cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Mÿ ņêŵ pĥòťo📷🎧🎨🎭

#hulunm_ngeroch_bezi_channel_ lay 💕💕 #🎶music🎤🎧🎤 #quote💑💏 #cover💕❤ #love_lyrics 💖💖 #tiktok😎😮😘 #m90c_music😙😙 #african_dance_music❤️💕 #photo 😍😘 #love_story💕💕 #school_life 😘😘 #Photo_ @my new photo

Show more
Advertising posts
198
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

(ቶረስ) ከሚያዚያ 13 እሰከ ግንቦት 13 ለተወለዱ ወንዶች ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። የቶረስ ወንድ ባህሪያት ጥቆማ ለሴቶች »» ቶረስ ለትዳር በሚፈልጋት ልጅ ላይ ቁርጥ ውሳኔ ለመውሰድ ረዘም ያለ ግዜ ይወስድበታል፣ አንዴ ከወሰነና የሚፈልጋትን ልጅ ለማጥመድ ከቆረጠ ግን አታመልጠውም፣ አስተዋዩ፣ ተግባራዊው፣ አድብተኛውና ቆራጡ ቶረስ አይኑን የጣለባትን ቆንጆ በጁ እስከሚያስገባት ድረስ በየግዜው አበባ ያበረክትላታል። ቶረስ ልዝብ እና ጨዋ ተንከባካቢ አፍቃሪ ነው፣ የልቡን የሚገልፅበትም የራሱ መንገድ አለው። »» ቶረስ ካፈቀረ አፈቀረ ነው አያስመስልም፣ ደበብ ያለ ብርሃን በለበትና ለስላሳ ሙዚቃ በሚንቆሮቆርበት ማራኪ መዝናኛ ውስጥ የራት ግብዣ ያዘጋጅላታል ወይ ስጦታ ያበረክትላታል፣ ቶረስን ማግኘት ማለት ሀብት መውረስ ማለት ነው፣ ነገን በዛሬ ውስጥ ያየዋል፣ በጥንቃቄ ያቅዳል። »» በጓደኞቹና ሰው በበዛበት ቀደም ቀደም ካልሽ ወይም መረን የመልቀቅ ሁኔታ ካሳየሽ ደግ አይደለም፣ በዚህ ወቅት ቆንጠጥ ወይም ነቅነቅ በማድረግ ከድርጊትሽ እንድትቆጠቢ ያስጠነቅቅሻል፣ አልሰማ ከልሽ እቤት ስትገቢ በጥፊ ያጮልሻል፣ ካናደድሽው ለማግባባት ከምትሞክሪ ቢቀርብሽ ነው ሚሻለው። »» ቶረስ ወንድ ምንም ቢናደድባት ሚስቱን በተኩላዎች መካካል ብቻዋን ትቷት አይሄድም፣ እንቢ ካልሽ በግድ ይዞሽ ይሄዳል፣ ስለዚ ከሌሎች ሰዎች ድጋፍ ለማግኘት ተነጥለሽ ለመቅረት እንዳትሞክሪ፣ ምንም ብታኮርፊ ወደቤቱ ሲሄድ አብረሽው ሂጂ ግን ቤት ከመድረሳቹ በፊት ይቅርታ ጠይቂው ፣ እሱ አያደርገውም። »» ቶረስ ወንድ ሚስቱ በሰው ፊት በተለይም በግብዣ ቦታ ላይ የተለየ አክብሮት እንድታሳየው እንጂ የቆሎ ጓደኛ እንድታደርገው የማይፈልግ መሆኑን መረደት ይጠቅምሻል። በመብት ጥያቄ ላይ ለሴት የሚሸነፉ ወንዶች ይኖሩ ይሆናል፣ ቶረስ ግን ንክች አያደርገውም፣ እሱ የሚወደው ሚስቱ ለስላሳ እንድትሆንለት ነው። ። ድፍን አመት ሙሉ በየሳምንቱ ቅዳሜ ሲኒማ የጋበዛት ሸበላ አንድም ቀን ወደ ቤቱ ስላልወሰዳት ሊገርማትም ግራ ሊገባትም ይችላል ቶረስ አይቸኩልም። ጓደኞቹ የበለጠ ባጥላሉት ቁጥር የበለጠ የማይበገር ይሆናል፣ ፍፁም የማይበገር። »» ይህ ሰው ሀገሩን ያፈቅራል፣ አሳ ማጥመድ፣ አበባ፣ የአትክልት ቦታና አንድ ቦታ መርጋትን ይወዳል፣ ከረቂቅ የፍልስፍና መፃፎች ይልቅ ስለቀደምት ጀግኖች መፃፍትን ማንበብ ይወዳል። »» ቶረስ የወንዶች ወንድ ነው፣ የወንድ ቁንጮ። እጅ የሚያስቆረጥም ባልትና ነው ሚወደው። ሲደክመው ነጭናጫ ሊሆን ስለሚችል በቂ እረፍት ማግኘቱን አረጋግጪ፣ እትነዝንዢው፣ ረጅም እረፍት ማግኘቱን አረጋግጪ፣ ረጅም እንቅልፍ መፈለጉንም ከስንፍና አትቁጠሪበት። »» ማንኛውም ቶረስ በራሱ ቤት መዝናናትን ይወዳል፣ ከብዙ ህዝብ ይልቅ ከጥቂቶቹ ወዳጆቹ ጋ መሆነ ይመርጣል፣ የሚያንባርቅ ሬድዮ ወይም ቴሌቪዥን በልክ ይሁን፣ የቤቱ እቃ በደንብ አምሮ ይቀመጥ፣ ሰላም ይስፈን። ። ቶረስ ዘላቂ ታማኝነት እና ትኩረት ከቅን ልቦና ጋ ይሰጥሻል፣ ይህ ንፁህ ፍቅሩ ሌሎች ጉድለትሽን ያካክስልሻል፣በርግጥ ግን ግትር ነው። በቀጣይ የጂሚኒ ወንድ ባህሪ የመጋበዣ ሊንክ https://t.me/MyNewPhoto1
Show all...
Mÿ ņêŵ pĥòťo📷🎧🎨🎭

#hulunm_ngeroch_bezi_channel_ lay 💕💕 #🎶music🎤🎧🎤 #quote💑💏 #cover💕❤ #love_lyrics 💖💖 #tiktok😎😮😘 #m90c_music😙😙 #african_dance_music❤️💕 #photo 😍😘 #love_story💕💕 #school_life 😘😘 #Photo_ @my new photo

#የፍቅር_አይነቶች 1. #ኤሮስ ፦ ተክለ ቁመናን አይተው የሚያፈቅሩ ናቸው ። 2. #ሉደስ ፦ ፍቅርን እንደ ጨዋታ የሚመለከቱ ናቸው። 3. #እስቶስ ፦ ፍቅርን ለህይወታቸው ንሮ መሰረት አድርገው የሚያስቡ ናቸው ። 4. #ማንያ ፦ ፍቅራቸውን እስከ ሞት ድረስ እማይረሱ አንዴ ልባቸውን ከሰጡ መቼም ተስፋ የማይቆርጡ ፍቅራቸውን መቼም እንደማያገኙ እያወቁ እንኩአን የሚያፈቅሩ ናቸው። 5. #ፕራግማ ፦ በፍቅር ግንኙነት ውስጥ መጣጣም እና ተመሳሳይነትን የሚፈልጉ ናቸው ። 6. #አጋፔ፦ በፍቅር ለመውደቅ ብዙ የሚቆዩ ግን በፍቅር ከወደቁ በሆላ ሁሉ ነገራቸውን አሳልፈው የሚሰጡ ናቸው ። https://t.me/MyNewPhoto1
Show all...
Mÿ ņêŵ pĥòťo📷🎧🎨🎭

#hulunm_ngeroch_bezi_channel_ lay 💕💕 #🎶music🎤🎧🎤 #quote💑💏 #cover💕❤ #love_lyrics 💖💖 #tiktok😎😮😘 #m90c_music😙😙 #african_dance_music❤️💕 #photo 😍😘 #love_story💕💕 #school_life 😘😘 #Photo_ @my new photo

(ካንሰር) ከሰኔ 15 እስከ ሐምሌ 16 ለተወለዱ ወንዶች ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። የካንሰር ወንድ ባህሪያት ጥቆማ ለሴቶች »» ካንሰር ወንድ ቁጥብ ነው፣ ሀሳበ ብትን አይደለም፣ መጀመሪያ እንዳገኘሽ ልቡን አይሰጥሽም፣ እንግዳ ፊትም ያፍራል፣ የቅርብ ጓደኞቹ እንኳን በውል የማያውቋቸው አንድንድ ፀባዮች አሉት፣ ይህን ሰው በደንብ ለማወቅ ረጅም ጊዜና ሰፊ ትግስት ይጠይቃል። »» ስሜተ ስስና ታማኝ ነው፣ ቅድም ንዴታም ሆኖ አግኝተሽው አሁን የጨዋ ፈገግታውን ተላብሶ ታይዋለሽ፣ የፍቅር ጥመኛ መሆኑ ጥርጥር የለውም፣ ስብእናው የሚቀያየር ሰው አይደለም፣ ስሜቶቹ ግን የሚቀያየሩ ናቸው፣ ፈገግታና ኩርፊያ፣ ሳቅና ሀዘን፣ ደስታና ትካዜ ቶሎ ቶሎ ይፈራረቁበታል፣ በያንዳንዱ ስሜት ውስጥ ሆኖ ታድያ ለራሱ ታማኝ ነው። »» ጥራት እና ቁጠባ የካንሰር መመሪያዎች ናቸው፣ገንዘብ ለክፉም ለደጉም በሚል ይቆጥባል፣ ሁሉም በአግባቡ ነው እሱ ጋ፣ ካንሰር የማይሰረው የፈጠራ ስራ የለም፣ ስራ መፍጠር ላይ ጎበዝ ነው። »» እናቱን ከልክ በላይ ነው የሚወዳት፣ በጨዋታው ውስጥ እንኳን ካፋ አጠፉም፣ እሱን ከፈለግሽ እናቱን መውዳድ አለብሽ፣ እናቱን ከዙፋናቸው ላይ አውርዶ አንቺን አዲሷን ፍቅረኛውን ማንገስ ይከብደዋል፣ እናቱ ከወደዱሽ ልብ ሙሉ ሆነሽ የሙሽራ ልብስሽን ምረጪ፣ አንድ ሺህ ድብቅ ፍላጎት ያለውን የካንሰርን ልብ ድል አድርገሻል ማለት ነው። »» ለፍላጎቶቹ ሁሉ የምትስማሚ ሆነሽ ሲያገኝሽ በሙገሳና በስጦታ ማጥለቅለቅ ብቻ ሳይሆን ጠበቅ አድርጎም ይይዝሻል፣ እዚ ላይ ግን ለመድረስ የጥራት ደረጃ መመዘኛው ቀላል አይደለም፣ ያለ በቂ ምክንያት ትዳር መስርተው ሲቃጠሉ መኖር አይፈልጉም፣ አንዴ ካፈቀሩ መለየት አይሆንላቸውም። »» ካንሰር ለልጆቹ እንዴት የሚያስደስት አባት መሰለሽ ፣ ሴቶቹም ወንዶቹም ካንሰራዊያን ለልጆቻቸው እናት ናቸው። »» ምንም ቢሆን ግን የተጨረማመተ ባርኔጣውን፣ የተቀደደ የቴኒስ ጫማውን፣ የሰበሰባቸውን ቴምብሮች ወይም የልጆቹን ሪፖርት ካርዶቹን አይጠቅሙም ብለሽ እንዳትጥይበት፣ ቅሪቶቹ መሆናቸውን ልትዘነጊ አይገባም ። ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ 👇 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MyNewPhoto1
Show all...
Mÿ ņêŵ pĥòťo📷🎧🎨🎭

#hulunm_ngeroch_bezi_channel_ lay 💕💕 #🎶music🎤🎧🎤 #quote💑💏 #cover💕❤ #love_lyrics 💖💖 #tiktok😎😮😘 #m90c_music😙😙 #african_dance_music❤️💕 #photo 😍😘 #love_story💕💕 #school_life 😘😘 #Photo_ @my new photo

ቅ ና ት ! (( በአበባው መላኩ)) ======©====== . ፍቅሬን ሜዳ ላይ ጥላ ስትከዳኝ አይቻታለሁ እንደገፋችኝ ትገፋ እያልኩ እረግማታለሁ። ~ ዘወትር ሙሾ ታላዝን የዕንባ ማዕበል ይጠባት ደስታዬን እንዳጨለመች ደስታዋ ይጨልምባት ሺህ እጥፍ ትጨድ አበሳ ለዘራችብኝ ጥፋት። ~ እያልኩ እረግማታለሁ። … የኮራችበትን ገላ መብረቅ ያንድደው በቁጣ በላይዋ ዲን ይውረድባት ጥጋት መሸሻ ትጣ። ~ እያልኩ እረግማታለሁ። … የምድር የቀላይ ጥፋት በላይዋ ይውረድ ኩነኔ ኑሮዋን ሲዖል ያድርገው ስቃይዋን ያሳየኝ በዓይኔ። እንደከዳችኝ ትከዳ የኔ ያለችው ይሽሻት ቀላዋጭ ዓይኗን ያፍርጠው ከውካዋ እግሯን ያልምሻት። ~ እያልኩ እረግማታለሁ ። … ክንዷ በመጅ ይሰበር ሌላ ያቀፈችበት አባጨጓሬ ይሙላው ፍራሹ የተኛችበት። ~ እያልኩ እረግማታለሁ። … የሌላ ሆና ብትከዳኝ አይጠሉ ጠልቻታለሁ ስለማተቤ ብጠየቅ በዓለም ላይ ካለ የምሻው የረገምኳትን እላለሁ ሌላም እርካታ የለኝ እሷን አምጡልኝ እላለሁ። ጥላቻዬና ፍቅሬ ናት እርግማኔና በረከቴ ያለሷ ሕይወት የሌለኝ ያሳበደችኝ ቅ ና ቴ ። ❤ https://t.me/MyNewPhoto1 👍👍👍👍👍👍👍👍
Show all...
Mÿ ņêŵ pĥòťo📷🎧🎨🎭

#hulunm_ngeroch_bezi_channel_ lay 💕💕 #🎶music🎤🎧🎤 #quote💑💏 #cover💕❤ #love_lyrics 💖💖 #tiktok😎😮😘 #m90c_music😙😙 #african_dance_music❤️💕 #photo 😍😘 #love_story💕💕 #school_life 😘😘 #Photo_ @my new photo

(ሊዮ) ከሀምሌ 17 እስከ ነሃሴ 17 ለተወለዱ ወንዶች ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። የሊዮ ወንድ ባህሪያት ጥቆማ ለሴቶች »» ሊዮ ወንድ የሚገኘው ህዝብ በተሰበሰበበት፣ የሰው አይን በበዛበት ባደባባይ ጣፋጭ ንግግር ሲያደርግ እንጂ በበረሃ ሲጠወልግ አይደለም።ጣፋጭነቱን ግን በባዶ አየር ላይ አይረጭም፣ ሁል ግዜ ተደራሲ ይኖረዋል፣ የሊዮ ምስጢር ይሄ ነው፣ ተደራሲ ሁኚ፣ አድናቂው ሁኚ፣ ለፍቅር ጨዋታ የተጋና የተባ ነው። ቀልብሽ ካረፈበት አድንቂው፣ አሞግሽው፣ አክብሪው። »» ሊዮ ያለ ፍቅር መኖር አይችልም፣ ፍቅር ቢሉሽ ፍቅር መሰለሽ፣ እንደ ጣኦት መመለክ ነው ሚፈልገው፣ ከዚያ ካነሰ ሞቱን ይመርጣል ለገንዘቡም አይሳሳም፣ በውድ ስጦታዎች ያጥለቀልቅሻል፣ በደስታ ያስፈነድቅሻል። »» ግን በአካልም፣ በመንፈስሽና በአእምሮሽ የሱ ነሽ፣ ምን አይነት ልብስ መልበስ እንዳለብሽ፣ ፀጉርሽን እንዴት መሰራት እንደሚኖርብሽ፣ የትኛውን መፃፍ እንደምታነቢና ከነማን ጋር እንደምትውዪ ሁሉ ሚመርጥልሽ እሱ ነው፣ ይቀናል። ማራኪ መሆንሽን አሳምሮ ያውቃል፣ የሌላ ሰው ማረጋገጫ አያስፈልገውም። ሊዮ የበደለውን ሰው ያነጥፈዋል፣ ባህሪው ሚዛኑን የጠበቀ እንዲሆን ያንቺ ትብብር ያስፈልገዋል፣ የጋለ ስሜቱን ከአሳማኝ ምክንያት ጋር እያስታረቅሽ ልታጓጊው ይገባል፣ የሱን ስሜት ለማረጋጋት አንቺ ራስሽ መራጋጋት ይኖርብሻል፣ የተራጋጋሽ ካልሆንሽ የፍቅር ህይወታቹ የጦርነት አውድማ መሆኑ ነው። »» ስራ ሊኖርሽ አይገባም፣ ሊዮ ባልሽ ፈፅሞ አይፈቅድልሽም፣ ስራሽ እሱ ነው ፣ ሊዮ ባልሽ ልክ እንደ ንጉስ ደግ ይሆንልሻል፣ ቤተሰቦችሽን ይረዳልሻል፣ የሚፈልገውን አክብሮትና ሙገሳ ካገኘ ለልገሳው ወሰን የለውም፣ አንቺን ከያዘ ቧላ እንደገና ወደ መምረጥ አይገባም። »» ወደ ግልፅ ጨረታ ቦታም ባይሄድ ይሻላል፣ ከሰው በላይ ዋጋ የመስጠት ፍላጎቱ ብልጭ ይልበትና ገንዘቡን ይዘራው ይሆናል፣ የፈጠራ ችሎታ እንዳላቸው ሁሉ የመቆመር እና ጨረታ የማሸነፍ አመልም አለባቸው። ሁሉም ሊዮዎች የእጅ ብልሀት አላቸው፣ እቤት ውስጥ ከሬድዮ እስከ ቴሌቪዥን ሲበላሽ ያድሳሉ። »» ሊዮዎች ማንኛውንም የፓርቲ ግብዣ ህይወት ይዘሩበታል፣ ባፀፋውም ይታዩበታል፣ ይከበሩበታልም፣ ሊዮን የሚፈልገው የሚያገኘ ነው፣ አያያዙንም ያቅበታል። »» ከጋብቻ በፊት በፍቅር ወዳጅነት በተቀራረባቹበት ወቅት ታማኝሽ እንዲሆን ከፈለግሽ የፍቅር ጥማቱን በደንብ አርኪለት፣ ባይኑ መቀንዘሩ ግን አይቀርም፣ አይንህን ቅጣ ከምትይው ውበትን ሲያደንቅ አብረሽ ብታደንቂ ታስገርሚዋለሽ፣ ውበትን አየ ብላ ፍቅረኛው ስትለየው ሊዮ ወንድ ይገረማል፣ያዝናል እንዲሁም ይጎዳልም። »» ልጆቹን ከሱ አታስበልጪ፣ ወደ ልጆችሽ አድልተሽ ለሱ የምትሰጪው ትኩረት ካነሰ ችግር ይፈጠራል፣ በስሩ ያሉ ሰዎችን የማዘዝና በነሱም የመፈቀር ፍላጎቱ ከፍ ያለ ነው። ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ 👇 https://t.me/MyNewPhoto1
Show all...
Mÿ ņêŵ pĥòťo📷🎧🎨🎭

#hulunm_ngeroch_bezi_channel_ lay 💕💕 #🎶music🎤🎧🎤 #quote💑💏 #cover💕❤ #love_lyrics 💖💖 #tiktok😎😮😘 #m90c_music😙😙 #african_dance_music❤️💕 #photo 😍😘 #love_story💕💕 #school_life 😘😘 #Photo_ @my new photo

(ቪርጎ) ከነሐሴ 18 እስከ መስከረም 13 ለተወለዱ ወንዶች ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። የቪርጎ ወንድ ባህሪያት ጥቆማ ለሴቶች »» ይህ ሰው የሚኖረው በተግባራዊና ቁሳዊ ደረጃ ስለሆነ ለረቂቅ የፍቅር ስሜት ያለው ጠቀሜታ ዝቅተኛ ነው፣ በእርግጥ ዋናው ምክንያት አካዳሚ ሊሆን ይችላል፣ ቪርጎዎች ገና ከልጅነታቸው ጀምሮ በፍቅር ይያዛሉ፣ ሆኖም የሮሚዮና ጁልየት አይነት አይደለም፣ ፍቅሩን የሚገልፅበት ዋነኛ መንገዱ ለቤተሰቡ፣ ለጓደኞቹ፣ ለደካሞችና ከእሱ ለሚያንሱ ሰዎች በታማኝነት መልካም አገልግሎት በመስጠት ነው። »» በድራማዊ ትወናና በስሜታዊ ቃል ኪዳን ታጅቦ በእንባ ጎርፍ የሚገለጽ ፍቅር የቪርጎን ስሜት ማቀዝቀዝ ብቻ ሳይሆን አስፈራርቶ ያስሸሸዋል። በእርግጥ ልቡን ለማግኘት መንገዶች አሉ፣ ጠብ ጫሪነት፣ ጉልበተኛ ወይም ወሲበኛ መሆን ከመንገዶቹ አንዱ አይደለም፣ በፍቅር ከብዛት ይልቅ ጥራት ይፈልጋል፣ በጥቂቱም ላይ አሳዛኝ ሁኔታ ሊያጋጥማቸው ይችላል፣ እንዲ አይነት አሳዛኝ የፍቅር ህይወት ሲገጥማቸው ራሳቸውን በከባድ ስራ ያስጠምዱና ከህብረተሰቡ ይርቃሉ፣ ለወደፊትም በጣም ጥንቁቆች ይሆናሉ፣ ቪርጎን በፍቅር የምታጠምድ ሴት እንግዲህ ምን ያህል ታጋሽና ስልታዊ መሆን እንዳለበት ያየሽ ይመስለኛል። »» ከሌሎች ቤተ ባህሪያት ይበልጥ ከወሲብ ታቅበው በቀላሉ መኖር ይችላሉ፣ አሪፍ አእምሮ እና ጠንካራ አካል አጣምሮ የያዘ ነው፣ እውነተኛ ፍቅር ለማቀጣጠል ብዙ ማገዶ ማንደድ ያስፈልጋል፣ ሴት ሲመርጥ በጣም ተጠንቅቆ እና ጊዜ ወስዶ ነው አስተሳሰቡ ጥርት ያለ ነው፣ ዝቅ ያለ የፍቅር ግንኙነት ጨርሶ አይቀበልም። »» የቪርጎን ወንድ ስሜት ለመቀስቀስ ያስቸግራል ፣ ከወሰነ ግን ወሰነ ነው። ቪርጎ ወንድ ከልክ በላይ ባይሆንም በጣም ቀናተኛ ነው ቅናቱን በግልፅ አለማሳየቱ ሊያዘናጋሽ አይገባም ከልኩ ካለፈ ጥሎሽ ላጥ ሊል ይችላል። ቪርጎ ወንድን ስታፈቅሪ አስተሳሰብሽንም ማጥራት ያስፈልግሻል፣ እንዲሁም ጥሩ ልብስ ልበሺ ፣ ፀጉርሽንም በጥሩ ስታይል ተሰርተሽ በንፅህና ያዢ። https://t.me/MyNewPhoto1
Show all...
Mÿ ņêŵ pĥòťo📷🎧🎨🎭

#hulunm_ngeroch_bezi_channel_ lay 💕💕 #🎶music🎤🎧🎤 #quote💑💏 #cover💕❤ #love_lyrics 💖💖 #tiktok😎😮😘 #m90c_music😙😙 #african_dance_music❤️💕 #photo 😍😘 #love_story💕💕 #school_life 😘😘 #Photo_ @my new photo

(ሊብራ) ከመስከረም 14 እስከ እስከ ጥቅምት 13 ለተወለዱ ወንዶች ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። የሊብራ ወንድ ባህሪያት ጥቆማ ለሴቶች »» በሊብራ ውበት አንዴ ከተማረክሽ ለመላቀቅ አስቸጋሪ ነው፣ ልታመልጪው ስትሞክሪ በዚያ ሎጂካዊ ክርክሩ አብረሽው እንድትሆኚ ያስገድድሻል፣ ከዚህ በተጨማሪም ጣፋጭ እና ጨዋ ሆኖ ስለሚቀርብሽ ያናደደሽን ሁሉ ረስተሽ ቁጭ ትያለሽ። »» ነገር ግን ፍቅሩ ውጣ ውረድ የሌለው የላባ ፍራሽ ይሆናል በለሽ ካሰብሽ የዋህ ነሽ ፣ ሚዛኑ ሲስተካከልለት ግን ህይወት ከሊብራ ጋ በፍቅር የምታሰክርና ምታስፈነድቅ ነው ምቶነው። »» የሚፈልጋትን ልጅ በቀላሉ በጁ የሚያስገባበትን ጥብብ ታድሏል፣ ሆኖም አንዴ በጁ ካስገባት ቧላ ቀጥሎ ምን እንደሚያደርግ ግራ ይገባዋል፣ እሺ ካሰኛት ቧላ ያቅማማል፣ ይጠቀምባት ወይስ የጋብቻ ሀሳብ ያቅርብላት? ምን ማድረግ እንዳለበት አያቅም። »» የሰውን ስሜት መጉዳት ብዙ አይፈልግም፣ እምቢ ማለትን ስለማይሆንለት ጊዜ እያረዘመ ማጉላላት በደል መሆኑን ቶሎ አይገነዘብም። አየሽ በሁለት አጣብቂኝ መካካል ያለ ሰው ነው ማለት ነው ፣ ሊብራ ወንዶች ሳይታሰብ ድንገት ልውጥ ማለታቸው ማይካድ ነው ፣ በተለይ በወጣትነት ጊዜ የማጥፋት አዝማሚያ አላቸው ፣ ጓደኝነትና ፍቅር ተስፋ በሚያስቆርጥ ሁኔታ ግራ ያጋቡታል፣ ሊብራ ወንድ ያልተሳካውን ግንኙነት ፈጥኖ ስለሚረሰ ብዙም የስሜት ተጎጂ አይሆንም። »» ሚስጥርሽን አያነፈንፍብሽም፣ የግለሰቦችን ግላዊ ሁኔታ እየቆፈረ ነፃነታቸውን መጋፋት አይወድም፣ አንድአንዴ ደግሞ ማፅናኛውን ፈልገሽ አንድ ሰው ምን ያህል እንዳናደደሽ ሮጠሽ ስትነግሪው " አንቺ ምን ብለሺው ነው? " ብሎ አንቺኑ ሲያፋጥጥሽ ቅር መሰኘትሽ አይቀርም፣ ፍትህ አዛብታላች ብሎ ካሰበ ላንቺ ይቆማል ብለሽ አጠብቂ። »» ሊብራ ወንድ የሴት ጓዳኛውን ውስጣዊ ፍላጎት ባለመረዳቱ የተነሳ ችግር ይፈጠራል፣ ከሊብራ ጋ ስትኖሪ መቻል ያለብሽ አንዱ ፀባዩ ይሄ ነው ። በያንዳንዱ ቀንና ሰዓት ቤቱ እንግዳ አይጠፋም። »» ሊብራ ወንዶች ፈጥነው ትዳራቸውን እንዲያፈርስ ከሚያደርጋቸው ሁኔታ ውስጥ አንዱ የቤታቸው መዝረክረክ ነው፣ ምስቅልቅል ሁኔታ ይጠላሉ፣ ውስጣዊ እርጋታን ለማግኘት ውጫዊው ሁኔታ ህብር መፍጠርን ይፈልጋል። »» ሊብራን ወንድን ከልብሽ ካፈቀርሽው "እንጋባ" ብለሽ ሃሳቡን አቅርቢለት ፣ ከወደደሽ ቅድሚያውን በመውሰድሽ እፎይታ ይሰማዋል፣ እሱ እንደሆነ ያቅማማል። https://t.me/MyNewPhoto1
Show all...
Mÿ ņêŵ pĥòťo📷🎧🎨🎭

#hulunm_ngeroch_bezi_channel_ lay 💕💕 #🎶music🎤🎧🎤 #quote💑💏 #cover💕❤ #love_lyrics 💖💖 #tiktok😎😮😘 #m90c_music😙😙 #african_dance_music❤️💕 #photo 😍😘 #love_story💕💕 #school_life 😘😘 #Photo_ @my new photo

(#ፓይሰስ_ሴት) ከየካቲት 13 እስከ መጋቢት 11 🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱 »» ይቺ ጨዋና ኮስታራ መሳይ ደመ ግቡና የደስደስ ያላት፣ ተግደርዳሪና ምስኪን ፍጡር ከሴትነቷ አንፃር ሰፊ ነፃነት እያላትና እንደፈለገችው መሆን እየቻለች መግደርደር ፀባይዋ ከመሆኑ የተነሳ የሚቀርቧትን ወንዶች በትልቅ ዱላ ስታባርር ትገኛለች። »» ፓይሰስ ሴት በጣም ፀባይ ያላትና በአመለሽጋነቷ በአከባቢዋ የተመሰገነች ናት ፣ በባልዋ ላይ አለቃ ልትሆንበት አትሞክርም፣ በማንኛውም ሁኔታ እሱን ለመጨቆን ምንም ፍላጎት የላትም። »» እሷ ከሱ ምትፈልገው ነገር ቢኖር ከዚህ አስፈሪ አለም እንዲጠብቃት እና በደንብ እንዲንከባከባት ብቻ ነው። »» ልስልስ፣ ወላንሳ ፣ ህልመኛና ቅልስልስ ናት፣ በሏ ያለቅጥ ጨካኝ ወይም ሰነፍ ከሆነባት ብቻ ነው ተሳዳቢ ምትሆነው፣ እንዲሁም በልጅነቷ አስተዳደጓ የተጓደለባት ከሆነች ደስታ የለሽና ነጭናጫ ትሆናለች። »» አይነተኛዋ ፓይሰስ ሴት ባህሪዋ ጥልቅና ረቂቅ ነው፣ አንተ ያየሀት ሴት የተለየች ናት፣ እኔም የማውቃት ሌላ ናት፣ ሆኖም ያልኩህ ትክክል ነው፣ ሁለታችንም ራሷን ነው ያየናት። »» ቁጠባ ሚባል ነገር አታዎቅም፣ ስሜቷም ተለዋዋጭ ነው፣ ሲከፋት አምርራ ታለቅሳለች። »» ይቺ ሴት ስጉና ተጠራጣሪ ናት ፣ ይህን ማስወገድ ይኖርባታል፣ ዝም ብላ በከንቱ ትጨነቃለች። ወጣት መስሎ መታየት ይፈልጋሉ። በአጠቃላይ ግን ፓይሰስ ሴቶች ምርጥ ናቸው።
Show all...
(#አኳሪየስ_ሴት) ከጥር 13 እስከ የካቲት 12 🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱 »» ከአኳሪየስ ሴት ጋ ወደ ፍቅር አለም ለመግባት አመቺው መንገድ ፀባይዋ በማንኛውም ነገር ላይ አይ-አዎ እንደሆነ ሁሉ በፍቅር ላይም እንዲሁ እምቢታንና እሽታን ያጣመረ መሆኑን ማስታወስ መቻል ነው። »» በፍፁም የቤትህ እስረኛ ወይንም የአልጋህ ዘበኛ ልታደርጋት አትሞክር፣ በማጀት ልትወስናት ከሞከርክ ድንገት ተነስታ እብስ ነው ምትለው። »» ይቺ ሰው አንተና እኔ ከምናልመው የተለየ ህልም የምታልም ናት፣ ከሩቅ ቦታ የሚደለቅ ከበሮ ይሰማታል፣ለብዙዎቻችን የማይታየን ኮከብ ለርሷ ይታያታል። »» አኳሪየስ ሴት የማንም ሆና ሳለ ያንድም ሰው ያልሆነች ናት፣ ፍቅሯ ከፍተኛና የተነቃቃ ሊሆን ይችላል፣ ሆኖም በከፊል ብቻ ትዝ እንደሚል ሙዚቃ ብዥ የሚል ደብዛዛ መልክ አለው ፣ ዜማውን ልታዜመው ትችል ይሆናል፣ ግጥሙ ግን ብዥ እያለ የሚጠፋ ዘፈን አይነት ነው። የሚናፍቅ ማግኔት አላት ፣ ይሄ ባህሪ የወንዶቹም ጭምር ነው። »» አኳሪየስ ሴት ነፃነቷን በጥብቅ ትሻለች ፣ ነፃነቷን አክብርላት፣ ከገንዘብህ ምንም ጉዳይ የላትም በእውቀትህና በአእምሮ ውጤትህ ግን ከበሬታ ያተረፍክ እንድትሆን ትፈልጋለች። »» በማህበረሰቡ ውስጥ እጅግ ብልህ፣ ማራኪና እንደወርቅ የነጠረች ፣ ከትልቁም ከትንሹም ተግባቢ የሆነች ናት። »» ውሸት መናገርና አውነቱን ከመናገር መቆጠብ በአኳሪየሶች ዘንድ የተለያዩ ነገሮች ናቸው፣ ብድር መበደርም ማበደርም አትወድም፣ ገንዘብ ማጋበስም ሆነ እዳ መግባት አትወድም። »» ባህሪዋ ይማርካል፣ አንድንዴ ግን ከርዕሰ ጉዳይ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው አስታየት ልትሰነዝር ትችላለች፣ አንድአንዴ ገራም አንዴ ግልፍተኛ ነች »» ሰውን ለመመዘን የራሷ መለኪያ አላት፣ ተፈጥሮዋ ግላዊ ስለሆነ ጥልቅ ስሜትን መግለፅ በቀላሉ አይሆንላትም፣ አንዴ ትክክለኛ ግጣማቸውን ካገኙ ትዳራቸውን ለደስተኛ ኑሮ ናሙና የሚሆን ነው።
Show all...
(#ካፕሪኮርን_ሴት) ከታህሳስ 13 እስከ ጥር 12 🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱 »» አይነተኛዋን ካፔ ሴት እንዲህ ናት ማለት ትንሽ ያስቸግራል፣ ነገር ግን ምንም ብትሰራ ፣ ማንኛውንም አይነት ልብስ ብትለብስ፣ አስተሳሰቧ፣ ድርጊቶቿና ድብቅ ህልሞቿና ዋናው ፍላጎቷ ጥራ ግራ አስተማማኝ የኑሮ ደረጃ ላይ መድረስና ቤተሰቦቿን መርዳት ነው። »» ካፕሪኮርን ሴቶች የስራ ሰዎች ናቸው፣ የህይወት ግቦቿ አስተማማኝ ኑሮ፣ ትልቅ ስልጣንና ክብር ናቸው። »» ከካፔ ሴት ጋር የፍቅር ግንኙነት የሚመሰርት ማንኛውም ወንድ ስለተፈጥሮ ባህሪዋ መሰረታዊ እውቀት ሊኖረው ይገባል፣ ፀባይዋ የረጋና ስሜቷም የሰከነ ይመስላል። »» ገራም ፀባይዋን ምንም ነገር ቅር የሚያሰኘው አይመስልም፣ እውነታው ግን በስጩ መሆኗ ነው፣ በርግጥ ማንኛዋም ሴት ለብስጭት የተጋለጠች ናት፣ የካፕሪኮርን ሴት በስጭት ግን ጠና ያለና ረዘም ላለ ግዜ የሚቆይ ነው፣ ትንሽ ስለምትፈራም፣ ማበረታታት አለብህ። »» ይቺ ልጅ ሲያሾፉባት ጨርሶ አትወድም፣ ዘወትር ልታመሰግናትም አይገባም፣ ምስጋናው ልባዊ ካልሆነ ታውቅብሃለች፣ ባልተጨበጠ ተስፋም አይሞኙም፣ የማህበረሰቡን ባህል፣ ወግ፣ ስነ ምግባር ህጎችና እሴቶች የምታከብር ሴት ነች። »» ቤተሰቧን መንቀፍ ከባድ በጣም ከባድ ስህተት ነው የሚሆነው፣ ያንተን ዘመዶች ታከብራለች፣ የሷንም ማክበር አለብህ። »» ይቺን ልጅ ታላላቅ ሙዚቃዎች ውስጧን ያምሱታል፣ ጥሩ ግጥሞች ስሜቷን ይነኩታል። በፍቅር ጨወታ ቶሎ ፈታና ዘና ማለት ብዙም አይሆንላትም፣ ግዜ ትፈልጋለች።
Show all...