cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

HOME || ቤት 🏚

Advertising posts
884
Subscribers
No data24 hours
+47 days
+1430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Let's just hope we will meet again, my lovely people! 💛🌼
Show all...
❤ 22👍 2
ዛሬ እሁድ ነው! በጠዋት ተነሱ፣ ሙቅ ሻወር ውሰዱ፣ ቀለል ያለ ቁርስ ብሉ [Preferably ሽሮ ፍትፍት for your hangover 😅 ጁስ ጠጡ ስትባሉ አትሰሙ መቼስ]፣ በእጣን የታጀበ ቡና እየጠጣችሁ የዳዊት ቸርነትን "ጽዮን" ስሙ፣ ከዚያ ቤተክርስቲያን ሂዱ። አንቂያችሁ ዮናታን ነኝ ከሐዋሳ ጊዜያዊ የስርጭት ጣቢያ። ደስ የሚል ቀን አሳልፉ! 💙
Show all...
❤ 15👍 4
[ A Hymn About Hymn 🎶 ] እሱ ንጉሡ ዝምታ ቢሆንም ፥ አንዳንዴ ምላሹ ቅኔ ነው ጠረኑ ፥ ግጥም ነው ትንፋሹ ሲሰባበር ልቤ ፥ ስከፋበት ልጁ ዳስሶ ሚያፅናናበት ፥ ሙዚቃ ነው እጁ!
Show all...
❤ 20
አሁን ማምሻውን ቁጭ ብዬ ያሉብኝን ዕዳዎች ከደማመርኩ በኋላ የመኖር ምክንያቴ ሁላ ጠፋብኝ። በቃ ዛሬ ለሊቱን በሙሉ "ማራናታ" እያልኩ ስፀልይ የማድር ይሆናል! #ወይ_ምጣ_ወይ_ልምጣ
Show all...
😁 25👎 1
My bad, my bot wasn't working - AGAIN! I don't know why it kept stop working. It's now fixed tho 😎 አስተያየት፣ ምክር፣ ሃሳብ፣ ቁጣ፣ ዛቻ፣ ማስፈራሪያ እና የ"ታገባኛለህ ወይ?" ጥያቄ ካላችሁ @yonis_home_bot ላይ መገናኘት እንችላለን 😅 Thank you again for being here and be the part of our home! @yonis_home_bot
Show all...
😁 5👏 1
በነገራችን ላይ ይኼን ሁሉ የምለው ራሱን ከሁለቱም ወገን እንደሆነ እንደማይቆጥር፣ የደረጀ ስነ-መለኮታዊ ንባብ እና ትምህርት እንደሌለው፣ ነገሮችን እንደሚታዘብ እና ጣቱን መጠቆም እንደሚወድ፣ ቸርች መሄድ እንደሚደብረው አንድ ሰነፍ፣ ነጭናጫና ተራ layman ሰው ነው። ካጠፋሁ እታረማለሁ... 🚶‍♂️
Show all...
❤ 7👍 1😁 1
[ ካልቪን ወይስ ጃፒ ] አንድ በጌታም በእኔም የተወደደች እህት ነበረች ( አሁን ግን የጌታን እንጃ በእኔ ግን የተወደደች አይደለችም 😅 ) በተገለጠልኝ መጠን መኃልየ መኃልየን እየጠቀስኩ በቅዱስ መጀንጀን እጀነጅናት ነበር። ያው የጴንጤ ጅንጀና ፒዛ ብቻ ሳይሆን ቸርች መጋበዝንም ያጠቃልላልና ለፒዛው የሚሆን ገንዘብ እስካገኝ ቸርች ጋበዝኳት። እሷ አዘውትራ የምትሄደው የሞክሼዬ የፓስተር ዮናታን ቸርች ነው። ከእኔ ይልቅ ያኛው ዮናታን ይመቻች ነበር (የዛሬን አያድርገውና "ቢያንስ እኔ ፀጉር ስላለኝ እኔን መምረጧ አይቀርም" እያልኩ እፅናና ነበር ) አልፎ አልፎ ደግሞ ሲላት ፓስተር ተዘራ፣ ሲያሰኛት ፓስተር ጃፒ ቸርችም ቤተኛ ነበረች። እኔ ደግሞ አዘውትሬ ቸርች ባልሄድም ከሄድኩ ግን የምሄደው ተኀድሶአውያኑ (Reformist Church) ጋር ነውና አብረን እንሂድ አልኳት። "የት ቸርች ነው?" ብላ የምንሄድበትን ቸርች ስም ጠየቀችኝ። ኮራ ብዬ ስነግራት የመለሰችልኝ መልስ እስካሁን እያናደደ ያስቀኛል። "አይ እዚያ ቸርች የስህተት ትምህርት ያስተምራሉ ይባላል ስለዚህ አልሄድም" አለችን ፈጠጥ ብላ። "ይልቅ ጃፒ ቸርች እንሂድ እስኪ ዮኒ ተጋብዟል ይሄን ሳምንት" ብላ ጭራሽ ልትጋብዘኝ ከጀላት። ኧረ ምኗን ድፍን ጣለብኝ! ይኼን ቃሏን ጃፒ ራሱ ቢሰማ በዚያ ግርማ ሞገስ ባለው ሳቁ ሆዱን እስኪያመው (😅) መሳቁ አይቀርም ነበር። ከዚያን ቀን ጀምሮ ይህቺን የስህተት ቁንጅና ያላትን እንስት መጀንጀን አቆምኩ (የስሕተት ጅንጀና የለም ያለው ማነው? 😅) ነገር ግን ይህቺ አንድ ፍሬ ልጅ አብዛኛውን ፕሮቴስታንት የምትወክል ስለመሰለኝ ልረሳት አልቻልኩም። እርግጥ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ የወንጌላውያን ክርስትና ከጴንጤቆስጤያዊነት ጋር ያለቅጥ ስለተዛነቀ ስሙሩ አስተምህሮ ጴንጤቆስጤያዊነት ብቻ የሚመስለው አማኝ ጥቂት አይደለም። ጴንጤቆስጤያዊው ክርስትና ሁላችንም በአንድም በሌላም መንገድ ጥቂትም የምትጠቅም ነገር ያገኘንበት ቢሆንም እንኳን ለብዙ ስኁት ምሁራን ምንጭ ብቻ ሳይሆን መጠጊያና መጠለያ ዣንጥላ እየሆነም ነው። ይበልጥ የሚገርመው ነገር ደግሞ ጴንጤቆስጤያውያኑም ለአስተምህሮታቸውና ለልምምዶቻቸው ቀይ መስመር አስምረው ድንበር ከማበጀትና በውስጣቸው ራሳቸው ለምድ ያለበሷቸውን የገዛ ራሳቸውን ተኩላዎች ከማኅበራቸው "ውጉዝ ከመአርዮስ" ከማለት ይልቅ ከልምምዶቻቸው የሚቀዱ ስርዓቶቻቸውን ከቀኖና በመቁጠር ተኀድሶአውያኑን ሲኮንኑ እና ሲያጣጥሉ ይታያል። ቅርብ ጊዜ እንኳን ጥቂት የካልቪኒዝምን ሀሳቦች እያነሱ ስህተት እንደሆኑ ሊያሳዩ የሞከሩ ወንድሞች ነበሩ። በእውነቱ በአንድ ጎኑ ስናየው ቢያንስ ካልቪንን የሚያውቅ ትውልድ መነሳቱም ይበል የሚያሰኝ ነው 😅 ደግሞ እንደሰለጠነ ሰው የሀሳብ ፍትጊያ እና ኅየሳ መኖሩ ስልጣኔ መሆኑም የጠፋኝ ሞኝ ቢጤም አይደለሁም (ማለቴ ሞኝ እኮ ነኝ ግን ያን ያህል ሞኝ አይደለሁም 😅 ወይም ጅል እንጂ ጅላጅል እና ጅላንፎ አይደለሁም ( በእርግጥ ጅል፣ ጅላጀል እና ጅላንፎ እያለ ለጅልነት ደረጃን ከሚመድብ ሰው በላይ ጅልም፣ ጅላጅልም፣ ጅላንፎም አለ ብዬ አላስብም 😅🚶‍♂️)) ነገር ግን እነዚህ በደምሳሳው በሪፎርምድ ማኅበረ-ምዕመናን በተለይም በካልቪኒዝም ላይ የሚነሱ ሰሞናዊ ትችቶች ቢያንስ ለእኔ በሁለት ምክንያት ውሃ የማያነሱ ናቸው። አንድም ሁሉንም ባይሆኑ ከአብዛኛዎቹ ተቺዎች ቁንፅል እውቀት የሚመነጭ ቅሬታ ነው። ብዥታ የሚፈጥሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባትን ፍቺ በቅጥ ሳይረዱ፣ በምንባባቱም ላይ የሚነሱ አማራጭ እና አከራካሪ ትርጓሜዎችን ከግምት ሳያስገቡ የመጽሐፉን መልዕክት እጅ እየጠመዘዙ ለገዛ ምኞት በማስገዛት ከየት እንደመነጨ በማይታወቅ "ሐዋርያዊ" በሚመስል ሥልጣን ማውገዝ ምንም ሳይሆን ንፁሕ አለማወቅ ወይም ፒዩር ኢግኖራንስ ነው ብንል ድፍረት አይሆንብንም። ማለቴ አለማወቅ እኮ ኖርማል ነው (ልክ ባይሆንም ኖርማል ነው 😅 አታየኝም እኔ ምንም ሳላውቅ ስቀባጥር 😂) ግን አለማወቅን ሳያውቁ ነጠላ ጥቅስ መዞ "ካልቪኒዝም የስህተት ትምህርት ነው" ብትል እንኳን እኔ አባታችን Jacobus Arminius ራሱ ይስቅብሀል። ብዙ ነገሮችን ብንክድ እንኳን ካልቪኒዝም በአስተምህሮት እጅግ የደረጀ፣ አስተምህሮቱንም ያደረጁልን የቤተክርስቲያን አባቶች በቤተክርስቲያን ታሪክ አንቱ የተባሉ መሆናቸውን መረዳት እና እውቅና መስጠት ያስፈልጋል። ሲቀጥል ደግሞ የፕራዮሪቲ ጉዳይ ይነሳል። የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት በሞራል፣ በአስተምህሮ፣ በልምምድ መዝቀጥ ውስጥ ሆና ሳለ ሌሎች ልትጨነቅባቸው የሚገባቸው እንደአሸን የፈሉ ዝንፈቶች እያሉ ካልቪን፣ ካልቪኒዝም እና ካልቪኒስቶች ላይ ዘመቻ መክፈት እንኳን ጥቅም ሊኖረው ጉዳቱ እጅግ ብዙ ነው። እስካሁን ባለኝ ውስን እና ጠባብ ምልከታም ቢሆን በተኀድሶአውያኑ አብያተክርስቲያናት ውስጥ ያየሁትን ያህል ተስፋ በሌላ ማኅበረ-ምዕመናን ዘንድ አላየሁም። ለስሙር ፍታቴ ያላቸው አቋም፣ ለቃሉ ያላቸው መገዛት እና መታዘዝ፣ ለአስተምህሮ፣ ለሐዋርያት ሥልጣን መገዛት፣ ለልምምድ ወጥነት፣ ለቤተክርስቲያን አደረጃጀት፣ ለወንድማማች ኅብረት እና ለሳክራመንቶች የሚሰጡት ትኩረት ጥቂትም ቢሆን ተስፋ ስለሚያጭር በክርስትና እና በቤተክርስቲያን እንዲሁም በራሴ ጭምር ተስፋ እንዳልቆርጥ ያደረገኝ ብቸኛው ነገር ነው። እንደው ነገሩን እንለጥጠው ካልን አብዛኛው ወንጌላዊው አማኝ እንደ ዐይኑ ብሌን የሚሳሳላቸውን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችና ልምምዶች በዚህ ዘመን እንደቆሙ ስለሚያስተምር በአብዛኛው አማኝ ዘንድ እንደ ስህተት የሚቆጠረው እና የሚፈራው ሴሴሽኒዝም (ቆሟል'ኢዝም) ራሱ በወንጌላውያኑ ዘንድ ቢያንስ ሊከበርና እንደ አንድ ሴክት ዕውቅና ሊሰጠው ይገባል ባይ ነኝ። በእኔ ዕይታ (በእኔ ዕይታ የሚለው ይሰመርበት) አማኙ እንደሚፈራው ሳይሆን ከሴሴሽኒዝም ይልቅ ካሪዝማዊነት ለቤተክርስቲያን አደጋ እየሆነ ነው። እንደው ነገሩን አከረርከው አትበሉኝና ካሪዝማዊነት እየተሰጠው ያለው የተጋነነ ቦታ ካልቀነሰና ከሴሴሽኒስቶቹ ልምድ ካልተቀሰመ ቤተክርስቲያኒቱ ያለችበት መዝቀጥ እዚህ ላይ የሚቆምም አይመስልም። በሀገራችን ለብዙ መዳን እና መታነፅ ምክንያት እንደነበር የማንክደው ካሪዝማዊው እንቅስቃሴ ከቃሉ ባልተናነሰ ሁኔታ ለግል ልምምዶች ቦታ ስለሚሰጥ፣ ለቃሉም ሆነ ለቤተክርስቲያን ታሪክ ባዕድ ለሆኑ ከጥንታዊ ጥንቆላ ነክ ልምምዶች ጋር ለተዳቀሉ ዘመን-ወለድ ዲቃላ ባህሎች ያስቀረው ቦታ ስላለው፣ በመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎችና በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች መሀከል ያለውን ሚዛን መጠበቅ እየከበደው ብዙውን ጊዜ ሲያነክስ ስላየነው፣ "እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናገረኝ" በሚሉ ሰዎችና በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መሀከል ራሱ ያሰመረውን ቀጭን መስመር ራሱ መለየት ስለሚከብደው ካሪዝማቲካዊው ክርስትና ራሱን መፈተሽና አስተምህሮቱንም ማጥራት ያለበት ይመስላል። [ የተወሰኑ ካሪዝማዊያን "ጥቂት ሰዎች ካሪዝማዊ እንቅስቃሴዎችን ያለአግባብ ስለተጠቀሟቸው ጴንጤቆስጤያዊነት ስህተት ነው ማለት አይደለም። ይሄ ሕፃኑን ልጅ ከታጠበበው ውሃ ጋር አብሮ መድፋት ነው" ሲሉ ቆሟሊስቶቹ ደግሞ "ስለምን ሕፃን ነው የምታወሩት? ቆሻሻ እጣቢ ውሃ ብቻ ነው እንጂ ምንም አይነት ሕፃን እያየን አይደለም" ሲሉ ይወርፋሉ ]
Show all...
❤ 7👍 3👏 1
መጽሐፍ ጽፌ ስለማላውቅ መጽሐፍ ስለመጻፍ ብዙ ነገር ማለት አልችልም። ግን እርግጠኛ ሆኜ መናገር የምችለው ነገር መጽሐፍ መጻፍ ቀላል ነገር እንዳልሆነ ነው። ቀላል ቢሆን ኖሮ እስካሁን እጽፍ ነበር። መጽሐፍ ለመጻፍ ማሰቡ፣ ካሰቡ በኋላ መጻፉ፣ ከጻፉ በኋላ ማረሙ፣ ካረሙ በኋላ ማደርጀቱ፣ ካደረጁ በኋላ ማሳተሙ፣ ካሳተሙ በኋላ መሸጡ እጅግ ከባድ ትግል ነው። ውዷ እናኑ ግርማ ይህን ከባድ ትግል አሸንፋ "መቆያ" የተሰኘች ቆንጆ የወጎችና የአጭር ልቦለዶች ስብስብን ሰጥታናለች (መጽሐፍ "አንተ" ነው "አንቺ" የሚባለው ግን? 😅) መጽሐፏን አንቤው ነበር፤ ደስ ይላል! በጥቂት ገፆች ብዙ ነገርን አሳይታናለች። በደፋር ግን ለዛ ባለው ብዕሯ ከፍቅር እስከ ሀገር፣ ከሴትነት እስከ ሀይማኖት ብዙ ነገሮችን ተመልክታ ትጠይቃለች፣ ትመልሳለች፣ ትሞግታለች። እናኑ ጥሩ ጸሐፊ ብቻ ሳትሆን መልካም ስብዕና ያላት ብርቱ ሴት እንደሆነች መመስከር እችላለሁ። በዚሁ አጋጣሚ "እንኳን ደስ ያለሽ!" ልበላት እንጂ! እና የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 2 ከቀኑ 8:00 ጀምሮ የስዕል አውደርዕይን ጨምሮ ሌሎች ደስ በሚሉ ዝግጅቶች የደረጀ የመጽሐፍ ምረቃ ፕሮግራም በሀዋሳ ሳውዝ ስታር ሆቴል ይኖራል። ሀዋሳ ያላችሁ ወዳጆቻችን ኑና እናኑን "በአቦሉ እንዳስደሰትሽን ደግሞ በርቺና በቶናው ነይልን!" እያልናት አብረን ጥሩ ጊዜ እናሳልፍ። ቀን: ቅዳሜ ሰዓት: ከ8:00 ጀምሮ ቦታ: ሀዋሳ ሳውዝ ሰታር ሆቴል 💙
Show all...
❤ 8👍 2
[ For Your Sunday Night 👼 ] ልቡ እንዳበጠበት ፥ የፍየል ወጠጤ አደለበኝና ፥ ምግብና መጠጤ ካንተ ማር መርጬ ፥ ያለምን ኾምጣጤ ላልመስሰ ነበር ፥ እኔስ አወጣጤ! ለታይታ አሸርግጄ ፥ እንዲያው ወጉ እንዳይቀር የወረት ፍቅሬ አልቆ ፥ ፊትህ ስመናቀር ብዬ ፎነን ፎነን ፥ ብዬ ቆንጠር ቆንጠር ምኞት ከርሴን ነፍቶት ፥ ከአታሞ ሲወጠር ከስስ ቆዳዬ ስር ፥ መንፈሴ ደድሮ "እሽ አትበለኝ" ስልህ ፥ ልክ እንደሹም ዶሮ ይህቺ ትንሽ ልቤን ፥ ትዕቢት ወጥሯት በልክ የሰፋኸው ፥ መጎናፀፊያዋ አጥሯት "ደምህ ተረጭቶብኝ ፥ ልብሴን አቆሸሸው" ብላ አይደል ወይ ካንተ ፥ ከደጅህ ምትሸሸው? ተናንሶ እንደመኖር ፥ ለአንተ ተጎናብሶ ጭራሽ ታኮርፋለች ፥ ደግሞ ከሷም ብሶ እርቃን ውሎ አደረ ፥ ከአካሏ ገሚሱ ፈሪሳዊ ክብሩ ፥ አይደል በቀሚሱ? የገዛ ጉድጓዴን ፥ በእጆቼ ቆፍሬ እርግፍ እርግፍ ልል ፥ እንደ ሾላ ፍሬ በቃ ለዚሁ ነው ፥ እንዲያ መዳፈሬ? ከዚያች ጋር ስፋታ ፥ ይህቺን እያጨኹ በእግዚኦታ ፋንታ ፥ በቄንጥ አያፏጨኹ በግማድ መስቀልህ ፥ ጥርሴን እያሟጨኹ መልኬን አሳምሬ ፥ እንደ ወሎ ፈረስ ይሰማል ግሳቴ ፥ እስከ ሰማይ ድረስ! በመላ አሸነፍከኝ ፥ ማረከኝ አንተ ግን ገደልከኝ ልታድን ፥ ሰበርከኝ ልትጠግን ከተርሴስ ኩብላ ፥ እያዘናጋኸኝ ማዕበል ሆንክና ፥ ከሥሬ አናጋኸኝ እሳት ኾነህ ላፍከኝ ፥ ጦር ኾነህ ወጋኸኝ በሽንቁሬ በኩል ፥ ምስጢር አወጋኸኝ እንዳትንጠራዘዝ ፥ ደርሳ እንዳትኮፈስ ያበጠችው ልቤን ፥ አደረካት ተንፈስ የገዛ መሻቴ ፥ ወደሳት ሲልከኝ እንቅፋት ሆንክና ፥ አደናቅፈህ ጣልከኝ! "ጓንዴ ሳይወለውል ፥ ሳያነሳ መውዜር በዝምታው ብቻ ፥ ይጥልሃል እግዜር" ብዬ ተገርሜ ፥ ዛሬ ምተርተው ያፀናኝ በትርህ ፥ ልቤን ቢነርተው! በቀኝህ አለብላቢት ፥ በግራህ ዘንባባ ይዘህ ከእልፍኜ ፥ ከቤቴ ስትገባ በገረፍኩህ ጅራፍ ፥ መልሰህ ገረፍከኝ ከሺ መቅበዝበዜ ፥ ሰብረህ አሳረፍከኝ! አንተ ድርብ ደርሳን... ወርውረህ ምትወጋ ወግተህ የምትገድል ፥ ገድለህ `ምታስነሳ ልብን የምታቀልጥ ሳትባርቅ እንደ መድፍ ፥ ሳትጮህ እንደ አንበሳ ነህሳ ጀብደኛ ፥ ጀብድህ የተረሳ! በስምህ አትመህ ፥ ስሙን ያስረሳኸው መስቀልህ ላይ ሰቅለህ ፥ እጁን የበሳኸው ሁሉን ልዝገን ብሎ ፥ አያግበሰብስም የአንድ ቀን ሽንቆጣህ ፥ ከሲኦል አይብስም ከሥጋዬ አይከብድም ፥ ልዝቡ ቀንበሬ ሰባኪው ቢለጉም ፥ ሰበከኝ ሰንበሬ! ልክ እኔ ስጠፋ ፥ ተገኘልኝ ጽድቄ ካንተ ጋር ተነሳሁ ፥ ብቻዬን ወድቄ! ፨ ፨ ፨
Show all...
❤ 27👏 1😢 1
"መቅረዝ ሥነ-ኪን" እጅግ በጣም ደስ የሚል እና ስክን ያለ የስነ-ጽሑፍ መድረክ እንደሆነ ከዚህ ቀደም የመጣችሁ ታውቃላችሁ [ እስከዛሬ ያልመጣችሁ ደግሞ ይሄኛው መድረክ አሪፍ አጋጣሚ ነው! ] እና ይህ መድረክ ደስ የሚሉ መድረኮችን እያስኮመኮመን ይኸው አንድ ዓመት ሞልቶታል። እና የፊታችን ሀሙስ ተገናኝተን አዘጋጆቹን እያበረታታን አናከብርም ወይ? እንደምታዩት ወሳኝ ወሳኝ ሰዎች ይገኛሉ (እኔን ጨምሮ 😂) ቀን: የፊታችን ሀሙስ ጥር 23 ሰዓት: 11:00 ቦታ: ወመዘክር አዳራሽ (ብሔራዊ ትያትር ፊትለፊት በኢቲቪ ሕንፃ እና በብሔራዊ ባንክ መሀል ባለው መግቢያ ገባ ብሎ) መግቢያ: በነፃ 💙
Show all...
❤ 4👍 2