cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Haramaya University Hiwot Fana Comprehensive Specialized Hospital

Show more
Advertising posts
4 230
Subscribers
+3024 hours
+2677 days
+67730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

‹ፍረሽ ማን› ፕሮግራም አጠናቀው የጤና ትምህርት ዘርፍ ለተቀላቀሉ 677 (ስድስት መቶ ሰባ ሰባት) ተማሪዎች የመማር ማስተማር ሂደት ላይ ገለፃና ማብራሪያ ተሰጠ። በሐረማያ ዩኒቨርስቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ‹የፍረሽ ማን› ፕሮግራም ጨርሰው ጤናና ህክምና ትምህርት ዘረፍ ለመረጡ ተማሪዎች የመማር ማስተማር እና ስርዓተ ትምህርት ላይ ለተማሪዎች ገለፃ እና ማብራሪያ ተሰጥቷል። የጤና ትምህርት ዘርፍ በባህሪው የተለየ በሰውልጅ ጤና ላይ ሙሉ በሙሉ ያተኮረ በመሆኑ ተማሪዎች በፍላጎታቸው መርጠው የገቡ እንደመሆናቸው ሙሉ በሙሉ ትምህርታቸው ላይ ሊያተኩሩ ይገባል ሲሉ የሐረማያ ዩኑቨርሲቲ (ፍረሽማን) አዲስ ተማሪዎች ፕሮግራም ዳይሬክተር ጌታቸው ተሾመ (ዶ/ር) አሳስበዋል፡፡ በየት/ት ቤቱ ስለሚሰጡ የትምህርት እና ምዘና ሂደቶች በሚገባ ማወቅና መገንዘብ ለቀጣይ ለሚኖራችሁ የትምህርት ቆይታ አስፈላጊ መረጃ ነው ሲሉ አቶ አዲሱ አለሙ ቺፍ አካዳሚክ እና ምርምር ዳይሬክተር ተናግረዋል። በሐረማያ ዩኒቨርስቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ የትምህርት ጥራት ምዘና ተባባሪ ዳይሬክተር ፤ የስርዓተ-ፆታ ተባባሪ ዳይሬክተር ፤የሪጅስተራል ፅህፈት ቤት ተባባሪ ዳይሬክተር የተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ሁለንተናዊ ተሳትፎ እንዲኖራቸው እና የውጤት እና ምዝገባ ሂደቶች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ደረጃ ስለሚወስዷቸው ትምህርቶች ወጥ ስለሆነው የውጤት ደረጃ ስርዓተ ትምህርት እና አጠቃላይ የመማር ማስተማር ሂደት ላይ ፤ ምን ምን መሰረታዊ ጉዳዮችን ያካተተ ስለመሆኑም በሐረማያ ዩኒቨርስቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ የፋርማሲ ፤ኮምፕርሄንሲቭ ነርሲግ፤ሚድዋይፍሪ፤ ህብረተሰብ ጤና ፤ ሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ እና የህክምና ትምህርት ቤቶች ኃላፊዎች እና ተወካዮች ሰፋ ያለ ገለፃ ለተማሪዎቻቸው አድርገዋል፡፡ ከትምህርታቸው ጎን ለጎን ተማሪዎች እርስባራሳቸው የመደጋገፍ እና የመረዳዳት በጋራ ሆነው አነዱ የሌላው ባህል ቋንቋ ሚመማማሩበት ማህበራዊ ግዴታቸውን የሚወጡበት አጋጣሚዎች መኖራቸውን በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት እና የሴት ተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎች በቆይታቸው ዘርፉ የሚጠይቀውን ስነምግባር የተሞላበት ትጉህ ተማሪ መሆን እንደሚገባቸው ተመላክቷል። የትምህርት አሰጣጡ ችግሮችን መፍታት ላይ ባተኮረ መልኩ የሚሰጥ መሆኑ እውቀትና ክህሎታቸው የዳበሩ ብቁ የጤና ባለሞያዎች ማፍራት ያስቻለ ነው ተብሏ። በዚህ መልኩ አጠቃላይ ከመማር ማስተማሩ ጋር ተያይዞ ባሉ ጉዳዮች ላይ ገለፃ መደረጉ ቀደም ሲል ጥያቆ እና ብዥታ የፈጠሩባቸውን እንደ ውጤት አያያዝ ላይ በቂ እና ግልፅ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ያነጋገርናቸው ተማሪ ሃናን ፈንታ ጫላ ሱፊያን ገልፀዋል፡፡ ኮሌጁ የትምህርት አሰጣጡ በተግባር የተደገፈ እና ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ሶስተኛ ዲግሪ በህክምናው እስፔሻሊስት እስከ ሰብ እስፔሻሊቲ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ያለ እና ላላፉት አመታት በርካታ ተማሪዎችን አስመርቆ ለአገር ብቁ ባለሞያዎችን በጤናው ዘርፍ ያበረከተ ተቋም መሆኑን አቶ አዲሱ አለሙ አስታውቀዋል። ግንቦት/2016 ዓ/ም የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ
Show all...
2👍 1
👍 1
(Colorectal Surgery) ከትልቁ አንጀት ጋር የተገናኙ ካንሰርን ጨምሮ ሌሎች ህመሞችን በቀዶ ህክምና የማከም አገልግሎት መስጠት ተጀመረ፡፡ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት ፋና ኮምፕርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለመጀመሪያ ጊዜ ከትልቁ አንጀት ጋር የተገናኙ ካንሰርን ጨምሮ ሌሎች ህመሞችን በቀዶ ህክምና የማከም አገልግሎት ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር መስጠት ተጀምሯል፡፡ በአገራችን የምስራቁ ክፍል ይህን መሰል የቀዶ ህክምና አገልግሎት ባለመኖሩ ህመሙ ያለባቸው ታካሚዎች ለከፍተኛ እንግልት ይጋለጡ እንደነበር እና አሁን ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሉ አገልግሎቱን በመጀመሩ ችግሩን ለመቅረፍ የሚያስችል መሆኑን ዶ/ር ቡርቃ መሀመድሳኒ የቀዶ ህክምና እስፔሻሊስት እና Colorectal Surgery ፕሮግራም ባልደረባ ተናግረዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሉ የላቀ እና ጥራት ያለው አዳዲስ የህክምና አገልግሎቶችን በማስጀመር በአካባቢው የጤና ቱሪዝምን ለማስፋፋት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ማሳያ ነው ተብሏል፡፡ የጨረር እና ኬሞ ቴራፒ ህክምናዎች በሆስፒታሉ መኖራቸው ከትልቁ አንጀት ጋር የተገናኙ ካንሰርን ጨምሮ ሌሎች ህመሞችን ጊዜውን በሚመጥን ቀዶ ህክምና አገልግሎት ለመስጠት እዲቻል ምቹ መደላድል መሆኑን ዶ/ር በዳሳ በየነ የቀዶ ህክምና እስፔሻሊስት እና Colorectal Surgery ፕሮግራም ባልደረባ ተናግረዋል፡፡ በሆስፒታሉ ከህክምናው ጎንለጎን የመማር ማስተማር ስራ የሚካሄድበት በመሆኑ Colorectal Surgery ፕሮግራም መጀመሩ ከታካሚዮች ባለፈ ለእስፔሻሊቲ ተማሪዎች የእውቀት ሽግግር የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡   ህመሙ ያለባቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት ፋና ኮምፕርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመምጣት አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ታወቋል፡፡ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ግንቦት /2016 ዓ/ም
Show all...
7👍 3
Yuunivarsitii Haramaayaa Hospitalaa hundaa galeessaa fi Addaa Hiwoot faanaattii tajaajilli kaansarii mari'imaan guddaa  (Colorectal Surgery ) waliin walqabatan dabalatee dhukkuboota biroo baqaqsanii wal’aanuun eegalameera. Yuunivarsiitii Haramaayaatti hospitaalli hundaa galeessa fi addaa Hiwoot faanaa yeroo jalqabaaf yuunivarsitii Jimmaa waliin ta’uun tajaajila wal’aansa baqaqsanii yaaluu  kaansarii mari'imaan guddaa  fi dhukkuboota biroo kennuu eegaleera. Akkaa bahaa Itiiyoophiyaatti  sababa hanqina tajaajila baqaqsanii yaaluu kun waan hin jireef  dhukkubsattoonni dhibee kanaan qabaman miidhaa fi baasii hamaaf kan saaxilamaa jiran yoo ta'u amma  garuu hospitaalli yunivarsiiti Haramaayaa hundaa galeessaa  fi addaa Hiwoot faanaa rakkoo kana  furuuf tajaajila kana eegaluun isaa naamootaa dhukkubaa kana  waaliin rakkachaa jiraani fi maatii isaaniif abdii fi boqqoonnaa   guddaa kan kennuu  ta’uu isaa ispeeshaaliistiin baqaqsanii yaaluu walii galaafi barumsaa wal’aansaa baqaqsanii yaaluu addaa kaanasrii mari'imaan guddaa  hordofaa kan jiran Doktoor Burqaa Mahammadiin himan. Hospitaallichii tajaajila wal‘aansa fayyaa haaraa sadarkaa olaanaa fi qulqullina qabu eegaluun akka bahaa biyyaattitii turizimii fayyaa guddisuuf hojiiwwan hojjetamaa jiran agarsiiftuu ta’uun himame. Akkasumaas hospitaalicha keessatti wal’aansi raadiyeeshiniifi keemooteraapii ykn wal’aansii kaansarii guutuun argamuun dhukkuboota kanneen akka kaansarii mari'imaan guddaa waliin walqabataniif tajaajila baqaqsanii yaaluu kennuudhaaf haalaa mijataa kan umuu ta’uu ispeeshaaliistiin baqaqsanii yaaluu walii galaa fi miseensi barumsa addaa baqaqsanii yaaluu kaansarii mari'imaan guddaa Doktoor Badhaasa   Baayyaana himaniiru. Dhuma irrattis jiraatoonnii naannoo fi haawaasni bal’aan wal’ansaa baqaqsanii yaaluu  kaansaarii mari'imaan guddaan wal qabataaniif yuuniivarsitii Haramaayaatti  Hospitaalaa hundaa galeessaa fi Addaa Hiwoot faanaa (Caaffee) deemuun argaachuu kan dandaa’an ta’uniis  himamera. Sab-qunnamtii alaa damee Kolleejii saayiinsi Fayyaa fi Wal'aansaa .
Show all...
👏 2👍 1
ቅድመ በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ላይ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት ፋና ኮምፕርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በእለት ተለት የሆስፒታል አገልግሎት እንቅስቃሴ የሚመነጩ ደረቅ እና ፍሳሽ ቁሻሻዎችን በተገቢው መልኩ በማስወገድ በሽታ አምጪ ተህዋሲያንን መከላከል እና ፅዱ አካባቢን መፍጠር በሚቻልባቸው አሰራሮች ላይ ተኩረቱን ያደረገ ለጤና ባለሞያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ በአገራቀፍ ደረጃ የጀርሞች ፀረ-ተህዋሲያን መድሀኒቶችን መላመድ ጉደይ አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን አስመልክቶ በሆስፒታሉ ላሉ ጤና ባለሞያዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና አስፈላጊ መሆኑን ዶ/ር አብዲ አሚን ቺፍ ክሊኒካል ዳይሬክተር በመክፈቻ ንግግራቸው ገልፀዋል፡፡   በሽታ አምጪ ተህዋሲያን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ አሰራሮች እና የጥንቃቄ መርሆች ትግበራ ላይ ባለሞያዎች የድርሻቸውን መወጣት እንደሚገባቸው እና ስልጠናው የአሰልጣኞች ስልጠና እንደ መሆኑ በስራቸው ላሉ የስራ ባልደረቦቻቸው ግንዛቤ ማስጨበጥ እንደሚኖርባቸው ዶ/ር አብዲ አሚን አስገንዝበዋል፡፡ የጀርሞች ፀረተህዋሲያን መድሀኒቶችን መላመድ በሆስፒታል አገልግሎት ላይ ከፍተኛ ጫና የሚፈጥር በመሆኑ መከላከሉ ላይ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን አክለው ገልፀዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሉ የደረቅ እና ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ ዳሰሳ ጥናት ተደርጎ በተለዩ ክፍተቶች ላይ የመፍትሄ እርምጃዎች መወሰዳቸውን እና በዚህም በአካባቢው ማህበረሰብ ይነሱ ለነበሩ ጥያቄ እና አስተያየቶች ምላሽ የሠጡ ተግባራት መከናወናቸውን በሆስፒታሉ በሽታ መከላከል እና የታካሚዎች ደህንነት ክፍል አቶ ደቻሳ አደሬ ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም ጥናቱ ላይ ተመስርቶ በሆስፒታሉ ላሉ 159 የተለያየ ስራ ክፍል ለሚሰሩ ሰራተኞች እና ጤና ባለሞያዎች ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች መሰጠቱን አሰታውቀዋል፡፡ ስልጠናው በስራ አካባቢያችን ላይ ብክለትን እንዳይኖር በማድረግ ለአገልግሎት ምቹ እንዲሆን እና የኛንም የታካሚዎቻችንን ደህንነት ለማስጠበቅ በተሰጠው ስልጠና መሰረት የበኩላችንን ለመወጣት  ያስችለናል ሲሉ የስልጠና ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡ ሰልጣኞች በየስራ ክፍላቸው የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ስራ ላይ ተጠሪ ሆነው የማስተባበር እና ግንዛቤ የማስጨበጥ ተግባራትን ማከናወን እንደሚጠበቅባቸው ተጠቁሟል፡፡ ግንቦት 1/2016 ዓ/ም የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ህዝብ ግንኙነት
Show all...
👍 4
Go to the archive of posts