cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Dr.banchi ዶ/ር ባንቺ🩺

እንኳን ደህና መጣቹ🙏 ይህ ስለ ጤናዎ ትክክለኛና የተረጋገጠ መረጃ የሚያገኙበት የዶ/ር ባንቺ ቻናል ነው። Join our channel👇👇👇 https://t.me/WtbEYXHQGR0wYTQ0

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
256
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

➕➕ ከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ ➕➕ 🖲 ቁጥራቸዉ ቀላል የማይባሉ ልጆች የዚህ የአፈጣጠር ችግር ይዘዉ ይወለዳሉ። የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ(cleft lip and palat) 🖲ወንዶች ላይ ከሴቶች በበለጠ የሚከሰት ሲሆን በግራ በኩል በብዛት ይከሰታል 🖲ከንፈር ወይም ላንቃ ብቻ ላይ ሲከሰት( isolated ) ሴቶች ላይ በብዛት ይከሰታል። 🖲ምክንያቱ በትክክል ይህ ነዉ ባይባልም የሚከተሉት ነገሮች በአጋላጭነት ይጠቀሳሉ 👉በዘር የሚተላለፍ (ተፈጥሯዊ ) 👉በርግዝና ጊዜ ለተለያዩ ቫዮረሶች እንደ Rubella virus መጋለጥ 👉በርግዝና ሰዓት አልኮል መጠጥ፣ሲጋራ ማጨስ 👉በርግዝና ጊዜ የሚከሰት የቫይታሚን ና ፎሊክ አሲድ እጥረት መጋለጥ 👉በርግዝና ወቅት የእናትዮዋ እድሜ መግፋት 👉በርግዝና ወቅት ከሀኪም ትዛዝ ዉጭ የሚወሰዱ መድሀኒቶች 👉ሌሎች አካባቢያዊ(enviromnenyal)ነገርች 🖲ከከንፈር ና ላንቃ መሰንጠቅ ጋር የሚከሰቱ ተጎዳኝ ችግሮች ✍️የአመጋገብ ችግር ።ጡት መጥባት መቸገር ✍️የጥርስ ችግር 👉የአፍንጫ ቅርፅ አለመስተካከል ና ተደጋጋሚ ለሆነ ላይኛዉ የመተንፈሻ አካል ኢንፌክሺንመጋለጥ ✍️ተደጋጋሚ የጆሮ ኢንፌክሺን ✍️አፍ መፍታትና የቋንቋ እድገት ችግር 🖲ይህ ችግር ያለባቸዉ ልጆች ጡት ለመጥባት ስለሚቸገሩ ለዚህ ተብለዉ የተዘጋጁ የጡጦ አይነቶች ስላሉ እነሱን መጠቀም ✍️ችግሩ በቀዶ ህክምና ስለሚስተካከከል ቶሎ ወደ ህክምና ቦታ መዉሰድ ማስተካከል ይቻላል 🖲የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ የብዙ የህክምና ባለሙያወችን ጥምረት 👉 የህፃናት ስፔሻሊ 👉ከአንገት በላይ ስፔሻሊስት 👉የፕላስቲክ ቀዶ ህክምና 👉የአፍና የጥርስ ስፔሻሊስት 👉የስነምግብ ባለሙያ ይፈልጋል 🖲በርግዝና ወቅት በቂ ክትትል በማድረግ፣አጋላጭ ነገሮችን በመቀነስ እንዳይከሰት መከላከል ይቻላል። ዶ/ር ዮርዳኖስ.መ
Show all...
➕➕ ከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ ➕➕ 🖲 ቁጥራቸዉ ቀላል የማይባሉ ልጆች የዚህ የአፈጣጠር ችግር ይዘዉ ይወለዳሉ። የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ(cleft lip and palat) 🖲ወንዶች ላይ ከሴቶች በበለጠ የሚከሰት ሲሆን በግራ በኩል በብዛት ይከሰታል 🖲ከንፈር ወይም ላንቃ ብቻ ላይ ሲከሰት( isolated ) ሴቶች ላይ በብዛት ይከሰታል። 🖲ምክንያቱ በትክክል ይህ ነዉ ባይባልም የሚከተሉት ነገሮች በአጋላጭነት ይጠቀሳሉ 👉በዘር የሚተላለፍ (ተፈጥሯዊ ) 👉በርግዝና ጊዜ ለተለያዩ ቫዮረሶች እንደ Rubella virus መጋለጥ 👉በርግዝና ሰዓት አልኮል መጠጥ፣ሲጋራ ማጨስ 👉በርግዝና ጊዜ የሚከሰት የቫይታሚን ና ፎሊክ አሲድ እጥረት መጋለጥ 👉በርግዝና ወቅት የእናትዮዋ እድሜ መግፋት 👉በርግዝና ወቅት ከሀኪም ትዛዝ ዉጭ የሚወሰዱ መድሀኒቶች 👉ሌሎች አካባቢያዊ(enviromnenyal)ነገርች 🖲ከከንፈር ና ላንቃ መሰንጠቅ ጋር የሚከሰቱ ተጎዳኝ ችግሮች ✍️የአመጋገብ ችግር ።ጡት መጥባት መቸገር ✍️የጥርስ ችግር 👉የአፍንጫ ቅርፅ አለመስተካከል ና ተደጋጋሚ ለሆነ ላይኛዉ የመተንፈሻ አካል ኢንፌክሺንመጋለጥ ✍️ተደጋጋሚ የጆሮ ኢንፌክሺን ✍️አፍ መፍታትና የቋንቋ እድገት ችግር 🖲ይህ ችግር ያለባቸዉ ልጆች ጡት ለመጥባት ስለሚቸገሩ ለዚህ ተብለዉ የተዘጋጁ የጡጦ አይነቶች ስላሉ እነሱን መጠቀም ✍️ችግሩ በቀዶ ህክምና ስለሚስተካከከል ቶሎ ወደ ህክምና ቦታ መዉሰድ ማስተካከል ይቻላል 🖲የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ የብዙ የህክምና ባለሙያወችን ጥምረት 👉 የህፃናት ስፔሻሊ 👉ከአንገት በላይ ስፔሻሊስት 👉የፕላስቲክ ቀዶ ህክምና 👉የአፍና የጥርስ ስፔሻሊስት 👉የስነምግብ ባለሙያ ይፈልጋል 🖲በርግዝና ወቅት በቂ ክትትል በማድረግ፣አጋላጭ ነገሮችን በመቀነስ እንዳይከሰት መከላከል ይቻላል። ዶ/ር ዮርዳኖስ.መ
Show all...
➕➕ በመሳሳም የሚተላለፍ በሽታ አለ?➕➕ 🖲 ከንፈር ለከንፈር በመሳሳም ግዜ የሚኖር የምራቅ ንክኪ፣ በምራቅ ውስጥ የሚገኙ እና የመተላለፍ አቅም ያላቸው ጥቃቅን ህዋሳትን ማስተላለፍ ይቻላል። 🖲በአንድ ሰው ምራቅ ውስጥ ብዙ አይነት ጥገኛ ህዋሶችን ማግኘት ይቻላል 🖲የመተንፈሻ አካልን የሚያጠቁ እንዲሁም የውስጥ ደዌ የበሽታ አምጪ ቫይረሶችን ከተበከለ ሰው ምራቅ ላይ ማግኘት የሚቻል ሲሆን 🖲ከዚህ ውስጥም ከ 40 በላይ አይነት ያላቸው በሽታ አምጪ ቫይረሶች ከተበከለና በሽታው ካለበት ሰው ምራቅ ውስጥ ይገኛሉ። 🖲በምራቅ እና በቆዳ ንክኪ የመተላለፍ አቅም ያላቸው በሽታ አምጪ ቫይረሶች የመተላለፍ አቅማቸው፣ በአይነታቸው፣ በአፍ እና በከንፈር ዙሪያ ቁስለት መኖር፣ ተጓዳኝ ስር ሰደድ የውስጥደዌ በሽታዎች መኖር እና በተፈጥሮ ሁኔታ ይወሰናል። 👉የኪንታሮት ቫይረሶች  (HPV እና MC) 👉የምቺ ቫይረስ (HSV 1 እና 2) 👉የመተንፈሻ አካል አጥቂ ቫይረሶች ( Corona, RSV, EBV Adeno virus, Influenza.. etc) የመሳሰሉት የቫይረስ አይነቶች፣ ከሰው ወደሰው በትንፋሽ ፣ መሳሳምን ተከትሎ የሚኖር የምራቅ እና የቆዳ ንክኪ ምክኒያት የመተላለፍ አቅም አላቸው። 🖲ከነዚህ ውስጥ በዋነኝነት ከንፈር ለከንፈር መሳሳምን ተንተርሶ በመተላለፍ የሚታቅ የቫይረስ አይነት አለ 🖲Epstein–Barr virus (EBV) ወይም የመሳሳም ቫይረስ በመባል ይታወቃል 🖲ይህም ቫይረስ በአፍ ቆዳ ውስጥ ስለሚራባ ፣ መሳሳምን ተንተርሶ የምራቅ ንክኪ ሲኖር በቀላሉ ይተላለፋል። 🖲ይህ ቫይረስ በየትኛውንም የእድሜ ክልል ያለ ሰውን የማጥቃት አቅም ያለው ሲሆን፣ ባብዛኛው ያለው ስርጭት በታዳጊ ወጣቶች ላይ ነው 🖲በዚህ ቫይረስ የተጠቃ ሰው ላይ አነስተኛ ትኩሳት ድካም እና የጡንቻ ህመምን ተከትሎ የሚመጣ የጉሮሮ እና የቶንሲል እብጠት እና ህመም ሊያጋጥም ይችላል። 🖲ይህ ቫይረስ ታዲያ ጤናማ የበሽታ መከላከል አቅም እስካለና ለተጓዳኝ ኢንፌክሽን እስካላጋለጠ ድረስ በራሱ የመዳን አቅም ያለው ቢሆንም 🖲በነጭ የደም ህዋስ ውስጥ የመደበቅ አቅም ስላለው የበሽታ መከላከል አቀም ባነሰ ግዜ በግዜ ሂደት ለካንሰር በሽታዎችም የመዳረግ አቅም አለው። 🖲ከዚህ ውጪ ያሉ በሽታ አምጪ ቫይረሶች፣ ማለትም፣ 👉የ ጉበት ቫይረስ  (HepV B,C) 👉የ HIV ቫይረስ 👉የጉድፍ እና አልማዝ ባለጭራ ቫይረስ (VZV) የመሳሰሉት እና ሌሎችም ቫይረሶች ፣ ምንም እንኳን ከተበከለ ሰው ምራቅ ውስጥ የሚገኙ ቢሆንም፣ ነገርግን ከሰው ወደሰው የመተላለፍ አቅማቸውን የሚያሳይ ተጨባጭ መረጃ የለም።
Show all...
➕➕ ኮፍያ ፀጉርን ይመልጣል እንዴ?➕➕ 🖲ኮፍያ ማድረግ ፣ፀጉርን፣ የራስ ቅልን እና የፊት ቆዳን ካላስፈላጊ የፀሀይ ጨረር በመከላከል፣ የፀሀይ ጨረርን ተንተርሰው ከሚመጡ የቆዳ ላይ ችግሮች አንዱ መከላከያ  መንገድ። 🖲ኮፍያ በቀጥታ ፀጉርን እንደሚመልጥ የሚያመላክቱ በቂ ጥናቶች የሉም። ነገርግን ንፅህናው የማይጠበቅ፣ የራስ ቅልን አጥብቆ የሚይዝ እና አየር የማያስገባ ኮፍያ ለረጅም ግዜ ማዘውተር የፀጉር እና የራስቅል ቆዳ ላይ የጤና ተፅእኖ ያሳድራሉ። 🖲ሆኖም ግን፣ ራሰ በረሀነት እና የፀጉር መሳሳት፣ ኮፍያ ማድረግን ብቻ ተንተርሰው የሚመጡ ችግሮች ሳይሆኑ፣ በተጓዳኝ ችግሮች ማለትም። 👉በዘር ራሰ በርሀነት ካለ፣ 👉የምግብ እጥረት መኖር 👉የደም ማነስ ፣ 👉ራስ ቅል ላይ በበሽታ አምጪ ተህዋስና በተፈጥሮ የሚመጣ ቁጣ ካለ፣ 👉እንዲሁም አንዳንድ የውስጥ ደዌ በሽታዎች እና፣ 👉የራስ ቅል ላይ የሚደርስ የጨረር የኬሚካል እና የሳት አደጋ መኖር ፣ እና የመሳሰሉ ምክኒያቶች፣ ለፀጉር መሳሳት ፣ መበጣጠስ እና መመለጥ የሚዳርጉ የተወሰኑ ምክኒያቶች ናቸው። 🖲ታዲያ ወደ ፀሀይ ሲወጣ ብቻ ከፍያን እንዲሁም ጃንጥላን በመጠቀም፣ ወይም ደሞ ወደፀሀይ ከመወጣቱ  ከሠላሳ ደቂቃ በፊት ቀደም ብሎ ለቆዳ አይነት የተስማማውን የፀሀይ መከላከያ ክሬም ተቀብቶ መውጣት ቢዘወተር በ አንድ ወር ውስጥ የሚፈለውን የፊት ቆዳ ለውጥ ማየት ይቻላል።
Show all...
የልብ ድካም ማስጠንቀቂያ ምልክቶች 1.ድካም፦ ከተለመደው የተለየ ድካም መሰማት፤ ልብ ሰውነት እና አንጎል የሚፈልገውን በቂ ኦክሲጅን ባለማድረሱ የሚከሰት ምልክት ነዉ። 2. የእንቅስቃሴ ገደብ፦ብዙውን ጊዜ የልብ ድካም ያለባቸው ሰዎች በቀላሉ ስለሚደክሙ እና የትንፋሽ እጥረት ስለሚሰማቸው መደበኛ ተግባራቸውን ማከናወን አይችሉም። ይህ ከ 60 ዓመት እድሜ በኋላ በሰዎች ላይ በጣም ስለሚከሰት ይህንን የማስጠንቀቂያ ምልክት በማሰናከል "እርጅና" እንደሆነ ያስባሉ። 3.ሰዉነት ማበጥ ( edema)፦ ጥቅም ላይ የዋለው ደም ከታችኛው ዳርቻ ወደ ላይ እንዲመለስ ለማስገደድ ልብ በቂ የፓምፕ ሃይል ከሌለው ፈሳሽ በቁርጭምጭሚት ፣ እግሮች ፣ ጭኖች እና ሆድ ውስጥ ሊሰበሰብ ይችላል። ከመጠን በላይ ፈሳሽ በውሃ ክብደት መልክ ፈጣን ክብደት እንዲጨምር ሊያደርግ ይችላል። 4.የትንፋሽ እጥረት፦በሳምባ ውስጥ ያለው ፈሳሽ ጥቅም ላይ የዋለውን ካርቦን ዳይኦክሳይድ ወደ አዲስ ኦክሲጅን ለመለወጥ አስቸጋሪ ያደርገዋል። በእንቅስቃሴ ላይ ብቻ ሳይሆን ተቀምጦም ሆነ ተኝቶ መተንፈስ ከባድ ይሆናል። ከእነዚህ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች አንዱን ስለተሰማዎ፣ የልብ ድካም አለቦት ማለት አይደለም። ነገር ግን 2 ወይም ከዚያ በላይ ከሆኑ ዶክተር ጋር መሄድ አለብዎት።
Show all...
በአፍንጫ የሚገባ የምግብ ቱቦ (Nasogastric Tube) ምን ያህል ጊዜ ነው መቆየት ያለበት? ታማሚዎች በተለያዩ ምክንያቶች (ስትሮክ ፣ የጭንቅላት አደጋ ፣ የአንገትና አፍ ካንሰር ፣ ስር የሰደደ የመርሳት በሽታ ፣ የጡንቻና የነርቭ ህመም ፣ ወዘተ) መብላትና መጠጣት ሊሳናቸው ይችላል። ይህ በሚፈጠር ጊዜ ታማሚው ምግብና ውሃ እንዲያገኝ የሚያስችሉ የተለያዩ ዘዴዎች አሉ ፤ አንዱና ብዙ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውለው በአፍንጫ በኩል ወደ ጨጓራ የሚገባ የምግብ ቱቦ (Nasogastric Tube) ነው። በዚህ ቱቦ ምግብ ፣ ውሃና መድሃኒት መስጠት ይቻላል። ነገር ግን ይህ ቱቦ ከ1 ወር በላይ ጥቅም ላይ የሚውል ከሆነ ለተለያዩ የጎንዮሽ ጉዳቶች ያጋልጣል፤ ለምሳሌ ፣የአፍንጫና የጉሮሮ መቁሰል፣ የጨጓራ አሲድ ወደ ጉሮሮ መመለስ እና የሳንባ ኢንፌክሽን (aspiration pneumonia) ያስከትላል። ስለዚህ አንድ ታማሚ ለረጅም ጊዜ በቱቦ ምግብ መውሰድ ካለበት ሌሎች አማራጮችን መጠቀም ያስፈልጋል። ከነዚህ አማራጮች ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውለው ከውጭ በኩል በቀጥታ ወደ ጨጓራ የሚገባ ቱቦ (gastrostomy) ሲሆን ይህ ቱቦ በቀዶ ህክምና፣ በራጅ (fluroscopy) ወይም ኢንዶስኮፒ በመጠቀም ወደ ጨጓራ ሊገባ ይችላል። ኢንዶስኮፒ በመጠቀም ወደ ጨጓራ የምግብ ቱቦ ማስገባት (Percutaneous Endoscopic Gastrostomy) ቀላልና ፈጣኑ ዘዴ ነው። ይህ የምግብ ቱቦ አንዴ ከገባ በኋላ እስከ ሁለት ዓመት መቆየት የሚችልና ከአፍንጫ ቱቦ ሲነፃፀር አነስተኛ የጎንዮሽ ጉዳት ያለው ነው። በተጨማሪም ቱቦው ሰፊ ስለሆነ ለታማሚው በዛ እና ወፈር ያለ ምግብ ለመስጠት ያስችላል። እንቅስቃሴ ለሚያደርጉና ስራ ለሚሰሩ ታማሚዎች (ambulatory and active patients) ምቹ ነው። የምግብ ቱቦውን ማውጣት ቢያስፈልግ ከባለሙያ ጋር ተማክሮ በቀላሉ ማውጣት ይቻላል። ማጠቃለያ ⒈ በአፍንጫ የሚገባ የምግብ ቱቦ መጠቀም የሚመከረው ከ 4 እስከ 6 ሳምንት ላልበለጠ ጊዜ ነው። ⒉ ለረጅም ጊዜ (ከ 1 ወር በላይ) የምግብ ቱቦ ለሚያስፈልጋቸው ታማሚዎች በሆድ (በውጭ) በኩል ወደ ጨጓራ የሚገባ ቱቦ መጠቀም ይመከራል። በቀጣይ ጽሑፍ የምግብ መስጫ ቱቦዎች እንዳይበላሹና እንዳይደፈኑ ማድረግ የሚገቡ ጥንቃቄዎችን እናያለን። ዶ/ር አብዱልሰመድ መሀመድ የውስጥ ደዌ፣ የጨጓራ ፣አንጀት ፣ ጉበት እና የኢንተርቬንሽናል ኢንዶስኮፒ ስፔሻሊስት ሐኪም
Show all...