስጠንጢኖስ አለችው:: በልቡናው ፍቅርን : ርሕራሄን : መልካምነትን እየዘራች አሳደገችው:: ቅዱሱ አባቱ በሞተ ጊዜ ተተክቶ ነገሠ:: ቅድስት እሌኒንም ንግሥት አደረጋት:: ያንን የአርባ ዓመት ግፍ በአዋጅ አስቀርቶ ለክርስቲያኖች ነፃነትን : ክብርን በይፋ ሰጠ:: አንድ : ሁለት ብለን የማንቆጥረውን ውለታ ለምዕመናን ዋለ:: ከነዚህ መልካም ምግባራቱ ጀርባ ታዲያ ቅድስት እናቱ ነበረች:: ቅድስት እሌኒ ጾምን : ጸሎትን ከማዘውተሯ ባሻገር አጽመ ሰማዕታትን ትሰበስብ : አብያተ ክርስቲያንን ታሳንጽ : ለነዳያንም ትራራ ነበር:: በኢየሩሳሌምና አካባቢው ብቻ ከሰማንያ በላይ አብያተ መቃድስ አሳንጻለች:: እነዚህንም በወርቅና በእንቁ ለብጣቸዋለች:: በዘመኗ መጨረሻም የጌታችንን ቅዱስ ዕፀ መስቀል ከተቀበረበት አውጥታ ለዓለም በረከትን አስገኝታለች:: እናታችን ቅድስት እሌኒ እንዲህ በቅድስና ተመላልሳ በሰማንያ ዓመቷ በ330ዎቹ አካባቢ ዐርፋለች:: ቤተ ክርስቲያናችንም ስለ ቅድስናዋና ውለታዋ በዓል ሠርታ : ታቦት ቀርፃ ስታከብራት ትኖራለች:: ††† ከቅድስት እናታችን ምልጃና በረከት አምላካችን ያድለን:: ††† ግንቦት 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅድስት እሌኒ ንግሥት 2.ቅዱስ ስልዋኖስ ††† ወርኀዊ በዓላት 1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ሁሉ አባት) 2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮጵያዊ) 3.ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ) 4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን 5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮጵያዊ) 6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት) ††† "ነገር ግን ለበጐ ነገር ጥበበኞች : ለክፉትም የዋሆች እንድትሆኑ እወዳለሁ:: የሰላምም አምላክ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ፈጥኖ ይቀጠቅጠዋል:: የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን::" ††† (ሮሜ. ፲፮፥፲፱) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
Show all...
ናሁ ሰማን(Nahu seman)

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 🚶‍♂️እንኳን ደህና መጡ👋 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የቅዱሳን ስንክሳር የድሮና አዳዲስ መዝሙራት ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን like share subscribers በYouTube✅

https://www.youtube.com/@nahu-seman-zema25

በማድረግ ይጎብኙ።

እግዚአብሔር የማመስገን ግዴታ አለብኝ 🤲🙏 ✍በውስጥ መስመር በጠየቃችሁት መሰረት ያስተምሯችኋል የምትሉአቸውን TOP  የቴለግራም ቻናል ይዘን መተናል መርጠው ይቀላቀሉ🙏             ይ🀄️ላ🀄️ሉ ይማሩ                   👇🏾👇🏾👇🏾 https://t.me/addlist/AQPOMxHXz_42NDE0
Show all...
የመዝሙሮች ግጥም
የኦርቶዶክስ ምስለ አድኖ
የኦርቶዶክስ ስብከት
ስንክሳር
የኦርቶዶክስ የዝማሬ መድብል
ይ🀄️ላ🀄️ሉ
ከሰባቱ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን ውስጥ የማይመደበው የቱ ነው ?
Show all...
ምስጢረ ቀንዲል
ምስጢረ ሥጋዌ
ምስጢረ ሜሮን
ምስጢረ ተክሊል
​​👼 ቅዳሴ ማለት ምንም ማለት ነው? 🤔 በቅዳሴ ጊዜ 5ቱ ምሥዋዕቶች ምን ምን ናቸው? 🥰 14ቱ ፍሬ ቅዳሴያት እነማን ይሆኑ? 😇 ካህናት በቅዳሴ ወቅት 2: 3: 4: 5: 7: 12: ወይም 24: ሆነው ከቀደሱ ምሳሌነቱ ምን ምን ይሆን? 🧎‍♂ እኛ ክርስቲያኖች ቅዳሴን ባስቀደስን ቁጥር 4 ነገሮች እናገኛለን ምን ይሆኑ? 👼 አምስቱ የስሜት ሕዋሳት በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ያስቀድሳሉ እንዴት?             ይ🀄️ላ🀄️ሉ ይማሩ                   👇🏾👇🏾👇🏾 https://t.me/addlist/AQPOMxHXz_42NDE0
Show all...
ሙሉ ትምህርት ለማግኘት
የቅዳሴ ተሰጥኦ ትምህርት
ይግቡ ይማሩ